አቻምየለህ
ታምሩ
የእሬቻ
ነገር. . .
10/1/2021
ኢትዮ ሰማይ
ዐቢይ አሕመድና የዘረጋው የአፓርታይድ አገዛዝ ባላደራዎች ባለፉት ሶስት
ዓመታት ውስጥ ጥንታዊቱን በራራን፤ ዘመናዊቱን አዲስ አበባን አፍርሰው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ውስጥ በተፈጠረችው ፊንፊኔ
ለመተካት ያላፈረሱት የቆየ አሻራና የከተማይቱን ጥንታዊነት የሚመሰክር ምልክት የለም። የከተማ አስተዳደሩን የፖሊስ ሠራዊት ኦሮሚያ
ከሚባለው ክልል በመለመሏቸው ለከተማው ከባሕር የወጣ አሳ በሆኑ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ቀሮዎች ተክተውታል። ደብረ ዘይት በሚገኘው
ሆራ ሐይቅ ከመስቀል በኋላ ይከበር የነበረውን እሬቻን "ሸገርን ለማስዋብ" በሚል ዐቢይ አሕመድ ግለሰቦችን [አብዛኛዎቹ
አማሮች ናቸው] አምስት አምስት ሚሊዮን ብር እንዲያወጡ አድርጎ ባስቋረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲከበር አድርገዋል።
በመሰረቱ እሬቻ የኦሮሞ ገዢ መደብ በየስምንት አመቱ ሲያደርግ የኖረውን ወረራ ገና ሳያካሂድ፤ ኦሮሞ የእርሻ ስራና ሰብል ማምረት ሳይጀምርና ኦሮሞ ዛሬ ኦሮምያ የሚባለውን ምድር ሳይረግጥ መስከረም በገባ መስቀል በተከበረ በሳምንቱ ሲከበር የኖረ የአራሾች ክብረ በዓል ነው። እሬቻ በሸዋ ውስጥ በብዛት ይከበረ የነበረው ደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ሥፍራ በነበረው ዛሬ ሆራ ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ነው።
በመሆኑም የእሬቻ በዓልንም የሚያከበረው አራሹ ገበሬ ክረምቱን በሰላም እንዲያልፍ፤ ያዘመረው እህል ለፍሬ እንዲበቃና እሸት እንዲቀምስ ያስቻለውን ፈጣሪውን ለማክበር ነው። በመሆኑም የእሬቻ በዓል እህል የሚያበቅል አራሽ ገበሬ የሚያከብረው አመታዊ ዝክር ነው።
በመሆኑም የእሬቻ በዓልንም የሚያከበረው አራሹ ገበሬ ክረምቱን በሰላም እንዲያልፍ፤ ያዘመረው እህል ለፍሬ እንዲበቃና እሸት እንዲቀምስ ያስቻለውን ፈጣሪውን ለማክበር ነው። በመሆኑም የእሬቻ በዓል እህል የሚያበቅል አራሽ ገበሬ የሚያከብረው አመታዊ ዝክር ነው።
ስለዚህ እሬቻ ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ ከነ ቃሉ ከሰብል አምራች የአማራ አርሶ አደሮች የወረሰው የምስጋና በዓል፣ ቃሉም አማርኛ ሲሆን ኦሮሞ አካባቢውን ከመውረሩ በፊት ጀምሮ ይከበር የነበረው ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ እንጂ አዲስ አበባ ውስጥ አልነበረም።
ይህ እውነት ቢሆንም ቅሉ የኦነጋውያን ኦሮሙማ ማዕከሉ ዘረፋ፣ ወረራና
ቅሚያ ስለሆነ አዲስ አበባን ዳግማዊ ምኒልክ የጥንቱን በራራ ፍራሽ አድሰው እንደገና ከማቆማቸው በፊት የነበሩት ኦሮሞዎች፤ እሬቻም
ከነ ቃሉ የኦሮሞ አይደለም፤ አዲስ አበባ ውስጥም ተከብሮ አያውቅም የሚለው የታሪክ እውነት ደንታ አይሰጣቸውም። ኦነጋውያን እንኳን
በአዲስ አበባ ዙሪያና በመላው አገሪቱ የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ቀርቶ ከቦረና ውጭ ያለው ኦሮምኛ ተናጋሪ በወራሪ አባገዳዎች መሬቱን
የተቀማ፣ ማንነቱን በኃይል የቀየረና ኦሮምኛ ቋንቋ በግዳጅ እንዲናገር የተደረገ እንጂ ኦሮሞ አለመሆኑን ኦሮሞዎ ብሔርተኞቹ እነ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፈሰር
መሕመድ ሐሰን፣ ወዘተ እንኳ ያጠኑትን ታሪክ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ ሕመምተኞች ናቸው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ትክክለኛ ኦሮሞዎቹ
ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። ከነሱ ውጭ ያለው ነባሩ ሕዝብ ተገዶ ኦሮምኛ እንዲናገር ተደረገ እንጂ ኦሮምኛ ስለተናገረ ኦሮሞ አይደለም።
ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው
ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች ትውፊት ውስጥ «Saglan Borana, sagaltamman garba» የሚል አባባል አለ።
ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርበ ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን
ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ ትውፊት መሰረት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝበ
መካከል ትክክለኛው ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል
ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው።
የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና ጋር አይደለም። ጀርመናዊው
የታሪክ ምሁር በርካምበር እንዳጠናው ከአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው። የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ
ጋር ምንም ዝምድና የለውም። አባጅፋር ራሱ አረብ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስርም አይሞሉም። እውነተኛ
ኦሮሞዎቹ ለባሪያ ፍንገላና ውሀና ሳር ፍለጋ መጥተው ሌላውን ገርበ አድርገው የቀሩት አባገዳዎችና ልጆቻቸው ብቻ ናቸው።
የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም።
በየትኛውም አለም ብሔርተኛ ሆኖ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር ሲያፈርስን እንጂ አገር ሲያረጋጋና ሲያስተዳድር ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም።
በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ በብሔርተኛነት እሳቤ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር የማስተዳደር እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ ያለው
አገዛዝ የለም። የኦሮሞ ብሔረተኞም ዓላማቸው ወንድምን በወንድም ላይ እኅትን በእኅት ላይ በማስነሳት የኦርሞ ኤምፓየር ቅዠታቸውን
ማሳካት እንጂ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የማስተዳደር ፍላጎት፣ እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ የላቸውም።
እእሬቻ የሚባል የአማርኛ እንጂ የኦሮምኛ ቃል የለም። እሬቻ የሚል ስር ያለው የኦሮምኛ ቃል የለም። ባለፈው ዓመት እሬቻ ቃሉም ሆነ ባሕሉ የኦሮሞ አለመሆኑን በጻፍሑት ጽሑፍ ላይ አንዱ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ባቀረበው ትችት እሬቻ አሮምኛ ነው፤ “ህርሱ” የሚል ቃል በኦሮምኛ ውስጥ አለ፤ ትርጉሙም መስጠት ማለት ነው፤ ስለዚህ እሬቻ የተወሰደው ከህርሱ ነው የሚል መልስ ቢጤ ጽፎ ነበር። ይህ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ግን የበዓሉ ትርጉም ህርሱ የሚል የኦሮምኛ ቃል ከሆነ በዓሉ ኦሮምኛ ወዳልሆነው ወደ እሬቻ ለምን እንደተቀየረ አልነገረንም። በዓሉ የኦሮሞ ከሆነ፣ ቃሉም ኦሮምኛ ከሆነ በዓሉ ህርሱ ተብሎ ለምን እንደማይከበር፤ በእርሻ የሚተዳደሩ ገበሬዎች የሚያከብሩትን ይህን በዓል ቀዳሚው ኦሮሞና ከብት አርቢው ቦረና ሳያከብረው ገርባው ብቻ ለምን እንደሚያከብረው መልስ የሰጠ ሰው እስካሁን አላየንም።
በእውነቱ እሬቻ የኦሮሞ ባሕል ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ፤ በዓሉንም ከሁሉ በፊት እሬቻን ሊያከብሩት የሚገባቸው ገርባዎች ሳይሆኑ ትክክለኞቹ ኦሮሞዎች ቦረናዎች ነበር። ያልተበረዘው ቀዳሚው ኦሮሞ የሆነው ቦረና የማያከብረው በዓል የኦሮሞ በዓል አይደለም። ቦረና ራሱ እሬቻን የገርባ በዓል ነው የሚለው። እሬቻ የኦሮሞ ባሕል አለመሆኑን ለማወቅ ቃሉ አማርኛ እንጂ ኦሮምኛ አለመሆኑን፤ በዓሉም በእርሻ የሚተዳደሩ እንጂ የከብት አርቢዎች በዓል አለመሆኑን፤ በዓሉ ኦሮሞ የእርሻ ስራን ከመልመዱ ዘመና በፊት ዛሬ በሚከበርበት በደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ በአማሮች ሲከበር የኖረ በዓል መሆኑን፤ ገርባው እንጂ ያልተበረዘውና ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ቃሉንም ሆነ በዓሉን የማያውቀው መሆኑን፤ ይልቁንም እሬቻ ሲከበር የኖረው ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ከሚኖርበት 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ መሆኑን ማስታወስ በቂ ነው። ቦረና የማያከብረውን በዓል ገርባው የኦሮሞ ነው ብሎ ማክበሩ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ገርባው ኦሮሞ አለመሆኑን ብቻ ነው። እሬቻ የኦሮሞ ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ ይሆን ነበር፤ በዓሉም በገርባው ምድር ሳይሆን ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነ ቦረና በሚኖርበት በቦረና ምድር እንጂ ቦረና ከሚኖርበት አካባቢ 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ገርባ እንጂ ቦረና በማይኖርበት ምድር በሸዋ ውስጥ አይከበርም ነበር። ይኼው ነው።
No comments:
Post a Comment