Wednesday, March 31, 2021

ሽልማት ሲሸለም አማርኛ ላለመናገር የተጸየፈ የኮካ ኮላው ትውልድ እና ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ጉልበት በማጠፍ ንቀት ያሳዩ የወያኔ ጋሪ ጎታች ፈረሶች ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) 3/32/2021

 

ሽልማት ሲሸለም አማርኛ ላለመናገር የተጸየፈ የኮካ ኮላው ትውልድ

እና

ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ጉልበት በማጠፍ ንቀት ያሳዩ የወያኔ ጋሪ ጎታች ፈረሶች

ጌታቸው ረዳ

(Ethio Semay)

 3/32/2021


የፎቶ ቅንብር ኢትዮ ሰማይ ላይ የተለጠፈ

በአሜሪካ አገር ሕገመንግሥት 36 አንቀጽ 301” (36 U.S. Code § 301) ብሔራዊ መዝሙርን እና ሰንደቃላማን በሚመለከት የከዋክብት ባንዲራ’ (Star-Spangled Banner) በመባል የሚታወቀው ስያሜ (Designation) ቃላቶችንና እና መሳጭ የዜማ ጥንቅር የያዘ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር እና ብሔራዊ ሰንደቃላማ ሲወጣም ሲወርድም ዜጎች (በርጌሶችና ወታደሮች) ማሳየት ያለባቸው ስነምግባሮችና ግዴታዎች ተደንግጓል።
 

ኢትዮጵያ እንደ አሜሪካ አገር አንድ ወጥ የሆነ ቋሚ መዝሙርና ሰንደቃላማ ባይኖራትም መሪዎች ሲለዋወጡ የራሳቸው መዝሙር እየቀረጹ ሕዝቡን ሲያስዘምሩት ሰንደቃላማዋንም እንደግል ንብረታቸው ያሻቸውን ምልክት የሚያኖሩባት ኢትዮጵያም አሳዛኝ ድርጊት ቢፈጸምባትም ለክብርዋ “መለያ” ተብሎ የተቀረጸ መዝሙርና ሰንደቅ አላማ አላት።

 በዚህ ሳምንት ውስጥ ይህንን በሚመለከት በመናበብ የተቀናጀ አገራዊ ጠል የሆኑ ከትግራይ ክ/ሃገር የተወለዱ ወጣት የኪነት ሰዎች እና ከአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ አያሌ የትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛነትን ክብር ሳይሰጡ “በትግራይ ሕዝብ ሽፋን” ለወያኔ ፍቅር ወድቀው ኢትዮጵያ ያነጠፈችላቸው የክብር ምንጣፍ ሲጸየፉት አይተናል። በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎቹ በሕዝብና በሽማግሌ ወላጆች ፊት ለፊት ተቀምጠው ጉልበታቸውን በማጠፍ ያሳዩት ብልግና እየኖሩባት ያለቺው አገር የምትከተለው ስነ ምግባር ውጭ ነው።

 

ወያኔ ባለፉት አርባ አምሰት ዓመታት የፈጠረውን አዲስ የትግራይ ማህበረሰብ አመለካከታቸውም ሆነ ስነ ምግባራቸው ጨርሶ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ መሆናችወ ያየንበት ሌላኛው አጋጣሚ ነው ። ይህ በአዲስ የፋሽስት አስተሳሰብ የተቀረጸው አዲስዩ የትግራይ ማህበረሰብ በርካታ አባሎ እንደ ሰው የሚገልጻቸውን በጥልቅ የማሰብና የማመዛዘን ክህሎት እንዳጡ ያሳየናል። ብዙዎቹ በትግራይ የኪነት ሰዎች የሚዘፈኑና የሚተወኑ ትወናዎች በተለይ ደግሞ ዘፈኖቻቸው ስናደምጣቸው በአክራሪ ብሄረተኛነት የተለከፉ ያንድ ጎሳ አባሎች ህሊናቸውን ስተው አዙሮ ማየትና ራሳቸውን መመልከት እንደተሳናቸው በተለያ ጊዜ ገልጸናል

 

 ይህ የህሊና መታወር በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩትን የትግራይ ማህበረሰብ አባሎች ባንድ መሪ ድርጅት፤ ባንድ ባለ “ራእይ መሪ” እየተመሩ በጭፍን ወደ ገደል እንዲገቡ ያደርጋል። የጣሊያን ፋሽስቶች “ጣሊያናዊ መሆን ማለት ፋሽስት መሆን ነው፤ ፋሽስት መሆን ደግሞ ሙሉ ሰው መሆን ነው” የሚል መፈክር ነበራቸው።ይህ ዛሬ ወያኔዎች “ወያኔ ማለት ትግራይ ማለት ነው፤ ትግራይ ማለት ደግሞ የክብር፤ የሞገስ፤ የጀግንነት፤ የአዋቂነት ወዘተ ምልክት ነው” እያሉ ከሚኩራሩበት መፈክራቸው ጋር ይመሰላል። (ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ አምስተርዳም ኗሪ)

 

ሰሞኑን የታዘብናቸው የሕሊና መታወር ምልክቶቻቸውን እንመልከት

1) ኤሊያስ ታደሰ (ተዋናይ)

2) ሰላም ተስፋይ (ተዋናይት)

3) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን የተመረቁ የግራይ ተወላጆች፤ (በቁጥር 9)

 

ኤሊያስ ታደሰ፡

ኤልያስ  የተባለ ወጣት ዘፋኝ ይሁን ተዋናይ በቅጡ ባላወቀውም ከዜናው ተዋናይ እንደሆነ ተረድቻለሁ።  እንደ ዜናው መሰረት “ጉማ” በመባል የሚታወቀው አጭር ፊልም በተዋናይነት በአበራታች መርሃ ግብር ሽልማት ሲበረከትለት ለአመስጋኞቹ እና ትግርኛ ማድመጥ ለማይችል ከመቶ ሚሊዮን በላይ የያዘ የኢትዮጵያ የራዲዮና የቴ/ቪዥን ተመልካች ሕዝብ ንቀቱን ለመግለጽ በትግርኛ የተናገረውን ንግግር ላስነብባችሁ። (ከስር የአማርኛ ትርጉሙን ይመልከቱ)

 

ትግርኛ

" ኣደይ ደም እናነብዐት፣ ሓወይ ተቐቲሉ ናብ ገደል እናተወርወረ፣ ሓፍተይ እናተደፈረት በዚ ሽልማት እዙይ ክሕጎስ ኣይክእልን። ዓደይ ናብቲ እነበረቶ ክብራ ክትምለስ ከላ ክሕጎስ እየ:: (ኤልያስ ታደሰ)

አማርኛ፦

"እናቴ ደም ዕምባ እያለቀሰች ወንድሜ ተረሽኖ  ከገደል አፋፍ ላይ እየተገፈተረ ክብርዋን የጠበቀች እህቴ በቆሻሾች እየተደፈረች በዚ ሽልማት ልደሰት አልችልም። የእናቴ እንባ ሲታበስ  ሃገሬ ወደ ነበረ ክብሯ ስትመለስ ደስተኛ እሆናለሁ እደርስበታለው። ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን።" (ኤልያስ ታደሰ - ጉማ በተሰኘ አጭር ሲኔማ ተሸላሚ)

 

ይህ ወጣት የተጋበዘበት መድረክ ለመቶ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያ ሕዝብ በመገናኛ ዘዴ ሚተላለፍ መድረክ ነው። እየተኮላተፈም ቢሆን አማርኛ እንጂ ትግርኛ የሚችል አድማጭ ከ104 ሚሊዮን ሕዝብ ምናልባት 4 ሚሊዮን ትግርኛ ተናጋሪ የትግራይ ሕዝብ ብቻ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። ታድያ የመልእክቱ እውነታ ከላይ እንደተተረጎመው ከሆነ ልጁ በሽፋን ሰበብ ተጠቅሞ እንደ አስተማሪዎቹ ለአማርኛና ለአማራ ያለው ጥላቻ ለመግለጽ ‘ሆን ብሎ’ ከቤቱ ተመክሮ አመካክሮ ተዘጋጅቶበት የመጣ ክፋት ነው።

 

አገሬ ክብሯ ሲመለስ” ብሎ ሲል “ስለ የትኛዋ አገሩ ነው ክብርዋ ሲመለስ እያለ ያለው? ኢትዮጵያን ማለቱ ከሆነ 27+3 በጠቅላላ 30 አመት በወያኔና በኦሮሙማው ኦነግ/ብልጽግና የነበረው ክብሯ ተነጥቆ የውርደት ውርደት ማቅ ከለበሰች ከወጣቱ ዕድሜ በላይ አስቆጥራለች። 27 አመትስ አንገቱ ላይ ወያኔ እና ሻዕቢያ “ኩሹኽ” ብለው የሚጠሩት አፋሮች ወገባቸው በታች የመያገለድሙት ወያኔ ግን ለብርድና የሽምቅ ተዋጊነት ማሳያ የሚጠቀምበት ስስ የአንገት “ጨርቅ” ጠምጥሞ በዩቱብ ላይ መታየቱ ስለቀረበት ነበር ያንን እንደ ክብር የቆጠረው?

 

የሚገርመው ነገር፤ ይህ አሰመሳይ ተዋናይ በተበረከተለት ሽልማት ‘ልደሰት አልችልም’ ካለ የተቀበለው ሽልማት ለምን አልቀበልም ብሎ ልክ እንደ አመሳያው ‘ሰለማዊት ተስፋይ’ እቤቱ ቁጭ አይለም ነበር? ያቺ ዋንጫም አጓጓቺው፤ ያቺ ለአማርኛ ያለው ጥላቻውም ለመግለጽ ደግሞ ዕድል እንዳታመልጠው ምቹ መድረክ አገኛና መጥቶ ተጠቀመባት። አዲስ አባባ መኖር እንዴት አራዳነት ያስተምራል አንባቢ ሆይ!? ያውም እኮ ወዳጄ ይነጋል በላቸው ባንድ ወቅት እንደጻፈው (እኔም በመጽሐፌ እንደጠቀስኩት) “ክርስቶስ፤- ‘ሁለት ባላችሁበት ሦስተኛ እኔ አለሁ’ እንዳለው አዲስ አበባ አሥር ሰው ካየህ ያለ ማጋነን ሦስትና አራቱ ትግሬዎች ናቸው፡፡” ያለውን ሳስታውስ ‘ኤሊያስ ታደሰም’ ዋንጫውን ወደ ኪሱ አስገባና በዚያው ለውጥ ትግርኛን በድምጽ ማጉያው አንቆረቆረላቸው። ከዚህ የበለጠ አራዳነት የት ይገኛል!?

 

ሰላም ተስፋይ


ጥንት የጎንደር ክ/ሃገር የነበረው የሑመራ/ወልቃይቴ ትውልድ አላት የሚሏት ሓረር የተወለደች በተዋናይነት አውቅና አላት የምትባል “በወቅቱ አጠራር” “የጁንታው አወዳሽ” የሆነች ሌላዋ ጉደኛ ሴት ነች። የዚች ልጅ ውሸት ልዩ ታርጋ ተለጥፎላታል። የውሸት መረጃ ካሰራጨቺው አንዱ ከብዙ አማታት በፊት በባድመ ጦርነት ጊዜ የፈረሰ ያውም ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ የተባለ አንድ የፈራረሰ ቤተክርሰትያን ህንጻ የኢትዮጵያ ወታደሮች አፈረሱት ብላ አምሰት መቶ ሺሕ ተከታይ ያላት የሚባልላት ‘ኢንስታግራምዋ፤ ላይ በመልቀቅ የሃሰት ዜና በማሰራጨትዋ ብዙ ሰው ሲጮህባት ፎቶውን አንስታዋለች። ፎቶግራፉ ብታነሳውም፤ ይቅርታ ግን አልጠየቀቺም። ለምን አትበሉ?” በትዕቢት የተወጠረ የወያነ ጀሌ የይቅርታ ትርጉም አያውቅም። ያልተማረቺው ከየት ታምጣው?

 ዛሬ ደግሞ እንዲህ ትላለች፤

 "ሕዝቤ በጠላት አሰቃቂ ጭፍጨፋ አስገድዶ መድፈር ዘረፋና ውድመት እየደረሰበት እኔ ልደሰት አልችልም።" በማለት ከተዘጋጀላት ትልቅ የእውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ላይ እንደማትሳተፍ እቤትዋ የተቀመጠች ተዋናይ ነች

 

3) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን የተመረቁ የግራይ ተወላጆች፤


ወያኔ የገጠመው የገዛ እራሳቸው መዝሙሩን መስማትካስጠላቸው (የገዛ እራሳቸው መዝሙሩ ስለጠሉት ግን አይደለም) ያም ቢሆን በምትኩ ለሕዝብ ክብር ሲሉ የሕሊና ፀሎት እንዲያደርጉና ሕዝቡ አብሮ እንዲጸልይ ጥያቄ በማድረግ ቅሬታቸውን ማስሰማት ሲችሉ ጭራሽኑ በበልግና እገራቸውን ወደ ጉልበታቸው አጥፈው የንቀታቸውና የብልግናቸው መጠን ለማሳየት ሩቅ ተሻግረዋል። አንድ ምሁር በአገሬው በሽማግሌዎችና በወላጆች ፊት አስጸያፊና ነውር ከተገቢና ከደምብ ለይቶ ካላወቀ ምን ትምህርት ተምረው እንደተመረቁ አላውቅም። የትግራይ ሕዝብ ግፍ ተፈጽሞበታል ካሉ ለትግራይ ሕዝብ የሕሊና ጸሎት እንዲደረግ ለምን መጠየቅ አልቻሉም? ስላልተማሩ ወይንስ የፖለቲካ ተልእኮ ስላላቸው? ለመሆኑ ላቡን አንጠፍጥፎ ግብር ከፍሎ ያስተማራቸው ሕዝብ ፊት ተቀምጠው ጉልበት አጥኦ ንቀት ማሳይት ምን እሚሉት ፖለቲካ ነው?

 

የኮካ ኮላው ትውልዶች፤

 

እነኚህ ወጣቶች ወያኔ ከተፈጠረ ወዲህ በቅርብ ጊዜ የተወለዱ በወያኔ ሥርዓተ ትምህርት ተኮትኩተው ያደጉ፤ “ወጋሕ ትበል ለይቲ” (ሌሊቱ እስኪነጋ) በመባል የሚታወቀው የወያኔ “ቶክሲክ” (መርዛማ) ዘፈኖችን እየተዘፈነላቸው በየዳንስ ቤቱና በዓላት ዳንኪራ ሲመቱ ሌሊት ሙሉ እልልታ ሲያቀልጡ እራሳቸውን አመርቅነው ሌላውን የሚያሳብዱ ዳንኪራ አስመቺና ዳንኪራ መቺ ሆነው “ኢትዮጵያን እንዲጠሉ” ተደርገው የተቀረጹ በጣፋጭ መጠጥና ምግብ አቀናጥቶ ወያኔ በልኩ መጥኖ የቀረጻቸው አዲስ አባባ ከተማ ያደጉ የኮካ ኮላ ዘመን ቅምጥል ትውልዶች ናቸው።

 

አየደረሰበት ስላለው ስለ ኢትዮጵያዊው ግፍስ ከመናገር ሆድ ይፍጀው እንበልና ፤ የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ ንብረቱ ያልተነጠቀ፤ ያልተደፈረ፤ያልተጨፈጨፈ፤ያልታሰረና ያልተደበደበ አስመስለው እኔ እና መሰሎቼ ወደ ትውልድ አገራችን እንዳንገባ አግደውን ፤ ክብራችን ሲነጠቅ አይተው እንዳላዩ “ሲጨፍሩ” የነበሩ ዛሬ ከ27 አመት በሗላ ወያኔ “በራሱ ጅራፍ ሲገረፍ” በማየታቸው ልባቸው ተሰብሮ ማዘናቸው እንጂ ስለ የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ ወያኔን እንዴት ነፃ ሊያደርጉት ይቻላቸዋል?

 

በስልኮቻቸው ፣ በኮምፒዩተሮቻቸው ፣ በአይፓዶቻቸው በትግራዋይነት ሰንሰለት የታሰሩ ያልተረጋጉ እነዚህ የኮካ ኮላ ትውልዶች የኢትዮጵያን ሰንደቅአላማና ብሔራዊ መዝሙር (ብሔራዊ መዝሙሩም ወያኔ የገጠመው ቢሆንም) ‘አናውለበልብም፤አንቆምም፤አንነሳም’ የሚሉ የወያኔ ጫጩቶች መሆናቸው እንዴት ልንስታቸው ይቻለናል?  ኢትዮጵያ ምድር ያውም አዲስ አበባ ውስጥ እየኖሩ “ኢትዮጵያ አይደለም” የሚሉ የባይቶና ፓርቲ “ዕብዶች እኮ መረን የጣሰው ድፍረታቸውን እኮ በቴ/ቪዥን ድምጠናል።

ስለ ሰንቱ ደፋር የፋሺሰት ጫጩቶች ብለን እናውጋው! ዕድሜ ለአብይ አሕመድ፤ አንኳን “ትግራዋይ” እንጂ “ኢትዮጵያ እኔን አትመጥነኝም አትወክለኝም” ማለት የሰው ልጅ ማረድም የሰው ልጅ ገድሎም  የሰው ሥጋ መብላት ጭምር የዲሞክራሲ አንዱ መገለጫ ነው ብሎን የለ!? አበይ አሕመድ የነገርን እኮ---እነዚህም እስራል አገር አንዳሉት ዓረብ ነን የሚሉ አንዳንድ የእስራሎቹ አክራሪ የክነሴት የፓርላማ አባለት “ጥግ” እንዲቀመጡ አዲስ አበባ ፓርላማም ወንበር ተፈቅዶላቸው የሰው ስጋ መብላት “መብት ነው” ለማትም መብታቸው ነውና እፈቅድላቸዋለሁ፤ሃሳብ አይታገደም ብሎናል እኮ “አስራለቃ አብይ አሕመድ”?

 

እነዚህ ወጣቶች ባለፉት ዕድሜአቸው ውስጥ (27) አመት በሚያወድሱት በወያነ ስርዓት እና 3 አመት ‘በኦሮሙማው የአብይ አሕመድ ኦነጋዊ ሥርዓት’ በአማራ ማሕበረሰብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ ሲፈጸም እንደ ምሁር ወጣትነታቸውም ሆነ እንደ የኪነት አባልነታቸው አያውቁም ነበር ብሎ የሚከራከር ፍጡር አይኖርም። ታዲያ እንደዛሬው ለትግራይ እንደተቆረቆሩት ሁሉ ለምን ያኔ አማራና ሌሎች ነገዶች ስቃይ ሲፈጸምባቸው አልከነከናቸውም ነበር? የሚል ነው ሕዝቡ እየጠየቃቸው ያለው። እነሱም ሆኑ ሌሎቻችን የማንክደው ምክንያታቸው “በሕዝብ ጀርባ” “ለወያኔ” ማልቀስ ስለፈለጉ ነው።

 አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከሰንደቃላማችን ጋር ጸብ ነበረው፤ ዛሬም “የመለስ ጫጩቶች” ፀባቸው ከሰንደቃላማችን ጋር ነው።45 አመት የተረጨውመርዝ” ለማጽዳት ሌላ 45 አመት የህሊና አጠባ ሊፈጅ ነው። ፈረንጆች ንደሚሉት It’s a cycle that goes on and on የበሽታው አገርሺነት  እየቀጠለ የሚሄድ ዑደት ነው። የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ተነስቶ ይጥላል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው እያልን ለማስረዳት ስንደክም የነበረውም ይህ ክስተት እንደሚከሰት ስለምናውቅ ነው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Tuesday, March 30, 2021

ንጉሠ ነገሥት አብይ አሕመድ ዓሊ ስለ በዓለ ሢመቱ ትንሽ ወግ... አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) Ethio Semay 3/30/21

 

 

ንጉሠ ነገሥት አብይ አሕመድ ዓሊ 

ስለ በዓለ ሢመቱ ትንሽ ወግ...

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) 

Ethio Semay

3/30/21


Photo Ethio Semay

ከኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ ማስታወሻ፡

ጸሐፊው አምባቸው ደጀኔ በዚህ ግሩም ጽሑፉ ላይ “ይልማ በቀለ” ስለሚባል “ተሳላሚ” ለበርካታ አመታት የሚሰነዝራቸው አስተያየቶች ስቃወመው የነበረ ሰው ነው። ዛሬ አምባቸው ደጀኔ ስለዚህ ማፈሪያ ሰው አብይ አሕመድን አስመልክቶ “በእንግሊዝኛ” የጻፈው አሽቃባጭነቱን ያሳየበት ጥቅስ ስመለከት “ይልማ” ዛሬም “አድሮ ጥጃ” ሆኖ ሳየው ገረመኝ። “ይልማ በቀለ” የወያኔን ፋሺስታዊ ሕገመንግሥት አክባሪ አለቃው ኮ/ል አብይ አሕመድን ለማሞገስ የሄደበት ርቀት በሦስት አመት የታየው እልቂት እና ዋይታ፤ “የሰው ስጋ የሚበላባት” “ምጽአተ ኢትዮጵያን” ወደ “ውብ አበባነት ተለውጣለች” ሲለን እጅግ አስደንጋጭ ብቻ ሳይሆን cognitive dissonance በተባለው የግንዛቤ ቀውስ በተው የሕዝቡን ዋይታ “እልልታ” ሆኖ የሚሰማቸው ለሕክምና የሚያቃስቱ የውይ ምሁራኖች ድምፅ ነው።  3/30/21

 

ዶክተር አቢይ አመድ የ3ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ሊያከብር ጉድ ጉዱ መጧጧፉን በሚዲያ እየሰማን ነው፡፡ አሳፋሪ ነው፡፡ አሳፋሪነቱን ማስረዳት እችላለሁ፡፡ የዚህ ሰውዬ ነገር እጅጉን የሚደንቅ ነው፡፡ የከበቡትም አሻንጉሊቶች እንጂ ሰዎች አይመስሉኝም፡፡

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

በ Ethio Semay የተለጠፈ

“በባዳ ቢቆጡ በጨለማ ቢያፈጡ” (ዋጋ የለውም) ቢባልም የተሰማኝን እንደልማዴ እጮሃለሁ፡፡ ቢያንስ ተናግሬው ይውጣልኝ፡፡ እንደጠባብ ዕድል ሆኖ ለነገ አዳሪ ከሆንኩም “እኔም ባቅሜ እንዲህ ብዬ ነበር” ብሎ ለመጎረር ያመቸኛል፡፡ እንግዲያማ ተናጋሪ እንጂ አድማጭ በጠፋበት ወቅት ይህን ያህል መድከም አስፈላጊ ሆኖ አልነበረም፡፡ ጊዜው ይታወቃል፡፡ የዘመኑ ምንነት ግልጽ ነው፡፡ 

 

በዓለ ሢመት ሲከበር የማውቀው የንጉሦች፣ የፓትርያርኮችና መሰል የሥልጣንና የሹመት ሰዎችን ነው - ሥልጣናቸው ዕድሜ ይፍታህ የሆነ ግለሰቦች፡፡ ኢትዮጵያን በመሰለች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለዓለም በማስተማር ላይ በምትገኝ ሀገር በምርጫ ሥልጣን ላይ የወጣ ጠ/ሚኒስትር ግን በዓለ ሢመት ሲያከበር ማየት አልተለመደም፡፡ የቀደሙት ፍጹማን ዴሞክራሲያዊያን መሪዎቻችን ለምሣሌ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ከነሙሉ ክብሩ፣ ግርማ ሞገሱና ጥቅሙ እንዲሁም የአዛዥ ናዛዥ የሥራ ኃላፊነቱ ጭምር እርሳቸውን ተክተው የነበሩት ጠ/ሚኒስትር ደሳለኝ ኃ/ማርያም (ሣቄ ሊያመልጠኝ ነው እናንተዬ ኧረ እባካችሁን ጸልዩልኝ!) አዎ፣ እነዚህን መሰል የዴሞክራሲ ፋና ወጊ መሪዎቻችን እንኳን በዓለ ሢመታቸውን ለማክበር አልደፈሩም - ምንም እንኳ እናቶቻቸው መሪዎቻችን እንደሚነግሡ የንግሥና ተራ ቁጥራቸውን ሳይቀር ጠቅሰው ቀድመው ባይተነብዩላቸውም፡፡ አቢቹ የማያሳየኝ ተዓምር ላይኖር ነው፡፡ ይህ ሰው በ16 ዓመቱ የዶክትሬት ዲግሪውን ይዞ በ17 ዓመቱ የሞተውን አንድ የከውካዋ ሕይወት ሰለባ ታዳጊ ወጣትን ታሪክ ያስታውሰኛል፡፡ ሲያሳዝን!

 

እውነትን ለመናገር ለይስሙላም ይሁን ከእውነት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተመረጠ የተባለ የአንድ ሀገር መሪ ይህን መሰል ቅሌት ውስጥ አይገባም፡፡ አንዱም የአሜሪካ መሪ ሥልጣን የያዘበትን ቀን በቤቱ ውስጥ ከሆነ እንጂ በጀት መድቦና ሕዝብን በግዴታ አሰልፎ በአደባባይ ሲያከብር አላየሁም፤ አልሰማሁምም፡፡ ይህን የጠ/ሚኒስትር አቢይን በዓለ ሢመት ለየት የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እናንተም መርምሩና ድረሱባቸው፡፡ ዐፄ አቢይ አመድ በዓለ ሢመታቸው በበርካታ ንጹሓን አማሮች ዕርድ መታጀቡን ታዲያ በቀዳሚነት እንድታስቡ ይሁን፡፡ አቢይ የነካው ተክል ሁሉ በፍጥነት እንደሚደርቅም ትዝ ይበላችሁ፡፡ ከዚህ በላይ ብጨምር የናንተን የማስታወስ ችሎታ እንደመናቅ ይቆጠርብኛል፡፡

 

ለስሙ አማካሪዎች አሉ፡፡ እነዳንኤል ክብረት እዚያ ቁጭ ብለው ይህንን እንኳን “ኧረ ጌታየ ይህስ እኛንም ጭምር ያዋርደናል ይተውት! መንግሥቱ ኃ/ማርያም እንኳን ነፍስ አውቆ ያላደረገውን ነገር እርስዎ ሲያደርጉት ሕዝብን ብንንቀው ሌላው ዓለም እኮ ይታዘበናል፤ ጥርሱን በዘነዘና ተወቅሮ ነው የሚስቅብን ጌታየ” ማለት ነበረባቸው፡፡ ሰው ጤፉ አቢይ ባይሰማቸውም አሁንም ይሞክሩ፡፡

 

ሌላ ጉዳይ ላውራ፡፡ ኪራይ ቤቶች ከዘበኛ እስከ ዋና ማጂነር አክራሪ ኦሮሞ ነው አሉ የወረሰው - የይስሙላውን የመጣያ ዓይነት ሹመት ትተን፡፡ በዚያም ምክንያት የኪራይ ቤቶች ንብረት የሆኑ የመንግሥት ቤቶች ለኦሮሞ ሀብታሞች ባወጡ እየተቸበቸቡ ነው፡፡ ድንቁ ደያስ የተባለው የዲግሪ ወፍጮ ባለቤት ከኪራይ ቤቶች የወሰደውን አንድ ቤት እንዴት አድርጎ እንዳሳመረው ራሴ አይቻለሁ፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋ እንዳለች በቄሮ ቅርጫ እንደጉንዳን ተወርራለች፡፡ አሁን ያልከበረ ኦሮሞ መቼም አይከብርም የተባለ ይመስላል፡፡

 

አዲስ አበባ አሥር የትራፊክ ፖሊሶችን ሰብሰብ ብለው ካየህ አሥሩም ኦሮሞ ለመሆናቸው ብዙም አትጠራጠር፡፡ አሥር የመንገድ ላይ ፖሊሶችን ካየህ ቢያንስ ዘጠኙ ኦሮሞ ስለመሆናቸው ጥርጣሬ አይግባህ፡፡ አሥር የአሥር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ታላላቅና ወሳኝ ባለሥልጣናት ሰብሰብ ብለው ቡና ሲጠጡ ብታይ አሥሩም ኦሮሞ መሆናቸውን ለማወቅ ማንንም መጠየቅ አይጠበቅብህም፡፡ የአሥራ ምናምኑን ክፍለ ከተማ ዋና ዋና ባለሥልጣናት ብታይ ከኦሮሞ ውጭ አይሆኑም፤ ወረዳና ቀበሌዎችንማ ተዋቸው፡፡ የመከላከያን አሥር ዋና ዋና ባለሥልጣናት ድንገት ሻይ ሲጠጡ ብታይ ከኦሮምኛ ውጪ ሲናገሩ የመስማት ዕድል የለህም፡፡ ወያኔ ሞትኩ አትበል፤ ዐይኗን ባይኗ አይታና ራሷን ተክታ ነው ፍግም ያለችው፡፡ እነዚህም እንደፈጣሪያቸው ፍግም እስኪሉ ጉድ እያሳዩን ነው፡፡ ምን አለፋህ አቢይ እላይ ሆኖ “ኢትዮጵያ የጋራ ናት” ይልሃል ከሥር ግን በእርሱ ዕውቅናና ሽፋን ሰጪነት ለአንድ የቀን ጅብ ተሰጥተን የትህነግን ዘመን እየናፈቅን ነው፡፡ “ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይመሰገንም” የሚባለው እውነት ነው፡፡ “በይሉኝታቢስነት ከወያኔ የሚበልጥ የለም” በሚል ብዙ ጊዜ እከራከርና እጽፍም ነበር፡፡ “የባሰ አለ አገርህን አትልቀቅ” ነው ወንድሜ፡፡ እነዚህ ብሰው ቁጭ አሉ - ኖቤል ከሚያሸልም የጅልነት ጭካኔ ጋር፡፡ እንዴ! ወያኔዎች እኮ ብልጥ ነበሩ - ማስመሰልን ይችሉበት ነበር፤ በተለይ ከ97 ምርጫ በፊት፡፡ ይበልጥ የተግማሙት ከ97 በኋላ ነበር፡፡ አሁን የምናየው ይህ ሁሉ የአንድ ነገድ የበላይነት የተፈጠረው ባጋጣሚ ቢሆን ምንም አይደለም፤ በሥራ ችሎታና በብቃት ቢሆን ምንም አይደለም፤ ሌላው ያልተማረና ብቁ ሆኖ ባለመገኘቱ ቢሆን ምንም አይደለም ... ግን ያ አይደለም፡፡ “ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡” 

 

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እንድትሆን በርግጥም መፍረስ አለባት፡፡ መፍረስ ሲባል ደግሞ አካላዊ መፍረስ አይደለም፡፡ አእምሯችን ፈርሶ ከእንደገና መሠራት ይኖርበታል፡፡ ለምሣሌ ዶክተር አሸብርን የመሰለ እምብርት የለሽ ሰው ይዘህ አገር ልትፈጥር አትችልም፡፡ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሀኪም ይንቀለኝ ብሎ የገገመው ይህ ሰውና መሰሎቹ ምን እንደሚሠሩ እናውቃለን፡፡ የኮሚቴ ሊቀ መንበርነታቸውን ለግል ቢዝነሳቸው ለመጠቀም ሲሉ የማይሠሩት ሸርና ተንኮል እንዲሁም ከባለሥልጣናት ጋር የጥቅም መሞዳሞድ የለም፡፡ በሚሊዮኖች ምናልባትም ከዚያም በበለጠ የሚቆጠር ገንዘብ አላቸው፡፡ ግን እምብርት ብሎ ነገር ስላልፈጠረባቸው በቃኝን አያውቁም፡፡ ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ የሀገራችን ነጋዴዎችና ባለሥልጣናት እንደዚህ ናቸው - የቀን ጅቦች፡፡ እነዚህ ፈርሰው ካልተሰሩ ሀገር አትኖረንም፡፡ አንድ ሰው በቃኝን ካላወቀ ደግሞ ሀገርንና ሕዝብን ተወውና ሚስቱንም ልጁንም አባትና እናቱንም ከመሸጥ ወይም ለዲያብሎስ ጭዳነት ከመገበር አይመለስም፡፡ የሚታየው ግድያና የዘር ዕልቂት ሁሉ መባቀያው እንግዲህ ይሄው ነው - ሆድና የሆድ መዘዝ፡፡ ሌላውና በየፖለቲከኛው አንደበት የሚተረከው ሁሉ ማስመሰያ ነው፡፡ እንጂ ህዝብማ ዱሮም ሆነ አሁን አብሮ እየኖረ ነው፤ ወደፊትም አብሮ መኖሩን ይቀጥላል፡፡

 

ግን ግን እባካችሁን የነገ ሰዎች አንድ ነገር ላሳስባችሁ፡፡ ሀገር ሲኖረን የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ አዲስ መሥፈርት ይውጣ፡፡ ድሃ ወደ ሥልጣን አይምጣ፡፡ ድሃ ድህነቱን እንጂ እምነቱን አያስብም፡፡ ክብረቱን እንጂ የሥራውን እንከን አያይም፡፡ ገንዘብ እያሳዩ ገደል የሚከቱት ይበዛሉ፡፡ ያኔ አገርና ሕዝብም አብረው ገደል ይገባሉ፡፡ ድህነት ይሉኝታን ያጠፋል፤ ማጣት ሀፍረትን ያሸጣል፡፡ የሰውን እጅ ማየት ኅሊናን ያሣውራል፡፡ ሀብት የማግኘት ጉጉት የሥራ ኃላፊነትን ያስረሳል፡፡ ስለዚህ ሥልጣን የሚይዝ ሰው በዕውቀትም በትምህርትም በሀብትም የተደላደለ ቢሆን ሀገር ትረጋጋለች፤ ፍትህ ትነግሣለች፡፡ ከሌሎች ሀገራትም እንማር፡፡ በበርካታ አገሮች ማንም ነጫጭባ ድሃ ከመሬትም በለው ከቆጥ አልጋ እየተነሳ ሥልጣን ላይ ፊጥ አይልም - ህግና ሥርዓት አለው፡፡ እንደኛ ሀገር በተገዛ ወይ በተጭበረበረ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ልባስ ምድረ ማይም ሥልጣን ላይ እየወጣ “we supporting they equivocally” በሚል “is”ን እና  “was”ን በቅጡ ባልለዬ እንግሊዝኛው የድንቁርና በጠጡን ሕዝብ ላይ አያራግፍም - ሰምታችኋል!! እንደሕዝብም እንደሀገርም በቁማችን እኮ ሞተናል፡፡ የባለሥልጣናትን የአመራር “ብቃት”ና ሀብትና ንብረት የማከማቸት ስግብግበነት ሳይ በኢትዮጵያዊነቴ አፍራለሁ፡፡

 

 አሁን በዚህን ዘመን ሙስና ውስጥ የማይገባ ሰው ዕብድ ወይም ወፈፌ ነው - እንደጤነኛ አይቆጠርም፡፡ ለነገሩ ለትራንስፖርትም የማይበቃ ወርኃዊ ደሞዝ እየተከፈለው አትሞስን ማለትም በሰው ኅልውና መፍረድ ነው - ችግር እኮ ነው ጎበዝ፡፡ የአምስት ሊትር የምግብ ዘይት ዋጋና የአንድ ሻይ ቤት አስተናጋጅ ወርኃዊ ደሞዝ ተመሳሳይ መሆኑን ስንቶቻን እንደምናውቅ አላውቅም፡፡ የአንዲት ሚጢጢዬ ክፍል የወር ኪራይ 2000 ብር ሆኖ ሳለ ለአንድ የቢኤ ዲግሪ ምሩቅ ብር 3000 የሚመድብ ሲቪል ሰርቪስ ያቋቋመ መንግሥት ያለን የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሥልጡናን እኮ ነን እኛ ኢትዮጵያውያን፡፡ የሚገርመው ባለሥልጣናት በስርቆትና በሙስና እንጂ በደሞዝ ስለማይኖሩ ይህ የሕዝብ ችግር አይገባቸውም፡፡ ፈርዶብን!

 

ምርጫ የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ካለም በደም የጨቀዬ ይሆናል፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ መጥፊያው ደርሷል፡፡ ኢትዮጵያ መነሳቷ እርግጥ ነው፡፡ ... ይልማ በቀለ የሚባለው ጉደኛ ፍጡር የሚያመልከው አቢይ አመድና መንግሥቱ ዕድሜያቸው እያለቀ ነው፡፡ ብዙ ነገር ለማየት፣ ብዙ ለማልቀስ፣ ብዙ ስቃይ ለመቀበል .... እንዘጋጅ፡፡ “የማን ሟርተኛ ነው” ደግሞ አትበል፡፡ አንተም የምታውቀውን ወይም ልታውቀው የማትፈልገውን ነው የነገርኩህ፡፡ ያለንበት ጊዜ “ዝም በል የኔን እግር እየበላ ነው” ከሚባልበት ደረጃም አልፏል፡፡  በቃኝ፡፡

 

 

ከፍ ሲል የጠቀስኩት የአቢይ አመድ አሽቃባጭ (አሽቋላጭ የሚለው ቃል ሲያስጠላኝ!) ሰሞኑን ስለአቢይ መልኣክነት በዘሀበሻ ድረገጽ ላይ ከጻፈው የሚከተለውን ሳልጋብዝ ላለማለፍ ለራሴ ቃል አለብኝና እባካችሁን ኮምኩሙልኝ፡፡ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነቱን ሆዳም ወይንም በሆዳምነት የማይታማ ከሆነም የሕዝብንና የሀገርን ተጨባጭ ኹነት ሊረዳ የማይችል ፍርደ ገምድል ገልቱ ዜጋም ፈጥራለች፡፡ አዝናለሁ፡

“We are blessed to have a fair and gracious foreman during this transition from chaos to order. The last three difficult years, Dr. Abiy Ahmed has proven he is a born leader. No one would have predicted such a beautiful flower to bloom from Woyane’s toxic garden.”  

“The sun is rising over Ethiopia.” (Yilma Bekele)

 

ልተርጉመው ይሆን? እስኪ ልሞክረው፡-

“ከዚህ ካለንበት ሥርዓት አልበኝነት ወደ ሥርዓታዊ ሀገራዊ ኑባሬ ሊያሸጋግረን የሚችል ዶክተር አቢይን የመሰለ ፍትኅ ዐዋቂና ግርማ ሞገሱ የሚያርድ አሻጋሪ ማግኘታችን በውነቱ መባረክ ነው፡፡ ያለፉት ሦስት አስቸጋሪ ዓመታት ዶክተር አቢይ ሙሤያዊ አሻጋሪነቱን አረጋግጠውልናል፡፡ እንዲህ ዓይነት በውብ አበባ ሊመሰል የሚችል ድንቅ ዜጋ በወያኔ መርዛማ ማሕጸን ውስጥ ሊፈጠር ይችላል ብሎ ቀድሞ የገመተ ሰው አልነበረም፡፡”

“በኢትዮጵያ ፀሐይ እየወጣች ነው” ይልማ በቀለ

Wednesday, March 24, 2021

የልጅነት ትውስታዎች እስከ ዛሬ ድረስ ያልተለያዩት የልጅነት ጓደኞች ኪዳነ እና ጌታቸው ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay 2/23/202

 

 

የልጅነት ትውስታዎች

እስከ ዛሬ ድረስ ያልተለያዩት የልጅነት ጓደኞች ኪዳነ እና ጌታቸው

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ

 Ethio Semay

2/23/2021


ስንወለድ እትብታችን ተቆርጦ የተቀበረው ከድንግል ጽዮን ማርያም አክሱም ከተማ አፈር ውስጥ ነው። ሁለታችን “ሀ” ብለን ትምሕርት መቁጠር እስከ ጀመርንባት ቀን ጀምሮ እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ አብረን መጥፎዉንም ደጉንም ተካፍለን፤ በሚያስቅ እየሳቅን በሚያጨቃጭቅ እየተጨቃጨቅን አሁንም አለን። ሊቃውንት እንደሚሉት እውነተኛ ጓደኞች ለማግኘት አስቸጋሪ ፣ ለመተው አስቸጋሪ እና ለመርሳት የማይቻሉ ናቸው፤ ይላሉ። እኔ እና ኪዳነ እንዲህ ነበርን።

ሁለታችንም በትምህርታችን ጎበዝ ተብለን ተለቅመን ከተመደብነው ክፍል አብረን ስንዘልቅ ከፍተኛ ውጤት ከሚያገኙት ጥቂት ትጉሃን ተማሪዎች ነበርን። ኪዳነ እኔን የሚበልጠኝ በሂሳብ ነበር። እርሱ በሂሳብ ትምህርት የታወቀ ሲሆን እኔ ደግሞ በተቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ከፍተኛ ውጤቶች አገኝ ነበር። በሂሳብ ጎበዝ ስለነበር ዛሬ በሚኖርበት አገር በከፍተኛ የመንግሥት ሥራ የኦዲቲንግ ሃላፊ ነው። በሂሳብ ደካማ ስለነበርኩ ኪዳኔ ያንን ማዕረግ ቀዳሚ ሆኖ ያገኝ ነበር። በተቀሩት በማገኛቸው በ90ናዎቹ እና 100 መቶዎቹ የትምህርት ውጤቶቼ ለሂሳብ ማለፊያ/መሸፈኛ/ ውጤት አደርጋቸው ስለበር፤ ኪዳነ ባጠቃላይ ውጤት ይበልጠኝ ነበር። ሆኖም አሉ ከሚባሉት ቀዳሚ ተማሪዎች ነበርን።

ኪዳነ በጣም እጅግ በጣም የምወደው አብሮ አደጌ ነው። ኪዳነ የት/ቤቱ እና የቤቱ ስም “ሽሻይ” በሚል ስም ሲጣራ በተፈጥሮው ጸብ የማይወድ፤ እጅግ ቀልደኛ ሳቂታና አዛኝ ነው። ከሰብኣዊ የሞራል መርሆ ከተዛነፍክ የሥጋ ዘመዱም ብትሆን ከመቃወም አይቆጠብም። በዚህ ባሕሪያችን ሁለታችን እንመሳሰላለን። ጸበኛ ስላልነበረ ሞገደኞች ወይን ከቅርብ ጓደኞቻችን ውስጥ ሊተናኮሉት ከሞከሩ ዘልየ እመሃል ለመደባደብ የሚቃጣኝ እኔ ነበርኩ።

ጸጋዘኣብ ደሞዘ፤ ፍጽስሃጽዮን ገሠሠ ኪዳነ እና እኔ አራታችን የማንለያይ፤የምንዋደድ አጅግ የቅርብ ጓደኞች ነበርን። የወቅቱ የክፍላችን ሴት ተማሪዎች ስለሚወዱኝ፤ ልጃገረዶች በመጥበስ እኔ አንደኛ ነበርኩ። ሲጃራ ማጨስ፤ መምህራችን ከገባበት ጠላ ቤት ወይንም ሻይ ቤት መግባትና መታየት ፤ልጃገርድ መጥበስ አክሱም ውስጥ እጅግ አስፈሪ እና ጥብቅ ስለሆነ ለሴቶች ፍቅረኞቻችን ፍቅራችንን የምንገልጸው በድብቅ እና አጅግ መገናኘት ካልተቻለም የፍቅር ግጥም እየገጠምን (አብረን በአንድ ክፍል እየዋልንም ቢሆን ‘እንደ ሰማይ ኮከብ የምትርቂኝና የምትናፊቂኝ’ እያልን የምንጽፍላቸውን ግጥም “በመሸፈኛ” ደብተራችን ከውስጥ አስገብተን ሰው ሳያየን በምስጢር ደብተሩን ለፍቅረኞቻችን በመስጠት) ፍቅራችንን እንገልጻለን። እኔ እና ኪዳነ የተፈጥሮ የሕይወት ጉዞና ግዴታ ሆኖ በተለያ  ሁኔታዎች መለያየት ኖርብን ተለያይትን ብዙ ኣመት ተነጣጥለንም ሳንነጣጠል አሁንም ማደጋችን የሚገርም ተፈጥሮ ነው።

ኪዳነ በሚመለከተው የፖለቲካ መነጽር ‘የወያኔ መስመር በመቃወሙ’ አብረውን ያደጉ አንዳንድ ጓደኞቻችን “ወያኔ የተባለ ነገዳዊ የፖለቲካ ሃይማኖት “ፋሺዝም መሆኑን” ሳይገባቸው የወያኔ አምላኪዎች ሆነው “እኛ የገነባት አገር እኛ ልናፈርሳት እንገደዳለን የሚለው የፋሺሰት ትግሬዎች ቅዠት” ጓደኛየን ኪዳነን ለመወረፍ ሲቃጣቸው እጅግ ይገርሙኛልም ያስቆጡኛልም።

እኛ የገነባት እኛ ልናፈርሳት እንገደዳለን የሚለው የፋሺሰት ወያነ ትግሬዎች ቅዠት ለሕዝባችን ስቃይ ምክንያት ናቸው። በታሪክ ያልሞከረውን ኢትዮጵያን የማፍረስ ቅዠት የትግራይ ህዝብ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ፍቅር ወድቆ የራሱን ነገድ ማንነትና ታላቅነት እንዲያመልክ ተደርጎ ለብዙ ሺህ ዘመናት አብሮ ከኖረው የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስነልቦናም ሆነ በእለታዊ ህይወቱና ማህበረሰባዊ ተራክቦው (social interaction) እየተለየ መጥቶአል። ዛሬ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ኢትዮጵያውያኖች በጋራ ከሚጋሩዋቸው ብሄራዊ እሴቶች በተቃራኒ የቆሙና ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ፤ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የተቃኙ ፋሽስታዊ እሴቶች ባለቤት በማድረግ ጨርሶ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ወጥቷል ማለት ይቻላል። የኪነጥበብ ስራዎች፤ ዘፈኖች፤ ትያትሮች፤ ፊልሞች ወዘተ የህዝብ መዝናኛዎች መሆናቸው ቀርቶ ጦረኝነትን፤ የትግራይን ሕዝብ የበላይነት፤ ምርጥነት፤ የንጹህ ዘር፤ የንጹህ ደም ባለቤትነት፤ ልዩና ወደር የሌለው የታሪክ ባለቤትነት፤ የሥልጣኔ ባለቤትነት፤ ጀግንነት፤ አዋቂነት፤ ወዘተ አጉልተው የሚያሳዩ ከማንም ፍጡር የተለየ የበላይነት ስሜት የሚያነጸባርቁ የግንጠላ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች በመጠቀም ከሰብኣዊ አስተሳሰብ አውጥተው ‘ራሺያል ሃይጂን” (ንጹህ ‘ዘረ መል’- “ክሊን ጂን”) የሚለው የናዚዎች አስተሳሰብ እንዲከተልና በነገዱና በአካባቢው ፍቅር እንዲወሰን አድርገውታል። አሁን ያለው ትውልድ ከናዚያዊ “የዘር ንጽሕና” አመለካከት ራሱ ነፃ ካላወጣ፤በዚህ ከቀጠለ ትግራይ እና አካባቢው የስቃይ የእሪታ የጦርነትና የእርዛት ቀጠና ሆና ትቀጥላለች።

የህ “ክፉ የፖለቲካ ሃይማኖት” ብዙዎቹ አብሮ አደግ ጓደኞቻችን እርስበርሳችን እንድንራራቅ መንገድ ከፍቷል። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ባለቸው የናዚ አምልኮ ምክንያት ስንለያይ እስካሁን ድረስ አብረን እንዳደግነው ዛሬም አብሮ ያልተለየኝ ጓደኛየ “ባለማስትሬት ዲግሪው” ምሩቅ የሆነው የሂሳብ ሊቁ ጓደኛየ እና ወንድሜ ኪዳነ አፈወርቂ እጅግ እያደነቅኩ ለወደፊቱ ስለ ልጅነታችን ያሳለፍናቸው አክሱማዊ “ካራክተሮች” “ባህላዊና ትምሕርታዊ” አዘል የሆነ “የልጅነት ትውስታችን” እንድ መጽሐፍ አብረን ለመጻፍ እያሰብን ነው።

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay አዘጋጅ

 

 

 


Monday, March 22, 2021

ክፍል 3 በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ ማኒፌስቶ 11 ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay March 22, 20213

 

ክፍል 3

በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ

ማኒፌስቶ 11

ትርጉም

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

March 22, 20213


ካለፈው ክፍል ሁለት የቀጠለ፤

ባለፈው ክፍል ሁለት እንደህ በሚል ክፍል ነበር በይደር የተውነው………  “የአጼ ዮሐንስ ሕልፈት በ19ነኛው ክ/ዘመን ማገባደጂያ የተፈጠረው ይህ የንጉሱ ሕልፈት ለኛ ለትግሬዎች “የዘመን መጠመዘዢያ ማኣዘን” (ተርኒንግ ፖይነት) ነበር።በዚህ አጋጣሚ እኛ በሕዝብ ብዛት በቁጥር የበላይነትን ይዘን ጂኦፖለቲካዊ የበላይነት ይዘን ማነጽ ልንችል የነበረቺውንና ለዓለማችን ፍላጎት የምትስማማ አገራችንን ከእጃችን ተነጥቀን ወደ ተንሳፈፈችና ጥገኛ ወደ ሆነቺው የአገር ትርጉም የሌላት አገር ለጠላቶቻችን የምትጥም ለኛ የማትጥም አገር የገባንበት የዘመን መጠምዘዣ መሆኑ ማሳያ ነበር በሚል ነበር ትርጉማችንን ያቆምነው። በዚህ ክፍል ትርጉም ሦስት እንዲህ ይቀጥላል፤

‘ትግርኛ ተናጋሪው ማሕበረሰብ ትግሬ እና ኤርትራ’ ቅኝ ገዢ በሚላቸው ጣለያን እና አማራው መንግሥት ትግራይ እና ኤርትራ በማለት ለሁለት ከፍለው ሃይላችንን ለማዳከም ያደረጉት ሴራ ጎድቶናል። ለሁለት መከፈላችንን ሳያንስ ወደ ኤርትራ የተካተተው ግማሹ ብሔራችን ከኛ ጋር የማይስማማና ከኛው ራዕይ ጋር የሚጋጭ ተጻራሪ ሃይሎች ሆነው እንዲፈጠሩ የፈቀደ ሁኔታ ነው። ሆኖም በሌላ በኩል ስንመለከተው ሁኔታው እኛ ትግሬዎች በቁጥር የማነሳችን እና ለሁለት በመከፈላችን ያህል ጠንካራ ሃይል እና ታሪካዊ ሃያል ሕዝብ ሆነን እንድንወጣ አድርጎናል። ዛሬ ኤርትራ ውስጥ ያለው ክፍል በባዕድ ሥር በመገዛቱ ምክንያት ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን የባዕድ ኣስተሳሰብ ባሕሪ ይዞ የሚጓዝ ስለሆነ በውስጡ አንድ ብሔራዊ ሃይል እንዲፈጠር ሁኔታው ስለፈቀደ፤ ተቆርጦ ወደ ኢትዮጵያ የተጠቃለለው ትግራይ ውስጥ ያለው ሃይልም በትግራዋይ ብሔረተኛ እና በኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ ለሁለት ተከፍሎ ያልነጠረና የተከፋፈለ ሃሳብ ይዞ እንዲጓዝ “የዘመን መጠመዘዢያ ማኣዘን” (ተርኒንግ ፖይነት) ብለን የጠራነው የዮሓንስ በሞት መለየት ለዚህ ክስተት ተጋልጧል።

በአፄ ዮሐንስ ህልፈት ምክንያት ተከትሎ የተከሰተው አስከፊው ሰበብ ተጋሩ/ትግሬዎች/ በአማራ አገዛዝ ሥር ወድቀን የራሳችንን የነጠረ ዓላማ ይዘን እንዳንጓዝ ጥገኛ ሆነን እንድንኖር በር ከፍቷል። የራስ መተማንነትን ተነጥቀን ከሥልጣኔ ጉዞ ታግደን ወደ ኋላ እንድንቀር አድርጎናል። ትግራይ ድሃ ነች ብለው የሕዝባችን የራስ መተማመን ለማደከም ሲሉ ከ100 አመት በላይ ጥቃት ሲከፍቱብን እኛም ተቀበልነው። በራሳችን የተፈጥሮ ፀጋና በታሪክ  የወረስነው ሥልጣኔ በጽናት መጠበቅ ሲኖርብንና ለተሻለ ሕልም ከማለም ይልቅ ወደዚያች ብዙሃን ደናቁርትና ያልሰለጠኑ ሕዝቦች ወደ ያዘች አገር ተቀላቅለን ልክ እንደ እነሱ ወደ እንሳሳ እርባታና ለም መሬት ወደ እሚያተኩር አድሃሪ የሆነ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ውስጥ ገባን። ባጠቃላይ ተገቢ ሥፍራችን የነበረው መገኘት የነበርንበትን የሥልጣኔ እርከን ወርደን ካልሰለጠኑት ሕዝቦች ጋር በመቀላቀላችን ወደ ተምበርካኪነት ሕልውና ተጋለጥን።

ያም ሆኖ ከአፄው ሕልፈት በኋላ ወደ አማራዎች አገር በሃይል እንድትዋጥ የተደረገቺው ትግራይ በወቅቱ ከነበሩት መሳፍንቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ብሔራዊ ልም የተሸከሙ ቢኖሩም እርስ በርስ ባለመናበባቸው ምክንያት በጠላትነት በመፈላለግ ግጭት ውስጥ እየገቡ ብሔራዊ ሕልማቸው ሊያሳኩ አልቻሉም። ለ100 አመታት ሲቀጥል የነበረው አሁን ዛሬ ነጥሮ የመጣብን  አደጋ በወቅቱ ሊረዱት ስላልቻሉ ወይንም “ኢትዮጵያ-አገራችን” ወደ እሚሉት የተሳሳተ ብሔራዊ አስተሳሰብ ሰለባ ስለነበሩ ፤ በጊዜው እርምት ስላልተደረገበት “ትግራይ” ከዚያው የእሽክርክሪት ፖለቲካ ሰብራ ልትወጣ ባለመቻልዋ እዛው ሰምጣ ቀረች።

በወቅቱ በነበሩት በመሳፍንቶቹ ሕሊና የታየው የተጋሩ ብሔራዊ ስሜት ነጸብራቅ የጀመረው ፍንጣቂ ቆይቶ ደግሞ በወቅቱ ምሁራን በነበሩት በእነ ገብረህይወት ባይከዳኝ የመሳሰሉ ምሁራን ተጋሩ የቀጠለ ስሜት ነበር። ሆኖም እነዚህ የወቅቱ የትግራይ ምሁራን ትግራይን አገራዊ በባለቤትነትን ለማጎናጸፍ የሚል የነጠረ አስተሳሰብ ታጥቀው ሳይሆን “ኢትዮጵያ የኛ ናት” (“ኢትዮጵያ ናትና እያ”) ወደ እሚለው መፍትሔ ወደ ያላመጣው ትግል ገቡ።

ከጊዜ በኋላ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የያዘ ነበር ማለት በሚቻል ዓይነት ትግል አንገቦ ተነሳ። በቀዳማይ ወያነ የተነሳው እምቢተኛነት እንደቀደሙት ሁሉ ግልጽ ከሆነ የብሔራዊ ትግል ዓላማ የራቀ ነበር።  ቀዳማይ ወያኔ እንቅስቃሴ የገጠመው ጥቃት ዛሬ እንደታየው በስመ ዲሞክራሲ እኛን ወደ ትርጉም የለሽ ሁኔታ እንዳስገባን የተሰራበት ሴራ ሳይሆን፤ ደመኛችን (ጠላታችን) የሆነች አገር ኢትዮጵያ “የኛ” (“ናትና”) ናት ብሎ ነው የታገለው። በዚህ በተኮላሸው ያልነጠረ አስተሳሰብ ምክንያት የተነሳ “እንግሊዝ” ሁለቱ ትግሬዎች (ኤርትራና ትግራይ) ወደ አንድ አምጥቶ አንድ አገር ለመፍጠር የታቀደው የእንግሊዞች ዓላማ “በቀዳማይ ወያኔ መሪዎች ተቀባይነት ሊያገኝ ባለመቻሉ” ምስረታው ባጭር ተቀጨ። እንግሊዝም ለራሱ ጥቅም ሲል ከኃይለስላሴ ጋር በማበር ቀዳማይ ወያኔን ደመሰሰው።

በዚህ አጋጣሚ ‘ወላጆቻችን በቀዳማይ ወያኔ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ብለው ይህን ይህን እንዲህ እንዲህ የመሳሰሉ አኩሪ ትግል አደረጉ’ ብሎ በወላጆቹ ትግሬዎች ገድል የሚኮራ ቢኖረም ያም ተገቢ ቢሆንም በትግራዋይ ብሔራዊ ዓይን አገራዊ ምስረታ ስንመለከተው ግን ይህ አመለካከት ያለፈው ጠማማ የሆነው የትግራይ አገር ምስራታ ብሔራዊ ስሜት አሰናካይና ጠላፊ ስለሆነ መታረም አለበት።

ከቀዳማይ ወያኔ ውድቀት በኋላም ቢሆን የኛ የተባለቺው አገር…………..     ክፍል 4 ይቀጥላል…..

አመሰግናለሁ።

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

 

 

 

Wednesday, March 17, 2021

የትግራይ ሕዝብ በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ? ስለ ማኒፌስቶ ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ጥያቄ ማብራሪያ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay March 17, 20213

 

 

የትግራይ ሕዝብ በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ?

ስለ ማኒፌስቶ ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ጥያቄ ማብራሪያ

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

March 17, 20213



ካለፈው የ ማኒፌስቶ 11 ትግራይ አገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ጥያቄ የሚለው የትግራይ ተገንጣዮች ‘የትግርኛ ማኒፌስቶ’ ትርጉም ሰሞኑን የምቀጥልበት ሲሆን ለዛሬ ስለ ማኒፌስቶው አንዳንድ ማብራሪያዎችን ባጭሩ አቀርባለሁ።

ወደ ማብራሪያው ከመግባቴ በፊት ይህ ከታች ያለው ማሳሰቢያ ለማስተላለፈው እወዳለሁ።

እባክዎትን አንድ ወንድም (ስምዎን ሰለረሳሁት ይቅርታ) አንዲት እህት ስለ አማራ ያደረግኩትን የአመታት ትግል ለማመስገን እንድታመሰግነኝ ፈልጋ ፈቃደኛነቴን ጠይቀውኝ ስልክዋን ሰጥተውኝ ነበር። ሆኖም ድንገት የእርስዎ “የፌስ ቡክ/መሰንጀር” ሰምም ይሁን የዛች እህት ስልክና ስም ስለዘነጋሁት እባክዎትን እንደገና በመሰንጀር ይጻፉልኝ። በብዙ መንገድ ስለምጠመድ ብዙ ጊዜ ብዙ ወዳጆችን የመርሳት ነገር ይታየኛልና ለብዙዎቻችሁ መልስ ባለመስጠቴ ይቅርታ። አመሰግናለሁ።

ሁለተኛው ማሳሰቢያ፤-

ጊዜየን መስዋዕት በማድረግ ትግሬዎች በቋንቋቸው ምን እያሉ እንዳሉ ትግርኛ ለማታውቁ ሰዎች በመተርጎም የምለጥፋቸው ጠቃሚ ሰነዶችን በብዛት ተሰራጭቶ ለሕዝብ እንዲዳረስ ላደረጋችሁ ታታሪ ዜጎች ምስጋና ይድረሳችሁ። 5000 የፌስቡክ ወዳጅ አለኝ፤ የሚገረመኝ ግን ከነዚህ 5000 ውስጥ ቢበዛ ከ30 እና 40 ሰዎች “ሼር” አያደርጉም። የትግሉ ስንፍና ለምን እንደተጠቃን ማሳያ መሆኑን ጥሩ ማስረጃ ነው። ጠላት ምን እንደሚል ካላወቅን በሃሳብ ተጠቂዎች ነን።፡ሼር ለምታደርጉ ዜጎች ጥረታችንን በመካፈላችሁ እጅግ አመሰግናለሁ።

ከብዙ ወራት በፊት ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ ላይ “አገር ያቀፈቻቸው ብዙሃን ሕዝቦችዋ ደናቁርት እስከሆኑ ድረስ የሰቆቃው ህይወት ማቆሚያ ሳይኖሮው አንዱ ‘ሲያባራ’ ሌላው ‘ይቀጥላል!’ (ጌታቸው ረዳ)” በሚል ርዕስ በጻፍኩት ጽሑፍ “ወጣቱ ቱርካዊው ““መሕመት ሙራት ኢልዳን” “የተባለው ፈላስፋ እንዲህ ሲል የገለጸውን ጠቅሼ ነበር፡

” በአንድ ወቅት ሚሊዮኖች ለአዶልፍ ሂትለር አድናቆት አሳይተዋል፤ እንዲሁም ደግፈዋል ፡፡ አላዋቂ የሆኑት ብዙሃኑ ብዙውን ጊዜ ቀላል እውነቶችን ማየት አይችሉም ፣ እና በግልጽም ግልጽ የሆኑትን ጫፎች የማየት ችሎታ የላቸውም! የታወቁት የብዙዎች ሞኝነት በታሪክ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጊዜያት ተረጋግጧል! እያንዳንዱን ጊዜ የተሳሳተውን መሪ ሲከተሉ በመጨረሻ ላይ እራሳቸውን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በሆነው የመዋኛ ገንዳ ተዘፍቀው ያገኙታል!” በማለት ገልጾ መኖሩን ጠቅሼ ነበር። እነሆ ለ27 አመት አላዋቂነቱን ያረጋገጠልን ብዙሃኑ ‘ማሕበረሰብ ትግራይ’ የተሳሳቱትን የትግራይ ሊሂቃን ሲከተል ቆይቶ፤ ዛሬ በመጨረሻ ሰዓት እራሳቸውን ባልገመቱት ቦታ አግኘተውት ለስቃይ እነሆ ተዳርገዋል።

 ለዚህ የጭለማ ህይወትና ስደት የዳረጋቸው የትግሬ ምሁራን በዘረጉት ትምክህት የማሕበረሰብን አነድነትና የተረጋጋ ህይወት የሚያደፈርስ ‘ፋሺስታዊ ማኒፌስቶ’ በመቀበላቸው ሰበብ እንደሆነ ብዙዎች ባትቀበሉትም እውነታው “የነገድ ፖለቲካ አስተማሪዎቻቸውን በማምለካቸው” ነው። እነሆ ዛሬ መራራው አማራጭ ከፊታቸው ተደቅኗል።

አማራጩም አንደኛው ለ45 አመት የተዘረጋው የፋሺዝም አምልኮ ከነ አካቴው መቃወምና ሊሂቃኖቹ በትግራይ ማሕበረሰብና በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸሙት የረዢም ጊዜ ወንጀል ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡና የተረጋጋ ኑሮ መመስረት፤ ካልሆነ ደግሞ ሞትን፤ርሃብን፤ስደትን እና እሪታን እያስተናገዱ የፈረሰ ማሕበረሰብ ሆኖ የሽምቅ ተዋጊ ሽብርተኛ ሃይሎች አገልጋይ ሆኖ አማራጭ ያልሆነ አማራጭን ይዞ መቀጠል።

ባለፈው ክፍል 2 ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም ሦስት ነጥቦችን ሳትገነዘቡዋቸው እንዳታልፏቸው የምፈልጋቸው ነጠይቦችን ላስታውሳችሁ፤

ማኒፌሰቶው የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን ጥሎ ሌላ አገር መመስረት እንዳለበት ምክንያት የሰጣቸው ነጥቦች

ቀዳሚው-

 ኢትዮጵያ አማራ የተባለ ማሕበረሰብ የገነባት ስለሆነች ለአማራው እንጂ ለትግሬዎች ስለማትመች ያትታል፡-

ሁለተኛው ፦-

ትግራይ በብዛት 6 ሚሊዮን ሕዝብ ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዛት ካላቸው ማሕበረሰቦች/ነገዶች/ ጋር በዲሞክራሲያዊ ድምጽ ለሥልጣን ቢወዳደር ደምጹ አነስተኛ ስለሚሆን “የአዛዥና ናዛዥነት” ሥልጣን ዳግም እንደማያገኝ ፤

ሦስተኛው ፦

ምክንያት ደግሞ አናሳ ከሚባሉት ነገዶች ግምባር ፈጥሮ ለዲሞክራሲ ቢወዳደርም አናሳ የሚባሉት ማሕበረሰቦች የማይታመኑ ስለሆኑ ውሎ አድሮ ከሥልጣን ተጋሪነት ስለሚወገዱ የራሳቸው አገር መመስረት እንዳለባቸው ያትታል። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለባችሁ፤ ትግሬዎች ተገንጥለው አገር ሲመሰርቱ ቀደም ብሎ ማኒፌስቶው እንደገለጸው “ትግራይ ውስጥ በሕዝብ ብዛት ትግርኛ ተናጋሪው ትግሬ” ስለሆነ አናሳ የተባሉት ትግራይ ውስጥ ያሉት ነገዶችን አሸንፈን የበላይነት በማረጋገጥ (የራሱን ቃል ልጠቀም -------“መሬታችን ላይ እንደፈለግነው” ማስተዳዳደር ስለምንችል፤ መገንጠል አማራጫችን ነው” በማለት ነው ‘ሁሌም’ ትግሬዎች “የበላይነት” በመፈለግ በፋሽታዊ ባሕሪውና መነሻው “ገዢ” የመሆን ፍላጎቱን በግልጽ መቀጠል እንዳለበት የገለጸው።                                                                               

ለዚህ ነው ትግሬዎች ካልገዙዋት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብለው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጫካ የወጡት።ወጣም ወረደ ትግሬዎች 27 አመት እንደፈለጋቸው ሲገዙ ሲመዘብሩና ሲገድሉ የነበረውን የግዛት ዘመን ሲያበቃ ሥልጣን ለዘላአለም ከትግሬ ካልቆየ አገሪቷን በትነን ሌሎቹን አናሳ የትግራይ ነገዶችን እንደፈለግን የምናደርጋቸው ተገዢዎችን ፈጥረን የበላይነት ዘላቂ ፍላጎታችንን ማረጋገጥ እንችላለን በማለት ከትግራይ እስከ ኤርትራ ለመዘርጋት ያቀዱትን የበላይነት ፍላጎት ብግልጽ ባለፉት ክፍል 1 እና 2 አይታችሗል።

ዛሬ እኔ የተወለድኩበት የትግሬ ነገድ የመገንጠል ፍላጎታቸው በተግባር እያሳዩን ስለሆነ ከ 34 አመት በፊት በጉልበት ወደ ትግራይ ያጠቃለሉትን የወልቃይት፤ሰቲት ሁመራ ፤ ጸገዴ ወዘተ…… ትልቅ መሬትና ሕዝብ የአማራ ነገድም ሆነ በነዚህ መሬቶች የሚኖሩ ሌሎች ነገዶች በምንም መልኩ እንደገና ትግሬዎች ሊወስዱት መፍቀድ እንደሌለበት በአጽንኦት የማሳስበው። ዛሬ የብዙዎቹ የትግሬዎች ጥያቄና ፍላጎት ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያና የመን አፍርሶ ትግራይን እንደ አገር ለመመስረት ከሆነ (እንኳን እና አገር እያፈረሱ አማራውን በዘር ጽዳት ወንጀል የፈጁትን ወንጀል እንዳለ ሆኖ፤ ትግሬዎች በሰላም አንድነትን ቢመርጡም በሕግና በታሪክ ዓይን እነዚህ ቦታዎች የትግሬዎች አይደሉም- ይህ እውነት ነው።) ፤ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው መሬቶች በፍጹም ወደ ተገንጣይ አገር አሳልፎ መስጠት የለበትም የምለውም ከሕጋዊ እና ታሪካዊ ብቻ ሳይሆን ማኒፌሰቶአቸው እንደሚያሳያው ትግራይን አገር ለማድረግ ከሆነ “ለአንድ ቀንም ቢሆን” እነዚህ ቦታዎች የትግራይን የምጣኔ ሃብትና የውጭ አገር መንገድ በር መክፈቻ አድርገው አማራውን ለመተናኮል ስለሚጠቀሙባቸው በነዚህ ቦታዎች የመስጠትና የመደራደር ነገር ዝግ መሆን አለበት። ማኒፌሰቶአቸውም ሆነ አሁን ጫካ ውስጥ ገብተውም ሆነ ተከታዮቻቸው ለኢትዮጵያ የሚመኙት ምኞት “ንቀትና ጥላቻ” አደጋው ለማንም ሰው ግልጽ ነው። 

ለትግራይ ምሁራንም ሆነ ተራው ማሕበረሰብ ማወቅ ያለበትና ላስተላልፈው የምፈልገው መልዕክት ወያኔ ኢትዮጵያችንን ለ27 አመት ሞት፤ ስደት፤ ውርደት፤ አመጽ፤ እንግልት፤ እስራት፤ ድብደባ፤ ጦርነት፤ ግድያ፤ ዘረፋ፤ ክሕደት፤ ግብረሰዶማዊ ዝሙት አገራችንን በተዘጋጀላት ሞገደኛ ማዕበል ውስጥ አስገብተው አሰቃይተዋታል። ትዕቢት ባሳበዳቸው ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ስሜት በራቃቸው ‘የቀወሱ የትግራይ ምሁራንና መሪ ድርጅታቸው ወያኔ) የሕዝባችን ሕይወት ዛሬም ሰግጠው ይዘውታል። እነዚህ ፋሺሰቶች 27 አመት ሙሉ ባዘጋጇቸው የጭለማ እስርቤቶች እርግብ ወጣት ሴቶችን መድፈር ሳያንሳቸው ተባዕትም ጭምር ደፍረዋል። አውላላ ሜዳ ላይ በቆሙ የኢትዮጵያ ሸበላ ወጣቶች ከሰማዩም ከፎቁም ጥይት በማዝነብ ቀጥፈዋቸዋል። ትግራይ ዛሬ በነዚህ ከሃዲዎች የኢያሪኮ ጩኸት የሚያበስር ‘ማንፌስቶ’ ይዘው ጫካ ገብተዋል። ታዲያ የትግራይ ሕዝብ በእያሪኮ ጩኸት እስከ መቸ?

ማኒፌስቶ ክፍል 3 ከነገ ወዲያ ይለጠፋል ተከታተሉ……

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

Sunday, March 14, 2021

ክፍል 2 በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ ማኒፌስቶ 11 ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay March 14, 20213/

 

ክፍል 2

በ21ኛው ክ ዘመን ትግራይ ሃገር የመሆን ሕጋዊ መብትና ዘለአለማዊ ይያቄ

ማኒፌስቶ 11

ትርጉም

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay

March 14, 20213/

 

………. ካለፈው ክፍል 1 የቀጠለ ክፍል 2-

……..አንድ የነበረን ሕዝቦች ለሁለት ተከፍለን ከስትራተጂ መንገዳችንን በማሰናከል የሕዝባችንን ቁጥር እንዲመናመን በማድረግ ትርጉም ወደሌላው ህይወት እንድንገባ ያደረገቺን የጠላቶቻችን አገር ነች (ኢትዮጵያ)

አሁን ኢትዮጵያ በምትባለዋ አገር ሆነን ጥያቄአችንን ልንመልስ እንችላለን ብለን ላለፉት 27 አመታት የታየው ማሳያ ድሉ ያልመታ የተቃጠለ ተስፋ ነው። ማወቅ የነበረብን ኢትዮጵያዊያኖች በሕልምም ከኛ ጋር የማይገናኙ ብቻ ሳይሆን እኛን ለመጉዳት ከሚያውጠነጥኑ በሕዝብ ቁጥር ብዛት ከሚበልጡን ጋር የተዳበልናት/የተቀላቀልናት/ አገር ናት። 27 አመት የቆየንበት ምስጢርም በስለላና በወታደራዊ መዋቅሮች ተጠቅመን የቆየንበት ምስጢር ካልሆነ በስተቀር ጠላቶቻችን እኛን ተቀብለው የኛን ሃሳብ አምነውበት አብረን የኖርንበት ጊዜ አልነበረም።  ለኛ እንደምትመች አድርገን ስላልተጓዝን ያለፍንባቸው 27 አመታት ጉልበታችን አሟጥጠን ያሳየነው ጥረት ስህተተኛ መንገድ ነበር።

ኢትዮጵያ እኛ ፈለግናትም አልፈለግናትም ከአፈጣጠርዋ ትክክለኛ አፈጣጠር ስላልነበረ ልትቀጥል ነው ወይስ አትቀጥልም ሌላ ጥያቄ ሆኖ ፤ትቀጥላለች ብንልም እንኳ ካለፉት 27 አመት የተለየ ኣከሄድ መሄድዋ አይቀሬ ነው። እርግጥ አማራ እና ኦሮሞ በስም ዲሞክራሲ በሚደረገው የበላይነት መራኮት መጋጨታቸው አይቀርም። ሆኖም በዚህ አሰላለፍ የሃይል ሚዛን አይተን ከኦሮሞ ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር እንደ ቁማር መጫወቻ ካርድ ይዘናቸው ‘መፍትሄ አድርገን ልንጠቀምባቸው’ እንችል ይሆናል። ይቻላልም እንበልና እኛ 6 % ከመቶኛው 6 ደምጽ ይዘን የምናገኘው ውጤት እኩልነትን የሚሳይ ሳይሆን የነሱ ባርያና ተገዢ ከመሆን አናመልጥም። 

 

እነዚያ እንደ እኛዎቹ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ንኡሳን ብሔሮች የጋርዮሽ ድምጽ ጣምራ በማድረግ ግምባር እንፍጠር ብለን እንወዳደር ብንልም እነዚህ አናሳ ብሔሮች ከኛ ከትግሬዎች ይልቅ ወደ ኦሮሞዎቹ መለጠፋቸው አይቀሬ ነው። በነሱ ተማምነን የጋር ግምባር መፍጠር ዘላቂ መፍትሄ አይደለም። ይህንን ለማብራራት ትንሽ ዘርዘር ስናደርገው፤ እነዚህ አናሳ ብሔሮች ቁጥራቸው ትንሽ ስለሆነ ውስጣዊ አንድነታቸው የላላ ስለሆነ ትንሽ ከተጓዙ በሗላ ስለሚፈርሱ የነሱ ድምጽ ለኛ ዘላቂነት ያለው ትርጉም አይሰጥንም። ስለዚህ ምንም በድምጽ አናሸንፍም።

አናሳ የሚባሉት አስታማማኝ ጥመረት የማይሆኑበት ምክንያት ሌላው ለምሳሌ ሶማሌን ብንወስድ ኢትዮጵያን ትተው የሚገነጠሉበት ዕድል የላቀ ስለሆነ ነው።በዛም ሆነ በዚህ ይህ ሁላ የገበጣ ጨዋታ ዕድላችንን ከእጃችን አውጥተን ሌሎችን አምነን የምናደርገው ጨዋታ ስለሆነ ዋስትና ያለው የሕሊና እርጋታ አይሰጠንም። በዚህ ከቀጠልን የነጠረ ብሔራዊ ዓላማ ይዘን ጥገኛ ሆነን እየንተሳፈፍን መኖር ብቻ ነው ማለት ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ባጭሩ እኛ እንደ ትግሬነታችን ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን የምንገነባው መንግሥት አይኖርም። የመደራደሪያ ክርዶቻችን ስለተመናመኑ አሁን ያለው ዋስትና ይሆነናል ብለን የገነባነው ሕገመንግሥታችንም ቢሆን በተቃራኒ ፍላጎታችን የሚጻረርበት ጊዜ ይመጣል። ስለሆነም 6 ሚሊዮን ድምጽ ይዘን ትርጉም ወደሌላው ጉልበት ወርደን ታዛዦች እንጂ ወሳኞች ልንሆን አንችልም።

እነዚያ አሁን መንግሥትነት የተቆጣጠሩ ሃይሎች እንደ አማራው የከረረ ጥላቻ በኛ ላይ የሌላቸው ቢሆንም፤ እየገነብዋት ያሉት ዓላማቸው “በኦሮሞዎቹ ምስል” የምትታነጽ ኢትዮጵያ ስለሆነ፤ ውሎ አድሮ እኛም የነሱ ባርያዎች መሆናችን አይቀሬ ነው። የፋይናንስና ንግዶች በነሱ ቁጥጥር ስለሚውሉ ጸረ ትግሬ መሆናቸው አይቀርም። አብረው የሚዳበሉዋቸው ጠላቶቻችንም ትግራይ ውስጥ የሚረባ ፕሮጀክት እንዳይታነጽ መስራታቸው የማይቀር ነው። አጣቃላይ ውጤቱ ትግራይ ወደ አመድነት መቀየርዋ ነው። ይህንን እንግባበት ወይንስ ያ አይቀሬው ብሔራዊ “አገረ መንግሥት ትግራይ” ወደ ግንባታ ትግላችን እንግባ?

 

()- ብሔራዊ ዓላማችን የኛ አገር ምስረታ ባለቤትነት እውን ማድረግ ወይስ ባርነትን አንምረጥ?

 

 ቀደም ብሎ እንደተገለጸው እኛ ትግሬዎች የገነባነው ባህልና ስልጡን ስነልቦና አለን። ይህ ማንነታችን የምንሞትለት ብቻ ሳይሆን ቁጡ ጠንካራ እልከኞች እንድንሆን አስችሎናል።ከአክሱም ውድቀት ወዲህ  በዓለም ውስጥ ተገቢውን በታችን ባናገኝም  ከአክሱም ፍጻሜ ወዲህ እስካሁን ድረስ ያለው የተዘረጋው ዘመን የተጻረሩንን በመመከት ጀግንነትን እንደ አንድ የሕብረተሰባችን መለያና መገለጫ ሆኖ እንደ ውርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፏል። የትግላችን ምስጢር ከዚህ ባሕሪ የመነጨ ነው።

ይሁንና በዚህ ዓለም ተገቢውን ቦታ አላገኘንም። እንዲያም ሆኖ በ19 ክ/ዘመን መጨረሻ አጼ ዮሐንስ እንደነገሰ ያቺ የሰለጠነቺዋ የአክሱም ዘመነ መንግሥት አገራቺን ለማነጽ/ለመፍጠር የሞከረበት ወቅት ነበር። ወቅቱ የቅኝ ግዛት ተወዳዳሪዎች የበዙበት ወቅት ስለነበር  ከነዚያ የአፍሪካ ቀንድ ለመቀራመት ፍላጎት የነበራቸው ቅኝ ሃይሎች ጋር  በመጋጨት አገራችን ትግራይ በ7ኘው ክ/ዘመን ከመዳከምዋ በፊት የነበረውን የቀይ ባሕር ጆኦ-ፖለቲካዊ ሃያልነት ለማምጣት ሞክሮ ነበር። ሆኖም በጣሊያኖች ሴራ እና ዛሬ ጠላታችን የሆነቺውን አሁን ያለቺውን አገር ኢትዮጵያ የገነባ ዛሬ ጠላታችን የሆነውን ሃይል (አማራ) ጥምረትና ሴራ ግንባታችንን በመሰናከሉ ግቡን ሊመታ አልቻለም።

ዛሬ ሕዝባችን ለሁለት ተከፍሎ የማይድን ቁስል ይዘን እንድንኖር ተደርገናል። መውደቃችንን እንዳይበቃ በ19 ክ/ዘመን ማገባደጃ የገጠሙንን ከአጼ ዮሐንስ ሕልፈት ወዲህ እያነሳን ያለንበት ምክንያት የመጥፎ ታሪክን ሱስ የማንሳት ይዞን ሳይሆን፤ የገጠመን ተራ አጋጣሚ ሆኖ ሳይሆን አስፈላጊ ትውስታ ስለሆነ ነው። የአጼ ዮሐንስ መንግሥት በድል ቢቀጥል ኖሮ ዛሬ አሁን እያየናቸው እየገጠሙን ያሉትን ችግሮች ይወገዱ ነበር። ይወገዱ ነበር በቻ ሳይሆን በዓለም ውስጥ ሊኖረን የሚገባ የክብር መንበር ሌላ መልክ ይይዝ ነበር።

ባጭር አገላለጽ የአጼ ዮሐንስ ሕልፈት በ19ነኛው ክ/ዘመን ማገባደጂያ የተፈጠረው ይህ  የንጉሱ ሕልፈት “የዘመን መጠመዘዢያ ማኣዘን”  (ተርኒንግ ፖይነት) ነው የምንልብት ምክንያት በሚከተሉት ምክንያቶች መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል፡

1)      በዚህ አጋጣሚ እኛ በሕዝብ ብዛት በቁጥር የበላይነትን ይዘን ጂኦፖለቲካዊ የበላይነት ይዘን ማነጽ ልንችል የነበረቺውንና ለዓለማችን ፍላጎት የምትስማማ አገራችንን ከእጃችን ተነጥቀን ወደ ተንሳፈፈችና ጥገኛ ወደ ሆነቺው የአገር ትርጉም የሌላት አገር ለጠላቶቻችን የምትጥም ለኛ የማትጥም አገር የገባንበት የዘመን መጠምዘዣ መሆኑ

2)     …………………..ክፍል 3 ይቀጥላል