Tuesday, August 29, 2023

ኦሮሞ በኦነግ እና በደርግ የጸደቀ መጠሪያ ስም ነው! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 8/28/2023


ኦሮሞ በኦነግ እና በደርግ የጸደቀ መጠሪያ ስም ነው!

ጌታቸው ረዳ 

(Ethiopian Semay) 

 8/28/2023

እስኪ በዚህ ልጀምር፡

በነገራችን ላይ ኦሮሙማው መንግሥት በ19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን  አዲስ አበባ ሲገባ አቀባባል ሲያደርግላቸው በያንዳንዱ እስፖርተኛ አንገታቸው ላይ ያጠለቀላቸው የአበባ ጉንጉን የያዘው ቀለም አያችሁት? አባ ገዳ ብሎ ራሱን የሚጠራ የባንዴራ ቀለም መለያ ነጭና ቀይ ነበር (ጥቁርዋን እንዳይጨምሩዋት የሃዘን እንዳታስመስለብቻው ተውዋት)። ይገርማል! አሁን ውነት ኢትዮጵያን ሰንደቅ  ዓላማ የሚያመለክት አበባ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ” አበባ የለም ተብሎ ነው? የዘንድሮ ጉድ አያልቅም።

እንደምን ናችሁ?

ችግራችን ለመፍታት በግልጽ እንነጋገር አደለም እየተባለ ያለው? ከላይ የተጠቀሱት ማሕበረሰቦች እንዳፈለጋቸው ሜዳውን ሲጋልቡበት ዘመን አልፎባቸው ሌላው ግን በአርምሞ ነበር እያለፈው አሁን እያየነው ላለው የዘር ጭፍፋና ጋጠወጥ ወረራ የተጋለጠው። ማነው ዘመድኩም በቀለ ነው “ነጭ ነጭዋን” ያለው?

 (መጎስ የተባለው ሕግ ተማሪና ድሮ ዳኛ የነበረ ፤ ዛሬ አውስትርያ ለዶክተሬት (ይመስለኛል) እየተማረ ያለው ወጣት ምሁር “በራሱ መድረክ የጋበዘው አንድ “ጋዜጠኛ ነኝ የሚል አክራሪ እስላም” አማራ የሚባሉት ሰዎችን ስለ እስልምና እና አገር ምስረታ የተናገሩትን እየለቃቀመ በራሱ ወገን ያሉትን አክራሪ እስላሞችና (የታወቁ የእስልምና ዩዜና ማሰራጪያዎችና መወያያ መድረኮች) ፤ድፍን ኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችና መሪዎች እንዲሁም በመንግሥትነት የተቀመጠው ኦፒዲኦ እና የሥርኣቱ መሪና ሹሟሙንቶችና ፖሊሶቹ ሚዲያዎቻቸው፤ ድርጅቶቻቸው ቀበሌ ሹሟምንቶች የሚናገሩትንና የሚሰሩትን አክራሪና ሰልቃጭ ጸረ ክርስትና፤ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ተግባር ግን “እየደበቀ” ለውይይቱ የጋበዘው ያንን መሳይ አክራሪ “ጤነኛ” ነው ብሎ ሲጋብዘው  ዘመድኩንን ከዚያ መሳይ አክራሪ ጋር በመስማማት “ዕብድ” ወዘተ…. ሲለው ሰምቼ “ወይ ዘመን አልኩኝ” (ይህን ብየም- እዚህ ላይ ‘መጎስ ተሾመ’ አክራሪውን ጋዜጠኛ በደምብ ስለሞገተውና በሃሳብ መፈናፈኛ ስላሳጣው ሳላመሰግነው አላልፍም)

የሆኖ ሆኖ ወደ ሃሰቤ ልግባና  አሁን በዚህ ስም የሚጠሩ ማሕበረሰቦች በድሮ ስማቸው ላለመጠራት የሚሸማቀቁበት  ምክንያት ምስጢሩ የተደበቀ አይደለም። ምስጢሩም ያ የ16ኛው ክ/ዘመን “ እራሱ ታሪክ” በሚያውቃቸው መጠሪያ ላለመጠራት በደርግ ዘመን የቀየሩት የዛሬ መጠሪያ በ16ኛው ክ/ዘመን ታሪክ አይታወቅም (ጀርመኑ ፕሮተስታንት ዮሃንስ ክራፈት ያንን ስም እንዳወጣላቸው እራሱ መዝግቦታል ያውቀዋል) የጥንቱን ስማቸውና አኗኗራቸው በዛው በ16ኛው ክ/ዘመን  እንደያዙ ከየት ተነስተው እስከየት ድረስ ኢትዮጵያን እንዳጥለቀለቁዋት እና ሌሎችን ማሕበረሰቦች አጥፍተው የዋጡበትና ቋንቋቸውም እንዲናገሩ ያደረጉበት ሰነድ በዛው በጥንት ስማቸው ታሪክ ስለመዘገበው በዛው ስም ላለመጠራት ይፈራሉ።

መጎስ በገበታ መድረኩ ለምን በዛው መጠሪያ ሊጠሩ እንደማይፈልጉና መጠሪያቸው ምን ሲባሉ እንደነበረና እራሳቸው ታወቂ ኦሮሞ መሪዎችም ሳይቀሩ በዛው በጥንቱ ስማቸው በኩራት ሲጠሩበት የነበሩትን የሚከራከሩ ምሁራንን ሁለቱን ወገኖች ጋብዞ ቢያወያይ ጥሩ ነበር። ቃሉ ሲነሳ “አንወያይም ብለው ካላቋረጡ (ላለመወያየት እንደ ሽፋን ካልተጠቀሙበት- እንዲያ ብለው የሸሹ ታዋቂ ሰዎች ካሁን በፊት ስላደመጥኩ ነው)። ቢሆንም መሮጥ ይቻላል፤ መደበቅ ግን አይቻልም።

 ታሪክ የራሱ ሰንሰለት አለውና መስተዋቱ በሰንሰለቱ አስሮ ተከታታይ ትውልዶች እንዲመለከቱት ያደርጋል። እነዚያ ዛሬ በሕግም በታሪክም በምናምንም ዲግሪ ጭነናል እያሉ በየ ዩቱብ “ምን ይሻላል” እያሉ የሚቦተልኩ “ምሁራንና ፖለቲከኞች” ለ35 አመት አድክመውናል። “አትጥራኝ ካለህ በዛው ስሙ አትጥራው” በቃ  ‘አትጥራው” እያሉ ታሪክን በሚጻረር መልኩ ወደ ጉሮሮአችን ሲደነቅሩብን ሰምተናል። እሺ አንጠራቸውም ግን ታሪክ ስንጽፍ ቃሉን እነሱ ባልነበሩበት ዘመን እንዴት ሲጠሩበት የነበረውን ትተን በዛው ወቅት በማይታወቁበት መጠሪየቻው ጥሩዋቸው እንባላለን?

  ያረጁት በሰላማዉያን እና  በሃገራዊ አርበኛነት በታሪክ ተመዝግበው ሲሄዱ ዛሬ የነዚህ ክቡራን ዜጎች ልጆች ነን የሚሉን የዛሬዎቹ ወጣት ምሁራኖች ግን የ18 እና ዩ19ኛዎቹ ክ/ዘመን ክቡራን ኦሮሞ ወገኖቻችን ሳይሆኑ የነዚያን የ16ኛው ክ/ዘመን ዘመኑ የፈቀደላቸው ያልተማሩ “የከብት አርቢዎቹ” ባሕሪ በዚህ በዛሬው በሠለጠነው ዘመን እንደገና “ህያው” በማድረግ ታሪካዊ ሃውልቶችና ግንቦችን አገርና ሃይማኖትን ቅርስን ቤተጸሎቶችን እያፈረሱ፤ ባንድ ነገድ ያነጣጣረ የዘር ፍጅት የሚያራምዱ “ሁሉም የኛ” ባዮችን ሊነገራቸው የሚገባውን መነገር አለበት።

 በዚህ በኩል የመልስ ምት ሲሰጥ ግን  “ነገር ያባብሳል” እያሉ እውነተኛውን ታሪክ እንዳትናገሩ እያሉ አክራሪዎች ብቻ እንዲናገሩና እንዲጽፉ ተፈቅዶላቸው፤ የልብ ልብ ለዘመናት ተሰምቷቸው “ውሸት እውነት መስሎ ሲደጋገም ዘመናት አልፈው” ይኸው እዚህ ደርሰን አባራሪና ተባራሪ ማሕበረስ ሆነናል።ይህን ታሪክ ስናቀርብ አንዳንዶቹ በቅንነት እንደ እሳት ይቃጠላሉ። ቢቃጠሉም ባይቃጠሉም “በቃ ማለት በቃ ነውና” ማስተማራችን ይቀጥላል።

እነዚህ ስማቸው ሲወሳ የሚደናገጡ የ16ኛው ክ/ዘመን የወራሪ ታሪካቸው እንዳይጋለጥ “ከፌስቡክ አስተዳዳር ቡድን ጋር ስለተቧደኑ” ታሪካቸውን ለመደበቅ እጅግ ተመችቷቸዋል። አምሐራ እና ትግሬ ወርረውናል እያሉ የመጻፍ መብታቸው ሲከበርላቸው በዚህ በኩል ያለው ወገን ስለ እነሱ ሲጻፍ ግን ወዲያውኑ እየተሯሯጡ እንዳይነበብ በፍርሃት እጠንቀጠቀጡ እንዲታደግ ያደርጋሉ። በራስ መተማመን ካለ መልስ መስጠት እንጂ ታሪክን መፍራት አያስፍልግም እና እንዲለማማዱት ዛሬም እንጠይቃቸዋለን።

ጊዜው የመነጋገር ነውና እንነጋገር። ዝምታ ለአህያም አልተመቻት” አደለም የሚባለው? ስለዚህ እንነጋገር። በዛው በጥንት ስማቸው ሲጠሩ የነበሩት የያኔው የ16ኛው ክ/ዘመን ከብት አርቢዎች’ "ግጦሽ ፍላጋ"  ወደ መላው አገራችን ሲስፋፉ ተወራሪዎቹባለገሮች” ቁጥራቸው "ብዛት" ስለነበራቸው በዚያው በሰፊው ባለሐገር ባሕር ውስጥ ገብተው በመካከላቸው ተጋብተው በሂደቱ ራሳቸውን እንዲዋጡ አድርገው  ተወራሪዎቹን ወደ ገባርነት (ገርባ) ለውጠው ቋንቋቸው በሂደት እንዲናገሩበት በማድረግ በቁጥር የነዚያ የ16ኛዎቹ መስለው ከፍተኛ ሕዝብ ያለቸው መስለው ታዩ (ዛሬ ያለው ብዛት የዚያው ውጤት ነው)።

የሆነውም እንዲህ ነው። በዚህም እነዚያ ግጦሽ ፍላጋ ወደ ሰፊው አገራችን የገቡ ከብት አርቢዎች የጎሳ ማንነታቸውን እያጡ፣ በአካል፣ በባህል፣ በቋንቋ የመዋጣቸው የመሰባጠራቸው ሂደትም  “በባለገሬው ነባር ሃይማኖቶች (የኦርቶዶክስ ክርስትናም ሆነ የኢትዮጵያ እስላም መቀበላቸውን ተከትሎ) ኢትዮጵያዊያን ሆነዋል።

በቋንቋም ቢሆን፣  – ኦሮሚፋ፣ አፋን ኦሮሞ ወዘተ… (የፈላገችሁት አጠራር ጥሩት) እሱም እንደ አካላዊ ቅርጻቸው ተቀይጧል።

ከብዙ አማታት በፊት የታሪክ መምህሬ እንደጻፉልኝ  “እነዚህ በኬንያ ድንበር ክልል የሚገኘውን የቦረና እና ባሬንቱ  ጥንታዊ ቀበሌኛ ኗሪዎችን ከሌሎች ማለት  ወደ ደቡብ ፣ሰሜን ፣ምስራቅ እና ምዕራብ ስትሄዱ እነዚህ ጎሳዎች በየሰፈሩበት መሬት በኬንያ ውስጥ ፣ሶማሊያ ውስጥ ቋንቋቸው ከአካባቢው ጋር ስብጥር እንጂ ወጥ አይደለም። ለምሳሌ ይላሉ፡… “ለምሳሌ ሶማሌ ውስጥ ያሉት ከጉተራ፣ በኢትዮጵያ ውስጥም እንደ በደናኪል መካከል ያሉት የአፋርኛ ቋንቋን ወስደዋል፣ ከሀዲያ፣ ከሲዳማ፣ ከጉራጌ እና ከኦሞቲክ ተናጋሪዎች ጋር በቋንቋ ተለዋውጠዋል።

ወደ አማርኛ ስንሄድም፤ በወቅቱ በከብት አርቢነት ሲኖሩ የነበሩት እነዚህ ዎች ከሸዋ አማራ እና አንጎት ከአማርኛ ተናጋሪዎች መካከል ሲኖሩ እንዲሁም እንደ ወሎ እና የየጁ አይነት አማርኛን አንስተዋል። እንዲሁም ከአባይ በስተደቡብ ከሚገኙት ጋፋት፣ ጊያንጀሮ እና ኤናሪያ የተሰባጠረ አካላዊ ቅርጽ እንዲሁም የባህል እና የቋንቋ ባህሪያት ስብጥር ወርሰዋል።

ከአገው የአገው ጎጃም እና ከአባይ ሰሜናዊ ላስታ መካከል አገውን አንስተዋል። ከዚያ የቆቱ ዘዬ አንስተዋል። እንዳውም በእርግጥም "አፋን ቆ" ይሉታል።

ለምሳሌ ይላሉ ወዳጄውና የታሪክ ተመራማሪው መምህሬ፦

 “የወለጋ ተወላጅ የሆነው ‘ኦኔሲሙስ ነሲብ‘ ፣ ምናልባትም የጋ*ኛ የመጀመሪያ ምሁር፣ ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ጋ**ኛ የተረጎመ እና የጻፈው። ጋ*ኛ አንባቢ “የጋ*ላ” ሆሄያት መጽሐፍ እንዲሁም “ጋ*ላ-አማርኛ መዝገበ-ቃላት” በሚል ርዕስ የሐረርን ቆቱ ካነጋገራቸው በኋላ እርሱን ከመረዳት ይልቅ እሱን ሊረዱት እንደቀለላቸው ተናግሯል። ልብ በሉ የዛዎቹ ኦሮሞ ፖለቲከኞች የሚያደንቁት የፕሮተስታንት ተከታይ የወለጋ ተወላጅ የሆነው ‘ኦኔሲሙስ ነሲብ‘  በየመጽሃፍቱ ውስጥ “ኦሮሞ” የሚባል ነገር አንዲትም ቃል አታገኘበትም፡ የለም።”

በሌላ መልኩ “ኦሮሞዎች አንድ ነን” የሚሉን ያዛሬ ኦሮሞ ምሁራን እርስበርሳቸው እንኳ እንዳያችሁት በደምብ መረዳዳት እንደማይችሉና ላቲን የመፍጠራቸው ዘዴም ይህ ምክንያት ነበር። ለዚህም ነበር ከላይ እንደጠቀስኩላችሁ “የወለጋ ተወላጅ የሆነው ‘ኦኔሲሙስ ነሲብ‘ የሐረርን ቆቱ ካነጋገራቸው በኋላ እርሱን ከመረዳት ይልቅ እሱን ሊረዱት እንደቀለላቸው የተናገረው።

 ባጭሩ ለሦስት መቶ ዓመታት የዘለቀውን የነዚህ ጎሳዎች ታሪካዊ ወረራ የኢትዮጵያን ቋንቋዎችን ሁሉ አንስተዋል ብለው የቋንቋ ሊቃውንት ይነግሩናል።

በዚህ ልደምድም፡ መምህሬ እንዲህ ሲሉ በውይይታችን በዚህ መደምደሚያ ተሰናበቱኝ፡

<< አየህ ጌታቸው አንድ ነገር ልንገርህና ልሰናበትህ። በአሩሲ፣ በወለጋ እና በቆቱ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች መካከል ያለው ልዩነት የቋንቋ እና የሀይማኖት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የባህል አመለካከት፣ የአኗኗር ዘይቤ ወዘተ... ብትመለከት አንድ ነን የሚሉት የዛሬዎቹ አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ “ፌዝ” ይሆናል። ለቆቱ ኦሮሞዎች ከወለጋ ወይም ከኢሉባቦር ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ይልቅ ኦሮምኛ ላልሆኑ ሰዎች አኗኗራቸውን ለሚጋሩት ቅርብ ናቸው። የሰሜን የራያ ወይም የአዘቦ ኦሮሞ ተናጋሪዎችን ብታመጣ እማ ደግሞ ልዩነቱ እጅግ በጣም የከፋ ይሆናል።>>  ሲሉ መምህሬ ውይታችንን በዚሁ ደመደሙት።

አዎ “ኦሮሞ” በኦነግ ወያኔ እና በደርግ የጸደቀ መጠሪያ ስም ነው! የምልበትም  ምክንያት በጸደቁባቸው ሕገ መንግሥቶችና ዘመኑን ማየት ይቻላል። ብግሃድ እንድንከራከር ይፈቀድልን አታፍኑን!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

 

 

Saturday, August 26, 2023

ተራራ ሠራቂው የትግሬው ትውልድ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/26/23


ተራራ ሠራቂው የትግሬው ትውልድ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

8/26/23

 

ህ ትንታተኔ ወልቃይት የትግሬወ ነው ለሚለው ለኦሮሙማው አሽከር ለትግሬው አብርሃም በላይ እና ይህንን አቋም ለሚያራምዱ ትግሬዎች በሙሉ በምጽሓፌ የተቀነጨበ ዛሬም የምሰጠው መልስ ነው።

 

       ‘ወዲ ዐበይቲ’ አንዳንዴም ዘጽአት እያለ እራሱን በብዕኢር ስም የሚጠራው ትክክልኛው በሙያው ሐኪም የሆነው መጠሪያ ስሙ ጎይተኦም የተባለው “አማራ ከሚለማ የሲናይ በረሃ ቢለማ እምርጣለሁ” በማለቱ የሚታወቀው ጸረ አማራ የናዚ ወያኔ ትውልድና የመሳሰሉት ትግሬዎችና የነዚህ ፋሺሰቶች መምህር የሆነው ሟቹ መምህር ገብረኪዳን ደስታ  “አማራዎች ባህላችን ነጥቀው ወልቃይትና ራያ መሬታችንም ነጠቁን” የሚሉትን እሮሮ ማስተጋባታቸው ይታወቃል።

 

ይህ የሄጂመኒ” (የስልጠቃ) ወረራ እና ማስተጋባት ዛሬም እልባት ስላላገኘ ይህ ደራሲ በመጽሐፍ መልክም ሆነበድረገጾች በዚህ ጉዳይ ሲለው የነበረውረ ዛሬም  የጉዳዩ አሳሳቢነት በማየት የወያኔ ትግሬዎች የዝርፍያ ማሕደሮችን ለማሳይት ዛሬም እንሆ፡፡

 

 አማሮች ፤ጎንደሬዎች ይህንን ዘረፉን የሚለው እሮሮ ተመልሼ እነ አብርሃም በላይ የድሮ የወያኔ የስለላ ኢንጂኔር ሰራተኛ እና  እና መሰል ጎጠኞችን መልሼ ልጠይቅ?

 

‘የጎንደርን ወልቃይትንና የወሎን መሬት የመዝረፋችሁ ሳያንስ፤ ብላችሁ ብላችሁ ራስ ዳሽንም ሰረቃችሁ፡ ተራራም ይሰረቃል እንዴ? ብለው ጎንደሬዎች ቢጠይቁዋችሁ ምን መልስ አላችሁ?

 

ይህ ጥያቄ ያቀረበኩላችሁ እኔው ትግሬው ሳልሆን አማራው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ነው፡ ክንፉን የጥቅሱ ጽሑፍ በመጽሐፌ ላሳትመው ብየ ጠይቄው በደስታ እንድጠቅሰው ስለፈቀደልኝ ያኔ ባሳተምኩት መጽሐፍ (የወያኔ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው?) በሚለው መጽሐፌ የታተመው ጥቅስ ። እንዲህ ይላል ክንፉ፦

 

<<ራስ ዳሸን ተራራ ከትግራይ “ክልል” ካርታ የመውጣቱ ‘አሲዮ ቤሌማ’ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ሲናገር፤ “ደፍረውናል! ንቀውናል! ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል!” የሚለው የኮሎኔል መንግስቱ ንግግር በጆሮዬ ላይ አቃጨለ። ድፍረቱ እና ንቀቱ እንዳለ ሆኖ፣ በቁም የሞቱት ግን እኛ ሳንሆን እነሱ መሆናቸውን የሚያበስር የዜና እወጃ ነበር።

ድምጽም በተደጋጋሚ ሰርቀዋል። ተራራ ተሰርቆ  ሲመለስ ግን የመጀመርያው ነው።

 

ከኢትዮጵያ አንደኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በከፍታ 4ኛው ተራራ ነው ራስ ዳሸን። ከሰሜን ጎንደር ከበየዳ ወረዳ ተሰርቆ ለ25 አመታት ሙሉ ትግራይ ክልል ገብቶ ነበር። ወንጀሉ ወደ ትግራይ “ክልል” መግባቱ ብቻ አይደለም። አንድ ትውልድ እና በስነ-ምድር ሳይንስ በውሸት ታሪክ እንዲታነጽ መደረጉ እንጂ!>> ይላል ጋዜጠኛ  ክንፉ አሰፋ (ተራራም ይሰረቃል እንዴ? የራስ ደሸኑ ፖለቲካ September 18th, 2016 ምንጭ ክንፉ አሰፋ ድረገጽ EMF ኢትዮ ፎረም አዘጋጅ) (በራሴው መጽሐፍ ገጽ የታተመ -ጌታቸው ረዳ (89)

 

ይህ ሁሉ ስርቆት በትግሬዎች መንግሥት እየተፈጸም እየታወቀ ወልቃይትና ራያ አማራዎች ሰረቁን እያሉ ራስን እንደ ንጹህ ማቆነጃጅት የሚገርም ዘመን ነው። ሌላው ዝርፊያው ከተከናወነ በኋላ የሚሰረቅ ታጥቶ ተራራ ሲሰረቅ ማየት እውነትም  <<ተራራም ይሰረቃል እንዴ?”!>> የሚያሰኝ የሚገርም ጉድ ነው። ‘አላርፍ ያለች ጣት ……..ምን ዘንቁላ ትወጣለች” ነው የሚሉት የአማራ ምሳሌዎች!?

 

በ1998 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግራይ የተከለለ ራስ ዳሸን ተራራ በስህተት ነው ብሎ በ2009 መንግሥት ተብየው በቴ/ቪ ያቀረበው ሳይወድ እርማት ያደረገው “ተራራ ሠራቂ” የሌባ ዓይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ይሉታል ይኼ ነው። የትግሬዎቹ መንግሥት  በተራራ ዘርፍያ ብቻ አላበቃም፤ፎቶግራፎቹ በመጽሐፌ የጣታሙ ምስሎች ናቸው።                                                         

ሌላው የመሬት/ የድምበር ዘረፋው/ (አነክሰሽን) ደግሞ እንደሚከተለው በስሕተት ነው እያለ ቅጥፈቱን ለማሳመር ይቅርታ ጠይቋል። የራስ ዳሸንን ተራራ ለ11 አመት ሙሉ በየትምህርት ቤቱ በእንግሊዝኛ መማርያ መጽሐፍ ውስጥ አትሞ ተማሪዎች የትግራይ ተራራማ መሬት መሆኑን ካስተማረ በኋላ ሲነቃበት <ስሕተቱ የማተሚያ ቤቶች ስሕተት ስለሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን> ብሎ 11 አመት አላወቅኩም ነበር ሲል ወደ ‘አማራ ክልል’ ወደ ጎንደር ለባለቤቱ መልሰናል ብሎ ሲያበቃ፤ እንደገና ሌላ የቡንሻንጉልና አማራ መካበቢያውን ወደ ትግሬ ቀላቅሎ በአማራ መሬት በስጀርባው/በጓሮ በኩል እንደ እባብ ተጠምጥሞ አልፎ የአማራ ሕዝብ) ለብቻው ታጥሮ ወደ ሱዳን መንደርም እንዳይወጣ አጣብቆ በመከለል ከቤንሻንጉልም እንዳይገበያይ ‘እንዲነጠል” ያደረገው የትግራይ ወያኔ የመሬት ዘረፋ (አነክሰሽን) አከላለል ‘ካርታው’ በ ኢ ብ ሲ-ቴሌቪዥን የታየው በስሕተት ከኢንተርኔት የተወሰደ ካርታ ስለነበር  ይቅርታ ሲል ጠይቋል።

 

እንግዲህ ደጋግሞ በተለያየ ስርቆቱ ይቅርታ መጠየቁ የሕዝቡን ‘ቅንድብ’ ስለሚያቆም ፤ሐፍረቱን ለመሸፈንና ሌብነቱንም ሕጋዊ አድርጎ በሕዝብ ሕሊና ለማስረጽ 

 

ላቀደው ተንኮል ለመሸፈን እንዲያመቸው በማለት ብዙውን  የአገራችን ሕዝብ  በማያውቀውና በስፋት የማይገለገልበት <በፌስ ቡክ> ብቻ (ልብ በሉ! በቴ/ቪዥን አይደልም ይቅርታ የጠየቀው በፌስ ቡክ ቲ/ቪ ብቻ ነው ይቅርታ የጠየቀው።) ያስተላለፈው።

 

 ይቅርታው እንዲህ  ይላል።

 

<< ለክቡራን የኢቢሲ ተመልካቾቻችን በ18/12/2009 ዓ.ም በ ኤቢሲ የቀን ሰባት ሰዓት ዜና ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ሽልማት መገኘቱን ተከትሎ በተሰራው ዜና ላይ ሰራውን ለማሳየት  ከኢንተርኔት የተወሰ የተሳሳተ ካርታ በዜናው ላይ የገባ ስለሆነ ለተፈጠረው ስህተት ኮርፖሬሽኑ ይቅርታ እየጠየቀ፤ ሌላ ምንም አይነት መነሻ የሌለው መሆኑን እንገልጻለን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን>> ይላል።>> (ታላቋ ትግራይን እንድለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ – ቬሮኒካ መላኩ (August 28, 2017 Ethioxplorer.com / Ethioforum.com) (91)  “ከኢንተርኔት የተወሰደ?” ይገባችኋል አነጋገሩ? መንግሥት ነኝ የሚል የአገሪቱን ትክክለኛ /ሕጋዊ የመሬት ነድፍ (ካርታ) ሳይኖሮው ከኢንርተርነት የተቀዳ ስሕተት ስለሆነ ብሎ ማለት ቀልድና ቅጥፈት ነው። ወያኔ ይቀልዳል! ኢንተርኔት ያለው ካርታ ማነው ያሰራጨውና የሰራው? “እራሱ “ወያኔ” ነው!

 

በመሰረቱ የሁለቱም ነጠቃ/ዝርፊያ/ይቅርታ ሲደረግ፤ 1ኛው በት/ቤት መማሪያ መጽሐፍ የሚያክል ትልቅ ጉዳይ፤ ለመጽሐፍት ጥራት የተቀጠሩ ምሁራን መርማሪዎች- ሳይጣራ፤ ሳይመለከቱት “ይለፍ” ተብሎ የታተመውን መጽሐፍ “አጣሪው’ ክፍል ስራው አልሰራም (የወያኔን ቃል “ስሕተት” የሚለው እንቀበለውና) ከፍተኛ “ስሕተት” ስለፈጸሙ ለግዴለሽነታቸው ከሥራቸው መባረር ነበረባቸው። አይደለም እንዴ? እርምጃ ከተወሰደባቸውም ለሕዝብ ወዲያውኑ ማሳወቅ ነበረበት። እይደለም እንዴ? ሌለው ወያኔ የሚለን “ማተሚያ ቤቱ ራስዳሽን ወደ ትግራይ የተካለለ አድርጎ አትሞታል በስሕተት” ይላል። ማተሚያ ቤቱ “ካርታ የማውጣትና መጽሐፉ ውስጥ የማስገባት፤የመደለዝ፤የማስወጣት፤የማረም፤የማስተካከል፤ መብት በየትኛው የሕዝብ ሥልጣን፤ ይሁንታ ወይንም  የፓርላማ ሕግ ስለተሰጠው ነው፤ይህ <ስሐተት> (የወያኔ ቃል) ወንጀል ለመፈጸም መብት የተሰጠው?

 

 ስሕተት ከሆነ ማተሚያ ቤቱ ወደ ሕዝብ ተጠርቶ በቴ/ቪዥንና ራዲዮ፤ ጋዜጣ ተጠይቆ  መልስ እንዲሰጥ ለምን አልተደረገም? ፍርድ ቤትስ ለምን ሄዶ ቅጣቱን እንዲያገኝ አልተደረገም? የአገሪቱ “ክልሎች” (አፓርተይድ ግዛቶችና ሰንደቃላማዎች) በሕግ ከጸደቀ ካርታ ዉጪ ያሰራጨ በሕግ እንደሚያስቀጣ በሕገ መንግሥት ተብየው ደንግጎ እያለ፤ በውስጡ የሚገኙ ዘርፎች በስሕተት ሰሩት ብሎ ከዋሸን ለምን አልተቀጡም? ወያኔ ሕዝብ አያውቅም እያለ በሕዝብ ሕሊና ይቀልዳል፤ያሾፋል። የጫካ ሕሊናው በከተማውም ውስጥ የሚሰራ እየመሰለው በለመደው በጫካ ባሕሪው አሁንም ማታለሉና ድንቁርናው ቀጥሎበታል። ሕጉ ለማን ነው የቆመው? ማተሚየ ቤቱና መንግሥት ሐላፊዎች ሥራቸውን በሚገባ ካልሰሩ  “በሕግ” ከመጠየቅ ነፃ ናቸው? ሕግ እያለ የሚያወራው ሕግ የት አለ? አማርኛ ቃል የታጣ ይመስል “ብሮድካስቲን ኮርፖሬሽን” እያለ የሚጠራው የወያኔ የዜና ማሰራጫ ማዕከል፤ በየድረገጹ እየለቀሙ  “ሕጋዊ ካርታ” አስመስለው ለሕዝብ ሲያቀርቡ ሥራቸውን ያልሰሩት የዜና ማዕከሎቹ (አርታኢዎቹ) ለምን አልተጠየቁም? ምንሰ እርምጃ ተወሰደ? አልተወሰደም፡ ምክንያቱም “ወያኔ” ሊያድረገው የፈለገው የራሱ “መመሪያ እና እምነትና ስርቆት” ስለሆነ።

 

 <<ይቅርታ> እና <ስሕተት> በሚሉ ቃላቶች ማላገጡን ቀልሎታልና የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ። የወያኔ ደጋፊዎችም የሚደግፉትን መንግሥት ተብየው፤ ሕግመንግሥት አያዩትም ፤ አያውቁትም ቢሆን ትግሬነታቸውና ድርጅታቸው ፍጹም ነው የሚል ምነት ስላላቸው እንደ ታቦት ያከብሩታል፤ ቢሳሳትም እያወቁም ቢሆን ተጨፍነው ይከራከሩለታል።

 

የሚቀርብባቸው ክስ ሁሉ፤ ሻዕቢያ የሰረው ካርታ ነው ሲሉ ጭፍን መለስ ሲዋሹ ተከታዮቹ ያምኑታል። <<ይህን ሐሰተኛ ካርታ የሰሩትና የተቀባበሉት ጽንፈኞች ናቸው ብለን እንወራረዳለን/እንሰደባለን።>> ሲሉ የሚወነጅሉንና እንወራረድ የሚሉንን ውርርዳቸውን በሚከተለው የወያኔ  ሕገ መንግሥታዊ ማስረጃ እንመልከት።  ታላቋ ትግራይን እንድንለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ – “ቬሮኒካ መላኩ” ወልቃይት.ካም welkait.com August 28, 2017) (92) <ለካርታው ይቅርታ ተጠየቀ! ሕገ መንግሥቱ እንዴት ይስተባበል?> (ሙሉቀን ተስፋው) (93) በሚል ካርታው በወያኔ ሕገ መንግሥታዊ አዋጅ የጸደቀ መሆኑን በማስረጃ እቅርቦታል እነሆ ፦


<<አሁን ጥያቄው የካርታውስ ጉዳይ በይስሙላ ይቅርታ ታለፈ! የተሰረቀው ተራራና የተሰረቀው ቤተ መቅደስም አፉ በሉን ተብሎ ተመለሠ፡፡ ይህ ሕገ መንግሥት ምን ዓይነት ማስተካከያ ሊደረግበት ነው? የሚለው ነው፡፡ ይህን  የቤንሻንጉል ክልል ሕገመንግሥት በፎቶው ላይ ይመለክቱ። ሕገመንግሥቱን ለማንበብ

እንዳይችግራችሁ እንዲህ ይነበባል፦

አንቀጽ 1

የክልሉ መንግስት ስያሜ ይህ ህግ መንግስት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዴሞክራሲያዊ አወቃቀርን ይደነግጋል። በዚህም መሠረት የሚቋቋመው መንግሥት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሚል ስም ይጠራል።

 

አንቀጽ 2

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ወሰን በምስራቅ--የኦሮሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፤ 

በምዕራብ -    ሱዳን በደቡብ -   ጋምቤላ ሕዝቦች ክልል በሰሜን -     የትግራይ ክልል

 

በሰሜን ምስረቅ -የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ያዋስናል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብሄራዊ መንግሥት

ሰንደቅ አርማ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልል የራሱ ሰንደቅ ዓላማና አርማ ይኖሮዋል።

(ሙሉቀን ተስፋው፡ የዘመኑ ዕልቂት ደራሲ፤ ጋዜጠኛ )

August 30, 2017 ETHIOEXPLORER.COM) (93)

(ምንጭ ይህ ደራሲ ፈልጎ ያገኘው የሚከተለው ምንጭም የላይኛውን ያረጋግጣል።)

<<የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስትና የቤንሻንጉል-ጉሙዝ ሕዝቦች ታሪክና ተጠቃሚነት ለ9ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ለውይይት የቀረበ ህዳር 2007 ዓ.ም አሶሳ>> ይመልከቱ። የወያኔዎች ተንኮል መልሶ መላልሶ ልብ ያናድደናል! ወደ ሌላው የወያኔ ዘርፋያ እናምራ።   አማራዎቹ በሚከተለው ሰነድና ፎቶ እንዲህ ሲሉ ወያኔ ትግሬን  በስርቆት ይከስሳሉ-

 

(ከላይ ከምስሉ ጋር የምታዩት የጎንደሩ አንደኛዉ የጄኔረተር ክፍል ከ 24 አመት በፊት ተነቅሎ ወደ ትግራይ ተወስዶ ዉቆሮ አካባቢ ወደ አለችው የወረዳ ከተማ ሲራገፍ) ከአማራ አካባቢ

ወደ ትግራይ የወሰዳቸዉ ትልልቅ ጄኔረተሮችና ማሽነሪዎች የታወቁት

1.   የጎንደር ጄኔረተር፡

(ይህንን ጀኔሬተር በተመለከተ በክልሉ ም/ቤት ላይ እና በግልም ሀላፊዎችን በመጠየቅ ከፍተኛ ጥያቄ ያነሳ የነበረ ሰው በርካታ መረጃዎችን ይዘረዝራል)፤ ይህ ጄኔረተር ጎንደር ከተማዉንና የጎንደር ዙሪያ ያሉ ከተሞችን ያለምንም ችግር የ24 ሰአት የመብራት አገልግሎት ይሰጥ የነበረ አሁን ዉቅሮ አካባቢ ያለ። ጄኔረተሩ የነበረበት ሰፊ ቦታ አሁንም ድረስ አዉቶ ፓርኮ የሚባለዉ የከተማዉ እመብርት ላይ ታጥሮ ይገኛል።ጄኔረተሩን አናስወስድም ያሉ ሰወች በጥይት ተደብድበዉ ሞተዋል። 

2.  የባህርዳር ጄኔረተር፡

ይህ ጄኔረተር የባህርዳር ከተማን ሙሉ ለሙሉ የመብራት ሽፋን ይሰጥ የነበረ ሲሆን በጠመንጃ አፈሙዝ ነቅለዉ ወደ ትግራይ ወስደዉታል

3.  ፓዊ ጄኔረተር።

በድሮዉ ጎጃም ክፍለሀገር አሁን በቤንሻንጉል አካባቢ የሚገኝ ተልቅ የንግድ ከተማ ሲሆን የነበረዉን ጄኔረተር እንደዚሁ ህዝብ አስፈራርተዉ በጨለማ ወሰዱት

4. የመርሀ ቤቴ ጄኔረተር (ሰሜን ሸዋ)። ይህ አንድ ወረዳ ያበራ የነበር ጄኔረተር ሜንሽን ፎር ሜንሽን በተባለ የጀርመን ግብረ ሰናይ ድርጅት ከጀርመን ተገዝቶ ለአካባቢዉ ጥቅም ይሰጥ የነበረ ሲሆን። ህብረተሰቡ ሳያይ በሌሊት ነቃቅለዉ ወስዱት

5.                ግምጃ ቤት አካባቢ እንደዚሁ አንድ ወረዳ ያንቀሳቅስ የነበረ ጄኔረተር ተነቅሎ ወደ ትግራይ ተወስደ

6.               አዲስ አባባ እጅግ ዘመናዊና ትልቅ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ለአንድ ሚሊየን የአዲስ አባባ ህዝብ አገልግሎት ይሰጥ የነበር ማሽን ተነቅሎ ወደ መቀሌ ተወሰደ

7.                ደብረማርቆስ እንደዚሁ በአይነቱና በመጠኑ እጅግ ዘመናዊ የነበረ የድንጋይ መፍጫ ማሽን ተነቅሎ ወደ አዲግራት ተወሰደ የመሳሉ ጀኔረተሮች ወደ ትግራይ መወሰዳቸው  ‘ምጽአተ አማራ በሚለው መጽሐፍ ውስጥ በሰፊው ተዘግቧል። እላይ ካለው ጄኔረተር ፎቶ በተመለከተ አንድ ግጥም መገጠሙን ያሳያል። እንዲህ የሚል

<<አንዳንድ ብር አውጡ ፎቶ እንነሳ          እንደ ጄኔረተሩ ፋሲል ግንብ ሳይነሳ >>  (welkait.com የተለጠፈ ጽሑፍ የተገኘ) (94)

 

ሌላ ቀርቶ ላሊበላም በትግራይ ውስጥና የትግራይ ነው በማለት በቱሪዝም ሚኒሰትር ድረገጽ ማስታዊያና በ ቪዲዮ ማስታወቅያ አሳትሞታል። በዚህ ሌላ ቀን እምለስበታለሁ።

 

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

 

Tuesday, August 22, 2023

የነቀዘው አዲስ አበቤስ መች ይሆን የሚነሳው? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/22/23


የነቀዘው አዲስ አበቤስ መች ይሆን የሚነሳው?  

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay                 8/22/23


ሰላም ለሁላቸሁ ይሁን።

እህልና ሰው አንድ ነው። እንስሳ ብቻ ነው በባሕሪ ስለሚለይ የማይነቅዝና የማይበላሽ። እህል ሲበላሽ በሰበሰ ወይንም ነቀዘ እንለዋለን። እህልን የሚያነቅዘው ነቀዝ የተባለ ከእህሉ ጋር ተደባልቆ የሚኖር ተባይ ሊሆን ይችላል ወይንም የአየር ጠባይ ነው። ሕብረተሰብስብም ልክ እንደ እህል ይበሰብሳል? የነቅዛል? አዎ። ሕብረተሰብንስ የሚያነቅዘው ምንድነው? መጥፎ መሪ እና መጥፎ ሥርዓት። እነዚህም የሕብረተሰብ ተውሳኮች/ተባዮች ናቸው።

ዛሬ ያላንዳች መሸፋፈን ልክ ካሁን 28 ዓመት በፊት ይህ ሕብረተሰብ የተነበረከከ ፤ሽንፈት የተቀበለ ሕበረተሰብ ነው፡ ብዬ ስል ‘ሕብረተሰብ እየዘለፍክ ነው’ ተብዬ እንደተጨኾብኝ ሁሉ ዛሬም በድጋሚ እንድትጮኹብኝ ለመጋበዝ ሳይሆን ላመስታወስ ነው፡ (የምትጮሁብኝ ወቅት ወደ ላ ቀርቶ እነሆ እናንተ ያኔ  ስለው ወደ ነበረው የትጥቅ ትግል ገብታችልና ያ ጩኸት ታሪክ ሆኗል)።

ትዝ ይላችሁ እንደሆነ በግልጽ አማርኛ  በውጭ ያለውም ሆነ በውስጥ  ያለው ሕብረተሰባችን ከመበስበስ ባሻገር እርከኑን ተሻግሮ እንግሊዞቹ እንደሚሉት “ሯትን/ሮትን” (Rotten) እንደሚሉት በስብሶ/ነቅዞ/ረጥቦ/ የጠላት ባንዴራ እየተሰሸከመ በየአደባባዩ የንከላወት እንደነበር  ታስታውሳላችሁ (የቅርብ ትዝታ ነውና ‘ብዙዎቻችሁ የነተካፈላችሁበት ነበርና ‘ነበራችሁ ልብል’ ባይከፋችሁ)። እኛ ትግሬዎች “እጋል” “የገማ/የጠነባ” እንደምንለው ዓይነት ነበር ወቅቱ።

 ውሃ ሲሸት “አጊሉ” እንለዋለን አማርኛው “ገማ/ጠነባ” እንለዋለን። ፤ረዢም ጊዜ ሳይንቀሳቀስ እንስራ ውስጥ የኖረ ውሃም ሆኖ ነፋስ እየመታውም የሚሸት የኩሬ ውሃ አጋጥሟችሁ ያውቃል?  ከይቅርታ ጋር እንደዛው ነበር ‘አብዛኛው ማሕበረሰባችን’ (አሁንም ከገማው ስርዓት ተሸክለው እየተግማሙ ያሉ ወገኖቻችን አሉ - ለእነሱ ፀሎት እናድርስ)።

 ውሃ እንዲገማ የሚያደርገው ምንድነው? ብዙ፤ ብዙ ምክንያት አለው። ሕብረተሰብም እንዲሁ ይበሰብሳል። ሕብረተሰብ ሲበሰብስ አፍንጫን አይደለም የሚሰነፍጠው የታዛቢን ዓይንና ሕሊናን ጭምር ያሸማቅቃል።    

ሕብረተሰብ መበስበሱን የምንፈትሽባቸው መንገዶች ልክ እንደ እንቁላል በሃይለኛ የብርሃን/የጸሃይ ጨረር ውስጥ እንደምንፈትሸው ሕብረተሰብም በእዛው የመፈተሻ ብርሃን ውስጥ ገብቶ ካልተፈተሸ መበስበሱን ተሎ አያስታውቅም። እናቶቻችን እንቁላል ሲገዙ “ማገሉን” (መበስበሱን/እርግዝና ይዞም እንደሆነ ‘ፕላዝማው/ውሃው’ (የጫጩቱ እንግዴ ልጅ) አለማገሉን/አለመበላሸቱን/ ለማወቅ እያንዳንዱ እንቁላል ወደ ዓይናቸው በማስጠጋት ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ወደ ጸሐይዋ አቅጣጫ በማነጣጠር መሃል ያለው የውሃው ንጣት ወይንም ጥቁረት  በመመልከት ‘ብልሹ/የበሰበሰ’ እንቁላል ወይንም ‘ጤነኛ’ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ወይንም ወደ ጆሮ አስጠግቶ እንቁላሉን በማነቃነቅ (ሼክ በማድረግ) ከውስጥ  ያለው ውሃ ካልተነቃነቀ ረግቷል እና የበሰበሰ ነው ማለት ነው (እናቴ እንዲያ ነበር የምታውቀው)።  እንደዛ ካላደረጉ እንቁላል ከላይ ንጣቱን ብቻ በማየት መበስበሱን አለመበስበሱን ማወቅ አይቻልም።

የተበላሸ እንቁላል ሲሰብሩት በጣም ይገማል። ውሃም እንቁላልም ሲገማ ለሰው ልጆች ለምግብነት አይፈለጉትም። በዛው ትይዩ ሕብረተሰብ ሲነቅዝም ሂደቱና ባሕሪው በመለወጥ ራሱን ወደ ሞት ሂደት ያሸጋግራል። ራሱን ያበሰብሳል። ራሱን ያበሰበሰ ሕብረተሰብ ለመምራት እልክ አስጨራሽና አስተዋይ መሪ እና ታጋዮች  ይፈልጋል።

ሕብረተሰብ ሲበሰብስ ‘ተንቀሳቃሽ ግኡዝ’ ስለሚሆን ሲሰለብ/ሲበላሽ/ አይታወቀውም። የበሰበሱ መሪዎች የበሰበሰውን ሕብረተሰብ ለመስለብ እንዲያመቻቸው ሕብረተሰቡን ማበስበስ አለባቸው። ያንን ካላደረጉ “የሚጫኝ አህያ አይሆንላቸውም”።ልክ ግምበኞች/የሕንጻ መሃንዲሶች አልፈርስም ብሎ ‘ነክሶ’ ጠንክሮ  የየዘ መሰረት “ውሃ” እያፈሰሱ፤ እንዲረጥብ እያለሳለሱ እንደሚያፈርሱት ጠንካራ መሰረት ጠንካራ ሕብረተሰብንም ለማበስበስ የተለያዩ ዘዴዎች በማስተዋወቅ እንደ ዋለሃ (ዋልካ) ተፍረክርኮ “ሊጥ ሆኖ  እስከሚታጠፍላቸው ድረስ” ሃይለኛ ስራ ይሰራሉ። የሚታጠፍ ነገር “ጥንካሬ ስለሌለው”  “ሃይል” ያጣል።የሚታጠፍ ሰው ስብእናውና ሞራሉ ደካማ ስለሆነ የበታችነት ስሜት ተሰምቶት ልጠፍህ ለሚለው ክፍል ሁሉ በቀላሉ ይታጠፍለታል።ተስፋ የሚባል ትርጉም የገባው ከሆነም፤ ምህረቱና ተስፋው በዛው ክፍል ይጥላል።ያችን የተነጠቀውን ተስፋውና ሰብእናው ለማግኘት በራሱ መቆም ስላልቻለ ሰላቢዎች ወደ ጠመዘዙት ለመጠምዘዝ ምቹ ሆኖ ይገኛል።አሁን የቀሩን የተበላሹ ወገኖቻችን አብይን እያገለገሉበት ያለውን ባሕሪ በዚህ ዘዴ ነው።

 የአምሓራን ሕብረተሰብ ተነስ እያልኩ ስቀሰቅስ የነበረው ብዙ ትዕግስትና መተጣጠፍ ሲያሳይ ስለነበር ነው። አማራዎች ባትቀየሙኝ (ያለፈው ድክመታችሁን ነው እያወራሁ ያለሁት) ፤በውጭም በውስጥም የመበስበስ በሕሪ ተጠናውቶአችሁ ነበር። በራሱ የቆመ መሰረት አልነበራችሁም። ኢትዮጵያ በሚል አገራዊ ፍቅር ብቻ ሳይሆን አድርባይነት፤ አገልጋይነት፤ራስ ወዳድነትም ቸልተኝነትም፤ ተሎ አለመገንዘብንም ነበራችሁ ብል ትንሽ አትቀየሙኝ። አማራው በተለያዩ ዘመቻዎች ስለተዘመተበት በተለይ አድርባይ ልሂቃኖች ወያኔን እና ዛሬ እያደረጉት ካሉት ጥቂት ሆዳሞች አምሐራውን ስለካዱት ፤መሰረቱ የፈረሰ ሕብረተሰብ ነበር።

ስለሆነ ማንኛውም “ገምቢ እና ቤት አጣሪ” የጥበቡ ክረዲቢሊቲው (ንጣቱን/አስተማማኝነቱን ኩዋሊቲው) ሳጣያጣራ “ልገንባህ/ልጠርህ” ለሚለው የፖለቲካ ግምበኛ ሁሉ በሚሰጠው የግምባታ ፕላን  “ፈቃደኛነቱን” ይገልጽ ነበር። እሺታ እንጂ መደራደርና መርምሮ መግባት ተስፋውን የሚያጨለምበትና የሚያራዝምበት ስለሚመስለው “የተሎ ተሎ ቤት’ ግምባታ ውስጥ ገብቶ ነበር።ዛሬ ቁጭቴንም ንዴቴንም እየገለጽኩ ስለሆነ እንዳትቀየሙኝ እጠይቃለሁ። አሁን ያለው የጀግንነት ሥራ ደስታ ቢሰጠኝም  ዘግይቶ መምጣቱ ነው እየቆጨኝ ያለው!

  አዲስ አባቤውን አላነሳም፡፤ እንዲያ የነበረው ከጥይት ጋር ሲታገል የነበረው አመርቂ የምኒልክ ጀግንነቱን ሲያሳየን የነበረው ወጣት ፤ ዛሬ አማራ በተነሳበት ወቅት ውሃ ውስጥ የገባ አይጥ መሰለ፡(ይገባኛል መሪ የለውም --- ግን ቢሆንስ!?)።

 ወያነ ትግራይና ኦሮሞ ኦፒዲኦ የዛሬው “ኦሮሙማ/ብልጽግና ፓር) በባእዳን አጀንዳ እየታጀቡ በጣምራ የሕዝባችን መሰረቶች የሆኑት “ድምበሮቻችን ፤ ወደቦቻችን ፤ሰንደቃላመችን ፤ ባሕል ፤ሃይማኖት፤ ብሄራዊ ቋንቋ፤ይሉኝታና ሉአላዊ ፍቅር”(ማሕበራዊ ተቋማት የሚባሉ) መሰረታቸው አነቃንቆ እንዲፍረከረኩ አደረጉ። የተማረው ግብዝና ያልተማረው ግብዝ ሁለቱም ክፍሎች “ኢትዮጵያን” የሚመለከቱበት  ዓይናቸው  ሸፍኖ፤ የምዕራቡን ዓለም ግብረገብ (ዌስተርን ማስ ካልቸር) ተከታይ እንዲሆን አድረጓቸዋል። ከአገር ሉዓላዊነት ይልቅ “ቅዠታዊ ዲሞክራሲ” በማስቀደም ሉኣላዊነት ዋጋ ቢስ በማድረግ ዛሬም እያጃጇሉዋችሁ ነው።

አሁንም ብዙውን ኢትዮጵያውያን ልሂቃን ከመግመማታቸው አልተላቀቁም።አብሮ ለ32 አመት ያበሰበሱት ሕዝብ በተለይ አዲስ አበቤው አሁንም ብዙ ሺህ አማራና ሌላው ብሔረሰብ ዜጋ እያተፈሰ ሲታጎርና ሲደበደብ ምንም እንዳላየ “ዳንኪራ እየመታ ነው” (ልክ እንደ ቀይ ሽብሩ ዘመን)።

 እኔ ከተወለድኩበት የትግራይ ማሕበረሰብም  ቢሆን  ከነከሱት የፋሺሰት ጅቦች ጋር አብሮ መኖር ለምዶታል።ከመልመዱ የተነሳ የመውደድ አባዜው ዛሬም የተጠናወተው ይመስላል። ይመስላል ሳይሆን ኩፉኛ ለ47 አመት ድፍን “ፈጣጣ ፍቅር
ዛሬም አልለቀቀውም (ኢትዮጵያ የምታቀርብለትን ፍጆታ እየተጠቀመም ቢሆን “የሃገረ ትግራይ ምስረታው ቅዠት አልለቀቀውም)።ስለ “ጠነቡት” የትግራይ ምሁራኖች ማውሳት ቆሽት ማሳረር ነው።

የትግራይ ነገር ሳነሳ “ሐረር” ውስጥ ማታ ማታ ሲመሽ ጅቦች የሚቀልቡ ፡አድቨንቸሪስቶች” (ጀብደኞች) አሉ። ይህ ጉደኛ ትዕይንት የወያኔ ዓይነት ጅቦች ዓይነት ታሪክ ይመሳሰልብኛል። ዛሬ ዛሬ ከመቸውም በበለጠ የጐብኚዎች መስህብ እየሆነ በካሜራ እየተቀረጸ መጥቷል። ቀላቢውም ሆነ ተመልካቹ  የሳቱት ነገር ቢኖር ጅቦቹ የቀላቢውም ሆነ የተመልካቹ ህይወት “ቀሳፊዎች” እና ተቀናቃኞች መሆናቸው የመገንዘብ ሕሊናቸው “በጊዜያዊ የመጠጋጋት የጀብደኝነት እርካታ” ውስጥ ገብቶ ስለተማረከ፡ ከመጋቢያቸው እያሽካኩ በጓደኝነት ባሕሪ  የሚመገቡት “ጅቦች” ቀላቢ ሲያጡ “የገዛ ቀላቢያቸውን እንደሚበሉት ቀላቢዎቹ የተረዱት አይመስሉም።

ጅቦቹ ከቀላቢያቸው የሚፈልጉት ነገር ቢኖር ‘መመገብ’ ነው። ቀላቢዎቹ ከጅቦቹ የሚፈልጉት ነገር ደግሞ “መናከሳችሁን” አቁሙ ነው። የመጠጋጋቱ የጨዋታው ትርጉም ሲመረመር ከዚህ  ያለፈ አይሆንም። መጋቢዎቹ የዘነጉት ጉዳይ ሺ ሰንጋ ቢታረድላቸውም ልጆቻችንና ከብቶቻችንን መናከስና መብላታችሁን አቁሙ ስለተባሉ “ጅቦቹ” መናከሳቸውን ያቆማሉ ወይ?” ነው ጥያቄው።

የሁለቱ ፍጡራን ትካት (ኢንስቲንክት) የጭምትነት ባሕሪ የጎደላቸው ስለሆኑ “ነካሹም” “ተነካሹም” የተፈጥሮ ባሕሪያቸው እንደማይገጥም እያወቁ ሁለቱም እየተጠጋጉ እና “ፈራ ተባ” እያሉ በማያዛልቅ ጨዋታ ገብተው “የበይ እና የተበይ” የመገዳደል ጨዋታቸው እያሳመሩ ጅቦቹ ከጀብደኛ ቀላቢያቸው አፍ ጥርስ ተነክሶ የተንጠለጠለላቸው ስጋ “ጠጋ” ብለው በመንጠቅ ይጎርሳሉ። ይህ አስገራሚ የገዳይና የተገዳይ ጀብደኛ ጨዋታ በካሜራ ተቀርጾ ለዓለም ሕዝብ እየታየ ነው።የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ባሁኑ ሰዓት  ሕግ የማያከብር ቡድን ሥልጣን ላይ መኖሩን እያወቀ ሕብረተሱም አብሮ ሕግ አፍራሽ በመሆን የበሰበሰ እይታ ያለው ጎዳና በመጓዝ ድርድር ከማያውቅና ከሚበላው አራዊት ጋር ተጠጋግቶ የበይና የተበይ የጨዋታ ሕግጋት እያሳመረለት ለሚበላው አራዊት ሲያሞግስና ሲያለቅስለት እየታዘብን ነው ።

መለስ ዜናዊ ሲሞት በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን ያስጠሩ እና ያኮሩ የስፖርት ባለሞያዎች ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱለት፤ካንደባታቸው የተናገሩት ፍሬ ነገር ሲመዘን አገራቸውን ወክለው በዓለም መድረክ የላቀ ውጤት ሲያስመዘግቡ ሲስሟት የነበረቺው ሰንደቃላማችን እና የሃይማኖታችን ምሰሶ የሆነቺው ቅድሰት ማርያም ምስል ከጉያቸው እያወጡ ሲሳለሙ ምድሪቱን ተንበርክከው የሰገዱላት፤ሃይማኖት፤ ምድር እና ሰንደቅ ላይ መለስ ዜናዊ በኮሚኒስታዊ የፋሺስት አጀንዳው የፈጸመው ሕገ ወጥ ሥራ ከሕግ አኳያ የመመልከት አቅማቸው ደካማ መሆኑን ያሳያል።

እነ ደራርቱ ወይንም መሰረት ደፋር ….የመሳሰሉ ሯጮች ሲሮጡ ሰንደቃላማ ይዞ አብሮ ልባቸው የሮጠው ውጭ አገር ያለው ኗሪ ግለሰቦቹን ስለሚያውቃቸው ሆኖ ሳይሆን “ሰንደቃላማ እና አገር” ያስከብራሉ በሚል ነበር። ሆኖም ወያኔ ያሰራው ሰማያዊ የሰይጣኖች አምልኮት ኮከብ ያለበት ሰንደቃላማ ካልሆነ ነባሩ እና ሕጋዊው ለዘመናት የቆየ የተውለበለበ ባለ ሦስት ቀለም ሰንደቃላማ ማውለብለብ “ሕገ ወጥ” ነው ብሎ ላወጀው “ፋሺስት” መሪ  “ሲቀሰፍ” ስቅስቅ ብለው አልቅሰዋል። ስቅስ ብሎ ለፋሺሰት መሪ ማልቀስ፤ የሕገ ወጥ  ቡድን ተባባሪ መሆን ነው።ሕብረተሰብ ሲበሰብስ ሕገ ወጥ ተግባሮችን ሕግ ነው ብሎ ይቀበላል። ማሰብ ያቆማል። የበሰበሰ ሕብረተሰብ ወንጀለኞች በዘረጉለት ሃዲድ ስለሚጓዝ “ሞራል ፕርንሲፕል” በመጣስ “ላገር ታማኝነትን” ያቆማል። ምልክት በሌለው ባጭበርባሪ ጎዳና የሚጓዝ ተጓዥ ለአደጋ እንደሚጋለጥ ሁሉ፤ይህ ሕብረተሰብ ለከፋ የሞራል መበስበስ መጋለጡ ዛሬም አላቆመም።

 ይህ ታሪክ ስለሆነ ታሪክ እንዲመዘግበውና እዳትረሱት ነው የያንጸባረቁት ባሕሪ እያነሳሁ ያለሁት።ሯጮቹ ነባሩን እና ሕጋዊውን ሰንደቃላማ ከተመልካች ሲሰጣቸው ወደ መሬት እየጣሉ የወያኔን ባንዴራ ባለኮከቡ መርጠው ይልብሱ ነበር። አምደጽዮን፤ ዮሐንስ፤ ምንሊክ እና  ተፈሪ እየኖሩበት ያለውን ሰፊ አገር ሲመሰርቱ ያችን ሰንደቃላማ ይዘው ነበር ታሪክ የሰሩ። ሆኖም ዛሬ በነዚህ ኩታራዎች ወደ አፈር ሲጣል ቢያዩ ምንኛ ባለቀሱ!? ዛሬ አዲስ አበቤውና ትግሬው በተመሳሳይ የበሰበሰ ጎዳና እና ትርዕት እየተጓዘ መሆኑን ስንታዘብ ያሳዝናል።

ካነበብኩት አንድ መጽሐፍ ውስጥ ከ1500 አመት በፊት የሮም መሪዎች በመበስበሳቸው ለታላቋ የሮም መንግሥት መበታተን ምክንያት እንደሆነ አንብቤአለሁ። የበሰበሱ መሪዎች አገር ሲመሩ የበሰበሰ ሕበረተሰብ ያፈራሉ። አገር ባይፈርስም በውስጧ የታቀፈው ሕብረተሰብ አቅፈውት ሲጓዙ የነበሩት ተቋማት (ሰትራክቸሮቹ) ስለሚፈርሱ የሕሊና መፍረስ ስለሚገጥመው ባስተሳሰቡ “መካን” እና “የበሰበሰ” ማሕበረሰብ ይሆናል ማለት ነው።

ዛሬም የበሰበሰና የነቃ መሕበረሰብ ሚናው እየለየ መጥጧል።   ‘ፍትሕ’ ለሚጠይቁ ፋኖዎች ሲያናንቁት የነበረው እነሆ ዛሬ አጥራቸው ውስጥ ብቅ ሲል ባንዳዎች ሌለቱንም ሆነ ቀትር መተኛት አልቻሉም። ወንበራቸው በፋኖ ተነጥቆ ፋኖዎች ተቀምጠውበታል (እሰየው!!)። አሳምነው ጽጌ ምነው ብቅ ባልክና ፍሬሕን ባየህ!?

ትግሉ አብይ እስኪወገድ መቀጠል አለበት። “እንቅስቃሴው” እንዳይጠለፍ ሕዝብ ነቅቶ መከታተል የዜጎች ዴታ ነው እያልኩ ለአመታት የምጮኸዩኩበትን የትጥቅ ትግል አማራው ተግባራዊ ማድረጉ ቅቤ አጠጥታችሁኛል። የነቀዘው አዲስ አበቤስ መች ይሆን የሚነሳው?  

ጌታቸው ረዳ

 

 

 

 

Friday, August 18, 2023

አብይ አሕመድና የኦሮሞዊው ኢንተርሃሙዌው ዱሩየ ቡድን የመቀናጀቱ ግልጽነት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/18/23

 

አብይ አሕመድና የኦሮሞዊው ኢንተርሃሙዌው ዱሩየ ቡድን የመቀናጀቱ ግልጽነት

ጌታቸው ረዳ

                                              Ethiopian Semay          

8/18/23


በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሕዝብን በጅምላ በመጨፍጨፍም ሆነ ከውጭ ጠላት ጋር አብሮ በማበር አገራቸውን የከዱ ባንዳዎች ታሪክ በየአይነታቸው መዝግቦአቸዋል

የባንዳ ነገር ካነሳን ዘንድ፤ በኢትዮጵ ታሪክ የባንዳ ደረጃዎች ስንመለከት ምናልባትም በዓለም ታሪክ ውስጥ የአገሩን ሰንደቃላማ አውርዶ የወራሪ ጠላት ባንዴራ የሰቀለ መሪ ትግራይ ውስጥ ብቻ ነው (አብይ አሕመድና መለስ ዜናዊን እንዳሉ ለየት ባለ የክሕደት ደረጃ ሳንዘነጋ ማለት ነው) እኚህ ሰው ማን ናቸው? የአፄ ዮሐንስ 4 የልጅ ልጅ የሆኑት ደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ   ናቸው።

የአፄ ዮሐንስ 4 የልጅ ልጅ የሆኑት የደጃዝማች ኃይለስላሴ ጉግሳ ለየት ያለ የባንዳነት ታሪክ የዘገቡት አቶ ዘውዴ ረታን እጠቅሳለሁ (አሳጥሬ ነው የምጠቅሰው)

<<…. ደጃዝማቹ ለጣሊያን ካደሩ በጣሊያኑ በዱቼና በንጉሥ ቪክቶርያ አማኑኤል ሹመትራስከተባሉ በኋላ የጣሊያን ወራሪ ሃይል ዋና ዛዥ የነበረው የጄኔራል ቦኖ የጦሩ አመራርአማካሪሆኖው ሕዳር 8 ቀን 1935 . መቀሌ በጠላት እጅ ስትወድቅ ራስ ኃይለስላሴ ጉግሳ አርአያ የተሰጣቸውን የፋሺስት የጦር ልብስ ለብሰው በግንባር በመገኘትበኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቦታ የጣሊያንን ባንዴራ የሰቀሉ ራሳቸው ሆኑ …….. በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዚያ 27 ቀን 1928 . የሙሶሎኒ ጦር ዋና አዛዥ ( ቦኖን የተካው) ማርሻል ባዶግሊዮ ድል አድራጊ ሆኖ በከፍተኛ አጀብ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሲገባ፤ ከክብር ተከታዮቹ ቀዳሚ ሆኖው የታዩት ኃይለስላሴ ጉግሳ ነበሩ።>> ገጽ 180 (የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግሥት (ዘውዴ ረታ)

ኢትዮጵያ ውስጥ በታሪክ ከፍተኛ ክሕደት የሰሩ በጥንት ዘመን የተከሰቱ ክፉ ባንዳዎች የኖሩ ቢሆንም የሳቸው ግን ዓይን ያወጣ ዓለም ውስጥ ያልተደረገ የጠላት ባንዴራን ሰቅሎ የገዛ አገሩን (ያውም የወላጅ ባታቸው አፄ ዮሐንስ ያውለበለብዋት የነበረቺውን ሰንደቅ ዓላማ) አርማ አውርዶአፈር ላይ የጣለ ዜጋተሰምቶ አያውቅም። ልዩ የሚያደርገውም ይህ ድርጊት ነው።

ወደ ዛሬዎቹ ወደ እኛው ዘመነ ወያኔ/ትግሬዎች እና ወደ ዘመነ ኦሮሙማ /ኦሆዴድ ኦነጎች ብንመለከትም ከዚያኛው እኩል የሆነ ለጠላት ወግኖ ከጣለት ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ሠራዊት በመውጋትና ከነቤተሰቦቻቻው ወደ ጎዳና ተዳዳሪነትና ለማኝነት በመበተን ሆነ እንዲሁም የባሕር በርን ለጠላት መስጠትና ኢትዮጵያን ያለ ባሕር በር አስቀርቶበጠላቶች እጅ ልመና እንድትወድቅና እንድተከበብ ለከበቡዋት አገሮች ዕቃ ለማስገባትና ለማስወጣት ግምቱ የሚያስቸግር ገንዘብ በመክፍል በምጣኔ እንድትደቅቅ ያደረገ ከትግሬው ደጃዝማቹ ባንዳነት እኩል ወይንም የባሰ የሃገር ክሕደት ለማየት በቅተናል። ክሕደቱ ጥንትም ዛሬም አልቆመም። 

 የወያኔ ትግሬዎችን ክሕደት ሁሉም ያወቀው ስለሆነ እዚህ ሳላነሳ የዛሬዎቹ አዳዲስ ተተኪዎቹ ተረኞቹኦሮሞዎችበዚህ 5 አመት ብቻ (ሌላውን 27 አመት የታየው ወደ ትተን ማለት ነው) ሰማዩም ምድሩም ያወቀው ስለሆነ ዝርዝር አልገባበትም።  በአብይ አሕመድ ኦሮሙማ ፕላን 1 ፕላን 2 ፕላን 3 …እየተባለ እየተሰራ ያለው አማራ ላይ ያነጣጠረው ከወያኔዎች የቀጠለ የኢንተርሃሙዌውፕላን  ቀስ እያለ ሲሰራ ቆይቶ እነ ሌንጮ እነ / ዲማ ነገዎ እና አሰፋ ጃለታ የመሳሰሉ የኦሮሙማ አጀንዳ አቀንቃኞች እንደተናገሩት፤ እንዳቀዱትም እንደዛቱትም፤ በአብይ አሕመድ በኩል ተግባሪ በማድረግ አማራዎች ወደ አዲስ አባባ እንዳይገቡ፤ የገቡም ቀስ በቀስ ከተከበቡ በኋላ አሁን እየተለቀሙ እስር ቤትና በየት/ቤት ማጎርያ ህንጻዎች እየታጎሩ እንዳሉ የምታውቁት ነው።

ይህንንም ዕቅድ የቆየ በጥናት ሲጠናበት የነበረ ኦሮሙማዊ አጀንዳ ነው። ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ባለፈው ሰሞን በዶ/ አሰፋ ነጋሽ የተለጠፈው ጽሑፍ የነገረን፤ ይህ አሁን እየተደረገ ያለው አማራን ሰብስቦ እየለቀሙ ማጎር ቀደም ብለው ያቀዱት የኦሮሞ ፖሊተካ መሪዎች ናቸው። አዲስ አበባና አካባቢው ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች (‘ነፍጠኞች’) እየለቀምን ከሰበሰብናቸው በኋላ የመውጫ ኮሪደር (በር) ከፍተን ወደ አገራቸውእንዲወጡእናደርጋለን ብለው በተለያዩ ሰነዶቻቸውና ንግግሮቻቸው ባስቀመጡት መሰረት  መጨረሻ አዲስ አባባ እንዳይገቡና የገቡትም እየተለቀሙ ተሰብስበው እንዲወጡናኦሮሚያየተባለ አገር ለመመስረት  እንዲያመቻቸው <<ወኪላቸው አብይ አሕመድ>> ይህንን በአዋጅ ተግባራዊ እያደረገው ይገኛል ይህንን ንግግር ያደረገውም አሁን በአብይ አሕመድ ፓርላማ አባል ሆኖ የጀርመን የፓርላማ አባላትን እያነጋገረ ፎቶውን እንድታዩት የለጠፍኩላችሁ </ ዲማ ነገዎ> የተባለ እጅግ አደገኛ የኦሮሙማ ቄሮ የኢንተርሃሙዌ ቡድኖች ቀስቃሽና የኦነግ መሪ ነው።

 ከሁለት አመት በፊትውጣልኝ!” የሚል የአብይ አሕመድ ኢንተርሃሙዌው የሙዚቃ ቡድን ቅስቀሳ በማድረግ ዓለም እያየው በዩ ቱብና በመሳሰሉት ተለጥፎ ብዙየኦሮሞ ኢንትርሃሙዌ ቄሮዎችቅስቀሳውን ተግባራዊ በማድረግ በበረሃም (አማራ ላይ የዘር ጭፍጨፋ በማድረግ) በከተማም ፖሊሱ ሳይቀር ካንገቱ የክርስትና ሃይማኖት ምልክት ያለው ኢትዮጵያዊ እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የያዘና የለበሰ ሰው እየነጠቁ እየደበደቡ እስርቤት በማስገባት ለቁጥር የሚያዳግት በሺዎቹ የተማረውና ያልተማረው አምሐራዊው ክፍልም ተሰብስቦ እስር ቤት ታጉሮ እየተሰቃየ ነው።

አብይ አሕመድኦሮሙማዊው ኢንትርሃሙዌው አጀንዳተግባራዊ ለማድረግም አዲስ አባባ ብቻ ሳይሆን የአማራ ከተሞችና ገጠሮች የጦር ቀጣና ሆነው ከዚህ አማራዎቹም እየተፈጸመባቸው የነበረው 27 አመት ጭፍጨፋ ህያው ሆኖ እንደገና በመቀጠሉ የሞት ሽረት የጦርነት ፍልሚያ በማድረግ ላይ ናቸው። ድል ለነሱ እንዲሆን እመኛለሁ!!

በሚገርም ክስተት ደግሞ እየመከርናቸውእባካችሁ ተው እያልናቸውአብይ አሕመድን አምነው ብዙ አገልግሎት ሲሰጡት የነበሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ አፍረዋል። ሰውየውዊርድነው። ወደ ሰውየው የተጠጋ ሁሉይሟሽሻል፤ ይሰወራል፤ ከትግሉ ይጠፋል፤ ወይንም ግራ ይጋባል ለዚህምየማታፍርባቸው መሪዎችና የማታፍርበት ሀገር ይስጥህ ወንድሜብሏል ነገሩ አስገርሞት ወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ።

<<አፄ አቢይ አህመድ ሥልጣን ከያዘባት ከዚያች ከዕለታት ሁሉ እጅጉን የተረገመች መጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ስንትና ስንት ታላላቅ ዜጎች በዚህ ሰውዬ እጆች ተነክተው እንደበከቱብን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ አፄ አቢይ አንድን ሰው ነካው ማለት፣ አንድን ዜጋ አቅፎ ሣመ ወይም አስጠግቶ በአስመሳይ ቅጥፍጥፍ ምላሱ አነጋገረ ማለት በቁሙ ገደለው ማለት ነው፡፡ ይህ ሰይጣናዊ ፍጡር ምን ትብታብ ይዞብን እንደመጣ ባላውቅም እርሱ ወደሥልጣን ማማ ከወጣ ወዲህ የደረሰብንን ሁሉ ለመጻፍና ለመናገር ግን አራት ዓመታትም አይበቁንም፡፡ ያገሬ ሰው ይህን መሰሉን የሰይጣን ውላጅየሰንበት ጽንስየሚለው ወዶ አይደለም፡፡

አቢይ ወደውጪ ሲወጣ ሰዎች ይገደላሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ራሱን ከሰወረም ብርቅዬ ዜጎች እየታደኑ ወደ ዘብጥያ ይወርዳሉ፡፡ ኦሮምያን በዋናነት ጨምሮ አንዳንድ ክልሎች እንደፈለጉ ያሽቃንጣሉ፡፡ በክልላቸው የሚገኙ የሌላ ዘውግ አባላትን በተለይም አማሮችን እንዳሻቸው ይገድላሉ፤ ያስራሉ፤ ያንገላታሉ፤ ያፈናቅላሉ፤ ይዘርፋሉ፤ መዝረፍ ያልቻሉትን ሀብት ንበረት ያወድማሉ፤ በጥቅሉ ምስኪኖቹ ዜጎች መፈጠራቸውን እስኪራገሙ ድረስ መከራና ስቃያቸውን ያበዙባቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ ከአፄው ቡራኬና ፍቃድ ውጪ እንደማይሆን በፍቅሩ የደነዘዙ/ የነሆለሉ መረዳት ባይፈልጉም እኛ ግን ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ቅቤው አፄ ቦካሣ ሰውን ሲጨብጥ በተቆራኘው የአጋንንት መንፈስ ሳቢያ የሚነካው ሰው ሁሉ ይፈዝና ልክ ቡዳ እንደበላውና ወደጋንነት ወይም እንሥራነት ተለውጦ ዞምቤ እንደሚሆነው በድን ሰው ሁሉ የርሱ ቅን ታዛዥ ይሆናል፡፡ አሁን አሁን እርሱን ላለማየትና ላለመጨባበጥ የሚፈራ የሚጠነቀቅም ሰው ሳይበዛ የሚቀር አይመስለኝም፡፡እባብ ያየ በልጥ በረዬእንዲሉ ነውና እነዳንኤል ክብረትንና እነታማኝ በየነን የተመለከተ አፄ አቢይን ሲያይ የሚገባበት ቢጠፋው አይፈረድበትም፡፡ እኔ ለምሣሌ አይበልብኝና አቢይ ባለበት አካባቢ ዝር ማለትን በፍጹም አልሻም፡፡>>

ካለ በላ ስለ  ጉደኛው ኦሮሙማው ኢነትርሃሙዌው ቡድን እንዲህ ይላል፡

<< …..ከፍ ሲል የጠቀስኩትን ምሥጋናዊ ጸሎት ወይንም ጸሎታዊ ምሥጋና ይበልጥ እንድገፋበት የሞራል ብርታት የሰጠኝ ደግሞ የዛሬ ሁለት ይሁን ሦስት ዓመታት ገደማውጣልኝ!” በሚል ርዕስ በዩቲብ የወጣው የኦሮሙማ ክሊፕ ነው፡፡ በዚያ ክሊፕ ውስጥ በጣም ብዙ ሰው ተሳትፏል፤ አንዳችም ሳያፍሩ ነው ታዲያ፡፡ ደራሲውም፣ አቀናባሪዉም፣ ዘፋኙም፣ ሙዚቀኞቹም፣ አጃቢዎቹም፣ ጨፋሪዎቹምምንም አያፍሩም፤ እኔ ግን ስለነሱ የምገባበትን አጣሁ፡፡ ያን ክሊፕ ያዬ ጤናማ ሰው - ኦሮሞም ይሁን ትግሬ ወይም ሌላ - ኦሮሙማዎች ምንኛ በዘረኝነት ደዌ እንደሚሰቃዩ ይረዳል፡፡

አሁን ባለኝ የአስተሳሰብና የአመለካከት ይዞታ ላይ እንዳለሁ ኦሮሞ ብሆን ኖሮ ያን ክሊፕ ሳዳምጥ ምን ይውጠኝ ነበር ብዬ ሳስብ አለማሰቡን ብቻ መረጥኩ ወንድማለም፡፡ በዘፈኑ ርዕስ ጉግል አድርጉና ያን ብዙ ኦሮሞ በደስታ ሲቃ እያነባ የሚዘፍነውንና የሚጨፍርበትን ዘፈን አድምጡት - አማራን አሁን በምናየው ፍጥነት ከአዲስ አበባ ለማውጣት ነው የዘፈኑ ማዕከላዊ ጭብጥ፤ በዘፈኑ የተገለጸው ቁም ነገር እኮ ነው እየተተገበረ ያለው። በነገራችን ላይ የሽመልስ ትንቢትና ፖለቲካዊ ዕቅድ እኮ ነው አሁን በተግባር እየተገለጠ የሚገኘው - ለታዛቢ ቀልድ ሊመስል ይችላል፡፡ ግን እውነት ነው፡፡ የኦሮሙማ አስፈሪ ገጽታ ደግሞ ይሄ ነው፡፡

ዘፈኑን ስሙት ብያችኋለሁ፡፡ ያኔ - ዘፈኑን ስትሰሙት - ኦሮሙማ ማለት - ጽንሰ ሃሳቡ ራሱ - ከጥልቁ የዲያቢሎስ ጽልመታዊ መንግሥት እንደመጣ ትረዳላችሁ፡፡ ያኔ አቢይና ሽመልስ የጥልቁ ተወካዮች ብቻ ሳይሆኑ ሊቀ ሣጥናኤል በሰው አምሳል ኢትዮጵያ ውስጥ በነሱ አካል በግልጽ እንደተከሰተ ትገነዘባላችሁ፡፡>> ብሎ ነበር ዳግማዊ ጉዱ ካሳ በዚህ ፌስቡኬ የተለጠፈው።

ትዝ ይላችሁ እንደሆነ እኔም

<<፡ኢትዮጵያዊያን ከአዲስ አባባ እየተገደሉ እንዲባረሩ አብይ አሕደመድ በነፃነት እንዲዘፍን የፈቀደለት የኦሮሞው ዘፋኝና መባረርን የተቃወመው ኢትዮጵያዊው ዘፋኝቴዲ ለምን ተለይቶ ታሰረ? >> ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/30/2022 በሚልውጣልኝየሚለው ኦሮሞዎች እየዘፈኑ አማራውን የማባረር ዘመቻ ያደረጉበትን በይፋ የተሰራጨ ቪዲዮ አቅርቤላችሁ ነበር። ያንን ጉደኛውን <<የኦሮሞዊው ኢንተርሃሙዌው ቪዲዮ>> እና አሁን አዲስ አባባ ውስጥ እየታፈሰ ወደ ማጎርያ እየገባ ያለው አምሐራዊው ሕዝብ <<የአብይ አሕመድ እና የኦሮሙማው ቄሮ የኢንተርሃሙዌው ዱሩየ የሙዚቃ ቡድን>> የመቀናጀታቸው አጀንዳ በግልጽ ዛሬ ህያው ሆኖ እያያችሁት ነው።

 በዚህ ቪዲዮ የምታደምጡትፈጣጣ ወንጀልዛሬ አብይ አሕመድ አዲስ አባባ ውስጥ ተግባራዊ እያደረገው ነው ስንል ከምንም ተነስተን አይደለም። በየዘመኑ በርካታ ከሃዲዎች ኢትዮጵያን ሲክዱ ታይተዋል። አዳከምዋት እንጂ አልገደልዋትም። ከሃዲዎች በየዘመኑ ያሳዩን ክስተቶች ታሪክ መዝግቦአቸዋል፤ ዛሬም የእነዚህ ከሃዲዎች ገመና ይመዘግባል።

ጽሑፉን ማሰራጨት አይሰልቻችሁ፤ ለዘመዶቻችሁ ህልውና ስትሉ እንጂ ለኔ ስትሉ አይደለም፡ እኔ በተመቸ ዓለም ውስጥ እኖራለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቻው ረዳ (Ethiopian Semay)