Tuesday, December 14, 2021

የወያኔ የክርስትና ልጆች “አብይ አህመድና ወታደሮቹ” በዜጎች ላይ ጭካኔ ጌታቸው ረዳ (ETHIO SEMAY) 12/15/2021

 

የወያኔ የክርስትና ልጆች “አብይ አህመድና ወታደሮቹ” በዜጎች ላይ ጭካኔ

ጌታቸው ረዳ

 (ETHIO SEMAY)

12/15/2021

የለጠፍኩላችሁ ቪዲዮ ስታዩ የሰው ልጅ ስሜት የሚሰማው የሓዘን እና የመናደደ ስሜት ካልተሰማችሁ “ልዩ” ፍጥረት ናችሁ ወይንም “የአብይ አሕመድ ተከታዮች” ናችሁ ማለት ነው። አንድ  ዜጋ የፈለገው ወንጀል ቢፈጽምም ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ የፀጥታ አባልትና ወታደሮች “ጠመንጃ” ስለታጠቁ ብቻ በጦር ሜዳ የተማረከም ሆነ በተለያየ ማሕበራዊ ወንጀል በመፈጸም ምክንያት የተየዘ ዜጋ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ ላይ እንዲህ እየቀጠቀጡ ሲያሰቃዩ ስታዩ ሓዘን እንደሚሰማችሁ እርግጠኛ ነኝ።

ታስታውሱ ከሆነ ካንድ አመት በፊት አሮሞ “ክልል” ውስጥ አንድ ታዳጊ ወጣት ያለ ምንም የፍርድቤት ትአዛዝ “ሽጉጥ አንገቱ ላይ አንጠልጥለው” የፍጢኝ አስረው አደባባይ  ላይ ወላጆቹ እያዩ በጥይት ሱረሽኑት በተቀዳ ‘ቪዲዮ’ ተመልክተናል።

አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ “ፖሊሶች እና መርማሪዎች በዜጎች ላይ ሲፈጽሙት የነበረውን ወንጀል በማውገዝ” በራሱ ስርዓት ግን ይህንን አሰቃቃ ማን ያህለኝነት “ሁለተኛ ጊዜ እንደማይደገም” ፓርላማ ውስጥ እየተመጻደቀ ሲናገር ታስታውሱታላችሁ።

ሆኖም እውነትና ንጋት እያደረ ይጠራል እንደሚባለው ድሮ በስለላ ስራ ሲሰራው የነበረ ጭካኔ ዛሬም በሚያስደግጥ ፍጥነት ሳይውል ሳያድር “ከሰላማዊ የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹ” ጋር “ጦርነት” ከፍቶ ፖለቲከኞችን በማሰር “ሀ” ብሎ የተካነበት የጭካኔ ሙያው ተግባራዊ በማድረግ አሳየን።

እርሱ እንዲህ ሲያደረግ ወታደሮቹ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ቪዲዮ የምትምለከቱት “ተባባሪ’ ተብሎ “ተናገር!!!” እያሉ እጆቹ እስኪዝሉ ድረስ በጨንቅላቱ ላይ የጫኑበትን ጠመንጃ እንዲይዘው በማድረግ “አምበርክከው” በግድ ሲያስለፈልፉትና ኩላሊቱና የጀርባ አጥንቱ ላይ በእርግጫ እየመቱ የሚያስቃዩ ወታደሮቹ በብዛትና በፍጥነት በየቦታው ኢትዮጵያ ውስጥ ከበፊቱ በባሰ እየተራቡ መጡ።

በወያኔ ዘመን እስረኞችን በቡጢ፣ በጥፊ እና በእርግጫ በሰከሩ  ወታደራዊ ፖሊስ አባላትና መርማሪዎች በእስረኞች ላይ ሆን ተብሎ የሚፈጸም በደል ነበር። ጥፍር መንቀል፤ ለፖለቲካ ፍጆታ እንዲውል የተራቆቱ ወንድና ሴት እስረኞችን በቪዲዮ መቅረጽ እና ፎቶግራፍ ማንሳት በሴቶችና በወንዶች አስገድዶ መድፈር እና ግብረ-ሰዶም” መፈጸም፤ ሴት መርማሪዎች ሓሺሽ እያጨሱ እርቃናቸው በመውጣት በገመድ ተንጠልጥሎ እየተገረፈ ያለውን እስረኛ “ብልታቸው እያሻሹ ና ይኼው እያሉ ” ሲያንቋልጡ እንዲያያቸው ማድረግ (ዮናስ የተባለ ኢትዮጵያዊ በድብደባ ብዛት |ፓራላይዝ ሆኖ” አሁን ለሕክምና አሜሪካ መጥቶ የነበረ ወጣት ምሁር ይህንን  ድርጊት የዓይን ምስክርነቱን ሲናገር ሰምታችሁት ይሆናል)፤ እስረኛን 19 ሰዓት በገመድ ሰቅሎ “ቁልቁል  ገልብጦ” ማሰቃየት፤ እስረኛ ከጅብ ጋር አብሮ ባንድ ክፍል እንዲታሰር ማደረግ…..  የመሳሰሉ እጅግ አሰቃቂ ነገሮች በዘመነ ወያኔ ተፈጽሟል።

ያ ሁሉ ስቃይ አንደግምም ብሎ ሲምልና ሲገዘት የነበረው “የሻዕቢያው ኩሊ” አብይ አሕመድ ሥልጣን ሲይዝ ያንን በመድግም አሰቃቃ የመብት ጥሰት ሲፈጸም በብዙ ማስረጃዎች ደጋግሜ ሳሳያችሁ 3 አመት ሙሉ የምታስታውሱት ነው።

ይህ ሁሉ ጭካኔ እንዴት እንደገና ሊደገም ቻለ? የሚል ጥያቄ ለናንተው ለኢትዮጵያ ሰማይ አንባቢዎቼ ዛሬም አቀርባለሁ። ይህ እስረኛ በነገዱ “ኦሮሞ” ይመስለኛል። አንድ ሰው የማንም ነገድ ይሁን “ወንጀል ስለፈጸመ” ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መደብደብ የለበተም። ፖሊሶችና የጦር አባላት ጠምንጃ እና የማሰር ሥልጣን ስለተሰጣቸው “እራሳቸው ፖሊሶች፤ እራሳቸው ሕግ አውጪዎች፤እራሳቸው ሕግ አስፈጻሚዎችና እራሳቸው ዳኞች” ሆነው ከመቀጽበት ያለተጠያቂነት በዜጎች ላይ እርግጫና ድብደባ በሚፈጽሙት ላይ ምን ቢደረግ ይሻላል?

ጋዜጠኛዋም፤ፖሊሶቹም ያሳዩት ጭካኔ ለማን ኣቤት ተብሎ በየትኛውስ መንግሥት በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ ይቻላል? እስከመቸ ድረስ? የተለየ ሃሳብ ካላችሁ እንወያይበት። ይህ ቪዲዮ ካየሁት የቆየ ቢሆንም እንደገና መየቱን ስለተቸገርኩ አቆይቼው ዛሬ እንደገና ቀስ ብየ አቀርበዋለሁ ብየ አቆይቼው ዛሬ ሳየው ምግብ ልበላ አልቻልኩም ከናንተው ጋር አብርን እንወያይበት።

ከሕግ በላይ እየሆኑ ዜጎቻችንን እያሰቃዩ ያሉት የወያኔ የክርስትና ልጆች “አብይ አህመድና ወታደሮቹ” በዜጎች ላይ ከሕግ ውጭ የማሰርና  የጭካ ድብደባቸውን ለማስቆም ምን ብናደርግ ይሻላል? ይህ ስርዓት ላንዴና ለመጨረሻ እንዴት እናሳጥረው?

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

(ETHIO SEMAY)

 

 

No comments: