Thursday, August 20, 2026

በቴድሮስ ጸጋዬ ሚዲያ የቀረበው 10ቱ ቃላት የጥላቻ ነዳፊው አሉላ ሰለሞን እና የሁቱ 10ርቱ ቃላት ነዳፊው ሓሰን ንገዜን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው። ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/13/22 በድጋሚ ብ8/20/26 የተለጠፈ

 

 

በቴድሮስ ጸጋዬ ሚዲያ የቀረበው 10ቱ ቃላት የጥላቻ ነዳፊው አሉላ ሰለሞን እና የሁቱ 10ርቱ ቃላት ነዳፊው ሓሰን ንገዜን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 11/13/22 በድጋሚ ብ8/20/26 የተለጠፈ

የርዕየት ሚዲያ አዘጋጁ ቴድሮስ ጸጋዬ፤ ወያኔ እንዳልለው በጣም ነበር ስጠነቀቅ የነበረው። አሁን ለይቶለታል፡ ስለዚህ በግልጽ የወያኔ ቆብ ለብሷል። ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዲስቶች ወደ ሚዲያው ሲቀርቡ ያለወትሮው እንደ ንብ ሲናደፍ የነበረው ምጠቅ ምላሱ “ሆን ብሎ” ሲሸብበው በተደጋጋሚ አይቻለሁ። እንደፈለጉት ሲጋልቡ እያደመጠ ዝም ብሎ የፈለጉትን ሲያቦኩ ይለቃቸዋል። እንደ ቴድሮስ የመሰለ የጥያቄና መልስ ልምድ ያለው ሕግ የተማረ ሰው እንዲህ ወርዶ ሳየው ምንም እንኳ በተለያየ ጎራ ብንሰለፍም እንዲያ ያለ ምጡቅ ሕሊና ጠውልጎ በትግራይ አክራሪ እቡይነት ተሸብቦ ሳየው አዘንኩኝ።

<< ትግራይና ኢትዮጵያ ምን እና ምን ናቸው? ከዚህ በኋላስ ወዴት?” በሚል ርዕስ አሉላ ሰለሞን ካሁን በፊት ያወጃቸው የጥላቻ አዋጆቹን አስመልክቶ እንዲያብራራ ጠይቆት ሲመልስ አዋጆቹን እያጣመመ እንዳሻው ሲመልሳቸው ቴድሮሰ ሆን ብሎ አሉላ በጽሑፍና በድምፅ ያወጃቸው 10ቱ የአሉላ የዘር ቅስቀሳ ወንጀል መሆናቸውን እያወቀ ቴድሮስ ከ10 ውስጥ ነጠላ አዋጅዋን ብቻ መዝዞ እንዲያብራራለት ጠይቆት አሉላ እንዲያ እያወላገደ አንዳንዴም እንደጀግንነት ቆጥሮት አዋጁ “ግቡን የመታ ስኬታማ” እንደሆነ በደስታ ሲገልጽለት አጥብቆ ላላመጠየቅ እንዲህ ያለ ወንጀል በቸልታ ዝም ብሎ እንዲያላግጥ ለቅቆታል።

 ቴድሮስ ጸጋዬ የአሉላ ሰለሞን የዘር ቅስቀሳ ሕግጋቶች ተስማምቶት ካልሆነ በስተቀር ቴድሮስ ባለው የሕግ ዕውቀት አሉላን የሚወጥርበት መሟገቻ ፍሬ ነገር ያጣል ብሎ መገመት የዋህነት ነው። አሉላ ሰለሞን የደረሳቸው 10ቱ የጥላቻ እና የብጥበጥ ማኒፌስቶ/ምመሪያ/መርሃ-ግብር ፈረንጀቹ እንደሚሉት ሕብረተሰባዊ ኑሮን የሚያደፈረስ “የሞት ቲኬት” የሚሉት ነው። ይህ አደገኛ ጥሪ ያወጀው የትግሬው “ሐሰን ንገዜ (አሉላ ሰለሞን)” ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ አቅልሎ ማየቱ አንድ ቀን በዚህ ርዕስ ሰዎች አንስተው በታሪክ ይወያዩበታል።  

እንደምታውቁት ቴድሮስ ጸጋዬ ዳኒኤል ክብረት እንዲህ አለ ፤ሞገስ እንዲህ አለ ፤ እገሌ እንዲህ ጻፈ ፤ እገሊት እንዲህ ተናገረች እያለ እየተነተነ ጠረጴዛን የሚደበድብ በንዴት የሚንጨረጨር ሰው ነው። በትግራይ ሰው የተጻፉት ስለ 10ቱ ቃላት የጥላቻ ሕጎች በሚመለከት ግን መንጨርጨሩንስ ተውት ማታለሉን እንዳያሰናክልበት በጥንቃቄ ነበር የያዘው።

የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜ በተመሳሳይ በወደጆቹ ሚዲያ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ሲደረግበት ሙልጭ አድርጎ በመካድ የተጻፉት አዋጆች እያጣመመ “ሰዎች በመሰላቸው” ሊያቀርቡት ችለው ይሆናል አንድም ማስረጃ በጽሑፌ ውስጥ ቱትሲዎቹ እንደሚሉት አላሳፈርኩም” እያለ እንደ አሉላ ሰለሞን ሲክድ በስምና በአገር የሌላ አገር ተወላጆች መሆናቸውን ካልሆነ በስተቀር “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” እና “የሩዋንዳው ሐሰን ንገዜ” የባህሪ ተመሳሳይነት ይገርማል

 ፍርድ ቤቱ ውስጥም ሲጠየቅ እንደ አሉላ እያጭበረበረ ሲመልስና ጣልቃ እየገባ ሄግ ፍርድቤቱ ሲረብሽ “የመሃል ዳኛዋ” (ፈረንጅ ነች) << አርፈህ ተቀመጥ ካልሆነ አስወጣሃለሁ!!>> ስትለው ነበር። ውጭ አገር የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን የሕግ ምሁራን እና በየ ኤምባሲው የሚርመጠመጠው የኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብና የሕግ ባለሞያዎች እንዲህ ያለች ዳኛ ዘንድ አሉላ ሰለሞን እንዲቀርብ ማድረግ ሳይችሉ “መቅረታቸው” ሁሌም ይገርመኛል።  

“የትግሬ 10ቱ ቃላት” ነዳፊው አሉላ ሰለሞን የሩዋንዳው “የካንጉራ” መጽሔት ዋና አዘጋጅ እንደነበረው “ሓሰን ንገዜ” የፍርድ ቤት ጥሪ ባይገጥመውም “ሓሰን ንገዜ” ግን ቀኑ ደርሶ ክስ ተመስርቶበት ዕድሜ ይፋትህ ዕስራት በይግባኝ ሰሚ ወደ 35 አመት ዝቅ ብሎለት ታስሮ ይገኛል። የሁቱ ነገድ የሆነው ይህ ሰው ከተከሰሰበት አንደኛው ነጥብ በፈረንጆች ዘመን በ1990 በጻፋው “Hutu Ten Commandments” በመባል የሚታወቀው “የሁቱ 10ቱ ቃላት” በማወጁ ነበር። የትግራይ ሚዲያ ሓውስ ተብሎ የሚታወቀው የፋሺሰት ፕሮፓጋንዳ የሚቀነቀንበት ጣቢያ መሪው “አሉላ ሰለሞን” ትግሬዎች ተግባራዊ እንዲያደርጓቸው ያስተላለፈው ጸረ አማራ፤ጸረ ኢትዮጵያ፤ ጸረ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ፤ ጸረ እስላም ጸረ ፕሮተስታንት፤ጸረ ካቶሊካዊት ተቋማት፤ ጸረ ኢትዮጵያዊያን ምግብ ቤቶችና ሱቅ ቤቶች እንዲሁም አማራ ያገቡ ባለትዳሮችና ፍቅረኞች በሚመለከት በሕዝብ መካካል ጸብና ጦርነት እንዲነሳ ያስተላላፋቸው ባለ 5 ርዕስ እና ባለ 5ንዑስ ዝርዝሮች የያዘ “በሕዝብና በጋብቻ ሰላምና አንድነትን የሚረብሽ የአሉላ ሰለሞን አዋጆች ከተጠቀሰው የሩዋንዳው ሰውየ ምንም ልዩነት የላቸውም በቁጥርም በዝርዝርም።`

 በ10ቱ ቃላቶቹ ላይ የአጻጻፍ ጥቂት ልዩነት ቢኖራቸው እንጂ ብዙዎቹ ተመሳሳይ እና ሁሉም በሚባል መልኩ የዘር ጥላቻ እና የማሕበረሰብ ግንኙነት፤ በትዳርና በንግድ ማሕበረሶቦች ግብይት ላይ እሳት ለኳሽ እና አፍራሽ አዋጆች የያዙ ናቸው

ሓሰን በሃይማኖቱ ‘እስላም’ ቢሆንም “ከሁቱ በቀር ሌላ ሃይማኖት የለኝም” የሚል ነበር። ይህ ኣባባል ደግሞ በትግሬ ምሁራን እንደ ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪ/ማርያም የመሳሰሉት “ከትግራዋይነት ሌላ ሃይማኖት የለኝም” ከሚሉት አክራሪ ብሔረተኞች የሚመሳሰል አደገኛ ሰው ነበር። ተመሳሳይነታቸው አልገረማችሁም?

የትግሬው ሓሰን ንገዜው “አሉላ ሰለሞንን”  << ትግራይና ኢትዮጵያ ምን እና ምን ናቸው? ከዚህ በህዋላስ ወዴት?” በሚል ርዕስ ቆይታ ላይ አሉላ ሰለሞንን ልክ እንደ አንጋፋ የታሪክና የፖለቲካ ሳይንቲሰት ቆጥሮ ስለታሪክ ስለ ፖለቲካ እንዲተነትን ጋብዞት “አጼ ቴድሮስ ትግሬ ናቸው” እስከማለት የደረሰ የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ ልጆች ሁሌም የተቃወሙት ውሸት ቴድሮስ ጸጋዬ የታሪክ መሃይሙ አሉላ “ቴድሮስ ትግሬ ናቸው” ሲል ዝምብሎ አለፈው (አፄ ቴዎድሮስ ከኦሮሞ ከትግሬ ወዘተ…ልጆች ወለዱ እንጂ የትግሬ ተወላጅ አይደሉም” ይህ ደግሞ በልጅ ልጆቻቸው የተነገረ ነው። ቋራ ስለተወለዱም “ቅማንት ናቸው እያለ ብዙ ሰው ሲዘባርቅ ሰምቶ አሉላም ሲዘባርቅ ነበር” ልክ የአክሱም ዘመነ መንግሥት ትግራይ ውስጥ ስለነበር እኛ ትግሬዎችም እዛው ስለተወለድን አክሱም የትግሬ ብቻ ነው እያሉ በወቅቱ /ትግራይ/የሚለው እንኳ ተሰምቶም ተጽፎም በማይታወቀው አክሱም “የኛ ብቻ ነው” እያሉ ቴድሮስ ጸጋዬ እና አሉላ ቁና ቁና ሲዋሹ ነበር ።

ቴድሮስ ጸጋየ ደግሞ ማሃይሙ አሉላ ሰለሞን ስለ ዮሐንስ እንግሊዞችን ጋብዞና መርቶ ቴድሮስን እና ለጃቸው እንዲሁም ባለቤታቸውና በአገሪቷ ቅርጽ ላይ ውድምት እንዲደርስ በባንዳነት አላገለገሉም እያሉ ስለትብብራቸውም ያደረጉት ውል እንደ ጀግንንት ተቆጥሮ ሲመጻደቁ ነበር።

 “መተባባር” ማለት “ባንዳነት” አይደለም የሚሉን እነ ቴድሮስ ጸጋየ “አዲስ የትግሬ አማርኛ የፈጠሩ ይመስለኛል፡” ሌላ ቀርቶ የራስ አሉላ ባንዳነትም እንኳ በጣሊያኖች የተዘገበው ተጽፎም ሊያምኑ የማይፈልጉ ብዙ ትግሬዎች አሉ። ከነሱ ውስጥ አንደኞቹ “ከመሃል ትግራይ በመወለዴ እጅግ እኮራለሁ” የሚለው “ተምቤንዬው” ቴድሮስ ጸጋዬ ነው። 

ጦርነት ባህላዊ ጫዋታችን ነው፤ ከሌሎች ጋር አትገበያዩ

ወደ እሚለን “ትግሬው ሓሰን ነገዜ ቃለ መጠይቅ” ልግባ ቴድሮስ ጸጋዬ እንዲያብራራለት የጠየቀው ጥያቄ (አልጠየቀውም ላለመባል ማለት ነው) ቴድሮሰ ፀጋዬ እንዲህ ይላል፡

<< ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በኋላ የተናገርካቸው ንግግሮች በከፍተኛ ደረጃ የቅስቀሳ “ጥሬ ዕቃ” ሆነው ጥቅም ላይ ሲውሉ ተመልክቻለሁ። የተጋባችሁ ካላችሁ ተፋቱ፤ ያልተጋባችሁ ካላችሁም አትጋቡ የሚሉ አስተያየቶች ብዙ ለቅስቀሳ ውለው ተመለክቻለሁ። እነዚህ አባባሎች ከምንም ጋር ሳናያይዛቸው ኢሞረላዊ እና “ስሕተት” አይደሉም ወይ? በነዚያ ንግግሮች ምክንያት ፤እነዚያ ቅስቀሳዎች ከተካሄዱ ሰዎችን ከተቀረው ኢትዮጵያ ክፍል አምጥቶ በማዝመት ተጋሩ እንዲገድሉ በመሆኑ ትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ ችግር ፈጥሬ ይሆናል የሚል ልብህ ውስጥ አለ? >> ሲል ይጠይቀዋል።

አስገራሚው ቴድሮሰ ፀጋዬ ግን በታወጀባቸው አማራ ማሕበረሰቦች ህይወትና ጋብቻ ግን ችግር ፈጥሬ ይሆናል የሚል ልብህ ውስጥ አለ ወይ? ብሎ አልጠየቀውም ፤ ቴድሮስ ያሳሰበው በዚህ ተንተርሶ በትግሬዎች ላይ የደረሰው ችግር ብቻ ነበር ትኩረቱና ልቡ! ያውም አዋጁ “ስሕተት” በሚል ቀላል ስሕተት አድርጎ መሳሉ ይገርማል።

አሉላ ሲመልስ ደግሞ እንዲህ ይላል፡

<< መልካም። አመሰግናለሁ፡ መብራራት ስላላበት ለማብራራት ይህ ዕድል ሰለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ።” በማለት ስለ ትግሬ ባህላዊ ጨዋታ ነው ስላለው የዘበራረቀውን ማምለጫውን ልተውና ስለ ጻፋቸው 10ቱ ቃላቶቹን እንዲህ ይመልሳል፡

< በወቅቱ ትግራይ ውስጥ ሚዲያ ተዘግቶ ስለነበር አዲስ አበባ ላይ ሉ የትግራይ ተወላጆች የሚደርስባቸው ዛቻና የጥላቻ ንግግር በየቀኑ ነበር የሚደርሰኝ፤ ከሌላ ማንነት ካላቸው ጋር የተጋቡ በየትዳሩ ሳይቀር በተለይ ከአማራ ጋር የተጋቡ የትግራይ ተወላጆች “እንዲህ እያለኝ ነው፤ካንቺ ነው የምጀምረው፤ልናጠፋችሁ ነው እያሉን ነው” የምትል እህት ብዙ መልዕክቶች ይደርሱኝ ስለነበር፡ ይህ ነገር ወደ ጀኖሳይ እየተቀራራበ እንደሆነ ወደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር እየቀረብኩ በተለይ ፍራንስ 24 ሚዲያ ቀርቤ ይኼ ‘ጀነሳይድ” አንደሆነ አስረድቻለሁ። ሌላ ቀርቶ ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ ከመከላከያ፤ ከፖሊስ ያሉት ትግሬዎች አንተም ታውቀዋለህ “አንድ ባንድ” ተለቅመው ነው አንዲወጡ የተደረጉት።በያንዳንዱ ቤት ሊደርስ የነበረ ሰቀቀን ከምትገምተው በላይ ነበር። እና ሕጋዊ ከለላ በሚያገኙበት አካባቢዎች ትግሬዎች ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንዳለባቸው ነው (የቀሰቀስኩት?) ። መጻህፍቶችን አነብ ነበር፤ የተለያዩ ጥቁር አሜሪካኖች ትግል አየሁኝ ፤የማልካም ኤክስ የማርቲን ሉተር ኪንግ ካነበብኩ በሓላ የትግራይ ሕዝብ በተመሳሳይ ትግል ማድረግ እንዳለበት “ጡቁሮች” ከጨፍጫፊዎቻችን ጋር ጸሎት አናደርግም ብለው የራሳቸው ቤተጸሎት እንደሰሩት ሁሉ እኔም ከዚያ ተመክሮ ተነስቼ…..ጦርነቱን የደገፉ ወይንም አይተው እንዳላዩ በትግራይ ጀነሳይደ ሲፈጸም ዝም ያሉ፤ በጭፍቸፋው ላይ ሲሳተፉ ……. የነበሩ ለገዳዮቹ (ዝም ያሉትም ይላል፤ ፖለቲካው ያልገባቸው/ ምን-እየሆነ እንደሆነ ያማያውቁትንም ፤ ከዚህም ከዚያም የሌሉትንም ነው የአሉላ አዋጅ አብሮ መላው ኢትዮጵያዊያን እያነጣጠረ ያለው)የኢኮኖሚ ፈርጣማ ክንድ እንዲኖራቸው መፍቀድ የለበትም በሚል ነው ያደረግኩት……።  “ጋብቻ” የምተለዋ ቃል፤ ሰዎች አትኩረዋል፤ ጓደኝነትም ጭምር አንስቻለሁ። ቴድሮስ ቤተሰቦችህ ጭምር ሲሰቃዩ ቤተሰቦችህ ያሉበትን ሁኔታ የማይጠይቅ ጓደኛ ነው ብሎ ተደላድሎ የሚቀጥል ሰው ካለ ልታሳዩኝ ይገባል። ከዚህ ሰው ጋር ወዳጅነት መቀጠል አያስፈልገኝም የማለት መብት አለህ።” እያለ እራሱን ከወንጀል ነጻ ለማድረግ ሲመጻደቅ “ሆን ብሎ ተሸብቦ የነበረው የቴድሮሰ ምላስ ድንገት አፈትልኮት እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል

<< ግለሰባዊና… ማሕበረሰባዊ ግንኙት ምርጫ ገብቶ በዛ ደረጃ “ኢቬሲቭ” (ማግለል/ማራቅ/ ለማት ይመስለኛል እንግሊዝኛውን ሲጠቀም ቴድሮስ) ማድረግ ከሞራላዊ ከማሕበራዊ ዕይታ አንጻር ነው ጥያቄው የነተነሳው እና ባጭሩ ንገረኝ እና ወደ ሌላ ርዕስ እንገባለን። >> የሚል ጠንካራ ጥያቄ ከመጠየቅ ይልቅና ከመቀጠል ይልቅ ወደ ሌላ ርዕስ እንግባ ይለዋል።ይገርማል!

“ካቡጋው” አሉላ ለ10ቱ ቃላቶቹ ለማወጅ ምክንያቶቹን እንመልከታቸው፡-

 << 1-ከአማራ ጋር የተጋቡ የትግራይ ተወላጆች “እንዲህ እያለኝ ነው፤ካንቺ ነው የምጀምረው፤ልናጠፋችሁ ነው እያሉን ነው” የምትል እህት ብዙ መልዕክቶች ይደርሱኝ ስለነበር፡ ይህ ነገር ወደ ጀኖሳይ እየተቀራራበ እንደሆነ ወደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር እየቀረብኩ በተለይ ፍራንስ 24 ሚዲያ ቀርቤ ይኼ ‘ጀነሳይድ” አንደሆነ አስረድቻለሁ እያለ በሚገርም ሁኔታ ሳቅ እያለ እያሾፈ እንዲህ ይላል-

ማሕበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ኢኮኒሚያዊ” የሚባሉ እኮ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ “ጀነሳይድ ነውጀነሳይድ ከባድ ወንጀል ነው እኔ ለኢትዮጵያዊያን ያቀረብኩላቸው ቀላል ነበር፤ ጀነሳይዱ ለተሳተፉ ብቻ ሳይሆን “ዝም ላሉ ጭምር ነው” መልዕከቱን ያስተላለፍኩትኢትዮጵያዊያን የስብዕና ልዕልና የላቸውም… >> እያለ ሲያሾፍ ቴድሮስ ምንም ሳይል በፈገግታ ወደ ሌላ ጥያቄ ሸኘው።

የማርቲን ሉተር ኪንግ ትግል አንብቤ ከዚያው የቀሰምኩት የትግል ቀመር ነው የሚለን ጋብቻ የማፍረስ አዋጁ አሉላ እንዴት እንደተረጎመው እንመለከት።  << ባሌ እንዲህ እያለኝ ነው የምትል እህት ደውላ ስለነገረቺው” አሉላ መላውን ምስኪን ሰላማዊ ኑሮ የሚገፉትን አማራና ትግሬዎች ብቻ ሳይሆን ዝምብለው ኑሮአቸውን የሚገፉ ልጆች የወለዱ ሁኔታውን በቅጡ መርምረው ሊረዱ የማይችሉ ፤ፖለቲካ ያማያውቁ አማራዎች ከዚህም ከዚያም የሌሉበትንም ጭምር አብሮ የሚደፈጥጥ “ልጆቻቻው ያለ ሁለት ወላጆች ፍቅርና እንክብካቤ’ ሳያገኙ ተለያይተው እንዲያድጉ የፍቺ ጥሪ እንዲፈጽሙ ጥሪ አደረገ (ግድያም እስራትም የሚጨምር ቢሆን ኖሮ አሉላ ዝም ባሉትንም ጭምር ያንን ያውጅ ነበር ማለት ነው) ።

ይህ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ቢሆን ኖሮ የሚሰጠው መልስ ይህ ከሆነ፤ በህግ ሙያ የተማራችሁ ኢትዮጵያዊያን በዚህ የምትሉት ነገር ካለ እስኪ እንስማ (መቸም የዝሆን ጀሮ ስላላችሁ በዚህ ጉዳይ የምትሉት ነገር ይኖራል ብየ የሚል ሕልም ባይኖረኝም) እስኪ ዕድሉን እንስጣችሁ።

አሉላም ሆነ ቴድሮስ ይህንን የወንጀል ተጠያቂነት ካለ በግለሰቦች ላይ ብቻ ሊወሰድ እንደሚችል እውነታ ላይ በመመስረ እንጂ የጋራ ቅጣት (ኮሌክቲቭ ፓኒሽመንት) የተከለከለ ነው እያሉ ሁለቱም ጠረጴዛ እየደበደቡ የሚከራከሩ ናቸው። በነቴድሮስ ጸጋዬ እና አሉላ” “ኮሌክቲቭ ፓኒሽመንት” የማይሰራው አማራው ላይ ሲታወጅ ሳይሆን ያ የሚሰራው ለትግሬው ብቻ ሲሆን ነው። አማራው ላይ ሲደርስ ግን ፖለቲካው ያልገባቸው ዝም ብለው ትዳራቸውን የሚያራምዱ ልጆች የወለዱ ሰላማዊያን ሁሉ ያለምሕረት እንደሚመለከት ዛሬም ሳይሸማቀቅ ደግሞታል

“እገሌ የተባለች ስልክ ደውላ አማራው ባሌ እንዲህ እያለኝ ነው” ስላለቺኝ የፍች አዋጅ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅሪቤአለሁ፡ የሚለው አሉላ “የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜም” ስላደረገው ጥሪ ተጠይቆ ያቀረበው ምክንያት በሚገርም ሁኔታ አሉላ የመለሰው ዐይነት ነበር የደገመው (ተመሳሳይነታቸው የሚገርም ነው!!) ቴድሮስ ድንገት ከምላሱ አምልጣው አሉላን የጠየቀውን ትክክልኛ ጥያቄ ሳይገፋበት ባጭሩ ቀጭቶት ወደ ሌላ ጥያቄ መራው። ለምን?

አሁንም አማራውን በሚመለከት ወደ ሁለተኛው ምክንያቱ ልግባ፤

እንዲህ ይላል፡-

 < ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ያሉት ትግሬዎች አንተም ታውቀዋለህ “አንድ ባንድ” ተለቅመው ነው አንዲወጡ የተደረጉት።በያንዳንዱ ቤት ሊደርስ የነበረ ሰቀቀን ከምትገምተው በላይ ነበር። እና ሕጋዊ ከለላ በሚየገኙበት አካባቢዎች ትግሬዎች ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንዳለባቸው ነው ያስተላለፍኩት መልእክት >> ይላል አማራን ያገቡ ትግሬዎች ፍቺ ማድረግ እንዳለባቸው የሰጠው አንዱ ምክንያት ይህ ነው

ከፌደራል መ/ቤቶች ከአየር መንገድ፤ከመከላከያ፤ከፖሊስ ውስጥ ያሉ ትግሬዎች “አንድ ባንድ” ተለቅመው እንዲወጡ ሲደረግ ፤ይህ ወንጀል እንዲፈጸም ያዘዘው አሉላ እየነገረን ያለው ፈጻሚዎቹ “አማራዎች እና አገሪቱ የሚመራው የአማራ መንግሥት” እንደሆነ ነው ያለ ምንም መሸማቀቅና የታሪክ ፍራቻ እየነገረን ያለው

በዚህ የፈጠራ ውንጀላ በትዳር ላይ ያሉ ሰላማዊያን ሰዎች እንዲፋቱ በጽሑፍ እና በቴ/ቪዥን ሲታወጅ ያፋታቸው ሰዎች በቅጡ ባይታወቅም፤ በፍርድ ቤት ዳኛ ብየና ግን የሚያስከስስ አንድን ማሕበረ ቤተሰብ ከሌለው ማሕበረ ቤተሰብ በዘር ላማናከከስ የተወጠነ የፈጠራ/የውሸት/ ሽፋን መሆኑን የሕግ አዋቂዎች አይስቱትም ብያ እገምታለሁ። ያለ መታደል ሆኖ የሕግ ምሁራኖቻችን በዚህ ሁኔታ አንስተው ሲወያዩ አላየሁም። ካሉም እኔ እንደማደርገው መጥተው ያስነብቡን።  “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” አዋጅ ብዙ ማለት ቢቻልም አዋጆቹን ለታሪክ የዘገብኩዋው ላስጨብጣችሁ

“ የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጅ እና ምላስ ብቻ የሆነው ተግባረቢሱ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)Tuesday, December 08, 2020

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2020/12/ethiopian-semay-sunday-december-06-2020.html

ብየ የዘገብኳቸው የአሉላ 10ቱ ዘረኛ አዋጆች አንዳንዶቹን ላስታውሳችሁና ልሰናበት

3- አማራ እና የእግዚአብሔር ሰላምታን በሚመለከት።

 

አማራዎች “ወንድሞቼ ሰላም እንባባል እንጂ ወንድማማቾች እኮ ነን  ምናምን ብለው “ሰላም” ቢሏችሁ ሰላም እንዳትሏቸው ከአማራ ጋር ጭራሽ እንዳታነጋግሩዋቸው! አማራ የሚባል “ሱፐር ማርኬት፤ ሞል ፤ ሌላም ሌላ ቦታ ስታገኝዋቸው ሰላም አትበሏቸው። ወዳጅነት ኖሯችሁ፤ አብራችሁ ስተበሉ ስትጠጡ የነበራችሁ ሁሉ “አቁሙ!” ጦርነቱ ሳይደግፍ ሳይለንት ሆኖ” (ዝም ካለም)አማራ ነውና አቁም! የትግራይ ሕዝብ ሲበደል አሳዝኖኛል ስትል ስላልሰማሁህ ጠላት ነህ ብላችሁ መልሱለት። ወዳጅነታችሁን አብሮ መብላት መጠጣትን አቁሙ። ስለትግራይ መበደል ምንም ያልተነፈሰ ሰው “ከዚህ ሰው ጋር በጋራ አብራችሁ “እንጀራ በሳህን” የምትበሉ የምትጠጡ ከሆነ ያ የምትመገቡት ምግብ ጸር ሆኖ ይገላችሗልየምትጠጡትም የወንድሞቻችሁ ደም ማለት ነውስለዚህ በተለምዶ ተዋልደናል ትዳር መስርተናል ምናምን የሚባል “ዝበዝንኬ” ዛሬ አይሰራም።

4- ኢትዮጵያ ምናምን እያለች እራስዋን በኢትዮጵያ የምትሸሽግ ከሆነ

 

ሀ-ወዲያ በሏት! ከቤታችሁ አባርሯት ወይንም አባርሩት፤

 

ለ-ግንኙነታችሁ በጣጥሱት!!

 

ሐ-ጓደኝነት ከሆነም (ወዳጅነታችሁን) በጣጥሱት፤

 

መ- ትዳር ከሆነ አፍርሱት፤ ማሕበራዊ ግንኙት ከሆነ በሙሉ በጣጥሳችሁ ወደ ቆሻሻ መጣያ ጣሉት!

 ሠ-ባጭሩ እንዲሰማቸው ማሳየት አለባችሁ!

(2)- “ቢዝነስ” በሚመለከት የሚከተለው ጥሪ አቀርባለሁ፤

የእንጀራ ቤቶች፤ ምግብ ቤቶች የሥጋ ቤቶች በጠቅላላ የኢትዮጵያዊያን ንግድ ተቋማት በሚባሉት ሁሉም ቦታ  ግብይት እንዳታደርጉ!! በገንዘብ እቅማቸውን ማጠናከር ብቻ ሳይሆን መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ። ይፈጅዋችኋልም። እነዚህ ጨካኞች ናቸው!! ብምትመገቡዋቸው ምግቦች ውስጥ መርዝ አስገብተው እንዳይፈጅዋችሁ ተጠንቀቁ። በመርዝ ተመርዛችሁ ከመሞት ለመዳን ከፈለጋችሁ መፍትሄው ትግሬዎችኤርትራኖች እና በአካባቢያችሁ ባሉት የኦሮሞ ንግድ ቤቶች/ቢዝነስ/ ካሉ ከነሱ ጋር ተገበያዩ። በተለይ ደግሞ ያቺ ልሙጥ ባንዴራ የሰቀሉ ወይንም በንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ ካያችሁ እንዳትገበያዩ ሌላ ቀርቶ ቅመምም ጭምር እንዳትገዙ

ኢትዮጵያ የምትባል ጠላታችን ስለሆነች በኢትዮጵያ የሚጠራ ወይንም ኢትዮጵያ የሚባል ስም ያለባቸው ማሕበራት እንዳትገቡ። መረዳጃ ማሕበር ይሁን ምንም ይሁን “ኢትዮጵያ” የሚል ካለበት ከነዚህ ማሕበረሰቦች ጋር እንዳትቀላቀሉ። በሙሉ አግልሏቸው። ገንዘባችሁ በትግሬዎች ብቻ “Spend” አድርጉ። አንዳንዱ “አሉላ ሰለሞን” “ራዲካል” ሆነ ምናምን ሊሉዋችሁ ይችላሉ። ኖ! እስኪያማቸው ድረስ መነገር አለበት። ማወቅ አለባቸው። ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችን አይወዱህም እና ባጭሩ ከነሱ እራስክን ነጥል።”

እያለ ያወጃቸው ለዘር ጥላቻ እና ብጥብጥ በር የሚከፍት አበራታች ዩነበሩት ዛሬ እስር ቤት ላይ የሚገኙት የሩዋንዳ ሁቱ የሚዲያ ዘረኞች የ ‘አር ቲ ኤል ኤም’ ዋናው የራዲዮ አዘጋጅ “ፌሊስ ካቡጋ” እና ‘የካንጉራ’ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የነበረው “ሐሰን ንገዜ” የትግሬው ዘረኛ ጸረ አማራው የ10ቱ ቃላት አዋጅ አሰራጭ አሉላ ሰለሞን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።

ጽሑፉ ታሪካዊ ሰነድ ነውና ተቀባበሉት

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Saturday, August 15, 2026

የአሉላ ሰለሞን "የውሻ ፊሽካ" (dog whistle) በአማራ ሕዝብ ላይ ያስተጋባው ዛቻ እና የሞት ቲኬት አስተናጋጅነት ክፈል 1 ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/13/22


የአሉላ ሰለሞን "የውሻ ፊሽካ" (dog whistle) በአማራ ሕዝብ ላይ ያስተጋባው ዛቻ እና የሞት ቲኬት አስተናጋጅነት

ክፈል 1

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/13/22

አሉላ ሰለሞን በአምሐራ ሕዝብ ላይ ከፈሩን የነክሰበት የዛቻ ንግግሩ

ትግሉን እና ተውናዮቹን  ለማስተካከል የተቻልንን ያህል ብናስተምርም ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ መሻሻል ባለማሳየቱ ትርፉ ድካም እየሆነ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ፋኖ የተባለውም የባሰ መንደርተኛ ሆኖ የሕዝቡን መከራ እራዘመ በማየቴ “ከማስተማርና ከመተቸት” ለመቆጠብ ስፈልግ አንዳንድ ነገሮች ፍጥጥ ያሉ ውሸቶችና ድርቅና የሞላበት ክሕደት የሚጫወቱ የጥላቻ ተዋናያን በኩራት ሲመጡ ማየት አላስችል ይለኝ እና እንደገና ወደ ክርከሩ እመለሳለሁ። ለዚህም ሰሞኑን የሆነውን መንሻየ ነው፡

መጀመሪያ አሜሪካ ውስጥ ያሉትንም ይሁኑ በሌሎች ሃገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሕግ ባለሞያዎች የወያኔዎቹ ባለውለታ “አሉላ ሰለሞንም” ይሁን በሕዝብ ላይ ብዙ ግፍ የፈጸሙ የወያኔ ባለሥልጣናት በምቾት ዓለም በኩራትና በድሎት ሲኖሩ የኛዎቹ የሕግ ምሑራን እነዚህን ግፈኞች በሕግ ፊት ባለማቆማቸው የሕግ መሁራኖቻችን “የቁም ሞታቸው እንደሞቱ” እቆጥረዋለሁ።

ለዚህም አሉላ ሰለሞን የተባለው ግማሽ ቅማንት፤ ግማሽ ትግሬ ነኝ የሚል (በራሱ ፌስቡክ እንደገለጸው) ካሁን በፊት የሩዋንዳዎቹ የሁቱ አሰርቱ ቃላቶች የሚመሳሰሉትን “በአማራ” እና በመላው “የኢትዮጵያ ሕዝብ” ላይ ያወጀው የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ አዋጆች ሰሞኑን ባንድ ሚዲያ ቀርቦ “እነዚያ ያስተላለፍኩዋቸው ቅስቀሳዎች በመቀስቀሴ እኮራለሁ” በማለት በኩራት እራሱን ሲኮፍስ ሰምቸው፤ ለኩራቱና ለፉለላው የቁም ሙት የሞቱትን የሕግ ምሁራኖቻችን ደካማነት በማየቱ ቢሆንም ፤ እኛ የዚህን የጥላቻ ሰካራም አጉል መኩራራቱን ለማጋለጥ ለታሪክ መዝገብ ምንነቱን እያስመዘገብን እናልፋለን። ወደ ትንተና መመለሴም መነሻየ ይህ ነው። በክፍል ሁለት የኮራባቸው አዋጆቹ በሕግ ፊት ምን እንደሚመስሉ እመለስበታለሁ ፤ ለዛሬ ክፍል 1 ይህንን እንመልከት።

ቪዲዮው ላይ የምታደምጡት የአሉላ ሰለሞን “የ100 አመት” የአማራ ሕዝብ (በቃሉ አነጋገር የተጠቀመው ቃል ነፍጠኛ) የጨፍጫፊነት እና  የጨቋኝነት ታሪክ የፈጠራ ውሸትና ቅስቀሳ ቢሆንም ፤ በሕግ ትንታኔ የፈጠራው ትርክት The "Lie as a Catalyst"፡- አነቃቂ ኃይል (catalyst) ሆኖ ትርክቶቹ ራሳቸው በሂደቱ ውስጥ ሳይለወጡ ወይም ሳይሟጠጡ፣ በቡድኖች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን፣በጠቀሰው ቡድን/ሕዝብ ማን እንደሆነ በመለየት ትርከቱ አነቃቂ ሞተር ሆኖ ጥቃቶችን ያፋጥናሉ ወይንም ያስነሳሉ።

 እንደ አሉላ ሰለሞን የመሳሰሉ የጥላቻ እና የውሸት ትርክት ሰባኪዎች በአማራ ሕዝብ ላይ ጥቃት እንዲደርስ "እንደ ማነሳሻ የሚያገለግል The "Lie as a Catalyst"፡- ውሸት " የሚጠቀሙበት ቃል የአማራ ሕዝብ “በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ” 100 አመት ከፍተኛ ጭፍጨፋ/ግፍ/ጭቆና እንደፈጸመ እና ግፍ የተፈጸምባቸው ነገዶችም ጠባሳውን በማስታወስ በአማራን ሕዝብ ላይ ለመበቀል ለጥቃት ጉጉት ከንፈራቸው እየነከሱ እንዳሉ ይናገራል።

 በቪዲዮው ላይ የምናደምጠው የሰለሞን አሉላም ሆነ የባልደረባው (ማሃይምዋ ሴት) የፈጠራ ትረካዎች  እየነገሩን ያሉት “በታሪክ የ100 አመት ጭፍጨፋ በሌሎች ነገዶች እና በእኛ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጸማችሁብን” ቅሰቀሳ የሚነግረን ነገር “የአትሮሶሲቲ ፕሮፓጋንዳ” ወይም "የሐሰት ባንዲራ ማውለብለብያ” false flag narratives" ትረካዎች እየተባሉ የሚጠሩትን ነው እያሰራጨ ያለው። 

የሕግ መጻሕፍት (እንዳነበብኩት) የሚነግሩን አመላካቺነታቸው “The "Lie as a Catalyst"፡- has frequently been used as a psychological trigger to justify preemptive violence or retaliation in real-world conflicts.” ይህ ማለት የእነ አሉላ ሰለሞን ፤ የእነ ኦነጎች (አብያ አሕመድ ንግግር ጨምሮ) የእነ ወያኔዎች ንግግር እና ማኒፌስቶ በእውነተኛ ግጭቶች ውስጥ እንዲህ ያሉ የውሸት ትረካዎች እና አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር ወይም አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደ ስነ-ልቦናዊ ማነሳሻነት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውሏል፡ ይላሉ። የአሉላ የፈጠራ የ100 አመት ትርክት የሚያሳየን በሕግ ትንተና ይህንን ያመላክታል።

ነፍጠኛ (Coded Language) አሉላ ሰለሞን እና እሱ የሚያመልከው የወያኔ ማኒስቶፌስቶ የአማራን ሕዝብ በCoded Language በምስጢራዊ ቋንቋ ነፍጠኛ ሲሉ ይጠሩታል።ይህ "የውሻ ፊሽካ" (dog whistle) ይባላል።

ይህንንም ጥቃት ለመሰንዘር ወይም አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜ እየጠበቅንላችሁ እንጂ የመቶ አመት ጥቃት በአጸፋዊ እርምጃ ለመመለስ ዝግጁ ነን። እያለ ነው “በራሱ አንደበት”። አሉላ እና መሰሎቹ በአማራ ሕዝብ ላይ ከንፍሩን እየነከሰ እንዳለ ሳይሸሽግ ለዓለም ሲያውጅ  በሕግ ትንታኔ ሕዝብንና ከትግሬዎች ጋር በተጋቡ አምሐራ ባለተዳሮችን ከንፈሩን በመምጠጥ/በመንከስ ለጥቃትና አጸፋዊ እርምጃ እያነሳሳ እንዳለ ሳይሰጋ ያውም እንደ ኩራት እንድሚቆጥረው ይናገራል።+ለዚህም ነበር አምሐራ ጋር ይተጋባችሁ ባለትዳሮች አሁኑኑ ትሎ ተፋቱ ሲል ያወጀው።

ነፈጠኞች ቀናችሁን ጠብቁ እያለ ከንፈሩን ለጥቃት ዘግጅት መጠበቁ ነፍጠኛ እያለ የሚጠራውን የአምሐራ ሕዝብን  እንደሚጠላ እና ለብቀላውንም ወቅት እየጠበቀላቸው እንድሆነ ሲገለጽ የጥላቻ ንግግር የዛቻ መስፈርቶች እና የያዙት ትርጉሞች የሚያስከተሉት ጉዳቶች እየነገረን ነው፡- ፤እዚህም ነው አሉላ ሰለሞን አመች ወቅት እየጠበቀና መላውን የአማራ ሕዝብ ለማጥቃት ከንፈሩን እየነከሰ መሆኑን እና ወቅታችሁን ጠብቁ እያለ ያለው አብዛኛዎቹ የዛቻ ንግግሮቹ በህግ ማዕቀፎች ውስጥ የተጠቃለሉ እና የጥላቻና የበቀላ ንግግሮች ናቸው። እንደምታስታወሱት የሩዋንዳ ዕልቂት ያፋጠነው ከንፍሩን ሲመጥ የነበረ ሕዝብ ወቅት ጠብቆ “የዛቻ ንግግሩን ወደ ግብር ለወጠው”።

አሉላ ሰለሞን በተለያዩ ወቅቶች ፣በሃገር፤ በሰንደቅ ዓላማ ፤ በነገድ በሃይማኖት፣ ልጆች ወልደው በሰላም ሲኖሩ በነበሩት ባለትዳሮች (በጋብቻ ላይ) የሚያጠቁ ንግግሮች ሰብአዊ ክብርን የሚነኩ (ኮዲንግ) እና ሰላም የሚነሱ ንግግሮችን ሲናገር ሰምተናል።

በአምሐራ ሕዝብ ላይ በሐሰት የተረከው የ100 አመት ጨፍጫፊነት/ግፍ ፈጻሚነት እና ነፍጠኛ የሚሉ ሁለቱ የአሉላ ንግግሮቹ በሕግ ትንተና የጥቃት አፋጣኝ ቤንዚኖች  (Catalyst) ናቸው። የአቀጣጣይ ቤንዚኖቹ ውጤት እንዴት እንደሚሰራ እንመልከት፤

የሀሰት ትረካዎች ሚና፡ 

ጉዳት ወይም ጭቆና እንደደረሰ የሚገልጹ ሀሰተኛ ክሶችን መፍጠር ወይም እንደ መሳሪያ መጠቀም፤ በተከሰሰው ቡድን ላይ ጥልቅ ጥላቻን፣ ከራስ ቡድን ውጭ ላሉት ላይ ጠላትነትን እና ስር የሰደደ አድልዎትን ለማራመድ እንደ ሰበብ ሊያገለግል ይችላል። ይላል ያንበብኩት የሕግ አተናተን። ከዚህ የተሻለ ካለም የሕግ መሁራን መልስ እጠብቃለሁ። በሌላ አገላለጽ The "Lie as a Catalyst": Faking narratives of severe repression (often referred to historically as "atrocity propaganda" or false flag narratives) has frequently been used as a psychological trigger to justify preemptive violence or retaliation in real-world conflicts. (እንደ ማነሳሻ የሚያገለግል ውሸት"፡- ከፍተኛ ጭቆና እንደተፈጸመ የሚያሳዩ የፈጠራ ትረካዎችን (በታሪክ "የጭካኔ ድርጊት ፕሮፓጋንዳ" ወይም "የሐሰት ባንዲራ" ትረካዎች እየተባሉ የሚጠሩትን) ማሰራጨት፣ በእውነተኛ ግጭቶች ውስጥ አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር ወይም አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደ ስነ-ልቦናዊ ማነሳሻነት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ውሏል።) የላሉ የጥላቻ ትርጉም ተንታኞች።

ስውር ቋንቋን በመጠቀም

 (ኮዲንግ/ ነፍጠኛ/የሚል ቅጽል ስም መስጠትን) የተወሰነ ቡድንን የሚያነጣጥር «የውሻ ፉጮት» "ዶግ ዊስል" (dog whistle) ምን ይመስላል? "ተዘዋዋሪ የጥላቻ ንግግር" (implicit hate speech) ለማስተላለፍ የሚረዳ ስልት ነው።

Hidden Meaning: A targeted group hears the secret, biased code- 

ተናጋሪው የሚጠቀምባቸው ቃላቶች (ነፍጠኛ) ለሰፊው ሕዝብ ምንም ጉዳት የሌላቸው የሚመስሉ ተራ ቃላት ቢመስሉም ቃላቶቹ ለታለመው ግብ የተለየ እና ስውር የሆነ ነጣይ አዘል መልእክት ለማስተላለፍ የመጠቀም ስልት ነው።

ሆኖም የቃላቱ አጠቃቀም ስልት Hidden Meaning: ሕቡእ (ሽፋን) ያለው ድምጸት ሰላለው ተራ ሰሚው ቀለል አድርጎ ሊተረጉመው ቢችልም (አልፎም የሕዝቡን ሕጋዊ መጥሪያ ስም ተረስቶ ከጥላቻ አራጋቢዎች የሰማውን ኮድ “ነፍጥኛ” የሚለው ስም ዘላቂ /ቅቡል/ ስም እንደሆነ አድርጎ ሊጠቀመው ይችላል)፤ በድብቅ ቃል የተጠራው የአምሐራ ሕዝብ/ነፈጠኛ) የሚለው ቃል ግን (The targeted group hears the secret, biased code) ግን ትርጉሙ ምን ለማለት እንደተፈለገ የተሰነዘረበት የጥላቻ ቃል እና መስጢር ለምን ግብ ሊውል  እንደተፈለገ ይገባዋል።

ባጨሩ

Ordinary Words:

Speakers/hate groups use everyday terms that do not sound bad on their own.

ተራ ቃላት፡

(የጥላቻ ቀስቃሽ ተናጋሪዎች የሚጠቀኑባቸው ቃላቶች በራሳቸው መጥፎ ስሜት የማይፈጥሩ የሚመስሉ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚዘወተሩ ቃላትን ይጠቀማሉ።) ለምሳሌ ነፍጠኛ የሚለው ቃል በዕለት ተዕለት  የሚዘወተር ቃል ቢሆንም ክ1981 (1993 በፈረንጅ ዘመን) ግን ምን ትርጉም እንዳለው እያደመጥን ነው።

Deniability: The speaker can claim they meant something else if people get upset.  ሰዎች ከተበሳጩ፣ የተጠቀመበት ቃል ሁለት ትርጉም ሊኖሮው ሰለሚችል ተናጋሪው እንዲህ ማለት አርበኛነትን የሚገልጽ ቃል ነው ወይንም እንዲህ ለማለት የፈለግኩት ሌላ ነገር ለማለት እንደነበር ነው ብለው ክሕደት ውስጥ ይገባሉ።ለዚህ ነው ሁለት ትርጉም ያለው ቃል መረጠው ዘረኞች ጥላቻችወን ለማስተላለፍ የሚጠቀሙበት። አሉላ ሰለሞን ግን ካጠቃቀሙ ሊያመልጥ አይችልም (ከንፈር እየመጠጠና እና እየነከሰ የምሐራን ሕዝብ ለመበቀል ወቅት እየጠበቀ እንደሆን ነው ከአራት አመት በፊት የነገረን)።

ይህ የሰሞኑ የ አሉላ ሰለሞን አላልኩም ክሕደት ወይንም እኮራበታለሁ አባባል፤ በእርሱ ብቻ አለተጀመረም፡ ለምሳሌ የሑቱ 10ቱ ቃላት ተብሎ የሚታወቀው የጥላቻ ቅሰቀሳ አዋጅ ያረቀቀው የሩዋንዳው ሓሰን ንገዜ በተመሳሳይ በወደጆቹ ሚዲያ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ሲደረግበት ሙልጭ አድርጎ በመካድ የተጻፉት አዋጆች እያጣመመ “ሰዎች በመሰላቸው” ሊያቀርቡት ችለው ይሆናል አንድም ማስረጃ በጽሑፌ ውስጥ ቱትሲዎቹ እንደሚሉት አላሳፈርኩም” እያለ እንደ አሉላ ሰለሞን ሲክድ ሰምተነዋል። አሉላ እና የሁቱ ሩዋንዳው ሐስን በስምና በአገር የሌላ አገር ተወላጆች መሆናቸውን ካልሆነ በስተቀር “የትግሬው ሓሰን ንገዜ” እና “የሩዋንዳው ሐሰን ንገዜ” የባህሪ ተመሳሳይነት ይገርማል።

ፍርድ ቤቱ ውስጥም ሲጠየቅ እንደ አሉላ እያጭበረበረ ሲመልስና ጣልቃ እየገባ ሄግ ፍርድቤቱ ሲረብሽ “የመሃል ዳኛዋ” (ፈረንጅ ነች) << አርፈህ ተቀመጥ ካልሆነ አስወጣሃለሁ!!>> ስትለው ነበር። ውጭ አገር የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን የሕግ ምሁራን እና በየ ኤምባሲው የሚርመጠመጠው የኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብና የሕግ ባለሞያዎች እንዲህ ያለች ዳኛ ዘንድ አሉላ ሰለሞን እንዲቀርብ ማድረግ ሳይችሉ “መቅረታቸው” ሁሌም ይገርመኛል።  

ለዚህም ነው አሉላ ሰለሞን ሰሞኑን፤ በተናገርኩት እኮራለሁ! ከሳሾቼ የት አሉ? ይምጡና ይክሰሱኛ! ማንም ፍርድ ቤት ቢያቀርበኝ ደስታውን አልችለውም\ ሲል በጥላቻ ንግግሩ ሲኩራራ መስማት ያስታወሰኝ ነገር ወያኔው ብስራት አማረ ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ  የአማራ ጥላቻውን የገለጸበትን መጽሐፍ ለማስመረቅ ሄዶ በነበረበት ወቅት ፤ «ወደ አሜሪካ ከተመለሰ ጫካ ውስጥ 17 አመት አማራ ላይ የፈጸመው ግፍ እና መሰል ወንጀሎች አስመለከተን ወደ ሕግ እናቀርበዋለን”» ብለው በዙ ሕዝብ ደስ ብሎት እነ ጠበቃ አበበ ገላው እና በርካቶች  ሲያጋግሉት ቆይተው፤ ብስራት አማረ ወደ ‘ኦሃዮ’ አሜሪካ ሲመለስ ግን ‘ገዛ ተጋሩ” ተብሎ ሲጠራ በነበረው የጥላቻ ሚዲያ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ሰለ ጉዳዩ ሲያብራራ ፤ “እነዚህ ፍካሪዎች” የት አሉ?  እነሆ አሁን ተመልሻለሁ ለምን ታዲያ አይከሱኝም? እያለ ሲዘባበት የሰማሁትን ነው አሁን አሉላ ሰለሞን “ተዲ አዋሳ” በተባለ ሚዲያ ቀርቦ “የት አሉ ታዲያ ለመን አይከሱኝም” ሲል በተናገርኩት እኮራለሁ እያለ ሲኩራራ መስማት የኢትዮጵያ የንግድ ማሕበረሰብና የሕግ ባለሞያዎች በቁም መሞታቸውን ማሳያ ነው። ክፍል የአሉላ ሰለሞን የጥላቻ 10ቱ ቃላት ከእነ ትርጉማቸው በክፍል 2 በዝርዝር አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 

Monday, July 20, 2026

ሞት ለዘላለም ይኑር! እያሉ የሞት ቅድስና እና ማራኪነት እየሰበከ ወጣቶችን ያስፈጀ የትግራይ ነፃ አውጭ ግምባር ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/20/26


ሞት ለዘላለም ይኑር! እያሉ የሞት ቅድስና እና ማራኪነት እየሰበከ ወጣቶችን ያስፈጀ የትግራይ ነፃ አውጭ ግምባር

ታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/20/26

ወያኔ ልክ እንደ የጀርመን ናዚዎች ልብ ያላዳበሩ ወጣቶች ቀዳሚው የትኩርቶቹ ኢላማዎች ነበሩ። የወያኔዎች እና የሻዕቢያ ተዋጊዎች ከመሪዎቹ በስተቀር 99% ወደ ጫካ ሲቀላቀሉ ከ12 እሰክ 15 ዕድሜ ያላቸው ነበሩ።

 በወጣቶች ላይ ያነጣጠረ ቀዳሚው የኢላማው ግብ፣ የመሪዎቹ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለማረጋገጥ ሲባል፤ በልጆች ላይ ያለ ምንም ጥያቄታማኝ” መሆንን፣ የአካል ብርታትን እና ጽንፈኛ የዘር ርዕዮተ-ዓለምን መምሪያቸው በማድረግ ታዳጊ ወጣቶችን ለራሱ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ግቦች እንደ መገልገያ መሳሪያዎች በማድረግ ከመሪዎቹ በፊት እኛ እንሞታለን እያሉ እነሆ ሞትና የአካል ጉዳተኞች በገፍ ትግራይ እና ኤርትራ ውስጥ ለማየት ችለናል።

ሂትለር ሰለ ወጣቶች ሲናገር እንዲህ ይላል፤

"አካላዊ እና ርዕዮተ-ዓለማዊ ተስማሚነት፡ 'ህመምን መቋቋም የሚችሉ ወጣት ወንዶችንና ሴቶችን እፈልጋለሁ። አንድ ወጣት ጀርመናዊ እንደ ግሬይሀውንድ (greyhound) እንደ “አዳኝ ውሻ” ፈጣን፣ እንደ ቆዳ ጠንካራ እና እንደ እማይታጠፍ ብረት ጠንካራ መሆን አለባችህ።ይላል፤

 ይህ ንግግሩ በኑረምበርግ በተደረገ ስብሰባ ላይ ሲሆን ዋናው ትኩረት ያደረገው  “ከትምህርታዊ ዕውቀት ይልቅ ለወታደራዊ ብቃት ቅድሚያ በመስጠት”፣ ከናዚ ወጣቶች ይጠበቁ የነበሩትን አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ባህሪያት የሚገልጽ ዋና ቅስቀሳ ነበር። ይላሉ ተንታኞች።

ወጣቶችን ለወታደራዊ አገልግሎት ለማዘጋጀት ሲባል፤ አገዛዙ ውጊያን፣ ግዴታን እና ለድርጅቱ ሲባል የሚከፈልን መስዋዕትነት (ሞትን) እንዴት ማራኪና ክቡር አድርጎ ያቀርብ እንደነበር ያየነው ነው።

በዚህ ጭፍን እና ዘረኛ የድርጅት ፍቅር የወደቁ ታጣቂ ወጣቶች ድቱ ዕድሜው ጨርሶ መበታተን ሲመጣ ታጣቂ የነበሩት በጭፍን አምልኮ የድርጅቱን ተልዕኮ ለመፈጸም ሲሉ በካታ አሰቃቂ ወንሎች ይፈጽሙ ስለነበር እነኚ ባንድ የጅት ዕዝ ሰንሰለት  የነበሩት ወጣቶች  ከጅቱ መበታተን ቀን ጀምሮ ቀጥታ የሚገቡት ወደ ለመዱበት ወደ ወንጀል ተግባር ነው። ይህ ድርጊት ትግራይ ውስጥ እንደ ባሕል የተለመደው “ዝርፍያ”፤ “ግድያ” “ሰው ማገት” የምሳሰሉ ወንጀሎች አይተናል። ብዙዎቹ ደግሞ ታጣቂ የነበሩ ናቸው። ይህም ሞት ለነሱ ብርቅ አይደለም እና እየዘፍኑም ሆነ እይታገሉ Viva la Muerte ቪቫ ሙወርተ” ሞት ለዘላለም ይኑር! እያሉ የሰው ሕይወትና የራሳቸው ሕይወት ይዘው ጠፋሉ።

ወንጀል በባህል ላይ ተጽእኖ ያሳድራል ባህል ደግሞ በወንጀል ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ላሉ በወንጀል ጥናት ያደረጉ ምሁራን ይህ ማለት ማሕበረሰቡ እንደሚከተለው የባሕል ዓይነት ፤ ያንድ “ማሕበረሰብ ደህንነት ጠባቂ” የሚሆበት ወይንም ‘’የደህንነት አስጊ’’ ሆኖ የሚከሰትበት ወቅቶች አሉት ማለት ነው

እዚህ ላይ “ወቅት” ብየ የጠቀስኩት ልብ እንድትሉት የምፈልገው “ባሕል የማሕበረሰቡ ደህንነት ጠባቂ ሆኖ ለዘመናት ከቆየ በላ ፤ ባንድ ወቅት ፤ የባሕል ብረዛ (ለውጥ) ሲደረግበት፤ ያ ጠባቂ ባሕል (ነባር) በአዲስ አስጊ ባሕል ይተካና ማሕበረሰቡ ልክ ትግራይ ውስጥና ኦሮሞ አካባቢ እየታዩ እንዳሉት አሰቃቂ የወንጀል ከስተቶች ምክንያት ማሕበረሰቡ አዝጋሚ ወይንም ፈጣን ሥጋት ውስጥ የገባል

አምና ትግራይ ውስጥ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው ያንዲት 12 አመት ያላት ታዳጊ ወጣት ታክሲ ሲያመላልሳት በነበረው ባንድ ጎረብትዋ ጎረምሳ ወጣት ተጠልፋ ተገድላ ከተሰወረች በ3ኛው ወርዋ ሬሳዋ መገኘቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም መላው ሕዝብ በሁታው መደናገጡና እንት ሊሆን ቻለ? የሚል ጠያ ሲጭር ሰንብ

ኢትዮጵያ ወስጥ በተለይም ሰኑ ክፍል አብዛኛው በጥንታዊው የክርስትና መጻሕፍትና ቁርአን መመሪያ የሚከተል ማሕበረሰብ ስለነበር ከንጉሡ (ክ1966 ዓብዮት) ሞትና ክ63 ምኒሰትሮቹ ርሸና ብላ ከዚያም ትግራይ ወስጥ የተከሰተው የ1967 የዳግማይ ወያ አብዮት ያሰክተለው የባሕል ለውጥ ማሕበረሰቡ በወንጀልና በሃገር ክሕደት እንዲዋኝ አድርጎታል

የካቶሊክ ፤ የፕሮተሰታንት፤ የኦረቶዶክስና እስልምና መሪዎች በሙሉ በወያ የፋሺስት ፖለቲካ አስተምህሮ (ዶክትሪን) የተቀኙ በመሆናቸው፤ ፈሪሃ ወያኔ እንጂ ፈሪሃ ፈጣሪ ሆኖ እንዳይቀረጽ ሆኖ ተሰብከዋል፡፡ ይህ በትግራይ ብቻ የታየ ክስተት ሳይሆን በተለይም ወንጀል እና ጥላቻ እንደ ዋና የሥርዓቱ መገለጫና መጋበያ (መሳርያ) ሆኖ ጣራ የነካበት ባሁኑ የኦሮሙማው የአብይ አሕመድ አገዛዝ በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለ አስደንጋጭ ክስተት ነው። (ሰሞኑን በሐምሌ 2018 (ጁላይ 2026) አብይ አሕመድ ባሕር ዳር ከተማ ሆኖ ሰለ አፄ ዮሐንስ በጎጃም ላይ የፈጸሙት ጭፍጨፋ እያነሳ ጎጃም እና ጎንደር ፤ጎጃምና ትግራይ ወዘተ....እንዲተላለቁ በስልትና በግሃድ የሰበከው አጋጪ ንግግሩ ሚነግረን ፤ ግጭቶችና  ወንጀሎች ሥርዓቱ የሚፈልጋቸው መሳሪያዎቹ እንደሆነ ማስርጃ ነው)

አትግደል የሚለው የፈጣሪ መመሪያን በመጣስ መግደል እንደባሕል ተወስዶ ወንድም እህቱን ሲገድል የጀብድ ምልክት ሆኖ እንዲታይ ፤ ልጅ የአባቱን ገዳይ እያሞገሰ መቀ ከተማ አዳራሽ ሲነገር አውድዮውን አስደምጨአችሁ እንደነበርና የሃየማኖት መሪዎችም ነን የሚሉ እዛው ተቀምጠው ልጁን በጭብጨባ ሲያጅቡት መኖራቸው ትችት መጻን አሰታወሳለሁ

ወያ ጫካ እያለና መንግሥት ከሆነ በኋላ ማሕበረሰቡ ገድያና ሞት ቅቡል ሆኖ እናት 3 ልጆችዋን ወደ ጫካ ልካ እስዋም ተዋጊ ሆና ልጆችዋ በማለቃቸው ምንም ቅር እንደማይላትና እንደገና ቢወለዱ መልሳ ወደ ጦርነት እንደምትልካቸው በኩራት ስትናገር መስማት፤ ከምናውቀው የእናት ሆድ ቡቡነት እጅግ የተለየ የልጆቻቸውን ሞት ደጋግመው ቢያዩ ልዩ ኩራትና ደስታ እንደሚሰማቸው የሚገልጹ የትግራይ እናቶች በርካቶች ናቸው

እንዲሀ ያሉት እናቶችና አባቶች ሞት ኩራት መሆኑን የሚያመኑ “ኡር ፋሺዝም” (Ur Fascism) የሜከተል ማሕበረሰብ መሆኑን ካሁን በፊት  Ur Fascism ኡር ፋሺዝም  የወያኔ ታጋዮች እውነተኛ መገለጫ በሚል አንድ መጣጥፍ መለጠፌ የታወሳል፡፡

የኡር ፋሺዝም (Ur Fascism) ባሕሪ ምንነት የነገረን  ጣሊያናዊው “ኡምቤርቶ ኤኮ” ነው። በትርጉም ካልተሳሳትኩ “ኡር ፋሺዝም” ዘላለማዊ ሺዝም ማለት ይመስለኛል፡፡ አንግሊዞች cult of tradition የሚሉት።ኡምቤርቶ ኤኮ << ህይወት>>  ለኡር-ፋሺዝም <<የህይወት ትግል የለም>> ይልቁንም  << ህይወት ለትግል ነው የምትኖረው>> ይላል።

<< ህይወት ዘላቂ ጦርነት ስለሆነ በጸጋ ይቀበለዋል። ይህ ግን የአርማጌዶን ስብስቦችን ያመጣልጠላቶች መሸነፍ ስላለባቸው የመጨረሻው ጦርነት ሊኖር ይገባል ስለሚል፤ በዛው ቦግ እልም እያለ ያልተቋረጠ የጸብና የጦርነት ጫሪነትእንቅስቃሴው ሂደት ዓለምንመቆጣጠር ወርቃማ ሰላምን ማምጣት ይቻላል የሚል ባህሪ አለው>> ይላል። ነገር ግን እንዲህ ያለው ሁሉንም ተቆጣጥሮ ሰላም የሚያመጣ ተስፈኝነት የተሳካለት ፋሽስት መሪ የለም>>

በማለት የኡር ፋሺዝም ባሕሪ ርቀት ይገልጽና መጽሐፉን ሳነበው፤ ከጠቀሳቸው የኡር ፋሺዝም 14 ባሕሪያቶች ውስጥ ቀልቤን የሳበው ከርዕሴ መግቢያ የለጠፍኩት በመጀመሪያው የ17 አመት የወያኔ የጫካ ጦርነት ዘመን “አማረ ታረቀ” የተባለ የወያኔ ታጋይ በውግያው ውስጥ ግራ እግሩ በከባድ የጥይት አሎሎ ተመትቶ ተቆርጦ በመውደቁ የተቆረጠው ቀኝ እግሩ አንስቶ ወደ ሰማይ በመቀሰር የሞት ብስራቱን በጸጋ በመቀበል ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።   

እንዲህ ያለ ሞት ኡምቤርቶ ኤኮ አንዲህ ሲል ይገልጸዋል።

<< … በእንደዚህ ዓይነት አመለካከት ሁሉም ሰው ጀግና ለመሆን ይማራልበእያንዳንዱ አፈ ታሪክ ውስጥ ጀግና ልዩ ፍጡር ነውነገር ግን በኡር-ፋሺስት ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ጀግንነት “ብርቅ” አይደለም የተለመደ ነውይህ የጀግንነት አምልኮከሞት አምልኮ” ጋር በጥብቅየተያያዘ” ነው። የፈላንግስቶች መሪ መፈክርViva la Muerte ቪቫ ሙወርተ” ("ሞት ለዘላለም ይኑር!") ይላሉ። ይህ የሞት አምልኮ ባሕሪ በአጋጣሚ አይደለምፋሺስትባልሆኑ” ማህበረሰቦች ውስጥ ምእመናንሞት ደስ የማይል” አንደሆነ ይነገራቸዋል። አማኞች ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ደስታ ላይ ለመድረስአሳማሚው መንገድ” እንደሆነ ይነገራቸዋል። በአንፃሩ የኡር-ፋሽስት ጀግናየጀግንነት ሞትን” ይመኛል፣ ለጀግንነቱሞት”ምርጥ ሽልማት” ተብሎ ይታወጃል። የኡር-ፋሽስት ጀግናለመሞት ትዕግስት የለውም”” ። ትዕግስት በማጣቱምሌሎች ሰዎችን” ወደሞት” ይልካል። >>

በማለት የ ኡር ፋሺሰቶች “ቪቫ ላ ሙርቴ” - "ሞት ለዘላለም ይኑር!" እያሉ የሞት ቅድስና በመስበክ በጦርነት ወቅት እኔ ልሙት እኔ ልሙት እየተሽቀዳደሙ ወደ ጦርነት እሳት በመግባት ይሰዋሉ። ይህ የኡር ፋሺዝም ከ14 ቱ ባሕርያቶች አንዱ ሞትን በቅድስና እንዴት እንደሚያመልኩት ስንመለከት የወያኔ እና የሻዕቢያ ተዋጊዎች ባሕርይ የ ኡር ፋሺዝም ባሕሪ እንደተላበሱ ከሚዘግብዋቸው የታሪክ ማሕደሮቻቸው ለማወቅ ችለናል።ለዝሀ ነው የትግራይ እናቶቸና አባቶች ልጆቻቸውን እና እራሳቸው ወያ በሚያደረግላቸው የሞት ጥሪ ሁሉ “ሞትን” የምርጥ ትግዎች ምርጥ ሽልማት” ነውና በቅደስና ተቀበለውት እነሆ <<ኡር ፋሺዝ>> ትግራይ ውስጥ ከነገሠ ውዲህ ሞገደኛ ማሕበረሰብ ተፈጥል፡፡ ሰለሆነም ወጣቱ በታነጸበት “ሞገደኛ ባሕል” ምክንያት ራሱን ወንጀል ፈጻሚና ጉዳተኛ ሆኖ የምናየው ለዚህ ነው፡፡

ባሕልና ሕግ  የኛን “ድምበር” (ባውንድሪ) ይወስናሉ፡፡ተፈጠሮ የራሰዋ ሕግ እንዳላት ሁሉ ማሕበረሰቦች የሚከተሉዋቸው ባሕሎችም ጎልተው የተሰምሩ የቆዩ  ሕጎች መጣስ ከጀመሩ፡ መጣስ የሌለባቸው የተሰመሩ ባሕላዊ ወሰኖች ከጣስን ዋጋ እንደሚያሰከትል ትግራይ ውስጥ ያለው ክስተት አመላካች ነው፡፡ ፋሺስቶች ይህንን ሃቅ አይቀበሉትም፡፡

የትግራይ ስትከተላቸውና ሰታከበራቸው የነበሩ ሃይማኖቶች፤ ሕግ፤ አገርና ሰንደቅ አላማ፤ ክ1967 ጀመሮ ተንቀው ተጥለዋል፡፡ትግራይ ውስጥ አመጽ ቅቡል ሆኖ ፤ <<እያባረርክ ግደለው ያንን ሞኝ አማራ>>  ክሚለው አመጸኛ ዘመቻና ዘፈን ጀመሮ የራሱን ጎረትና አብሮ አደግ ወንም ወንድምና እህት በጥይት ወይንም በስለት አርዶ መግደል ንቡር ሆኖ “ኡር ፋሺዝም” ቁቡል ባሕል ከሆነ ወዲህ የማሕበረሰቡን ሰላምና ደህንነት የሚጠበቁባቸው ነባር ባሕሎች በፋሺስት ፖለቲካ ተተክተው አነሆ ትግራይም መላው ኢትዮዮጵያም  “ባሕል በመታመሙ” ምከንያት ሕዝቡ ችግር ውሰጥ ይገኛል፡፡ አመታዊ በዓላትና ሃየማኖታዊ ስብሰባዎች

የሚሰበኩት ፡ ስለ “ግደለው አፍነው፤አንተ ሞት አይፈ  ድንጋይ አናጋሪ ፤ተራራን አንቀጥቃጭ ባለ ልዩ ዲ ” የሚሉ ዘፈኖችና መፈከሮች የምታስተጋባ ትግራይ ነኛ ልትሆን አትችልም፡፡ ሁም ሐዘንና ሞት ይከብዋታል፡፡

ታስታውሱ እንደሆነ ትግራይ ውስጥ ተገደለች የተባለቺው የ12 አመት ታዳጊ ውጣት ብዙ ሰዎች እንት ወደዚህ አስነዋሪ የግድያና የእገታ  ባሕል ገባን? ሲሉ ከጠየቁት ካሰገረመኝ አንዱ <<ገነጠላና መከፋፈል፤ ጸብ ፤ ጠላቻ፤ ሞትና አመጽ ቅቡል እንዲሆን ከሚቀሰቀሱ <<የፋሺስት ቀሳወስትና ጳጳሳት>> አንዱ “የትግራዩ አባ ሰረቀበረሃን” ነው፡፡

“ይህ ነብሰ ገዳይ ከየት ነው የተላለፈብን? እውነት የትግራይ ሰው ነው ይህንን ወንጀል የፈጸመው? እንት ወደዚህ ክስተት ገባን? እያለ ተገርሞ ተከታዮቹን ይጠይቃል፡፡

ትግራይ ውስጥ ሰረቀ በረሃን የሚያመልከው “ወያ” እነ አቶ ገዛኢ ረዳ እና የ ዘመድ የሆኑት አቶ ገብረሊባኖስ መዘገቦ የመሳሰሉ አረጋውያንን እስከ እነ  ሕይወታቸው እሳት ወሰጥ እየጨመሩ እንዳላሰቃዩዋቸውና እንዳልገደልዋቸው፤ ሰረቀ ብረሃን ያንን ወንጀል ስመቶ እንዳልሰማ (ራስ መንገሻ ወንድም አይደለህም ብለው የካዱት) ከደጅ የተወለደ ኢሕጋዊ የሆነ የራሥ ሥዩም ልጅ አታኸልቲ ሥዩም መቀበሪያውን ጉድድ አሰቆፈርው ከነ ሕይወቱ  ጉደጋድ ውስጥ ገብቶ እንዲቀበር ያደርገ የአባ ሰረቀበረሃን ብቸኛ ሿሚ እና መሪ የሆነው የወያ ወንጀል ሸሸጎ ተከታዮቹን ሰብሰቦ ያችን ታዳጊ ህጻን የገደለ ለመሆኑ ትግራዋይ ነው? እኛ ውስጥ ነው የበቀለው? እውነት የኛ ሰው ነው? እያለ እጆቹን እያወራጨ ተከታዮቹን ሲጠይቅና የትግራይ ሰው ንጹህነት ሲመጻደቅ መስማት “ከአባ ሰረቀበረሃን” የምሳስሉ አመጽና ጠላቻ ሰባኪ ፋሺስቶች ሲነገር በመሰማ ብገረምም በዙም አልገረመኝም፤

 (fascism had profound archaic roots. it represented the crude transformation of Christian doctrine into slogans of political violence) (Theodor Adorno- Anti Semitism and Fascist Propaganda- (A Brief history of Fascist lies (Federico Finchelstein p/88)

<<(አመጽን አሰመለከቶ)ፋሺዝም ጥልቅ የሰደደ ነባር ሥር አለው፡፡ ነጹሁን የክርስትና አስተምህሮ ወደ ፖለቲካዊ መፈክሮች በመቀየር የፖለቲካ አመጽ ያበረታታል፡፡>> (A Brief history of Fascist lies (Federico Finchelstein p/88) ከሚለው መጽሐፍ ለዚህ ረስ ስዘጋጅ ሰሞኑን ካነበብኩት መጽሐፍ፡፡

 ትግራይ ውስጥ የመናየው አምጽ ማሕበርሰቡ የፋሺስት ተከታይ ሰለሆነ አመጽ በመለመዱ ሐዘን በመከሰቱ ለሳምንት ያጉረመርምና ክዚያ ወደ ወትሮው ይመለሳል፡፡ የትግራይ ወጣቶች በሙሉ በሚያስብል አሃዝ የፋሲስት ታጋዮች ናቸው፡፤ ለወያኔ መሪዎቸና ባንራ ይሰዋሉ፤ ተሰወተዋልም፡፡ ዛሬም  በኩራት፤ለመሞት ትዕግስት የላቸውም”። ሌሎች ሰዎችን በመረሸንም ሆነ ወደ ሞት ለመላክ ግድ የሌላቸው ገራፊዎችና ጨካኞች በበዛት የተበራከቱበት አክባቢ ነው፡፡

 በሁለመናዊ መልካቸው ከኡር ፋሺዝም ገንዳ የተቀዱት የትግራይ ወጣቶችና ምሁራኖቻቸው ሞትን ቅዱስ ባሕል አድርገው አሁንም እገፉበት ነው፡፡ ሞትን በማቆለጳጰስ “መስዋእት” የሉታል፡፡ ይፈክሩበታል፤ የጨፈሩበታል፤ይደሰቱበታል፡፡ ሰውን ድበደቦ አሰቃይቶ ገድሎ ቆሻሻ መጣያ ላይ መጣል በአመጽ ተወለዶ በአምጽ ያደገ ወጣት ሰለሆን መግደልና መሞት ምኑም ማለት አየደለም፡፡

ሞት ተወዳሽ በሆነበት ማሕበረሰብ የተወለደ ወጣት እንን ለጎረቱ ሕይወት ሊያዝን ቀርቶ ለራሱ ሕይወትም የማየጨነቅ  ትግራይ ወስጥ በሺዎቹ አሉ፡፡

ከላይ የጠቀሰኩትና የምታዩት ፎቶገራፍ በ17 አመት የወያኔ የጫካ ጦርነት ዘመን “አማረ ታረቀ” የተባለ የወያኔ ታጋይ በውግያው ውስጥ ግራ እግሩ በከባድ የጥይት አሎሎ ተመትቶ ተቆርጦ በመውደቁ የተቆረጠው ቀኝ እግሩ አንስቶ ወደ ሰማይ በመቀሰር የሞት ብስራቱን በጸጋ በመቀበል ወዲያውኑ ህይወቱ እንዳለፈ ወያንዎች በኩራት ሲተርኩለትና ቅዱሰ ሞት መሆኑን ለተቀረው የትግራይ ወጣት በፈለጉ እንዲከተል ይሰብካሉ (ለሞተውም ሆነ ለቆሰሉት ቤተሰቦቻቸው ግን አይረዱም፟ የንን ቤተሰብ ለመሳሌ)  እንዲሀ ሞትን የሚንቅ እንዲገደልና እንዲሞት ሲሰበክ ሞትን የማይፈራ ሞገደኛ ማሕበረሰብ በተለይ “ሲገድልና ሲደፍር ፤ እየደበደበ ሲመረምር የቆየ ከጦርነትና ከጫካ ወደ ከተማና ገጠር (ማሕበረሰብ) የተመለሰ የፖለቲካም ሆነ የጦር አዋጊም ሆነ ተራ ተዋጊ ሕሊናው በደም የተነከረ እንቅልፍ ሲተኛ የሚያባንነው “ድንጉጥ (ሲፍሮዘኒክ) የቀውሰ  ሰለሚሆን የሕሊና ጭንቀቱ ለመወጣት መጠጥ አልያም ያልታከመ “ነበሰ ገዳይ” ሆኖ የጎረቤቱ ለጃገርዶችና ወዳጅ ዘመድ ቢደፍርና  ቢገድል በአእእሮ ሐኪሞች የሚጠበቅ ከሰትተ ነው፡፡

በግፍ ሰለተገደለቺው ምስኪን ታዳጊ ወጣት፤ ባጭር መቀጨትዋ ቢያሳዝንም ትንሽ ብትቆይ ኖሮ እስዋም የዚያ ያልታከመ የወያ ታጣቂ ወጣት ማሕበረሰብ አባል ትሆን እንደነበር የሚያጠራጥር አይሆንም ነበር፡፡

ትግራይ ውስጥ የተለመደ ከሰተት አለ፡፡ሰው ሲገደልና ሲታገት፤ ቶች ሲደፈሩ ውት በማያስገኘው በሰላማዊ ሰልፍ ከመቃወም ይልቅ ሰከን ብሎ ትግራይ ወሰጥ ከ48 አመት በላይ እንክብካ ተደረጎለት በቅሎ ሥር የሰደደው <<የአመጽ ሁሉ እናት>> የሆነው “ኡር ፋሺዝም” እንዲወገድና ወያ የሚባል ድርጅት ከፖለቲካ እንዲታገድ ካልተደረገ ችግሩ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ሞት ቅዱስ ሆኖ ቪቫ ሞርቴ” ("ሞት ለዘላለም ይኑር!") እያለች ትግራይ በማትወጣበት ከባድ ማእበልና ጸጸት ትገባለች፡፡

ታቸው ረዳ