ትግሬዎች በኢትዮጵያ አንገት ያጠለቁላትን የመታነቂያዋ ገመድ ለማስለቀቅ በሚደረገው ትግል የምትቃወም ሶማሌም ሆነች ኤርትራ እንዲሁም የአብይ አሕመድ ታቃወሚዎች ከፈለጉ በገመድ መታነቅ ምርጫቸው ነው!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
1/6/2024
ካሁን በፊት ትግሬዎች በዘመነ ሥልጣናቸው የሚያስመሰግናቸው ያስቀመጡት “የአባይ ግድብ” ‘መሰረተ ድንጋይ’ ተቃዋሚው ገደብ የለሽ መንጫጫት ሲያስማ፤ ዘግየት ብልም <<መንጫጫት አያስፈልግም>> ስል ጌታቸው ረዳ “ወያኔ ሆነ” እንዳላችሁኝ ሁሉ፤ ዛሬም እንደልማዳችሁ ጌታቸው ረዳ “ኦሮሙማ ሆነ” ማለታችሁ ስለማይቀር ረጋ በሉ። Check the Video at the end of this article.
የዛሬ ቀን ወጋችን የወደብ ጉዳይ ነው። ከተቃዋሚው ጋር የተለየ አቋም ይዤ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ እየተነተንኩ ነው። አንደኛው በቀደም ስለ ዓሰብና ጁቡቲ ወደብ ባለቤትነት ልመና የነበረው አድካሚ ሙከራ እና ቀጥሎ ዛሬ ደግሞ በሶማሊ ላንድ እተደረገ ያለው የ50 አመት የ20 ኪ.ሜ የባሕር ወደብ ባለቤትነት ስምምነት በኢትዮጵያ ስምና ለኢትዮጵያ ህልውና ስለሆነ የወደብ ፍለጋ ጉዳይ እየተደረገ ያለው በአብይ አሕመድ የሚመራው ፋሺሰቱ የኦሮሙማው መንግሥት ካለው የአገሪቱ የወደብ ችግር “ከሰይጣንም” ጋር ተፈራርሞ ወደብ ለማግኘት መሞከሩ የሚመሰገን እንጂ የሚያስኮንነው መሆን የለበትም የሚል ድጋፍ እያስሰማሁኝ ነኝ።
ዓለም በምቾት አትንቀሰቀስም። ሞተናልና መሞታችን ላይቀር ፤ ሞት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም። አገርም እንዲሁ ለህልውና ሲባል መሞትና መነሳት ያለ ነውና ትግሬዎችና ኤርትራኖች ተስማምተው 1983 (1991 ፈረንጅ ዘመን) ባንገታችን ላይ ያጠለቁልንን የ36 አመት ገመድ ለማውለቅ የፈለገው የሥልጣን ብልግና የሚፈጽም መንግሥትም ይሁን “የተንጠለጠለብንን ያንገታችን ገመድ” ላማውለቅ የሚጥር መሪ <<ማውለቅ ከቻለ>> በዝምታ መመልከት እንጂ መንጫጫት ተገቢ አይደለም።
ያው የተቃዋሚው ጀሌ እንደለመደው ሊንጫጫ ይችላል፤ እርሱም በመንጋነት መነዳቱ ሱስ ካደረገው አመታት ያስቆጠረ ስለሆነ እርሱም እንደ ሶማሊያዎቹና እንደ ኤርትራኖቹ ሲፍልግ ትግሬዎች ባንገታችን ያጠለቁልንን ገመድ ተጠቅሞ መታነቅ ይችላል።
ኤርትራዊው መለስ ዜናዊ ግድብ ለማነፅ ሲያቅድ መንጫጫታችን ትክክል እንዳልሆነ ሁሉ ኦሮሙማውም ወደብ ፍለጋ መራኮቱ መንጫጫት አያስፍልግም። ቢቻል ቢቻል እንኳ መደገፍ ካልፈለጋችሁ “ዝምታን” እንጂ ከሶማሊያኖችን ኤርትራኖች እንዲሁም ከግብፆችና እንዲሁም ከዓረቦች ብሳችሁ መንጫጫት ያስተዛዝባልና ሰከን ማለት አለባችሁ።ለነገ በይደር የሚደረግ አርምጃ ሁሉ “ነገን ከነገ ወዲያ” ምን ውልዳ እንደምትመጣ ስለማይታወቅ ነገር ባደረ ቁጥር ገመዱ እየጠበቀ መሄዱንም ማስተዋል ያስፈልጋል። ፖለቲካና አገር መለየት ልባምነት ነው።
አንዳንድ ተቃዋሚ ሚዲያዎች የሚያስሰሙትና የሚዝቱት ድምፀት፤ ጠላትን እያጎለበቱ ኢትዮጵያን የሚያንኳስስ ፕሮፓጋንዳና ውይይት ስሰማ “ጠመንጃ ይዘው” ከሶማሊያ እና ከዓረቦች ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ለመውጋት የፈቀዱ እስከሚመስል <<የሚያስሰሙት ድምፀት>> እጅግ የሚገርም ዕብደት ነው።
ይባስ ብሎም የሶማሊያ ተወላጆችም ሆኑ ኤርትራኖችና አክራሪ ሶማሊ እና ኦሮሞዎችን ወደ ሚዲያቸው እየጋበዙ ተቃውሞ እንዲያስሰሙ በመጋበዝ እያደረጉት ያለው አስገራሚ ፕሮፓጋንዳ “ሶማሊያዎች ወይስ ኢትዮጵያኖች” ናቸው የሚል ጥያቄ ያስጭራል።
በጥር 1991 የሲያድ ባሬ መንግስት መውደቅ እና በ1998 ዓ.ም የሽግግር ብሄራዊ መንግስት ተመስርቶ ከዚያም ሶማሊያ በ6ቱ የነገድ ጎሳ (ክላን) መሪዎች ተከፋፍላ ወደ ስብርባሪ “አገርና መንደር” ተለውጣ <<የዘላን ምንግሥታት የሚያስተዳድርዋት ‘ሥርዓተ አልባ’ ሆና የዘመናችን “የወደቀች የተበላሸች አገር” ተብላ “አክራሪ እስላማዊ ሽብርተኞች” ሶማሊያን ሰላም ነስዋት። ከዚያ <<ምፅአተ ሶማሊያ>> ለማላቀቅ ኢትዮጵያ ልጆችዋን ወደ ሶማሊያ በመላክ መስዋእት ከፍላ ሶማሊያ አሁን ወዳለችበት መረጋጋት ካደረስዋት አገሮች ግምባር ቀደም ሚና የተጫወተቺው ኢትዮጵያ ነበረች።
ስለ ሁሉም ጎረቤት ሕዝብ የምትጨነቅ፤ ሁሉንም አስተናግዳ የምትንከባከብ ኢትዮጵያ ዛሬ <<እጇ አመድ አፋሽ ሆኖ>> የወለደቻቸውም ሆኑ የውጭ ዜጎችና ጎረቤቶችዋ ሁሉም ተዛበቱባት (ዕድሜ ለትግሬዎችና ለኤርትራኖች ባንገትዋ ገመድ አጠለቁባት)
ሶማሊያ ማእከላዊ መንግሥት አልነበራትም ፤አሁንም የሚንገዳገድ ነው። ሶማሊያ አገር የሆነቺው በቅርቡ ነው። በ1960 ዓ.ም <<ፑንትላንድ እና ጋልሙድ>> ያሉ ትላልቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያልተሰጣቸው እና የሶማሊያ የራስ ገዝ ክልሎች ሆነው ይተዳደሩ የነበረ ሲሆን በሰሜናዊ ምዕራብ የሚገኙ ኃይሎች የሶማሌላንድ አሁን ካለቺው ሶማሊያ በቋንቋ እንጂ በአገራዊ አመሰራራት ዕድሜአቸው ሁሉም ለየብቻ የጣሊያንና እንግሊዝ ተገዢዎች ስለነበሩ ዛሬ ሶማሊ ላንድም ሆነች ፑንት ውሎው አድረው ሪፐብሊክን አወጁ።
ሶማሊ ስትወድቅ አጋጣሚውን አገኙና ዋና ከተማዋን ሞቃዲሾን ጨምሮ ቀሪዎቹ አካባቢዎች በተፎካካሪ አንጃ መሪዎች የሚተዳደሩ ትንንሽ ግዛቶች ሲካፋፈሉ <<ሶማሊ-ላንድም ልክ እንደ “ከሃዲዋ” ኤርትራ የጣሊያን ገዢ ነበርኩ ብላ አርስዋም ከኤርትራ እንዴት አንሳለሁ ብላ ነፃነቷን አወጀት። ኤርትራ ነፃ መውጣት ከቻለች (ሕጋዊ ባይሆንም) ያውም ሶማሊ-ላንድዋ “ይልቅኑም” ከኤርትራ በበለጠ አገርነት ለማወጅ ሕጋዊነት አላት። ሶማሊያ ዘላን እንጂ የተሰባሰበ አገርነት አልነበራትም። ይልቁኑ የጥንትዋ ኢትዮጵያ አካልም ነበረች።
በዚህ ወቅት ሶማሊያ አገር አልባ የሆነች ማህበረሰብ እና መደበኛ የህግ ሥርዓት የሌላት ሀገር የገሃዱ ዓለም ምሳሌ ተደርጋ የምትጠቀስ አገር በሌላት አቅሟ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ስትዝት ተቃዋሚው ድጋፍ ሰጥቶ “አብይ አሕመድን ለመዘባበት” ሲል ኢትዮጵያ ላይ ሰይፉን ሲመዝ ማየት ያበሳጫል።
አሁን በመንጫጫት የባሰ ደምፅ እያስተጋባ ያለው ተቃዋሚው ሆኖ ከሚያስደምጠን አስገራሚ ተቃውሞና “ትያትራዊ ፌዝ” ወግንተኛነቱ ከኢስላሚክ ፍርድ ቤቶች ህብረትና አልሸባብ ጋር እስኪያስመስለው ድረስ እየጮኸ ስለሆነ፤ ተቃዋሚ ሚዲያዎች “አደብ” እንዲያደረጉ እጠቁማለሁ።
አሁን ሶማሊያ በምትፎክረው ፉከራ ‘‘እስላማዊ ሃይሎችንም ሆኑ ተገንጣይ ኢትዮጵያ ቡድኖች እደግፋለሁ ካለች’’ “እያሳከካት ያለው ወደ ነበረቺበት “ሥርኣተ አልባነት ለመመለስ ስለሆነ ያ እንዳይመለስባት መጸለይ ያስፈልጋታል”።
ሶማሊያ ሕልውናዋ በኢትዮጵያ ወታደሮች ጥበቃ ስር ስለሆነ 6 ሚሊዮን ሶማሊ-ላንድ እና 100 ሚሊዮን ኢትዮጵያን እገጥማለሁ ካለች (አብይ አሕመድ ወለዋይና አቋመ ቢስ የሆነ ስለሆነ እንጂ ቃሉን ከጠበቀ) ሞቃዲሾን እና አብዛኛውን የሶማሊያን ክፍል በአማፂያን እጅ እንደምትወድቅ ሶማሊያ ልብ ያለቺው አትመስልም።
ሶማሊያ በእግሯ ለማስቆም ሕግና ስርዓትን ለማስፈን የታገለቺላትን ኢትዮጵያ የታሪክ ወንጀለኛ ትግሬዎች ያስገቡላት ገመድ ለማጥበቅ መዛትዋ ለኛም ለእርሷም ለማንም አይበጅምና <<በትግሬዎች የታነቅንበትን ገመድ>> ለማውለቅ ስንሞክር የሚታገልንን ማንኛውም ፖለቲካ እናወግዘዋለን። ኢትዮጵያ ስትጨነቅ አብሮ ከጠላት ጋር ጭንቋን የሚያባብስ በታሪክ ነበር ፤ዛሬም አለ፡ ለወደፊቱም ይኖራል።
ጽሑፉን “ሼር” ብታደርጉም ባታደርጉም የራሳችሁ ጉዳይ፤ እኔ የዜግንት ድርሻየን ወርውሬአለሁ። check the video at the bottom of this page. video credit to Futurology. If you cant open the video, just copy and paste the title given to Google (you tube)
አመሰግናለሁ!
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment