Tuesday, August 8, 2023

በሻለቃ ዳዊት ንግግር ልደቱ አያሌው እና ቴድሮስ ጸጋዬ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/6/23

 

በሻለቃ ዳዊት ንግግር ልደቱ አያሌው እና ቴድሮስ ጸጋዬ

 

ጌታቸው ረዳ

 

Ethiopian Semay

 8/6/23



<<ዛሬ ኢትዮጵያ አንድ ታላቅ ሰው አጣች ብሎ ለአማራ ሕዝብ መርዶ የነገራቸው የመለስ ዜናዊ ሞት ያስለቀሰው ልደቱ አያሌው ሻለቃውን ይቅርታ ይጠይቁ ብሎ የመጠየቅ ሞራሉ ከየት አገኘው? እውን መለስ ዜናዊ ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበር? (ጌታቸው ረዳ)

<< አማራና ኦርቶዶክስ ክርስትያን የአገሪቱ ዋና አከርካሪዋ ናቸው!>>  (ጥቅስ የራሴ)

ሰሞኑን ሻለቃ ዳዊት የተናገርዋቸው ንግግሮች ለብዙ ሰዎች አነጋጋሪ ሆኖ ሲንሸራሸር ቆይታል። ንግግራቸው ከወደ ታች እጠቅሳለሁ። የሻለቃው ንግግር በተለይ አክራሪ ክፍሎችና መደዴዎቹ (ዮኒ ዮኒዎቹ) አደንቋሪ ከበሮአቸው ሲደልቁበት ሰንብተዋል። ከፖለቲከኞች ደግም ጠንከር ያለ ተቃውሞዎች ያቀረቡ ሁለቱ ልደቱና የርዕዮት ሚዲያው ቴድሮስ ጸጋ እንመለከታለን።

በሻለቃው ንግግር ቴድሮስና ልደቱ በራሱ በቴድሮስ ጸጋዬ በርዕዮት ሚዲያ ላይ ሁለቱም ሲወያዩ ስለ ሻለቃው ቴድሮስ ልደቱን እንዲህ ሲል ውይይቱን ይጀምራል።

<< በጣም ችግር ፈጣሪ የሆኑ ንግግሮች ሲንጸባረቁ አይቻለሁ>>…<<ወደ እዛው ወደ ገሃነም የሚወስዱ አስተያየት እንዳይሆኑ የሚል ስጋት ስላለኝ ነው አስተያየት ካለህ ስጥበት።

የሻለቃ ዳዊት ንግግር በአውድዮ ቪዲዮ ለአድማጮች ግንዛቤ እንዲረዳ ሻለቃው የተናገሩትን ቴድሮስ ለልደቱ እንዲህ ያስደምጠዋል።

የሻለቃ ዳዊት ንግግር፡

<<ኢትዮጵያ የአማራ ነች ኢትዮጵያ እዚህ አሁን ድረስ ያደረሳት አማራ ነው። ስለዚህ ለማን ነው የምንሰጠው ኢትዮጵያን? ኢትዮጵያ እኮ የኛ ነች፤ የኛ ነች! እኛ ነን እዚህ ያደረስናት ታሪካችን ባህላችንሰንተርማዕከል ሆነን እዚህ ድረስ ያመጣናት ኢትዮጵያ እኛ ነን።>>

ቴድሮስ ከላይ የሻለቃ ንግግር ካደመጠ በኋላያገሪቱን ስሪት በተመለከተ የተሰጠ አስተያት ሲሆንቀጥሎ ደግሞ ፖለቲካዊ ግብን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት በስፋት አወያይቷል፡ፕሪኮዥንይኖረዋል የሚል ስጋትም አለኝ።ይላል ቴድሮስ ጸጋዬ የሚከተለው የሻለቃው ንግግር ልደቱ ሃሳብ እንዲሰጥበት፡

የሻለቃ ዳዊት፦

<<በኛ ኮንዲሽን በኛ ተርም እኛ በምንፈልገው መንገድ አዲስ ሥርዓት እንመሰርታለን።>>

ቴድሮስ ጸጋየ፡ ይህንን አስመልክቶ ለልደቱ እንዲህ ይለዋል፡

ይሄ ብዙ ተዋንያን ላሉት አገር ብዙ ሕልም ላሉት አገር፤ ይህ በጎ መልዕክት ነው ወይ? የአጋርነት መልዕክት ነው ወይ? የመተባባር መልዕክት ነው ወይ? ሲል ቴድሮስ ልደቱን በተለመደው መመጻደቁ ይጠይቀዋል። መመጻደቅ ስል ግራ እንዳይገባችሁካሁን በፊት የቴድሮስ ንግግር የአጋርነት መልዕክት አስተላላፊ ከነበረ (ካሁን ጦርነቱን አስመልከቶ የቅርብ ገዜ ንግግሮቹ ማለቴ ነው) እስኪ ቴድሮስ ካሁን በፊት ስለ እሚንገበገብለት ኤፍእያለ የሚጠራው ወያኔ የሚመራውየትግሬ ጦርና ስለ አማራ ሕዝብየተናገራቸው ንግግሮቹ የጋራ አብሮነት አስተሳሳሪና አስማሚና ተቀባይነት ያለው ንግግር ከሆነ እስኪ ላስታውሳችሁ፡

 እንዲ ል፡-

<< የሕልውና አደጋ ያለበት ሕዝብ፤ አማራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያልሞተበት ቦታ የለም፤ (ነገር ግን) እንዴት ግፍ መሮኛል፤ ከዚህ ግፍ መውጣት እፈልጋለሁ የሚል ሕዝብ እንዴት ይህንን ይፈጽማል? እንዴት ለሌላው አደጋ ሊሆን ይችላል? ተከዜን እያሻገረ ይጥላል? ችግር አለብኝ የሚል ሕዝብ፤እንዴት የተገፋን የትግራይን ሕዝብ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ይጨቁናል፤ ወዘተ….” ይላል (ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ

የአማራ ሕዝብ የተገፋን የትግራይ ሕዝብጊዜ አገኘሁብሎ ግፍ ፈጽሞበታልሲል አማራውን በግልጽ በትግራይ ሕዝብ የዘር ማጥፋት ፈጽሟል ፤አማራለሌላ ሕዝብ አደጋ የሆነ ሕዝብ ነውሲል ሲከስ የነበረ ነው: (ቴድሮስ በቻ ሳይሆን አማራ ጋር ጋብቻ እንዳትፈጽሙ የተጋባችሁም፤የወለዳችሁም ካላችሁ ተፋቱ ሲል የቀሰቀሰ የትግሬው "ካቡጋ አሉላ ሰለሞንም" የቴድሮስን ውንጀላ በተመሳሳይ መልኩ ማርያማዊት ከተባለችወያኔበምታዘጋጀው ሚዲያ ጋር ቀርቦ ከልደቱ አያሌው ጋር ሰሞኑን ባደረገው ውይይት ሲደግመው ሰምተናል (ምንም እንኳልደቱ አያሌውአሉላ ሰለሞን ስለ አማራ የተናገረውንየተፋቱ አትጋቡንግግሩ በሚገርም ሁኔታ ሊያነሳለት ባይፈልግም)  

እስኪ ይህንን የቴድሮስ ጸጋዬ ንግግርስ ስለ አብሮነት የሚያስማማ ንግግር ነው ወይ ብላችሁ ተወያዩበት (አሁን እርሱ በሻለቃ ዳዊት እንደሚመጻደቅበት ከሆነ ማለት ነው። ሰው መጀመሪያ ራሱን መፈተሽ አለበት)

ምን ይሄ ብቻ ከየገጠሩና ጎዳናው እየታፈሰ በድህነትም በምንም ተሰቃይቶ ወደ ውትድርና የተመለመለ ምስኪን ወታደር ትግራይ ውስጥ ተመድቦሰሜን ዕዝ ተሰማርቶእያለበዘር ማጥፋት እልቂት (ጀነሳይድ) የተፈጸመበት ወታደርከመንግሥት መመሪያ ውጭ ግድያን የፈጸሙ ሴት የደፈሩ ስለተገኙ ሁሉንም ወታደሮች ጠቅልሎ መጨፍጨፍ አለባቸው የሚል ሰው ነው።  ቴድሮስ ስለይህንን ምስኪን ሰራዊት እንዲህ ያለበትን ላስታውሳችሁ፤-

እምሽክ ብሎ ደቅቆ ተዋርዶ እስኪበቃውመቀጥቀጡእጅግ ደስ ብሎኛል! ረክቻለሁ! እፎይታ ነው! ይህ ሠራዊት ፈርሶየትግራይ ጦር /..ኤፍየአገር መካለከያነቱን መያዝ አለበት። አገር መከላከያ ተብሎ ሊጠራ የሚገባው የአገሪቱ ሕገ መንግስት ያስቀመጣቸውን ወሰኖችን (ክልሎች) የሚያስከብርና የአገሪቱ ልዓላዊነትን የሚያስከብር ኤፍነው።እንደኔ እንደኔ መከላከያ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ብቸኛ ሃይል ኤፍነው ባይ ነኝ።>>

ሲል የሰሜን ዕዝን የጨፈጨፈ አደገኛ ሚሊሺያና ሠራዊት (በዚህ ዙርያ የተጻፉ መጻሕፍትን ተመልከቱ) ለግንጠላ የታገለውናእያባረርክ በለው ያንን ሞኝ አማራእያለ እየጨፈረ የተዋጋየሰከረ የትግራይ የአፓርታይድ አቀንቃኞች የሚመሩት ሠራዊትበዚያው መልኩ የነገረን ቴድሮስ አሁን ስለ ሻለቃ ንግግር <“ለአብሮነትንአያሻግርም”> ጠንቅ ነው ሲል መመጻደቁ ልክ ነው ወይ? እራሱስ ይቀርታስ መጠየቅ አልነበረበትም ወይ? የአማራ ሕዝብ ጊዜ አገኘሁ ብሎ የትግራይን ሕዝብ ተከዜን አሻግሮ የጣለ ለሌላው አደጋ ነውሲለን የነበረ ቴድሮሰ አሁን በሻለቃው ማትኮር ሚዛን የሳተ ኣይሆንም ወይ?

አሁን ወደ ልደቱ ልውሰዳችሁ፡

ቴድሮስ ጸጋዬ በሻለቃው ንግግር ሃሳብ እንዲሰጥበት ከላይ ያደመጥነውን የሻለቃው ንግግር ልደቱ አያሌው እንዲህ ይላል፡

<< አሁን ያቀረብከው የሻለቃ ዳዊት ጉዳይ ተንቆ ተድበስብሶ የሚታለፍ ጉዳይ አይደደለም።…..እኔ አማራ ነኝ እሳቸው የተናገሩት ብምንም ተአምር አማራን ሕዝብ አይወክልም።ንግግራቸው የአማራን ሕዝብ መገለጫ ተደርጎ የሚወስዱ ሃይሎች ትክክል አይደሉም። በሌላ በኩል ደግሞ እሳቸው የተናገሩትን በመደባበቅ ለማለፍ የሚደረግ ሙከራ ደግሞ በጣም የተሳሳተ ነው።ይሄ ደግሞ የሕዝቡን ትግል ዋጋ የሚያስከፍል ነው።እንዲኮላሽ ማድረግ ነው።እነዘህ ሁለት ነገሮች በሚዛን ማየት አለብን።አሁን እየተደረገ ያለው የሕልውና ጥያቄ እንጂ የሥልጣን ጥያቄ አይደለም፡ ሆኖም ከትግሉ በኋላ አማራ እንደ ማንኛውም ሕዝብ የሥልጣን ተጋሪ ነው፤ እዚህ ላይ ጥያቄ የለም።አገሪቷ በኔ ስሪትዲፋይን፡ ያደረግኳት እኔ ነኝ፤እኔ ብቻየን ነኝ የፈጠርኳት፤ ብሎ ሕዝቡ አያምንም' ያለፉት ሁሉም ነገሥታቶች የኔ ስርዓቶች ናቸው ብሎ አያምንም። የቀድሞ ስርዓቶች ሁሉ ሲበዘብዙት ሲጨቁኑት የነበሩ ናቸው።ጨቁነውኛል ብሎ የሚያምን ሕዝብ ነው።..”

እርግጥ ነው የአማራ ሕዝብ የነገድ ፖለቲካ ባልታወቀበት ስርዓት ነገሥታቶቼ አማራዎች ናቸው፤ስርዓቱም የኔ ነው የአማራ ነው ብሎ አያውቅም፤ ምክንያቱም የነገድ ፖለቲካ አያውቅም ነበር። ሆኖም፤ መሪዎቹ ሲወርዱ ሲዋረዱ ብዙዎቹ አማራዎች ወይንም የአማራ ዝርያ ነገዶች መሆናቸው ያውቃል። ስለጨቆኑት ግን አማራዎች አይደሉም አይልም። ምክንያቱም አሜሪካ ያሉት ወይንም እንግሊዝ ያሉት መሪዎች ፈረንጆች/ነጮች የታችኛውን ክፍል ነጭ ድሃ ረግጠው በዝብዘው አኑረውታል። ግን ስለተጨቆኑ መሪዎቹ የነጭ ዝርያ መሆናቸውን አይክድም ስለተጮቆነ የመሪዎቹን ማንነት ሊክደው አይችልም። አጼ ዮሐንስም ቴድሮሰም፤ ምኒሊክም እንዲሁ…..ሲጨቁኑ ነገዳቸው ሊጥሉባቸው አይችሉም። አብይ አሕመድ ኦሮሞ ነኝ ብሎ ነግሮናል፡(አብይ የሌላ ነገድ ትውልድ አለው ብለው እስካላረጋገጡ ድረስ) እርሱ  የሚያስራቸው ኦሮሞ ተወላጅ እስረኞች ስላሰራቸውና ስለጨቆናቸውኦሮሞአይደለም ሊሉ አይችሉም ስለዚህ ልደቱ ሆይ መሪ ስለጨቆነ ነገዱ የኛ ኣይደለም ሊባል ከቶ አይቻልም።

……<< እሳቸውን በሃላፊነት ያስቀመጣቸው እርምጃ መውሰድ አለበት።የሳቸው አመለካከት የድርጅቱ/የሕዝቡ አመለካከት እንልሆነ ባደባባይ ውጥቶ ማመን ናገር አለበት ።ሰውየው ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ወይንም ከሓላፊነታቸው መነሳት አለባቸው።ስለዚህ ይህ ንግግር መወገዝ አለበት!>> (ልደቱ አያሌው)

እንደግዲህ፤ የሻለቃ ዳዊት ንግግር በአማራዎች ልሳን ባልተለመደ መልኩ ስለተናገሩ አነጋጋሪ ንግግር ሆኗል። ለምን የሚለው ስንመለከት የአማራ ፖለቲከኞች እንደተቀሩ ፖለቲከኞች ቀጥተኛ ንግግር ሳይሆን ተቅለሽላሽ ንግግሮችን መናገር አድማጮቻቸውን ስላስለመዱት እንዲህ ያለየፈጠጠ መስመርመናገራቸው ለስለስ ያሉ ንግግሮችን መስማት ሱስ አድረጎት የነበረው አድማጭ አስደንግጦታል። ምናልባትም ዘዴ የጎደለው አንደኛዋ የመጀመሪያዋ ሐረግ አነጋገር ዕርምት የሚያስፈልጋት ካልሆነ የሻለቃ ንግግር ብዙዎቹ ንግግራቸው እስከዚህ የሚያስጮህ አይደለም።  ተቀባይነት አለው የለውም በፖለቲከኞች የሰጥቶ መቀበል (የሚሉት) በድርድርና በስምምነት ወቅት የሚፈተሹ ናቸው።

ምክንያቴን ላስቀምጥ ልደቱና ቴድሮስ እየመረጡ ማስጠጋት እና እየመረጡ አውግዞ መገፍተር፤ ይቅርታ ጠይቅ የማለት አባዜ የለመዱበት ካልሆነ እራሳቸውንም ይቀርታ እልጠየቁም። ተመሳሳይ ወይንም የባሰ ንግግርና መስመር ያራመዱና እያራመዱ ያሉት የትግራይ ፖለቲከኞች እና ኦሮሞ ተገንጣዮች ሁሉ በልደቱ ዓይን ሲገለሉ ወይንም ይቅርታ ይጠይቁ ሲል ልደቱ ሰምተነው አናውቅም።

ይባስ ብሎኦላ” (Oromo Liberation Army) ብሎ ራሱን የሚጠራ ነብሰጡሮችን በካራ ቀድዶ የተጸነሰን ሽል/ጽንስ/ በሞተቺው እናት ጉያ የሚያስታቅፍ፤ ግፈኛ አራዊት እና ግብረሰዶምነት ወንድ ሬሳ ላይ የሚፈጽም፤ የአማራ ነብስ ገድሎ ስጋውን አርዶ የሚበላ የሰው ደም የሚጠጣ ጭራቃዊውሸኔ” (OLF) ሳይቀር በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ድርድሩ መጋበዝ እንጂ መገለልና መወገዝ የላባቸውም ሲል ልደቱ ተከራክሯል።

ይህ ብቻ ሳይሆን፤ በጸረ አማራነቱና ጸረ ኦርቶዶክስነቱ የታወቀው በተለያዩ የአገሪቱ ነገዶች ላይ የዘር ማጥፋትና (ጀነሳይድ) የፈጸመ የትግራይ ወያኔና ከእርሱ ያልተሻሉ የግንጠላ ፖለቲካ የሚያራምዱትን ትግራይ ውስጥ ያሉት ተገንጣይ ፓርቲዎች ሁሉ መገለልና መወገዝ ሳይሆን ከኛው ጋር ሆነው ወደ ትግሉ በጋራ መወያየት አለባቸው ፤መብታቸው ነው፤ መገለል የለባቸውም የሚለን ልደቱ አያሌው፤ ዛሬ በሻለቃው ደርሶመወገዝና ከፖለቲካው መድረክ መገለልአለባቸው ይላል። እንዲህ ዓይነት አግላይ (ባያስ) ይዞ መጮሁ ተመጻዳቂነት ብቻ ሳይሆን እየመረጠ ወደ ፖለቲካው ድርድር ጥሪ እያደረገ የሚያቅፍና እየመረጠ ይቅርታ ጠይቅ ካልሆነ ከፖለቲካ መገለል አለበት ብሎ የሚያገልል አግላይ ፖለቲከኛ ነው ብየ ልደቱን ብከራከር እስኪ ችግሩን ንገሩኝ።

መጀመሪያ ነገር ልደቱ እራሱ ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ምክንያቴን ልግለጽ።

ልደቱ አማራ የሚባል ነገድ መኖሩን ለመሆኑ ያምናል? የሚል ብጠይቃችሁ ስለ አማራ የተናገረው ታውቁ ይሆን?

ልደቱ ስለ አማራ እንዲህ ይላል።

<<አማራ ማለት ክርስትያን ማለት ነው። ኦሮሞ ሆነህ ክርስትያን ከሆንክ አማራ ነው የምትባለው።ትግሬ ሆነህ ክርስትያን ከሆንክ አማራ ነው የምትባለው።አማራነት የሃይማኖት መገለጫ እንጂ የሌላ መገለጫ አይደለም።እኔ ተወልጄ ባደግኩበት አካባቢ አማራ ማለት ክርስትያን ማለት ነው። (ልደቱ አያሌው)

አማራ የኦርቶዶክስ ክርስትያን መገለጫነት እንጂ አማራ የሚባል ሕዝብ የነገድ፤መገለጫ አይደለም እያለ ሲቀሰቀስ የነበረው ፖለቲከኛው ልደቱዛሬ በማናውቀው ምክንያት’ “እኔ አማራ ነኝ ሲል እየሰማነው ነው እኔ አማራ ነኝ ሲል እኔ ክርስትያን ነኝ ማለቱ ነው ወይስ አምኖበት አማራ የተባለ ሕዝብ ስላ ነውየትግሬ ማሕበረሰብ አብዛኛው ክርሰትያን ነው፡ ግን የትግራይ ክርሰትያን አማኝ “አማራ” ነው የሚል ስያሜ መስማቴ የመጀመሪያ ጆሮየ ከልደቱ ነው።

ልደቱ በትርጉም ላይ ተሳስቼ ነበር የሚል ከሆነስ ትግሬ፤ጉራጌ ፤ኦሮሞ፤ ወላይታየሚባል ሕዝብ እንጂአማራ የሚባል ሕዝብ የለም አልኖረምም እንዲህ የሚባል መጠርያ ያለው ሕዝብ አላወቅምእንዳለው ሁሉ እናሻለቃ ዳዊትንይቅርታ ጠይቅ ብሎ እንደተመጻደቀው ሁሉ ልደቱ የአማራን ሕዝብ ይቅርታ ለምን አልጠየቀም? ወይንስ ምብሎ የሆነውን ንግግር የመቀበል ልምድ የያዘው አማራው ፈጠን ብሎ ቆፍጠን ብሎ ልክ እንደ መስፍን ወልደማርያም ልደቱን ተጋፍጦ ይቅርታ ጠይቅ ስላላለውአይታውቅብኝ ጠያቂ የለምበሚል እሳቤ ይሆን?

ለነገሩ ሊቀ ሊቃውንቱ የታሪክና የግዕዝ ሊቅ አለቃ አያሌው 1914 . አስመራ ውስጥ የታተመውየኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክበሚል ታሪካዊ መፅሐፋቸው ስለ አማራ እንዲህ ይላሉ፦

<<አማርኛ እና አማራ በዘመነ አጼ ይኩኖ ኣምላክ ዘመን የተከሰተ ነው የሚሉ ሞኞች አሉ። አማርኛ ቋንቋ እንኳ ብንመለከት ዘመነአመተ ምሕረትሳይሆን ከዚያ በፊትበአመተ ዓለም ዘመንየነበረ ነው። የአክሱም ነገሥታት ስም እንኳ ብትመለከቱ ንጉሥ ነጋሽ፤ንጉሥ አግባ፤ ንጉሥ ወረደ፤ ንጉሥ ጉም፤ ንጉሥ አስጎምጉም፤ ንጉሥ ጎሽ፤ ንጉሥ አይዞር፤ ንጉሥ መራወዘተ የመሳሰሉ የነገሥታት ሥሞች አማርኛ የነበረ ጥንታዊ እንደሆነ ነው።

አማራ ከግዕዝ ፊደል አጠቃቀም ያከለባቸውሸ፤ ጀ፤ ጨ፤ኘ…” ፊደሎች የራሱ ናቸው። እነዚህ ፊደሎች ግዕዝ ውስጥ አይገኙም። …. እያሉ ሲነግሩን

ልደቱ ወደ እሚነግረን ስለ አማራ እና እስላም ኦሮሞ ስለ ትግሬ ወዘተንግግሩን አለቃ ታየ የሚነግሩንን ስለ አማራ ማንንት ትንታኔአቸውን እንመልከት፡

<< ጥንትም አማሮች ክርስትያኖች ናቸው የነበሩ። ስለዚህ Oromo ወይም እስላም ክርስትና ሲነሳ አማራ ሆነ ይባላል። ባገሩ ልማድም አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋራ ሲጣላ አንተና እኔ እስላም እና አማራ ነን ይላል።ይህም አንተ እና እኔ እንደ ክርስትያን እና እንደ እስላም በሃይማኖት በንብረት አንድነት የሌለን ነን ማለት ነው።>> ይላሉ 1914 . የታተመው መጽሐፋቸው።

ስለዚህ ልደቱ አማራ ማለት ክርስትያን ማለት እንጂ ምንም ማለት አይደለም የሚለው ሃሰተኛ ትርጓሜ አለቃ ታየጥንትም አማሮችመኖራቸው፤ ጥንትም ክርስትያኖችመኖራቸውን እንጂ አማራ የለም አላሉም። የአለቃ ታየባገሩ ልማድምየምትለዋን አነጋጋር ስትመለከቱ አገሬው በተለምዶ አማራ ክርስትያን ስለሆነ እስላም ወይንም Oromo ክርስትና ሲነሳአማራሆነ ይላሉ። አማራ ነገድ እንጂ የሕዝብ መጠሪያ እንጂ የሃይማኖት መጠሪያ አይደለም። ልደቱ ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት፤ ግን አልሰማንም። ሻለቃው ላይ ደርሶ ግን ይቅርታ ይጠይቁ መወገዝ አለባቸው በይፋ እያለ ይመጻደቃል።

 ልደቱም ሆነ ቴድሮስ ጸጋዬ ማንኛቸውንም የፖለቲካ እይታ ያለውወያኔም ኦላም/ ኤል ኤፍ” (የፈለገው መስመር አራማጅ ይሁን ልደቱ ነው እንዲህ የሚለው) ከፖለቲካው ድርድር መገለልና መወገዝ የለበትም ይላል።እንዲህ የሚል ምነት ካለው ልደቱሻለቃ ብቻቸውን ይቅርታ የሚጠይቁበት ምን ምክንያት የተለየ ስላላቸው ነው?” የሰው ሥጋ የሚበሉ ወንድ የሚደፍሩ፤ ነብሰ ጡር የሚገድሉይቅርታ ይጠይቁ ፤ከፖለቲካ ይገለሉ ያልተባሉእንዴት ሻለቃው ጋር ሲደርስ ልዩ ይቅርታ እንዲጠየቅ ተጠየቀ?

አስቀድሜ እንደጠቀስኩት የሻለቃው ንግግር እርማት ማድረግ ካለባቸው አንዲት ቃል ብቻ ናት አርሷም፡

<<ኢትዮጵያ የአማራ ነች>> የምትለዋ ሐረግ ቢያርሟት ጥሩ ነው፡ በተረፈ የሚከተለው ንግግራቸው ማለትም፤

 <<ኢትዮጵያ እዚህ አሁን ድረስ ያደረሳት አማራ ነው።>> የሚለው ንግግራቸው ትክክለኛ ክርክር ነው! (ሰፊ ስለሆነ በሌላ ቀን እመለሳለሁ)

በማስከተልም የሚከተለው ንግግር ያሉትን በተሳሰተ መልክ መተርጎም አያስፈልግም፡

<<ስለዚህ ለማን ነው የምንሰጠው ኢትዮጵያን?>>

ሲሉ ጠያቂዋአንፈልጋችሁም ሂዱ እኮ ነው ብለው እየገፉን ነውብላ ስትጠይቃቸው;

ሻለቃው ለልጅቷ መልስ

<<ስለዚህ ለማን ነው የምንሰጠው ኢትዮጵያን?>> ማለታቸው ምን ሕገ ወጥ ንግግር አለው? ትክክል ነው። ሰዎች እየቆራረጡ እንደሚመቻቸው እያደረጉ ከበሮ መምታት አያስፈልግም።

በማስከተልም ለልጅቷ እንደሚከተለው አስረግጠው መልስ ሰጥተዋታል፡

<<ኢትዮጵያ እኮ የኛ ነች! እኛ ነን እዚህ ያደረስናት ታሪካችን ባህላችንሰንተርማዕከል ሆነን እዚህ ድረስ ያመጣናት ኢትዮጵያ እኛ ነን።>> ንግግራቸው ችግር የለውም። ኢትዮጵያ የኛ ነች ማለት እንደ ተረጓሚው ሊሄድ ይችላል፤ ግን ቀና አስተያቱ ስንመለከት እኛ ነን እዚህ ድረስ ያደረስናት <<ሰንተር፤ ማዕከል ሆነን እዚህ ድረስ ያመጣናት ኢትዮጵያ እኛ ነን።>> ልክ ነው።

አንድ ሕዝብ ማዕከል እኔ ነበርኩ ሲልአልነበርክምብለህ በክርክር ልትሟገት ትችላለህ። ሁሌም ከትግሬዎች ጋር የምናደርገው ክርክር ነው። አዲስ አይደለም።

ኮር/ኮርድ (አስኳል) ማእከል ማለት ነው? በሌላ አነጋጋርአከርካሪማለት ነው ፈረንጆች (ኮርድ/spinal cord) የሚሉት።

የአንድ አገር ስሪት በዋና ዋና አስተዋጽኦ ያደረገ መሪ ተዋናይ ሆኖ በማዕከላዊ አካልነት፣ በጣም አስፈላጊ ክንውኖችን መርቶ ብቅ ያለ ሕዝብ የግድ ይኖራል። ተፈጠሮአዊ ነው።ነጥረው የሚወጡ ተሸላሚ ማሕበረሰብ ወይንም የንግድ፤ወይንም የሃገር ውከላ ሽልማቶች አሉ። እነዚህ የሚታዩ ምጥቀት ያሳዩ ክፍሎች የዓለም ፤የአገር፤ የክፍለሃገር፤ የነገድ አስኳሎች አሉ። በኢትዮጵስሪት ውስጥ ጎልቶ የሚታይ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አማራና ኦርቶዶክስ ክርስትያን የአገሪቱ ዋና አከርካሪዋ ክፍሎች ናቸው።

የሰው አካል በአከርካሪው ነው የሚንቀሳቀሰው፤የሚራመደውና የሚሰራው።ወያኔዎችና የጣሊያን ፋሺስቶች ኢትዮጵያን የተሸከማትንአከርካሪዋንሰበርነው፤ ብለው ሲሉ ማንን ይመስላችኋል? አማራና ኦርቶዶክስ! አደለም እንዴ?!!

እነዚህ ሁለቱ ክፍሎች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ያላቸው ናቸው። አለቃ ታየ ከላይ የተናገሩት አስታውሱ። በማንኛው የታሪክ ሂደት እነዚህ ሁለት ክፍሎች ሳይነጣጠሉ የአገሪቱ ወገብና ትከሻ (አከርካሪ) ሆነው በብዙ ረገዶች አገር እንድትሆን መርተው እዚህ ድረስ አድርሰዋታል። ሕዝቡ የሰው ልጅ ግንኙነት እንዲኖሮው ሃይማኖትና ቋንቋ ሰጥተው ከጫፍ እስከ ጫፍ እንዲገበያይ አድርገውታል። ለዚህ ዋና ተዋናዩ አማራና ኦርቶዶክስ ናቸው።

 ጣሊያኖችም ወያኔዎችም (ኦነጎችም) አገር ለማፍረስ ሲፈልጉ እነዚህ ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መስበር ነበረባቸውና ለመስበር ሞክረው እስካሁን ድረስ ግማሹ ተሳክቶላቸዋል። ሁለቱ ካልተሰበሩ ግን ኢትዮጵያ የነፃነት አርማ ሆኖ ትቀጥላለች። ይህ አባባሌ አሳንሰው የሚያዩ ግብዞች አሉ፤ ግን ሃቁ እኔ የምለው ነው!

 ያለ ምንም መደባባቅ የአገሪቱ ዋና ዋናዎቹ ጡንቻዎች ሁለቱ ናቸው።ሁለቱም አከርካሪዎች ከተሰበሩ (አሁን ለማድረግ እየተሞከረ እንዳለው) ከባድ መናጋት ያመጣል። ግዝገዛ እየተከናወነባቸው ስለሆነ አገሪቱ እይታ በማታውቀው መናጋት ውስጥ አሁን ገብታለች። ምክያቱም አማራና ኦርቶዶክስ የሚገባቸው ዕውቅና ተሰጥቶአቸው የሚገባቸው ቦታ ተሰጥቶአቸው አክብሮት ካልተሰጣቸው አክርካሪ ክፍሎቿ ስለሆኑ አከላትዋ ዘጭ ብሎ መውደቁ አይቀሬ ነው። ያኔ በአከርካሪ ዙርያ ያሉት ጡንቻዎች ብቻቸውን ለመቆም ቢፈራገጡም መንፈራገጣቸው ከንቱ ልፋት ይሆናል (ፓራላይዝ ይሆናሉ)

ስለዚህ የሻለቃ ዳዊት ንግግር ተጋንኖ መቅረብ አያስፈልግም። ከባህላዊ ተጓዳኝ ባህሪያት ጋር ነገዶች (ጎሳዎች) ቢለያዩም ስልጡን ማዕከል (ነገድ/ሃይማኖት አለ) ሌሎችን በማስተጋብር ባሕሪ የጋራ (ሁሉም የሚገበያይበት መነጋጋሪያ) ቋንቋ፣ ባሕሪ፤ ሞራል እና የመሳሉ ዕሴቶች ለሌሎች በማጋርት አስኳል ሆኖ የሚጫወትእንደሚዘረጋ ባሕርማሕበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሯል አሁንም አለ።ባንድ ባህር መሃል ላይ ውስጥ ድንጋይ ስትወረውር ንዝረቱ በመላው የባሕሩ መልክኣ (እይታ) ሲዘረጋና ሲንቀሳቀስ ታያለህ። አማራውና ኦርተዶክሱ በመላው አገሪቱ አካላትና ምድር ይናጋል። አይተነዋል። የጋራ አገር ታሪክን በሚጋራ ሁኔታ መጓዝ ሲባል ሁሉም ነገድ አስተዋጽኦ አድርጓል ቢባልም፤ የጋራ ጉዞውን ማዕከል ሆኖ ሁሉንም ያገናኘና ያስተባባረ ተዋናይ አስኳልአልነበርምወይንምየለምየሚል ክሕደት ውስጥ መግባት ንድያኮር ስቴትየሚባለው የፖለቲካ፤ የማሕበራዊና የምጣኔ ሓብት ግንባታና አስተዋጽኦ ያለማወቅ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ለማስተካከል የምንጥረው አገራዊ ስሪት መልካም መርህ አይሆንም።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

 

 

 

 

No comments: