Sunday, December 31, 2023

የጃዋር መሐመድ ቃለመጠይቅ በኬኒያ ያለኝን እይታ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/1/2024

 

የጃዋር መሐመድ ቃለመጠይቅ በኬኒያ ያለኝን እይታ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

1/1/2024

የጀመርነው የፈረንጅ አዲስ አመት ነው። አዲስም አሮጌም ይምጣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የለወጥ ዘመን አይደለም። ዘመን በመጣ ቁጥር እየባሰ እንጂ ሲሻል አላየንም። ለዚህ ተጠያቂዎቹ እነ ጃዋርና አብዛኛው የአትዮጵያ (ትግሬ/ኦሮሞ/ጉራጌ. /አማራ……..ወዘተ… ፣ሊሂቃን ናቸው። ችግሩ አንደኛቸውንም ስሕተታቸውም ሆነ ወንጀላቸው አምነው አያውቁም። ይባስ ብሎ  “ለኢትዮጵያ ከፍታን አመጣንላት” ይላሉ።

ከብዙ አማታት በፊት ጃዋርን በአካል አግኝቼው ተነጋግረን ነበር፡ እንደ ሰው ተወዳጅ ነው። እርሱና እኔን በሃይል የሚጠላኝ ጓደኛው በኔ ላይ የነበረው አስተያየት በቅርብ ስንገናኝ ጭራሽ ያልጠበቀው ተወዳጅ ሰው ሆኜ እንዳገኝ እና በጽሑፍና በአካል ሁለት ሰዎች እንደሆንኩት ለጓደኛውንም እንደሚነግረው በኔ ባሕሪ እንደተገረመ (ሰርፕራይዝድ_ አንደሆነ እና “በጽሁፌ ላይ” ሲያነበኝ ግን እልም ያለ “ነፍጠኛ” መስለኸኝ ነበር’’ ብሎ ሳስቀን ከተጎሻሸምን በሗላ “ነፍጠኛ  መስለኸኝ ነበር” ባላት ቃል ወደ ሕዝብ ማምጣት ስለነበረብኝ በማግስቱ በጽሑፍ ተቸሁት። ጃዋር አንደ ሰው ሳገኘው እኔ ለእርሱ እርሱም ለኔ የነበረን የዜጋዊና ወንድማዊ ልውውጥ በቀላሉ ተግባብተን  ነበር። ስለዚህ ጃዋርን በሚከተለው ፖለቲከም ሆነ በአካል አውቀዋለሁ እና በዚህ ቃለመጠይቁ የተሰማኝን ባጭሩ የተሰምማሙኝ እና ያልተስማሙኝን መስመሮቹን ልተንትን።

ታዋቂው ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ ኬኒያ ድረስ በመሄድ ለጃዋር ያቀረበለትን ቃለመጠይቅ ክፍል አንድ አደመጥኩ። ጃዋር በአካልና በድምጸት ለውጥ ይታይበታል። በአካል የከሳ/ ገርጠት ያለ የሚመስል ግን ግርማ ሞገስ የተላበሰ ምቾት ያለው ተክለሰውነት እና ጉርምስናውን ወደ ማገባደድ እና ሽበትም እስከመቼውም ላይለቀው ተዋውቆታል። ለማንኛውም ከበፊቱ ይልቅ የሰከነ “ምራቁን የዋጠ/ጀንትል ማን” ይመስላል።

ይህ ሁሉ ለውጥ ቢታይበትም የአካል እንጂ ያስተሳሰብ ለውጥ ከነበረው መስመር የራቀ ቢመስልም ብዙም የራቀ አይደለም።   

መጀመሪያ በበጎ ቃላቶቹ ልጀምር “አገራችን” ይላታል ኢትዮጵያን (ይህ አዲስ አመርቂ ቃል ነው)፤ ኢትዮጵያ ጥንታዊ አገር ስለሆነች ላፍርሳት ብትልም እንኳ ‘ልታጎሳቁአለት ትችል ልትደክም ትችል እንደሆን እንጂ’ ወድቃ የመነሳት ልምድ ስላላት ማፍረስ  አይቻልም” ይላታል ኢትዮጵያን በአድናቆት። (የኔ አገላላጽ ንግግሩን ሳጠቃልለው)። ይህ እውነታ ያለው ጥቂቶች ብቻ ስንለው የነበረው ዛሬ ጃዋር የተቀላቀለን “የብዙ ሰዎች ስጋት የሚቀርፍ አባባል ነው” (አገራችን የተጋረጠበት የሃይማኖት፤የባህል ብረዛና የወንጀል ብዛት እንዳለ ሳንስት ማለት ነው)።

ሰላምን በጽናት እንድናደምጣት ፤ ስለ  ሰላም አስፈላጊነት ብዙ ጊዜ ሲደጋግም ይደመጣል።ሰላም ለማምጣት በጠምንጃ ሳይሆን በክብ ጠረጴዛ በሰጥቶ መቀበል ነው መምጣት አለበት”” ይላል።  ስለ ሰላምና ጦርነት ማስወገድ አሰስፈላጊነት የሚመሰገን ንግግሩ ቢሆንም  ዛሬም በነበረው መስመር በፖለቲካው እንዳልተገለለ ፍንጭ ጣል ያደርጋል።

አሁን ወደ ጎረበጠኝ ፖለቲካው ልጥቀስ፡

 አዲስ አባባን ፍንፍኔ ይላታል። ይህ ቃል አዲስ አባባ የኦሮሞ ናት የሚለው “ኦነጋዊ የባለቤትነት የይገባኛል ድምፅ”  (ክለይም) ዛሬም በዚች ቃል እየነገረን እንደሆነ እንረዳለን።

ሌለው ንግግሩ ደግሞ የወያኔ ትግሬ መሪዎችን ባንድ ነጥብ ሲያወድሳቸው ሰማሁ።ትግሬዎች ምንም ጊዜም ቢሆን ጥርሳቸው ውስጥ ተሰክቶ ያልተላቀቃቸው፤ ጊዜ ሲጠብቁለት የነበረውን (ሥልጣናችን ከተቀማን ወደ እየመንደራችን እንበታተላለን የሚለው የወያኔዎች ማኒፌስቶ) በማስታወስ ክስተቱን በመጠቀም የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ   እውን ለማድረግ << ሆን ብለው የጫሩትን ጦርነት>> ጃዋር መሐመድ መቃወሙን አልወደድኩለትም (ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ጃዋር ስለ ወያኔዎች የጦርነት ዝግጅታቸው ተጠይቆ ምን ይል እንደነበረ እናውቃለን) ። ወያኔዎች ወደ መቀሌ ጠቅልለው የመሄድ ስልታቸው  ጃዋር “የአዋቂዎች እርምጃ ነበር” ሲለው እኔ ደግሞ “ሴራና ቂመኝነት፤እልህነት፤ጅልነትና ተንኳሽነት፤ሥልጣን አልጠግብ ባይነት አገር አፍራሽነት፤ ዕብሪትና ዕብደት የተጠናወተው እርምጃ ነበር” እላለሁ።

ታስታውሱ እንደሆነ ፋሺስቱ አብይ አሕመድ እነ ሥዩም መስፍንን በነበረው የአምባሳደርነት ሥራው ልስጥህ ብሎት እራሱ ሥዩም አምቢ እንዳለው ነግሮናል። በረከት ስሞኦንም እንዲሁ ሹመት ተሰጥቶት አምቢ እንዳለ እና እነ ሞንጆሪኖ በሚኒሰትርነት ተቀምጠው ሥልጣናቸውን ይቀጥሉ እንደነበር እናስታውሳለን። የፓርላማ አባላትና የመሳሰሉ ትግሬዎች ሙጠጥ ብለው ወደ መቀሌ የሚያስኬዳቸው ጦርነት ፍለጋ’ ሥልጣን ተቀማን እና ዕብሪት ካልሆነ አንዳችም ምክንያት ወይንም የአዋቂነት ምልክት አልነበርም። በዚህ ርዕስ እስኪሰለቻችሁ ድረስ ስለጻፍኩ ምክንያቶቼን እዚህ አልሄድበትም፤እዚህ ላቁምና  ወደ ሌላው ነጥብ ልግባ።

ሌለው የጃዋር ጎረባጩ አቋሙ “ሥር ነቀል” ፖቲካ “አንከተል” የሚለው ነው። (ይህ መስመር ሚወቀስ እንኳ ባይሆንም ችግር ያለበት መስመር ነው) በኢትዮጵያ ሰላምን፤ዕድገትን፤ዲሞክራሲን እና የሰከነ መንግሥት ለማምጣት “በሥር ነቀል አብዮት ሳይሆን፤ "በጥገናዊ ለውጥ" መሆን አለበት” ይላል ጃዋር።

አሁን የመጣው የፋሺስቱ አሮሙማው መንግሥት “በሥር ነቀል” እንዲመጣ ነድፎ (በፎቶግራፉ    ላይ ከምታይዋቸው ከጓዶቹ ጋር) እንዲከሰት እንዳደረገ ሳይደብቅ ዛሬም ካሁን በፊትም ነግሮናል። እራሱ አብይ አሕመድም እዚህ ውጭ አገር መጥቶ ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህንን መስመር እንደሚከተል ነግሮን መኖሩን ታስታውሳላችሁ። ስለዚህ ሆን ተብሎ ትግሬዎች ወጥተው ኦሮሞዎች እንዲተኩና አሁን ያለው የባንቱስታው አስተዳዳር እንዲቀጥል እነ ጃዋር ከነ ካንዳንድ የወያኔ “አልትራ ናሺናሊስት” ባለሥልጣኖች እንዲሁም ከነ አብይ አሕመድ፤ከነ ለማ መገርሳ እና የመሳሰሉ “የኦሮሙማ ጀሌ አማራዎችም ጭምር” ግንኙነት አድርገው ጥገናዊው ለውጥ በጥናት ነድፈው እንዲመጣ እንዳደረጉ አሁን ግልጽ ሆኗል (ጃዋርም ለዚህ ግምባር መሪ እንደነበረ መገመት አያቅታችሁም)።

ካሁን በፊት ጃዋር ስለ ወያኔ አወዳደቅ ሲነግን ወያኔዎችን <ተገዝግዞ እንደወደቀ ትልቅ ዋርካ ክፉ አወዳደቅ እንዲወደቅ አድርገነዋል>> ሲል እናስታውሳለን እንጂ አንድም ቃል ካንዳንድ የወያኔ ባለ ሥልጣኖች ጋር ውስጥ ለውስጥ ለጥገና ለውጥ  የመስራት ንድፍ ሲናገር ሰምቼ አላውቅም።          

ጃዋር በቃሉ ካሁን በፊት ስከታተለው “ሪፎርም” (ጥገናዊ ለውጥ) የሚለው አቋሙ ካሁን በፊት ሲናገረው አድምጬውም ባለውቅም።

 ለውጥ ሲመጣ በጥገናዊ ለውጥ እንዲመጣ “በንድፍ” ነድፎ እንደተንቀሳቀሰ ይናገር እንጂ እኔ የማውቀውን ጃዋር  “ሸዋጅ” (ብልጥ/ትሪኪ) ስለነበር ካሁን በፊት ሰውን በሚያታልሉ ብልጠቱ ይጫወት እንደነበረ ባውቅም በግልጽ ግን “ጥገናዊ ለውጥ” እንደሚያራምድ ሰምቼው አላውቅም። እንዲያውም ጭራሽኑ <<ኢትዮጵያውያን ከኦሮሞ ይውጡ/ይባረሩ>> << ኦሮሞዎች ወደ ‘አበሾች’ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አትሂዱ>> ኦሮሞ እስላሞች ወደ ‘አበሾች’ መስጊድ አትሂዱ>> የራሳችሁን መስጊድና ቤተክርስትያን አሰርታችሁ ኦሮሞ ብቻ የሚጸልይበት መገንባት አለባችሁ >> የሚለው ከፋፋይና “የጀነሳይዳል ጥሪው” ከሥር ነቀልም “ሥር አጥፊ” እንቅስቃሴ ይከተል እንደነበር እንጂ ጥገናዊ ለውጥ እንዳልነበረ ነው እኔ የማውቀው።  

ታዲያ ጃዋር “ሥር ነቀል አብዮት አገርን ያጠፋል” ሲለን አገር ያላጠፈው እና ሕዝብ ያልጨፈጨፈው የጃዋር “ጥገናዊ ለውጥ” ያመጣልንን ጥገናዊ ለውጥ  ምን ይመስላል?

አንባቢዎቼ ካሁን በፊት አብይ አሕመድ እና የመቃዲሾ ሶማሌዎችም የኛ ዜጋ ነው የሚሉት የ16ኛው ዘመን ሶማሊያዊው(?) ግራኝ አሕመድ እንዲሁም የናዚ ጭካኔዎች በማነጻጻር ካሁን በፊት የጻፍኩት ጽሑፍ እንዳነበባችሁት ተስፋ አደርጋለሁ።እንግዲህ ሥር ነቀል አብዮት የተሻለ ነው ተብሎ የተሰበከንን <<ጥገናዊ ለውጥ>> የሚባለውን ነው አሰቃቂ ፍጻሜ ልናይ ያደረገን።

እኔ ደጋግሜ የተጠቀምኩት ቃል ጥገናዊ ለውጥን << ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ>> ብየ የምገልጸውን ጥገናዊ ለውጥ እነ ጃዋር ለምን እንደፈለጉት ግልጽ ነ

 ካሁን በፊት ጃዋርም ሆነ የተቀሩት አሮሞዎች 3/4ኛው የመላው ኢትዮጵያ ባለቤት የሆነው አሁን በባለቤትነት የያዙት ‘’ኦሮሚያ’ የሚበላው መሬት (ፍንፍኔ የሚሉት አዲስ አባባ ከተማን ጨምሮ) ኦሮሞዎች ለማንም ኢትዮጵያዊ ሊለቁት እንደማይችሉ ጃዋርና የኦነግ መሪዎች ጃዋርም እራሱ ካርታውን በድንጋይ ተቀርጾ የሃውልት መሰረት ሲያኖር “ኦሮሚያ” የሚባል አገራዊ ካርታ እንዳኖረ በቪዲዮ የተቀረጸ ምስል አለ።

  ዓይን ባወጣ ወንጀልና ንቀት  የባሕል ሚኒስተር የተባለው የኦነጉ አንደኛው መሪ  ጽ/ቤቱ ውስጥ ተለጥፎ የሚታየው ካርታ የኢትዮጵያ ሳይሆን ኦሮሙማ ካርታ ነው። ይህ ሁሉ ጥገናዊ ለውጥ ሊደረግ የተፈለገበት ዋናው ምክንያት “ግልጽ” ነው።

 ለነጃዋር ጥገናዊ ለውጥ ያመጣው ፍሬ በጣም ግልጽ ነው። ያ እንዲቀጥል አሁንም እየሰበከ ነው።ኦሮሙማ በሚል ፕሮጀክት ታንጾ ወደ ሥልጣን የወጣው ኦነጉ አብይ አሕመድ ነብሰገዳዮችንም፤ ወንጀለኞችንም  አጭበርባሪዎችንም  አገር ገንጣዮችንም ሁሉም ያለ ምንም “ሬስትሪክሽን” ወይንም “ውል” ወደ አገር ገብተው ረገብ ብሎ የነበረው ግንጠላቸውን እና  የመግደል ጥማታቸውን ለማስቀጠል ባንዴራቸውን ሳይቀር ማውለብለብ እንደሚፈቀድላቸው ቃል ገብቶላቸው ገብተዋል። በገባላቸው መሰረት፤ ኢትዮጵያን ዛሬ ባለችበት አሳዛኝ እርከን አዳክመዋታል።

ጥገናዊ ለውጥ የተባለው ብዙ ሰው ያጃጃለው ለውጥ የጥገና አራማጆቹ  ሥልጣን በያበት ሳምንታት ሳይሞላው አገሪቷን በደም ት። በወቅቱ ከግራኝ አህመድ ዘመን ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ የሰው ልጅ በአደባባይ ደብድቦ እንደ ክርስቶስ ሽቅብ ሳይሆን  እግሩን ወደ ላይ አናቱን ወደ ታች ዘቅዝቀው ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጡር እንደ እንሰሳ እየተሳለቁ ተሰብስበው ሕዝቡም ምንም ሳይሰማው ሰቀሉት። ይህ ከግራኝም ከናዚዎችም ክርስቶስን ከሰቀሉት አይሁዶችም የባሰ የዘመናችን ትዕይንት ነው። ይህ የነጃዋር የዘመናት ቅስቀሳ ውጤት ነው። ይህ ሁሉ ሲሆን “አንድም ቀን ጸጸት ወይንም ይቅርታ አላልጠየቀም>> ።

ያ አልበቃ ብሏቸው ጥገናዊ ለውጥ አራማጆቹ አገር ውስጥ ያለ ምንም ገደብና ውል እንዲገቡ የተፈቀደላቸው የኦሮሙማ ፖለቲከኞች በሚየዝዋቸው ጋጠወጥ ታጣቂዎቻቸው  በኩል 70 ቤተክርስትያናት በጠቅላላ እና 11 ቤተክርስትያናት  “ባንድ ቀን”  ወደሙ ፥ ቁጥራቸው ያልታወቀ ቀሳውስት እና ምዕመናን እንዲሁም ሰላማዊ አማራዎች በዘግናኝ አገዳደል ተገድለው የከፋ እልቂት በማካሄድ ሥልጣናቸውን በደም ባረኩት። ኦሮሞኣዊ የኦነግ ነብሰ ገዳዮች ወደ ሰላማዊ ሕዝብ እንዲቀላቀሉ በመደመር ጭፍጨፋና 29 ባንኮች ዘረፋ በሚገርም ፍጥነት አቀጣጠለው። ወያኔዎች ከኋላ ሆነው ሸኔ እያለ የሚጠራቸው ኦነጎችን  በማስታጠቅና ግምባር በመፍጥር ጥምረታቸው ሲያጋግሉ ፤ በጥገና ለውጥ ወደ ሥልጣን የመጣው አብይ<<ኢትዮጵያን ኦሮሞ የማድረግ ፕሮጀከትና የዘር ጭፍጨፋ እንዲካሄድ በመፍቀድ>>   ነብሰገዳዮችንና ኦነጎችን ከሥልጣን ወደ ሥልጣን እያሸጋጋረ መዲናችን አዲስ አባባም ጭምር እንድትታወክ እደረገ።

ታስታውሱ እንደሆነ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን” ከዚያም በማግስቱ 11 ሰዓት ላይ ገጀራ/ንጫና ጩቤ ታጥቀው አሸዋ ሜዳ፤ ቡራዩ፤ ከፋ እና አስኮ በተባሉ ኢዲስ አበባ ከተማ የከበቡ ቦታዎች በሚኖሩ አማራዎችና ጋሞዎች ላይ የንብረት ዘረፋ፤የድብደባ እና የግድያ ወንጀል እንደተፈጸሙ በቪዲዮ ሲሰራጭ አብይ አሕመድ አድፍጦ ቆየቶ ጥቃቱ ከተጠናቀቀ ቀን አሳልፎ አልሰማሁም እንዳለ ታስታውሳላችሁ። 

ጃዋር ከዚህ ወንጀል በምን መልኩ ነጻ ሊሆን ይችላል? ወንጀለኞቹ የነጃዋርና የነ ሌንጮ ባቲና የነ ነገዎ እንዲሁም የነ ቀጀላ መገርሳ ወዘተ…የዘመናት ቅስቀሳ ውጤት እንደሆነ ማን ይክደዋል? እንዲህ ያለ ጭፍጨፋ መንግሥት አለ በሚባልበት ርዕሰ ከተማ (አብይ በሚኖርበት ከተማ) ሲፈጸም አልሰማሁም ማለት ምስጢሩ ምን እንደሆነ አንባቢዎች ታውቃለችሁ። ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው ብለን ደጋግመን ለዘመናት ገልጸናል። ጥቂት ጠያቂዎች ቢኖሩም እስከዛሬ ድረስ ጩኸታችን ውጤት አላመጣም።  ቢሆንም ከተጠያቂነት ነፃ አይሆኑም::

ኢትዮጵያ የሚከላከልላት መንግሥት ስታጣ መዳከምዋን ሲያዩ ኢትዮጵያን ማጥቃት የኦሮሞ ፋሺስት ቡድኖች ‘ዓይነተኛ መለያ’ ባሕሪያቸው ነው ብየ ካሁን በፊት ብዙ ጊዜ የጻፉኩት ብዙዎቻችሁ ስትንጫጩብኝ ነበር 16ኛው /ዘመን ወን በማያያዝ የዓይን ምስክር የዘገቡትን ታሪክ የጻፍኩትን የታሪክ ፈሪዎች ለፌስቡክ አቤት ብለው ፌስቡክ እንዳይለጠፍ ያደርጉ እንደነበር ታስታወሳላችሁ።

 የጥገና ለውጥ አስፈላጊነት የሚነግረን ጃዋር መሓመድ ከመላ ኦነግ መሪዎችና ከነ አብይና ለማ መገርሳ ሆነው ሲመካካሩ ሲጠጡ ሲጎራረሱ የነበረውን ምስሎች አይተናል። ለውጡ በማን እየተነዳ እንደነበር ግልጽ ነበር።እነ ጃዋር የመጡልን የጥገና ለውጥ “የዱሪየዎችና አናሪኪዎች” ስብስብ ነበር። “ክራባትና ገበርዲን ለባሹ ዱርየው” አብይ  የሚመራው ሥርዓት በነገዱ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞዎች የሚያራምዱዋቸው ማኒፌስቶዎች እና ምልክቶች እርሱም የሚጋራቸው ስለሆነ ለአክራሪ ኦሮሞዎች የልብ ልብ ዛሬም ሰጥቶአቸዋል (አትሸወዱ)።

ለውጡ ምን ፍንጭ እንደነበረው ከጅምሩ አስታውሳለሁ። ታስታውሱ እንደሆነ አባገዳ  “በየነ ሰንበቶ”  የተባሉት የኦሮሞ ገዳ መሪዎች ሰብሳቢ አብይ ባይመረጥ እያንዳንዳችን ኦሮሞዎች ቢላዋና ገጀራ ይዘን ታጥቀን በየቤታችን በተጠንቀቅ ተዘጋጅተን ነበር!” ብለው ያሉት ማስታወስ በቂ ነው።

 ኦሮሞዎች ሥልጣኑ ሊቆጣጠሩት የተፈለገበት ዋናው ዐይነተኛ ምክንያት ኦሮሞዎች በወያኔ ዘመን የማይገባቸውን 3/4 ኢትዮጵያ መሬት በዋናነት እንዲይዙ እና ያልነበረና በታሪክ የማይታወቅ ስም በመስጠት ኦሮሚያ” እንዲባል ጥቅም ያገኙ ቢሆኑም ፤ወያኔ በነበረበት ወቅት ኦሮሚያ የሚባል አገር” እንዲመሰርቱ ስላልፈቀደላቸው፤ ዛሬ አብይን በሴራ እና በተንኮል ወደ ሥልጣን በማስገባት ኦነግን የሚያክል በጣምአደገኛ እና በዘር ማጥፋት የተከሰሰ ወንጀለኛ ቡድን ወደ አገር ገብቶ የራሱን ባንዴራ እንዲያውለበልብ እና አገር እንዲመሰርት በሬፈረንደም የማወጅ ወይንም አማራውን በመፈፍጀት ከኦሮሞ ምድር በማስወጣት አገር የመመስረት መብት የመጠየቅ መብት እንደሚሰጣቸው ስላወቁ ነው።ጥገናዊ ለውጥ በጥናት የመጣበትም መንገድ ይህንን ለማጽናት ነበር።

አብይም ብሏል ፤ አበበች አደኔ የተባለች የአዲስ አበባ የኦሮሞዎች ከንቲባም ማንም ሕዝብ የመገንጠል መብት እንዳለው ነግረውናል። የሕዝቡ ጥንታዊ ሥሪት አልፈርስ አላቸው እንጂ ወያኔዎችም ሆኑ ኦሮሞዎቹ ያለፈነቀሉት ድንጋይ የለም።

ይህ አባባሌ የማትስማሙ ሰዎች ካላችሁ አብይ እራሱ ነግሮናል። <<ኦሮሞም ሆነ ኦጋዴን ሶማሊ እንዲሁም ትግሬውም ሆነ ሌሎቹ ልገንጠል የሚል ጥያቄ አቅርቦ ወደ ፓርላማ ማመልከቻ ካስገባም ሆነ የመገንጠል መሪ ዓላመውን ለማሳካት ወደ ፓርላማ አባልነት አግባለሁ ካለ ፓርላማ ውስጥ ገብቶ ሕዝቡ ዘንድ ሄዶ የማስገንጠል አጀንዳውን አስመዝግቦ በሬፈረንደም ማስገንጠል ይችላል>> ሲል ኢትዮጵያን ከእስራኤሉ ‘የከነሴት’ ፓርላማ አሰራር ጋር እያመሳሰለ የተናገረውን አስታውሱ።

እነ ጃዋር በጥናት ያመጡልንን የጥገናዊ ለውጥ መዘዙ ብዙ ነው።ፋሺሰቱ አብይ አሕመድ” ወንጀለኞች ሁሉ እንደ መርከብ ኖህ ባንድ መርከብ አሽጎ ከግብጽ ከአሜሪካ ከአስመራ እራሱ _በአይሮፕላን አስጭኖ በማስመጣት በሕዝባችን ላይ ዳግም ወንጀል እና የዘር ማጥፋት እንዲፈጽሙ በር ከፍቶላቸዋል።ይኼው ክስተቱ ከታየ ቆይቷል።በርካታ አድርብ ባይ እና ነብሰ ገዳይ ሁሉ መንገዱ ጨርቅ ሆኖለታል። ወለጋ ውስጥ ከአራጆቹ ለመዳን ተሰባስበው ወደ ጎጃም ሲሸሹ የነበሩና አዳሩን ቤታቸው እየተቃጠለ 70 ሺሕ አማራዎች ባንድ ውድቅት ቀን ተጨፍጭፈው እንዳለቁ ባስተማማኝ መረጃው ተቀባይነት ያለው የኢትዮ 360  የዜና መረጃ  በዛው ወቅት እንዳስተላለፈው ታስታውሳላችሁ።

 የሩዋንዳ ዕልቂት በአማራዎች ላይ አገራችን ውስጥ ሲፈጸም የተባበሩት መንግስታትና የዜና ማሰራጫዎች ሩዋንዳ ውስጥ እንዳደረጉት እዚህም በአርምሞ ደግመውታል። ጃዋርም ሆነ ጠያቂው ‘ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ’ በዚህ ክፍል አንድ ይህንን ትልቅ ርዕስ አንስተው አልተ

የጭፍጨፋው ተዋናዮች ካሁን በፊት ሥልጣን ላይ የነበሩ ትግሬዎች ሲሆኑ ዛሬ ደግሞ ሥርዓቱን እየመሩት ያሉት ኦሮሞዎች ናቸው ለብዙ ዘመናት ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን አስተዳድረዋል (እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ ዛሬም ሥልጣን ላይ ናቸው) ኦነጎች እና 40 አመታትየኦሮሞዎቹ የብሔር ፖለቲካ” ታጥቦ ሊጠራ አልቻለም እያልኩ ለብዙ አመታት ስከራከር የነበረበት ዋናው ነጥብ ይኼው ነበር።

ጃዋር ዛሬም አዲስ አባባን “ፍንፍኔ” እያለ ደጋግሞ ሲናገርና “አዲስ አባባ” ለማለት እንዴት እንደሚጠየፈው ከምን የተነሳ እንደሀነ መዳከር አያስፍልግም። ግልጽ ነው። ዛሬ በተከታታይ ያያችሁት የኦሮሞዎች ፖለቲካዊ ስነ ኣእምሮአዊ እና የባሕሪ ስነምግባር ጥልቅ ማስረጃ መፈለግ አያሻውም። አዲስ አባባን “ፍንፍኔ” ብሎ መጥራት በአደባባይ ሰው ከመስቀል እስከ የአገሪቱ ሰንደቃላማ ከተሰቀለበት እያወረዱ መጣል እና አማርኛ ጽሑፍ በሚኖሩባቸው ከተሞች እንዳይታዩ በቀለም ማጥፋት ሁሉ ያሳዩት ስነምግባር እነ ጃዋር በጥናት ነድፈው ጥገናዊ ለውጡ ያመጣው ሰበብ ነው። ለክርክሬ ማስረጃ ግልጽ ነው።

በቅርቡ ኦነግ የተባለው በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ የፈጸመ የነበሰገዳይ ቡድን ሸሽቶ በጥገኛነት ተጠልሎ ከነበረበት የኤርትራ ምድር ለቆ 1300 ሰራዊቱን (ብዙውን ጊዜ ቶክስ ተካፍለው የማያውቁ 40 አመት ትግሉ ያፈራቸው 1300 ተዋጊዎች ብቻ ነበር። አብይ አሕመድ ወደ አስመራ የላካቸው ለማ መገርሳና ኦሮሞው ወርቅነህ ገበዮህ እርሻ ውስጥማሽላ ቆረጣላይ የነበሩ ኦነጎች ባጣዳፊ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ  በኢሳያስ ፈቃጅነት በተሰጠው ማዘዣ መሰረት አዲስ አበባ ገብተው ወለጋና ባሌ ውስጥ ዛሬ 200,000  ሰው የሚያርዱ በዱር ሕሊና የተበረዙ የኦሮሞ ቄሮዎች እንዲባዙ አድርጓል።

 እነዚህ ሰው የሚያርዱ እና ሰው የሚበሉ አልፎም ከወንድ ጋር ግበረሰዶም የሚፈጽሙ የሰው አራዊቶች (ሺመልስ አብዲሳ እራሱ የነገረን እና አማራዎች ባይናቸው ያዩ እማኞችን የተገኘ ነው ጥቅሱ) ከ700 በላይ የሚሆኑ ቄሮዎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በተለያዩ አውቶብሶች ተጭነው ፒያሳ መሀል ላይ የተበተኑ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው ባንዴራቸውን እያውለበለቡ ኗሪውን እያስጨነቁ ይዘርፉ እንደነበር የተደጋጋመ ክስተት ነበር። የጃዋር ጥገናዊ ለውጥ ያመጣው ሰበብ ነው። ይቅርታም አልጠየቀበትም። ባንዳንዱም እራሱ የተካፈለበት ትርኢት ነበር።

ይህ ሲፈጸም ጥገናዊ ለውጥ እንዲመጣ በንድፍ የሰራንበት ሥርዓት ነው የሚሉት ሁሉም የዚህ የጥገና ለውጥ ነዳፊዎችና መሪያቸው አብይ አሕመድ በሚመራው  አፓይታይዳዊው የነገድ ፖለቲካ በሕዝብቻን ህይወት ላይ ያስከተለው ጥፋት ተጠያቂዎች ቢሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ ላንዴና ለመጨረሻ ይህ የነገድ አክራሪ ፌደራሊዝም ከሕገ መንግሥት እንዲፋቅ ጃዋር መሓመድ እየታገለ እየታገለ እንደሆነ ማስረጃ የለም። ይሁ ሁሉ ጥፋት ሲፈጸም ያለ የእነ ጃዋር አስተዋጽኦ አብይ ብቻውን ሊፈጽመው አይቻለውም እና ኢትዮጵያ ካሳ ባይከፈላት እንኳ  ይቀርታም ሆነ የነገድ ፌዴራሊዝም እንዲወገድ ጃዋር የበኩሉ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪየን አቀርብለታለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

 

 

No comments: