Friday, October 15, 2021

በሞኖማኒያ የቀወሰው መሪ ጌታቸው ረዳ­­ (ኢትዮ ሰማይ) 11/16/2021

 

በሞኖማኒያ የቀወሰው መሪ

ጌታቸው ረዳ­­

(ኢትዮ ሰማይ)

11/16/2021

አብይ አሕመድ በበርካታ የሕሊና ሕመሞች የሚሰቃይ ባለ ብዙ የገጽታ ባሕሪ ፍጡር ነው። አብይ አሕመድ እንደ የበቃ ሰው እና መሪ ሳይሆን አለመታደል ሆኖ የሚያንጸባርቃቸው የልጅነት ባህሪዎቹ አመዝነው ሲከሰቱ ይታዩበታል። ከፍተኛ ስሜታዊነትና የማይጨበጡና ሊሆኑ የማይችሉ የስሜት ንግግሮች በመናገር ሕዝብ ለማሞኘት ሲሞክር ያስታውቃል።

 የልታይ ልታይ ባሕሪው ከፍተኛ የመንግሥት ገንዘብ በማባከን ዝናን የመጓጓት ባሕሪ ከማሳየት ጀምሮ በሃይማኖት፤ በሰንደቅዓላማና በነገዶች ላይ ከባድ፤ ከባድ የሆኑ ድፍረቶችና ጉዳቶች እንዲከሰቱ መንገድ በማመቻቸት፤ ሰው የሚያርዱ የሰው ስጋ የሚበሉ፤ ግበረሰዶም የሚፈጽሙ የታጠቁ ሃይሎች ወደ አገር በማስገባት፤ በገንዘብ እና በሃሳብ በመርዳት (እራሱ የተናገረው ነው) ጉዳት እንዲደርስ የሚፈቅድ አውሬአዊ የሆነ የሕሊና ህመምተኛ ሰው ነው።

ሰይጣናዊ (ኢቭል) የሆነ ባሕሪ ስለተላበሰ፤ ተቀናቃኞቹን በውሸት አስሮ ሕክምና የሚነፍግ እርጉዝ እናቶች እናወተት የሚያጠቡእናቶች በፖለቲካ አሳብቦ እስርቤት በማስገባትህጻናትሲቸግሩና ሶያለቅሱ ማየት የሚደሰት በመሆኑ በሥልጣን በቆየ ቁጥር አደገኛ ገዳይ እየሆነ እንደሚመጣ አያጠራጥርም።

ብዙ አገሮች በቀወሱ መሪዎች ሲመሩ አይተናል። በራሱ መቀወስ ግን አንዳንዱን እጅግ አስገራሚ የሆነ አመራር ሲሰጡ ታይተዋል። ለምሳሌ 4 ታዋቂ መሪዎችን እንመልከት።

 

አሜሪካዊው አብርሃም ሊንከን በዲፕረሽን (የሕሊና ድብርት) ሲሰቃይ ነበር። እራሱንም ለመግደል የሚዳዳበት ወቅት ነበር (ሥልጣን ላይ እያለ)

እንግሊዛዊው ቸርችልም እንዲሁ የሕሊና ቀውስ ደርሶበት ነበር።እራሱም ሲሰማው የነበረውን ስሜትና ጫና ይናገራል።

የጥቁር አሜሪካኖች መሪማርቲን ሉተር ኪንግእንዲሁ በሕሊና ድብርት ሲሰቃይ ነበር።አማካሪዎቹ ወደ ሕክምን ሊወስዱት ቢጠይቁትምአምቢሲል ነበር። ሆኖም እራሱ መታመሙ ቆይቶ አምኗል።

ሌላ፤ እንግሊዛዊትዋልዕልት ዳያናናት። እርስዋም እንዲሁ በድብርት ተሰቃይታ እራስዋን እስከመግደል ደርሳ ነበር። በዚህ ቀውስ መያዝዋንም ይፋ አድርጋ መኖርዋን ታስታውሳላችሁ።

እንዲህ ሆኖም እነዚህ መሪዎች በዛው የሕሊና ቀውስ ታመውም እያሉ አስገራሚ ድሎች እና የተለያዩ ዕቀዶችን በማቀድ በርካታ ድሎችን አስገኝተዋል። የአገራችን መሪ ተብየውህጻኑ አብይ አሕመድ ግንበሽታው በጣም በርካታ ስለሆነ ከዚያ በሽታው ለመላቀቅ የሚያደርገው አንድ ነገርከቅጠልና ከችግኝ ጋር የሚያደርገውተደጋጋሚ ትኩረትነው።

ደጋግሞ ቅጠልና ችግኝ ወይንም አዝርእት ላይ ፎቶግራፍ እየተነሳ ተደጋጋሞ የምናየው ምክንያት የሕሊና ቀውስ ነው። የሕሊና ጠበብቶች ይህንን ተደጋጋሚ ቀውስ “Monomania” ይሉታል።

እንደምታውቁት በወለጋም ይሁን በበርካታ አካባቢዎች የአማራ ሰብል ሲቃጠል፤ አማራዎች እንደ እንሰሳ ተጋድመው ሊታረዱ ፈቅዷል።አማራዎችን ያተኮረ ጥቃት የተፈጸመውአብይ አሕመድ በሚያስተዳድረው እራሱ በሚያዛቸው የመንግሥት ታጣቂዎች ተባባሪነትነው። የዩኒቨርሲቲ 21 ልጃገረዶች ታፍነው በኦሮሞ ታጣቂዎች ሲወሰዱውጭ ጋር ሄደው ሊሄዱ ይችላሉ፤ ወይንም ለዝና ብለው ታፍነናል ብለውም ይሆናል…” በማለት የአፈናው ተባባሪ ሆኖ ሲያሾፍ አደምጠናል። አሽከሮቹም፤ የታፈኑት ወደ ወላጆቻቸው ተመልሰዋል፤ ሲሉ አደምጠናል። ይህ ሁሉ ለቀውሰኛው መሪ የባሕሪው መገለጫ ነው።

ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈጸም ፤አገር በጋጠ-ወጥ ጦረኞች ስትፈርስ፤ የሕዝቡን ደህንነት መከላከል የማይችል፤ ሳያሸንፍ አሸንፌአለሁ እያለ ዜጎችን ሲያስፈጅ፤ ይህ የአእምሮ በሽተኛ ሰው በመታመሙ ምክንያቱ አካባቢው ዙርያ ላይ ምን እየሆነ እንዳለ ምንም ሊያሳየው አልቻለም።ይባስ ብሎ በተደጋጋ ችግኝ እና ቅጠል እየጨበጠ ፎቶ በመነሳት እየተፈጸመ ያለው እውነታ አሳንሶ በማየት እራሱን ሲያክምም ይታያል።

 የአፍሪካ መሪዎችን በመጋበዝ በዓለም ፊት ለመታየት የሚቃጣው ሁኔታው ጋር የማይሄድ መሽቀርቀር እያሞረው የምናየው፤ የአእምሮ ጤና የውጥረት ውጤቶች ናቸው።የአእምሮ ህመምተኛተብሎ መጠራት ድክመት መስሎ ስለሚታያቸው፤ ትልቅ ሸክምም ስለሆነ በዚህ ቀውስ የሚሰቃዩ መሪዎች ሊታወቅባቸው አይፈልጉም። ስለዚህም ለሕመማቸው ውጥረትመሽቀርቀርን” “መዋሸትንአቅም በላይመወጠርንማምለጫ ያደርጉታል።

 ታዋቂ ገናና መሪዎች በአእምሮ ጤና ሁኔታ የሚሰቃዩ አሉ። እንዳውም የት እንዳየሁት አላስታውሰውም እንጂ ሥልጣን የሚመኙ በሕሊና ቀውስ የሚሰቃዩ ሰዎች ብቻ ናቸውየሚል አንብቤአለሁ።

 “ማኒያ” (ከተለመደው ውጪ) ይላሉ ሊቃውንትፈጠራን እናለአሰቃቂ ሁኔታ የመቋቋምችሎታን ታሳድጋለች፤ ይላሉ።  የመንፈስ ጭንቀት ደግሞ እውነታን እና ርህራሄን ይጨምራልየሚሉም አሉ።

ወጣም ወረደ የአብይ አሕመድ ቀውስ ብዙ አይነት የገጸ ባሕሪ በሽታ ስላለው አንዱን ካንዱ ሲጋጭበት አስቀድሜ የገለጽኩትን “Monomania” በሚባለው የውጥረት ማስታገሻ አንድ ነገር ላይ በማተኮር እራሱን ሲያክም ይታያል። አብይ አሕመድ የዚህ Monomania” በሽታ ማሳያ ነው።

 “Monomania” ማለት አንድ ሰውበአንድ ነገር ብቻበማተኮር ጊዜውን ትኩረቱን እዛው ላይ በማተኮር የሚታይ የገጸ ባሕሪ በሽታ ነው። ጤነኛ ሰው ቢሆን ይህ ሁሉ የዘር ጭፍጨፋ፤ስደት፤እልቂት፤ ራሃብና መፈናቀል ባለበት አገርየስንዴ ማማር ጉብኝትላይ በተደጋጋሚ በማሳለፍ ጊዜውን አያሳልፍም።

በተለይ በተጧጧፈ ጦርነት ተዋጊ ጦር እጥረት አለ በሚባልበት ወቅት፤በሺዎቹ በተማረኩበት ጊዜ፤ ልዩ  ሃይሎችንና ወታደሮችንችግኝ እንዲተክሉ በማድረግ” “ፓርክ ላይ እየሄደ አበባ እና ቅጠልበመጨበጥ ፎቶግራፍ ይነሳል።

በሚገርም ሁኔታም አደባባይ ላይ የተከልኳቸው፤ ውሃ ያጠጣሁዋቸውየሚያማምሩ አባባዎቼንሰዎች እየቀነጠሱብኝ ነው፡ ብሎ ለፓርላማ አቤቱታ ማቅረብን የሚያሳየን ክስተት ሰውየውበጭለማ ድብርት” (ዲፕረሽን) ውጥረት ሲሰቃይ “Monomania” ሂደት እራሱን ሲያክምና በችግኝ ላይተደጋጋሚ ንግግሮችንሲናገርና ሲያተኩር  ያየንብት ምክንያትም ለዚህ ነው። ይህ በሽታ በሳይኪያትሪክ ሊቃውንት እንጂ በመደዴ ታዛቢ አይታወቅም።

ይህ ሁሉ ሲሆን እግዚአብሔርንም ተጠያቂ አድርገው የት እንደተሸሸገም የጠየቁ ዜጎች አሉ። ይህንን አስገራሚ አገላለጽ አንብቡ፡

እንጨት ቁጭ ብሎ ሰው እየነደደ

ሕግ አዋቂ ቆሞ ሌባ እየፈረደ

አሳ መረብ ጥሎ ሰው እያጠመደ

አንበሳ በጅቦች እየተሳደደ

የእርግቦች ማህጸን ጊንጥ እየጸነሰ

ሰማይ ጭስ አርግዞ እሳት እያፈሰሰ

ሰው እየተጋዘ አውሬ እየነገሰ

ቀሳውስት ተወግዘው ሌባ እየቀደሰ

እምየ ማቅ ለብሳ ልጅ እየደነሰ

ይህ ሁሉ ሲሰራ መላው ጠፍቶን እኛ

እረ ወዴት ገባህ የሰማዩ ዳኛ?”

ሲሉ ዜጎች ጠይቀዋል፡

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ- Ethiopian Semay)

No comments: