Wednesday, December 10, 2008

ቀይ ባሕርን በኑክሌር አተላ መበከል፤የኢሳያስ አፈወርቅ ትብብርና የአምባሳደሩ ግድያ








ቀይ ባሕርን በኑክሌር አተላ መበከል፤
የኢሳያስ አፈወርቅ ትብብርና የአምባሳደሩ ግድያ ጌታቸዉ ረዳ
አቶ ዉሕሉል ፈዳይ ንጉስ በተባሉ ኤርተራዊ በተከታታይ በተለያዩ ርዕሶች በትግርኛ ጽሑፍ ለትግርኛ አንባቢዎችhttp://www.asena-online.com/
ይፋ እያደረጓቸዉ ያሉትን ምስጢራዊ ሰነዶችን እንድትከታተሉት በማለት በአማርኛ ተርጉሜ ለአንባቢዎች አንኳር ሰነዶችን እያዘጋጀሁ እንዳስነበብካችሁ ይታወሳል። ይህ የዛሬ ጽሁፍ ካለፈዉ የቀጠለ ተከታታይ ሰነድ ነዉ። የሰነዱ አቅራቢ/ምንጭ ሲዘግቡት ከላይ በአርዕስቱ እንደተመለከተዉ የቀረበ ርዕስ ሳይሆን በኔ በኩል ለታሪክ ዘጋቢዎች ዳሰሳ እንዲያመች በማለት ባንድ ተሰባስበዉ የተዘገቡና የተሰበጣጠሩ ሰነዶች ሰብሰብ በማድረግ ድርጊቶቹ የየራሳቸዉ ርዕስ ጠብቀዉ እንዲነበቡ አድረጌ አለሁ። ድርጊቶቹ የየራሳቸዉ አመድ ጠብቀዉ መዘገባቸዉ እንጂ ትርጉሙ ያዉ የቋንቋ መልስ እና ያጠቃቀም ስርዓት ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ከፍሬ ነገሩ የተለወጠ ነገር የለዉም። ሰነዱ ጠለቅ ያሉ ብዙ ነገሮችን በዉስጡ ይፋ አድረጓል። የዘመን ቆጠራዉ “በኤርትራዉያኖቹ -በፈረንጅ” አቆጣጠር ነዉ።ተከታተሉት። መልካም ንባብ።

“የኢጣሊያ መንግሥት ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ከኢንዱስትሪዎቿ የተገኙ ቆሻሻዎች እና የኑክሊየር አተላዎች መጣያ ስታፈላልግ ባጀታ፤ሕዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ በ02/17/1988 ደርግን የቀይ ባሕር ዉሃ የቆሻሻ መጣያ አድርጎታል፡ በማለት ሲቃወመዉ የነበረዉን የዉንጀላ አቋም በመዘንጋት በ14/03/2005 ኢሳያስ አፈወርቅ እና የኢታልያዉ መንግሥት ጠ/ሚኒስትር ቢሎስኮኒ መካከል በተደረገዉ ሰምምነት መሰረት፤ የ ኤርትራዉ ፕረዚዳንት ወደ ኢታሊ በመሄድ የጣሊያን የኢንዱስትሪዎች መርዛማ ቆሻሻ አተላዎችን በቀይ ባሕር እንዲጣሉ እና አንዲደፉ ዋና የጉብኝቱ አጀንዳ ያደረገ ስምምነትን ነበር።

በስምምነቱ መሰረትም በምፅዋ ደሴት(2) ‘ዕዳጋ’ በመባል በሚታወቀዉ የከተማዉ ቀጠና ዉስጥ (1) እና ሌላም ‘ጥዋለት’ በተባለዉ የምፅዋ አካባቢ ከሕዝብ ዕይታ በአጥር ከላላ ተጋርዶ በነበረዉ አካባቢ ላይ በድምሩ 136 ቶን መርዛማ አተላ አንዲጣል በመሰማማት 136 ቶን ክብደት ያለዉ መርዛማ አተላ በተጠቀሱት ቦታዎች ተደፍቷል።

ጉዳዩም በአንዳንድ የአካባቢዉ ሹሞች ዘንድ ቁጣ አስነስቶ ነበር። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢሳያስ ጋር ወደ ጣሊያን አገር ጉብኝቱን አጅቦ አብሮት የሄደዉ በጣሊያን አገር የኤርትራ አምባሳደር የነበረዉ አምባሳደር ዓንደሚካኤል ካሕሳይ ሚስጥራዊ የስምምነቱ ዉል በመቃወሙ ምክንያት በኢሳያስ አፈወርቅ ትዕዛዝ ለኮሎኔል ጋይም ተላልፎ በደህንነቱ ክፍል በካፕቴን እስቲፋኖስ እና በካፒቴን ነጋሲ ዓንደ አቀነባባሪነት “ጣባ” በተባለዉ አካባቢ ገድለዉት ሬሳዉ ተጥሎ ተገኝቷል።

ሰበቡ በዛ ብቻ አላቆመም።የቀይ ባሕር አዉራጃ አስተዳደር አስተዳዳደሪ የነበረዉ ‘አብራሂም ቶቲል’ በሰሜናዊ ቀይ ባሕር በምፅዋ ከተማ ሲካሄድ የነበረዉ ምስጢራዊ የመሬት ቁፈራ ባማያዉቀዉ እና አሱ ሳይፈቅድ በመደረጉ ቁፈራዉ ለምን እዳስፈለገ እና ማብራሪያ አስካልተሰጠዉ ድረስ ቁፈራዉ እንዲያቆም በማዘዙ፡ ‘ከሚገባህ በላይ ምስጢር ለማወቅ ሙከራ አድርገሃል”፡ በሚል ሰበብ ከስልጣኑ እንዲወገድ በማድረግ በጀነራል ሙሳ ራባዕ ተተካ። ጀነራል ሙሳም ብዙ ሳይቆይ ተመሳሳይ ዕጣ ደረሰበት።

የኤርትራ መንግሥትም ለዚህ ክንዉን 12 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሎታል። የኤርትራ የዜና መገናኛዎች እንደሚያወሩት፤ ኢሳያስ ወደ ጣሊያን አገር በሚመላለስበት ወቅት ‘የኤርትራ እና የኢጣሊያ መንግሥት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ተፈራረሙ’ እያለ ዜና ቢያስተላልፉም፤ ትላልቅ ከተባሉት ፕሮጀክቶች አንድም የተሰራ የለም። በምትኩ የተከናወኑት ስምምነቶች- በቀይባሕር ምድር ቆሻሻ እንዲጣልና ለመጣያዉም የገንዘብ ክፍያ ስምምነቶች ብቻ ነበሩ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን ከሩቅ ሆና ስትከታተለዉ የነበረዉን ትራጄዲ ወደ ራሷ ኮመዲ ለመለወጥ ጊዜ አልፈጀባትም።በመሓመድ ቓስም አቀነባባሪነት ከ2007 ጀመሮ ኤርትራ የኢራን የኑክሌር አተላ ወደ ኤርትራ ቀይ ባሕር ዉሃዎች እንዲደፋ ስምምነት ፈርማለች። ቀይ ባህርን የምትቆጣጠረዉ ኢራን አስካሁን ድረስ በሁለት መርከቦች የተጫነ 680 ቶን መርዛማ የኒኩልየር ዌስት/አተላ ለመድፋት አስችሏታል።ለዚህም ትብብር ኤርትራ በመቶ ሚሊዮኖች ዶላር ተከፍሏት እንደ የዉጭ ምንዛሪ ገቢ ተጠቅማበታለች።

ቀደም ብለን እንደተመለከትነዉ በብርጋዴር ጀነራል ፍጹም ገ/ሕይወት ሲቀነባበር የነበረዉ የባሕር ላይ የጠለፋ ዉምብድናዉ ሁሉ፤ ይህ አደገኛ መርዛማ የኢንዱስትሪ ቆሻሻ መድፋት ምስጢራዊ ክንዉንም በማዕከልነት የሚመራዉ ጀኔራል ፍጹም ገ/ሕይወት ሆኖ አብሮት በጣምራ የሚሰራዉ የባሕር ሃይሉ አባል ኮሎኔል መሓሪ ደስታ ነወ። በዚህም መሰረት በ11/06/2007 ቆሻሻዉን የመድፋት ክንዋኔ ተፈፅሟል።
ኮሎ ኔ ል መሓሪ ደስታ በዚህ የምስጢር ተግባር በመሳተፉ ለስራዉ አገልግሎት ጉርሻ በብርጋዴር ጀኔራል ኢዮብ ፍስሃየ (ሓሊባይ) አስተዳደር ሥር ሚካሄደዉ የመንግሥት ቤቶችና የምሪት ቦታዎች ዕደላ ጽ/ቤት፤ ድሮ ጣሊያናዊዉ ሃብታም ‘ሲኞር-ባራቶሪ’ ገንብቷቸዉ በነበሩት ምርጥ የመኖርያ ቤቶች (ደቡባዊ ምዕራብ አስመራ አካባቢ) አካባቢ በየማነ ገብረመስቀል (ቻርሊ) በኩል በኢሳያስ አፈወረቅ ትዕዛዝ ምርጥ የመኖርያ ቪላ እንዲሰጠዉ ተደረገጓል። ከዚህ ሌላ ከብርጋዴር ጀነራል ፍጹም ገ/ሕይወት እጅ $25,000 ዶላር ጉርሻ ተሰጥቶታል።

ኢሳያስ አፈወርቅም በበኩሉ በ04/15/2002 ወደ ሊቢያ ሲጓዝ ለሶማሌ እስላሞች ፍርድቤት ግምባር ትብበር እና እርዳታ በማድረጉ ምክንያት ከኮለኔል ጋዳፊ እጅ የ$1,000,000,000.00 (አንድ ቢሊዮን ዶላር) ጉርሻ አግኝቷል።

የኢራን መርከብ የኒኩልየር ዝቃጭ ቆሻሻ ጭና ወደ ቀይ ባሕር ስትጓዝ የነበረችዉን መርከብ የአሜሪካን ባሕር ሃይሎች ለፍተሻ በማስቆም ፤መርከቢቷ የጫነችዉን ጭነት ማስፈተሽ እንዳለባት ወይንም አቅጣጫዋን በማዞር ወደ መጣችበት ማዞር እንደሚኖርባት ትዕዛዝ ሰጥተዉ ያስቆሟት ዕለት መርከቧ ዉስጥ ተሳፍሮ የነበረዉ ኤርትራዊዉ ሰዉ በዳይቪነግ ከፍተኛ ችሎታ ያለዉ የኤርትራ የባሕር ሃይል አባል የነበረዉ ሌተናል ኮሎኔል ተስፋሚካኤል ባሲሎስ ነበር።

በዚህ ወቅት በOctober 06/2008 የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታዉ ክፍል በሶማሊ ቀይ ባሕር አካባቢ እየታዩ ያሉት የተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባሮችን ለመቆጣጠር በአካባቢዉ ሚንቀሳቀሱ ተዋጊ አይሮፕላኖች እና የመርከብ ባለቤቶች ሁሉ አስፈላጊዉን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ያስተላለፈዉ።እንደሚታወሰዉ ባለፈዉ ምዕራፍ እንደተገለጸዉ በዚህ ምክንያት ተነሳ ነበር ሁሉም የዓለም አባል ሃገሮች ማሕበር በዉሳኔዉ እና በጥሪዉ ሲስማሙ ኤርትራ ግን በወኪሏ በተባበሩት መንግታትሥታት የኤርትራ አምባሳደር በአቶ አርአያ ደስታ በኩል ተቃዉሞዋን አሰምታ እንደነበር ይታወሳል። ይቀጥላል… “

No comments: