የነቀዘው አዲስ አበቤስ መች ይሆን የሚነሳው?
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay 8/22/23
ሰላም ለሁላቸሁ ይሁን።
እህልና ሰው አንድ ነው። እንስሳ ብቻ ነው
በባሕሪ ስለሚለይ የማይነቅዝና የማይበላሽ። እህል ሲበላሽ በሰበሰ ወይንም ነቀዘ
ዛሬ ያላንዳች መሸፋፈን ልክ ካሁን 28
ዓመት በፊት ይህ ሕብረተሰብ የተነበረከከ ፤ሽንፈት የተቀበለ ሕበረተሰብ ነው፡ ብዬ ስል ‘ሕብረተሰብ እየዘለፍክ ነው’ ተብዬ እንደተጨኾብኝ
ሁሉ ዛሬም በድጋሚ እንድትጮኹብኝ ለመጋበዝ ሳይሆን ላመስታወስ ነው፡ (የምትጮሁብኝ ወቅት ወደ ኋላ ቀርቶ እነሆ እናንተ ያኔ ስለው ወደ ነበረው የትጥቅ ትግል ገብታችኋልና ያ ጩኸት ታሪክ ሆኗል)።
ትዝ ይላችሁ እንደሆነ በግልጽ
አማርኛ በውጭ ያለውም ሆነ በውስጥ ያለው ሕብረተሰባችን ከመበስበስ ባሻገር እርከኑን ተሻግሮ
እንግሊዞቹ እንደሚሉት “ሯትን/ሮትን” (Rotten) እንደሚሉት በስብሶ/ነቅዞ/ረጥቦ/ የጠላት ባንዴራ እየተሰሸከመ በየአደባባዩ የንከላወት እንደነበር ታስታውሳላችሁ (የቅርብ ትዝታ ነውና ‘ብዙዎቻችሁ የነተካፈላችሁበት ነበርና ‘ነበራችሁ
ልብል’ ባይከፋችሁ)። እኛ ትግሬዎች “እጋል” “የገማ/የጠነባ” እንደምንለው ዓይነት ነበር ወቅቱ።
ውሃ እንዲገማ የሚያደርገው ምንድነው? ብዙ፤ ብዙ ምክንያት አለው።
ሕብረተሰብም እንዲሁ ይበሰብሳል። ሕብረተሰብ ሲበሰብስ አፍንጫን አይደለም የሚሰነፍጠው የታዛቢን ዓይንና
ሕሊናን ጭምር ያሸማቅቃል።
ሕብረተሰብ መበስበሱን የምንፈትሽባቸው
መንገዶች ልክ እንደ እንቁላል በሃይለኛ የብርሃን/የጸሃይ ጨረር ውስጥ እንደምንፈትሸው ሕብረተሰብም በእዛው የመፈተሻ ብርሃን
ውስጥ ገብቶ ካልተፈተሸ መበስበሱን ተሎ አያስታውቅም። እናቶቻችን እንቁላል ሲገዙ “ማገሉን” (መበስበሱን/እርግዝና ይዞም
እንደሆነ ‘ፕላዝማው/ውሃው’ (የጫጩቱ እንግዴ ልጅ) አለማገሉን/አለመበላሸቱን/ ለማወቅ እያንዳንዱ እንቁላል ወደ ዓይናቸው
በማስጠጋት ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ወደ ጸሐይዋ አቅጣጫ በማነጣጠር መሃል ያለው የውሃው ንጣት ወይንም
ጥቁረት በመመልከት ‘ብልሹ/የበሰበሰ’ እንቁላል ወይንም ‘ጤነኛ’ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ወይንም ወደ ጆሮ
አስጠግቶ እንቁላሉን በማነቃነቅ (ሼክ በማድረግ) ከውስጥ ያለው ውሃ ካልተነቃነቀ ረግቷል እና የበሰበሰ ነው
ማለት ነው (እናቴ እንዲያ ነበር የምታውቀው)። እንደዛ ካላደረጉ እንቁላል ከላይ ንጣቱን ብቻ በማየት መበስበሱን
አለመበስበሱን ማወቅ አይቻልም።
የተበላሸ እንቁላል ሲሰብሩት በጣም ይገማል።
ውሃም እንቁላልም ሲገማ ለሰው ልጆች ለምግብነት አይፈለጉትም። በዛው ትይዩ ሕብረተሰብ ሲነቅዝም ሂደቱና ባሕሪው በመለወጥ ራሱን
ወደ ሞት ሂደት ያሸጋግራል። ራሱን ያበሰብሳል። ራሱን ያበሰበሰ ሕብረተሰብ ለመምራት እልክ አስጨራሽና አስተዋይ መሪ እና
ታጋዮች ይፈልጋል።
ሕብረተሰብ ሲበሰብስ ‘ተንቀሳቃሽ ግኡዝ’
ስለሚሆን ሲሰለብ/ሲበላሽ/ አይታወቀውም። የበሰበሱ መሪዎች የበሰበሰውን ሕብረተሰብ ለመስለብ እንዲያመቻቸው ሕብረተሰቡን
ማበስበስ አለባቸው። ያንን ካላደረጉ “የሚጫኝ አህያ አይሆንላቸውም”።ልክ ግምበኞች/የሕንጻ መሃንዲሶች አልፈርስም ብሎ ‘ነክሶ’
ጠንክሮ የየዘ መሰረት “ውሃ” እያፈሰሱ፤ እንዲረጥብ እያለሳለሱ እንደሚያፈርሱት ጠንካራ መሰረት ጠንካራ
ሕብረተሰብንም ለማበስበስ የተለያዩ ዘዴዎች በማስተዋወቅ እንደ ዋለሃ (ዋልካ) ተፍረክርኮ “ሊጥ
ሆኖ እስከሚታጠፍላቸው ድረስ” ሃይለኛ ስራ ይሰራሉ። የሚታጠፍ ነገር “ጥንካሬ
ስለሌለው” “ሃይል” ያጣል።የሚታጠፍ ሰው ስብእናውና ሞራሉ ደካማ ስለሆነ የበታችነት ስሜት ተሰምቶት ልጠፍህ
ለሚለው ክፍል ሁሉ በቀላሉ ይታጠፍለታል።ተስፋ የሚባል ትርጉም የገባው ከሆነም፤ ምህረቱና ተስፋው በዛው ክፍል ይጥላል።ያችን
የተነጠቀውን ተስፋውና ሰብእናው ለማግኘት በራሱ መቆም ስላልቻለ ሰላቢዎች ወደ ጠመዘዙት ለመጠምዘዝ ምቹ ሆኖ ይገኛል።አሁን
የቀሩን የተበላሹ ወገኖቻችን አብይን እያገለገሉበት ያለውን ባሕሪ በዚህ ዘዴ ነው።
ስለሆነ ማንኛውም “ገምቢ እና ቤት አጣሪ” የጥበቡ ክረዲቢሊቲው (ንጣቱን/አስተማማኝነቱን ኩዋሊቲው)
ሳጣያጣራ “ልገንባህ/ልጠርህ” ለሚለው የፖለቲካ ግምበኛ ሁሉ በሚሰጠው የግምባታ ፕላን “ፈቃደኛነቱን” ይገልጽ
ነበር። እሺታ እንጂ መደራደርና መርምሮ መግባት ተስፋውን የሚያጨለምበትና የሚያራዝምበት ስለሚመስለው “የተሎ ተሎ ቤት’ ግምባታ
ውስጥ ገብቶ ነበር።ዛሬ ቁጭቴንም ንዴቴንም እየገለጽኩ ስለሆነ እንዳትቀየሙኝ እጠይቃለሁ። አሁን ያለው የጀግንነት ሥራ ደስታ
ቢሰጠኝም ዘግይቶ መምጣቱ ነው እየቆጨኝ ያለው!
ወያነ ትግራይና ኦሮሞ ኦፒዲኦ የዛሬው “ኦሮሙማ/ብልጽግና ፓር) በባእዳን አጀንዳ እየታጀቡ በጣምራ የሕዝባችን መሰረቶች የሆኑት “ድምበሮቻችን ፤ ወደቦቻችን ፤ሰንደቃላመችን ፤ ባሕል ፤ሃይማኖት፤ ብሄራዊ ቋንቋ፤ይሉኝታና ሉአላዊ ፍቅር”(ማሕበራዊ ተቋማት የሚባሉ) መሰረታቸው አነቃንቆ እንዲፍረከረኩ አደረጉ። የተማረው ግብዝና ያልተማረው ግብዝ ሁለቱም ክፍሎች “ኢትዮጵያን” የሚመለከቱበት ዓይናቸው ሸፍኖ፤ የምዕራቡን ዓለም ግብረገብ (ዌስተርን ማስ ካልቸር) ተከታይ እንዲሆን አድረጓቸዋል። ከአገር ሉዓላዊነት ይልቅ “ቅዠታዊ ዲሞክራሲ” በማስቀደም ሉኣላዊነት ዋጋ ቢስ በማድረግ ዛሬም እያጃጇሉዋችሁ ነው።
አሁንም ብዙውን ኢትዮጵያውያን ልሂቃን
ከመግመማታቸው አልተላቀቁም።አብሮ ለ32 አመት ያበሰበሱት ሕዝብ በተለይ አዲስ አበቤው አሁንም ብዙ ሺህ አማራና ሌላው ብሔረሰብ
ዜጋ እያተፈሰ ሲታጎርና ሲደበደብ ምንም እንዳላየ “ዳንኪራ እየመታ ነው” (ልክ እንደ ቀይ ሽብሩ ዘመን)።
እኔ ከተወለድኩበት የትግራይ ማሕበረሰብም ቢሆን ከነከሱት የፋሺሰት ጅቦች ጋር አብሮ መኖር ለምዶታል።ከመልመዱ የተነሳ
የመውደድ አባዜው ዛሬም የተጠናወተው ይመስላል። ይመስላል ሳይሆን ኩፉኛ ለ47 አመት ድፍን “ፈጣጣ ፍቅር
ዛሬም አልለቀቀውም (ኢትዮጵያ የምታቀርብለትን ፍጆታ እየተጠቀመም ቢሆን “የሃገረ ትግራይ ምስረታው ቅዠት አልለቀቀውም)።ስለ
“ጠነቡት” የትግራይ ምሁራኖች ማውሳት ቆሽት ማሳረር ነው።
የትግራይ ነገር ሳነሳ “ሐረር” ውስጥ ማታ ማታ ሲመሽ ጅቦች የሚቀልቡ ፡አድቨንቸሪስቶች” (ጀብደኞች) አሉ። ይህ ጉደኛ ትዕይንት የወያኔ ዓይነት ጅቦች ዓይነት ታሪክ ይመሳሰልብኛል። ዛሬ ዛሬ ከመቸውም በበለጠ የጐብኚዎች መስህብ እየሆነ በካሜራ እየተቀረጸ መጥቷል። ቀላቢውም ሆነ ተመልካቹ የሳቱት ነገር ቢኖር ጅቦቹ የቀላቢውም ሆነ የተመልካቹ ህይወት “ቀሳፊዎች” እና ተቀናቃኞች መሆናቸው የመገንዘብ ሕሊናቸው “በጊዜያዊ የመጠጋጋት የጀብደኝነት እርካታ” ውስጥ ገብቶ ስለተማረከ፡ ከመጋቢያቸው እያሽካኩ በጓደኝነት ባሕሪ የሚመገቡት “ጅቦች” ቀላቢ ሲያጡ “የገዛ ቀላቢያቸውን እንደሚበሉት ቀላቢዎቹ የተረዱት አይመስሉም።
ጅቦቹ ከቀላቢያቸው የሚፈልጉት ነገር ቢኖር ‘መመገብ’ ነው። ቀላቢዎቹ ከጅቦቹ የሚፈልጉት ነገር ደግሞ “መናከሳችሁን” አቁሙ ነው። የመጠጋጋቱ የጨዋታው ትርጉም ሲመረመር ከዚህ ያለፈ አይሆንም። መጋቢዎቹ የዘነጉት ጉዳይ ሺ ሰንጋ ቢታረድላቸውም ልጆቻችንና ከብቶቻችንን መናከስና መብላታችሁን አቁሙ ስለተባሉ “ጅቦቹ” መናከሳቸውን ያቆማሉ ወይ?” ነው ጥያቄው።
የሁለቱ ፍጡራን ትካት (ኢንስቲንክት)
የጭምትነት ባሕሪ የጎደላቸው ስለሆኑ “ነካሹም” “ተነካሹም” የተፈጥሮ ባሕሪያቸው እንደማይገጥም እያወቁ ሁለቱም እየተጠጋጉ እና
“ፈራ ተባ” እያሉ በማያዛልቅ ጨዋታ ገብተው “የበይ እና የተበይ” የመገዳደል ጨዋታቸው እያሳመሩ ጅቦቹ ከጀብደኛ ቀላቢያቸው
አፍ ጥርስ ተነክሶ የተንጠለጠለላቸው ስጋ “ጠጋ” ብለው በመንጠቅ ይጎርሳሉ። ይህ አስገራሚ የገዳይና የተገዳይ ጀብደኛ
ጨዋታ በካሜራ ተቀርጾ ለዓለም ሕዝብ እየታየ ነው።የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ባሁኑ ሰዓት ሕግ የማያከብር ቡድን
ሥልጣን ላይ መኖሩን እያወቀ ሕብረተሱም አብሮ ሕግ አፍራሽ በመሆን የበሰበሰ እይታ ያለው ጎዳና በመጓዝ ድርድር ከማያውቅና
ከሚበላው አራዊት ጋር ተጠጋግቶ የበይና የተበይ የጨዋታ ሕግጋት እያሳመረለት ለሚበላው አራዊት ሲያሞግስና ሲያለቅስለት
እየታዘብን ነው ።
መለስ ዜናዊ ሲሞት በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን ያስጠሩ እና ያኮሩ የስፖርት ባለሞያዎች ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱለት፤ካንደባታቸው የተናገሩት ፍሬ ነገር ሲመዘን አገራቸውን ወክለው በዓለም መድረክ የላቀ ውጤት ሲያስመዘግቡ ሲስሟት የነበረቺው ሰንደቃላማችን እና የሃይማኖታችን ምሰሶ የሆነቺው ቅድሰት ማርያም ምስል ከጉያቸው እያወጡ ሲሳለሙ ምድሪቱን ተንበርክከው የሰገዱላት፤ሃይማኖት፤ ምድር እና ሰንደቅ ላይ መለስ ዜናዊ በኮሚኒስታዊ የፋሺስት አጀንዳው የፈጸመው ሕገ ወጥ ሥራ ከሕግ አኳያ የመመልከት አቅማቸው ደካማ መሆኑን ያሳያል።
እነ ደራርቱ
ወይንም መሰረት ደፋር ….የመሳሰሉ ሯጮች ሲሮጡ ሰንደቃላማ ይዞ አብሮ ልባቸው የሮጠው ውጭ አገር ያለው ኗሪ ግለሰቦቹን
ስለሚያውቃቸው ሆኖ ሳይሆን “ሰንደቃላማ እና አገር” ያስከብራሉ በሚል ነበር። ሆኖም ወያኔ ያሰራው ሰማያዊ የሰይጣኖች አምልኮት
ኮከብ ያለበት ሰንደቃላማ ካልሆነ ነባሩ እና ሕጋዊው ለዘመናት የቆየ የተውለበለበ ባለ ሦስት ቀለም ሰንደቃላማ ማውለብለብ “ሕገ
ወጥ” ነው ብሎ ላወጀው “ፋሺስት” መሪ “ሲቀሰፍ” ስቅስቅ ብለው
አልቅሰዋል። ስቅስ ብሎ ለፋሺሰት መሪ ማልቀስ፤ የሕገ ወጥ ቡድን ተባባሪ መሆን ነው።ሕብረተሰብ ሲበሰብስ ሕገ
ወጥ ተግባሮችን ሕግ ነው ብሎ ይቀበላል። ማሰብ ያቆማል። የበሰበሰ ሕብረተሰብ ወንጀለኞች በዘረጉለት ሃዲድ ስለሚጓዝ “ሞራል
ፕርንሲፕል” በመጣስ “ላገር ታማኝነትን” ያቆማል። ምልክት በሌለው ባጭበርባሪ ጎዳና የሚጓዝ ተጓዥ ለአደጋ እንደሚጋለጥ
ሁሉ፤ይህ ሕብረተሰብ ለከፋ የሞራል መበስበስ መጋለጡ ዛሬም አላቆመም።
ካነበብኩት አንድ
መጽሐፍ ውስጥ ከ1500 አመት በፊት የሮም መሪዎች በመበስበሳቸው ለታላቋ የሮም መንግሥት መበታተን ምክንያት እንደሆነ
አንብቤአለሁ። የበሰበሱ መሪዎች አገር ሲመሩ የበሰበሰ ሕበረተሰብ ያፈራሉ። አገር ባይፈርስም በውስጧ የታቀፈው ሕብረተሰብ
አቅፈውት ሲጓዙ የነበሩት ተቋማት (ሰትራክቸሮቹ) ስለሚፈርሱ የሕሊና መፍረስ ስለሚገጥመው ባስተሳሰቡ “መካን” እና “የበሰበሰ”
ማሕበረሰብ ይሆናል ማለት ነው።
ዛሬም የበሰበሰና የነቃ መሕበረሰብ ሚናው
እየለየ መጥጧል። ‘ፍትሕ’ ለሚጠይቁ ፋኖዎች ሲያናንቁት
የነበረው እነሆ ዛሬ አጥራቸው ውስጥ ብቅ ሲል ባንዳዎች ሌለቱንም ሆነ ቀትር መተኛት አልቻሉም። ወንበራቸው በፋኖ ተነጥቆ
ፋኖዎች ተቀምጠውበታል (እሰየው!!)። አሳምነው ጽጌ ምነው ብቅ ባልክና ፍሬሕን ባየህ!?
ትግሉ አብይ እስኪወገድ መቀጠል አለበት።
“እንቅስቃሴው” እንዳይጠለፍ ሕዝብ ነቅቶ መከታተል የዜጎች ግዴታ ነው እያልኩ ለአመታት የምጮኸዩኩበትን የትጥቅ ትግል አማራው ተግባራዊ
ማድረጉ ቅቤ አጠጥታችሁኛል።
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment