ቴድሮስ
ፀጋዬ መስከረም አበራን ለመሞገት የኢሳያስ አፈወርቂን የትግርኛ ንግግር ለምን ማጣመም አስፈለገው?
ጌታቸው
ረዳ
(Ethiopian
Semay)
10/9/2022
የርዕዮት ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴድሮስ ፀጋዬ “የመስከረም አበራ የማያነጽር መነጽር . . . | ይድረስ ለዘር ጭፍጨፋ አስቻይ
እና አስተባባይ አንደበቶች” በሚል ርዕስ በ 10/07/22 መምህርት መስከረም አበራ በልደቱ አያሌው በትግራይና ኤርትራ እንዲሁም
ኢትዮጵያን አስመልክቶ በፃፈው ጽሑፍ ላይ አስምለክታ “ንቃት ሚዲያ” በተባለው የምትቀርብበት ሳምንታዊ ቃለ መጠይቅ ላይ “ኤርትራኖች
ትግራይ ውስጥ የገቡበት ጦርነት አስመልክታ” በሰጠቺው አስተያየት ቴድሮስ ፀጋየ አልተስማማበትም። ስለሆነም እንደተጠቀሰው ርዕስ
በራሱ ሚዲያ ሰፊ ትችትና ተቃውሞ አቅርቦባታል።
ስለ ሰነዛራቸው ሃሳቦች እራስዋ የመመከት እቅም ስላላት እኔ ጣልቃ አልገባም (በቴድሮስ ንግግሮች ላይ ካሁን በፊት አንዴም
ሁለቴም በግሌ ስለተቸሁት መስከረምን ደግፌ መተቸት አላስፈለገኝም። ዛሬም ብዙ ስሕተቶች አድምጬበታለሁ፤ ቦታው የኔ ስላለሆነ እራስዋ
መልስ ትስጥበት)። ያስገረመኝ እና አጣምሞ የኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ትግራይ ገብቶ የትግራይን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ምክንያት አድርጎ
የገባበት የኢሳያስ ንግግር ብሎ ቴድሮስ የተከራከረበትን ከትግርኛ ወደ አማርኛ ለአድማጮቹ የተረጎመው የተጣመመ ትርጉም ለምን ማጣመም
እንዳስፈለገው ስለገረመኝ ትክክለኛውን ትርጉም ወደ አማርኛ ተርጉሜ
አቀርብላችሗለሁ።
ቴድሮስ የተጠቀመበት ከኢሳያስ አፈወርቂ ተወሰደ ያለው የንግግር ትርጉም እራሱ ይተርጉመው ሌላ ሰው ይተርጉምለት ባለውቅም፤
ቀጥተኛ ትርጉም ያልሆነ እና ከተነገረው ንግግር የማይሄድ ስለሆነ
የኔን ትርጉም፤ ለናንተም ለቴድሮስ አቀርባለሁ።
መስከረም አበራ የኢሳያስ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ በጦርነቱ
ለመሳተፉ ምክንያት የትግራይን ሕዝብ እፈጃለሁ ብሎ ሳይሆን የኔን መንግሥት ገልብጣችሁ ሌላ መንግሥት ለማስቀመጥ እየዛቱብኝ ነው
የሚል እምነት ስላለው ስጋት ናቸው ብሎ አምኗል፡ በተጨማሪም የባድሜን
መሬት አስምልክቶ የመሳሰሉ ምክንያቶች ወደ ጦርነቱ መግባት ምክንያቶች እንጂ የትግራይን ሕዝብ እንዳለ ለመጨፍጨፍ ፍላጎት ኖሮት
አይደለም…. የሚመስል አባባል በመናገርዋ ቴድሮስ ፀጋየ ደግሞ ምክንያቶቹ መስከረም የጠቀሰቺው ሳይሆን “ፖለቲካዊ አጠባ” በሚል ነው ወደ ትግራይ የገባው
ሲል በዘለፋ ክፉኛ ይከራከራታል።
ቴድሮስ ደግሞ ‘’የመሬት ችግር ኖሮት አይደለም “አያሳስበኝም” ብሎ እራሱ ተናግሯል ሲል የኢሳያስ አባባል አንሻፍፎ ተርጉሞታል። ኢሳያስ ደግሞ የሚለው ይህንን ለመፍታት መሬታችን የትም አይሄድም ፤ ለጊዜው ይህ የተገኘው ሰላም እንዳይበላሽ እየተነጋገርን እንፍታው ብለን ለጊዜው ቀለል አድርገን በጎ ነው ብለን ስናስብ ወያኔ ግን በአንጻሩ ዛቻ፤ ነገር ቁስቆሳ እና ጦር ማከማቸቱን ተያያዘው። በዛላምበሳና በደቡብ በኩል (ዓሰብ) በኩል ያለው ብዙም ቀልቤን አላሳሰበኝም ፤ በምዕራቡ በኩል ማለት “በኡምናሓጀር” ያለው ትኩረቴን ስለሳበው፤ አብይ አሕመድ ደግሞ እኔን እየገፋፋኝ እባክህን አነጋግራቸው ዕርቅ አድርጉ እያለ ሲገፋፋኝና ሲወተውተኝ ስለነበር “ሦስተኛ አካል ባያስፈልገኝም፤ እንግዲያውስ ካልክ ብየ “እምሓጀር” ላይ ለመገኘት አይመቸኝም ብየ ነበር ሆኖም አንድ ቀን ሲቀረው (በዋዜማው ላይ) ሓሳቤን ቀይሬ፤ “ምን አለ እስኪ መልዕክቴንም ላስተላልፍላቸው” እሺ ብየ እግረመንገዴም ለምን የጦርነት ዝግጅት ማድረግ አስፈለጋችሁ ብየ ደብረጽየንን የመጠየቅ ዕደል አገኛለሁ ብየ፤ ‘አንድ ሁለት ደቂቃ ይሆናል ድግስ ላይ ተነጋገርን። “ደብረጽዮን ለምንድነው የጦርነት ዝግጅት ማድረግ ያስፈለጋችሁ?” ብየ ብጠይቀው “አይሆንም!!” አለኝ፤ ለምን ብየ ብለው “አይሆንም!!” ብሎ መለሰልኝ’ እኔም “ባሁኑ ወቅት ‘ጦርነት’ አያስፈልጋችሁም” ብየ መለስኩለት። ከዚያ ነገሩ እንደማያምር ተረዳሁኝ።
ከዚያም
ዓለም ታይቶ የማያውቀው እራሳቸው 27 አመት ሲያስተዳድሩት የነበረው 3/4 የአንድ ሀገር ሰራዊት ሰሜን ዕዝ የነበረው
ያውም ከ30 እስከ 35 ሺሕ የሚገመት የሰሜኑ ዕዝ ሠራዊት ውስጥ ¾ኘው ትግሬዎች የሚበዙበት ነው፤ በሕዳር 3/3020 (ጥቅምቲ
24/2014) ማንም ባልጠረጠረው ዓለምን ያስደነገጠ “ዕብደት” ጦሩ በተመደበባቸው የተለያዩ ጦር ካምፖች ከብበው ጨፈጨፉት። እጃቸው
አንሰጥም ብለው ተታኩሰው ከበባውን ሰብረው ወደ ኤርትራ የተሻገሩ ጦሮች ተቀበልናቸው። ከዚያም ሕዳር 4 ወደ ኤርትራ ሚሳይሎች መተኮስ
ጀመሩ።///”እያለ… ኢሳያስ ሁኔታዎችን ይዘረዝራል።
ቴድሮስ ፀጋየ ግን ኢሳያስ ወደ ትግራይ የገባበት ምክንያት ‘’የፖለቲካ አጠባ’’ ለማድረግ ነው ይልና ኢሳያስ የተናገረውን
ድምጽ በትግርኛ ለአድማጮቹን ያስደምጣል።
የተደመጠው ዜና ፤ የኢሳያስ ትግርኛ የድምፅ ቅጅ ደምፂ ሓፋሽ ከሚባለው የኤርትራ ራዲዮና ቴ/ቪ ጣቢያ (ጋዜጠኛ ገብረዝጊሔር)
ያነበበው ደግሞ እንዲህ ይላል።
<<”ወያነ ዝፈጠሮ ፖለቲካዊ ጸወታን ኣሽካዕላልን ኣኽቲሙ እዩ።’’ ዝበለ ፕረዚደንት ኢሳያስ ፤ ንሱ ዝፈጠሮ
ሓድጊ ንምጽራይ ፖለቲካዊ ሕጽቦ ንምክያድ ግን ዑቱብን ንቑሕን ጻዕሪ ከምዘድሊ አስሚሩሉ።”>>
ወደ አማርኛ ትርጉም፡
<<“ወያነ የፈጠረው ፖለቲካዊ ጨዋታና ልግጫ (ማላገጥ)
አክትሟል።’’ ያለው ፕረዚደንት ኢሳያስ’ አርሱ (ወያኔ) የፈጠረው ቅሪት (አስተሳሰብ/ፖለቲካዊ አይዲኦሎጂ) ለማጥራት የፖለቲካ
አጠባ ለማካሄድ ግን ንቁ የሆነ ጠንካራ ጥረት እንደሚያስፈልግ
አስምሮበታል>>” ይላል።
በቅንፍ ያስቀመጠኩዋቸው ትርጉሞች ይበልጥ ለማብራራት አጽንኦት ለመስጠት የተጠቀምኩባቸው ቃላቶች ናቸው።
ከላይ የተረጎምኩት የኢሳያስ የትግርኛ ንግግር ወደ አማርኛ መተርጎም ያለበት ትክክለኛ ትርጉም ይህ ነው። በሚገርም ሁኔታ
ግን ቴድሮስ ጸጋዬ ደግሞ ኢሳያስ ወደ ትግራይ እገባለሁ ያለበት ምክንያት ከትርጉም ውጭ ንግግሩን አጣምሞ አቅርቦታል። የቴድሮስ
ትርጉም እንዲህ ይላል።
“<መስከረም አበራ የቶክስ ሽፋን የምታደርግለት ሻዐብያን ኢሳያስ ወደ ትግራይ የገባበት ምክንያት ፖለቲካዊ እጥበት
ለማካሄድ ነበር የገባው እንጂ የአልጄሪስ ስምምነት ምናምን አይደለም። ሻዕቢያ ወደ “ትግራይ ገባሁ” የሚለን “ፖለቲካዊ እጥበት
አካሂዳለሁ” ብሎ ነው። ይህ እኔ አይደለሁም የምለው ዋናው መነሻ በራሱ ኦፊሴላዊ ሚዲያ የተነገረ ነው። “የፖለቲካ እጥበት” ለማካሄድ እንደገባ ነው የነገረን። መሰረት አበራ የምታገኟት ከሆነ ጥርጣሬ
ከገባትም ተርጉሙላት።>> ባለን መሰረት እኔም ድንገት የኔን
ፌስቡክ የምትጎበኝ ከሆነ እንሆ ተርጉሜላታለሁ።
ቴድሮስ በመቀጠል፤ እንዲህ ይላል፦
<<ትግራይ ውስጥ የፖለቲካ እጥበት ለማካሄድና እንሻለን እንሰራለንም።በላቀ
ደረጃ እየሰራንበት ነው፡”.. ይላል; ካለ በሗላ በኤርትራ የዜና ማሰረጫ የተላለፈው የኢሳያስ ንግግር ዜና “አውድዮ ድምፅ” ቴድሮስ
እንደማስረጃ ለአድማጮች እንዲሰሙት አድርጓል።
ቴድሮስ እንደሚለው <<“ኢሳያስ ወደ ትግራይ የገባባት ምክንያት ‘የፖለቲካ አጠባ’ ለማካሄድ ወደ ትግራይ እገባለሁ”>> የሚል አንዳችም ፍሬ ቃል በኢሳያስ ንግግር የለም።
ወያኔ የተወውን አስተሳሰብ ለማጥራት ተግባራዊ ጥረት እንደሚያስፈልግ እንጂ
“ወደ ትግራይ ገብቼ የፖቲካዊ እጥበት አደርጋለሁ አላለም። <<“ወደ ትግራይ ገብቼ የፖቲካዊ አጠባ አደርጋለሁ”>>
ብሏል ብሎ ያልተባለ ንግግር አጣምሞ ቴድሮስ ለምን መተርጎም እንዳስፈለገው አልገባኝም። “ወያኔ የተወውን አስተሳሰብ ለማጥራት ተግባራዊ
ጥረት እንደሚያስፈልግ” ገልጿል ማለት <<“ወደ ትግራይ ገብቼ የፖቲካዊ አጠባ አደርጋለሁ”>>ብሎ ተናግሯል የሚለው
ቴድሮስ ባቀረበው የኢሳያስ ንግግር ቴድሮስ ሊጠቁመን አይችልም።
በመቀጠል ቴድሮስ ፀጋዬ የፖለቲካ እጥበት ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ሲያብራራ የሚከተሉት ክስተቶችን ለማከናወን እንደሆነ
በሚከተለው ይገልጸዋል።
1) የፖለቲካ እጥበት ቆሻሻ ያውን ማስወገድ
2)
…. (?) ታሃትያን (?) ተደርገው የተፈረጁ ያላቸውን ገድሎና ፈጅቶ የሚከናወን ቀጥተኛ የሆነ የልሂቃን
ኤክሰተርሚነሽን የፍጅት ዕቅድ ነው።
3) ይህም በትግራይ ውስጥ ከአቡነ አረጋዊ የጥዋ ማሕበር በላይ ምንም አይነት የፖለቲካ አደረጃጀት እንዳይኖር የማድረግን እቅድ ያካትታል።
በማለት ተርጉሞታል።
እኔ በትርጉሙ ላይ አልስማማም። ስለ መስከረም ወክየ ባልሆንም ፤ ቴድሮስ እንደሚለው ኢሳያስ እነዚህን ሦስት ነገሮች ለማካሄድ እገባለሁ ብሎ ኢሳያስ ገብቷል የሚልበት አተረጓጎም የኢሳያስ ሙሉ ድምጽ አላቀረበውም ቆርጦ ነው የቀረበው። በድምጹ ቅጂ ላይ ተከትሎ ቴድሮስ ተሎ የቆረጠው “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊት ኢትዮጵያ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የያዘው የአመለካካት ጥራትና አሰራር ያሞገሰው ፕ/ኢሳያስ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ሕዝቦች…..>> ከሚለው ንግግር ሳይቀጥል ቴድሮስ አውድዮውን ቆረጠው። ሙሉውን ቢያስደምጠን የፖለቲካ አጣባ ማካሄድ ያለበት ማን እንደሆነ አባባሉ ግልጽ ይሆን ነበር።
እዚህ ላይ ለማለት የፈለግኩት ግልጽ ላድርገው የኢሳያስ “ወያኔ የተወውን የአስተሳሰብ ቅሪት ለማጥራት ተግባራዊ ጥረት ለማካሄድ ንቁ የሆነ ተግባራዊ ጥረት እንደሚያስፈልግ” ሲገልጽ ከላይ የጠቀስኩት የተቆረጠው ኢሳያስ ስለ አብይ አህመድ” የሚጠብቀው የፖለቲካ አጣባ ስራ የያዘው የአመለካካት ጥራትና አሰራር “ወያኔ የተወውን ያስተሳሰብ ቅሪት አብይ የፖለቲካ አጣባው ተግባራዊ ጥረት እያደረገ ወይንም ማድረግ እንደሚያስፈልግ ከባድነቱን” እየመከረ ወይንም እያደነቀ ይሁን እየጠቆመ ከሆነስ አድማጭ እንዴት ልያውቅ ይችላል። አውድዮው ተቆርጧል። በመቆረጡ ምክንያት “ፖለቲካዊ አጠባው ጥረት አስፈላጊነት” ከአብይ ጋር/ኢትዮጵያ የተያያዘ ከሆነስ በምን እናውቃለን ነው፡ እንደ አድማጭ የምጠይቀው።
የሆኖ ሆኖ ቴድሮስ የተረጎመው የኢሳያስ የትግርኛ ንግግር ኢሳያስ <<“ወደ ትግራይ ገብቼ የፖቲካዊ እጥበት አደርጋለሁ ብሎ ነው የገባው”>> ወይንም “የፖለቲካ እጥበት ለማካሄድ ወደ ትግራይ እገባለሁ ብሎ ተናግሯል” የሚለው የቴድሮስ ትርጉም በኢሳያስ ንግግር ላይ አንዳችም ቃል “ትግራይ” ወይንም “እገባለሁ” ወይንም “ለማካሄድ ገብቻለሁ”… የሚል ቃል የለበትም፤ አልተናገረም፤ አልዛተም”።
4)
በሚገርም ሁኔታ በተራ ቁጥር 2 እና 3 የቴድሮስ የፖለቲካ አጠባ ትርጉም በራሱ መንገድ እንጂ ኢሳያስ
ትግራይ ውስጥ ገብቶ ከአቡነ አረጋዊ የጥዋ ማሕበር በላይ ምንም አይነት የፖለቲካ አደረጃጀት እንዳይኖር የማድረግ እቅድን ያካተተ
ነው የሚለው ኢሳያስ ንግግር አንዳችም እንዲህ የሚል ቃል/ዛቻ/ የለም። የኢያሳስ ዕቅድ ነው ብሎ እራሱ በተረጎመውም ቢሆን የፖለቲካ
አጠባ ብዙ መልክ ያለው እንጂ ቴድሮስ እንደተረጎመው አይደለም።
የፖለቲካ አጠባ “ቆሻሻ ያለውን ማስወገድ” ብሎ ቴድሮስ ሲል ሰው እንዳልሆነ
እገምታለሁ። ቆሻሻ አስተሳሰብን ማስወገድ ብሎ ግልጽ ቢያደርገው ጥሩ ነበር።
በተራ ቁጥር 2 የተረጎመው ትርጉም “….ጠላት ተብለው የተፈረጁ ያላቸውን ገድሎና ፈጅቶ የሚከናወን ቀጥተኛ የሆነ የልሂቃን ኤክሰተርሚነሽን የፍጅት ዕቅድ ነው’’። የሚለው እንደ ማስረጃ ያቀረበው ደግሞ እንዲህ ይላል፦ “ጉምት የሻዕቢያ ባለሥልጣኖች ካሁን በፊት ይህንን ተናግረዋል” ሲል ለትርጉሙ እንዲመች አስቀመጦታል። ሆኖም ይህ የዛቻ ንግግር እንጂ “የፖለቲካ እጥበት አይደለም። የፖለቲካ እጥበት አንድን ማሕበረስብ ያለውን አስተሳሰብ በራስህ መንገድ እንዲጓዝ መቆጣጠር እንጂ “ቀጥተኛ የሆነ የልሂቃን ጭፍጨፋ ዕቅድ ነው” ተብሎ ከፖለቲካ አጠባ ጋር በማያያዝ መተርጎም ስሕተት ነው።
የፖለቲካ ፕሮፓጋምዳ ወይንም የፖለቲካ እጥበት ማለት “አስተሳሰብን መለወጥ/አስተሳሰብን
ማሳመን መቆጣጠር/ ማለት አንጂ “መጨፍጨፍ” አይደለም። መጨፍጨፍ ግብራዊ ነው። እጨፈጭፋለሁ ካለ “የዛቻ ንግግሮች ናቸው እንጂ’
‘የፖለቲካ እጥበት’ ማለት አይደለም። የፖለቲካ እጥበት ጊዜ የሚፈጁ ትምህርታዊ፤ሰበካዊ አስተሳሰባዊ ሕሊናን የመለወጥ ክንዋኔዎች
ናቸው። ፖሊካዊ አጠባ ለማድረግ ኢሳያስ ወደ ትግራይ እገባለሁ ብሎ
ከነበር ‘ከትርጉሙ ቀጥተኛነት ፖለቲካዊ ሰበካ ፤አስተሳብን በሰባካ/በትምህርት/በስብሰባ ማሳመን” እንጂ ትግራይ ውስጥ ተደረገ የሚባለው
ጭፍጨፋ ቅጽበታዊ ወይንም የነበረ የፀብ ውጤት እንጂ “የፖለቲካ እጥበት” ውጤት አይደለም።ሊሆንም አይችልም።
ፖለቲካዊ እጥበት (ፖለቲካዊ አጠባ) ለምሳሌ አገራችን ውስጥ የፕሮተስታንት
ፓስተሮች “እየሱስ አብይ አሕመድ የተባለ 15 አመት/30 አመት ኢትዮጵያን ያስተዳድራል ለአብይ አሕመድ ተገዙ ፤ ወዘተ….. ወዘተ…
እያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ እንዝሕላሎችን አዳራሽ ላይ ሰብስበው ሲሰብኩና ሲያስጨፍሩ እናያለን፡ ያ ስብከት ፖለቲካዊ አጠባ ወይንም
የፖለቲካዊ እጥበት አንዱ ገጽታው ነው። የፖለቲካ አጠባ ማለት ስብከት ማለት ነው፤መቆጣጠር ማለት ነው። ሌላ ትርጉም የለውም።
ሲጠቃለል፡ <<<<“ወያነ የፈጠረው ፖለቲካዊ ጨዋታና ልግጫ (ማላገጥ) አክትሟል።’’ ያለው ፕረዚደንት ኢሳያስ አርሱ (ወያኔ) የፈጠረው ቅሪት (አስተሳሰብ/ ፖለቲካዊ አይዲኦሎጂ) ለማጥራት የፖለቲካ አጠባ ለማካሄድ ግን ንቁ የሆነ ጠንካራ ጥረት እንደሚያስፈልግ አስምሮበታል>>” የሚለው የኢሳያስ ንግግር
ቴድሮስ በማጣመም <<“ዋናው መነሻ በራሱ (በኢሳያስ) ኦፊሴላዊ ሚዲያ የተነገረ ነው። “የፖለቲካ እጥበት” ለማካሄድ ወደ ትግራይ እንደገባ ነው የነገረን።>> የሚለው ቴድሮስ ፀጋዬ ንግግሩን ለራሱ እንደሚመች አድርጎ ተርጉሞት ካልሆነ በስተቀር ባስደመጠን አውድዮ በኢሳያስ ንግግር ላይ አንዳችም ቃል “ትግራይ” ወይንም “እገባለሁ” ወይንም “ለማካሄድ ገብቻለሁ”… የሚል ቃል አላነሳም ፤ የለበትም፤ አልተናገረም፤ አልዛተም፤አልተደመጠም”።
ዕጥበት ማለት የነበረውን አስተሳሰብ በአዲስ ለመለወጥ የሚደረግ የሕሊና ሰበካ ነው። ወያኔ ደግሞ ብዙ መጥፎ ያስተሳብ ቅሪቶችን ፈጥሯል። ያንን በፖለቲካዊ እጥበት መቀየር የሁላችንም ፍላጎት ነው።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment