አብይ
አሕመድና
የኦሮሞዊው
ኢንተርሃሙዌው
ዱሩየ
ቡድን
የመቀናጀቱ
ግልጽነት
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian
Semay
8/18/23
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሕዝብን በጅምላ በመጨፍጨፍም ሆነ ከውጭ ጠላት ጋር አብሮ በማበር አገራቸውን የከዱ ባንዳዎች ታሪክ በየአይነታቸው መዝግቦአቸዋል።
የባንዳ ነገር ካነሳን ዘንድ፤ በኢትዮጵ ታሪክ የባንዳ ደረጃዎች ስንመለከት ምናልባትም በዓለም ታሪክ ውስጥ የአገሩን ሰንደቃላማ አውርዶ የወራሪ ጠላት ባንዴራ የሰቀለ መሪ ትግራይ ውስጥ ብቻ ነው (አብይ አሕመድና መለስ ዜናዊን እንዳሉ ለየት ባለ የክሕደት ደረጃ ሳንዘነጋ ማለት ነው) ። እኚህ ሰው ማን ናቸው? የአፄ ዮሐንስ 4ኛ የልጅ ልጅ የሆኑት ደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ ናቸው።
የአፄ ዮሐንስ 4ኛ የልጅ ልጅ የሆኑት የደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ ለየት ያለ የባንዳነት ታሪክ የዘገቡት አቶ ዘውዴ ረታን እጠቅሳለሁ (አሳጥሬ ነው የምጠቅሰው) ።
<<…. ደጃዝማቹ ለጣሊያን ካደሩ በኋላ በጣሊያኑ በዱቼና በንጉሥ ቪክቶርያ አማኑኤል ሹመት “ራስ” ከተባሉ በኋላ የጣሊያን ወራሪ ሃይል ዋና አዛዥ የነበረው የጄኔራል ዲ ቦኖ የጦሩ አመራር “አማካሪ” ሆኖው ሕዳር 8 ቀን 1935 ዓ.ም መቀሌ በጠላት እጅ ስትወድቅ ራስ ኃይለስላሴ ጉግሳ አርአያ የተሰጣቸውን የፋሺስት የጦር ልብስ ለብሰው በግንባር በመገኘት “በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቦታ የጣሊያንን ባንዴራ የሰቀሉ ራሳቸው ሆኑ” ። …….. በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዚያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም የሙሶሎኒ ጦር ዋና አዛዥ (ዲ ቦኖን የተካው) ማርሻል ባዶግሊዮ ድል አድራጊ ሆኖ በከፍተኛ አጀብ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሲገባ፤ ከክብር ተከታዮቹ ቀዳሚ ሆኖው የታዩት ኃይለስላሴ ጉግሳ ነበሩ።>> ገጽ 180 (የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግሥት (ዘውዴ ረታ)
ኢትዮጵያ ውስጥ በታሪክ ከፍተኛ ክሕደት የሰሩ በጥንት ዘመን የተከሰቱ ክፉ ባንዳዎች የኖሩ ቢሆንም የሳቸው ግን ዓይን ያወጣ ዓለም ውስጥ ያልተደረገ የጠላት ባንዴራን ሰቅሎ የገዛ አገሩን (ያውም የወላጅ ባታቸው አፄ ዮሐንስ ያውለበለብዋት የነበረቺውን ሰንደቅ ዓላማ) አርማ አውርዶ “አፈር ላይ የጣለ ዜጋ” ተሰምቶ አያውቅም። ልዩ የሚያደርገውም ይህ ድርጊት ነው።
ወደ ዛሬዎቹ ወደ እኛው ዘመነ ወያኔ/ትግሬዎች እና ወደ ዘመነ ኦሮሙማ /ኦሆዴድ ኦነጎች ብንመለከትም ከዚያኛው እኩል የሆነ ለጠላት ወግኖ ከጣለት ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ሠራዊት በመውጋትና ከነቤተሰቦቻቻው ወደ ጎዳና ተዳዳሪነትና ለማኝነት በመበተን ሆነ እንዲሁም የባሕር በርን ለጠላት መስጠትና ኢትዮጵያን ያለ ባሕር በር አስቀርቶ “በጠላቶች እጅ ልመና እንድትወድቅና እንድተከበብ” ፤ ለከበቡዋት አገሮች ዕቃ ለማስገባትና ለማስወጣት ግምቱ የሚያስቸግር ገንዘብ በመክፍል በምጣኔ እንድትደቅቅ ያደረገ ከትግሬው ደጃዝማቹ ባንዳነት እኩል ወይንም የባሰ የሃገር ክሕደት ለማየት በቅተናል። ክሕደቱ ጥንትም ዛሬም አልቆመም።
የወያኔ ትግሬዎችን ክሕደት ሁሉም ያወቀው ስለሆነ እዚህ ሳላነሳ የዛሬዎቹ አዳዲስ ተተኪዎቹ ተረኞቹ “ኦሮሞዎች” በዚህ 5 አመት ብቻ (ሌላውን የ27 አመት የታየው ወደ ኋላ ትተን ማለት ነው) ሰማዩም ምድሩም ያወቀው ስለሆነ ዝርዝር አልገባበትም። በአብይ አሕመድ ኦሮሙማ ፕላን 1፣ ፕላን 2፣
ፕላን 3 …እየተባለ እየተሰራ ያለው አማራ ላይ ያነጣጠረው ከወያኔዎች የቀጠለ የኢንተርሃሙዌው “ፕላን”
ቀስ እያለ ሲሰራ ቆይቶ እነ ሌንጮ እነ ዶ/ር
ዲማ ነገዎ እና አሰፋ ጃለታ የመሳሰሉ የኦሮሙማ አጀንዳ አቀንቃኞች እንደተናገሩት፤ እንዳቀዱትም እንደዛቱትም፤ በአብይ አሕመድ በኩል ተግባሪ በማድረግ አማራዎች ወደ አዲስ አባባ እንዳይገቡ፤ የገቡም ቀስ በቀስ ከተከበቡ በኋላ አሁን እየተለቀሙ እስር ቤትና በየት/ቤት ማጎርያ ህንጻዎች እየታጎሩ እንዳሉ የምታውቁት ነው።
ይህንንም ዕቅድ የቆየ በጥናት ሲጠናበት የነበረ ኦሮሙማዊ አጀንዳ ነው። ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ባለፈው ሰሞን በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ የተለጠፈው ጽሑፍ የነገረን፤ ይህ አሁን እየተደረገ ያለው አማራን ሰብስቦ እየለቀሙ ማጎር ቀደም ብለው ያቀዱት የኦሮሞ ፖሊተካ መሪዎች ናቸው። አዲስ አበባና አካባቢው ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች (‘ነፍጠኞች’) እየለቀምን ከሰበሰብናቸው በኋላ የመውጫ ኮሪደር (በር) ከፍተን ወደ አገራቸው “እንዲወጡ” እናደርጋለን ብለው በተለያዩ ሰነዶቻቸውና ንግግሮቻቸው ባስቀመጡት መሰረት መጨረሻ አዲስ አባባ እንዳይገቡና የገቡትም እየተለቀሙ ተሰብስበው እንዲወጡና “ኦሮሚያ” የተባለ አገር ለመመስረት እንዲያመቻቸው <<ወኪላቸው አብይ አሕመድ>> ይህንን በአዋጅ ተግባራዊ እያደረገው ይገኛል ። ይህንን ንግግር ያደረገውም አሁን በአብይ አሕመድ ፓርላማ አባል ሆኖ የጀርመን የፓርላማ አባላትን እያነጋገረ ፎቶውን እንድታዩት የለጠፍኩላችሁ <ዶ/ር
ዲማ ነገዎ> የተባለ እጅግ አደገኛ የኦሮሙማ ቄሮ የኢንተርሃሙዌ ቡድኖች ቀስቃሽና የኦነግ መሪ ነው።
ከሁለት አመት በፊት “ውጣልኝ!” የሚል የአብይ አሕመድ ኢንተርሃሙዌው የሙዚቃ ቡድን ቅስቀሳ በማድረግ ዓለም እያየው በዩ ቱብና በመሳሰሉት ተለጥፎ ብዙ “የኦሮሞ ኢንትርሃሙዌ ቄሮዎች” ቅስቀሳውን ተግባራዊ በማድረግ በበረሃም (አማራ ላይ የዘር ጭፍጨፋ በማድረግ) በከተማም ፖሊሱ ሳይቀር ካንገቱ የክርስትና ሃይማኖት ምልክት ያለው ኢትዮጵያዊ እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የያዘና የለበሰ ሰው እየነጠቁ እየደበደቡ እስርቤት በማስገባት ፤
ለቁጥር የሚያዳግት በሺዎቹ የተማረውና ያልተማረው አምሐራዊው ክፍልም ተሰብስቦ እስር ቤት ታጉሮ እየተሰቃየ ነው።
አብይ አሕመድ “ኦሮሙማዊው ኢንትርሃሙዌው አጀንዳ” ተግባራዊ ለማድረግም አዲስ አባባ ብቻ ሳይሆን የአማራ ከተሞችና ገጠሮች የጦር ቀጣና ሆነው ከዚህ አማራዎቹም እየተፈጸመባቸው የነበረው የ27
አመት ጭፍጨፋ ህያው ሆኖ እንደገና በመቀጠሉ የሞት ሽረት የጦርነት ፍልሚያ በማድረግ ላይ ናቸው። ድል ለነሱ እንዲሆን እመኛለሁ!!
በሚገርም ክስተት ደግሞ እየመከርናቸው “እባካችሁ ተው እያልናቸው” አብይ አሕመድን አምነው ብዙ አገልግሎት ሲሰጡት የነበሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ አፍረዋል። ሰውየው “ዊርድ” ነው። ወደ ሰውየው የተጠጋ ሁሉ ‘ይሟሽሻል፤ ይሰወራል፤ ከትግሉ ይጠፋል፤ ወይንም ግራ ይጋባል’። ለዚህም ‘የማታፍርባቸው መሪዎችና የማታፍርበት ሀገር ይስጥህ ወንድሜ’ ብሏል ነገሩ አስገርሞት ወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ።
<<አፄ አቢይ አህመድ ሥልጣን ከያዘባት ከዚያች ከዕለታት ሁሉ እጅጉን የተረገመች መጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ስንትና ስንት ታላላቅ ዜጎች በዚህ ሰውዬ እጆች ተነክተው እንደበከቱብን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ አፄ አቢይ አንድን ሰው ነካው ማለት፣ አንድን ዜጋ አቅፎ ሣመ ወይም አስጠግቶ በአስመሳይ ቅጥፍጥፍ ምላሱ አነጋገረ ማለት በቁሙ ገደለው ማለት ነው፡፡ ይህ ሰይጣናዊ ፍጡር ምን ትብታብ ይዞብን እንደመጣ ባላውቅም እርሱ ወደሥልጣን ማማ ከወጣ ወዲህ የደረሰብንን ሁሉ ለመጻፍና ለመናገር ግን አራት ዓመታትም አይበቁንም፡፡ ያገሬ ሰው ይህን መሰሉን የሰይጣን ውላጅ “የሰንበት ጽንስ” የሚለው ወዶ አይደለም፡፡
አቢይ ወደውጪ ሲወጣ ሰዎች ይገደላሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ራሱን ከሰወረም ብርቅዬ ዜጎች እየታደኑ ወደ ዘብጥያ ይወርዳሉ፡፡ ኦሮምያን በዋናነት ጨምሮ አንዳንድ ክልሎች እንደፈለጉ ያሽቃንጣሉ፡፡ በክልላቸው የሚገኙ የሌላ ዘውግ አባላትን በተለይም አማሮችን እንዳሻቸው ይገድላሉ፤ ያስራሉ፤ ያንገላታሉ፤ ያፈናቅላሉ፤ ይዘርፋሉ፤ መዝረፍ ያልቻሉትን ሀብት ንበረት ያወድማሉ፤ በጥቅሉ ምስኪኖቹ ዜጎች መፈጠራቸውን እስኪራገሙ ድረስ መከራና ስቃያቸውን ያበዙባቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ ከአፄው ቡራኬና ፍቃድ ውጪ እንደማይሆን በፍቅሩ የደነዘዙ/ የነሆለሉ መረዳት ባይፈልጉም እኛ ግን ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ቅቤው አፄ ቦካሣ ሰውን ሲጨብጥ በተቆራኘው የአጋንንት መንፈስ ሳቢያ የሚነካው ሰው ሁሉ ይፈዝና ልክ ቡዳ እንደበላውና ወደጋንነት ወይም እንሥራነት ተለውጦ ዞምቤ እንደሚሆነው በድን ሰው ሁሉ የርሱ ቅን ታዛዥ ይሆናል፡፡ አሁን አሁን እርሱን ላለማየትና ላለመጨባበጥ የሚፈራ የሚጠነቀቅም ሰው ሳይበዛ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ “እባብ ያየ በልጥ በረዬ” እንዲሉ ነውና እነዳንኤል ክብረትንና እነታማኝ በየነን የተመለከተ አፄ አቢይን ሲያይ የሚገባበት ቢጠፋው አይፈረድበትም፡፡ እኔ ለምሣሌ አይበልብኝና አቢይ ባለበት አካባቢ ዝር ማለትን በፍጹም አልሻም፡፡>>
ካለ በኋላ ስለ ጉደኛው ኦሮሙማው ኢነትርሃሙዌው ቡድን እንዲህ ይላል፡
<< …..ከፍ ሲል የጠቀስኩትን ምሥጋናዊ ጸሎት ወይንም ጸሎታዊ ምሥጋና ይበልጥ እንድገፋበት የሞራል ብርታት የሰጠኝ ደግሞ የዛሬ ሁለት ይሁን ሦስት ዓመታት ገደማ “ውጣልኝ!” በሚል ርዕስ በዩቲብ የወጣው የኦሮሙማ ክሊፕ ነው፡፡ በዚያ ክሊፕ ውስጥ በጣም ብዙ ሰው ተሳትፏል፤ አንዳችም ሳያፍሩ ነው ታዲያ፡፡ ደራሲውም፣ አቀናባሪዉም፣ ዘፋኙም፣ ሙዚቀኞቹም፣ አጃቢዎቹም፣ ጨፋሪዎቹም … ምንም አያፍሩም፤ እኔ ግን ስለነሱ የምገባበትን አጣሁ፡፡ ያን ክሊፕ ያዬ ጤናማ ሰው - ኦሮሞም ይሁን ትግሬ ወይም ሌላ - ኦሮሙማዎች ምንኛ በዘረኝነት ደዌ እንደሚሰቃዩ ይረዳል፡፡
አሁን ባለኝ የአስተሳሰብና የአመለካከት ይዞታ ላይ እንዳለሁ ኦሮሞ ብሆን ኖሮ ያን ክሊፕ ሳዳምጥ ምን ይውጠኝ ነበር ብዬ ሳስብ አለማሰቡን ብቻ መረጥኩ ወንድማለም፡፡ በዘፈኑ ርዕስ ጉግል አድርጉና ያን ብዙ ኦሮሞ በደስታ ሲቃ እያነባ የሚዘፍነውንና የሚጨፍርበትን ዘፈን አድምጡት - አማራን አሁን በምናየው ፍጥነት ከአዲስ አበባ ለማውጣት ነው የዘፈኑ ማዕከላዊ ጭብጥ፤ በዘፈኑ የተገለጸው ቁም ነገር እኮ ነው እየተተገበረ ያለው። በነገራችን ላይ የሽመልስ ትንቢትና ፖለቲካዊ ዕቅድ እኮ ነው አሁን በተግባር እየተገለጠ የሚገኘው - ለታዛቢ ቀልድ ሊመስል ይችላል፡፡ ግን እውነት ነው፡፡ የኦሮሙማ አስፈሪ ገጽታ ደግሞ ይሄ ነው፡፡
ዘፈኑን ስሙት ብያችኋለሁ፡፡ ያኔ - ዘፈኑን ስትሰሙት - ኦሮሙማ ማለት - ጽንሰ ሃሳቡ ራሱ - ከጥልቁ የዲያቢሎስ ጽልመታዊ መንግሥት እንደመጣ ትረዳላችሁ፡፡ ያኔ አቢይና ሽመልስ የጥልቁ ተወካዮች ብቻ ሳይሆኑ ሊቀ ሣጥናኤል በሰው አምሳል ኢትዮጵያ ውስጥ በነሱ አካል በግልጽ እንደተከሰተ ትገነዘባላችሁ፡፡>> ብሎ ነበር ዳግማዊ ጉዱ ካሳ በዚህ ፌስቡኬ የተለጠፈው።
ትዝ ይላችሁ እንደሆነ እኔም
<<፡ኢትዮጵያዊያን ከአዲስ አባባ እየተገደሉ እንዲባረሩ አብይ አሕደመድ በነፃነት እንዲዘፍን የፈቀደለት የኦሮሞው ዘፋኝና መባረርን የተቃወመው ኢትዮጵያዊው ዘፋኝ “ቴዲ ዮ” ለምን ተለይቶ ታሰረ? >> ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/30/2022 በሚል “ውጣልኝ” የሚለው ኦሮሞዎች እየዘፈኑ አማራውን የማባረር ዘመቻ ያደረጉበትን በይፋ የተሰራጨ ቪዲዮ አቅርቤላችሁ ነበር። ያንን ጉደኛውን <<የኦሮሞዊው ኢንተርሃሙዌው ቪዲዮ>> እና አሁን አዲስ አባባ ውስጥ እየታፈሰ ወደ ማጎርያ እየገባ ያለው አምሐራዊው ሕዝብ <<የአብይ አሕመድ እና የኦሮሙማው ቄሮ የኢንተርሃሙዌው ዱሩየ የሙዚቃ ቡድን>> የመቀናጀታቸው አጀንዳ በግልጽ ዛሬ ህያው ሆኖ እያያችሁት ነው።
በዚህ ቪዲዮ የምታደምጡት “ፈጣጣ ወንጀል” ዛሬ አብይ አሕመድ አዲስ አባባ ውስጥ ተግባራዊ እያደረገው ነው ስንል ከምንም ተነስተን አይደለም። በየዘመኑ በርካታ ከሃዲዎች ኢትዮጵያን ሲክዱ ታይተዋል። አዳከምዋት እንጂ አልገደልዋትም። ከሃዲዎች በየዘመኑ ያሳዩን ክስተቶች ታሪክ መዝግቦአቸዋል፤ ዛሬም የእነዚህ ከሃዲዎች ገመና ይመዘግባል።
ጽሑፉን ማሰራጨት አይሰልቻችሁ፤ ለዘመዶቻችሁ ህልውና ስትሉ እንጂ ለኔ ስትሉ አይደለም፡ እኔ በተመቸ ዓለም ውስጥ እኖራለሁ።
አመሰግናለሁ
ጌታቻው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment