Wednesday, August 28, 2024

ወያኔዎች ከራስ መንገሻ ዮሐንስ ለነጮች መነጠፍ የወረሱት ባሕልና በአብይ አሕመድ ተባባሪነት በትግራይ መልከዓ ምድር ላይ የሚንጎባለለው ‘አጭበርባሪው ዝሆን’ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/28/24

 

ወያኔዎች ከራስ መንገሻ ዮሐንስ ለነጮች መነጠፍ የወረሱት ባሕልና በአብይ አሕመድ ተባባሪነት በትግራይ መልከዓ ምድር ላይ የሚንጎባለለው ‘አጭበርባሪው ዝሆን

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

8/28/24

ፕሮፌሰር ሌማርቻንድ (Professor Lemarchand) የተባሉ ምሁር ሲአይኤንን (CIA) “ስድ ዝሆን” (‘rogue elephant’) ይሉታል። ይህ ቀጪ የሌለው ሁሉንም ሕጎችና ፍጡራንን የሚረጋግጥ “ስድ ዝሆን” በአገር ገንጣዩ አብይ አሕመድ ተባባሪነት ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በክብር ተንሳፎ መቀሌ ከተማ በመገኘት የትግራይ ወያኔ መሪዎች ራሳቸው እንደቻሉ እንደ አገር መሪዎች ቆጥሮ የወያኔ ባንዴራ ጠረጴዛው ውይይት ላይ በክብር ተቀምጦላቸው ከሲ አይ ኤው ወኪሎችና አምባሳደር ተብየው ሲጨባበጡና ሲሳሳቁ አይተናል። “እርይ በይ አገሬ CRY MY BELOVED COUNTRY!!!!

የዚህ “ስድ ዝሆን” ከጅምሩ የኤርትራ ሽምቅ ተዋጊው የሻዕቢያው ቡድን በሙስሊሙ ኤልኤፍ/ጀብሃ/ ላይ እንዲዘምት ሪቻርድ ኮፕላንድ የተባለው የ ሲ አይ ኤ ወኪል በ1969 የዛሬው ኢሳያስ አፈወርቅን በአካል በማነጋገር ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል በመሳሪያ ትጥቅና ምክር በመስጠት ሲ አይ ኤ ከፍተኛ በደል ፈጽመውብናል። 

ያ አልበቃ ብሎት ሲ አይ ኤ ከባሕር መነጠቃችን ሴራ ጀምሮ እስከ አፓርታይዳዊ  የወያኔ የጎሳ አስተዳደር መመስረት እጁ ረዢም ነበር።በዚም አልተወሰነም የዩሁዲ ሃይማኖት ተከታዮችን የእስራል ዜጎች እንጂ ኢትዮጵያዊያን አፍሪካዊያን አይደሉም በማለት ዜግነታቸውና ማንነታቸውን በሴራ በመለወጥና በማሳመን በሺዎቹ የሚቆጠሩ ወጣቶች ፤ሕጻናት (ማንነታቸው ለመናገርና ለመከራከር መብት የሌላቸው ሕጻናት) እና በምርኩዝና በሰው ተደግፈው የሚሄዱ አረጋውያን የኢትዮጵያ ዜጎች ከመንግሥቱ ሃይለማርያም ጋር ተመሳጥረው ወደ እስራል በገንዘብ ልውውጥ (ሂውማን ትራፊኪንግ ብየ የምጠራው)  ወደ እስራኤል በማስገባት እዛው የተወልዱ አዲስ ትውልዶች ከፍልስጢኤማዊያን በሚደረገው ጦርነት እንዲያግዙት እየመለመለ ለጦርነት እሳት እየማገዳቸውና የዘርና የቀለም ልዩነት ተጠቂ እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

THE SLAVE TRADE IN FALASHA OF ETHIOPIA” የሚለው የወዳጄና አስተማሪየ ዶ/ር ዓለሜ እሸቴ ጽሑፍ ያንብቡ።በተጨማሪም Operation Solomon- the darling rescue of the Ethiopian Jews) By Stephen Spector) የተፈፀመው ኢ ሕጋዊና የዜግንት ነጠቃ በዝርዝር በሚደንቅ አጻጻፍ የተደረገው ሴራ ሳይሸሽግ ይነግረናል (አንብቡት፤ ታዝናላችሁ)።

በአብይ አሕመድ ተባባሪነት ትግራይ ለማስገንጠል ከሰንቃላማችን ማጥፋት ጀምሮ የትግራይ ሪፑብሊክ ግንጣላ በይፋ የሚሰብኩ ትግራይ ወስጥ በግሃድ እንዲንቀሱ መፍቀድ ብቻ ሳይሆን፤ ይህንን የግንጠላ አጀንዳ ለማካሄድ የግንጠላ አጀንዳቸውን ሕጋዊ ለማድረግ ሳልሳይ ወያኔ የመሳሰሉ ወያኔን የተኩ አዳዲስ ባንዳዎች ፕሮግራማቸውና አላማቸው የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት እንደሆነና የሸዋ አማራዎች ስሪትና የትግራይ ሕዝብ ቀበኛ የሚልዋት ኢትዮጵያን ለመፋለም በውድድር ምርጫ ተመዝግበው እውቅና እንዲሰጣቸው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ  “ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት” ተብየው ሳይቀር ማኒፌስቶአቸው በማቅረብ እንዲመዘገቡ ከተዘረዘሩት ስምንቱ የድርጅቱ ዓላማዎች ውስጥ በመጀመሪያ ረድፍ የሚነበበው “ሃገረ ትግራይ” ለመመስረትየሚለው ተቀባይነት አግኝቶ እንደተመዘገበ የሳልሳይ ወያኔ አቶ ሃይሉ ከበደ የተባለው በተደረገለት ቃለ መጠይቅ ነግሮናል።(ሰነዱ ለቦርዱ የቀረበው የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተደረገ በኋላ ነው።)

ዛሬ ደግሞ መለስ ዜናዊን የተካው የአሜሪካኖቹ አዲሱ “ቹዋዋ” (ፑፐት) አብይ አሕመድ ለሀገር መበታተን መነሳሳት የማይታለፍ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው ብለው ለሚያምኑት አሜሪካኖች ትግራይ ቀዳሚ አጀንዳቸው እንድትሆን እየተባበራቸው ነው።

እንደምታውቁት  ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ (ሶቪየት ከፈረሰች ወዲህ) አሜሪካ የሚመራው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በጎሳ ንቃተ ህሊና በማተኮር ለማስገንጠል አዳዲስ አገሮች ለመሆን አሰፍስፈው ባገጠጡ “የክልሎችና የመንደር ልሂቃን” ፍለጋ ላይ ተጠምዶ ይገኛል። ይህ የማፍረስ አጀንዳ “ፕሮፊለቲክ ፓናሲያ” ብሎ ይጠራዋል፡ (ካልተሳሳትኩ ፈውስ ያልተገኘለት የመከላከያ ፈውስ/መፍትሔ’ እንደማለት ይመስለኛል (የሚገርም ነው!!!)  

ኢትዮጵያ ፤ሱዳን እና ሶማሊያ ለዚህ ምሳሌ ናቸው። በተለይም የ ሲ አይ ኤ የአፍሪካ መናሃሪያ የመጫወጫወቻቸው ሜዳ የሆነቺው ኢትዮጵያ “በጎሳ” (ኤትኒክ ፌደራሊዝም) መጋዝ እተገዘገዘች ማየታቸው በጠመንጃና በመድፍ ባይሮፕላን ድብደባ ለማፍረስ ከባድ የሆነቺውን ጥንታዊትዋ አገር፤ በጎሳ ፖለቲካ ታምሳ ስትንገዳገድ ማየታቸው ሌሎች አገሮችን ለማፍረስ ቀላል እንደሚሆንላቸው ደስታቸው ወደር የለውም።

የብሔር ድንበሮች፣ የሀይማኖት ድንበሮች እና የጎሳ ድንበሮች ያልነበራት ሶማሊያ በዓረቦችና  በ ሲ አይ ኤ መጋዝ  ተገዝግዛ ትገኛለች። ዛሬም ትግራይ ወስጥ ተመሳሳይ መጋዝ በፍጥነት እየሰራ ነው። ጣሊያኖችን ማማ ሚያ (እናቴ ድረሺ!) ያስባለቻቸው ኢትዮጵያዊትዋ ሰንደቃላማችን ካሸነፈቻቸው ምድር “በትግራይና በዶጋሊ” ፤ እንዲሁም  “ሱዳኖችን በሰሐቲ” ፤ በተጨማሪም “አሜሪካኖችን፤ ግብጾችንና ቱርኮችን በጉንደትና (1867) በጉራዕ (1868 በራሳችን ዘመን አቆጣጠር) ተውለብልባ ያሸነፈቻቸው ሰንደቃላማችን በነኚህ  ተራሮች ላይ እንዳትውለበለብ በወኪሎቻቸው በወያኔና ሻዕቢ በኩል ስለታገደች ቱርኮች፤ ዱርቡሾች፤ ግብጾች፤ አሜሪካኖችና ጣሊያኖች ዓላማቸው ተሳክቶላቸዋል።

የማፍረሱ ሂደት ጋብ ያዝ ለቀቅ እያደረገ ሲጓዝ የነበረው የማፍረስ ጉዞው ድንበሮች ቢኖሩም ባይኖሩም፣ በአሜሪካ መንግሥትና በሲ አይ ኤ ወኪሎችዋ በእነ “ፓል ሄንዝ” እና “ሄርማን ኮኸን” የተቀናጀው የቆየው ኢትዮጵያን የማፍረስ ሥራ  ዛሬም እንደ አዲስ አገርሽቶበት ይገኛል።

በሲ አይ ኤ ጣልቃ ገብትና ዕቅድ የሚከተሉት አገሮች ፈርሰዋል ወይንም በመፍረስ ላይ ናቸው፡

1. ሶማሊያ

2. ኢትዮጵያ

3.ሊቢያ

4.ዒራቅ

5. አፍጋኒስታን (ባትፈርሰም ለዜጎችዋ የምድር ሲኦል አንደሆነች ይነገራል) አሜሪካኖች የተጫወቱት ሴራ ነው።

6. የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ

7. የመን

8. ሶርያ

9. ሱዳን

10. ሄይቲ

11. ኤርትራ፤-  

ኤርትራ፤ ባትፈርስም በተደረገው ጥናት በዓለም በፍልሰት ብዛት የያዛች አገር ኤርትራ ነች። ሕዝቡ “ፈልሶ” ለስደትና ለተመጽዋችነት ተዳርጎ አገሪቱ ባጀት ስለሌላት ጥቁር ገባያ ለገቢ ማስገኚያ በመጠቀም መንግሥት ተብየው ወኪሎቹን በየአገራቱ በመሰማራት በረሃ እያለ ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ ጥቁር ገበያ እንደ ኢምፖርት ኤክስፖርት የገቢ ምንጭ ቆጥሮ ለራሱ ሥራ ማስኬጃው ይጠቀምበታል። ሕዝቡ ግን የገቢ ምንጭ ስለሌለው ውጭ በሚኖሩ ኤርትራኖች ለቤተሰቦቻቸው በሚልኩት ገንዘብ እየቆነጠረ ይኖራል።

ዜጎችዋ የኢንተርኔት አቅርቦት እቤታቸው ውስጥ አያገኙም። ሌላ ቀርቶ የእጅ ስልኮቻቸው ባትሪ ሲደክምባቸው (ቻርጅ ለማድረግ) ባትሪውን ለማሞቅ መሃል ከተማ ሄደው ገንዘብ በመክፈል ስልኮቻቸው እስኪሞሉ እዛው ትተውላቸው ሄደው በማግስቱ ይወስዱታል። ያልፈረሰ የሚመስል ግን ከፈረሱት አገሮች የሚቆጠር። 

ኢትዮጵያ በአሜሪካኖች ዕቅድ ከሚፈርሱት (ያው ያልፈረሰች ግን የፈረሰች “ፈይልድ ስቴት ነች) አገር አንዷ ስለሆነች፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በጎሳ ፌደራሊዝም የጀመረው የመለስ ዜናዊ ሴራና ተባባሪነት እውን ለማድረግ የመጀመሪያ ታርጌታቸው (ዒላማቸውን)  ለማሳካት “ትግራይ” ተመራጭ አካባቢ ሆና አግኝተዋታል።

ይኸየውም ሟቹ መለስ ዜናዊ የአሜሪኖችና የአውሮጳዊያኖች በተለይም የእንግሊዝ አይርሾች አሽከር ስለነበር፤ በመለስ አማካይነት ብዙዎቹ የወያኔ መሪዎች በነሱ ሥር የተመለመሉ ስለሆኑ (ስብሓትም በቃሉ መስክሯል) የአሜሪካን አምባሳደር የሚያክል ወደ መቀሌ በመሄድ ልክ “ትግራይ” እንደ አንድ አገር ተቆጥራ የተገንጣይ መሪዎችን እነ ጌታቸው ረዳን ብዙ ሰው አላወቀዉም እንጂ: “የእኔ ፍላጎቴ እንደ እናንተው ትግራይ አገር እንድትሆን ነው ፍላጎቴ በማለትባሳለፍነው ሓምሌ ውስጥ (ከአንድ ወር በፊት)የተናገረበት ቪዲዮው አለኝ): CIA እነኚህን ወንጀለኞችና ገንጣዮች እንደ ሕጋዊና ራሳቸው የቻሉ የአገር መሪዎች አድርጎ እስከ መቀሌ ድረስ ተጉዞ ሲያነጋግር ማየት ለብዙዎቻችን አዲስ ዜና ባይሆንም አሜሪካኖችን ትግራይ ድረስ ሄደው ሥራው እንዲሰሩ የፈቀደላቸው ምከንያት “አብይ አሕመድን ልክ እንደ የሱዳኑ አልበሽር (ዳርፉርን ጠቅሰው ደቡብ ሱዳንን ገንጥል የጀነሳይድ ክስም እንሰርዝልሃለን ብለው እንዳስፈራሩትና እንደፈጸመላቸው)  አብይንም በጀነሳይድ እንከስሃለን እያሉ ስለሚያስፈራሩት አድርግ የሚሉትን እያደረገላቸው፤ ዛሬ የቄሳርዋ አገር አምባሳደርና የሲ አይ ኤ ወኪሎች መቀሌ ድረስ ሄደው የድርጅት ባንዴራ ጠረጴዛው ፊት ለፊት አንደ የአገር ባንዴራ ተቆጥሮ ተቀምጦላቸው ንግግር ሊያደርጉ በቅተዋል። ይህ የአገራችን ሞት አበሳሪና የ ሲ አይ ኤና የጎሳ ፖለቲካ ያስተዋወቀው የጣሊያን ፋሺሰቶች ድል ነው

ዛሬ ትግራይ ውስጥ እየተደረገ ያለው ለፈረንጅ መነጠፍ አዲስ አይደለም። ወያኔዎች ለፈረንጅ መነጠፍ ያገኙት ትምሕርት ከራስ መንገሻና ከራስ አሉላ ያገኙት ነው። (ስለ ራስ አሉላ ሌላ ቀን አቀርባለሁ) ለምሳሌ ስለ ራስ መንገሻ ዮሐንስ ለዛሬ ይህንን እንመለክትና ልደምድም። 

ታሪኩ የተዘገበው የትግሬ ጠባብ ብሔረተኞች ብዙ ጌዜ ለሙግታቸው ድጋፍ የሚጠቀሙበት በዓድዋ ጦርነት የተገኘው ብቸኛ የእንግሊዝ ቴሌግራፍ ጋዜጠኛ የነበረው “አጉስተስ ዋይልደ Augustus Wylde” የዓይንና የጀሮ ምስክርንቱን እንዲህ ሲል ዘግቦት ይገኛል። ወደ አማርኛ ትርጉም የራሴ (ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ)፡

እንዲህ ይላል፡

“ከፍርድ ቤት ውሎአቸው በኋላ መቀሌ ውስጥ ወደ ራስ መንገሻ መኖሪያ ቤት እንድመጣ ተጠየቅኩኝና፤ አትክልት ሥፍራ ሆነው ከልጅ ምርጫ ጋር ብቻቸውን አገኘሁዋቸው (ልጅ ምርጫ ማለት የአፄ የሐንስ የእንግሊዝኛ አስተርጓሚ የነበረ ወጣት ነው)። የተጠራሁበት ምክንያት ሲገልጹልኝ ንጉስ ምኒልክ እኔን ማየት እንደሚፈልጉ እና እኔን ማግኘት እንደሚፈልጉ የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተነገረኝ በተቻለ ፍጥነት ወደ አዲስ አበባ መሄድ እንዳለብኝ ነበር የደብዳቤው መልእክት።

ሆኖም ራስ ከዚያ ይልቅ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከዚያም ወደ ለንደን ሄጄ የእንግሊዝ መንግሥት የጠየቁኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ እንደሆንኩ እንዲያውቁልኝ እንድትነግርልኝ ነው የምፈልገው ብለው ጠየቁኝ። ከጣሊያኖች ጋርም መጣላቴ መቼም ቢሆን እጅግ ማዘኔንናጣሊያኖች ጋርም ምን ያህል ከእነሱ ጋር ወዳጃቸው መሆን እንደምፈልግ ንገርልኝ። አሉኝ።

 እኔም ስመልስ እንዲህ አልኩ፡ ‘አንድ መልስ ልስጥ፣  የጠየቁኝን ነገር ላደርገው የማይቻል ነው፡ የኔ ተልዕኮ ፖለቲካ አይደለም፣ የኔ ሥራ በእንግሊዝ ውስጥ ካሉት ታዋቂ የዜና ማሰራጫ ጋዜጦች አንዱ የሆነው ቴሌገራፍ ጋዜጣ የላከኝ በአቢሲኒያ ውስጥ ስላሉ ሁኔታዎች ለማጣራት  እና ሙሉ ዘገባ ለመዘገብ የተላክሁኝ ዘጋቢ ነኝ እንጂ የፖለቲካ ሥራ አይመለከተኝም። አለኩዋቸው።

አሁንም ወደ ሰሜን (ኤርትራ ማለቱ ነው) እንድመለስና የተላኩልኝን ዕቃዎችና ቴሌግራም ስለደረሰኝ ወደ ሰሜን እንድሄድ እንዲፈቀድልኝ ጠየኩኝ።

ሆኖም ለሁለተኛ ጊዜ በማግስቱ መኳንንት ባሉበት ስብሰባ ተጠራ። ራስ አሉላ፣ የተምቤኑ ራስ ሐጎስ፣ ሹም አጋሜ፣ እና ሐጎስ ተፈሪ፣ የንጉስ ምንሊክ ወኪል የሆኑት ነብሩድ ወልደጊዮርጊስ እና እጀግ ወዳጄ የሆኑት የሟቹንጉስ ዮሃንስ ነብስ አባት የነበሩት ሊቀ ካህናት ወልደ ማርያም በራስ መንግሻ ሰብሳቢነት አብረው ተቀምጠው አገኘሁዋቸው። የተጠራሁበትም ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መሄድ እንዳለብኝ ወስነው እንደነበር ገባኝ። አስተርጓሚው ልጅ ምርጫም አብሮአቸው አለ።

ምን የመሰለ ቁርስ ከጠጅ ጋር ቀርልን ቁርሳችንን በደስታ ከተመገብን በሗላ፤ ሰራተኛው መስርያውን (ምግቡን) አንስቶ ወደ ውጭ ከሄደ በላ የንጉሥ ምኒልክ ደብዳቤ እንድመለከተው ተደረገና ይዘቱ ተነገረኝ። የደብዳቤው ይዘት ወደ አዲስ አበባ ሄጄ የእስረኞች አያያዝ እንዴት እንደተያዙ ለማየት ወደ አዲስ አበባ እንድመጣ የሚል ነው እኔም የቴሌግራም መልእክቶቼን ለማግኘት ወደ ማሳዋ መሄድ አለብኝ ብዬ አጥብቄ ገለጽኩ። ሆኖም ውሳኔ ስለተወሰነ አልሆነም።

በማግስቱ ጠዋት እጀግ ወዳጄ ወደ ሆነው ራስ አሉላን ልሰናበት ሄድኩ። ወዲያው ወደ ደቡብ (አዲስ አበባ ማለቱ ነው) ከመሄዴ በፊት ዓድዋ ከተማ የተውኩትን ዕቃዬን ወደ ዓድዋ ሄጄ እንድወስድፈቀደሉኝ እሳቸው ብቻ መሆናቸውን ነግረውኝ እንደገና እንድጎበኛቸው አደራ አሉኝ፣ እኔም እድል ካገኘሁ ላደርገው ቃል ገባሁ። ለመለያየት እጄን ጨብጣቸው እሳቸውንማየት የመጨረሻ ጊዜ እንደሆነ እና የብዙ የጦር ሜዳ ጀግና ህይወታቸው በማይረባ የመሬት ባለቤትነት ንትርክ እንደሚያጡ ፍጹም አላሰብኩም ነበር። የሚገርመው፣ ቀጥሎ የተሰናበተኩዋቸው ሰው ከራስ አሉላ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡት ሌላው የተምቤን ራስ ሐጎስ ሲሆኑ፣ በተመሳሳይ እሳቸውም ሕወታቸው ተቀጨ

ከዚያም ራስ መንገሻን ለመሰናበት ሄድኩኝእሳቸውም እንግሊዛውያንን ምን ያህል እንደሚወዷቸው እንዳሳውቅላቸው ሲጠይቁኝ እውነቱን መናገር እንዳለብኝ ነገርኩዋቸው። እኝህ ራስ ምንም የጀርባ አጥንት” የሌላቸውከጄሊ-ዓሣ ተራ ጋር የሚሰለፉ በዚህ ልፍስፍስነታቸው አውሮጳውያኑ ወደ ማንኛውም ነገርሊቀረጽዋቸው” እንደሚችሉ አልጠራጠርም። ራስ መንግሻ በአውሮፓ ይል ከተደገፉ ያዘዝዋቸውን ሁሉ እንደሚፈጽሙጠንካራ መሪ መሆን የማይችሉ ለአውሮጳዎቹ “የተሻለ አሻንጉሊት” ታዛዥ ቹዋዋ (ውሻ) ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው። .. (When he asked me to let the English know how fond he was of them, I told him, I should tell the truth. This Ras belongs to the jelly-fish order, with no backbones. I have no doubt he could be molded into anything, and if backed up by a European power, would do everything he was told, and perhaps, therefore, might be a better puppet to run than a stronger-minded man; ..,)" (አውግስጦስ ዋይልዴ (Modern Abyssinia –Augustus Wylde)

ዛሬ የኛ ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ የተከሰቱ መሪዎችዋ ሕሊናቸው ለቅኝ ገዥዎች የማሰሪያ ሰንሰለት በመስጠት ይህ ቅጣትና ቀጪ የሌለው ሁሉንም ሕጎችና ፍጡራንን ደፍጥጦ የሚረጋግጥ CIA የተባለ “ስድ ዝሆን” (‘rogue elephant’) በታሪክዋ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍጢኝ እንዲያስራት ተባብረዋል።

እዚህ ላይ ፋኖን ለመምከር የምፈልገው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወዴት እያመራ እንደሆነ እያዩት ናቸው ብየ እገምታለሁ። የአማራ ፋኖዎች  አጀንዳቸው ኢትዮጵያን ለማዳን ከሆነ በቂ ትምሕርትና ጥንቃቄ ወስደው ብቁ የሆኑ ልምድ ያላቸው በሳላ የፖለቲካ መሪዎችን እንጂ በደመነብስ የሚነዱ የጠመንጃ አርበኞች ድርጅቱን እንዲመሩት መፍቀድ የለበትም። የዘመኑ ፖለቲካ ከጠመንጃው የተለየ ረቂቅ ብስለተን ይጠይቃልና።

 ያም ሆኖ አገራችን ዓለምንና የአለምን ፍርድ እጅቻው ወስጥ ባስገቡ ን በኩል ብዙ ግፍ ስለተፈጸመባት የምንጠብቀው የዓለም ፍርድ ሳይሆን የአምላክን ፍርድ ነው!

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ 

 

Sunday, August 25, 2024

ለወረቅ ጥጃ የሚሰግዱና ለሥርዓቱ ጭራቸውን የሚቆሉ ሰዎች በእጄ ልጨብጣቸው አልፈልግም! ሞት የነጠቀን ትንታጉ የሕግ ምሁር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ጌታቸው ረዳ (የEthiopian Semay አዘጋጅ) 8/25/24

 

ለወቅ ጥጃ የሚሰግዱና ለሥርዓቱ ጭራቸውን የሚቆሉ ሰዎች በእጄ ልጨብጣቸው አልፈልግም!

ሞት የነጠቀን ትንታጉ የሕግ ምሁር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ

ጌታቸው ረዳ (የEthiopian Semay አዘጋጅ)

8/25/24

ደረጀ ዘለቀ (ዶ/ር) ምክንያቱ ባልተገለተጸ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መሰናበቱ ስሰማ እጅግ አዘንኩ።

ዶክተር ደረጀ ሲያቀርባቸው የነበሩ አንዳንድ ሃሳቦቹ ስላልተስማሙኝ ሁለት ወይንም ሦስት ጊዜ የተቸሁት መሰለኝ። አንዳንዴም ያንዳንድ ሰዎች ንግግሮች በማጣመም ያላሉትን አሉ የሚላቸው ለምሳሌ አንድ ካሕን “ እነኚህ ሰዎች “ወያኔ” ከሚገዙኝ ሰይጣን ቢገዛኝ ይሻለኛል” ያሉትን ንግግራቸው “የትግራይ ሕዝብ ከሚገዛኝ ሰይጣን ቢገዛኝ ይሻለኛል” ብሏል በማለት ሲተረጉማቸው የነበሩትን እና የመሳሰሉት አይጥሙኝም ነበር። ያም ሆኖ ከነ አንዳንድ ድክመቶቹ እንዲያ የመሰለ ብሩህ ምጡቅና ሞጋች ኢትዮጵያ ማጣትዋ ከባድ ጉዳት ነው።

የዶ/ር ደረጀ እና የአቶ አሰፋ ጫቦ ሕልፈት ሳስበው አንጀት ይበላል።የዶ/ር ደረጀ ድክመቶቹ ብቻ ሳይሆን ብርቱ ቃላቶቹ ሳስባቸው አይበገሬነቱ ማሳየት የሚችል ብቃት ያለው የሚሞግታቸው ግለሰቦችና ድርጅተቶችን አንደበት የሚዘጋ  የሚያርበደብድባቸው የንግግር አንደበቱ ከውስጤ ስወድለት ነበር።

ይሉኛል የማይል አንደበተ ርቱዕ፤ የተሰማውን የሚዘረገፍ ግሳንግስ ምሁራኖችንና “የአማራ ናሺናሊስቶች የሚላቸውን በደም በአጥንት ጉልጥምጥሚት እየተበጠረ ብቻ አማራ ይሰለፍ እያሉ (ዛሬ እንደምናያቸው ዘመነ ካሴ እራሱ እና እዚህ ውጭ አገር የሚኖሩ የዘመነ ካሴ የሁሉም አማራ የድሮ ብአዴን ተዋጊና ካድሬ የነበረው የኖርዲኮች ጥራት ዓይነት የሚሰብክ አጥንት ሲሸነሽን ማን አማራ ማን ትግሬ እንደሆነ ሲቆጥር የሚውል የእስክንድር ባለቤት “ትግሬ ነች እያለ ዘር ሲቆጥር በየሚዲያው የምንሰማው “ሳሙኤል አበራ (“ሳሚ” ይሉታል በቁልምጫ ሲጠሩት)” ፤ እንዲሁም አኪላ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው “ኤልያስ” የተባለ የ “ዋን አማራ” የኢንተርኔት ድርጀት መሪ እና ወጣት ፋሺሰት የመሳሰሉትን ጠባቦችን ዶ/ር ደረጀ “ባለ ሁለት እግር አሳማዎች” እና “ገጣጣ ዘረኞች” ይላቸዋል። እኔ እንደምጠየፋቸው ሁሉ እርሱም ይንቃቸዋል።

ስለሚሰነዝራቸው ቃላቶችና ንግግሮች ሁሉ በሙሉ ሐላፊነት የሚወስድ ደፋር፤እጅግ መራራ ተናጋሪ በመሆኑ አድማጮቹን እንዲህ ይገልጻቸዋል፡

“ የሰው ሙገሳ አይሞቀኝም፤ዓለም ሁሉ ተሰብስቦ ውግዝ ከመአርዮስ ቢለም I don’t give a dumb!!” ግድ አይሰጠኝም” ሲል የሚሰማውን በገሩ የሚቆጭ ሳይሆን በሙሉ ልቦና የሚደሰት አስገራሚ ልዩ ኢትዮጵያዊ ነበር።

ከላይ የገለጸው አነጋገር ዶ/ር ደረጀ እኔን ወክሎ የተናገረልኝ መስሎ ይሰማኝ ነበር። እኔና ደረጀ ተመሳሳይ ባሕሪ ያለን ይመስለኛል። ሰዎች ይሉኛል ሳይል የተሰማውን ያፈነዳዋል፡ በራሱ ቃላት “mushroom cloud” ይለዋል (“የፍንዳታ ቁልል” ይመስለኛል በአማርኛ ስተረጉመው)።

ትንታጉ ሊቀሊቃውንቱ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ “የአማራ ናሺናሊሰቶችን” ብቻ ሳይሆን፤ የኦሮማ ናሺናሊሰቶችን ኢሕአፓዎችን አሁን ያለው የኦሮሙማው ሕጻን የሚመራው መንግሥት ኦሆዴዱ አብይ አሕመድን በፖለቲካ የጉማሬ ኮርማጅ እስኪበቃቸው ድረስ ይለበልባቸዋል። እነዚህ መርገምቶች እና Idiotic ብሎ ከሚጠራቸው ይልቅ ደርግ የሰራው መጥፎ ነገሩ እንዳለ ሆኖ በጎ ጥረቱን ያደንቃል። ለትግራይ ሕዝብ ያለው ሙገሳ፤ ፍቅር እና ከበሬታ ከፍተኛ ሲሆን፤ አክሎ የሚከተለውን ምክር ይለግሳቸዋል፡

“የማከብውን ቅዱስ የሆነው ከዚያች ቅድስት መሬት የተፈጠረው የትግራይ ሕዝብ ልው ምፈልገው “እንደ ወያኔ ያለ ከማሕጸናቸው ድጋሚ እንዳይወለድብን ብለው መጸለይ አለባቸው” ሲል ሃሳቡን ያጋራል። የወያኔ ፈለግ ተከትለው እንደ አዲስ የተወለዱ ወያኔዎች (እኔ “የወያኔ ዕንቁላሎች” የምላቸውን እነ ባይቶና፤ ሳልሳይ ወያኔ ወዘተ…የሚባሉትን እዚህ ግቡ ያማይባሉ “የወያኔ ስባሪዎች” ይላቸዋል።

መርገምቶች እና Idiotic ኮች እንዲሁም “ባለ ሁለት እግር አሳማዎች” እና “ገጣጣ ዘረኞች” ፤ለወቅ ጥጃ የሚሰግዱና ለሥርዓቱ ጭራቸውን የሚቆሉ ሰዎች በዚህ በኢትየጵያዊው ገናናው የሕግ መምሕር ሞት ሲደሰቱ ለኛ ግን መራራ ሐዘን ነው።

ለቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ጽናቱን ይስጣችሁ እያልኩ፡ነብስሕን አምላክ በገነት ያኑረልን።

ጌታቸው ረዳ (የEthiopian Semay አዘጋጅ)

 

Tuesday, August 20, 2024

የዘመነ የጎጃም አማራ ፋኖ የሰለጠነ የፖለቲካ መሪ ያስፈልገዋል! ጌታቸው ረዳ 8/29/24

 

የዘመነ የጎጃም አማራ ፋኖ እና የምሬ ወዳጆ የወሎ ፋኖም እንዲሁ

የሰለጠነ የፖለቲካ መሪ ያስፈልጋቸዋል!

ጌታቸው ረዳ

8/29/24

በዚህ የታላቁ እስከንድር ንግግር ልጀምር፡

<< የብሄር ስም እና ማንነታችን ያገኘነው የዘር ማጥፋት ሰለባ ከሆኑ ሰዎች ነው የእኛ ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ የዘር ማጥፋት መከላከል ነው>> Sep 8, 2023 ከጄፍ ፒርስ ቃለ መጠይቅ

ታላቁ እስክንድር ወደ ፋኖ የተቀላቀለበትና ግቡ ምን እንደሆነ ለእውቁ ጋዜጠኛ ለጄፍ ፒርስ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ልጀምር፦ ሙሉውን ወደ መጨረሻ ታገኙታላችሁ::

ወደ ዋናው ርዕስ ልግባ!

ሰሞኑን በዘመነ ካሴ የሚመራው በጎጃም የአማራ ፋኖ ያስተላለፈው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እገዳ በሚመለከት በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በአወንታዊ ምላሽ ደግፎ ያስተላለፈው የድጋፍ ጥሪ ከሰለጠነ መሪና ከሰለጠነ ድርጅት የሚጠበቅ ጥላቻና ቅራኔ ወደ ጎን ትቶ የጋራ ችግር በጋራ የመወጣት የስልጣኔ ምልክት ሲሆን፤ በአንጻሩ የዲገላው የዘመነ ካሴ ድርጅት ግን ያንን ድጋፍ አወንታዊነቱን ተቀብሎ በምስጋናና ወንድማዊ የትግል አጋርነት በማሳየታቸው መልስ ከመስጠት ይልቅ ያንን የዲገላነት ማይምነቱን ለማሳየት መልስ ሳይሰጥ ዘግቶታል። ያ አልበቃ ተብሎ ደጋፊዎቹ በእስክንድር ሲሳለቁ በየሚዲያው መስማት የሚገርም ባርባሪዝም (ማይምነት) ምልክት የሰለጠነ አስተካካይ መሪ ያጣ “ኮሚኒቲ” መሆኑን ነጋሪ ነው።

ፖለቲካና ሥልጣኔ ምንድናቸው? ፖለቲካ ሰዎች ኑሮአቸውን ለማሻሻል የሚጠቀሙበት መወጣጫ መሰላል ነው። ስልጣኔ ግን የአረመኔነትን ተቃራኒ የሚገልጽ የዓዕምሮ ብስለት ነው። የሰለጠነ ሰው ጨዋ ነው። ትንሽዋን ቃል "አመሰግናለሁ" እንዴት እንደሚል እንኳን ያውቃል። ዲገላው ግን የሰለጠነውና ጓዳዊ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ድጋፍ ትንሽዋን ቃል "አናመሰግናችለን" እንኳ ለድጋፋቸው መልስ ሊሰጥ አልፈለገም። ለዚህ ነው “የጎጃም አማራ ፋኖ” በሥልጡን ፖለቲካ የተካነ መሪ ፈልጎ ማግኘት እንዳለበት ሁሌም የምመክረው። ከተማና ገጠር ስለያዝክ አጃቢና ትጥቅ ስላከማቸህ አድካሚውና ትዕግስትና ጥበብ የሚጠየቅ ፖለቲካ መሪ ከሌለህ ትግሉ ውሃ መውቀጥና ስቃይ ማራዘም ነው።

ስለ ምሬ ወዳጆ

ምሬ ወዳጆ የተባለ ትምሕርትና ልቦና የጎደለው የወሎ ፋኖ ማይም ስለ ኮለሜል ፋንታሁን ሞሓባ እና ስለ እስክንድርና ስለ የሸዋ ፋኖ የመከታ ማሞ አመራር በማይም ቃላት ሲሰድባቸው ሰምታችሁ ይሆናለ። አንዳንዶቹን ልጥቀስ

ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሓባ ባንዳንድ ሃይሎች ስለተጠለፈ አባርረነዋል

ስለ የሸዋ ፋኖም እንዲህ ሲል ብልግናውን ሲተፋባቸው ሰምተናል፡

<<የሸዋ ፋኖን እየመራ ያለው “አባ ዱላ ገመዳ” ነው>> ሲል ማይምነቱን በሚዲያ ገልጽዋል።

ይህ ማይም ጥይት እንዲቶክስ እንጂ የማያውቀውን ፖለቲካና የሚዲያ መድረክ መቅረብ ስለሌበት፤ አብረው የሚታገሉ ልባሞች ካሉ ይህ ማይም ከሚዲያ አስርቁት ፡ ብዙ ነገር ያበላሽባችል።

ከዚያ በፊት የጎጃም ፋኖ ቃል አቀባይ ተብየው ማርሸት ፀሃየ የተባለ ሲዋሽ ሰማይና ምድር የሚያጣብቅ ልጅ እስክንድር ከአብይ አሕመድ የኦሮሙማ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ደርሰንበት ማስረጃው እልክልሃለሁ ሲል ለእሱ መሳይ የሚዲያ ዋሾ ምናላቸው ስማቸው የተባለ ጎጀሜው ማፈሪያ (ባለቤቱ ውድ አርበኛዋ የኢትዮ 360 ኢየሩስ ይቅርታ እየጠየቅኩ) ቃለ መጠየቅ ሲሰጠው “እየቀለድክ ነው ማስረጃው አለህ? አዎ አለኝ፡ በቃ አገሩ ይተረማመስ ላክልኝ” ብሎት እስካሁን ድረስ አንዲት ብጣሽ ማስረጃ አላቀረበም። እነጂህ ያልበሰሉ ማይሞች ከሚዲያው አስወግዳችሁ የበሰለ ትዕግሥትና የፖለቲካ ጥበብ ያላቸው መሪዎች ፈልጉላቸው።

በእስክንድርና በጓዶቹ የሚመራ የፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በአክብሮትና በአድናቆት ቆቤን በማንሳት ክብር ይገባችኋል፤ ስላሳያችሁት ጓዳ ትሕትና እና ሥልጡን ዲፕሎማሲባላችሁበት አድናቆቴ ይድረሳችሁ!

አሁን በመግቢያየ የጠቀስኩት ቆየት ያለ የእስክንድር ቃለ መጠይቅ ቅስ ላቅርብ (አማርኛውና እንግሊዝኛው) Sep 8, 2023

Jeff Pearce: Fano and APF for that matter keep getting lazily referred to online and in news reports as ethnic extremists or militants. Western news claims Fano has killed government officials and wrecked offices. What should people know?

Eskinder Nega: The best way to describe Fano is as a historical grass roots movement of resistance for either justice or defense of country.

Over what is assumed as a very long time in Ethiopia’s history, Fano has become a pan-Ethiopian cultural phenomenon. That we now see Fano as manifest only in the Amhara region attests to the unique challenge facing the Amharas — the challenge of genocide, I should point out — not to the ethnicity of Fano.

We have an ethnic name and an ethnic organization as a byproduct to to the ongoing state-sponsored leveling, categorization, demonization, mass displacement, mass killing of Amharas. All these are well known hallmarks of genocide. In other words, we derive the ethnic name and identity from the victims of genocide. Our paramount quest and vision is the prevention of genocide. To these noble ends, we recognize the de-emphasis of identity politics is an essential goal. That is the goal we shall strive for.

ጄፍ ፒርስ፡- ፋኖ እና ኤፒኤፍ ለነገሩ በመስመር ላይ እና በዜና ዘገባዎች ላይ እንደ ጎሳ ጽንፈኞች ወይም ታጣቂዎች እየተባሉ ይጠቀሳሉ። የምዕራቡ ዓለም ዜናዎች ፋኖ የመንግስት ባለስልጣናትን ገድሏል እና ቢሮዎችን ያወድማሉ እያሉ ይዘግባሉ። በዚህ ጉዳይ ሰዎች ምን ማወቅ አለባቸው?

እስክንድር ነጋ፡- ፋኖን ለመግለፅ የተሻለው መንገድ ለፍትህ ወይም ለሀገር መከላከያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ታሪካዊ ሥረ መሠረት ያለው ነው።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጣም ረጅም ጊዜ ነው ተብሎ በሚታሰበው መሰረት ፋኖ የመላው ኢትዮጵያ የባህል ክስተት ሆኗል። አሁን ፋኖን በአማራ ክልል ብቻ እንደግልጽ አድርገን መመልከታችን የአማራዎችን ልዩ ሁኔታዎችና ተግዳሮች ስላሉ ነው።

የብሄር ስም እና ማንነታችን ያገኘነው የዘር ማጥፋት ሰለባ ከሆኑ ሰዎች ነው። የእኛ ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ የዘር ማጥፋት መከላከል ነው። ለእነዚህ መልካም ዓላማዎች የኝኝ ባይ ብሔረተኛነትን ፖለቲካ ማጉደል አስፈላጊ ግብ መሆኑን እንገነዘባለን። እኛ የምንጥርበት ዓላማ ይህ ነው።

መልካም ሳምንት!

ጌታቸው ረዳ