በኩንታሎች የታሸጉ ወርቆች እና 10 ሚሊየን ዶላር በትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረፂዮን እና ረዳቱ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) ተሳትፎ የተመዘበረበት ሚስጥር - (መዘክር አባዲ ዘሞ በትግርኛ ከፃፈው ትርጉም)
ጌታቸው ረዳ (Editor
Ethiopian Semay)
12/7/23
ከትግርኛ
ወደ አማርኛ ትርጉም ጌታቸው ረዳ
በቅርቡ መዘክር አባዲ ዘሞ የተባለ ወጣት ይህንን ምስጢር በጻፈው ተከታታይ
19 ክፍሎች ውስጥ በክፍል 13 ዕትሙ ላይ ለሕዝብ ይፋ ያደረገውን ምስጡር እንመለከታለን።
ይህ ወጣት
ለማታውቁት ካላችሁ ትንሽ ልበል። አባቱ በሱዳን የወያኔ ተጠሪ አምባሳደር እና በ17 የጦርነቱ ወቅት ድርቅ በሚል ሰበብ የተገኘ
ሚሊዮኖች ብርና እህል ዕርዳታ (ሬስት) በሚል ሲጠራ የነበረ የትግራይ ድርቅ መረዳጃ ድርጅት ሓላፊ የነበረና ከዚያም “The
Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT; Tigrinya: ትካል እግሪ ምትካል
ትግራይ) የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (EFFORT) በመባል የሚታወቀው ከመሰረቱትና በሃለፊነት ከመሩት አንዱ ነው።
(የአባዲ
የቤት መጠሪያው ስሙ ‘አስመላሽ ዘሞ’ ይባላል። አብረን አክሱም ውስጥ ያደግንና ጎረቤታሞች የነበርን በወቅቱ በጠባዩ ተግባቢ ትዕግስተኛና
ዘረኛነት የማይታይበት ለየት ያለ ግሩም ሰው ነበር)።
እንግዲህ መዘክር አባዲ ማለት የአምባሳደር አባዲ ዘሞ ልጅ ነው።
አባዲ በ2013 በተደረገው የትግራይ ጦርነት ከተማረኩት የወያኔ ከፍተኛ
ባለሥልጣኖች እና አንዱ ነው።
አሁን ወደ ነጥቡ እንግባ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ግዙፉ አባል የነበረው ትግራይ ውስጥ የተመደበው
“የሰሜን ዕዝ” ቀኑን ሙሉ ሕዝቡን በተለያዩ መስኮች ሲረዱ ውለው ደክሟቸው ጥቅምት 24 /2013 ሌሊት ሀገር አማን ብለው በተኙበት
ውድቅት ሌሊት በወያኔ መሪዎች ትዕዛዝ በተጨፈጨፉበት ወቅት በተነሳው ጦርነት ይህ ወጣት ከወላጅ አባቱና ከወያኔ አማራሩ ጋር ወደ
በረሃ በማፈግፈግ ጦርነቱን በመሳተፍ የጌታቸው ረዳ ጸሐፊ ሆኖ የአመራሩ ሥራ አስፈጻሚ የቅርብ ሰው ሆኖ ሲዋጋ የነበረ ነው። በፕሪቶርያ
ስምምነት ጦርነቱ ከቆመ በኋላ ይህ ወጣት ከትግራይ ወደ አዲስ
አበባ በመሄድ በጦርነቱ ወቅት የድርጅቱ አመራሮች ያሳዩት የጦርነቱ አያያዝ ዝርክርክነት፤ ያንጸባረቋቸው የነበሩት ንቀትና ወዘተ…
የመሳሰሉትን ብዙ ክፍሎች የያዙ ጽሑፎችን ለትግርኛ አንባቢዎቹ እያስነበበ ይገኛል። ይሁን እንጂ ወጣቱ በብዙ መንገድ ያመሰገንኩት
ቢሆንም፤ “ትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረትም ቢሆን “ኢትዮጵያዊነትን” በሽፋን መጠቀም አለብን” ብሎ የሚመክር ከወያኔነት ያልተላቀቀ
መሆኑን ላስምርና ወደ ሰነዱ ላምራ።
ወጣቱ ካሰራጫቸው በርካታ ጽሑፎቹ በክፍል 13 ላይ ያንቀላፋን ዓይን የሚያስከፍቱ
አስገራሚ የምዝበራ ምስጢሮችን አውጥቷል።
በክፍል 13 በገጽ 3 ላይ የትግራይ ክልል ፕረዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን
ገ/ሚካኤል ፤ የትግራይ ክልል ም/ፕረዚዳንት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) እንዲሁም በብዙዎቻችን የማይተወቅ በ1968 ዓ.ም የድሮ የወያኔ ታጋይ የነበረ ከዚያም (1984) ወደ እንግሊዝ አገር ሄዶ በስደት ሲኖር የነበረ “ሃይለ ሊባኖስ” ስለ ተባለ፤ እንመለከታለን።
(ሃየለ ሊባኖስ ከሌሎች በግሌ አጣርቼ ማን እንደሆነ ባጣራሁት ያገኘሁት
መረጃ መሰረት ትውልድ አውራጃው “ሽሬ” ሲሆን ቅጽል ስሙ “ሃይለ ፋሺሰቲ” (ሃይለ ፋሺስት) በመባል ሲጠራ የነበረ ነው። ይህ ስም
የተጠራበት ምክንያት ይላል አንድ አውሮጳ የሚኖር ወዳጄ በሰልክ እንደነገረኝ፡
<< ሓሓይለ በሚባል ገጠር ወረዳ በሃይለ ሊባኖስ ስር 139 የነበሩ እስረኞች የደርግ ‘ፓራ ኮማንዶ’ በአካባቢው ስለታዩ
በስብሓት ነጋ ትዕዛዝ 139 እስረኞች በሙሉ እንደረሸናቸው እና መለስ ዜናዊ መጥቶ ሃይለ ሊባኖስ እስረኞቹ ወደ ሌላ ቦታ ውሰድዋቸው
ብሎ ሲነግረው “በሙሉ ረሽኛቸዋለሁ” ብሎ ሲመልስለት መለስ ዜናዊም ‘ፋሺሰት” በማለት በቁጣ ስለሰደበው በዚያ ስም “ሃይለ ፋሺሰት”
የሚል መጠሪያ የሚጠራ እንደሆነ ወዳጄ ከአውሮጳ ነግሮኛል)።
እንግዲህ “ወጣት መዘክር አባዲ ዘሞ” እነዚህ የተጠቀሱ ሦስት ሰዎች ላይ የአስተዳዳር ብልሹነትና የምዝበራ ምስጢር እንደሚከተለው
ይገልጸዋል።
<< ደብረጽዮን የትግራይ ፕረዚዳንት ቢሆንም ምክትሉ ወ/ሮ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) የምታስተላልፋቸው ትዕዛዞች ፤ የምታፈልቃቸው
ሃሳቦችና ፖሊሲዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በድክመትም ይሁን ወይንም ባልታወቀ ምክንያት የደብረጽዮንን ቦታ በመጋፋት የፈለገቺው
ነገር እንትፈጽም ይፈቅድላታል። ከዚህ ተያይዞ ከጦርነቱ ወዲህ ወደ
ክስተት የመጣው ሰው “ሃይለ ሊባኖስ” የሚባል በብዙ ሰው የማይታወቅ ግለሰብ ነው። ግለሰቡ ከሞንጆሪኖ ጋር እጅግ በጣም የቅርብ
ወዳጀነት ያለው ነው፤ እደግመዋለሁ የቅርብ ወዳጅነት ያለው ሰው ነው።”
ካለ በኋላ (የቲ ኤም ኤን ሚዲያ አዘጋጅ ናትናኤል አሰመላሽ እንደሚለው
ሃይለ ሊባኖስ የሞንጆሪኖ “ውሽማዋ” ነው ይላል- ይህ ሐረግ ከኔው ከጌታቸው ረዳ የተጨመረ እንጂ ከመዘክር የተጻፈ አይደለም)።
ወደ ውሽማዋ ወደ ሃይለ ሊባኖስ ከመሸጋገራችን በፊት ባጭሩ ስለ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) መዘክር አባዲ ዘሞ ካጻፈው ረጆም ጽሑፍ ባጭሩ እንዲህ ይላል።
<…ፈትለወርቅ ያልነካቺው የሃላፊነት ዘርፍ የለም። ሁሉም የሀብት እና የቀውስ እይታ ዘርፎችን የሚመራው
በፈትለወርቅ ሥር ነው።ባጭሩ ከፖቲካው ማለትም ከፕሮፓግንዳው ክፍል በስተቀር ማሕበራዊና ምጣኔ ሓብቱ ዘርፍ በሙሉ በወቁጥጥርዋ ሥር ይመራል።በዚያ ላይ የሠራዊት ሎጅስቲክስ (የጦር መሣሪያና አቅርቦት) ኃላፊ ስትሆን ከምንም በላይ ደግሞ የማዕከላዊ ኮማንድ (ዕዝ) አባል በመሆን ሥልጣን ይዛለች። ወታደራዊ መሪዎችን ከማዘዝ ባለፈ ሲታስፈራራቸው በዓይኔ አይቻለሁ።አንዳንዶቹ አንገታቸው አቀርቅረው ቁጣዋን ያሳልፉታል። ሰውን ማሸማቀቅና መስፈራራት በግዙፉ ይታይባታል።
,…ምክትል ፕሪዳንት ሆና በገባችበት ቦታ ሁሉ ተጠያቂነትን ለማስቀረት ስትል ፌርማዋን አታስቀምጥም። ለምሳሌ የማህበራዊና ኢኮኖሚ አዛዥ
ሆና የሎጂስቲክስ ሀብቶች ስትቆጣጠር በነበረቺበት ወቅት ከቃል ትዕዛዝ በስተቀር ምንም አይነት የጽሁፍ ትዕዛዝ አታስተላልፍም ቢባል ማጋነን አይሆንም።በሥርዋ ያሉ ክፍሎችም ባዘዘቺው መልክ ዝም ብለው ይፈጽማሉ። በማለት ስለ ሞንጆሪኖ ከሓለፊነት ለመሸሽና በሥርዋ ላሉ ታዛዦች ወንጀሉን እእንዲሸከሙት የምታደርግ
ተንኮለኛ ሴት መሆንዋን ይገልጻል።
መዘክር በመቀጠል እንዲህ ይላል፤
<<ሃይለ ሊባኖስ በምዝበራው ውስጥ ዋናው ተዋናይ ሰው ነው።
ከፈትለወርቅ ጋር
በቅርብ ወዳጅነቱ በመተማመን ትላልቅ የማጭበርብር ወንጀሎችን
ከፈጸሙ ሰዎች ቀዳሚው ሰው ሃይለ ሊባኖስ ነው። ሃይለ የንብረት ሓላፊ ሆኖ ከተሾመ ወዲህ
ኮምቦልቻ (ወሎ) ውስጥ የተገኘው 24 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ዋና ሃላፊ
በመሆን ብምስጢር ለገበያ ሽጦታል። ከጠላት የተማረኩ ማሺኔሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በሙሉ “ሞኾኒ” ከተማ ውስጥ እንዲከማቹ አድርጎ
በኋላ ወደ መቀሌ እንዲከማቹ ሲደረግ
ማሺኖሪዎቹና መኪኖቹ መንቀሳቀስ (መስራት) አይችሉም በሚል ሰበብ “እስፔር ፓርቶቹ” (ተለዋጭ ዕቃዎች) ሃይለ ሊባኖስ በምስጢር
እንዲሸጥ ካደረገ በኋላ፤ ሁኔታውን የተጠራጠሩ በአንዳንድ
ሰዎች ጥያቄ ምክንያት መጣራት እንዲደረግ ሲጠየቅ፤ ሆን ተብሎ በሚመስል መልኩ ሃይለ ሊባኖስ ከንብረት ሃላፊነቱ ለቅቆ “ኦዲት” ከመደረጉ በፊት ለቅቆ ወደ ሌላ ሓላፊነት እንዲዛወር ተደረገ።
ይህ እንዳይበቃ ሃይለ ሊባኖስ ደብረጽዮን እና ፈትለወርቅ የተሳተፉበት የገንዘብና የወርቅ ዝርፍያ ተከሰተ።በትግራይ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ስህተትና ኪሳራ ከዚህ በታች ያለው ነው።
በሱዳን የትግራይ ሰራዊት መሪ የነበረው ጄኔራል ፍስሃ ማንጁስ ወደ ትግራይ እንዲመጣ ታዘዘ።
በምትኩ ጀኔራል ወዲ መድህን ወደ ሱዳን እንዲሄድ ተደረገ። በዛው ልውውጥ ወቅት ወዲ መድህን
እና ሃይለ ሊባኖስ በትግራይ መንግሥት መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ሠፍሮ የሚገኝ የወርቅ ብዛት በምስጢራዊ አውሮፕላን በኩንታሎች የታሸገ ወርቅ ይዘው ወደ ሱዳን በረሩ።
ግብይቱ ማደረግ ላልቀረ ፤ በግዥው ክንዋኔ በሰላም ማስከበር ስራ ተመድበው የነበሩ ሱዳን
ውስጥ የነበሩ የትግራይ ወታደሮች መደረግ ነበረበት። ምክንያቱም ወደ
ትግሉ ለመቀላቀል ሱዳን ውስጥ ሆነው የተቀላቀሉት ነባር ታጋዮች “ ፈንጂዎችንና ጥይቶችን ከጥቁር ገበያ በመግዛት በሕገ ወጥ አይሮፕላን ወደ ትግራይ እንዲገባ በማድረግ መልካም ልምድ ያካበቱ ስለነበሩ ወደ ሱዳን ተሸሽጎ የተላከው ወርቅ የጥቁር ገበያ ግብይቱን በነዚህ ልምድ ያላቸው ወታደራዊ
ታጋዮች በኩል በተካኑበት መስመር እንዲሸጥ ከማድረግ ይልቅ በእነ ጀራል ወዲ መድህን እና ሃይለ ሊባኖስ እንዲከናወን የተደረገው ክስተት
እንዴት እንደነበር እንመልከት። ይላል መዘክር፤
በመቀጠል
<< በነ ደብረጽዮን እና ፈትለወርቅ እውቅና ትዕዛዝ ወርቁ በሃይለ
ሊባኖስ ሓላፊነት አንድ ቻይናዊ ደላላ ለመሳሪያ ግብይት እንዲሸጥላቸው ተዋውሎ፤ ቻይናዊው ደላላ ለሥራው ልፋቱ $10ሚሊዮን ዶላር
ስለጠየቃቸው፤ 6.7 ሚሊዮን ዶላር ቢሰጡትም፤ ቻይናዊው በሙሉ ካልሰጣችሁኝ
ብሎ አይሆንም ስላላቸው፤ ከዲያስፖራ ትግሬዎች ለጦርነቱ “ለመክት ዘመቻ” ተብሎ የተዋጣ $10 ሚሊዮን ዶላር ሰጥተውት፤ ቻይናዊው
ዶላሩን ታቅፎ ደብዛው እንዳጠፋ ይነገራል።…..>>….
<<በሕዝብ ስም የተመዘገበው የሕዝብ ንብረት የሆነው ወርቅም
በሃለ ሊባኖስ ተበልቶ ይዞት ወደ እንግሊዝ አገር በረረ። ሃይለ ሊባኖስ እንግሊዝ አገር ብዙ ቤቶች እንደገዛ ሰማሁኝ።ግብይቱም በበላይነት
ሲመሩት የነበሩት ደብረጽዮን እና ፈትለወረቅ ገብረእግዚአብሔር ናቸው። ጀኔራል ወዲ መድህን ግን በማጭበርበሩ ትርፍ እጁ ስላላገባ
ይመስላል ያለ ሰቀቀን ትግራይ ውስጥ ተመልሶ እየኖረ ነው።……..
<< ከ4ወይንም ከ5 ወራት በፊት “ጂ ኤስ ቲ ኤስ” GSTS << Global Society of Tigray Scholars and Professionals” (ዓለም አቀፍ የትግራይ ምሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር) ከደብረጽዮን ጋር ባደረጉት አንድ የውይይት መድረክ ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ "ለድሮን እና ለጥይት መግዢያ ከዲስፖራ ትግረይ የተዋጣው $10 ሚሊዮን ዶላር የት ገባ?" የሚል ነበር። ደብረጽዮንም "ስርዓቱን እያጸዳን ነው፣ በሕግ እየተከታተልነው ነው” ሲል መለሰላቸው። ይሄ ግን ነጭ ውሸት ነው።በጥቁር ገበያ ከቻይናዊ ደላላ ጋር ሲገበያዩ ነበር ተብለው በዓለም አቀፍ የጦር እና የንግድ ወንጀል እንዳይከሰሱ በመስጋት በደፈናው “ግብይቱን ሳይጠቅስ” በደፈናው መለሰላቸው።>>……....
<<…….ይህ በዲያስፖራ ትግሬዎች ላብ የተገኘ ገንዘብ በዚህ መልክ መጥፋቱ ትልቅ ወንጀል ተፈጽሟል።በእዚህ ወንጀል በዋናነት ተጠያቂዎቹ ደብርፅዮን እና ፈትለወርቅ ናቸው።>>……..
<…….እርስበርሳቸው እየተፈራሩና እየተጠራጠሩ ተከባብረው እየቀጠሉ ያሉበት ምክንያትም ይህ የወንጀል ሱታፌአቸውና ተጠያቂነት ስለሚያሰጋቸው ነው። ሁለቱም ያጠፉት ጥፋት አለ። በገንዘብ ማጭበርብር ብቻ እንደሆነም መታሰብ የለበትም።>>…..
<…….ሠራዊታችን ጠላት
ደምስሰውት በነበረበት ወቅት ተተኳሽ ጥይት በማጣታቸው
ምክንያት ወደ ኋሊት እንዲያፈገፍጉ በተደረገበት ወቅት በብዙ
ቦታዎች ውግያዎች ቀጥለው ነበር። በውግያው ወቅት በተተኳሽ ዕጥረት ምክንያት ስንት ሰው እንደተሰዋ ሳስበው ጫናው
ይከብደኛል።በብፕሬዚዳንት ፈትለወርቅ የታየው ቸልተኝነት ይሁን ወይንስ አቅም ማነስ ወይንስ የቅንነት ጉድለት ይሁን ምክንያቱን
መነሻው ለመገመት ይህ ነው ለማለት ባልችልም ያስከተለው ጉዳት ከባድ ዕዳ እንዳስከፈለን አውቃለሁ።>….
<……የመጨረሻ ተስፋ እንድቆርጥ ያደረገኝ በመጨረሻው የጦርነቱ ወቅት የተከሰተው በጣም አሳዛኝ ክስተት
ነበር።ካለፈው ጦርነት ጋር ተያይዞ በየቦታው ከባድ የነዳጅ እጥረት ችግር እንዳለብን ባለፈው ጽሑፌ መግለጼ ይታወሳል። ታንኮች
በነዳጅ ዕጥረት ምክንያት አደጋ ላይ የወደቁበት፤ የቆሰሉ ታጋዮች ነዳጅ ስላልነበረ ካሉበት መንቀሳቀስ አልተቻለም።>….
……ይህ ዕጥረት ለመቅረፍ ወፍጮ ቤት አለ ወደ ተባለ ቦታ ሁሉ በመሄድ ‘በሃይላንድ’ (በፕላስቲክ ጠርሙስ) ከየወፍጮ ቤቶች ጀኔሬተሮች የያዙት ትንሽየ ናፍጣም ብትሆን በመገልበጥ በተገኘው ትንሽ ናፍጣ በመጠኑም ቢሆን ታንኮችን ለማንቀሳቀስ ተሞከረ።……>
<………የተወሰኑት ከጠላት እጅ እንዳይገቡ
ሲደረግ ፤ማንቀሳቃስ ያልተቻሉትን ግን በርከት ያሉት ታንኮች በጠላት እጅ ወደቁ።ከከባድ የደም መፋሰስ በኋላ ጥይት ጨርሰን የነበረን አማራጭ “በድንጋይ ውግያ” ግባ በተባልንበት ወቅት ውግያው ይቁም
ተብሎ የቶከስ ማቆም ስምምነት ፕሪቶርያ ላይ ተፈረመ።………
<…….ጊዜያዊ መንግስት ተቋቁሞ አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዝዳንት ከሆኑ ከሳምንት በኋላ በትግራይ ውስጥ “አግበ” በሚባል ቦታ 380,000 ሊትር ዘይት ተከማችቶ ተገኘ። በነዳጅ ዕጥረት የደረሰው ጉዳት እንዳለ እየታወቀ ይህ ያህል ክምችት በክልሉ ውስጥ መገኘቱ ያስደነገጣቸው ሰዎች ወ/ሮ ፈትለወረቅን “ይህ ሁሉ ነዳጅ እንዴትና ለምን እስካሁን ተከማችቶ ቆየ? ተብሎ ስትጠየቅ የሎጂስቲክስ አስተባባሪ መሆኗን በመዘንጋት በጦርነቱ ውስጥ ስላለው የነዳጅ ችግር እንደማታውቅ የሰጠቺው መልስ ፤-
<< ለቢሮ መኪናዎች መጠባበቂያ እንዲሆን ታስቦ ነው>>
ብላለች።……
<……….እስኪ አስቡት! በነዳጅ እጦት ስንት ታንኮች እንደተዘረፉ፣
ስንት ታንክና መድፍ በጠላት እጅ እንደወደቀ ፣ስንት ልጆች በየወፍጮ ቤቶች እየሄዱ በብልቃጥ
የተገኘውን ሁሉ እያንቋረሩ እያጠረቃሙ በየቦታው የተንከራተቱ አግኝተው እስኪመለሱ ድረስ በየታንኮቹና ከመኪና ጥበቃ የነበሩ ጓዶቻቸው
በሰው አልባ አውሮፕላኖችና (ድሮኖች) ሲገደሉ፣ስንቱ የቆሰሉ ተዋጊዎች እንዳሉ አስቡት። የሕክምና ክትትል ሳያገኙ በየቦታው ወድቀው
የቀሩት ማሰብ ለሕሊና ይከብዳል።……
ቀዳሚው ነገር ከምንም በላይ የቢሮ መኪናዎች የሚጠቀሙት ነዳጅ ቅድሚያ
ተሰጥቶት በአውደ ውግያው ግን በነዳጅ ዕጥረት ምክንያት የደረሰው የሰውና የንብርት ኪሳራ ሲነጻጻር እውን አብረን እየታገልን ነበርን?
የሚል ጥያቄ ያስጭራል። ……..
……..የተገኘው ነዳጅ ጊዜአዊው የትግራይ ክልል መንግሥት ከፈትለወርቅ መረከቡንም እዚህ በምታዩት የሰነድ ማስረጃ ደረሰኝ መስጠቱን ይታወቃል።…..
…..ክቡራን አንባቢዎች ፤ ትግራይ አሳፋሪ በሆነ የአመራር ውድቀት እጅ
እንደወደቀች የእኔን 13 ክፍሎች ጽሑፍ ያነበበ ማንኛውም ሰው ችግሩ የት እንዳለ በተወሰነ ደረጃ እንደተረዳው ተስፋ አደርጋለሁ።>>
ሲል መዘክር አባዲ ዘሞ ጽሑን አሁንም እስከ ክፍል 19 እየተነተነ ይገኛል።
መዘክር ከአዲስ አበባ ወደ ወደ ትግራይ የማይሄድበት ምክንያት ሲገልጽም
ከላይ በጠቀሰው ወንጀል የማጋለጥ ጥረቱ የተነሳ ትግራይ ውስጥ ከመንግሥት እስርቤቶች ሌላ ጀኔራሎችና የግል ሰዎች የመሰረትዋቸው
እስርቤቶች በየቦታው እንደ አሸን በመፍላታቸው ምክንያት “ማን እንደሰረህ፤ የሰትስ ቦታ እንደታሰርክ ማንስ እንደሚገድልህ ስለማይታወቅ”
መሄድ እንዳልቻለ ይገልጻል።
ለዘመናት በኛ የደረሰን ዕጣ ፈንታ ለታጋዮቻቸውም እየደረሰ ሳይ ከመገረም ሌላ ምን ልበል። መከርን እምቢ አሉን፤ ዛሬ ወደ እነሱ ዞረባቸውና የታገሉለትን የትግራይ መሬት መርገጥ አይፈቀድላቸውም። ጥናቱንና ብርታቱን ይስጣችሁ እላለሁ።
ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment