Sunday, March 30, 2025

ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣው አፓርታይድና ፋሺዝም መጠለያው ኢትዮጵያ ውስጥ ካደረገ 33 ዓመት ሆኖታል! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 3/30/25

 

ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣው አፓርታይድና ፋሺዝም መጠለያው ኢትዮጵያ ውስጥ ካደረገ 34 ዓመት ሆኖታል!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 3/30/25

የሰቆቃ ድምጽ መስማት አይሰልቻችሁ። ቢያበሳጭም ካለማድመጥ ይልቅ ‘’ማድመጡ’’ ኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋው አፓርታይዳዊ መንግሥት ለመገርሰስ የመፍትሔ ማፈላለጊያ መንገድ የሚረዳ የሰቆቃ ድምፅ ነውና ላለማድመጥ አትሽሹ። የእናቶች አምባ ላለማድመጥ መሸሽ “እናቶችን መካድ” ነው። ቪዲዮው ከሥር በመጨረሻ ትችቴ ላይ ተለጥፏል።

የምታደምጡት የኢትዮጵያዊያን አምሐራ ሰቆቃና እምባ የሚደመጠው ቪዲዮ ሐገር ለማፍሰረስ 27 አመት በወያኔ ትግሬዎች (“በትግራዋይነት ማኒፌስቶ”) ፤ 7 ዓመት ደግሞ እስካሁንዋ (2017 ዓ.ም)  “በኦሮሙማዊ ማኒፌስቶ” በጠቅላላ 33  ዓመት ለአምሐራ እና ለጋሞ ሕዝብ መሰቃየትና መጨፍጨፍ (ሌሎችም የጥቃት ሰለባዎች እንዳሉ አልዘነጋሁም) ምክንያት የሆነው ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣው “አፓርታይድና ፋሺዝም ሥርዓተ መንግሥት” በኦሮሞና በትግራይ ምሁራን ቀያሺነትና ስምምነት ተባብረው ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የመንግሥት ሥርዓት እንዲሆን በሕገመንግሥት በመደንገጉ ምክንያት ነው የምታደምጡት የምስኪን አምሐራ ሴቶች እምባና ልቅሶ።

ብዙ ሰዎች እንዳውም የማስታውሳቸው የአምሐራ ምሁራን እና ትግሬዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው ሥነ መንግሥት ኢትዮጵያን የሚጠሉ፤ሃገር ለማፍረስ ተፈራርመው የመጡ፤ “ከጣሊያን የባሰ ‘ጣሊያን ቀመስ’ የሆነ ‘አገር በቀል የቅኝ አገዛዝ’ ሥርዓት ነው” እያልኩ ስጽፍ ከላይ የጠቅስኳቸው ምሁራን ለጽሑፌ መልስ ሲመልሱልኝ የነበረው መልሳቸው “በድንጋጤና በመገረም ተውጠው እንዴት ያንድ ሃገር ሰዎች በዚህ ዓይነት አገላለጽ ታስቀመጣቸዋለህ? አሁን ያለው ሥርዓት <<የአምባገነኖች ሥርዓት እንጂ አፓርታይዳዊ አይደለም፤ አባባልህ ሕዝብ ለሕዝብ ያቃቅራር…>> እያሉ ብዙ ስድብ ሲሰድቡኝ ነበር።

የጊዜ ጉዳይ ሆነና የሚሰማኝ ሳጣ ከመስመሬ ሳልወጣ በዚያው መከራከር ቀጠልኩበት። እንዳልኩትም የጊዜ ጉዳይ ሆነና ጊዜ ፈጅቶ ከባድ ጉዳት ደርሶ “ብዙ ሕዝብ በልቶ” ከጨረሰ በሗ እነዚህ ምሁራን እኔ ስለው ወደ ነበረው መስመር ገቡና ከኔ ብሰው መጮህ ጀመሩ ማለት ነው። ለዚያ አምላክ (ምናልባት) ሐላፊነት ወስዶ ዓይናቸው ስላበራላቸው አመሰግነዋለሁ።

እንደውም ለክርክሬ ማገር አድርጌ ሳነሳው የነበረው ነጥብ፤ ደቡብ አፍሪካ እና ሮዴሺያ (ዚምባቡዌ) የነበሩት ፓርታይዶች 33 ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋው “አፓርታይድ” ሲነፃፀር “የኢትዮጵያው አፓርታይድ የከፋ በዓይነቱም የተለየ ነው ስል ነበር። ካሁን በፊት ክርክሬን ላልተከታተላችሁ አዳዲስ አንባቢዎቼ ስለምትኖሩ በአባባሌ እናንተም ልትገረሙ ትችሉ ይሆናልና ላይላዩን ብቻ ባጭሩ ምክንያቴን ላስቀምጥ፡

  ቦር ወይንም “አፍሪካና” በመባል የሚጠሩት የሳውዝ አፍሪካ የነጭ ዝርያዎች የሚገዝዋት <<አፓርታይዳዊዋ ደቡብ አፍሪካ>> እና በእያን እስሚዝ የምትመራዋ <<ሮዴሺያ (የዛሬዋ ዚምባቡዌ)>> ይኖሩ የነበሩ ሁሉም ዘሮች ዕኩል የምጣኔ ሐብት ባለድርሻዎች ሳይሆኑ ተጠቃሚዎቹና የበላይ ገዢዎቹ “ነጮች” ብቻ (ሕንዶችም አሉበት) የሚቆጣጠሩት ሥርዓት ነበር።

ስለሆነም ይህንን አድሎአዊ ዘረኛ አስተዳዳር ለመቃወም የተነሱት የነዚህ ሁለት ሐገሮች ታጋዮች ዋናው ትኩረት “ምጣኔ ሐብትና  የሥራ አቀጣጠር ለሁሉም ዜጋ በዕኩልነት እንዲዳረስ ነበር ትግላቸው።

“በጥቁሮች ላይ ጭፍጨፋ ግድያ ዕስራት መሰወርና ግርፋትም እኮ ነበር?!” ልትሉኝ ትችላላችሁ፡ ቢኖርም ሆን ተብሎ ሥርዓቱን ለመቃወም በወጡት ሰላማዊ ሰልፈኞችና የተቃዋሚ ቡድን አባሎች ንክኪ አላቸው በሚል በየመንደሩ ገብቶ የጭካኔ ብትር ሲያሳርፍ ነበር እንጂ አርፈው የተቀመጡ ጥቁሮች ግን ልክ እንደ ኢትዮጵያው አፓርታይድ በየመንደሩ እየሄዱ ማረድና ዘራቸውን ለማጥፋት ቤቶቻቻውን፤ ፤ንብረቶቻቻውና ሰብላቸውን፤ እያቃጠሉ ከደቡብ አፍሪካ  “እንዲባረሩ” ብዙም ትኩረት አላደረገም። ብዙዎቹ የታዩት ጭፍጨፋዎች በሰላማዊ አድማ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ “አፓርታይድ ብሔር ብሔረሰብ አስተዳደር” ስመንለከት ግን ሕክምናው፤ የትምሕርትና የኩባኒያ ተቋማት፤ ሰፋፊ እርሻ መሬቶች፤ ለትግሬዎችና ለኦሮሞዎች እንዲዳረስ በማድረግ ሌሎቹ እንዲቆረቁዙ (ጋምቤላና ጉሙዝ አካባቢ እርሻ መሬቶችን አስታውሱ) በማድረግ የምጣኔ ሐብቱ ለገዢዎቹ ነገዶችና አለቅላቂዎቻቸው የተሻለ ኑሮና “የገዢነት መንፈስ” ልዩ ኩራት ትግሬዎችና ኦሮሞዎች እንዲሰማቸው በማድረግ ሌሎች ተሸማቅቀው በፍርሐትና በስጋት እየኖሩ እነሱ ግን “የኛ” የሚሉት መንግሥት መስርተው እንዳሻቸው ሲሆኑ አይተናል።

የሮዴሺያና የደቡብ አፍሪካ አፓርታይዶች እንዲሁም የጣሊያን ፋሺዝምና የናዚ ሥርዓቶችን ስንመለከት ግን ፡ ሐገራቸው ለማበልጸግና ለማጠናከር ከነበራቸው ይዞታ እንዲሰፋ ሲያደርጉ ፡ 33 አመት የተመሰረተው የኢትዮጵያ አፓርታይድ ግን በተጻራሪ መልኩ የሃገሪቱ የዘመናት የነፃነት አርማ የተባለቺው ሰንደቅአላማ መልክዋን በመቀየር 44 ጨርቆችን በማሰፋት “አፓርታይዳዊ ክልሎች” ልክ እንደ ራስ ገዝ ሃገሮች ባንዴራ እንዲኖራቸው በማድረግ <<ብሔር/ሃገር ብሎ በመሰየም የሐገሪቱ ሰንቃዎችን በማፍረስ ፤ ይዞታዋ የነበሩ የሃገሪቱ መርከቦች በሽልማት ለጠላት ሃገሮች በመሸለም፤ የባሕር በር ለጠላት በመሥጠትና ወደብ አልባ በማድረግ፤ ሠፋፊ ለም መሬቶች ለሱዳንና ኤርትራ ለምትባለዋ በመስጠት አፍራሽ ዒላማ የተገበረ ከተጠቀሱት አፓርታይዶችና ፋሺሰት ሥርዓቶች የተለየ አፓርታይድ ነው።” ፤

ልዩ የሚያደርገው ደግሞ “ለዘመናት ድርና-ማግ ሆነው ያቆዩዋት ሐገራዊ ባሕሎችዋና ሓይማኖቶችዋ” እንዲበረዙ በማድረግ’’ ‘ብሔራዊ ቋንቋ የሆነው የመረዳጃ ልሳን አማርኛ’ እንዲዳከምና እንዲጠፋ በግሃድ መንግሥታዊ ጥቃት ደርሶበት አልሞት ብሏቸው እየታገላቸው እነሆ በሰፊው ሕዝብ ምላስ አልጠፋ ብሏቸው ሲታገላቸው ማየት የመቸገራቸው ክስተት ደግሞ ሌለው አስገራሚው ከስተት ሆኖ እያየን ነው

ንግድቤቶች ትምሕርተቤቶች ሆስፒታሎች የሃይማኖት ተቋማት መንገዶች ሁሉ ስማቸው እንግሎዝኛ፤ ዓረብኛ ሆነው  ወጣቶቹ “ክ” ፊደልን በ “ህ” (እንዴት ነህ? አይዞህ! ለማለት “እንዴነክ? አይዞክ!” ይላሉ) ፊደል እየለወጡ ሲቸገሩ እንሰማቸዋለን። በሚገርም ሁኔታ ያነጋገር ስልታቸው ዓረብኛና እንግሊዝኛ ሆኗል። ይህ ሁሉ ሐገር በቀል አፓርታይዱ ሆን ብሎ 33 አመት የሰራበት ትውልድና ባሕል ለመግደል የሰራበት ዘመቻ  ሲሆን ፤ የመንግሥት ወታደሮች ተብለው መሎየና ጠብመንጃ የያዙ የሃገሪቱ የደሕንነት፤ የመከላከያና የፖሊስ ሃይል <<የፔንጤ   ሃይማኖት መሪ ወስላታ መሪዎች (እንደ እዩ ጩፋ የመሳሰሉትን)በወታደራዊ ሞተር ሳይክል፤ በወታደራዊ መኪኖች፤ በወታደራዊ ሰልፍ እና አጀባ እያደረጉ ፤ ወታደራዊ የክብር መሎዮአቸው ወደ ሰማይ እየወረወሩ አብረው ሲጨፍሩና ሲዘሉ የሚደረግበት ምክንያትም የሃገሪቱ አፓርታይድ ሥርዓት <<የሃገር መፍረስ>> አበሳሪነቱ እየነገረን መሆኑ ምልክት ነው።

ይህ ሁሉ ብልሽት ኢትዮጵያ የምትባል ሐገር እንዳትኖር የሁለቱ ነገድ ተወካዮች (መለስ ዜናዊና ሌንጮ ለታ) ተፈራርመው የመጡበት ዓላማ ለማከናወንም ‘’ነገዶች (ብሔር ብሔረሰብ በሚል ስያሜ) በሚናገሩት ቋንቋ በሚኖሩበት አካባቢ “ተከልለው” የማንም ኢትዮጵያዊ ሳይሆን የሃብትና የመሬት በባለቤትነቱ ለቋንቋ ተናጋሪዎቹ ብቻ እንዲሰጥና እንዲቆጣጠሩት በማድረግ፤ ሁለቱ ገዢዎች ያልነበራቸው የመሬት ስፋት በመያዝ፤ ሌሎች ነገዶች ጥገኛ ሆነው ባለቤቱ በሚፈቅድላቸው አሰራር ብቻ የሚኖሩ “በገዛ ሃገራቸው ጥገኛ ወይንም ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን”  እንዲሆኑ ያደረገ ነው።

ነገድንና ሃይማኖትን በጥቃት ቀለበት አስገብቶ “አምሐራ (ክርስትያንና-ዕስላም አምሐራ) <<በምድሪቱ እንዳይኖር በመጨፍጨፍ የሕልውና አደጋ እንዲደርሰው አምሐራውና ጋሞው በሚናገሩት ቋንቋ ብቻ ተለይተው <<በጥቃት ቀለበት>> ለይቶ ያስገባ ከሌሎቹ አፓርታይዶችና ፋሺስት ሥርዓቶች የተለየ ነው የምልበት ምክንያት፤ <<ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ተደራጅቶ የሚሰራ እስካሁን ድረስ መጠሪያ ስም ያጣሁለት ሐገር በቀል አፓርታይድ ሥርዓት ነው>> የምለው በቀላል አላለጽ ነው።

ከላይ የተጠቀሱ አፓርታይድ ሐገሮች ከሐገራችን አፓርታይድ የሚለያቸው መንገድ <<ኢትዮጵያ አንደ ሐገር የሕልውና አደጋ አንዲጋረጣት በጥናት በገዛ ልጆችዋ ዘመቻ ሲታወጅባት>> <<የዚምባበዌው ሙጋቤና የደቡብ አፍሪካው ኔልሰን ማንዴላ በአፓርታይድ ያቀረቡት ክስ ግን <<ነጮቹ ሐገራቸው በማፍረስ ዘመቻና መሬት ለባዕድ በመሸንሸን ሳይሆን አፓርታይዱን የከሰሱበት ፡የትግላቸው ዋናው ትኩረትጥቁሩ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ባለመኖሩ ዕኩል እንደ ነጮቹ ተጠቃሚ የሚንበትን መንገድ መቀየስ ነበር ዋናው ትኩረታቸው>>

ይህ ነበር ዋናው የትግላቸው ትኩረት እንጂ እንደ ኢትዮጵያውን 33 አመት ሐገር በማፍረስ የተጠመደው የኛው አፓርታይድ <<የዚምባበዌና የደቡብ አፍሪአካዊያን ጸረ አፓርታይድ ታጋዮች “ሐገር እንዳያፈርስባቸው ስጋታቸው አልነበረም”። ያ ነው የነሱና የኛው አፓርታይድ የሚለየው።

ለማጠቃለል፡

 ጥቁሩ ዛሬ እንደ እኛው ሐገራዊ ሕልውናው አደጋ ላይ አይደለም ሆኖም ዋናው ፓርታይድ ያካበተው የሃገሪቱ ሃብት ግን “አፓርታይድ ተወገደ” ከተባለ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የጥቁሮች ድሕነት ባሰበት እንጂ አልተሻለውም። ምክንያቱም ፤ሕልውናው ለአደጋ የተጋለጠው እንደ ኢትዮጵያ የጀነሳይድ ጥቃት  ስለደረሰበት ሳይሆን ዋናው የጭቆናው መሳሪያው “ሥልጣንና ምጣኔሐብቱ” በተለይ ምጣኔ ሃብቱ (ዕርሻው ማዕድኑ እና ኢንዳስትሪው) ዛሬም ከነጮቹ እጅ ስላለወጣ ጥቁሩ ሕዝብ ዛሬም የፍትሕ ያለህ እያለ ነው።

እኛ ግን ከነሱ የሚለየን “ነብስ አድን የሕልውና እና የሐገር ያለሕ! እያልን ነው። በዕምባ እየታጀበ የምትሰሙት የአምሐራ እሕቶቻችን ኡኡታ ከዓለም አካባቢ በጥራጊ መልክ የወጣው አፓርታይድና ፋሺዝም መጠለያው ኢትዮጵያ ውስጥ በማድረጉ ያመጣው ጠንቅ ነው።

ሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ

 

 

Wednesday, March 19, 2025

በዋሃቢያው ጂሃዲስት ቡድን ባለበት ተፈልጎ እንዲታረድ መስጊድ ላይ እና መስቀል አደባባይ የታወጀበት እፎይ የተባለው ልጅ ጉዳይ! ጌታቸው 3/19/25


በዋሃቢያው ጂሃዲስት ቡድን ባለበት ተፈልጎ እንዲታረድ መስጊድ ላይ እና መስቀል አደባባይ የታወጀበት እፎይ የተባለው ልጅ ጉዳይ!

ጌታቸው

3/19/25

            The scary development of extreme wahhabism in Ethiopia!

ወደ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት ዋሃቢ የሚለው ቃል ልግለጽ። ውሃቢ/ሰለፊ/ መነሻው ሳዑዲ ዓረቢያ ነው። በዛው ምድር (ሥርዓተ መንግሥት) ሁለት ግንዶች አሉት። ፖለቲካዊው እና ሃይማኖታዊ

የሳዑድ ቤተሰቦች ፖለቲካዊው/መንግሥታዊው ዘርፍ ሲቆጣጠሩ የአብደል ወሃብ ቤተሰብ ደግሞ “አውልያው” (ቤተ ክሕነቱን/ሲኖዶስ እንደምንለው) በበላይነት ይቆጣጠሩታል።

ዋሃቢው Mutaween /መጠዊን/ የተባለ የራሱ ፖሊስ አለው። (መጠዊን) እስልምናውን ለማራመድ እና ማንም ሰው ከዛው ዕምነት እንዳይወጣ የሚቆጣጠር በክርስትያን አማኞችም ሆነ በሴቶች ላይ ምሕረት-የለሽ አውሬነት የተላበሰ ተቆጣጣሪ ፖሊስ ነው

 በነዳጅ ገቢ የሚገኝ ዶላር/ፔትሮ ዶላር/ የሚውለው በውጭ አገር የሚገኝ እስላም እና ክርስትያን ወደ ውሃቢ/ሰለፊ እምነት ለመለወጥ እና ለማስፋፈት ያውሉታል።

በዋሃቢስቶች ትንታኔ ሁለት የሰው ልጆች አሉ ይላሉ። አንደኛው «ትክክለኛ የእስልምና አምልኮ ያላቸው፣ የተመረጡ፣ ያሸነፉ» የሚሏቸው ሲሆኑ ሁለተኞቹ ደግሞ «ቃሪፎችና/ቃፊሮች/ እና ሙሽራኮች» የሚሏቸው እንደ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች እንዲሁም ዋሃቢስቶች የማይደገፉትን እንደ መውሊድን ማክበር የመሳሰሉ ስርዓቶች የሚከተሉ ሌሎች ሙስሊሞችን ያካተተ ነው። ባጭሩ የሌሎችን እምነት አክብሮ፣ ተስማምቶ የመኖር ነገር በነርሱ ዘንድ በፍጹም የማይታሰብ ነው።

ከታች በፎቶግራፉ ላይ የምታዩት አክራሪው ዋሃቢያው <<ኦርቶዶክስን እናጠፋለን>> የሚለው እና <<ፋኖና ማሕበረቅዱሳን ካልፈረሱ ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን>> የሚለው ማስረጃ ክርሰትያንን በማረድ የተደራጀ የዋሃቢው ክፍል ነው።

ይህ ቡድን የተፈጠረበት ምድር ሳዑዲ ዓረብ እና ፓኪሰታን የኢትዮጵያን ነባራዊውን እስልምና ወደ ዋሃቢና ሰለፊ እምነት እንዲከተል “ነባሩን የእስላም ማሕበረሰብ” “እጅግ አክራሪ እንዲሆን” ሰይጣናዊ ተልዕኮአቸውን በመበከል ላይ ናቸው።ከነዚህ እንደምሳሌ ሊጠቀሱ የሚገቡት

ሳድቅ መሐመድ (ኡስታዝ አቡ ሓይደር)

የተባለው አጅግ ዓለም አቀፍ ሽብርተኛነት ሊሰት መመደብ የሚገባው አክራሪና <<የኢትዮጵያን ቤተክረስትያናት ባያችሁበት ሁሉ በእሳት አጋይዋቸው>> ፤ <<ክርሰትያኑን እረዱ./…>> <<ከግርማቸውና ከሐጎስ ወይንም ወልደስላሴ የሚለው የኩፋሮች ስም የያዙት ጋር ወዳጅነት አትፍጠሩ>> እያለ ዩቱብ ላይ ምንም የማያውቁ የዋህ ወጣት እስላሞቹን (በተለይ ምስኪን ወጣት ሴቶችን) እየሰበከ የሚገኘው ውሃቢዎቹ በሚሰጡት ስንቅ እየተመገበ  በጥገኝነት ሱዑዲ ዓረብ የሚኖር “ኢትዮጵያዊው “አይሲስ”

እንዲሁም አቡበከር አሕመድ የተባለው ሌላው አስመሳይ

<<ዓለም እስላሞች ሲያስተዳድሯት ሰላም ነበረች፤ ኩፋሮች ከያዝዋት በሗላ ግን ተበጠበጠች>> እያለ እስላማዊ ቅኝ-ግዛት (እስላማዊ ኢምፔሪያሊዝምን) የሚሰብክና የሚመኝ አስመሳይና “ቅዠታም”

አክራሪው ያልተወላገደ ጥሩ አማርኛ የሚናገር በትውልዱ የዓፋር ተወላጅ የሆነው ወሎ ያደገው “አቡበከር መሐመድ” እና

በዋሃቢነቱ መንትያ የሆነው ሌላው  ጓደኛው ጸረ ክርስትያኑን ‘’ግራኝ አሕመድን’’ <<የነፃነቴ ምልክትና የነጻነታችን አርበኛ>> እያለ መጽሐፍትን የጻፈ አክራሪው አሕመዲን ጀበል ነው።

አሕመዲን ጀበል ማለት በተመራማሪው ሊቅ አቻምየለህ ታምሩ አገላለጽ

<<የኦነግ የፖለቲካ ታሪክ ደራቹ የአሕመዲን ጀበል ተልዕኮ በሃይማኖት ስም የኦነግን የፈጠራ ታሪክ እየደገመ ኢትዮጵያውያንን በተለይም ኢትዮጵያውያን-ሙስሊሞችን በኢትዮጵያዊነታቸው እና በኢትዮጵያ ላይ እንዲያምጹ ማነሳሳት ነው። በደረታቸው የፖለቲካ ድርሰቶቹ ሁሉ ለማጉደፍ ያልሞከረው የኢትዮጵያ መልካም ታሪክ የለም። በሃይማኖቱ ሙስሊሞ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያን እድሜ 100 ዓመት አድርጎ ኦነጋዊነቱን ለማጽናት ሲል ብቻ በሰው ሃይማኖት በክርስቲያኖች መጽሐፍ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ገብቶ የተጠቀሰችዋ አገር ኢትዮጵያ እንዳልሆነች አድርጎ ለማቅረብ የክርስቶስ ሐዋርያትን ሳይቀር አላዋቂ አድር ለማቅረብ የሚቃጣው ካድሬ ነው ።>> ባጭሩ

 ኦነጋዊው አሕመዲን ጀበል>> ስንመለከት፤ እስላሙን ለማነሳሳት እንዲመቸው

<<«የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሙስሊሞች» እንባል ነበር ብሎ «ሦስቱ አጼዎችና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች» በሚለው ድርሰቱ ውስጥ ያቀረበው ትርክቱ የሚገርም ነው። «ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሙስሊሞች» የሚለውን አገላለጽ የራሱን ትርጉም ሰጥቶ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንደ ኢትዮጵያዊ አይቆጠሩም ነበር ያለን ሰውዬ እሱ ራሱ ግን LTV ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ «ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሙስሊሞች» ሲል ይደመጣል!>> ሲል አቻም ስለ ሰውየው ዓይን-ዓውጣ ውሸት አጋልጦታል።

በተጠቀሱ እስላማዊና ዓረባዊ አገሮች ሄደው በሥራም ሆነ በኑሮ የኖሩም ሆኑ እው እየሄዱ ቁርኣኑን የተማሩ ወጣት እስላም ኢትዮጵያዊያን ሴቶችና ወንዶች ብዙዎቹ አክራሪ እስላም ሆነው በመምጣት “አነጋገራቸው ጺማቸውባሕሪያቸውባሕላቸውአለባበሳቸው፤ “ዓረባዊ” በመሆን ሃገርን በማበጣበጥ ሳይመቻቸው በማድፈጥሲመቻቸው “በግሃድ” ብጥብጥንና ግድያን ያጎለብታሉ።  ስለ አክራሪው ውሃቢያ መጠነኛ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ይህ ካልኩኝ ወደ ርዕሱ ልግባ።

ባለፈው ሰሞን “እፎይ” የተባለ ኢትዮጵያዊ  እስላሞች የሚያመልኩት “በቁርኣንና ሃዲስ” መጽሐፋቸው ውስጥ <<መሐመድ የሕጻን ልጅ የወንድ --- ሞጭሙጯል>> ብሎ በማለቱ  የመሐመድን ስም በጸያፍ ቃል ሰደብኸዋል ብለው ባለበት እንዲታረድ አክራሪ ውሃቢዎቹ  በመሰጊድም በዩቱብም “ጂሃድ” አውጀውበታል።

በሌላ በኩል ልጁ “ሞጨሞጨ/መጠመጠ” ከማለት ይለቅ “ሳመ” የሚለው ለማለት ስለነበር ስለ ቃላቱ አቃቀሜ ስሕተት  ይቅርታ እየጠየቅኩ ደርጊቱ ግን የተጻፈና እኔን ለመሞገት የሚፈልግ “ኡስታዝ” ለመከራከር ዝግጁ ነኝ”  ብሏል እፎይ የተባለው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወጣት።

በሌላ ወገን ደግሞ “ሕጋዊ መጅሊስ አይደለም” ሲባል በብዙዎቹ ወሃቢያዎች ግን የተደገፈ “ሕጋዊ መጅሊስ ነው” ተብሎ በኦነጉ አብይ አሕመድ የተሾመውና <<ስለሾምኩዎት እኔን ይወዱኛል? አዎ! ወይም አልወድህም! የሚለው አንዱን ይምረጡ>> እያለ አስቂኝ የህጻን ባሕሪው ደጋግሞ አዳራሽ ውስጥ በሕዝብ ፊት ዓለም እየሰማው የተጠየቀው አዲሱ ተሿሚው “ኦሮሙማዊው የመጅሊስ ተጠሪ” እፎይ በተባለው የቁርዓንና ሃዲስ ጥቅሶችን እየጠቀሰ የሚከራከራቸው ወጣት “ሕጋዊ ክስ እንደመሰረተበት ብቻ ሳይሆን (ታስሮ የተፈታ ይመስለኛል፤ ካልተሳሳትኩኝ) እኝህ መሪ “ዩቱብ ላይ” ያስተላለፉት መልዕክት እንደ ወጣቶቹ አስጸያፊ ቃል እየተጠቀሙ ልጁን ሲሰድቡና ንትርክ ውስጥ ገብተው አድምጬአቸው እፎይም <<እንደ እርስዎ የመሰለ ትልቅ አዛውንት እና መሪ ጸያፍ ስድቡን ትተው መከራከር ከቻሉ በጨዋ ይምጡና ይከራከሩኝ>> በማለት መልስ ሲሰጣቸው አድምጬ ገርሞኛል። እሳቸውም ከመከራከር ይልቅ ወደ ክስ መሄድ መርጠዋል።

ሌላው አስገራሚ የታዘብኩት ጉዳይ መስቀል አደባባይ በሺዎቹ የሚቆጠሩ እስላሞች <<እፎይ ይገደል>> እያሉ በማቸው ዕለት ተሰልፈው አዲስ አባባን ቀውጢ ሲያደርጓት እና “የአላህ ቤት ነው” ብለው እስላሞች የሚጸልዩበት መስጊድ ውስጥ በሥርዓት የእስልምና መዝሙር እየተዘመረ <<እፎይ የተባለ መልኩ እንደዚህ አከላተ ቅርጹ እንደዚህ ..የመሰለ በቅርቡ ይገደላል>> እያሉ ጂሃዲስቶቹ ያወጁትን አስደንጋጭ የግድያ አዋጅ ለመሸፋፈን እንዲመቻቸው <<ይገደል>> የሚሉት እስላሞች Tekbir Media - ተክቢር! በሚል ፌስቡክ የሚታወቀው  ሥራዩ ብየ የምከታተለው ታላቅዋንና ሰፊዋን ሃገር ያስታቀፉት ነገሥታቶቻችንን ስም በማጠልሸት የተጠመደው ይህ ዋሃቢስት "ዩ ቱበር“ እና "ቲክ ቶከር”“በቁጥር እዚህ ግባ የማይባል የጥቂት ሰዎች የተናገሩት ነው” በሚል <<ክብደት እንደሌለው>> ለማሳየት ሲያጣጥል ሰምቻለሁ።

እንዲህ ከሚሉት ቀንደኛው እጅግ “ሞለጭላጫና የተካነ አሰመሳይ” ፤ ‘ዕብሪቱ” መጠን ያለፈ፤ የነ አሕመዲን ጀበል ጋሻ ጃግሬ የሆነው ፎቶው ላይ የምታዩት ልጅ  ነው።

ይህ ደግሞ የውሃቢዎቹና የሰለፎቹ የቆየና የለመድነው “ቀንደኛ” መገለጫ ባሕሪያቸው ነው።

ይህ የሚያስታውሰኝ “ኦሮሚያ በሚባለው የሞት ምድር “የሚታረደው ሁሉም አምሐራ አይደለም ብዙ አምሐራዎች በሰላም እየኖሩ ነው ብለው እንደሚያጣጥሉት የሽፋን ስልት” ተመሳሳይ ነው።

ከዚህ በታች ያለው ፎቶግራፍ << ሠፊዋን ሃገር ለፍተው ያስረከቡን ኢትዮጵያን ነገሥታቶችን ስም በማጥፋት የተጠመቁ “በጣሊያን ወረራ ወላጆቻቸው ለጣሊያን አድረው ሃገር የወጉ ጸረ አምሐራ “የአስካሪ (ባንዳዊ) እስላም” ልጆች እና የጂሃዳዊው ዋሃቢያው እስላሞች መፈክር ነው። ሃገራዊ ቋንቋ ሳይሆን ዓረብኛ የተጻፈበትን ባንዴራቸውን እዩት።

ሰለፊ ጂሃዲሰቶቹ ቁርአናቸው ገልጠው ከመከራከር ይልቅ “መግደል፤ ማረድ” የለመዱበት ባሕሪያቸው መቸ እንደሚያቆሙት ይገርመኛል (አመጽ ለምን እንደመመሪያቸው እንደሚያደርጉት አልገባኝም። ምባት ከታች በተለጠፈው የተለያዩ የቁርዓን/ሃዲስ አንቀጾች እውነት ይሆን?

እፎይ በተባለው ልጅ ላይ ጥቂት ሰዎችም ይሁኑ መቶና ሺሕ ሰዎችም ይሁኑ “የይገደል” አዋጅ የሚያሳየው “መሟገት የማይችል አቅመቢስነት ወይስ በሚያምንበት መጽሐፍ ዕውቀት የሌለው የተጻፈውን ማንበብና መረዳት የማይችል አማኝ በመሆኑ?” ችግሩ ምንድነው? አንድ ሰው ስለ ክርስቶስ ወይንም ስለ መሃመድ መጥፎ ቃል ስለተናገረ ዓለም ምድሩ የሚገለበጥበት ምክንያት የለም። መፍትሔው መከራከር ነው! አለቀ!

እውነት ለመናገር ልጁ እንዳደመጥኩት <<ቁርአናቸውን እያነበበና እየጠቀሰ>> በሚገርም ሁኔታ ሲከራከራቸው እና የሚሰብኩት ስብከት እውነታ እንዳልሆነ ከቁርኣናቸው እየጠቀሰ ሲከራከራቸው ሰምቼው  ‘እየተንደፋደፉ ወደ ክርክሩ መድረክ በመምጣት ሲከራከሩት የነበሩት እስላሞች (ሸኮች ሁሉ ሳይቀሩ)” እያፈሩ መልስ ሲያጡ ሰምቻለሁ።

 እሱ ብቻ ሳይሆን እስልምና ሲከተሉ የነበሩ ወደ ክርስትና የተጠመቁ እፎይ የተባለው ወጣት የሚደግፉ “ዓረብኛውን ጽሑፍ የሚያውቁ” ወጣት ተከራካሪዎች እስላሞቹን በሚገርም ሁኔታ ሲወጥርዋቸውና መልስ ሲያንሳቸው አድምጬ ገርሞኛል።

ሆኖም ዋሃቢያዎቹ የተጠቀሙት እርምጃ ልጁን ተከራክሮ ካማሳመን ይልቅ “ይገደልን” ምን አመጣው? እኔን የሰደቡ ግደልዋቸው ብሎ “ነብስ ማጥፋት” መሐመድ ፈቅዶ ከሆነ እኔ አልገባኝም።

በክርስትያን እምነት ላይ 10 ቃላት መመሪያ ግን አትግደልየሚለው ብቻ ሳይሆን <<አያውምና ይቅር በላቸው>> ነው የሚለው።እኔን የሰደቡ ሁሉ ይቅር በቸው/በላቸው/ ነው የሚለው እንጂ ስለሰደቡኝ ግደላቸው አላለም። እንዲያ ብሎ ከሆነ ደግሞ ስሕተት ነው።

እስልምና በጣም ብዙ የተለያዩ እምነቶችና ጥቅሶች አሉት፡ ማንን እንመን?

73 የእስልምና ክፍሎች አሉ። እነዚህ ሁሉ “ቁርኣን” እንቀበላለን ይበሉ እንጂ እርስ በርስ ቁርኣኑን በመተርጎም ላይ አይጣጣሙም። ባለመጣጣማቸውም ይገዳደላሉ። እንዲህ ባለበት ሁኔታ “እፎይ” የተባለው ልጅ ቁርኣናቸውን እየጠቀሰ ሲከራከራቸው (የተጠቀመውን ቃል አጠያያቂ እንዳለ ሆኖ) እስላሞቹ ጋር ያደረገው ክርክር ሳደምጥ እስላሞቹ መጽሐፋቸውን የሚያውቁ ሆኖ አላገኘሁዋቸውም (እስካሁን ድረስ ያየሁዋቸው መረጃዎች ከሆነ ፤ ሌላ ያላየሁት ከሌለ በቀር )።

ሆኖም መስጊድ  ላይ አሰላም አለይኩም ወራሕመቱላህ” እና “አላሁ ወአክበር” እያለ ግድያን (ያውም መስጊድ ውስጥ) የሚያውጅ ጂሃዲስቱ ውሃቢያወ ቡድን (የተለጠፈው ቪዲዮን አድምጡት) እውን ቁርዓናቸው ግድያን ያበረታታል?

የኢትዮጵያ አክራሪ እስላም በፖለቲካውም በመንግሥት ውስጥም በሽምጥ ተዋጊው ክፍል ውስጥም በስፋት ተንሰራፍቶ “ክርስትያኑን” በማረድ ለበርካታ አመታት ምንም ሳይሆን አሁን የቀጠለ መሆኑን ታውቃለችሁ። ክርስትያኑ ደግሞ “ል ብሎ” በዝምታ ግድያው እንዲቀጥል አድርጓል። ኦርቶዶክስ እንወክላልን የሚለው ዋናው “ሲኖዶስ” እንኳን ግድያን እና የግድያ አዋጅ በሕግ ከስሶ ሊያስቆም  “ተገንጥሎ የትግራይ አባ ሰላማ ሲኖዶስ እያለ  ጳጳሳት የሾመ <<የወያኔ አባ ሰላማ>> ላይም ምንም እርምጃ አልወሰደም። ማፈሪያ ሲኖዶስ ነውና ኢትዮጵያ ተዋርዳለች! ይገርማል።

ታስታውሳላችሁ ካሁን በፊት <<ያንቀላፋ የሚመስለው ጽንፈኛው የውሃቢው ቡድንሰበብ የማሽተት ሱሱ ተነስቶበት ፋኖ ይውደምፋኖ ሌባ ማለት ጀምሯልጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 4/28/22 የሚለው ጽሑፌ?

ትችቴ ያተኮረው “አክራሪው ዋሃቢያው” ቡድን አዲስ አበባ ዋናው መስጊዳቸው ውስጥ ሐጢያታቸው እንዲሰረዝላቸው በጎ እንዲያስቡ ከመጸለይ ይልቅ <<ፋኖን ሌባ>> <<ፋኖ ይገደል>> በሚል የአማሐራን ሕዝብ ጭፍጨፋ ለማስቆም <<ጀነሳይድ” የታወጀበትን ማሕበረሰብ መከታ ለመሆን ጫካ የወጣን ፋኖ  <<ባለበት ሁሉ እንዲታረድ>> ጂሃዳዊ ጥሪ ሲያደርጉ ምንም አልተኮነነም

በዛው ጽሑፌ ዋሃቢያው ጫካ ውስጥ አምሐራን በማረድ ብቻ ሳይወሰን አዲስ አበባም ውስጥ ሁለተኛ ምሽጉ እንደሆነች ለማሳየት የጻፍኩት ነበር።እስከዛሬ ድረስ ችለን እንጂ ተቻችለን አልኖርም የምትለዋ ውሃቢዎቹ የሚወድዋት 30 አመት ሙሉ መፈክራቸው ከጥቂት ወራት በፊት ባሳዩት አዲስ አበባ የመስጊድ ሰልፋቸው ላይ በጽሑፍ ዘርግተዋት ሲያስነንብዋት የነበረቺው ይህች የብዙዎቹ ጽንፈኛ ዋሃቢዎች ተወዳጅ መፈክራቸው ዛሬም እፎይ” በተባለው ልጅ ላይ እየተጠቀሙባት ነው።

ዋሃቢያው በሚጸልይበት መስጊድ  ውስጥም “እፎይ የሚገደት ሰዓት እየመጣ ነው” እያሉ ሲቀድሱ መስማት የሚገርም አገር ሀኗል።እና ወዴት እያመራን እንደሆንን አመላካች አዋጅ ነው።

ዋሃቢያው ያንቀላፋ ቢመስልም ዛሬም ትንሽ ከሸተተቺው ያችን የሚፈልጋትን ምክንያት አድርጎ <<ግደለው፤ እረደው፤ አፈናቅለው>> የምትለዋ የማረድ ሱሱ እየተጠቀመባት ነው።

ሌላ አጀንዳ ካልመጣ በክል 2 እስልምናው ለጎሰኛነት መገልገያ እየሆነ ከመጣ መቆየቱን እንመለከታለን።

ሳንታረድ በሰላም እንሰንብት!!

ጌታቸው ረዳ

 

Saturday, March 15, 2025

አፓርታይዳዊው የኦሮሙማው ሥርዓተ ዘመን የፓስፖርትና የደሕንነት ክፍሎች በተጓዦች ላይ እያደረሳችሁት ያለው ሰቆቃ እግዚአብሔር አምላክ ድፍት ያርጋችሁ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 3/15/25

 

አፓርታይዳዊው የኦሮሙማው ሥርዓተ ዘመን የፓስፖርትና የደሕንነት ክፍሎች በተጓዦች ላይ እያደረሳችሁት ያለው ሰቆቃ እግዚአብሔር አምላክ ድፍት ያርጋችሁ!!!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

3/15/25

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

3/15/25

ስለ ቦሌ አየርፖርት እና ስለ ዋናው “የፓስፖርት እና ኢሚግረሺን” መ/ቤት ጉቦኛነት በሕዝብ ሕይወት ላይ እያደረሱት ያለውን ስቃይ ከመግባቴ በፊት ለዚህ ሁሉ ብልሹ አሰራር ተጠያቂው የዛሬው <<ሥርዓተ ኦሮሙማ>> እና የተወገደው <<ሥርዓተ ትግራዋይነት>>  የአመራር ብልሹነት እንደሆነ አንድ ነገር ብየ ወደ ዋነው ርዕስ እገባለሁ።

 ባለፈው በአፓርታይዳዊው የትግሬዎች ሥርዓተ ዘመን እና አሁን ደግሞ 6 አመት ያለንበት ኦሮሙማዊው የኦሮሞዎች ሥርዓተ ዘመን ሥራየ ብለው ኢላማ ያደረጉት በተለያዩ ‘የመንግሥት’ ዘርፎሮች ሕዝብን  በማስለቀስ የተጠመዱ ናቸው።

ሁለቱ አፓርታይድ ሥርዓቶች አፓርታይድነታቸውን የተገበሩት በተለይም በአምሐራ ሕዝብ  ላይ (የጋሞዎችን እንዲሁም የጉራጌዎችን ስቃይ ሳንረሳ ማለት ነው) ሲሆን ሁለቱ አፓርታይዶች እየተፈራረቁ ያደረሱትን በደል አሁን ግልጽ እንደሆነላችሁ እገምታለሁ።

የኦሮሙማ እና ትግራዋይነት ትርጉም ደጋግሜ እንድንነጋገርበት ሁሌም የምጽፈው ከምንም ተነስቼ አይደለም። ምክንያት አለኝ። ሁለቱም ቃላቶች በጥሬ አተሮጓጎም እየተተረጎሙ የሚነገሩ ትርጉሞች ብዙ የዋሆችን ለማታለል ተሞክሯል። ሃቁ ግን ሁለቱ ማሕበረሰቦች እንደ “መከታችን” ናቸው ብለው የሚከተልዋቸው ድርጅቶች አሉዋቸው። ሁለቱ ድርጅቶች ደግሞ ትግሬው (በትግራዋይነት) ኦሮሞዎቹ ደግሞ (በኦሮሙማ) ርዕዮት የሚመሩ ናቸው።

ሁለቱም የሚመሩበት ማኒፌስቶ “ፋሺዝም” ነው።

ሌላ ቀርቶ ሁለቱ ማሕበረሰቦች የሚከትለዋቸው የተለያዩ ሃይማኖቶቻቸው ሳይቀሩ ጭምር ከማንኛቸውም ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ይልቅ ግንጠላንና ጥላቻን ለሚሰብኩ <<ለኦነጎች/ ኦፒዲኦዎች እና ለወያኔዎች>> ከፍተኛ ድጋፍና ፍቅር እንዳላቸው የሚያከራክር አይደለም።

ኦነግ ማለት ለዘመናት በብዙሓኑ የኦሮሞ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ድርጀት ነው። <<ኦነግ ማለት ኦሮሞ>> <<ወያነ ማለት ትግራይ ሕዝብ ነው>> ስል የከረምኩነት ክርክር ሁለቱ ማሕበረሰቦች ከሚከተሉትና ከሚሰጡት ድጋፍ በመነሳት ነው። በቁጥር ብዘሓን የሚባሉት ትግሬዎችም ሆኑ ኦሮሞዎች “ወጣት የዕድሜ ጣራ” ያለ ክፍል ነው። ወጣቱ ደግሞ የነዚህ ድርጅቶች አማኝ ነው።

 ስለሆነም ርዕሱ ለይ የጠቀስኩት ቃል <<ኦሮሙማ>> በየዋህ ተርጉሙ ሳይሆን በሚወስዱት “መንግሥታዊ” እርምጃ እና ፖለቲካዊ ትርጉሙ ዘመናዊ ትምሕርት በቀሰሙ የኦሮሞ ተገንጣይ “ምሁራን” እምነት (ኦነገ መሪዎች ዳውድ ኢብሳ ዲማ ነገዎ፤ ሌንጮ …ጫልቱ….ብዙዎቹ አብይ በሚመራው ኦሮሙማዊው መንግሥስት ሥር ዛሬም እፓርላመውም ሆነ በሚኒሰትሮች ደረጃ ሥልጣን ላይ ሆነው ፖለቲካዊው የኦሮሙማው አጀንዳ በመተግበር ላይ ናቸው)  “ኦሮሙማ” የሚል ቃል ሲተረጉሙት <<ኦሮሚያን በቅኝ ግዛት የያዘው የአቢሲኒያ (ኢትዮጵያ) ተስፋፊነት ማለትም የቢሲያኒ ሃበሻዎች ሥልጣኔ ባሕል ፤ቋንቋ፤ እና ሃይማኖት የሚጻረር ነጻ አሮሚያ ለመመስረት የምንጠቀምበት አታጋይ መርህ ነው>> በማለት << (ኦሮሙማ) ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን የዐምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ ይታይ ነው።>> ሲሉ በግልጽ ነግረውናል።

 አንዳንዶቹ ደግሞ <<ኦሮሞነት>> ማለት እንጂ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጻረር ባሕሪ  ነገር የለውም ሲሉ ሰምተናቸዋል። ከላይ ያለው የመጨረሻው አባባል   የዋሃን ሊያታልል ይችል እንደሆን እንጂ ከሥር መሠረቱ የቃሉ አመጣጥና የቃሉ ለውጥ ከጥንት የተጻፉ መጻሕፍት ስንመረምር እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን ትርጉም ያለው የዜግነትና ሌላ ሃገርነትን የሚመኝ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የሚያልም አጠራር ነው

የትርጉም ጉዳይ በዚህ ከሄድንበት አሁን “ፍንፍኔ እና ሥልጣን ኬኛ” ብሎ በኢ-ሕጋዊ አያያዝ ሥልጣን የያዘው የኦሮሙማው ቡድን <<የፓስፖርትና የደህንንት ክፍል>> (ኢሚግረሺን እና ፓስፖርት) ብሎ ራሱን የሚጠራው ኦሮሞዎችና ኦሮሙማው ሥርዓት የሚያገነብሱ የተሰገሰጉበትና የሚቆጣጠሩት ድርጅት ከዋናው ጽ/ቤቱ ጀምሮ ቦሌ ላይ ያቋቋመው ቅርንጫፉ ዘርን (ነገድ ማለት ነው)  በተለይም ትግሬዎችን እና አምሐራዎችን እየለየ ጉቦ ለመቀበል እንዲያስችለው ተጓዡ ለበረራው አንድ ወይንም ሁለት ሰዓት ሲቀረው “ፓስፖርታቸውን እየነጠቀ>> ጉቦ እንዲሰጡ ልዩ ቦታ በማሰር ያሰቃይዋቸዋል። አንዳንዱም እንደሚገርፏቸው ይነገራል።

ባለፈው ጥቂት ወራት የአንድ ወዳጄ ባለቤት ከዚህ ወደ አገርቤት ሄዳ ስትመላስ የገጠማትን ልንገራችሁ። ከወራት በፊት አገር ቤት ሄዳ ተመልሳ ወደ አሜሪካ መምጣትዋን ታስታወስና እንደገና ተመልሳ ለሁለተኛ ጊዜ እንደ እናትዋ የምታያቸው የባለቤትዋ እናት “በማረፋቸው” ለቀብር መሄድ ስለነበራት አንደገና ተመልሳ በመሄድዋ የቦሌ አያርፖርት የፓስፖርት ሰውየ በነገዱ <<ኦሮሞ>> የሆነ መጀመሪያ ያነጋገራት በኦሮምኛ ሲሆን <<አዝናለሁ እኔ ኦሮምኛ አላውቅም ትግርኛ ወይንም አምሐርኛ ነው የማውቀው፤ ምን እንዳልክ አልገባኝም>> ብላ ስትለው፤ <<ጊዜሽ አልፏል በግድ ኦሮምኛ አማወቅ አለብሽለመሆኑ ምን ምስጢር ስላለሽ ነው የምትመላለሺው? >> ሲል ይጠይቃታል።

ልጅትዋም << ተደናግጣ ፤ ምንም ምስጢር የለኝም አገሬ ነው ፤ መመላለስ አልችልም እንዴ? አሁን የናቴ ቀብር ፈጽሜ ወደ አሜሪካ እየተመለስኩ ነው>> ብላ ስታስረዳወ <<አገርሽ አሜሪካ ነው በማለት “ፓስፖርትዋን” ነጥቆ “ስልክዋን እና ዕቃዋን ነጥቆ” ብዙ “የሶርያ ተወላጆች” በታጎሩበት ማጎርያ እስርቤት ወስዶ በረራዋን አስሰርዞ ሙሉ ቀን አስሮ ሲመሻሽ መጨረሻ አንድ ደግ ሰው ሰልክ አሾልኮ እንድትደውል ስላደረገ፤ ቤተሰቦችዋም መብረርዋን እንጂ “መታገድዋን” ሳውቁ ደንግጠው ሁኔታው ከነገረቻቸው በሗላ፤ ጉዳዩ የዘር ጉዳይና “ጉቦ” መሆኑን ስለተረዱት ልጅቷ ወደ አሜሪካ ወደ ሥራዋ በአስቸኳይ መመለስ ስለነበራት ፤የመክስስና ከባለጊዜዎች ጋር መነካካት እዛ ለሚኖሩ ቤተሰብ አደጋ ስሰለሚኖሮው ሰግተው አማራጭ የወሰዱት  መነገድ “ኦሮሞ” የሆኑ የሚያውቋቸው አንድ ጎረቤት ሰው ወደ ቦታው ይዘው በመሄድ “ፓሰፖርቱን” የያዘው የፓስፖርትና የደሕንንቱ ሰውየ ዘንድ በመሄድ “ስለ ጉዳዩ በመነጋገር፤ በማግስቱ እንደ ሚጋብዙትና በአንድ የግብዣ ቦታ እንደሚገናኙ ተቀጣጥረው፤ ልጅቷን አስፈትተው በማግስቱ ተገናኝተው ለሰውየው “ጉቦ” ሰጥተው “ፓስፖርትዋን” በኪሱ ይዞ እንደሚመጣ ስለነገራቸው ፓስፖርቱን መልሶላቸው ካሰበቺው የመብረር ቀን ተሰናክላ እንደገና ጊዜ ጠብቃ ልጅቷ ሌላ በረራ ፈልጋ ወደ አሜሪካ መመለስዋን ነገረችን።

በየአመቱ 25 ሚሊዮን መንገደኛ የሚጓዝበት የቦሌ አየርፖርት “ሕገ ወጥ ዕጽ” አመላላሾች ምቹ የማሸጋገሪያ መስመር መሆኑን በብዙ ዜናዎች መዘገቡን እንዳለ ሆኖ፤ ቦሌ ላይ የሙስና አሰራር በማንኘውም ኢትዮጵያዊ እና የውጭ አገር ተጓዥ የገንዘብና የወርቅ ዝርፍያ ቦሌ ላይ እየደረሰባቸው እንደሆነ በየጊዜው ሪፖርት እየተደረገ ቢሆንም በተለይ ግን መንገላታቱ የሚበረታው “አምሐራዎችና ትግሬዎች” ላይ ከፍኛ በደል በኦሮሞ ተናጋሪ “የፓስፖርትና ኢምግረሺን” ሠራተኞች አማካይነት መሆኑን በተደጋጋሚ የደረሰ ያለ በደል ነው።

አየርፖርቱ ይህንን አስመልክቶ ከጥቂት ወራት በፊት <<“መስፍን ጣሰው” ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ>> ወደ ሚዲያ ቀርቦ የተነጋረውን እዚህ ላስታውሳችሁ እንዲህ ይላል፡

<<አንዲት መንገደኛ ወደ አሜሪካ ስትሄድ ‘ፐርሰናል ቫሊዩ’ ይዤ ነበር “ወርቅና ዶላር” ይዘሽ መውጣት አትችይም ተባልኩ፤ ከብዙ ውጣ ውረድ እንግልት በሗላ “ዶላሩን ወስዳ ሌላውን ለቀቀቺሊኝ” የሚል ክስ ነው የቀረበው። በጊዜው ይሄ መረጃ እንደ ደረሰ “በ ሲ ሲ ቲቪ” ታይቶ ሠራተኞቹ ተለይተው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ሕጋዊ ክስ ይመሰረትባቸዋል፤ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃም ይወሰድባቸዋል።በነዚህ “ጉምሩክ ካስተም” ሕጋዊ እርምጃ ይወስድባቸዋል ብለን እናስባለን።>>

ማለቱ ይታወሳል።

 አቶ መስፍን መግለጫውን ሲያጠቃልል በደምበኞች ላይ ለሚደርስ በደል የቅሬታ ማቅረቢያ “ዴስኮች” ፈጥረናል ፤ በጥቂት ቃናት ውስጥ ሥራው ይጀምራል።>> ሲል ጉዳዩ ለማስቆም የተደረገ ጥረት መኖሩን ከሥራ አስኬያጁ ቢነገርም፤ ዛሬም ጉበኞች ተጓዡን እያሰቃዩት ነው።

የቅሬታ “ዴስክ” ቢዘጋጅም ደምበኞች ለወፊቱ ሲመለሱ በነሱና በቤተሰቦቻቸው  “ሪቨንጅ” (የብቀላ ጥቃት) እንዳይደርስባቸው የሚሰጉ ስለሚኖሩ እውነት ኦሮሙማው ሥርዓተ መንግሥት ይህንን በደል ለማስቆም ፍላጎት ካለው የደምበኛ ቅሬታ ማቅረቢያ ክፍል (ዋናው ኢሚግረሺን ውስጥ የለም) ኤርፖርቱም ውስጥ ካለም << ከደምበኛች ቅሬታ መቀበሉ በጎ እርንጃ እንዳለ ሆኖ፤ ሌላ ተጨማሪ ሃሳብ ላቅርብ፡

ይሄውም ”የሚመለከታቸው ድርጅቶች” <<አንደር-ካቨር>> (የምስጢር ሰራተኛ) ተራ መንገደኛ አስመስሎ ወርቅና ዶላር አስይዞ አንዲያልፍና “ጉበኛ ሠራተኞችን” እንደ ዓሳ ለማጥመድ እንዲመቸው ምስጢራዊ (አንደር ካቨር ፖሊስ) ማዘጋጀት ይኖርበታል። ካልሆነ “ቅሬታ ማቅረቢያ” ሳጥን እና ክፍል ብቻ ሙሰኛን ለማስቆም በቂ አይደለም። በተለይ በዋናው መስርያቤት የሚታየው አስለቃሽ የፓስፖርት ዘረኛ አሰራር የምንሰማው ዕሮሮ አሳሳቢ ነው።

 በተረፈ ወደ አረመኔዎቹ የዓረብ አገሮች በባርነት እየሸቀሉ ያጠራቀሙትን ጥቂት ገንዘብና ወርቅ እንዲሁም ሻንጣ እየዘረፉ እህቶቻችንን ደም የሚያስለቅሱ ጨካኞች ‘ልጅቷ እንዳለቺው’ <<እግዚአብሔር አምላክ ድፍት ያርጋችሁ!!!!>>

ጌታቸው ረዳ  

Ethiopian Semay