Tuesday, March 29, 2022

ለትውስታችሁ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ለማን ቆሞ ነበር? ጌታቸው ረዳ (Getachew Reda--Ethiopian Semay)

 

ለትውስታችሁ፤

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ለማን ቆሞ ነበር?

ጌታቸው ረዳ

 (Getachew Reda-- Editor Ethiopian Semay)

የህ ሰነድ ለማሳየት የፈለግኩት ምክንያት በዚህ 4 አመት ውስጥ ወደ ትግሉ የተቀላቀላችሁ አዳዲስ ታጋዮች ከናንተ በፊት ሲደረግ የነበረው እልክ አስጨራሽ የተለያዩ ትግሎች በተለይ አማራ ብሶቱ እንዳይናገር ሲታፈን የነበረ ውስብስብ “ሴራ” በግምባር ታግለናል።

በወቅቱ ታገዮች የተባልነው እጅግ በጣት የምንቆጠር ነበርን። ሁለት ትግል ታግለናል። “ኣንደኛው” በፖለቲካው መድረክ ገብተው አማራውን ለማፈን ያካሄዱት የምሁራን ሴራን ስንታገል “ሁለተኛው ትግላቨችን እና ከባድ የነበረው ደግሞ” አሁን በሺዎቻችሁ በተጋይነት ተሰልፋችሁ ለአማራና ለኢትዮጵያ  የምትጮሁ አገር ውስም ሆነ ውጭ አገር ያላችሁ ወገኖቻችን በመተኛታችሁ እናነተን ከተኛችሁበት ለመቀስቀስ ሌላው ፈታኝ ትግል ነበር። እውነት ለመናገር ደምጻችን እንዳይሰማ ስታፍኑነም ሆነ ስትሰድቡን የነበራችሁ እና ለሴረኞቹ በገንዘብም በሞራልም በመሳተፍም ከጎናቸው ጋር ቆማችሁ እኛን ስታስገግሩ የነበራችሁ እና የባሳችሁብን እናንተ ነበራችሁ። እነሆ ትግላችን ፍሬ አስገኝቶ አገር ውስጥም ውጭ አገርም ወደ ትግላችን በመቀላቀላችሁ በጠመንጃም በብዕርም የምታተገሉ ታጋዮች እኛ ጥቂቶቹ እናንተን ሚሊዮኖችን አፍርተን በማየታችን ተደስተናል። ቢሆንም ቀይ መስመር የሚያሳይ ምልክት እያየሁ ስለሆነ “አክራሪ” ላለመሆን ጥንቃቄ ቢደረግ እግረ መንገዴን እመክራለሁ።

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ለማን ቆሞ ነበር?

ሴራው ከኦነግ ከኢሳትና ከግንቦት 7 እንዲሁም ከሻዕቢያ ጋር የተያያዘ ጸረ አማራ የተጎነጎነ ጉድ ነበር። ድርጅቱ ሕዝባዊ ስብሰባ በጠራ ቁጥር ኤርትራኖች ዕደል ተሰጥቶኣቸው አማረውን እና ኢትዮጵያን በቅኝ ገዢነት ሲዘልፉበት የነበረ መድረክ ነበር። ቢያምም ታሪክ ነውና እንድተውቁት ለትውስታችሁ እነሆ።

(1)   የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተበሎ የሚጠራው የፖለቲካ አቃቂረኞችየኢትዮጵያ እና የኦሮሞ አገራዊ ምስረታ ንቅናቄስንለው የነበረ ድርጅት ነው። ግንቦት 7 እና ኦነግ የሚያሾሩት አማራ ሕዝብ ደምፅ ለማፈን ሲሰራ የነበረው ይህ ድርጅት ምርኩዝ የነበሩት የኢሳት ሰይጣናዊ ሰዎች እና ምሁራን ተብየ አስቂኝ ምሁራኖች የተጓዙበት ጉዞ አሳያችሗለሁ። እኛም ከነዚህ ሰዎች ጋር በወቅቱ የገጠመን ግብግን እጅግ አድካሚ ነበር። የሚገርመው ደግሞ ይህ ድርጅት ግምባር ቀደም የስብስቦቹ ዋና ተጠሪ የነበረው አማራው “ዶ/ር ጌታቸው በጋሻ’ እና የመሳሰሉ አማራዎች ነበሩ። አሁን ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው ወደ ልቦናው የተመለሰ ይመስለኛል። ላለፈው ክረምት አይሰራም፤ ለወደፊቱ እናስብ በሚል ምረቴን  ወደ ጎን አድርጌዋለሁ። ሰነዳቸውን ለምስክርነት ታዩታላችሁ።

ይህ ሰነድ ኢሳት የተባለ ብዙ ጸረ አማራ የሆኑ ግለሰቦች የተሰባሰቡበት ሚዲያ ድርጅት በ እነ ሲሳይ አገና እና ንአምን ዘለቀ “አሞካሺነትና” እና በኢሳት ቲቪ ዋና “አቃፊነት” (ስፖንሰር) ሲካሄድ የነበረ የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ በሽፋን ተንቀሳቅሶ ለጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ለሆነው  በሰው ልጆች ደም እጁ የተጨማለቀው አሸባሪ የሆነው ለኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር “ኦነግ” ፖለቲካ በማመቻቸት ሲሰራ የነበረው ከላይ የተጠቀሰው የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የተባለው “ቡድን” በአማራ እና ኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት ሴራ ሲሰራ ነበር? ሴራው ከታች እንመለከተዋለን።

አሁን ላለንበት ለውጥ የተባለው የከሸፈው ለውጥ በከንቱ አልመጣም። ብዙ መስዋእት ከፍለናል። ሴራውን ስናጋልጥ ብዙ ዘለፋ ሲደርስብን እንደነበር ይታወሳል። የተጋፈጥነው አውነት ሆኖ መረጃው እነሆ በጽሑፍም፤ በቪዲየው/አውድዮም ሲዋሽ የነበው  ቅጥፈታቸው በወቅቱ አወጣነው። በወቅቱ ላልነበራችሁ ወይንም ከጊዜ ብዛት ታሪኩን ከትውስታችሁ ለጠፋ እንደገና እንድታስታውሱት “ኢትዮጵያን ሰማይ” የመዘገበው የወቅቲ ሰነድ ተመልከቱት እነሆ እንዲህ ነበር።

(1)

የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድ

ሰሞኑን በአራት የተቃቃሚ ድርጅቶች ማለትም፡-

በግንቦት 7 (G7) በኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) በሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( SNDM ) እና በአፋር ህዝብ ፓርቲ (APP) መካከል በዋሽንግተን ዲሲ ኦክቶበር 30 2016 ..የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የሚባል ስብስብ ተፈራርመው መመስረታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) የስምምነት ሰነድ ከተካተቱት ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች እና ለህዝብ ያለተገለጡት ጉዳዮች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን የያዘ ነው።

* የአማራ ህዝብ ተወካይ ባለመኖሩ በስብስቡ አለተካተተም የተባለው ውሸት ነው።

* የንቅናቄው ሰነድ እንዳለ የግንቦት 7 ፕሮግራም የተቀበለ ነው።

* የንቅናቄው ሰነድ በወያኔ መንግስት የወጣውን እና አሁን ወያኔ እየተገበረው ያለውን ህገ መንግስት ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ነው።

* ንቅራቄው በወያኔ መንግስት የተዘረጋውን የአስተዳደር መዋቅር እንዳለ የተቀበለ ነው።

* የንቅናቄው ሰንደ ወያኔ እንደሚለው የኢትዮጵያን ህዝብሕዝቦችእያለ የሚጠራ ነው።

* ይህ በነዚህ በአራቶ ድርጅቶች የጸደቀው ሰነድ ካሁን በኋላ ሰነዱን ማንም ማሻሻም አይችልም የሚል ማሰሪያ አንቀጽ አለው።

* አዲስ ወደ ንቅናቄው የሚገቡ ድርጅቶች በአራቱ ድርጅቶች የጸደቀውን ይህንን ሰንድን እንዳለ ተቀብለው መግባት እንጅ ሰነዱ እንዲሻሻልና እንዲስተካከል የመጠየቅም ሆን የማሻሻል ጥያቄ መብታቸው የተከለከለ ነው።

* ግንቦት 7 ( G7 ) የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ODF ) ማንኛውም የአማራ ድርጅት ተወካይ ወይም በአዛጋጆች ተጋብዞ የነበረው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በዚህ የንቅናቄ ስብስብ ውስጥ ሊገባ አይገባውም የሚል እገዳ ጥለዋል።

* በንቅናቄ የተገኙት የአፋር እና የሲዳማ ድርጅቶች የአማራ ህዝብ ተወካይ የለለበት የድርጅቶች ስብስብ የትም አይደርስምና የአማራ ህዝብ ተወካይ በንቅናቄው ስብስብ እንዲካተት ከፍተኛ ድምጽ ያሰሙ ቢሆንም  ግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) ግን የአማራ ተወካይ በንቅናቄው ውስጥ መገኘት የለበትም በማለት እገዳ ጥለዋል።

በዚህ አጋጣሚ የአፋርና የሲዳማ ህዝብ ድርጅቶች ሃላፊዎች ምንም እንኳ በጉልበተኞቹ በግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) መሪዎች ተጽእኖ ምክንያት የአማራ ህዝብ ተወካይ በስብስቡ እንዳይገኝ ቢደረግም እናንተ ግን እውነተኛ የነጻነት ታጋዮች በመሆናችሁ የአማራ ህዝብ ተወካይ የለለበት ስብስብ ዋጋ የለውም ብላችሁ ያነሳችሁት ጥያቄ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የአማራ ህዝብ ያላችሁ ቅን ልብና ወገናዊትነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ለእናንተ ያለው አክብሮት ከፍ ያለ መሆኑን እየገለጽን በዚህ አጋጣሚ ላሳያችሁት አጋርነት እናመሰግናችኋለን።

አቶ ተክሌ የሻው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅትና ሊቀመንበር እና የአማራ ህዝብ ጠባቃየኢትዮጵያሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድን በሚመለከት የሰጡትን አስተያየት ከዚህ በታች ያድምጡ።

ስለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄን - Ethiopian National Movement የአቶ ተክሌ የሻው አስተያየት

https://youtu.be/j4gLQDvHUM8

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ (Getachew Reda Ethiopian Semay)

 

 

Monday, March 21, 2022

ባሮን ፍራንከስታይንና የትግራይ ሕዝብ መመሳሰል የዘመናችን አሳዛኙ ክስተት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/22/22

 

ባሮን ፍራንከስታይንና የትግራይ ሕዝብ መመሳሰል የዘመናችን አሳዛኙ ክስተት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/22/22

ባንድ ነገር ተጠምጄ ስለነበር ወቅታዊ ትችቶቼን አቁሜ ነበር፡ ይቅርታ። የርዕዮት አዘጋጅ ቱድሮስ ፀጋዬን አስመልክቼ ስላለፉት ተከታታይ ጽሑፎቼ ክፍል 3 ላይ እንዳቆምኩ አይዘነጋም። ክፍል 4 ተዘጋጅቷል። ሆኖም ለዛሬ አንገብጋቢ የሆኑ ነገሮች እየመጡ ስለሆነ ያንን በይደር አቆጥቼዋለሁ።

ዛሬ የምንወያየው ሁለት ጉዳዮችን ነው። ስለ ፓትሪያሪኩ እና እንዲሁም “በብዙ መቶ” የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ጦርነቱ ባስነሳው በርሃብ ምክንያት ወደ ጎረቤት ጠ/ግዛቶች (በአፓርታይዶቹ አጠራር “ክልሎች”) የመሰደዳቸው ጉዳይ “የወሎ አብን” የተባለው ሰደተኞቹን አስመልክቶ እና ወያኔዎች የሰጡት በስደተኞቹ ላይ ያላገጡበት “ፌዝ” ጸያፍ ክህደትን እንመለከታለን።

መጀመሪያ ስለ ፓትሪያሪኩ አቡነ ማትያስን እንመልከት።

አቡኑ በቀርቡ በእሳት ተቃጥለው ስለሞቱት የትግራይ ተወላጆችን አስመልክተው ሐዘናቸውን እና ተግባሩ “የአረመኔዎችና የጥላቻ ቡድኖች” ስራ መሆኑን አውግዘዋል። ይህንን አስመልክቶ የአብይ አሽከር የሆነው “ዳኒኤል ክብረት” የተባለው የዘመናችን ማፈሪያ ሰው በጠባብነት አውግዞአቸዋል። ስለ ዳኒኤል ክብረት አስመልክቶ “ኢትዬ 360” ያዘጋጀው ጥሩ የሆነ ውይትን አድምጡ፤ ትምህርት ታገኙበታላችሁ።

ሌላው ፓትሪያሪኩን አስመልክተው በዘረኛ ትግሬነት የከሰስዋቸው ሰዎችም አሉ። አቡኑ በበኩሌ በዘረኛነት መክሰሱ አግባብነት የለውም ባይ ነኝ። ምክንያቱም ከፓትሪያሪኩ ንግግሮች “አንዳንድ ሐረጎች” በመምዘዝ አጉልተው በመጠቀም እንደ ትግራዊ ተገንጣይ አውግዘዋቸዋል። እኔ ግን እስካሁን ድረስ (የወደፊቱን አላውቅም) ፓትሪያሪኩ የወያኔ ዘረኞች ጠባብ አመለካከት ቢኖራቸው ኖሮ “ከዋናው ኦርቶዶክስ” አፈንግጠው “የሃገረ ትግራይ ቤተክርስትያነ ሃገረ ስበከት”
ያቋቋሙት “ፋሺሰት ካህናትን” ማውገዛቸው ቃል በቃል ባላስታውስም እንዳወገዝዋቸው በጆሮዬ ሰምቻለሁ። ስለዚህ ፓትሪያሪኩ ያላቸው ድክመት ካለ እንደድክምት ማየት እንጂ እንደ ወያኔ ተደርገው የመውሰድ ውንጀላ አግባብነት የለውም የሚል አቋም አለኝ።

አሁን ወደ ትግራይ ስደተኞችን እንመልከት፤-

በርዕሱ እንደምትመለከቱት የትግራይ ሕዝብ፤ የወያኔና “የፍራንክስታይን” ተመሳሳይነትን እንመልከት።  “ፍራንክስታይን ሞንስተር” ማለት በ1818 ሜሪ ሼሊ የተባለች ልብ ወለድ ደራሲት በደረሰቺው ልብ ወለድ ድርሰት ውስጥ (1818) “ባሮን ፍራንክስታይን” የተባለ ተመራማሪ “ሙታንን” ለማስነሳት በሚል ምርምር በመነሳሳት ከሙታን ሬሳዎች አካላት በመውሰድ ባንዳች የመመራመር ጥበብ “አዲስ ሰው” እፈጥራለሁ ያለውን ምርምሩ ሳይሳካለት ድንገት የፈጠረው ነገር “አስፈሪ ጭራቅ” ሆኖ በመፈጠሩ ተመልሶ ፈጣሪውን “ባሮን ፍራንከንስታይን” ውጦ ስባብሮ ድምጥማጡን አጠፋው።ስለሆነም “ፍራንክስታይን ሞንስተር”በመባል ይታወቃል። ወያኔዎች ወይንም ብዙ የትግራይ ምሁራን “ወያኔ” የፈጠረው የትግራይ ሕዝብ እንጂ “ወያኔ” የትግራይን ሕዝብ አልፈጠረም ሲሉ ሁሉም በሚገርም መስማማት አንድ  ዓይነት ስምምነት ደርሰዋል።

 ፍራንኬንስታይን ጭራቅ በመፍጠርየሕይወትን እና የሞትንምስጢር ማወቅ  የሞከረውን ፈጠራ ፈጣሪውን ቢያጠፋም አዲስ ዝርያመፍጠር እናሕይወትን ማደስይቻላል ብሎ ያምናል። እነዚህን ነገሮች በፍላጎት ለመሞከር ይነሳሳል። ፈጠራው ትልቅ ዋጋ ቢያስከፍልም ትልቅ ነገር ማሳካት ይቻላል ቢልም ራስን እስከማጥፋት የሚኬደው ጥፋት “የትግራይ ሕዝብና የወየኔ ትግሬዎች” ታሪክ ተመሳሳይነት አለው።በዚህ ተመሳሳይነት የትግራይ ሕዝብ ወያኔ የተባለ “ጭራቅ” ፈጥሮ “ጭራቆቹ” በፈጣሪው በትግራይ ሕዝብ ላይ ያስከተሉት ጥፋት ለታሪክ ማሕደር ለማስገንዘብ ብዙ መቶ አመታት ይፈጃል።

የቅርቡን ጥፋት እንመልከት። “ጭራቆቹ” እስከ ደብረብርሃን ጫፍ እስኪደርሱ ድረስ የብዙ ሰው ንብረት፤ ኑሮ እና ህይወት አበላሽተዋል። ጭራቆቹ የፈጸሙዋቸው ዘግናኝ ወንጀሎች ስለምታውቁት በዝርዝር ከመሄድ ይልቅ ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽሙ በኢትዮጵያ ሕዝብም ይሁን በትግራይ ሕዝብ ህይወት ላይ ከፈተኛ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ልለፈው።

በሚያስደነግጥ እና በሚገርም ሁኔታ በምስኪን ወጣት የትግራይ ወጣት ተዋጊዎች ላይ የደረሰባቸው የሞት፤የመቁስልና አካል ጉዳት ኪሳራም ሆነ እንዲሁም በሌሎቹ በዓፋሮችና በአማሮች ያደረሱት ጉዳት ከመጤፍ ሳይቆጥሩ አገኘን የሚሉት ድል ስንመለከት “ፒሪክ ቪክትሪ” የሚሉት ድል ነው።

 ካሁን በፊት ከኤርትራኖች ጋር ስከራካር ስለ “ፒሪክ ቪክትሪ” ሰፊ ሃተታ አቅርቤአለሁ። “ኤርትራኖችም ሆኑ ትግሬዎች” ድል የሚሉት ይህንን “ፒሪክ ቪክትሪን” ነው። የፒሪክ ድል “ብዙ ዋጋ የሚከፍልበት ድል ነው” ፣ ምናልባትም ለማሸነፍ የሚከፈለው ዋጋ “ትርፉ” ከስሜት ውጭ ጊዜአዊ ፍንደቃ ካልሆነ ኪሳራው ከድሉ ጋር መመጣጠን ካልሆነ “ድል” ተብሎ የተጠራው “አራስን በራስ ከማጥፋት” የሚተረጎም ፍራንሰተይን ሞንተር” ዓይነት ወጤት ነው ማለት ነው።

በቅርቡ በርሃብ ምክንያት “በመቶዎች” ተብለው ይቆጠሩ እንጂ በሺዎች እንደሚከተሉ የሚገመት የትግራይ ተወላጆች ወደ አማራ “ክልል” በመምጣት ከጭራቁ ወያኔ እያመለጡ ምግብና መጠለያ  ፍለጋ መምጣታቸው በዜና ማሰራጫ ሲናገሩ ሰምተናል።

 ወደ ወገኖቻቸው በመምጣታቸው እንደመደሰት ይልቅ “የውሎ አብን” የተባለ የፖለቲካ ድርጅት “ወያኔ” የላካቸው ናቸው በሚል በሙሉ ልቦና በመተማመን ሀፃናትን የታቀፉ እናቶች እና ትንንሽ ልጆችን በወያኔነት በድርጅታዊ መግለጫው ወንጅሎአቸዋል። ይህ እጅግ የሚኮነን የአብይ አሕመድ አሽከር በመሆን መሳቂያ ሆኖ የቀረው “ዘረኛ ድርጅት” መላው ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ ሊያወግዘው ያስፈልጋል። ስደተኞች መስለው ሊላኩ የሚችሉ ሰዎች ይኖራሉ ወይ? አዎ! ወያኔ የተካነበት ታሪኩ ነው። ሆኖም መላውን ስደተኛ እና ህጻናት የታቀፉ ሁሉ በወያኔነት መወንጀል “ዘረኛነት” እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም።ያውም በገዛ አገራቸው!!

ስለ ወሎ አብን ስናወሳ የወሎ አብን ችግር አለበት። ካሁን በፊት “ዮሱፍ ኢብራሂም” የተባለ ዘረኛ 30000 ትግሬ አቅፈን የምንቀልብበት ምክንያት የለም በማለት ትግሬዎች ኢትዮጵያዊያን እንዳልሆኑና የወሎ ሕዝብ ዕርጥባን የሚተዳደሩ በማስመሰል የተናገረው ለብዙ ትግሬዎች የጅምላ እስራት ምክንያት እንደሆነ እናስታውሳለን። የወሎ “አብን” በትግሬዎች ላይ ጥላቻ እንዳለው ተደጋጋሚ ልሳኖቹን እድምጠናል። ይህ እናወግዘዋለን።

ሌላው ዋናው ጭራቅ የትግራይ ሕዝብ የፈጠረው “ወያኔ” የተባለ የጉግ ማንጉግ ስብስብ ነው።በርሃብ አለንጋ የተገረፉትን ህጻናት፤ እመጫት፤እርጉዞች፤ሽማግሌዎች ወጣቶች ከትግራይ ሸሽተው ወደ ወሎ ሲጠለሉ በውጭ አገርም ሆኑ በውስጥ አገር ያሉ የወያኔ ጭራቆች በርሃብ ምንክንያት የተሰደደ የትግራይ ሰው እንደሌለ እና ትግራይ ውስጥ ‘ርሃብ እንደሌለ’ ተናግረዋል።

“ካሁን በፊት የተዋለድዋቸውን ዘመዶቻቸውን ለመጎብኘት የሄዱ እንጂ “ከቤተሰብ ጋር ግንኙነት ከሚደረግ አንቅስቃሴ ውጪ በርሃብ” ምክንያት ከትግራይ ወደ አማራ አገር የተሰደደ የትግራይ ተወላጅ የለም” ሲል ካናዳ ተመችቶች ልጆቹን እያስተማረ የትግራይ ሕዝብ ሲቸገር ግን “የትግራይ ሕዝብ የተራበ የለም” በማለት በርሃብተኞች ላይ ሲያሾፉና በሕዝባችን ህይወት ሲቀልድባቸው የሰማነው

“የትግራይ ክልል የውጭ ጉዳይ ግንኙነት አስተባባሪ” ነኝ የሚል  ዮሃንስ አብርሃ የተባለ  ከጭራቆቹ ወያኔ በርሃብተኞቹ ላይ ሲቀልድ ሰምተናል።

ስደተኞቹ በርሃብ ተቸግረው ከትግራይ ወደ አማራ መምጣታቸውን ‘ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ክፍል” በሰጡት ቃለ ምልልስ ተንተርሶ ጭራቁ ዮሃንስ አብርሃም “አንድም የትግራይ ተወላጅ የሆነ ምግብ ፍለጋ ወይንም በርሃብ ምክንያት ወደ አማራ የሄደ የለም። የሄዱበት ምክንያትም ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ የተጠለሉ የትግራይ ስደተኞች ከዘመድ ጥየቃ ግንኙነት ጋር የተገናኘ ነው ሲል በርሃብተኛው የትግራይ ሕዝብ ህይወት ከቀለዱት አንዱ ነው።

ይህ የጭራቆቹ በርሃብተኛ ሕዝብ መቀለድ አዲስ አይደለም፡ በ1977 ዓ.ም በትግራይ ርሃብተኛ ገንዘብ የተጫወቱበት አሳፋሪ ማሕደር በገብረመድህን አርአያ እና በአረጋዊ በርሐ የተዘገበ ነው። የትግራይ ሕዝብ ወደ ወሎ ተሰድዶም ቢሆን የምግም የመጠለያ አቅርቦት እንዳላገኘ ቢሆንም ስደተኞቹ በርሃብና በነፃነት የመናገር ፤የመተንፈስ መብታቸው ኩፉኛ መሰቃየታቸው ከጭራቆቹ ከበባ ሰብረው መምጣታቸው ይናገራሉ።

ጭራቆቹ ግን የተራበውን ሕዝብ እንደመያዣ አድርገው ለፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ እንደፈለጉ “ ዮሃንስ አብርሃ፤ጌታቸው ረዳ፤ ደደቢት ሚዲያ እና ወዘተ…” የመሳሰሉ የወያኔ ጭራቆች በተራበ ሕዝብ ላይ ቁማር እየተጫወቱ መሆኑን ከሚያስተላለፉት መልእክት መረዳት ይቻላል።

የሚገርመው ባንድ በኩል ሕዝባችን ተርቧል፤ በርሃብ ምክንያት በሺዎቹ ሞተዋል፤ እያሉ ሲጨሁ፤ የተራቡ ሰዎች ምግብ ፍለጋ ወደ አቅራቢያ ሲሸሱ ደግሞ “ዘመድ ጥየቃ እንጂ ምግብ ፍለጋ አልሄዱም” እያሉ በረሃብተኛው ላይ ሲቀልዱ መስማት በቀላሉ የማይታይ በታሪክ ሊመሰገብ የሚገባ የወያኔ “ጉግ ማንጉጎች” አንጀት ምን እንደሚመስል ማሳያ ነው።

ታዲያ “ባሮን ፍራንክስታይን” የተባለ ተመራማሪ “ሙታንን” ለማስነሳት በሚል ምርምር በመነሳሳት ከሙታን ሬሳዎች አካላት በመውሰድ ባንዳች የመራመር ጥበብ “አዲስ ሰው እፈጥራለሁ” ያለውን ምርምሩ ሳይሳካለት ድንገት የፈጠረው ነገር “አስፈሪ ጭራቅ” ሆኖ በመፈጠሩ ተመልሶ ፈጣሪውን “ባሮን ፍራንከንስታይን” ውጦ ስባብሮ ድምጥማጡን እንዳጠፋው ሁሉ “ወያኔ” የተባለ “ሰዋዊ ጭራቅ” ወደ “ጉግ ማንጉግ” የተለወጠው “አዲስ ሰው” ፈጣሪውን የትግራይ ሕዝብን መልሶ በመዋጥ ከመኖር ወደ አለመኖር አሸጋግሮታል። ባሮን ፍራንከስታይንና የትግራይ ሕዝብ መመሳሰል የዘመናችን አሳዛኙ ክስተት።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Sunday, March 13, 2022

ሰውን ከነ ነብሱ መቅበርና በእሳት ማቃጠል የወያኔ ትግሬዎች ባሕል!! በግደይ ባሕሪሹም (የአሞራ መጽሃፍ ደራሲ) ((1985 ዓ.ም አማርኛ መጽሐፍ) Ethiopian Semay

 

  

ሰውን ከነ ነብሱ መቅበርና በእሳት ማቃጠል የወያኔ ትግሬዎች ባሕል!


በግደይ ባሕሪሹም


(የአሞራ መጽሃፍ ደራሲ

((1985 ዓ.ም አማርኛ መጽሐፍ)

 

አቅራቢ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

3/13/22

ይህ ሰነድ በወዳጄ ግደይ ባሕሪሹም አሞራው የተባለ አማርኛ መጽሐፍ የተገኘ ሲሆን እዚህ የተሰነደው ጽሑፍ በ1985 ዓ.ም ወዳጄ አቶ ግደይ ባሕሪሹም አስፈቀጄ የምፍልገውን ክፍል ብቻ በኢንተርኔትና በመጽሐፌ ላይ እንዳስቀምጥ እና በድረገጼም የሚከተለው ክፍል እንዳትመው አስፈቅጄ ነበር የጻፍኩት። ሆኖም አንዳንድ የፌስቡክ ባለቤቶች ጽሑፉን ከጥቂት አመታት በፊት ቆራርጠው የመጽሐፉንም ሽፋንና ፎተግራፍ ከድረገጼ ላይ ሲቀዱት አበላሽተው እንደለጠፉት አይቻለሁ። እንዲያም ሆኖ ለደራሲውም ምስጋና ሳይሰጡ የተቆራረጠ ሰነድ ሲለጥፉት አይቻለሁና እርማት ይደረግለት።

ወዳጄ ግደይ ስለ ግል ህይቱ ታሪክ የጻፈው ሌላ መጽሐፍ እንዳርምለት ጠይቆኝ እኔ እና የድርሰት ችሎታ ያለው አንድ ወዳጄ አርመን ልኬለት ነበር፤ ፍላጎቱ አገር ውስጥ እንዲታተም ነበርና “ይታተም አይታተም አላወቅኩም( ወያኔ ሥልጣን ላይ እያለ ማለት ነው)።

ዛሬ የማቀርብላችሁ ይህ ታሪክ በአማርኛ እና አማርኛ ለማያውቁ በትግርኛ ከአማርኛ ቀጥሎ ለጥፌዋለሁ። ትርጉም የራሴ።

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ደግሞ ሰሞኑን እነማን እንደሆኑ በስም ያልታወቁ የትግራይ ተወላጆች በ (መንግሥት ታጣቂ ኦሮሞዎች ወይንም በኦነጎች ወይንም በጉሙዝ ወታደሮች/የሽምቅ ታጣቂዎች…(?)) እየተባለ በቅጡ ያልታወቀ የሽብር ቡድን እነዚህ የትግራይ ተወላጆች ከነ ነብሳቸው ሲቃጠሉ በቪዲዮ ሲሰራጭ ያዩ የወያኔ ሊሂቃን (ከጌታቸው ረዳ ጀምሮ እስከ ምሁራን ተብየ አሽከሮቹ ድረስ) ያቃጣላቸው “አማራ/ፋኖ” ነው እያሉ ሲወነጅሉ ሰምተናል።

ሰዎቹ ሲቃጠሉም የትግራይ ወያኔ ሴት ደጋፊዎች ሰብስበው፤ ወያኔዎች ለሰው ልጅና ለትግራይ ተወላጆችም ጭምር የሚራሩ ብጹአን እስኪመስሉ ድረስ ሴቶችን ሰብስበው “ሲያስለቅሱ” ለፕሮፓጋንዳቸው መጠቀሚያ ሲያደርጓቸው በቪዲዮ ተለጥፎ አይቻለሁ።

አድራጊወ አማራ ነው ብለው መወንጀሉስ እሺ ማስረጃ እስካላቸው ድረስ መወንጀል ይችላሉ፤ የገረመኝ ግን ትግረዎችን በእሳት ሲያቃጥል የነበረ ሰው ከነ ነብሱ ጉድጓድ ውስጥ አስገብቶ “እስኪተላ” ድረስ ይገድል እንዳልነበረ ምንም የማያውቁ ምስኪን ጀሌ ሴቶችን ሰብስበው ሲመጻደቁ መስማት የሚገርሙ የወያኔ ምሁራን በቪዲዮ ተሰራጭቶ አይቻለሁ።

እስኪ በአለም አቀፍ የሽብር መዝገብ ለ47 አመት ስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው የወያኔ ሽብርተኛው ቡድን እወክለዋለሁ በሚላቸው የትግራይ ተወላጆች ላይ በረሃ ውስጥ እያለ ምን ሲፈጽምባቸው ነበር? በማስረጃ እንመለከታለን።  

ከእዚህ በታች የምታነብቡት አሰቃቂ የወያኔዎች የጭካኔ ማሕደር የተገኘው “አሞራ” ከሚለው መጽሐፍ በደራሲ ግደይ ባሕሪሹም (1985 ዓ.ም) የተገኘ ሲሆን ይህን አማርኛ ወደ ታች ቀጥሎ የምታነብቡት ክፍል ወደ “ትግርኛ” ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትየጵየን ሰማይ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 1999 ዓ.ም የተተረጎመ::

በግደይ ባሕሪሹም

 

( አሞራ መጽሐፉ የተገኘ- ገጽ 197)

 

“…ሴቶች ለማገዳ እንጨት ለቀማ ከሠፈራቸዉ ወጣ ብለዉ ወደጫካ ሲሄዱ፤ በክረምት ወራት በጎርፍ የተጠራቀመዉን በደረቀው ወንዝ አፋፍ ላይ ዳሰሳ ጭራሮዉንና ጉቶዉን መምዘዝ ሲጀምሩ ፤ ጎርፍ ካጠራቀመዉ ቅርፊትና ግንድ ጋር የተቀላቀለ፤ የሰዉ አጽምና ያልፈረሰ የራስ ቅል፤ደጋግመዉ ያገኛሉ።

 

በተለይ በትግራይ ክፈለ ሃገር፤በሽሬ አውራጃ፤ በሰየምት አድያቦ ወረዳዎች ውስጥ፤የሰዉ አጽም ያልተበተነበት በረሃ ቋጥኝ የለም። ከሰላሳ ሁለት ጊዜ የወያኔ እና ኢዲህ ጦርነት እልቂት ፤ አካባቢው በወያኔ ቁጥጥር ከዋለ ወዲህ፤ የኢዲህ ደጋፊ ነበርክ፤ነበርሽ ተብለዉ በወያኔ ቁጥጥር ሥር ከዋሉ ኋ  ላ ፤በተሓህት አፈሙዝ እየተረሸኑ፤ በየፈፋዉና በየጋምስቱ የተደፉት፤ አፈር ተነፍጓቸዉ ፀረ ትግራይኮራኹር አምሐሩ” ( የአማራ ቡችላ) እየተባሉ ለአሞራ ቀለብ የሆኑትን፤ የወለደና የተወለደ፤ተሸማቅቆ ያየ ቤት ጎረቤት ይቁጠረዉ።

 

በእርስ በርስ ጦርነት ካለቀዉ ይለቅ፤ በጥርጠራና በጥቆማ ተይዘዉ፤ ለዘርና ለታሪክ እንዳይተርፍ፤ በስዉር (በሻዕቢያ ባንዳዎች) ያለቀው የትግራይ ሕዝብ እጥፍ ድርብ ነው።

 

ከክፍለሃገሪትዋ ከመቀሌ ከተማ ጀምሮ፤ በስምንቱ አዉራጃዎችና በአምሳ ሁለት ወረዳዎች ያለዉ ሕዝብ፤ፈጠን ብሎ ለእነሱበርከክ” ካላለናትግሬና አማራወይምኢትዮጵያና ትግራይበሚለዉ መሰረታዊ መፈክራቸው ላይ፤ ጥያቄ ያቀረበ ሰው ሁሉኢዲህነው፤ እየተባለ ወላጅ በልጁ እጅ እንዲመታ እና እንዲረሸን ያደረጉት ለሻዕቢያ ያደሩ የሻዕቢያ ባንዳዎች፤ በግማሽ ከኤርትራ ክፍለ ሃገር በመወለዳቸዉ፤ለነገዉ ትውልድ ጥቁር ታሪከና የማይደርቅ ደም አተረፉ እንጂ፤ በተተኪዉ የትግራይ ትውልድማ ለልጆቻቸዉ ቂም አትርፈዉ፤አመላቸውን ይዘዉ በተራቸዉ ማለፋቸዉ አይቀርም።

 

ደግ ይሁን ክፉ ሰው መቸም እንደ ድንጋይ ለዘላለም አይኖርም። ከናዚ ጀምሮ የነበረ አረመኔ ሁሉ አላለፍም ብሎ ዛላለም የኖረ ሰዉ የለም። ይህች የአረመኔዎችና የካሃዲዎች የትምክህተኞችና የቂመኞች ዘመን በተራዋ ሳትወድ በግዷ ታልፋለች። ትዉልድና ታሪክ ግን ይቀየራሉ።

 

ቁጥቋጦና ታሪክ ከመቃብር በላይ ነዉይባል የለ! ደርግ በቀይ ሽብር የከተማዉን ወጣት ሊጠርግ የሻዕቢያ ቅጥረኛ የሆነዉ ወየኔም፤ ትግራይ ዉስጥ በገጠሩ፤ ኢትዮጵያዊነቱን ያልካደና እምነታቸዉን ያላመነ ገበሬዉንና ወዛደሩንኮራኹር አምሐሩ፤ ሽዋዉያን ተጋሩ” (ያማራ ቡችሎች - የሸዋ ትግሬዎች) እያለች ኢዲህታጋይ ቤተሰብ ዘመድና አዝማድ የተባለ ሁሉ በጠቅላላ፤በሬና ላሙን፤በግ አና ፍየሉን፤ አህያዉን በቅሎዉን፤ ደሮዉንና ጎተራ እህሉን፤ ማርና ቅቤዉን፤እየወረሰች ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ለሐማሴኖች መደሰቻ ተብሎ፤ላሻዕቢያ ያልሰገደምስኪን የትግራይ አራሽ ገበሬ፤ዘር ማንዘሩከምድር እነዲጠፋ እየረሸነች፤ ለሌሎች መቀጣጫ ተብሎም በወጉ በቤተዘመድና በጎረቤት እንዳይቀበር፤ለንቃተ ህሊና ትምህርት ወደ በረሃ ተልኳል እየተባለ፤ ሳይመለስ የቀረዉ የቤትና ጎረቤት ሰዉ ታዝቢ ይቁጠረዉ።

 

ሻዕቢያ የተባለዉ የኤርትራዉ ድርጅት፤ በግማሽ ትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ዘመዶቹን፤ ወያኔ ትግራይ ድርጅትቁንጮላይ አስቀምጦ፤በንጹህ የትግራይ ዘርና ትዉልድ ላይ ግፍ የፈጸመበትበሃያኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጊዜእንደነበር፤ ለተተኪዉ የትግራይ ትዉልድ ታሪክ መጥቀስና ማዉረስ የተቆርቋሪ ወገን ግዴታ ነዉ።

 

ሻዕቢያ በወያኔ ትግራይ ስም ተሰይመው ፤ አመራሩን በወኪሎቻቸዉ ተቆጣጥረው፤ገበሬውንና አገር ወዳዱን የትግራይን ሕዝብ፤ ወጣቱንና ሕጻናቱን አሰባስበው (ትግራይ ዓደይ በል!!) “ላገሬ ለትግራይ በል!! እያሉ፤ የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት የጦርነት ምሽግና ተገን እንዲሆንላቸው አታልለውና አሞኝተው፤ ባልተወለደ አንጀታቸው በገዛ ጓሮው ኢትዮጵያዊነቱንና አነድነቱን በሚያስከብር የጠራናፊት ሠራዊት (ኢዲህ) እግር እነዳይተክል ትግራይ ወጣት እርስ በርሱ ወንድም በወንድሙ ላይ ሰይፍ እንዲማዘዝ አደረጉ።

 

ትግርኛ በመናገራቸውና ወላጆቻቸው ትግራይ ውስጥ ተወልደዉ የትግራይን መሬት ፍሬና እህል በልተው በማደጋቸው፤ ትግሬዎች ነን በማለት፤ትግራይን ህዝብለነጻነትህ ብርሃን ነው እያሉ፤ በዘር ወገናቸዉ ለሆነው ለሻዕቢያ በተንኮል ተወክለዉ፤የትግራይን ሕዝብ የወገኑ የመሃል አገር ያማራና የኦሮሞ ወዳጅነት ለዘላለም እንዳይኖረው ፤በኤርትራዊያን ተጨቁኖ፤ በአማራውም ተጠልቶና ተራርቆ እንዲኖር፤ በተንኮል ወደ ገሃነም ጨለማ  መሩት።

 

በነሱ አጠራር- “ዓጋሜ የአማራ ሰላይ”; በአማራውም በኩል ባንዳ አስገንጣይ ተገንጣይ ታሪክ ሻጭእየተባለ እንዲወቀስ፤ ዘላለም እንዲከሰስና በታሪክ እንዲኮነን አደረጉት። በሻዕቢያ መሠረተ ዓላማ የተጠመቁ ሃማሴኖች፤ የትግራይ ሕዝብ በመሀል አገር ህዝብ እንዲሞገስና እነዲመሰገን አይፈልጉም። ይልቁንም በትግሬውና በአማራው መካከል የከረረ ጠብ ተፈጥሮ የትግራይ ሕዝብ ከመሀል አገር የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየተጋጨና እየተነጫነጨ እንዲኖር፤እነሱ ግን” ግፋ በል -ጠቡን አታብርደዉ>> እያሉ የዳር ድንበር ጠያቂ ሳይኖራቸዉ  በሰላም ሊኖሩ ሕልማቸው ነው።

 

ቀን የጣለው የትግራይ ሕዝብ ቂሙን ይረሳል ማለት መሽቶ አይነጋም እንደማለት መሆኑን አላወቁትም።አንድ ቀን ዳግማዊ አሉላ ይወለዳል ቀይ ባሕር ራሱ የኢትዮጵያ ድንበር መሆኑን የሚያረጋግጥከተንቤን አንድ  ሰዉ ይወጣል” ታሪክ ይደገማል!-/-/ ግደይ ባሕሪሹም።

 

ለአቶ ግደይ ባሕሪሹም በአንባቢዎች ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። ጌታቸዉ ረዳ 

ለትግርኛ አንባቢዎች

ሰብ ብህይወቱ ቀቢርካ ምቕታልን ብሓዊ ምልብላብን ባህሊ ወንቲ ትግራይ!

ኣሞራ ገጽ 207- 209

ካብ ግደይ ባሕሪሹም - ትርጉም  ትግርኛ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

ደጋፋይ < ኢ.ዲ.ዩ “ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት” ኢኻ ፡ ወድኻ ወይ ሓዉካ እውን “ኢዲዩ” ኢዩ’ ተባሂሉ ይታሓዝ’ሞ፡ ናብ ‘ባዶ ሽድሽተ’ ይውሰድ። ኣብኡ ምስበጽሐ ዘለዎ ንብረትን ብዝሕን ኣበይ ከምዘሎን ይጥየቕ። ንዝቐረበሉ ጥያቐ መልሲ ሂቡ ምስወደአ፡ ንቑሩብ መዓልቲ ‘እዚ ዘይባሃል ጡዑም ብልዒ” እንዳተቐለበ ኣብ ካልኣይ ሳልሳይ መዓልቲ ምስ ከምኡ ዝበለ እሱር እንዳታሓጋገዘ እንተዋሓደ ክልተ ሜትሮ ዑምቀት ዘለዎ ጉድጓድ ንክኹዕት ይእዘዝ።

 

ብስፍሓቱ ኮነ ብዓይነቱ መቓብር ሰብ እዩ ዝመስል። ከም ጉድጓድ ጽብብ ኢሉ እንዳተኹዓተ ፤ እቲ ዝተፍሓረ ሓመድ ኣብቲ ኣፍ ጉድጋድ ከባቢ ወሰን ወሰኑ ዙርያ ምላሽ ይኹመር፡ አቲ ኡሱር ብደዉ ዝቕበረሉ ናይ ደዋደዉ መቓብሩ ፍሒሩ እንተብቅዕ፡ ካበቲ ጉድጓድ ይወጽእ።

ብድሕሪኡ ብገመድ ኢዱን እግሩን ተኣሲሩ ናብታ ዝፋሓራ ጉድጓድ “ኣለም በቃኝ” ይመልሱዎ።

ወየንቲ ኡሱር ቅደሚ ሞቱ እንዳተሳቐየ ምርኣይ ብጣዕሚ እዩ ዘርውዮም፡- ባህ ይብሎም - ይፍስሁ። ቀልጢፉ ንከይመውት‘ዉን ቀስ ብቐስ እንዳማናጎዩ  “ቁርማም ቅጫን - “ጽንቃቕ ማይን” መመሊሶም ብመገለል ዝመስል መትሓዚ ብገመድ ሰዲዶም ናብታ ዝኣተወላ ጉድጓድ የቐብሉዎ። ”ሽንቲ ማይ ኮነ - ቀልቀል ዝናፈሰላ -ኣብታ ዉሽጢ ጉድጓድ እዩ።” ሓንሳብ ናብታ ዝዃዓታ ጉድጓድ ምስተደርበየ ፡ምስኣተወ ፤ ብዝደኾነ ይኹን ታኣምር ተመሊስካ ምውጻእ የላን።

 እቲ ኡሱር ኣብታ ጸባብ ጉድጓድ ውሽጢ እግሩ ምዝርጋሕ ወይ ብጎኒ ምድቃስ ኣይኽእልን። ክገብሮ ዝኽእል “ተኾርሚኻ ኮፍ” ምባል ጥራሕ እያ።

“ኩርምይ” ኢሉ፤ ቀትሪ “ብጻሓይ ሃሩርን” ለይቲ “ብቀዝሒ  ኣሳሒይታ” ፤ ብዱውሉ እንዳተሳቐየ ፤- ዝተወለደላ መዓልቲን ሃገርን ዝተወለደሉ ዘርኢን እንዳረገመ ምስኣስተንተነ፤- ኣብ’ቲ ዘሰክሕ ከይዲ ሞት ቅድሚ ሙማቱ ግና እቶም “ካብ ኣብቲ ጉድጓድ መሬትን”  “ኣብቲ ኣካላቱን ዝፍጠሩ ሓሳኹ’  መርዛማት ስለዘይኮኑ ዓይጓድኡን። ቀለጢፎም ኣይቀትሉዎን።

 ቆርበቱ ሰርሲሮም፤ ሥጋኡ በሊዖም ዓዕጽምቱ ጎጥጚጦም ምፍርካሽ እንትጅምሩዎ፡ አቲ ኡሱር ኣብ መወዳእታ ብኣፉን ብኣፍንጭኡን ከምኡዉን ብዓይኑን “ሓሰኻ ድዱቛታት ፎሎቕሎቕ” ይብሉ’ሞ መሰክሕ ብዝኾነ መርገም ህይወቱ ምስሓለፈት፤- ካበዚ መርገም’ቲ ትርኢት ጭጉርጉር ዘይብሎም ወየንቲ አብቲ ኣፍ ጉድጋድ ዝተኾመረ ሓመድ “ድፍን ድፍን” ኣቢሎም ኢዱን እግሩን ታአሲሩ ብኹርምዩ አብኣ ይቕበርዎ።

 እሞ’ሲ ካብ ኮም’ዚ ዝመሰለ መስገልገላይ ሞት፤ አብ ማዕከል ሜዳ አብ ማዕኸል ጸምጸም በረኻ ፤እንተይታአሰረ ማይን እኽልን ብምስኣን፤ ህይወቱ እንዳሃለወት “ዓቕሚ ስኢኑ” ዓይኑ እንዳራኣየ “ኣሞራ” ዓይኑ እንትምንጥሎ፤ ዓርሱ ምክልኻል ምስ’ስኣነ፤ ህይወቱ እነዳተጋዓረት ፡ ስጋኡ ብኣሞራ እነዳተተኹቶኸ ተባዛጊሉ ተማናጢሉ ህይወቱ ዝሓለፈ ፤ ምስ ሻዕቢያ ግፍዒ ካብዝፈጸመሉ ሙሩኽ ሰራዊት ደርጊን ፡ - አየናይ ኮን ይሓይሽ? ኢልና እንተጠየቕና ንዘስካሕክሕ ዝተፋላለየ ስቅያት ሞት ምምርማር ካብ “ናዚ ጀርመናዊያን “ውጥጥ” ኢሎም፤ብጭካነ “ልዕል” ኢሎም” ዝተረኽቡ “ወየንቲን ሻዕቢያን” ፤- ምስ እቶም ሰብ ንሰብ ካብ ሕማሙ ንክፍወስ ምርምር ዘካይዱ “ጥበብ አብዝተስፋሕፋሓሉ ዘበን” እንትንዕዘብ ፤- ናይ ሻዕቢያን ወያነን ናይ ጭካነ-ተፋላሰፍቲን ተማራመርቲን፤ “ደቂ ኣኮን ደቂ ሓትኖን” ግን ኣብ ታሪኽ ንወለዶ “ዘሕፍር ዘኹንን” ግብሮም አብ ልዕሊ ወገን ዝፈጸሙዎ እንትናጻጸር፤ “አሸጋርን መስካሕክሒ ጨካን ኣቃታትላኦም” ክልቲኦም ወያነን ሻዓብያን ኣይባላለጹን ፤ኣይሳኾኑን፤-ኢልካ ጥራሕ አዩ ምሕላፍ ዝካኣል።

ብሂይወቶም እንዳሃለዉ ኣብ ዉሸጢ ጉድጓድ አትዮም እንዳተሳቐዩ ንክሞቱ ዝፍረዶም ተጋሩ ፤ ብመትከሎም ዘይኣምንን ኣብ ጥርጣረ ዝኣቱን እዩ። ብከመዚ ዝበል ኣቃታትላ ተፈሪዱዎም ዝሞቱ እኒ “ሃበተ ገብረተንሳይ፤ ተኽላይ ገብረመስቀል ፤ ወይዘሮ ወርቂ ምንጭራን ፤ አቶ አታክልቲ ሥዩም (አብ ከተማ ሸራሮ ራፖል ጸሓፊ ዝነበረ ወዲ ልዑል ራዕሲ ሥዩም)” ዝመሳሰሉ ተጋሩ ይርከቡዎም።

ኣብ እግረ-መንገድና ምናልባሽ “አታኽልቲ ሥዩም” መን ሙኻኑ ዘይትፈለጡ እንተዳሃሊኹም፤ ልዑል ራእሲ መንገሻ ሓወይ አይኮንካን፤ ኣቦይ’ዉን ኣይተዛረቡንን፤ ኢሎም ሕዉነቶም ዝካሓዱዎ ፡ ኣብ ኣዉራጃ ሽረ ኣብ “ሰየምት” ኣብ ዉሽጢ “ኣድያቦ” ዝነብር ዝነበረ እዩ።

 ትዉልዲ ዕብየት ወላዲቱ አብ መደባይ ታብርን ኣብ ሠመማን እየን። ኣዲኡ ካብቶም ብናይ ቀደም ኣጻዋዋዓ “ጸለምቲ” (ባሮት) ታበሂሎም ተናዒቖም ዝጽረፉ ዝነበሩ ስደራቤታት ወረጃ ወይዘሮ እየን። ንሰን እዉን ብክብሪ በቲ ዝነበረ “ባህላዊ መስፈናዊ ሥርዓት” መሰረት “ታሓዛይ ጽላል” ገይረን ፤ አሕሽኪረን ፤ ብስናር በቕሊ ዝኸዳ፤ ክሳብ ጊዜ እርጋነን ብክብረት ተኸቢረን ዝነብራ ነበራ ዓባይ ወላዲት እየን።>>

ግደይ ባሕሪሹም (አሞራዉ ካብ ዝብል መጽሓፎም)

ትርጉም ትግርኛ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay