Saturday, December 11, 2021

ትግሬዎች በነገሡበት 27 አመት ውስጥ ተቃወሚ ትግሬዎችን ምን ያደርጓቸው ነበር? ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 12/12/2021

 

 

ትግሬዎች በነገሡበት 27 አመት ውስጥ ተቃወሚ ትግሬዎችን ምን ያደርጓቸው ነበር?

ጌታቸው ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY 12/12/2021

ከዚህ በታች ምስክርነታቸው የሚሰጡን ማይጨው የተወለዱት የስነጽሑፍና የእንግሊዝኛ ቋንቋ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ምሁሩ ትግራይ ተወላጁየቅንጅት ፓርቲ  አመራር” አባል የነበሩት ዶክተር ሃይሉ አርአያ ናቸው

ዶክተር ሃይሉ ለረዢም ጊዜ በእስትሮክ በሽታ ታመው በቅርቡ ተሽሎአቸው ማየቴ በጣም ደስብሎኛል።በዚህም ምክንያት በጣም በጣት የምንቆጠር የትግራይ ተወላጆች ጸረ ወያኔነታችን ሳናመነታ ለረዢም ጊዜ ከዘለቁነው አንዱ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ዶክተር ሃይሉ አርአያ ናቸው።በተለያዩ የፖለቲካ ልዩነታችን አለፍ አለፍ ብየ ብወቅሳቸውም ለአርበኛነታቸውና ቆራጥ ትግላቸው ልዑል ክብር አለኝ።

እኚህ አገር ወዳድ ብርቱ ሰው መርሳት ስለሌለባችሁ በቅርቡ ወደ ፖለቲካው የተቀላቀላችሁ አዳዲስ ወጣቶች እንደገና እንድታውቁዋቸው ዘንድ እነሆ ባለፈው 27 አመት ወያኔዎች በእሳቸው ላይ ያደረሱት ምን እንደነበር ለትውስታ እነሆ እንደትመለከቱት ይህቺን አጭር ማስረጃ ከአንደበታቸው እነሆ ጀባ እላችሗለሁ።  

“…ከቤቴ እየደበደቡና እየተሳደቡ የወሰዱኝ የትግራይ ልጆች ነበሩ። ማዕከላዊ እንደደረስኩ ቀበቶዬን ያስፈታኝ የትግራይ ሰው ነው። ከእርሱ ተቀብሎ አንድ የፍሪጅ ያህል የሚቀዘቅዝ ክፍል አስገብቶ የቆለፈብኝ የትግራይ ሰው ነው። ሲመሽ ሽንት ቤት ወስዶ ያሸናኝ ሰው የትግራይ ሰው ነው።እየተሳደበ ቃሌን የተቀበለኝ የትግራይ ሰው ነው።በእርግጥ እኔ የትግራይ ሰው ሆኜ ከአንድ አካባቢ በወጡ ሰዎች ጥቃት እየደረሰብኝ እንደሆነ ከተሰማኝ ሌላው ሰው ምን ሊሰማው እንደሚችል አስቤ ለትግራይ ህዝብ ከልቤ አዘንኩለት። ይሄ ሁሉ የሚደረገው ለትግራይ ህዝብ ሲባል ነው መባሉ ደግሞ የበለጠ ሰላሜን ነሳው።

ይህን ምስክርነት የሰጡት የትግራይ ተወላጁ የቅንጅት አመራር የነበሩት ዶክተር ሃይሉ አርአያ ናቸው ምንጭ ዶክተሩን ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን ከንግግራቸውና ከግጥማቸው ወስጄ  ካሳተምኩት መጽሐፌ የተገኘ ነው።

ከግጥማቸው ለቅምሻ ትንሽ ላስቀምሳችሁ

                               

ኑሮ ከፋኝ ብሎ ሲፈልስ ወጣቱ፤

ኑሮ ከፋኝ ብሎ ሲፈልስ አዛውንቱ

አገር ከፋኝ ብሎ ሲሰደድ ሙሁሩ

ሰው መኖር ሲያቅተው በትውልድ አገሩ

“ልሂድ!” “ልውጣ!” ሲሆን የሰው ንግግሩ

“አንተ እንኳን አትሄድም ባታስበው ብሎ

ያገር ፍቅር ደዌ ይዞኛል ቸክሎ!

ግጥም

ሃይሉ አርአያ

ETHIOPIAN SEMAY

No comments: