ሲንጋፖር እና ማሌዥያ ትግራይ እና ኢትዮጵያ
ጌታቸው ረዳ
6/30/26
Ethiopian Semay
ከዚህ በታች የምተቻቸው እና የምንዳስሳቸው የትግራይ ምሑራን እና የድርጅታቸው የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ «ሉጋም የበጠሰ» (Balky/Nappy) ባሕሪ ዋናው ተጠያቂው ሥልጣን ላይ ያለው አብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞዎች ሥርዓት ነው። ይህ ለምን እንዲያ ሊሆን እንደቻለ በጦርነቱ ወቅት እና ጦርነቱ ከመነሳቱ በፊት ስለ አብይ አሕመድ የሰጠኋቸው ትችቶች እና ማስጥንቀቂያዎች አንባቢዎች ማስታወስ ይኖርባችኋል። ያንን አሁን አልገባበትም። አሁን የምናየው የትግራይ መሑራን በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት ገና ትግሉ ከ1967 ዓ.ም “ተጋድሎ ሓርነት ትግራይ” (ተ.ሓ.ህ.ት) ብሎ ራሱን በመሰየም የተመሰርተው የትግራይ ፋሺስት ፓርቲ ሲጀመር ጀምሮ እሰካሁን ድረስ «በትግራይ exceptionalism» እየዳከሩ ባልጠፋባቸው ማንነት “በራስ ፍለጋ ዑደት” ሲጋጋጡ ብዙ ሕዝብ አስፈጅተዋል (ኢትዮጵያዊያኖችንም ሕዝባችን የሚሉት የትግራይ ሕዝብንም ጭምር)።
በዚህ የፋሺስቶች ውልደትና ዕድገት ግስጋሴ ዋና ተዋናዮች ሆነው የተገኙ የትግራይ ምሑራን ናቸው። የነዚህ መሁራን ቅስቀሳና ድጋፍ ምክንያት ቀስ በቀስ ከምስረታው ጀምሮ ፣ ድርጅቱ ጉልበት እያገኘ፤ ሕዝቡን ከማስፍራራት እሰክ ማሰር ፥ በእሳት እየለበለቡ ማሰቃይትና መግረፍ ፥ ከነሱ የሸሸውም ንብረቱን በመውረስ ፤ ጠንክሮ የተዋጋቸውም በመግደል እና በማሳደድ በዙሃኑን የትግራይ ሕዝብ በማሰለፍ 17 አመት የጫካኔ ጦርነት አካሂደው ደርግን ቦርቡረው በመጣል ሲመኙት የነበረው የበላይ የመሆን ሥልጣንን አገኙና 27 አመት ሕዝቡን ረግጠው አለያይተው አበጣብጠው አጣልተው ቅጥቅጥ አርገው ገዙት።
የትግራይ ተወላጆችም “ከደቂቅ
እሰከ ሊቅ” ሕሊናው በበላይነትና ማን አሕሎኝነት ሰክሮ “ዞር ብሎ ያያቸው ሁሉ” እንደጠላት እያዩ ”ምን አባህ ታየኛለህ!” እያሉ ሲያንጓጥጡት 27 አመት ከገዙ በኋላ ወዳጄ “ጉዱ ካሳ” ጠብ ያላለቺው
ትንቢቱ ልክ እንዳለው ውስጥ ለውስጥ ሲፍም የነበረው እሳት በጥቂት
ወራት ልዩነት ወያነ ፈነዳ፦
(በነገራችን ላይ ሚነሶታ ላይ ቁጭ ብሎ ሲያሻው አስመራ እየተሽሞነሞነ ከአንዳርጋቸው እና ብርሃኑ ነጋ ጀምሮ እሰክ ምሁራን ተብየዎች ወያነ በ3 ወር ውስጥ ያልቅለታል አዲሰ አበባ እንገባለን ሲሉን ከነበሩት እና አሁን ደግሞ ፋኖዎች በጥቂት ወራት አዲስ እበባን እንጭብጣታለን ከማለት አልፈው ለሚመጣው አመት አስተላለፈውት ሰምቻለሁ፤ ከነዚህ ሁሉ ትንባዊ ሽምቅ ተዋጊዎች ትንቢቱን በትክክል መትቶ ያየሁት የወዳጅ ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ትንቢት ብቻ ነው)።
ታሪክ ነውና እሰኪ ላስታውሳችሁ
እንዲህ ይላል ስለ ወያኔዎች
አወዳደቅ፡
«.........አዲስ አበባ
ማቀጣጠያ ካምሱሯ የተለኮሰ ፈንጅ ሆናለች። መቼ እንደምትፈነዳ ትክክለኛ ሰዓቱን አንድዬ ብቻ የሚያውቀው ሆኖ በቅርብ መፈንዳቷ የማይቀር
ስለመሆኑ ግን የማንም ተራ ግንዛቤ ሊሆን ይገባል። በቃኝ። ስለነሱ አፈነዳድ ትንሽ ልናገር ነበር ይቅርብኝ። እንዴትም ይፈንዱ ዋናው
መፈንዳታቸው ነው፤ እናም እንዳፈነዱን አይቀሩም እነሱም አሁን በቅርቡ ይፈነዳሉ!!» ምንጭ “አዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ትፈነዳለች! (በኤፕሪል 2,
2018 ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)::
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ የትግሬዎቹ
የአዲስ አበባ የልብ እብጠት (እነሱ “ፍናን” ይሉታል) ሲያስታውስ እንዲህ ይላል፤
<<….ሌት ከቀን የሚዝናናው፣ በመኪናው ውስጥ በሚከፍተው የሙዚቃ
ድለቃ ሕዝብን እንቅልፍ የሚነሳው፣ በየቡና ቤቱ እየዞረ ትግርኛ ካልተከፈተልኝ በማለት ሌላውን ዘፈን በነፍጠኛነት የሚፈርጀውና የሚያስፈራራው ጠግቦ እየዘለለ የሚገኘው ትግሬ ወያኔና አሽከሮቹ ናቸው፡የሚገርመው
ጠጪዉና ተዝናኙ ትግሬ ብቻ ነው ተብሎ በአዋጅ የተነገረ ይመስል በየመዝናኛውና በየምሽት ክበቡ የሚከፈተው ዘፈን ከሞላ ጎደል ትግርኛ ብቻ ነው። ትግርኛ ካልከፈታችሁ
ቡና ቤታችሁ ይዘጋል የተባለ ይመስል አዳሜ
ከገዢው ወገን ጋር የተዛመደ እየመሰለው የሚከፍተው ሙዚቃ ትግርኛ ብቻ የሚሆንት አጋጣሚ ሞልቷል>> ይላል ዳግማዊ ጉዱ ካሣ።
ዘልሎ ፥ ዘልሎ ሕዝብን
ሲያሰለቹት በሚያደርሱበት ስቃይና ግፍ በመጨረሻ ሕዝቡም ቋቊ ሲለው ከነጭራሹ ሙዚቃቸውን ሁሉ ሳይቀር መስማት አስጠላው።
ይህንን ትዕይንት በማስረጃ ላስታውሳችሁ፦
ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ይባላል፤
ድሮ የኢሕአፓ ታጋይ የነበረ አሁን ግን “ሃገረ ትግራይ ይመስረት” ከሚሉት እና የሽዋ ሕዝብ ቤተ ክርስትያን ከመሳለሙ በፊት
‘’ጠንቋይ ቤት” የሚሳለም ሕዝብ ነው፡” ሲል የነበረ ኤርትራ
ውስጥ ተወልዶ ያደገ የዓጋመ አውራጃ ተወላጅ የሆነ ከትግራይ ፋሺስት መሁራኖች አንዱ ነው።
ከትግርኛ መጽሄት ወደ አማርኛ
የተረጎምኩትን ላስነብባችሁ፡
እንዲህ ይላል
«አንዳንድ ጊዜ በኢትዮጵያ
ውስጥ የተዘጋጁ ለሕዝብ ሚቀርቡ መዝናኛዎች አያለሁ። አንድ ቀን “ሰይፉ ሸው” መዝናኛ እመለከት ነበር። የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰይፉ
አንዲት የትግራይ ተወላጅ የሆነች ድምጻዊት ቃለ መጠይቅ ያደርግላት ነበር። ለተመልካቾቹ ዘፍን እንድትዘፍንላቸው ጠይቋት፤ እሷም
እሺ ብላ በጣም ቢመገርም ድምጽ የትግርኛ ዘፈንዋን አቀረበች። አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተመልካቾች ግን አያንጨበጭቡ፤ እስክስታ አይመቱ፤
እጆቻቸውን አጣምረው “ዝም ፥ ዝም ፥ ብቻ” ዝም ብለው ይመለከትዋታል።እኔ ያኔ በጣም ገረመኝ። በጃንሆይ ጊዜ እኮ ትግርኛ ሲዘፈን
ጉራጌው፤አማራው፤ኦሮሞው ከኛ ጋር አብሮ ነበር አስከስታውና ደስታው ሲያስኬደው የነበረ። እስከዚህ ድረስ ትግርኛ ሙዚቃ እንኳ እስከመጥላት
የሚደርስ ሁኔታ እየተከሰተ ነው። እኛ ብቻ ካልገዛን የሚለው አስተሳሰብ መወገድ አለበት።>> ይላል ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ
“ውራይና” በሚባለው የትግርኛ መጽሄት (ሕታም ቁ31 2010)
«አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተመልካቾች ግን አያንጨበጭቡ፤ እስክስታ አይመቱ፤
እጆቻቸውን አጣምረው “ዝም ፥ ዝም ፥ ብቻ” ዝም ብለው ይመለከትዋታል።እኔ ያኔ በጣም ገረመኝ” ሲል ዶ/ር ገላውዴዎስ አርአያ ተመልካቹ
ለምን እንዳላንጨብጨብላት ሰፊ ሐተታ ካሁን በፊት በሰፊው ስለገለጽኩት ፤ባጭር አገላለጽ የወዳጄን የይነጋል በላቸው አባባል ላስቀምጥና
ሕዝቡ ወደ ጸጥታ ስሜት የገባበት ምክንያት ስለነበረው ነው፡ ይህም የሚከትለው ግፍ ሲፈጸም እስዋ እና መሰል ትግሬዎች ይጨፍሩ ነበር
(ጎንደር ሲጮህ ትግራይ ላይ ጠጅ ሲንቆረቆር” የሚለውን ጽሑፌን አስታውሱ)።
ይነጋል እንዲህ ይላል፤
«አብዛኛው ትግሬ ተጠቀመም
አልተጠቀመም በፕሮፓጋንዳው ተሸንፎ ወያኔ ሆኗል ወይም መስሎ ነበር።አምባሻ ሻጯ፣ ቁራሌው፣ መጥረጊያ አዟሪው፣ ወዘተ. እየተራበና
እየተጠማም ቢሆን ህወሓትን ከልቡ ይወድና ግፉ የደግፍ ነበር።“ዘር ከልጓም ይስባል” ወይም “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” የሚባለውም
በትግባር ሰላየው..”
ሕዝቡ ጸጥታን መርጦ “ዝም ፤ዝም አለ።
የሚክተለው ግፍ በዓይኑ
አይቷልና።ለመሰል ትግሬዎች ሲደግፉት የነበረው መንግሥት
“...ዐማራውና ሌላውን
የሚያቆራኘውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አውድሜ ድራሹን አጥፍቻለሁ ብሏል፡፡ ታዋቂና ተሰሚ የዐማራ ምሁራንንና የሀገር ሽማግሌዎችን
ገድዬ ጨርሻለሁ ብሏል፡፡ የኢትዮጵያዊነት ምልክቶችን ሁሉ አንድባንድ ደምስሻለሁ ብሏል፡፡ በተቃውሞው ጎራ የሚገኙ ዐማሮችን ለቃቅሜ
አይቀጡ ቅጣት በመስጠት – በስድብ፣ በግርፋት፣ በወፌላላ፣ በግብረ ሶዶም፣ በወሲብ ጥቃት፣ በጥፍር ንቅላትና በፈላ ዘይት ጥብሳት
… ስብዕናቸውን በማዋረድ መቼም እንዳያንሠራሩ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ የዐማሮችን ቅስም ሰባብሬ ዳግመኛ ወደ ሥልጣን ዝር እንዳይሉ
በአካልም በመንፈስም ኮድኩጃቸዋለሁ ብሏል፡፡ በአዲሲቷ ሕወሓት ሠራሽ ኢትዮጵያ ዐማራ ምንም ዓይነት ቦታ እንዳይኖረው በማድረግ ብዙ
ግፍ ፈጽሟል..” ታዲያ ሕዝቡ ይትግርኛ ዘፋኝ እና ዘፍን ሲይጣድመጥ አብሮ 27 አመት ሲጨፍርበት የነብረብረበትን ሙዚቃ ደንገት
ለምን “ቋቍ” አለው?
ወቅታቸው ነበርና ወዳጅ
ዳግማዊ ጉዱ ብ1983 ሥልጣን ሲይዙ ያስታወሰውን የትግሬዎቹ ንግግር እንዲህ ያስታውሰናል፤
አስታውሳለሁ – በ83 ዓ.ም ወያኔ አዲስ አበባ እንደገባ በወያኔ ሬዲዮ የትግርኛ ፕሮግራም ስለትግራይ ሕዝብ
በወያኔ ሥልጣን መያዝ ተጠቃሚነት የተጠየቀ አንድ ትግሬ ባለሥልጣን “የመጀመሪያው ጠቀሜታ ሥነ ልቦናዊ ነው፡፡ ‹የኔ ሰው
ሥልጣን ያዘልኝ› ብሎ ማሰቡ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሁለተኛ ….” እያለ በኩራት ይደሰኩር ነበር፡፡ እየተናገረኩት ያለሁት ጉዳይ
እነሱ በተግባር ሲፈጽሙትና የሚኮሩበትን፣ እኛ ግን ስንናገረው እንኳን በሀፍረት
የምንሸማቀቅበትን የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡
አንድ የወዳጄ ወዳጅ የላክለት
አዲስ አበብ አደርሶ ከመጣ አንድ ሰው የታዘበውን በመጽሐፌ የጠቀስኩትን ላስታውሳችሁ፡ የሰማዩን ምድሩን መሰሶ የሚያነቃንቅ ጥጋባቸው
ምን ይመስል እንደነበር አዲስ አበባ ደርሶ ከመጣ ወዳጅ የተላከልኝን ላስነብባችሁ፦
<<…….እግዚአብሔር
ይስጥልኝ ወንድሜ። ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር የተወሰነ ወር ቆይቼ ነው የመጣሁት። የሰውን ፊት አይተው ይለያሉ ሊቃወመን ይችላል
ብለው የሚያስቡትን ኤርፓርት ኢሚግሬሽን ቡት ውስጥ ከሚቀመጡት ዘረኛ ትግሬዎች ጀምሮ። በተለይ ቦሌ መድሐኒአለም ፊት ለፊት በኤድና
ሞል ዝቅ ብሎ ብዙ ዘመናዊ ባለ 5 ኮከብ
ሆቴሎች ተከፍተዋል ሁሉም የትግሬ ናቸው። ነጮቹ ‘ሆቴል ዲስትሪክት’ ይሉታል። የኛ ህዝብ መቀሌ እና አፓርታይድ ይለዋል ሰፈሩን። በተለይ “ቬኒሺያን” የሚባለው የትግሬ ሆቴል ገብተን
10 ዲቂቃ እንደተቀመጥን ካውንተሩ ላይ የሚቀመጠው እጅግ በጣም የጠገበ ሲራመድ መሬት የሚነቀንቅ ትግሬ የተቀመጥንበት ድረስ መጥቶ
ያፈጣል። አስተያየቱ ሀሉ በጣም ነው የሚከብድው። ህዝቡ ኪሱ ውስጥ ያለውን ብር ቶሎ አራግፎ እንዲወጣ ነው የሚፈልጉት።
ጥላቻቸው በግልፅ የሚታይ ነው። በዘረኝነት እና በጥላቻ ከተመረዘ ህዝብ ጋር መኖር በጣም ነው የሚከብደው። ህዝባችን በገዛ አገሩ ላይ እንዲሸማቀቅ
እየተደረገ ነው። ባካባቢው ባሉት ሌሎች የትግሬ ሆቴሎች ውስጥም ተመሳሳይ ዘረኝነት ነው ያየሁት። “> ይላል፡ ለዚህ ደራሲ
የተላከለት ደብዳቤ (ምንጭ-የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ክመን የመነጨ ነው? ገጽ 176)። ይህንን
ወታደሮች ያልሆኑ የወያነ ወጣት ትግሬዎች በየቡና ቤቱ የሚያሳዩት ጥጋብ አዲስ አበባ ውስጥ ሽጉጥ ታጥቀው፤ ምድሪቱን እንዴት አንደሚነቀንቋትና የአማራን ሕዝብ እልቂት
መሪ የነበርረውና የባሕር በራችንን ለጠላቶቻችን ያስረከበብንን ታላቁ መሪያቸው መለስ ዜናዊን ለምን ተቻችሁ እያሉ እንዴት
ይዝቱ እንደነበር ይህንን ጥጋብ በቪዲዮ ይመልከቱ፤
ይነጋል እንዳለውም ፈነዱና
በየመጠጥ ቤቱ እናንት አህዮች
“የትግርኛ ሙዚቃ“ ካልክፈታችሁ እያለ ቡና ቤቶችን ሲያስፈራራ “ወዲ ትግራይ” እያለ ሲፎክር የነበረው እና “ይህን አህያ ንዳው” ሲል ቆይቶ በመጨረሻ ግፉ ሲያበዛ በባለተራው
የኦሮሞ ሥርዓት ተገፍትሮ ሲገለል፤ ምሁራን ተብየዎቹና መሪዎቻቸው በልባቸው ውስጥ ይዘዋት የነብሩዋትን ሃገረ ትግራይ ለመመስረት ወደ ትግራይ
አፈገፈጉ።ይህ ድንገት ያለሙት ሳይሆን በማኒፍስቷቸው ይሁን በንግግሮቻቸው ሲነግሩን ይነበረው ነው። የወያነ አባት ‘’የስብሓት ነጋን’
“ሥልጣናችን ከተቀማን በየምንደራችን እንከፍጋፈላለን”
ንግግር አስታውሱ።
ያንን ጥጋብ እና የሃገረ
ትግራይ ምስረታ ዓላማ እውን ለማድረግ በወሰዱት የተሳሳተ የልብ ዕብጠትና ጉራ ሕዝብ አሳልቀው ራሳቸውም ተዋርደው ግማሹ
ተማርከው፤ ግማሾቹ ተግድለው አሁን ወዳሉበት የጭለማ መሰላለ ተንጠልጥለው አንዱ እግር ሰማይ አንዱ እግር ምድር የፖለቲካ ዥዋዥዎ
እየሰሩ “እግር ተወርች ታስረው ፥ ምሁራኖቻቸውም የሚይዙትና የሚጨብጡት አጥተው ሃገረ ትግራይን ለመመስረት “እሰኪሳካልን ድረስ
ኢትዮጵያዊያኖችን መስለን ኢትዮጵያን እየበዘበዝን እና እየቦረቦርን በስልት እንራመድ በሚል በየወቅቱ እይተሰበሰቡ እየተነጋገሩ ነው።
ብዙዎቹ ምሁራኖቻቸው በሁለት
የቆመ ፍላጎት ቆመዋል።ጠላቶቻችን የሚጓጓዋት ሃገር እንመሰርታለን የሚሉ
አንደኛው ጎራ ነው። ሌላኛው በሁለት “ባላ” ላይ የቆመ ፍላጎት
(Ambivalent) ኢትዮጵያ ሃገራችን ነች” ይልና እንደገና የትግራይ ናሺናሊዝም ጎራ “ሲብረታ” ወደ ሃገረ ትግራይ ቡድን የሚያዘነብል
ወላዋዩ ሁለተኛው ጎራ ነው።
በሁለት ባላ የቆመ ፍላጎት
በሚመለክት (ሃገረ ትግራይ እመሰርታለሁ ከሚለው አንዱ (ገ/መድህን ሮምሃ በጥሩ አግላለጽ ያቀረበውን ላቅርብ ፤ እንዲህ ይላል፡
«ባለሁለት ገጽታ ፍላጎት’
ያልኩበት ምክንያት፤ ምሁሩ በአንድ በኩል ስለኢትዮጵያዊነት ይሰብካሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ብሔረ ሰቦች እርስ በእርሳቸው የሚያጋጭና
የሚለያይ መርዙ ይረጫሉ፤ ባለሁለት ገጽታ ፍላጎት፡፡ የመጽሐፉን አሉታዊ ጎኑን ለግዜው እናቆየውና፤ ሞቲ ቢያ (2009) ‘የኦሮሞ
ጥያቄና ፈተናዎቹ’ በተሰኘ መጽሐፉ፤ የዚህ ዓይነት ባህርይ ‘የአንድነት ስም እየጠሩ ለበላይነት ለቅሶ’ በማለት ገልጾታል፡፡» (ገ/መድህን
ሮምሃ (ዶ/ር)
ይህ እውነተኛ አገላለጽ
ስንመለከት አንድ የፖለቲካ ድርጅት ስለ አንድ አገር አንድነት እተሰበከ ወደ
ሥልጣን ሲወጡ ግን ከ8 አመት በፊት የነበረው ወያነ እና
አሁን ያለው ኦሮሙማው ስርዓት ስትመከቱዋቸው አንድነትን ይሚቀበሉት እነሱ የበላይ ሲሆኑ ብቻ ነው። የሁለቱ ችግሮች በገልጽ አይተነዋል።
የትግራይ ምሑራን ስንመለከት
የምናየው ወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ እንዳለው ፣ ከአላውኃ ምላሽ (ወንዝ) ጎጥ-ሰቀል አድማስ ያልዘለለ የአእምሮ ስንኩላን አስተሳሰባቸውን
ስናስተውል ምን እንደገጠማቸው ለማወቅ አዲስ ጥናት መደረግ ይኖርበታል ባይ ነኝ፡፡
«ዕይታቸው ከአላውኃ ወንዝ
ጎጥ-ሰቀል አድማስ ያልዘለለ የአእምሮ ስንኩላን የሆኑ የትግራይ ኤሊቶች ይህን በዘረኝነት ደዌ የተመታና ሀገርን የሚያወድም ወያኔ
መደገፋቸውን ስናይ ከዕውቀትና ከጥበብ ለሚመነጭ አስተዋይነት መገዛታቸውን ሣይሆን እንደውሻ ደምና አጥንት እያነፈነፉ ወደ እሚከረፋው
የሆድ ውስጥ ዕቃ ወደ ጨጓራና ጅብ አይበላሽ መውረዳቸውን እንገነዘባለን።» ይላል።
በሁለተኛው ጎራ የተሰገሰገው
ወላዋይ የትግራይ ምሑር የሚክተለው ስልት የሚክተለው ይመስላል፦
ለምሳሌ መዘክር ዘሞ (የወያኔ
አምራረ አባል የአባዲ ዘሞ ልጅ) መዘክር ዘሞ እንዲህ ይላል በትግርኛ (ወደ አማርኛ ልተርጉመው)
ሃገረ ትግራይ ዝብሃል ሃገር
ክርእዮ ይደልይ እየ- (ሃገረ ትግራይ የሚባል ሃገር ለማየት እፈልጋለሁ) በሚል ረዕስ መዘክር ዘሞ እንዲህ ይላል፤-
«....መሬት ላይ ያለውን
እውነት እንረዳ። ትግራይ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንወቅ። ትግራይ ውጥንቅጥ ውስጥ ነች። ችግሩን ለመፍታት በጋራ ከመስራት ይልቅ
በትንንሽ ጉዳዮች እንዳንገመት መጣር አለብን። ኦሮሞዎች (ሥልጣን ላይ ሆነው) በስልት ለሃገረ ኦሮሚያ ምስረታ ለምን እንደሚሠሩ
ግልጽ ነው። አገር ለመመስረት ነው የሚንቀሳቀሱት ፣ ግን እንደኛ ጮክ ብለው “ለሃገረ ኦሮሚያ” ምስረታ ነው ውጥናችን እና ግባችን
ብለው ሲናገሩ አትሰሙዋቸውም። ተጨባጭ ትግል ሲኖር ነው የሃገር ምስረታ
ሞራል የሚዳብረው፤ የትኛው ትግል መስርተን ነው ለትግራይ ምስረታ የምንጮሆው? በመጀመሪያ ኢኮኖሚያዊ ጥቅማ ጥቅሞችን መገንባታችን ማረጋገጥ አለብን። ከግጭት
የወጣች ሀገር ( መዘክር - ትግራይን ነው “ሀገር” እያላት ያለው) በተከበብንበት እና መውጫ በር በተቆለፈብን ወቅት ትግራይ ምን
እንደምትመስል አይተናል:: ታጥሮ መከበብና የመቆለፍ ከስተት ሳይዘጋጁ ለሃገር ምስረታ መሮጥ “ጥሩ ምሳሌዎች” ናቸው። እንዲያ ባለ
ሁኔታ ሃገር መመስረት ትንፋሽ ማጣት ነው። ማስተንፈሻና መውጫ በር የሌለው ሀገር መሆን ከንቱ መሆኑን በቅርቡ አይተናል።ሰለዚህ
ምኞቶቻችንን ለማሳካት አስቀድመን ኢኮኖሚያዊ ዝግጅቶችን ማድረግ አለብን።ከጠላቶች የተሻለ መሆን አለብን።ከዛሬው ጦርነት ልንማር
ከምንችላቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች አንዱ ሁሉም ሰው አንጻራችን ተሰልፎ ሊገለበጥብን እንደሚችል ነው ያየነው።ግባችን ላይ እስክንደርስ ድረስ
ግን ግንኙነታችንን ስትራቴጂ አስይዘነው እስከምስረታው ድረስ “ኢትዮጵያዊያን ነን” እያልን በብልሃት እይተራመድን ግባችን ላይ መድረስ ይገባል።»
(መዘክር ዘሞ (አዲሰ አበባ)
እንግዲህ የሃገር ምስረታቸው
በስልት እንዴት እየተንቀሳሱ እንዳሉ እና ሃገር ላምውደም የሚከተሉት ስልት አይተናል (ያውም አዲሰ አበባ እምብርተዋ ውስጥ እየኖሩ)
አይዝዋችሁ የሚል ፤ እኛም ወደ ዚያው ግብ እያመራን ነው የሚል መንግሥት መኒሊክ ቤተመንግሥት ስላለ፤ ስልታቸው ቨዝግታና በደፈጣ
የድንጋይ መሰረት እየጣሉ እያደመጥናቸው ነው። አስገራሚ ይሚያድረገው ደግሞ ለሀገረ ትግራይ ምስረታ በፕሮግራማቸው አጽደቀው “በተወዳዳሪ
ፓርቲ” በሕግ ጸድቆላቸው እውቅና አግኝተው አብይ አሕመድ ፈቅዶላቸው የሚንቀሳቀሱ ሰብ ሕድሪ ፥ ባይቶና፤ ሳልሳየ ወያነ፥ ሰብዓ እንደርታ
ወዘተ....ወዘተ.. ፡ አዲሰ አበባና ትግራይ እየተመላለሱ መሪ ያጣች አገር “ኢትዮጵያን ማውደም” መብታችሁ ነው ተብለው
ያለ ስጋት እየተንቀሳቀሱ ነው። ዞምቢው ኢትዮጵያዊ ምሁር ግን ሰለዚህ ምንም አይተነፍስም።
ይህንን የሃገረ ትግራይ
ምስረታ የሚተጉ በዘረኛነት ደዌ የተመቱ ፋሺስቶች “አማራ እና አማርኛን” “ኢትዮጵያን እና ሰንደቃላማዋን” እንዴት
እንደሚያዩት ከአንድ የትግራይ ምሑር ተብየው ለዩኒቨርሲቲ ተማሪች ምረቃ ዕለት የጻፈውን ልጥቀስ ።
እንዲህ ይላል፡
Always
remember that we have to keep fighting until we make sure the social and
political contract that sustained and enabled the genocidal empire (Ethiopia) is dismantled. It is not something new. The
Irish people have done it against the greatest empire to ever exist—the British
Empire—and we will do it so.
For instance,
during your graduation, you could have claimed that you feel so traumatized to
listen to any Amharic speech delivered in front of you on your special
day, and that you prefer it to be in English.
And also, no
University—specially those in Tigray are mandated to use the genocidal flag to
the gold medalists.»
እንዲሕ ያሉ አገር እና
መሪ ለይተው ማየት ያቃታቸው ደናቁርት የትግራይ መሑራን “ትግራይ ታስራለች” የሚልዋት ትግራይ እራሳቸው በድንቁርናቸው እንዳሰርዋት
አላወቁትም ውይንም እያውቁም ሊያምኑ አይፈልጉም። ለዚህ ሁሉ ውድመት ሲከተሉት የነበረው የፋሺስት ድርጅት እንደሆነ ግን ጨርሰው
አይቀበሉትም። በውያኔነቱ የልብ ኩራት የሚሰማው ሲሳይ ሕሸ ይተባለ ሙዚቀኛ እና ካናዳ ቶሮንቶ ውስጥ የስደተኞች የሕግ ጠበቃ -በመለስ
ዜናዊ ሞት” የገጠመው የትግርኛ ግጥም ምሑራኖቻቸው ለፋሺዝም ያላቸው ፍቅር ምን ያህል ጥልቀት ውስጥ እንደገቡ ማሳያ ነው።
እንደ ጥጋበኛ ፈረስ ሉጋማቸው
(Balky/Nappy) ከበጠሱ ለሃገር ትግራይ መስረታ ከሚረጉት የትግራይ ፋሺስቶች አንዱ ኢንጅኔር ታደሰ የማነ ነው፤-
እንዲህ ይላል
«ትግራይ ታስራለች ብየ
አምናለሁ። ስለዚህ «ኣን ሎክ ትግራይ/Therfore, unlock Tigray/» በሚል መመሪያ መጀመር አለብን። ለምሳሌ በቅርቡ
በተደርገው «መኸተ» (የመክት ጦርነትና ዘምቻ) «ተአምር» የሰራ ሕዝብ ነው። ትግራይ እግር ከወርች መታሰርዋ እውን ነው።
90% ሕዝባችን ርሃብ ላይ ነው። ለማኝ ሕዝብ ደግሞ አክብሮት አያገኝም። ለማኞች ሆነን ዓለም ጀሮው አይሰጠንም። የተጋሩ ምኞትና
ጉጉት ምንድነው? የኔ አስተሳሰብ ልስጣችሁ። ፍላጎታችን ዋስትና ያለው ሰላም እና ያልተገደበ ዕድገት ናቸው። እነዚህ ሁለት ጉጉቶች ማሳካት ይኖርብናል። ቢያንስ ፥ ቢያንስ የአፍሪካ ሮል ሞዴል የሆነች
የሰው ልጆች የሚመኝዋት ትግራይ ማነጽ ነው። ይህንን እውን ለማድረግ የሲንጋፖር ትይዩነት እና ልምድ ከኛ ጋር ለዩነት
ቢኖርም ፣ እጀግ እጅግ በጣም የሚመሳሰል ነገር ሰላለን ያንን ጠቃሚ ልምድ እንመልከት።
ሲንጋፖር በ1965 (በፈረንጅ
አቆጣጠር) ወደ ማሌዥያ ፈደረሽን ስትጠቃለል፤ማሌዥያኖቹ “አንፈልጋችሁም ፤እሳት ልትጭሩብን ነው ስለዚህ ራሳችሁን ቻሉ ሂዱ አንፈልፍጋችሁም”
ብለው ማሌዥያኖች ገፈተርዋቸው። የሆነው እንዴት ነው፤ የማሌዥያ ፓርላማ 126 ለ 0 ድምጽ አንፈልጋችሁም ብለው ድምፅ በመስጠት ፈደረሺኑን አንቀበላችሁም አሉዋቸው። በወቅቱ ሲጋፖርያዊያኑ የወሰዱት ውሳኔ
«አንቀበላችሁም ካሉን ማሌዥያዊያን የሚጓጉዋት ሲንጋፖር እናንጻለን/እንመሰርታለን!!”
ያ ነበረ የወሰኑት ቃል። እኛም ጠላቶቻችን የሚጓጉዋትን ትግራይ እንመሰርታለን። ሲንጋፖራዊያን ማሌዥያዊያኖች ጂ ዲ ፒ (GDP) ሲነጻጸር፣ ሲንጋፖራዊያን ማሌዥያዊያኖች በ6 ዕጥፍ ጂ ዲ ፒ ይበልጥዋቸዋል። አንዳንድ አንባቢዎች
(ጂ ዲ ፒ) ምን ማለት እንደሆነ ያልገባችሁ ሰለምትኖሩ GDP (Gross Domestic Product) ማለት ትርጉሙ ጠቅላላ የሀገር
ውስጥ ምርት በአንድ የተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚመረቱ ሁሉም የመጨረሻ እቃዎች እና አገልግሎቶች አጠቃላይ የገንዘብ ዋጋ ሲሆን ይህም
የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ቁልፍ መለኪያ ሆኖ የሚያገለግል መለኪያ ነው።
እንግዲህ ሲንጋፖራዊያን
ማሌዥያዊያኖችን በምጣኔ ሀብት ስለሚበልጥዋቸው ማሌዥያዊያኖች “የጉጉት ልሃጭ ማንጠባጥባቸው ብቻ ሳይሆን ማሌዥያዊያኖች ወደ ሲንጋፖር እየሄዱ
ይሸቅላሉ።” ይላል።
ተናጋሪው ባያብራራውም፤
አንባቢዎች ግራ እንዳይገባችሁ ትግራይ እና ሲንጋፖር በጣም በጣም ይመሳሰላሉ የሚለው የተናጋሪው ንግግር ስሕትተ መሆኑ ልንገራችሁ።
ሲንጋፖር ልክ እንደ ኤርትራ (ጣሊያን) በእንግሊዝ ቅኝ ስትገዛ የነበረች
ትንሽየ አገር ነች። የሲንጋፖርን በማሌዥያ ሕብረት ውስጥ መካተቱን በማሌዥያ ብሔርተኞች ተቃውሞ የደረሰበት ምከንያት ብዙ ምክንያቶች
ቢኖሩም ዋናው ምክንያት፣ ሲንጋፖር ውስጥ ቻይናዎች አብላጫውን የህዝብ ቁጥር ሰለሆኑ ፣ ማሌዥያ ብሔርተኞች የቻናዎቹ በሲንጋፖር
ሕዝብ ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው ለማሌዥያዊያን የወደፊት ስጋት ሰለሚሆኑብን አንፈልጋቸውም .. በነበሩብት ይሂዱ ፣ የማለታቸው
ምክንያት ዋነኛው ይህ ነው።
በመቀጠል ተናጋሪው ለትግራይ
መፍትኄ ሲያስቀምጥ (መፍትኄ ዝርዝሩ ለማስቀመጥ እዚግ ቦታ አይበቃም) ከየአሕጉራቱ ወደ መቀሌ መጠው ይተሰበስቡትን ታላላቅ አካዳሚክ
የትግራይ ምሑራን እና የሃያምኖት የፕሮተስታንት የእስላም እና ካቶሊክ እንዲሁም ለኦርቶዶክስ ተጠሪ መሪዎችና ተናጋሪዎች ባጨሩ በትግርኛ
እንዲህ ይቀጥላል፤
«...ስለዚህ እኛ ምን
ማድረግ አለብን። የኛ ነገር እንደምታውቁት 90 በመቶ የተራበ ሕዝብ ነው ያለን፤ አገራዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታ ለመገመት ሚያስቸግር
ህነታ ነው እየኖርንብት ያለው አካባቢ፡ድሆች ንነ፤ ባጀት ትሁት ነው፤ ትግራይ በመአከላዊ መንግሥት አትታወቅም (እውቅና የላትም)
፤ እልቂት ደርሶብናል ወዘተ ወዘተ....... ስለዚህ ምን ይደርግ።
መደረግ ያለበት የጫዋታው ቀያሪ ( Game Changer) ቁልፎች በትክክል ለይቶ ማውቅ ነው። ትግራይ እራስዋን ደፍታ እንደትኖር
ትከሻዋ አጎምብሳ እንድትኖር የሚፈልግ ኃይል ትናንትም ነበረ ዛሬም አዲስ ኃይል አለ። አሁን እያሰብን ያለነው ልክ
4 ኪሎ ተቀምጥነ እንደነበርነው ነው እያስብን ያለነው (ይህ ስሕተት ነው)።
በዚህ አገር “የሃርድ ካረንሲ”
(ጠንካራ የሆኑ የውጭ ገንዝቦች) ችግር አለ። ይህ የሃርድ ካርንሲ ወደ ትግራይ የሚያሸጋግርበት ስልት ቀይሶ ለትግራይ ፍጆታ ብቻ
እንዴት መዋል እንዳለበት የትግራይ ኢንቭስተሮች
ማሰብ አለባቸው።.....በማለት
( ሰውየ እያለ ያለው የሃገሪቱ
ብር እንዲወደቅና እንደወደቀም በመገንዘብ “ሃርድ ካረንሲ” ወደ ትግራይ በማስገባትና በማከማቸት ሃገሪትዋ መውድቅዋ ስለማይቀር ግን
“ገና ያ ከመሆኑ በፊት ለመጪዋ ሃገረ ትይራይ ግናባታ እንዴት እንደሚውል ነው እየነገራቸው ያለው።) ይህ ስልት ካሁን በፊት ትግራይ
ኦን-ላይን በተባለ አፍቃሬ ወያኔዎች ሚዲያ “የኢትዮጵያ ብር ያላችሁ ወርቅ በመግዛት እና ወደ ውጭ አገር ገንዘብ (ሃርድ ካረንሲ)
በመለወጥ ለትግራይ ግናባታ ክምች እንዲያደርጉ እና አገሪቱ እንድትወድቅ እንዴት እንደታቀደ ካህን በፊት እንድ መጣጥፍ እንደጻፍኩ
ታስታውሳላችሁ ብየ እገምታለሁ።
ኢንጅኔር ታደሰ የማነ ንግግሩን
በመቀጠል አጋሮቹን እንዲህ ይመክራል፤-የተከማቹ mega
projects (ትልልቅ ኩባንያዎች..... ወዘተ) (ባለፈው ጦርነትና በድንገተኛው ይመንግሥት ለውጥ እንዳይነው) ለአደጋ የተጋለጡ
ናቸው። ሰለዚህ በምትካቸው ምን እንተካ? ማድረግ ያለበን ኢትዮጵያ ውሥጥ የማይረጋ እና መቸውንም የማይድን ከባድ የምጣኔ ቀውስ
አለ። በዚህ ምክንያት ሃገሪቱ የምግብ አቅርቦት ችግር ይገጥማታል፡ ይበልጥኑ የባሰ ሊገጥማት ነው። So, we have to unlock Tigray at house hold
level (የእያንዳንዱ አባወራ ቤት በምጣኔው ውስጥ ፤በፖለቲካው ውስጥ ፤በማሕበራዊ፤ በሃያምኖት፤ በኢኮኖሚ ወዘተ...ሚና እንዲኖሮው
ማድረግ አለብን ማልት ነው።፡እነዚህ የተዘጉ ቁልፎች እንዲፈቱ የምንላቸው ምንድናቸው? መጀምሪያ ፖለቲካው መፈታት አለበት፤ እየተከተልነው
ያለው ፖለቲካ የትግራይ ችግር የሚፈታ አይደለም (ሁሉም የትግራይ ተወላጅ እኩል የመናገርና ሃሳብ የምስጠት መብት መፍቀድ አለብን)።
የኛ ብልጫ (በነፊት) ሆሞጂኒቲ ነው። ሆሞጂኒይቲ ማለት አንድ መሆን
ማለት ነው። በታሪክ በጎሳ፤ በሃይማኖት በታሪክ ሆሚጂኒቲ አለን። ይህ ግን ወጥ (አንድ) መሆን እንጂ አንድነት
አያመጣም። ችግራችን ቁጥራችን በጣም ንኡሳን ነን ፤ ችሎታችንም ዝቅተኛ ነው። ስለዚህ ይልና 3 መፍትኄዎች ብሎ ካስቀምጣቸው ሰፊ
ዝርዝሮች ውስጥ
How to unlock Tigray (ትግራይ ከታሰረቺበት እንዴት እንፍታት)
ለሚለው ፣ እንዲህ ያስቀምጣል፤
1ኛ equal
political level (ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ያለ ምንም ቅደም
ሁኔታ ድምፁ መሰማይት አለበት። ላልሆነ አንደ ትናነቱ ሳይሆን ወደ በጥበተ እና እርስበርስ ለነባላ ነው።) 2ኛ- elite of the elite in every
sector (|ሊቀ ሊቃውንትን መፍጠር” የምስለኛል ወደ አማርኛ ስተረጉመው) ቁጥራችን ከብዙሃን ከሚባሉት ጋር
እኩል ላምድረግ quality (ጥራት) መኖር አለብን። ይህ ማለት
ልሂቅ ምሑር፤ ሊሂቅ ገበሬ ፥ በየትኛውም “ሰክተር” የሙያ እና የንግድ ዘርፎች ሊሂቅ መፈጥር አለብን። 3ኛ- ገበያ፦ ሻጮች (አቅራቢዎች) እንጂ ገበያ ሸማቾም መሆን የለብንም።
ሸማች ሆኖ “ፖሊሲ” ሊያዋቅር ሊያወጣ አይችልም። እሰራኤል ፥ ሲንጋፖር ፥ ቻያና “ሸማቾች ስላልሆኑ” አቅራቢዎች /አምራቾች/ ስለሆኑ
ፖሊሲ አላቸው። ሰለዚህ ትግራይ ሸማች
ሆና ፖሊሲ ማውጣት አትችልም ፤ አምራች አቅራቢ መሆን አለባት። ቁጥራችን ትንሽ ስለሆነ በየዘርፉ elite
of the elite ለመፍጥር ከፈለግን ንኡስነታችንን በጥራት መቀየር
እና በጥራት
በልጠን መገኘት አለብን። እያለ ኢትዮጵያ የትግራይ፡ ሸቃይ እና ገብያተኛ (ሸማች) ትግራይ ደግሞ ለኢትዮጵያና ላካባቢዋ አቅራቢ ፥ አምራች እና ቀጣሪ የምትሆንበትን የሃገረ
ትግራይ ምስረታ ስልት በሰፊው ይዘረዝራል።
በመጨረሻ
ለዚህ ሁሉ ቅዠትና መከራ የዳረጋቸው ምንድ ነው? በሚል ልደምድምና ልሰናበታችሁ፡
የተቃወማቸውን ወደ “አገር እንዳይገባ አገር የነሱ ብቻ አድረገዋት”፡ ግማሾቻችንም ገድለው
ከምድረ ገጽ እንደንጠፋ አድርገው፣ በመላው አፍርቃ እና በዱባይ እንዲሁም በሱዳን ፥ አሜሪካ እና በመላ ሃገሪቱ እንደ ዱባ
ሐረግ የተንሰራፉት ከባድ ከባድ ኩባንያዎች፤ ትላልቅ ሕንጻ ቤቶች ፥ እርሻዎች ፥ ንግዶች አዛዥና አምራች ሆነው “ጠቅላላ
የምዝበራውና ይበላይነቱ ጥጋብ” አላስችል አላቸውና ጦርነት ከፍተው “እኛ ትግሬዎች እናስልቀሳለን እንጂ አናለቅስም!
ብላ ማይምዋ “አጀብነሽ”
እንዳለቺው አልሆነላቸውምና መጨረሻው የአጀብነሽ ለቅሶና ሐፍረት ተከናንበው እነ ስብሓትና እነ ፥ እነ..... ውስጣቸው
ረጥበው የቁም ሬሳ ሆነው ግብአተ-መሬታቸው አየን።
በህይወት ያሉትም “ከዚያ ዕብሪት ሳይማሩ አሁንም ወደ ሃገረ ትግራይ ቀዥት ገብተው
ይቃዣሉ”፡ ግማሹም ወደ ተፉት ትፋታቸው
ተመልሰው ትፋታቸውን
ለመላስ ወደ አሥመራ ሄዱ፤ ግማሹም ጀነሳይድ ፈጸመብን ወደ አሉት አዲሰ አበባ ገስግሰው የአብይ አሕመድ ጫማ ላሽ ሆኑ። ለራስ ከፍ ያለ
ግምት በመስጠት አጉል የሚኮፈሰው የትግራይ በሔረተኞች ዕብሪት
፣ ቀስ ብሎ እየተጋባበት የምናየው የአማራ ወጣትም ከዚህ እንደሚማር ተሰፋ አደርጋለሁ እያልኩ፡ የትግራይ ምሑራን ቅዠት
‘’ኢትዮጵያ የትግራይ ሸቃይ ፥ ተቀጣሪ እና ገብያተኛ (ሸማች) ፥ ትግራይ ግን ሸቀጥ አቅራቢ አምራችና ቀጣሪ የምትሆንበትን “ሲንጋፖር
እና ማሌዥያ ትግራይ እና ኢትዮጵያ” የሚለው ከኤርትራ የተጋባቸው ቅዠት የት እንደሚደርስ ታዛቢዎች ሆነን እየጠብቅን
ነው።
ሰላም እንሰንብት
ጌታቸው ረዳ

No comments:
Post a Comment