Thursday, December 28, 2023

የሰንደቃላማችን ሕብር መቸ ተጀመረ? ምንስ ትርጉም ተሰጠው? መልስ ለወያኔዎች ከጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/28/23

 የሰንደቃላማችን ሕብር መቸ ተጀመረ? ምንስ ትርጉም ተሰጠው? መልስ ለወያኔዎች

ከጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

12/28/23

እንደምታውቁት የወያኔ መነሻና ባሕሪው << ጸረ አማራ’ ፀረ ኢትዮጵያና ጸረ የአትዮጵያ ሰንደቅዓላማ>> እንደሆነ ከወያኔ ትግሬዎች መሪው ከባንዳው “የባሕር ወደብ ዘጊው” ኤርትራዊው መለስ ዜናዊ ከተናገራቸው እና እንዲሁም የወያኔ ጸሐፍቶች ከሚጽፉዋቸው መጽሐፍትና ከሚናገሩት ንግግራቸው ማወቅ ትችላላችሁ።

 በዚህ ላይ ብዙ ጽፌአለሁ፤ በመጽሐፌም በመጣጥፍም ጭምር። ሰሞኑን በየስብሰባው ኢትዮጵያን አማራን፤ሰንደቃላማችንን ፤ አጼ ምኒሊክን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መሪዎችን በመዝለፍ የወያኔ ፋሺሰቶች መቀሌ ውስጥ በሚያደርጉት <<የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታና የትግራይ ኦርቶዶክስ ምስረታ>> ላይ ቅስቀሳቸው ያለገደብ ልቅ ሆነው የትግራይን  ወጣት ትውልድ  እንዲያደናግሩት <ሆን ብሎ> አብይ አሕመድ በር ከፍቶላቸዋል። ትፍረስ እያሉ በሚማግጡባት “በኢትዮጵያ በጀት” ተቀጥረው “ደሞዝ እንዲያገኙ፤ መኪና፤ ነዳጅ፤መድሃኒት፤ቴሌፎን እና የቁሳቁስ ፍጆታ ከሚጠሉዋት ከኢትዮጵያ እንዲጠቀሙ እያደረገ ነው። የሚያስራቸው፤የሚቆጣጠራቸው የለም። የግንጠላ ቅስቀሳ <<በፕሪቶሪያ ስምምነቱ>> ቁጥጥር እንዲደረግበት ቢፈራረሙም። ታዲያ በፖለቲካውና በሃይማኖታዊ ግንጠላ ስብሰባ ሲያደርጉ በግጥምና በንግግራቸው ላይ መነሻቸው የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ የአማራ መለያ እንጂ የትግሬዎች መለያ እንዳልሆነና በታሪክም እንዳልነበረ ሳይሸማቀቁ አዲሱን ትውልድ “የወያኔ የሼል ነዳጅና የሜክዳኖልድ ሳንድዊች መለያ ምልክት  የሚመስለው”  የወያኔ ባንዴራ ፤ የትግራይ መላያ ሆኖ እንዲኖር ወጣቱን እየሰበኩት ነው።

ሌላ ቀርቶ ኢትዮጵያውያን (በተለይ የአማራ ነገሥታት) በገነቡዋቸው የአክሱም ቤተክርስትያናት ላይ የወያኔ ድርጅት እንጂ የአገራዊ መለያ የሆነው ሰንደቅዓላማችን እንዳይታይ በሕግ አግደውታል። በሚያስደነግጥ ሁኔታ ትግራይ ውስጥ ልክ እንደ ጀርመን ናዚዎቹ <ሃይማኖትና ፖለቲካ> ተደበላልቀው እጅና ጓንቲ ሆነው ለግንጠላ እያሴሩ እንዳሉም የምታውቁት ነው።

እንዲህ ሆኖም ፤ አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ የአክሱም ነገሥታትም ሆኑ የትግራይ ተወላጆች የሆኑት የኢትዮጵያ ነገሥታት ተጠቅመውበት አያውቁም ፤ጀማሪው የሸዋው አጼ ምኒሊክ ነው>> እያሉ ድንቁርናቸው ስያስተጋቡ ሰምተናል። እስኪ እውነታውን የመንደፈራ አውራጃ (ኤርትራ) ተወላጅ  ከሆነች ተመራማሪት በ ወ/ት ሰሎሜ ገብረ እግዚአብሔር  በ1956 በኢትዮጵያ አቆጣጠር በፈረንጅ (1966) የተጠቀሰው ሰነድ እንመርምር።

<<የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዴት እንደተፈጠረ እና የቀለማቶቹ ትርጉም የመጨረሻ ዕልባት አልነበረም እና በሰዎች አመለካከት ላይ ቀጣይነት ያለው ማስተካከያ እየተደረገበት መጥቷል። ሁሉንም የትርጉም ልዩነቶች መከተል በተወሰነ ደረጃ ግራ ያጋባ ቢመስልም። ሆኖም፣ የቀለማቶቹ ዓይነቶች እና መቸ እንደጀመረ እንዲሁም ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ለአብነት ያህል፣ <<የኢትዮጵያ ኢንስቲትዩት ጥናትና ምርምር ረዳት በሆነችው ወይዘሪት ሰሎሜ ገብረ እግዚአብሔር>> የተሰበሰበውን የጥናት እትም በመጥቀስ እንመለክት።

እንዲህ ትላላች፡

<<ቀለሞቹ እና አቀማመጣቸው አሁን እንዳሉ ነበሩ (ነገር ግን አንድ ላይ አልተሰፉም)። የቀለማቶቹም ትርጉም እንደሚከተለው ነው-

አረንጓዴ ለንጉሱ

ለአይሁዱ ሃይማኖት ቢጫ

ቀዩ ቀለም ደግሞ  ለሠራዊቱ ነበር።

ሰንደቅዓላማው የተጀመረው <<የንግሥት ሳባ እና የንጉሥ ሰለሞን ልጅ የሆነው በቀዳማዊ ምኒሊክ ሰለሞን>> ንግሥና የተጀመረ  ነው።  ሆኖም አክሱምን ባጠፋችው “በንግስት ዮዲት” ዘመን ቀለማቱ ትርጉማቸውን ቀይረው ፤

 አክሱም ቀይ፣

 ላስታ አረንጓዴ

 አማራ ቢጫ ወሰደ።

 ከዚያም አጼ ይኩኖ አምላክ ቀለማቱን አንድ ላይ አደረጎ ሰፋቸው። በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጼ ዮሃንስ የሠራዊቱን አስፈላጊነት ለማሳየት <<ቀይ ከላይ አስቀምጠው><፣ <<በመሃል ቢጫ ለቤተክርስቲያን>> << አረንጓዴ ከታች ለንጉሱ>> ሰየሙት። ይህ እትም ከቀድመው የበለጠ ጥቅም አለው።

የአፄ ዮሐንስን ባንዲራ ከግምት ውስጥ በማስገባት <<የላይኛው እና የታችኛው ቀለም አቀማመጥ ተጠብቆ የቆየበት ፣ የላይኛው እና የቀለም አቀማመጥ የሚገለበጥበት ። ሆኖም የዚህ ባንዲራ መካከለኛ ሕብር “ነጭ” እንደነበረ በእርግጠኝነት መቀበል ይቻላል።>> ትላላች የትግራይ ተወላጅዋ ሰሎሜ ገብረ እግዚአብሔር ባደረገቺው ምርምር።

ከዚያ የቀጠሉ ገሥታት ደግሞ ቀለሞቹ አረንጓዴ ለልምላሜ ቢጫው ለሰላም ቀዩ ለአንድነት ሲባል የሚከፈለው ደም ሲሉ ደንግውታል።

ምንጭ - (Second Note on the Ethiopian National Flag, with comments on its historical and sociological sources (by Stanislaw Chojnocki) presented at Proceedings of the Third International Conference of Ethiopian Studies Addis Ababa 1966 ( p.137) ከሚል እኔ ጋር ከለው ሰነድ የተገኘ። ትርጉም የራሴ።  

እንግሊዝኛውም እነሆ እንዲህ ይላል።

<<፡The version of how the flag created and of the meaning of the colours was by no means final and there is a continuous adjustment of it to the attitude of people. It seems somewhat frustrating to follow all variants of it. It however, as ab example, one can quote the version collected by Wayzerit Salome Gabra Egziabher, research and assistant at the Institute of Ethiopian Studies The flag was created by Menelik I, son of Solomon and the Queen of Sheba

The colours and their arrangements were as they are now (but not sewn together). The meaning of the colours being as follows:

Green stood for the king

Yellow for the Jewish religion

Red for the army.

Under Judith, the Queen who destroyed Aksum, the colours changed their meaning: Aksum took red, Lasta Green and Amhara Yellow. Emperor Yikuno Amlak put the colours together. In the 19century Emperor Yohannes put red on the top in order to show the importance of the army, yellow in the middle for the church green at the bottom for the king. This version has the advantage over the previous that it takes into account the flag of Emperor Yohannes, still preserved in which the arrangement of the upper and lower colours is preserved, in which  the arrangement of the upper and colours is reversed. However it can be accepted as certain that the middle band of this flag was white.>>  

(Second Note on the Ethiopian National Flag, with comments on its historical and sociological sources (by Stanislaw Chojnocki) presented at Proceedings of the Third International Conference of Ethiopian Studies Addis Ababa 1966 (p.137) ይላል።

ከሰነዱ አንድ ነገር ጠቅሼ ልጨርስ፡

<<Insult to the flag is sentenced to death and there is no amnesty for it>>

ሰንደቅዓላማን የሰደበ በሞት ይቀጣል፤ለዚህም ምሕረት የለም>>። ይላል ሰነዱ።

በተጨማሪ አፄ ዮሐንስም ቆይተው አሁን ያለው የሕብሮቹ ቅደም ተከተል እንደተከተሉ ሰነዱ ያብራራል። ሰነዱ ብቻ ሳይሆን አቻምየለህ ታምሩም በራሱ ፎቶግራፍ በቤተመንግሥታቸው ለጉብኝት ሄዶ ያነሳው ሰንደቅዓላማ አሁን ያለው ሰነደቅዓላማ (የወያኔን ማለቴ አይደለም) መሆኑን በፌስቡኩ በለጠፈው ሰነድ እንደተመለከታችሁት አምናለሁ። 

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

 

No comments: