ከወያኔ የገበና ማሕደር
የወያኔ የፖሊስ እና የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣኖች
ሌቦችን በማስተባበር ወንጀል ሲፈጽሙ የሚያመለክት ማህደር
ጌታቸዉ ረዳ
ከጥቂት ዓመታት በፊት የመቶአለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የተባሉ በወያኔዉ መንግስት በፖሊስ ሰራዊት የመቶአለቅነት ማዕረግ የነበራቸዉ በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ 21 ፖሊስ ሹም እና የምርመራዉ ክፍል ሹም በመሆን አገራቸዉን በቀና ለማገልገል በሙያቸዉ ተሰልፈዉ እንደነበር እና የሗላ-ሗላ ግን የወያኔ ባለስልጣኖች በጎሰኝነት እና በዘረፋ በተራ ስርቆት ሌቦችን አሰማርተዉ ሕዘቡን ሲያሸብሩ እና ሰላም ሲነሱ በመታዘባቸዉ እና በምርመራዉም ላይ ግምባር ቀደም ሚና በ አካልም ዘራፊዎቹ እና አስዘራፊዎቹን የሚያሰማሩ አንዳንድ የደህንነት እና የፖሊስ ከፍተኛ ባለስለጣኖችን ሰለ ፍትሕ እና ስለተማሩበት ሙያ ሲሉ በሙያቸዉ ጸንተዉ ሲጋፈጧቸ እና እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሌቦችን እየለቁቁ ካለ ቦታቸዉ ጣልቃ እየገቡ አላሰራም ስላሏቸዉ የነበራቸዉን ስራ እና የሚወዷት አገራቸዉ እና ቤተሳባቸዉን ጥለዉ ወደ ስደት በማምራት የሻዕቢያ ራዲዮ አሳቸዉን አፈላልጎ ከአዉሮጳ የስልክ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዉ እንደነበር ይታዋሳል። መኮንኑ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ እና ያጋለጡት ምስጢራዊ ሰነዶችን በዚህ ለናንተ “ከወያኔዎች የገበና ማሕደር” ርዕስ ቀርቧል።
“ምናልባትም ካልተሳሳትኩ” የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን- አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በየትኛዉ የ አርበኞች ግምባር ጦር መሆናቸዉን አላዉቅም እንጂ በኤርትራ መንግስት ሲደገፉት ከነበሩት የአርበኞች ግምባር በአንደኛቸዉ ዉስጥ መሰለፋቸዉ ትዝ ይለኛል። ጽሁፋቸዉም በየትናዉ የህዋ ሰሌዳ እነደሆነ ትዝ አይለኝም እነጂ ስለ ግምባሮቹን በሚመለከት ስለ አንድነት እና መተባበር የጻፉት የ አማርኛ ጽሑፍ አንብቤአለሁ። ምናልባትም ይህ ዝግጅት ማንበብ ከቻሉ በ እኔ እና በ ኢትዮጵያን ሰማይ ዳት ብሎግ ሰፖት.ካም (Ethiopiansemay.blogspot.com) አንባቢዎቼ ስም ከፍተና ምስጋናን አቀርባሉ። ባሉበት ምድ እና ትግልም ተቃና ኢትዮጵያዊ ግዳጅዎ እንዲቃና እመኝለዎታለሁ።አምላክ ከ እርስዎ እና መላ ቤተሰቦ በሰላም ይጠብቀዎት እአልኩ በቀጥታ ወደ ቃለ መጠይቁ ማህደር ወደ ወያኔ የስረቆት እና ዝርፊያ ገበና እናምራ።
በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳዉ ምርመራ ሹም እነደነበሩ እና የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ሌቦችን በቡድን እና በግለሰብ በማሰማራት በዘረፋ ስራ እንደተሰማሩና የሚዘርፉበትም መሳሪያ በ ባለስልታኖች ስም ተመዘገበ ማሳሪያ እነደነበር በምርመራዉ እንደረሱበት እና ሌሎች ዝርዝር ታሪኮችን ያጋለጡበት አነሆ፡-
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን
"በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 21 የፖሊስ ምርመራ ክፍል ሹም እንደመኖሬ መጠን በዛች ወረዳ ብቻ የተፈጸሙትን እኔ የተከታተልኳቸዉ መንግስታዊ ወንጀሎችን ነዉ በማስረጃ አስደግፌ ማቀርበዉ። ካገሬ ብወጣ እና በሰደድም ፖሊስ እንደመሆኔ መጠን ሙያየም ስለሚያስገድደኝ ከሕግ ዉጭ የተፈጸሙ መንግስታዊ ደባዎችን ህዝቡን የማስረዳት ግዴታ አለብኝ።
ለምሳሌ ብጠቅስ፣ በወረዳ 21 ቀበሌ 01 ሳህለስላሴ ህንጻ የሚባል አንድ ህነጻ አለ። ህንጻዉ ዉስጥ “ኢሰመጉ” የሚባል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅት ጽ/ቤት የነበረበት ነዉ።የጽ/ቤቱ በር ተሰብሮ ተዘረፈ።የተሰረቀዉ ምነድ ነዉ!ሰነዶች፤ፋይሎች መጽሐፍቶች እና የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች ናቸዉ ተሰረቁት።በመሰረቱ ቢሮዉን እንዲዘረፍ የተፈለገበት ምክንያት ሰነዶችን ለመዉሰድ ነበር። እኔ በዛዉ ወቅት የወረዳዉ ሸም ስለነበርኩ፤በአካባቢዉ የተፈጸሙ የወንጀል ድረጊቶችና ፈጻሚዉን ተከታትሎ ወደ ሕግ ማቅረብ ሃለፊነት አለብኝ። ኢሕአዴግ አይደልም ይህነን ሐላፊነት የሰጠኝ።አንደኛ የተማርኩበት ት/ቤት ኮርሴን አጠናቅቄ ስመረቅ ለእዉነት እና ለሕግ ተገዝቼ ሕዘቡን ለማገልገል አስምሎ ነዉ ያስመረቀኝ።ሁለተኛ ሕገ መንግስቱ ራሱ ይህነን እንድከታተል ያስገድዳል።በዚህ መሰረት ክትትል በማድረግ ይሄነን ኢሰመጉን ቢሮ ሰብሮ የሰረቀዉን ሌባ፤ከሌሎች የስራ ባልደረቦቼ ጋር ሆኜ (አሁን ስማቸዉን ለመትቀስ አልፈልግም) ከነሱ ጋር ሆነን ተከታትለን ነዉ ግለሰቡን የያዝነዉ “ኤርሚያስ መብራህቱ” ይባላል።
የኢሰመጉ ጽ/ቤት የያዘዉ የማመለክቻ ፋይል ከተለያዩ ቦታዎች ከደቡብ፤ ከአማራ፤ ከኦሮሚያ ክልል፤ ከትግሬ ክልል እንኳን ሳይቀር ወዘተ ያለ ሕግ ከስራ አባረሩኝ፤ ተደበደቡኩኝ ወዘተ የሚሉ ሰብአዊ ነክ ጉዳዮችን ለዚህ ለኢሰመጉ ቢሮ እሮሯቸዉን ያስገቡበት የግለሰቦች ማመልከቻ ነበር የተዘረፈዉ።የነሱ ፋይል ነዉ የተሰረቀዉ።ኤርሚያስ መብራቱ ፋይሎቹን ዘርፎ ለማን ይሰጠዋል፤ በዞን 2 የኢሕአዴግ ሐለፊ ሆኖ ብዙ መስሪያ ቤቶችን የሚቆጣጠር “ገብረ እግዚአብሔር” ሚባል ከፍተኛ ካድሬ አለ።ሰነዶቹን ለእረሱ ነዉ የሰጠዉ።
ገብረእግዚአብሔር … “ኤርሚያስ መብራህቱ” መያዛችንን ሲሰማ፤ ባስቸኳይ ምርመራዉ እንዲቆም ብሎ ነዉ ትዕዛዝ መመሪያ ለእኔ የሰጠኝ። አይ- ምረመራዉንም እማ አላቆምም! ምክንያቱም ወንጀል ተፈጽሟል።”ወንጀል ከተፈጸመ ደግሞ ፈጻመዉ ወደ ሕግ መቅረብ አለበት” የሚል መልስ በምሰጥበት ሰዓት፤ ከእኔ ጋር ሆኖ ሲሰራ የነበረ የጣቢያ አዛዥ አስጠንቅቀዉ (ለሱ ነበር ማስጠንቀቅአዉ የተሰጠዉ) መዝገቡን ወደ እኛ ባስቸኳይ ላክ ተባለ።መዝገቡ ወደ ክልል እንዲላክ ተደረገ። አሁን በዚህ ሰዓት ላይ እዛዉ ከኔዉ ጋር ሲሰሩ ነበሩ የክፍል ሃላፊዎች አሉ፡አነዚህ በቀጥታ መዝገቡን አንሰጥም ማለት ይችላሉ። ይህ አቋም ከያዙ ደግሞ በቀጥታ ከኢሕአዴግ ጋር ተጋጩ ማለት ነዉ።ምክንያቱም ወንጀሉን የፈጸመዉ ኢሕአዴግ ነዉ (ኤርሚያስ መብራህቱ ነዉ)። ኤርሚያስ መብራህቱ ቃሉን ሲገልጽ ምነድ ነዉ ያለዉ_”ገብረእግዚአብሔር ነዉ ሂድ ስረቅ ያለኝ። ሂድ እና መዝገቦቹን ሰርቀህ አምጣ ያለኝ ምክንያት እኔ ሌባ መሆኔን ያዉቃል።እንዲያዉም ይረዳኛል።መዝገቦቹን ብቻ ስጠን ብሎ መዝገቡን ስጥቼዋለሁ” አለን። የግድግዳ ሰዓቶችን እና ሌላ ሌላ የተዘረፉት ንብረቶች ግን ሄዶ ከመረካቶ ነዉ የሸጠዉ።የሸጠዉን ዕቃ ደግሞ አስመልሰን በእግዚቢት ይዘነዋል።
ጥያቄ፦ የመቶ አለቃ አሁን እርሰዎ ያሉት ያሉት ፤ወያኔ ገንዘብ እየከፈለ ወንጀል ያስፈጽማል ነዉ የሚሉት ።ልከ ነዉ?
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን-
በሚገባ እንጂ! ይሄ ኤርሚያስ መብራሕቱ የምልህ ከወላጅ አባቱ ጋር ተጣልቶ የወጣ ስርዓተ አልበኛ ዱርየ ነዉ።የሚኖረዉ በመስረቅ ነዉ። አበዛኛዉ በዋናነት የቅርብ ጓደነኝቱ ግን ገብረ እግዚአብሔር ካልኩህ ጋር ነዉ። የሚያመሹትም ሚዉሉትም አበረዉ ከገብረእግዚአብሔር ጋር ነዉ።ገብረእዝግዚአብሄር ማለት ደግሞ በዞን ሁለት የኢህአዴግ ባለስልጣን ነዉ።የዞን አስተዳደር፤የዞን የትምህርት የጤና ወዘተ በዉስጡ ብዙ ዘርፍ የያዘ ክፍል ነዉ። ጠቅላላ ኢህአዴግን ወክሎ በእነዚህ እና በመሳሰሉት ሕዝባዊ ነክ ዘርፎች የሚቆጣጠረዉ ይህ ክፍል ነዉ።ይህ ክፍል ደግሞ የሚቆጣጠረዉ “ግብረእግዚአብሔር” ነዉ። ስለዚህ ሂድ እና ይሄነን ተግባር ፈጽም እያለ የሚያዘዉ “ገብረእግዚአብሄር፡ ነዉ።ይህ ልጅ ፍላጎቱ በመሰረቱ የሚሸጥ ነገር መስረቅ ነዉ። ምክንያቱም “ኢሰመጉ” ቦሮ ዉስጥ ገብቶ “ሰነዶችን” ሰርቆ ልሽጥ ቢል ማንም አይገዛዉም።ገንዘብ የሚያስገኝለትን ስርቆት እና ዕቃ አጥንቶ ነዉ የሚሰርቀዉ። አነጋግረነዋል።በሚገባ እንዲሰርቅ ማን እንዳዘዘዉ ግልጹን ነግሮናል። ይህነን የወረዳ 21 መርማሪ ፖሊሶች በሚገባ ያዉቁታል።የሰጠዉም ቃል በወረዳዉ ዕለት ሁኔታ መዝገብ ተመዝግቦ ይገኛል። ኢሕአዴግ ብቃቱ እና ሞራሉ ካለዉ እና ልከታተለዉ ካለ ‘እዛዉ ሄዶ መዝገቡን ማየት ይችላል፤ ዉሸት ከሆነ። ስለዚህ ኢህአዴግ የሚያሰማራቸዉ ወንጀለኞች አሉ።
ሌላዉ ልጥቀስ። አንድ የቀድሞ ሰራዊት አባል በሻምበልነት ማዕረግ የነበረ፤በወረዳ 21 ቀበሌ 22 እና 24 መካከል ስሙን ዘንግቼዋለሁ ማዕረጉን ነዉ የማስታዉሰዉ (ማስታወሳን ስለወሰዱብኝ)።
ጥያቄ፡- ማነዉ መስታወሻዎን የወሰደበዎት?
የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን-
ኢሕአዴግ።ቤቴን ሰብረዉ ስኖርባት ነበረችዉን አንዲት ክፈል እኔ በሌለሁበት ሰብረዉ ማስታወሻዎቼን ወሰዱት። ይህ ድረጊት የፈጸመዉ “ጀማል” የሚባል መጀመሪያ የአዲስ አበባ የደህንነት ሃለፊ የነበረ በሗላ ደግሞ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል እና መርመራ ክፍል ሹም የነበረ፤- እሱ ነዉ ማስታወሻ ሰነዶቼን በሙሉ የወሰዳቸዉ።
ጥያቄ፦ ይገርማል! በዚህ ጉዳይ ወደ ሗላ እንመለስበታለን እና ስለ ሻምበሉ ጉዳይ አስኪ ይቀጥሉ፦
..ሻምበሉ፤በድሮ ሰራዊት አባል ሰራዊት የነበረ ነዉ።በወረዳ 21 እና በቀበሌ 22 መካከል ከቀኑ ስድት ሰዓት አካባቢ ክላሽ በታጠቀ ግለሰብ ተተኩሶበት ተገደለ።ይሄ ግለሰብ ተገድሎ፤ገዳዩ ሻምበሉን ገድሎ እየሮጠ ወዴት ነዉ የገባዉ (?) በወረዳ 21 ቀበሌ 04 “ገነት ሆቴል” የሚባል አንድ ሆቴል ፊት ለፊት ካለዉ የደህንነት ህንጻ ጸ/ቤት በቀጥታ ሮጦ ገባ። ሕዘቡ ተከተታትሎ ሪፖርት አደረገ። ከዛ እኛም ደረስን። ከዚያ በሗላ ደህንነት ጽ/ቤት አባሎችን በማነጋገር “ሰዉ ገድሎ ከእናንተዉ ቢሮ ዉስጥ ሸሽቶ አምልጦ ገብቶ የተደበቀ ሰዉ አለ እና ስጡን ወይንም እንግባ እና እንፈትሸዉ ብለን ስንል፡ “በቀጥታ ከዚህ ጥፉ!” ነዉ የተባልነዉ።
በሬድዮ “ልዩ ሃይል” ተጠርቶ በነሱ እንድንባረር ተደረገ። “ልዩ ሃይል” የሚባል አለ ስለ እሱ ወደ ሗላ አነሳዋለሁ። ልዩ ሃይል ማለት የሰዉን ጭንቅላት ለመቀጥቀጥ የተሰራ “መዶሻ” ነዉ ማለት ይቻላል። እና ከነሱ ጋር ተጋጭተን ስለነበረ ወዲያዉ ከክልሉ ፖሊስ -ፖሊስ ኮሚሽነር “ተስፋይ አብርሃ” በተባለ ግለሰብ ወደ መ/ቤታችን እንድንመለስ ትዕዛዝ ተሰጠን እናም ወደ ቢሮአችን ተመልሰን ሄድን። ወደ አካባቢዉ ስንሄድ የሰዉየዉ አስከሬን ወደ ሆስፒታል ተላከ።ከዚያ በሗላ በክልል ደረጃ ይጣራል ተባለ እና የሰዉየዉ አስከሬን በምኒሊክ ሆስፒታል ሃኪሞች እንዲመረመር ተደረገ። የነበረዉ መረጃ ወደ ክልል ስጡ ተባለ። እነ መቶአለቃ ተማም ኑር ከኔ ጋር ሲሰራ የነበረ ነዉ፦ ከላይ ክልል ደግሞ እነ መቶ አለቃ ዘላለም የሚባሉ በክለል ነብስ ግድያ ወንጀል ምርመራ ቡድን መሪ ነበሩ፤- ጉዳዩ እነሱ ሁሉ ያወቁታል።ሻምበሉ የተገደለዉ ከፖለቲካ ንክኪ ነዉ።የተገደለዉ ደግሞ በጠራራ ጸሐይ ነዉ። ገድሎት ወደ ደህንነት ገብቶ ገዳዩ ሳይጠየቅ ቀረ።
ሌላዉ የወንጀል ዓይነት ደግሞ ልንገርህ። ቡድን አደራጅቶ ወንጀልን የመፈጸም ድርጊታቸዉን ልግለጽ።
ለምሳሌ አንዴ “ጸሐየ” አንዴ “በየነ” አንዴ “እያሱ”፤አንዴ ገብረእግዚአብሔር አንዴ … በተለያዩ ስሞች የሚጠራ የ“ተስፋይ አብርሃ” የእህቱ ልጅ ነዉ።እሱ ነዉ ቡዱኑን የሚመራዉ።ተስፋይ አብርሃ በዛ ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊስ ፖሊስ ኮሚሽነር ነበር።በሗላ ደግሞ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ግጭት ሲፈጠር “ጌታቸዉ አሰፋ” (የማዕከላዊ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረዉ) ወደ ጦሩ ሲሄድ የሱን ቦታ ተክቶ ሲሰራ የነበረዉ ነዉ። ተስፋይ አብርሃ የነጌታቸዉ አሰፋ፤የነክንፈ ገብረመድህን ቡድን ነዉ ‘ተስፋይ አብርሃ” ማለት። ተስፋይ አብርሃ የሚታወቀዉ “ተስፋይ አፍረሶም” በመባል የሚታወቀዉ ነዉ።ተስፋይ አፍረሶም ብለዉ በአብዛኛዉ የሚጠሩት “ተስፋይ አብርሃ” ማለት ነዉ። እንግዲህ “በየነ፤እያሱ…ወዘተ በሚል ስም የሚጠራዉ ለተስፋይ አብርሃ የ የእህቱ ልጅ ነዉ። በዚህ ግንኙነት በመሳሪያ ታጥቀዉ ሃብታም ነጋዴ ቤት ወይንም ድርጅቱ ድረስ ሄደዉ እያስፈራሩ “በደህንነት ትፈለጋለህ” “በፖሊስ ትፈለጋለህ” እያሉ እና ሚፈልጉዋቸዉን ሃብታሞች በመኪና ጠልፈዉ ይዟቸዉ ይሄዳሉ። ወያኔ ነጋዴ ስለሆነ የሚጫረቱትን ነጋዴዎች ማስፈራራት ማዋከብ ይፈልገዋል እና ነጋዴዎቹም ይህ ባህሪዉ ስለሚአዉቁት ነጋዴዎቹ ስጋት ላይ ናቸዉ። ሰዎቹ ወደ ንግድ ቦታቸዉ ወይንም ከሆነ ካገኙዋቸዉ ቦታ ተልፈዉ በመኪና ለምሳሌ ወደ ባምቢስ የድህንነት ቢሮ አለ ካዛንቺስ ዉስጥ “አንደር ግራዉንድ” አስርቤት ወዳለበት አንድ ድህንነት ኦፊስ አለ ወደ ማዕከላዊ እ…. ወደ ሜክሲኮ ወዳለዉ ልዪ ኦፊስ አለ …ወደ ተላያዩ ወደ እነዚህ ቦታዎች እየወሰዱ በማሳየት ያስፈራሯቸዋል።
ወደ እነዚህ ደህንነት ጽ/ቤቶች ይወስዱ እና አስፈራርተዉ በሺዎች ብር የሚቆጠር ገንዘብ እተቀበሉ ይለቋቸዋል።ለምሳሌ በኔ በ21 ወረዳ ልዩ ቦታዉ “ባክሻፍት” (?) ተብሎ በሚጠራ አጠገብ አንድ ህንዳዊ ዜጋ ነገዴ ነበር። ያ ሕንድ ነጋዴ በተከታታይ ወደ 60 ሺህ ብር በእነ “ጸሃየ” ተወስዶበታል።ይህ የምርመራ ወንጀል እኔ እና ባልደረቦቼ ደርሰንበታል።ይህ ወንጀል ስናዉቅ ሰዉየዉን ሄደን አነጋገርናቸዉ። እንደዚህ ዓይነት ወንጀል ተፈጽመዎበታል፤ ለምንድ ነዉ ወደ እኛ ድረስ መጥተዉ ወንጀሉን ያላመለከቱበት ምክንያት? ብለን ጠየቅናቸዉ። እንግዲህ ካሁን ወዲህ ወንጀለኞቹ እንደልማዳቸዉ ወደ እርስዎ ሲመጡ እኛኑን ወዲያዉኑ ይጥሩን አልናቸዉ። “ታስገድሉናላችሁ” አሉን። ግዴየለዎትም፣ ብለን ቃል ገባንላቸዉ። በመጨረሻ ኦኬ (እሺ) አሉ።
አሁንም ያ “ጸሃየ” የተባለዉ ሰዉየ ደወለላቸዉ።መደወሉን ለእኔ ነገሩኝ። ሲደዉሉ አኔ እና ባለደረቦቼ ወደ ድርጅታቸዉ ስንሄድ 3ሺህ ብር አስፈራርቶ ካሳቸዉ ተቀበለዉን ገንዘብ ይዞ ሲወጣ ወዲያዉኑ እጅ ከፍንጅ ደጃፋቹ ላይ ያዝነዉ። መሳሪያ ታጥቋል።ፎርጂድ የሆነ የታጋይ መታወቂያ ይዟል። ታጋይም ሁን- ሌላም ሁን ምን የምተሄደዉ መንግሥት ቦታ ነዉ፤ ፖሊስ ጣቢያ ነዉ። እዛ ሄደን እነንጋገራለን፡ እና አንሂድ ብለን ከነ ማሳሪያዉ እና 3ሺህ ብሩን ሁሉ ያዝነዉ። የሚገርመዉ ደግሞ ከኪሱ ደግሞ “ካገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር” የሚል ለነጋዴዉ የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ በማሕተም የታተመ የተጻፈ የማስፈራሪያ ደብዳቤ ይዟል። ሻምበል (የሻምበሉ ስም ይጠቅሳሉ- ከቴፑ ጥራት ግን ስሙን በትክክል መለየት ያስቸግራል) ሻምበል (ጥሃፌ/ጸሀፌ (?) ከተባለ ተወካያችን የተለካ ደብዳቤ ነዉ የሚል ማህተም ያለበት ደብዳቤ ሁሉ ይዟል።ከደህንነቱ ተጻፈ አስመስሎ ማለት ነዉ።ይሄን ሁሉ ያዝን እና ወደ ጣቢያ ሄድን።
እኔ ወደ ቢሮ ገብቼ፤ የዕለት ሁኔታ መዝጋቢዎች የተያዛወን ንብረት እግዝቢት እየመዘገቡ እያሉ፡እኔም ይሄን “ጸሃየ” የተባለዉ ሰዉ እያነጋገርኩት እንደለሁ ወዲያዉኑ ከክልል ምመሪያ “ረዳኢ ገ/አነንያ” የተባለ በፖሊስ ሬንጀር መኪና እበረረ ወደ እኔ ቢሮ መጣ። ማን እንደነገረዉ፤እንዴት እንደሰማም አይታወቅም። መጣ። የታያዘዉ ሰዉ አለ ወይ? አለኝ። አዎ አለ፡ አልኩት። ከዚያ ሲያዉ ሰዉየዉን በትግርኛ ተነጋገሩ። እኔ ትግርኛ አልችልም- ግን ፍሬ ነገሩ የተረዳሁት ምንድነዉ፦ለምን አባትክ በየወረዳዉ ትልከሰከሳለህ! የሚል ነዉ።መጨረሻ ሁለቱም ከተነጋገሩ በሗላ “ይህ ጉዳይ በክልል ደረጃ መታየት ስላለበት በክልል ደረጃ እንዲጣራ እኔ ይዤዉ እሄዳሉ አለኝ። እኔም “አይሆንም” ብየዉ ጭቅጭቅ አድረገን፤ ወዲያዉኑ “በላይ” የሚባል ካገር ዉስጥ ደህንነት “በላይ” እባላለሁ ነኝ ያለኝ፦ደዉሎ “ይሄ አሁን የያዝከዉ ኬዝ እኛም እየተከታተልነዉ የነበረ ስለሆነ እና በስፋት ለማጣራት ስለምንፈልግ ለረዳኢ ስጠዉ፡ ረዳኢ ይዉስደዉ!” አለኝ። ማነህ አንተ? ስለዉ- እኔ ከደህንነት ነኝ እደወልኩ ያለሁት። አለኝ። እንዴ ታድያ ደህንነት ከሆንክ የደህንነት ስራ ስራ እንጂ ይሄ እኮ የፖሊስ ስራ ነዉ፡ እርግጥ ሚያገናኘን ስራ ዘርፍ ቢኖርም፤ይሄ የወጣለት፤የለየለት ደረቅ የማጭበርበር ወንጀል ስለሆነ-ግለሰቡ እና ማስረጃዎች “ኦልሬዲ” የተያዘ ስለሆነ ማስረጃዎች ተጣርቶ ወደ ሚመለከተዉ ሕግ ይቀርባል እንጂ እንዴት ወደ የበላይ ይሂድ ትለኛለህ? ስለዉ “ስጠዉ ማለት - ስጠዉ ነዉ “ስጠዉ ብየሃለሁ! ስጠዉ ብየሃለሁ!” አለኝ።
በመጨረሻ ተስፋይ አብርሃ (አፍረሶም) (ቅድም የፀሃየ የእህቱ ልጅ ነዉ ብየ የጠቀሰውኩት ባለስልጣን ደዉሎ ለረዳኢ አስረክበዉ ብየሃለሁ ብሎ ደዉሎ አሱም ከኔ ጋር ንትርክ አድርጎ የተያዘዉን መሳርያ እና የመሳሪያዉ መለያ ቁጥር፤ እንደዚሁም 3ሺህ የተያዘዉ ገንዘብ ረዳኢ ይዞት ሄደ። ለታሪክም መዝገቡ ካልጠፋ ወይም ካልቀደዱት በወረዳ 21 የዕለት ሁኔታ መዝገብ አስከ እነ ቁጥሩ ቀን ዓ/ም ይገኛል።መሳሪያዉ ቁጥር፤ የሐሰት የደህንነት ደብዳቤ ከነ ሸኚ ቁጥሩ ሳይቀር ሁሉ ተመዝግቦ ይገኛል።ተጠያቂዉም አብሮ ከነ መዝገቡ ይዞት ሄደ። አንድ ሰዓት አልቆየም ይሄ ይዞት የሄደዉ ‘በየነ’ ‘እአሱ’ ‘ጸሃየ…እገሌ እገሌ እያለ በተለያየ ስም የሚያጭበረብረዉ ወንጀለኛ ስልክ በቀጥታ ወደ እኔ ደወለ። ደዉሎ ምንድ ነዉ ያለኝ- “ከማን ጋር እየታገልክ እንደሆንክ እወቅ! ለምድነዉ አርፈህ እንጀራህን በሰላም እየበላህ የማትኖር? ካስፈለገ እኮ የአንተ ጉዳይ የደቂቃ ስራ ጉዳይ ነዉ! ብሎ በስልክ ደዉሎ አስጠነቀቀኝ።
እኔም ስመልስ_ አንተ ምትችለዉን አድርግ እኔም አለሁኝ! አልኩት እና በዚህ ተለያን።
አንግዲህ በነ ተስፋይ አብርሃ በእነ ረዳኢ ገብረአነንያ በኩል ነዉ መሳሪያዉን የሚያገኘዉ። ይዞት የነበረዉን ያጭበረበረበትን መሳሪያ ፈቃድ አሳየን ብለን ስንጠይቀዉ የማሳሪያዉ መለያ ፈቃድ የሚያሳየዉ “”ረዳኢ ገብረአነንያ” ይላል።ረዳኢ ገብርአነንያ ማለት ደግሞ ‘የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ሃለፊ” ነዉ። ሌሎች ትግሬ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን ግን በሆነ አጋጣሚ መሳሪ ይዘዉ ከተገኙ ተይዘዉ ይታሰራሉ።ወይ ኦነግ ነዉ ወይ መኢአድ ነዉ ወይ የኦሮሞ ኮንግረስ ወይ የደቡብ ህዝቦች አባል ነዉ የሚል የፖለቲካ ስም ይለጠፍበት እና “ጀርባዉ ይጣራ” የሚሉት ቋንቋ አላቸዉ። ይሄ ጸረ ኢሕአዴግ ነዉ፡መሳሪያ ከየት ሊያመጣ ይችላል? ተብሎ ስቃዩን ያያል። የትግራይ ተወላጆች ግን 3 አራት ማሳርያ አላቸዉ። ይሄ የሚደረግዉ እንግዲህ ወያኔ ራሱ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” እንደሚባለዉ “ራሱ ዳኛ ነዉ” ራሱም “ይዘርፋል ወይም ያስዘርፋል” ።ስለዚህ በቡድን በእጅ አዙር በመንግስት ባለስልታኖች የሚሰራ የወንጀል መተባበር ተግባር እና ትስስር ተለመደ ነዉ።
ሌላ ዓይነት ቡድን ደግሞ አለ።
አንድ ቀን ታጋይ ሐዱሽ፤ታጋይ ጀማል፤ታጋይ ዜናዊ የተባሉ በቀን መኪና አስቁመዉ ከዛዉ ከእነ ተስፋይ አበርሃ ቢሮ ትንሽ ዝቅ ብሎ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ (የተስፋይ አበርሃ ቢሮ ነዉ) ከዚየዉ ዝቅ ብሎ ከጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ጀምሮ አስከ መክሲኮ ድረስ በአንድ መኪና እየበረሩ መጥተዉ፤ ክላሽን ጠመንጃ ይዘዋል፤ሽጉጥ ታጥቀዋል፤የመከላከያ ደምብ ልብስ ዩኒፎረም ነዉ የለበሱት፤ሦስት ናቸዉ፡ አንዱ ሾፌር ነዉ-ከደጅ ሆኖ ይጠብቃል፤ ሁለቱ በመደዳ በወቅቱ ክፍት በነበሩ ቡናቤቶች ገብተዉ ለመዝናናት የመጡ ደምበኞችን ሁሉ ወለል ላይ በሆዳቸዉ አስተኝተዉ -ሰዓት ያለዉ ሰዓቱን፤ወርቅ ያለዉ ወርቁን፤ የቡና ቤቱ ቴፕ ሪኮርደር እና ከመጠጥ ሽያጭ የተገኘዉ የቡና ቤቱ ባለቤት ገንዘብ ካለም ገንዘቡን ዘርፈዉ መኪናቸዉ ይሰወራሉ። እንግዲህ እንደዚህ እያደረጉ ከላይ ከ እዛ… እንግዲ አዲስ አበባ ለሚያዉቅ ሰዉ ግልጽ ነዉ፤-ከፕያሳ ጀምረዉ በቴድሮስ አደባባይ አድርገዉ በመስቀል አደባባይ አድርገዉ እንደገና እየዞሩ አስከ ሜክሲኮ አደባባይ ድረስ ሲመጡ መደዳዉን ስላዳረሱት ህዝብ ተዘርፏል እና ለእርዳታ ድረስ ተብሎ ለክልሉ በስልክ ሲነገር_ የክልሉ ተረኛ ፖሊሶች ይህነን ይሰማሉ።-
ድርጉቱ ሲፈጸም አጋጣሚ ምሽት ስለነበር፤-የበላይ አለቆች በእዛ ሰዓት በየአረቄ ቤቱ ስለነበሩ ከወገንተንነቱ ነጻ የሆኑ ፖሊሶቹ ይህነን ሃላፊነት ለመወጣት ጥሩ አጋጣሚ አግኝተዉ የዘረፋዉ ዜና በየወረዳዉ በስልክ ስያስተላልፉልን፤ጥበቃ ማድረግ ጀመርን። በዘረፋዉ ወቅት ዘራፊዎቹ የተጠቀሙባት የታክሲ መኪናዋ ልዩ መለያ ምልክት ተነግሮን ስለነበር እመክሲኮ አደባባይ ስትደርስ ታክሲዋን አየናት። ተከታተልንባቸዉ። እነሱን ተከታትለን ወደ ልደታ አቀናን ቀጠሉና ሄዱ፡ ከልደታ ወደ…(የቴፑ ድምጹ ጥራት በደምብ አይሰማም) ሲሄዱ እዛዉ ደረስንባቸዉ። ከመኪና ሲወርዱ አስቆምናቸዉ። ስናያቸዉ የለበሱት ልብስ የመከላከያ ነዉ፡ሽጉጥ ይዘዋል፤ክላሽ አነግተዋል፡ ይገርማል! ይሄነን ለተመለከተ ሰዉ እነኚህ ሰዎች ዘራፊዎች ናቸዉ ብሎ ደፍሮ ለማለት የስቸግራል። መጨረሻ እጃችነን አንሰጥም አሉን። እኛም አግባብተን “አይ ሌሎች ሰዎች መስላችሁን እኮ ነዉ፣ ለካ እናንተም ታጋዮች ናችሁ’ ብለን አዘናጋናቸዉ እና በመጨረሻ የተጠቀምነዉ ስልት አለ፦አያነጋገርን ያዝናቸዉ።መሳሪያቸዉንም የዘረፉት ንብረትም ገንዘቡንም ሁሉ አነሱንም ይዘን ወደ ጣቢያ ሄድን።
ታክሲዋ/መኪናዋም ጭምር ወረዳዉ ፖሊስ ጣቢያ ታግታ ለብዙ ጊዜ ቆማ ነበር። ሾፌሩ “እኔ ተገድጄ አስገድደዉኝ ነዉ እንጂ በዚህ ስራ ወድጄ አልተሰማራሁም” ስላለ ዳኛዉም ዉሳኔ መስጠት አቅቶት ነገሩ ሲጎትተዉ መኪናዋ ለብዙ ጊዜ ቆማ ተገትራ እዘዉ ነበረች። በመጨረሻ ላይ ምርመራ ተደርጎላቸዉ ሲጠየቁ “ዛሬ ብታስሩን -ነገ እነፈታለን”እያሉ ያሾፉብን ነበር። የዉም የሚገርመዉ “መታሰራችን ሳይሆን የሚቆጨን የዘረፍነዉን ገንዘብ ሳንጠቀምበት መቅረቱ ነዉ”-አለን ‘የማነ’ የሚባለዉ ከዘረፉት ንብረት ጋር ፎቶግራፍ ሳስነሳዉ።”እኔን ዘረፍክ ትሉኛላችሁ-የተዘረፍኩት ግን እኔ ነኝ” አለን የዘረፉት ንብረት ባንድነት ተቀምጦ ሲያየዉ አሳሳዉ/አስጎመጀዉ። “ይሄ ሁሉ ይዤ ብሄድ ኖሮ ነበር “ዘረፍክ የምባለዉ፤ነገር ግን የተዘረፍኩት አኔ ነኝ እያለ ሲቀልድብን ነበር።
በመጨረሻ ተጣርቶ ለሚመለከተዉ ስናስረክብ በዋስ እንዲለቀቁ ተደረገ። መሳሪያን ተጠቅሞ በሰላም የሚዝናናን በሰላም በየጎዳናዉ እና በየ አደባባዩ ወደ ቤቱም ወደ ስራም የሚንቀሳቀስ ሰላማዊ ዜጋን መዘርፍ እና ሽብርን መልቀቅ በጣም ከባድ ወንጀል እና አስከ 15 ዓመት በእስር የሚያስቀጣ የወንጀል ድርት ነዉ።ዜጎች እንደልብ እንዳይንቀሳቀሱ በየመንገዱ እና በንግድ ተቃሟት እገባ የሚያስጨንቅ በፍርሃት ሚገድብ ሚያሸማቅቅ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዎች በወቅቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት የነበሩት የትግራይ ሰዉ “አቶ ሐጎስ” የሚባሉ እንዲለቀቁ አደረጓቸዉ።
አብዛኛዉ እንደዚህ ያለ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት ከተማ ዘረፋ ሽብር ላያዉቀዉ ወይንም ሰምቶት የማያዉቅ ብዙ ሰዉ ሊኖር ይችላል።ለዚህም ነዉ እኔ በፖሊስ ሞያነቴ ተሰማርቼ እንደዚህ ዓይነቶቹ መንግስታዊ ወንጀሎች ሲፈጸሙ በማየቴ ያየሁትን መረመርኩትን ለህዝብ ምስጢሩ ተደብቆ እንዳይቀር የማጋለጥ ሃለፊነት ሙያየ ስለሚያስገድደኝ ህዝቡ እንዲያዉቀዉ ይገባል በሚል ነዉ።በመንግሥት የተቀነባበረ ግድያ (ለምሳሌ ሻምበሉን እንደገደሉት ዓይነት)፤በቡድን እና በግለሰብ በባለስልጣኖች የተቀነባበረ ዘረፋ፤ነጋዴ ሕብረተሰቡን ማስጨነቅ ማስፈራረት የመሳሰሉት ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር እተመሳጠሩ የወንጀል ድረጊቶች ተፈጽመዋል። ኢሕአዴግ ነጋዴ በመሆኑ ፤ነጋዴዎችን በማስፈራራት እንዲሸማቀቅ እና ከጨዋታዉ ዉጭ ሊያደረግዉ ይፈልጋል። ወደደም ጠላም ከፍራቻ ነፃ ለመሆን (እንዳይዘረፍ) ከኢሕአዴግ ባለስልጣን ቢያንስ አንድ ወዳጅ እንዲይዝ እንዲሞዳሞድ ሰላም በዉስጡ እንዲሰማዉ ጀርባዉን እንዲተማመን ያደርጉታል። ስለዚህ በሕዘብ ላይ የሚደረግ መንግሥታዊ ደባ ህዝቡ ማወቅ አለበት።
ይህ ተቀነባበረ የዘረፋ እና የፖለቲካ ወንጀል ፖሊስ ኮሚሽነረሩ አቶ ተስፋይ አብርሃ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወንጀል መከላከል ሃለፊ የአቶ ረዳኢ ገብረአነኒያ እጅ እንዳለበት ከላይ የገለጽኩት በወረዳችን በወረዳ 21 ሲካሄድ የነበረዉ የተቀነባበረዉ ዘረፋ ወደ ወረዳ 20 ሽፍት አድረጎ ወደ ወረዳ 20 አዞሩት። ወረዳ 20 ማለት በዞን ሁለት ቄራ አካባቢ የሚገኘዉ ወረዳ ማለት ነዉ። እና በሌሎች ወረዳዎች በወረዳ 19 17 20 23 24 ወረዳዎች እየተዘዋወረ የሚዘርፍ ቡድን ነበረ። ከነዚህ ቡድኖች ዉስጥ አሁንም ዜናዊ ነበረበት። ዜናዊ ማለት ቅድም ስጠቅስ ከነ ጀማል ጋር የነበረ ነዉ። እንደገና ከዚህ ቡድን ጋራ አስቀድሞ ሲዘርፍበት በነበሩት ወረዳዎች ትቶ በእነዚህ በተጠቀሱት አዳዲስ የዘረፋ ወረዳዎች መዝረፍ ጀመሩ። እነዚህ በተከታታይ በጦር መሳሪያ በመደገፍ በየመንደሩ በየቤቱ እየገቡ እያሰሩ ዘረፋቸዉን ያካሂዱ ነበር። ይህ ድርጊት በጊዜዉ ጉዳዩን ሲከታተሉት የነበሩት እነ መቶ አለቃ ክፍሉ እነ መቶአለቃ ስሞኦን እ… እራሱ የወያኔዉ ሹም የነበረዉ የዞን አዘዥ “አጋዓዚ” እ…… እነ ወታደር ማዕርጉ እ….. ምሕረታብ የሚባሉ ይህነን ነገር ያወቁታል። ምክንያቱም እነሱ ነበሩ እንዲመረምሩ ትዕዛዝ ተሰጣቸዉ።
ከላይ የጠቀስኳቸዉ የምርመራ ባልደረቦች በምርመራዉ ላይ ጥሩ አልሰራችሁም ተብለዉ ከስራ አገዷቸዉ።ሜርኲሪ የሚባል የማጭበርበሪያ ስልት አለ፡ የተጣራዉ ዝርዝር ምርመራ በእዛኛዉ በሜሪኩሪ ኮሚቴ አልፎ ወደ ደህንነት ከዛዉ ወደ ትላልቆቹ ባለስልጣኖች ቢሮ ሲሄድ የነበራቸዉ አማረጭ ምርመራዉን ማስቆም ነዉ። ምርመራዉን ለማስቆም ደግሞ ሲመረምሩ የነበሩትን ልጆች ምርመራ አሳጥታችሗል/አጋልጣችሗል፤ሰብአዊ መብት ረግጣችሗል በሚል እነ ወታደር ማዕረጉ እነ ምሕረታብ እነ መቶአለቃ ክፍሉ እራሱ “አጋዓዚ” ሳይቀር ይመሰክሩታል። አጋዓዚ ራሱ በዚህ ምክንያት ከስራዉ ታግዶ ነበር። መርማሪዎቹ ከስራ ሲባረሩም ሁኔታዉ በጣም ስለገረማቸዉ “ ሰራቂዉ ትግሬ፤ዓቃቤ ሕጉም ትግሬ፤ዳኛዉም ትግሬ፤ ታዲያ ይሄ ከሆነ የኛ በቦታችን ሆነን ጉዳዩን መመርመር ፋይዳዉ ምንድነዉ? ብለዉ በምሬት ስለተናገራቸዉ -ከስራ ተባረሩ። ምክንያቱም በተጨባጭ የተረጋገጠ እና የምናዉቀዉ ሲዘርፉ የነበሩት ትግሬዎች ናቸዉ፤
ጉዳዩ ተጠርቶ ለከፍተኛ ሲላክ ጉዳዩን በአጋጣሚ የተላለፈለት የተረከበዉ አቃቤ ሕግም ትገሬ ነዉ፤ አሱ ጋር ሲደርስ አሱም በዋስ ልቀቁዋቸዉ አለ። ዳኞች ጋር ቀርበዉ ሲያመለክቱ “አይ እኛ አናስርም” አሉ። አናስራቸዉም ብሎ ትዕዛዝ የሰጠዉ ዳኛ ደግሞ ትገሬ ነበር። በዚህ ተበሳጭተዉ ነበር “እንዴ! ዘራፊዉ ትግሬ ፤ዓቃቤ ሕጉም ትግሬ ዳኛዉም ትግሬ ስለዚህ በማሃል ገብተን መዳከራችን ምን ዉጤት አመጣ?” በማለታቸዉ “መንግሥትን ነቅፋችሗል የመንግስት ወገኖች ሳትሆኑ መንግስት ጠላቶች ናችሁ” ብለዉ እንዲባረሩ ተደረገ። አሁን ስራ የላቸዉም እነዚህ ሰዎች። አጋዓዚን የዞኑን አዛዥ የነበረ በዚህ ረገድ የኢሕአዴግን ጥቅም አላስጠበቅክም ተብሎ አሱንም ከ ሌሎቹ ቅን መርማሪዎች ጋር አግደዉት ለወራቶች ካንከራተቱት በሗላ ይመስለኛል መልሰዉ ከዞን አዘዥነት ስልጣኑን አዉርደዉ በወረዳ 28 አካባቢ በጣም ትንሽ ደካማ ጣቢያ በሆነች የወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ አድርገዉ መለሱት። የተቀሩት ስራ አጥ ሆነዉ ተንከራትተዉ ነበር። ዛሬ በምን ሁኔታ ላይ አንዳሉ አላወቅኩም። እና እነዚህ የመሳሰሉት ወንጀሎች፤ባለስልጣኖቹ የፖሊስ ሃይል ጽ/ቤቶችን የደህንነት ስለጣኖችን በመጠቀም ያስዘርፋሉከዘራፊዎችም ጋር ጥቅም ይካፈላሉ።
ሌላዉ በጣም ልብ ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊገነዘበዉ የምፈልገዉ ነገር ለየት ያለ የአገሪቱን ከኢኮኖሚ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የዘረፋ ድርጊት ልግለጽ። አንድ ባገሪቱ ዉስጥ በግምባር ቀደም የሚጠቀስ ድረጅት አለ፡ እና በጥሞና እንድታዳምጡኝ እጠይቃለሁ። የድርጅቱ ስም “የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን” የሚባል መረጃዉ እንደሰማሁት ምናልባትም ካገሪቱ በጀት ግማሹን ለዚህ ድርጅት ተመድቧል። በዚህ መ/ቤት ዉስጥ ሚደረግ ምዝበራ አስመልክቶ አንድ ማስረጃ ላቅርብ። የህ ድርጅት በወረዳ 021 ቀበሌ 24 ልዩ ቦታዉ መክሲኮ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነዉ የሚገኘዉ።ትልቅ ህንጻ ነዉ። እ…. መስርያቤቱ በማዕከልነት ለመምራት የተቋቋመ መስርያቤት ነዉ። ሌሎች የክልሎች ባለስልጣኖች አሉ። ይሄ የጠቅላላ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ነዉ።ግዙፍ ነዉ። ስራዉ መንገድ መስራት ነዉ። ሁለት የመንገዶች የስራ ዘርፎች አሉት። አንዱ በመንግስት የሚከናወን ሌላዉ የግል ኮንትራክት ተጫራቾች የሚያከናዉኑት አሰራር ነዉ። ኮንትራክተሮቹ ከዚህ ድርጅት ጋር ተፈራርመዉ የሚሰሩ ተዋዋየች ናቸዉ።
እኔ አስከ ማዉቀዉ ድረስ በ1989 ዓ/ም አካቢ ጀምሮ በዚህ መስርያቤት ዉስጥ በተከታታይ ዘረፋዎች ሲካሄድ እኔ የማዉቀዉ በተጫባጭ የደረስኩበት ምርመራ ነዉ።ዘረፋዉ ሚካሄደዉ ምንድ ነዉ? የመስሪያቤቱ ንብረት ይሰረቃል፤ በወረዳ 21 እና ቤሎችም ንበረቶች የሚቀመጥበት ግምጃ ቤት አለ።ሌሎችም በወረዳ 18 እና ሌሎች ግምጃቤቶች አሉት። ግን እኔ መግለጽ የምፈልገዉ በእኔ ወረዳ በነበረዉ ጉዳይ ነዉ። ምረመራዎች በሂደት እየተደረጉም እያሉ፤ አሁንም በተደጋጋኒ ያለማቋረጥ ሌላ ስርቆት ይካሄዳል። ዕቃዎች ይጠፋሉ ይዘረፋሉ። ዘራፊዉ አይታወቅም። መቸ ተዘረፈ? በማን ተዘረፈ? የሚል አይታወቅም።የመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ለይስሙላ ብቻ መሰረቁን ደብዳቤዎች ይጽፉ ነበር። የሚጽፉት ለማን ነዉ_ለማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራ ማስተባበሪያ ለእነ “ታደሰ መሰረት”፤ ታደሰ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ነዉ። ለነሱ ይጻፋል። ቀጥሎ የሚጽፉት ለአዲዩስ አበባ ፖሊስ ነዉ። “ተስፋይ አብረሃ” ሳይቀር ያዉቀዋል።ኮሞሽነር በነበረበት ጊዜ በተከታታይ ደብዳቤ ተጽፎለታል።
ይሄ መስርያቤት በእኛ ወረዳ በወረዳ 21ፖሊስ ጸ/ቤት ክልል በመሆኑ ለተጠቀሱት መ’ቤቶች ሲጻፍ ለእኛ በግልባጭ ያመለክቱን ነበር። እኔ ጋር ይመጣል፡ ቢሮ ዉስጥ ተመዝግቦ ይቀመጣል። ሁኔታዉን አያለሁ።ከስድስት ወር በፊት የተጻፈዉ ደብዳቤ መለስ የለዉም፤ዘረፋዉ አሁንም ቀጥሏል፤ አሁንም አዲስ የዘረፋዉ አመላካች ደብዳቤ በተከታታይ ይጎርፋል። በክልሉ የምርመራ ሃለፊ የነበሩ መቶ አለቃ አስፋ አየለ የሚባሉ ይሄን ነገር ጠየቅካቸዉ።እንዴ! ይሄ መስሪያ ቤት ተከታታይ ደብዳቤዎች ለናንተ ይጽፋል፡ ለኛም በግልባጭ ያስታዉቀናል፤የተካሄደ ምርመራም የለም። ይሄ ብሔራዊ ወንጀል/ናሺናል ክራይም ነዉ እና እንዴት ነዉ መቶ አለቃ አሰፋ የምታዉቀዉ ነገር አስቲ አካፍለኝ፤ይሄ ጉዳይ አሳሳቢ ነዉ፤አገሪቱን ይጎዳል ብየ አወያየሁት። መቶ አለቃ አሰፋ አየለ ጥሩ አዋቂ የፖሊስ መኮንን ነዉ። አይ! “አበረ” ይሄን ነገር ባታነሳብኝ ጥሩ ነዉ አለኝ። የተወሰኑ ሦስት የመስሪያ ቤቱ ዘበኞች ምርመራዉን ለማጣራት አስሮ አንደነበር ነገረኝ። በሁለተኛዉ ቀን ልቀቁዋቸዉ ተብሎ ተለቀቁ። እንዴት? ለምን? ሲባል -በስረቆቱ ጉዳይ ብዙ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣኖች እጅ ስላለበት እነኚህ ዘበኞች ለትንሽ ጊዜ በእስር ቢቆዩ ምስጢሩን ስለሚያወጡ እና ባለስልጣኖቹ እና ንክኪያቸዉ አብረዉ ስለሚጋለጡ በዚህ ስለሰጉ እንዲለቀቁ ተደረገ። ይቀጥላል…….
5 comments:
People may think that TPLF/EPRDF is a government, not true they govern the Mafia way; they have been doing that since Yekatit 11, 1975. We are dealing not with civilized people, but majirat-mechi group.
Ye-Mekelle Lij
Dear editer, it is really very historic and important. You did very excellent work.I know Abere Adamu in person when he was in the police force. He was very couragous and capable officer. But no one was able to listen him. He was speaking loudly about the regime. I really want to know where he is. Please.I hope he is fine.i also read an article WRITTEN BY Abere Adamu about TPLF election trapings some time 2005 on Ethiomedia.com.That article was very interesting too.Thank you Abere Adamu and the editer of this website.
From Getachew Reda (the editor):-
Thanks for your positive comment regarding Lieutenant Abere Adamu’s interview and the positive comment you gave to our blog. I thanks indeed. The interview is a living document and future testimony when justice starts to breath in freedom. As I did said it many times in the past, that TPLF is a corrupt , most of all it is the continuation of a feudal legacy that just took a different form, by changing its true color in order to fool the eye of the people. In practice, it is the typical if not worst feudal ruler surrogating imperialism to hatch in Ethiopia in order to destroy the core value of the nation. Based on the interview as you read it, not only that such heinous crime is carried by TPLF government, but also as you can see it on the Audio/video section to the right side of the blog –children are abused by neo-colonialists and imperialists in the name of religion. TPLF is preaching this crime as you saw it posted on the most brutal liar among the TPLF web sites calling itself “Aigaforum.com” as Freedom of religion flourishing in Etjhiopia. This children’s abuse by imperialists and its surrogates is now openly agitated by the regime as freedom. Yes, Ethiopia is at the hand of dangerous sailing boat lead and crazed by the CIA child calling itself TPLF. Ethiopians are now loosing their pride by these thieves calling themselves “freedom fighters or Tigrayan people Liberation front. So, this TPLF thieves and feudal are going to be there as long as Imperialists are getting ground in Ethiopia to destroy our culture and justice. TPLF can’t challenge our posted documents, because, such documents that are posted here are all based on facts. TPLF new its inside and its dirty laundry as a feudal ruler. Keep in touch sir. I thank again all of you for commenting and visiting.
Mr.Getachew Reda, you did very good job. Can you post the rest? It is very interseting and important for this time.
Mr.Getachow Reda, how are you? The interview you did with Lt. Abere Adamu is really very clear indication that TPLF is ready to distroy our beloved nation by organizing criminal groups.
Please would you, post the rest one and look for Lt.Abere to have another interview about the courent situation? We have to look for him. He knows many things and we have to encourage him also.
Thank you.
Post a Comment