Tuesday, October 4, 2022

ትችቴ “ጦትነት በቃን በል!” ስለ ሚሉት የኢትዮ 360 ሚዲያ የፖለቲካ ተንታኞች ምክር ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 10/5/2

ትችቴ “ጦትነት በቃን በል!” ስለ ሚሉት የኢትዮ 360 ሚዲያ የፖለቲካ ተንታኞች ምክር

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 10/5/22


 ስለ ማከብራቸው የኢትዮ 360 ሚዲያ የፖለቲካ ተንታኞች ሌት ተቀን ሰለቸን ሳይሉ መረጃዎችን በወቅቱ ለሚያቀርቡልን እና በበሰለ ትንተና ለሚያስተምሩን የኢትዮ 360 ሚዲያ የፖለቲካ ተንታኞችና አባላት ትችት ሳቀርብ የምር እንደምቃወማቸው አድርጋችሁ አንባቢዎቼ አንደማትወስዱት ተስፋ አለኝ። እኔ ደጋፊያቸው ነኝ። ይህ ትችት ለማንኛቸውም ተንታኞች እንደማቀርበው ትችት ሁሉ የመልስማማባቸው ነገሮች ሳደምጥ ግን መተቸቴ የምትከታተሉኝ ሁሉ አዲስ ነገር እያደረግኩ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ እና በገምቢ ሃሳብ ይወሰድልኝ።

 በትችቴ ላይ ሃብታሙ አያሌውን እጠቅሳለሁ። ከሃብታሙ የምለይበት ምክንያትና ሃብታሙን ስተች  “ፋሺሰቱና የዘር ማትፋት ወንጀለኛው ተፈላጊና በሥልጣን ባላጊው አብይ አሕመድ እና በእሽክርና ታሪክ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ያልታየው “ብአዴን” የተባለው “ሎሌ” ድጋፍ መስጠቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።  

አሁን ወደ ትንተናው።

Ethio 360 Zare Min Ale "በደም የጨቀየ ጦርነት!" የ UN ሚስጥራዊ ዶክመንት Sunday Oct 02, 2022

ባሰተላለፈው ትንተና ወንድም ሃብታሙ አያሌው  እንዲህ ይላል፦

“……ይሄ ስብስብ በሚመራው ጦርነት (አብይ እና ብአዴን ማለቱ ነው) ጦርነት በቃን! ጦርነት መቆም አለበት ወደ ጦርነት እየማገድከን ነው! ብሎ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ማስተጋባት አለበት!.....ጦርነትን አቁም ሲባል፤ ሆን ብለህ የሰሜኑን ክፍል እያፈራረስክ ነው ያለኸው ተብሎ መመጎት ነው። …ተወደደም ተጠላም ሰሜን ላይ ያለው ጦርነት ሰሜን ላይ ባሉ ተገዳዳሪ ሃይሎች ላይ ነው ጦርነቱ እየተካሄ ያለው። ምክንያቱም ጦርነቱ ሰሜን ላይ ነው ያለው።…..የአማራ ሕዝብ ሕዝባ ሃይል ቢመሰርት እና (ከስብስቦቹ አማራር ቢላቀቅ)፤አብይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚጫወተው ቁማር ያቆማል።….“…(አማራው) የማንም ጥገኛ ሆኖ ሳይሆን፤ በቂ አቅም ይዞ የሕዝቡን ፍላጎት ከሚወክሉት አካሎች ጋር የሚገባባት፤ በሃይል እምቢ ብሎ ለመጣም ራሱን ለመከላከል በሃይል  የሚያስከብርበት በቂ ሃይልና የትግል መስመርና አደረጃጃት ከመፍጠር ውጪ አማራጭ የለውም።”

  ባለው  ሃሳብ የምለይበትና የምስማማበት ሃሳብ አለ።

እስኪ  “……ይሄ ስብስብ በሚመራው ጦርነት (አብይ እና ብአዴን ማለቱ ነው) ጦርነት በቃን! ጦርነት መቆም አለበት ወደ ጦርነት እየማገድከን ነው! ብሎ ሕዝባዊ እምቢተኝነት መስተጋባት አለበት!.....ጦርነትን አቁም ሲባል፤ ሆን ብለህ የሰሜኑን ክፍል እያፈራረስክ ነው ያለኸው ተብሎ መመጎት ነው።…” በሚለው እንመልከት።

ጦርነት በቃን ጦርነት ይቁም፡ ተብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ቢወጣ እንኳ ሁለቱ ሽፍቶች ይህንን አቤቱታ የማድመጥ ፍላጎትና ባህሪ አላቸው ወይ? የሚል ጥያቄ አቀርባለሁ። ባለፈው ወር ከተማውን ዘነጋሁት “ጦርነት ይቁም” የሚል እህቶችና እናቶች ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ አይተናል። ሆኖም ሰሚ የለም። ወያኔ አንደሆነ የምታውቁት ታሪኩ “ከመሃል አገር ወደ ሰሜኑ መቀሌ የተላኩ ሽማግሌ እናቶችና አባቶች በሚያስነውር ትምክሕት ወያኔ እንዴት እንዳልተቀበላቸው የምታስታውሱት ታሪክ ነው። እንበለውና አሁን አማራ ወጣት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ቢስማማ እና ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግ እነ አብይ እና ወያኔዎች የሚያደምጥ ጀሮ አላቸው ወይ? መልሱ “የላቸውም፡ አይሰሙም”። ይልቁንም ያስራቸዋል። ሲታሰሩ በጠመንጃ የአጸፋ መልስ የመመለስ አቅም አላቸው ወይ? የሚለው ብንጠይቅ “ፒ ፒው አብይ አሕመድ ትቀፈደዳለህ እያለ እንደሚዘባበተው “ከመቀፍድ ውጪ ወጣቱ አቅም ሲያሳይ አላየንም””

ጦርነት ይቁም ማለት ክፋት ባይኖሮውም፤ ጦርነት የተከፈተበት ማሕበረሰብ በጦርነት መመከት እንጂ አትውጉን፤አታዋጉን ብሎ መጠየቅ ያውም “ውሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ” እንደመጮህ አይሆንም ወይ? “አብይ እና ወያነ” እየነከሱትና እያስነከሱት ያለውን ማሕበረሰብ አቤቱታ ማድመጥ ከቶ ተፈጥሮአቸው ይፈቅዳል ወይ?

ጦርነቱነም ለማስቆም ሦስት መፍትሄዎች አሉ።

1)   

 አማራው መንቃት ፤መደራጀት እና መታጠቅ።

2)   በሕዝባዊ አመጽ ስርዓቱን በማስበርበድ ለውጥ አምጥቶ

ጦርነቱ መልክ ማስቀየር/መቆጣጠር/።

3)   ሥርዓቱ በሚተልምላቸው ዕቅድ አለመነዳትና አለመሳተፍ

 በተራ 1 የተጠቀስኩት ታጥቆ ምን ለማድረግ የሚል ጥያቄ ብታቀርቡልኝ ቅድም ሃብታሙ አያሌው እንዳለው ‘’አማራው የማንም ጥገኛ ሆኖ ሳይሆን፤ በቂ አቅም ይዞ የሕዝቡን ፍላጎት ከሚወክሉት አካሎች ጋር የሚገባባበት፤ በሃይል እምቢ ብሎ ለመጣም ራሱን ለመከላከል በሃይል  የሚያስከብርበት በቂ ሃይልና የትግል መስመርና አደረጃጃት በመፍጠር ራሱን ከጥቃት መከላለከል፡’’ ወዳለው ይወስደናል ማለት ነው።

በተራ 3 የተመለከተውም ቢሆን፤ እስካሁን ለ30 አመት እንደታየው ቅዥ ገዢዎቹ የወያኔ ትግሬዎች እና የኦሮሙማዎቹ እነ አብይ አሕመድና ሌንጮዎቹ የሚያቅዱት ሁሉ እነሱን በሚጠቅም ሁኔታ ስለሆነ በሚያቅዱት ስትራተጂ ያለመካፈል። ሲካፈሉም ህልውናችሁን በሚያስጠብቅ መልኩ ካልሆነ አለመቀበልና ከተቀበሉም ወደ ራስ ጠቀሜታ ስትራተጂ መበዝበዝ ወይንም እንደማይሰራ ማኮላሸት።

በ2ኛው ረድፍ የጠቀስኩት “ህዝባዊ አመጽ”፤ ብዙ ጊዜ የሕዝባዊ አመፅ ምንንት ተነጋግረንበታል፤ ሁላቻሁም ያያቸችሁት የአብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን አመጣጥ ታሪክ እንዴት እንደመጣ ስለምታውቁ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም።

ሕዝባዊ አመጽ ለማምጣት ብዙ ጊዜ ለፍተን ሊከሰት አልተቻለም። ታጥቆ ራሱን ለመከላከልና ሥርዓቱን አሽሸብሮ መጣል ብዙ ብለን ፤ ብለን አልተከሰተም። ለዚህም ምክንያቱ ግልጽ ነው። ሰሞኑን በማሕበራዊ መገናኛዎች እየታየ ያለው የምሕለላ ቪዲዮ ላይ የምታዩት የወጣቱ አጎንብሶ ወደ ሰማይ መፍትሄ ፍለጋ ላይ ያለው ሕሊናው የላሸቀ ወጣት ህዝባዊ አመጽ ላለመሳተፍ ሲል “ፈጣሪ ነው ሃይላችን” ወደ እሚለው በጣም አኮላሽ የሆነ አደንዛዥ ባህል አምላኩ “ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ህዝባዊ አመጽ” እንዲያካሂድለት ስለሚጠብቅ “አብዮት ማካሄድ” አልቻለም”። ይህ አደንዛዥ የሕሊና ዕጽ በ360 ሚዲያ ላይም ፤በበርካታ ሚዲያዎችም ሲደነቅ አይቼው ገርሞኛል።

በጣም የሚገርመው ይህ “ምህለላ”” እንደ ባህላችን ከሆነ “እናቶች” ብቻ ነበሩ ወደ መሬት አጎንብሰው ጉልበታቸውን/ጭናቸውን  እየፏከቱ ፈጠሪያቸውን የሚለምኑት። ዛሬ ደግሞ ወጣት ወንዶች ወደ ጦርነት እየማገዳቸው ያሉትን ሃይላት በሕዝባዊ አመጽ ወይንም በመሳሪያ ታጥቀው ከማስወገድ ይልቅ እንደ እናቶች ወደ መሬት አጎንብሰው ጉልበታቸውን እየፏከቱ እንደ ተጠመደ የአውድማ በሬ በክብ እየዞሩ ሲማለሉ ማየት አስገርሞኛል። አብይ አሕመድም የሚፈልገው ይህንን ነበር። ወያኔዎችም ይህንኑ በደምብ ተጠቅመውበታል። ፈጣሪ ሁሉንም ነገር ሊሰጣቸው የሚጠብቁ ወጣቶች እራሱ ፈጣሪ “ግብዞች፤ደካሞች” የሚላቸው ይመስለኛል።  ጦርነቱ አምላክ አምጥቶት እንደሆነ በበኩሌ አለውቅም፤ እንዳላመጣውም አውቃለሁ ብ መከራከር እችላለሁ። ስለዚህ ጦርነቱን ካላመጣው ሃይል ምህረቱን ለምን እንደሚጠብቁ አይገባኝም።

ስለዚህ ወደ ፖለቲካ ተንታኞቹ ስመልስ፤ ይልቁንስ ጦርነት የተከፈተበት ማሕበረሰብ በጦርነት መመከት እንጂ አትውጉን፤አታዋጉን ብሎ መጠየቅ የለበትም። አማራው ለ27 አመት (አሁንም) የታጠቀውን “ብረትና ብትር” እየተነጠቀ ለአጥቂዎች ሲጋለጥ መኖሩንና አሁንም “ራሱን ቀና ሲአደርግ” እየተነጠቀና እየታሰረ እንደሆነ እነዚህ ፖለቲከኞች ያውቃሉ።

 አሁን ጦርነቱን በመጠቀም ማርኮም ሆነ ገዝቶ ጠመንጃ እንዲታጠቅ እያየን ያለው አማራው  ማሕበረሰብ ወጣትና ገበሬ “አብይ አሕመድ ወዶ ሳይሆን ብግዱ” “በጦርነቱ ሳቢያ አንዲታጠቅ” መንገድ ሲያገኝ የህንን ዕደል ተጠቅሞ እራሱን ከአጥቂዎች የመከላከል ዕድል ስላገኘ ያንን ዕደል አንዲኮላሽ ማደረግ የለበትም።  “ጦርነቱን” አቁሙ ብሎ ማስቆም ስለማይችል፤ መጠቃት ላይቀር ጦርነቱን ሰበብ አድርጎ የውግያ ልምድ እየቀሰመ ራሱን ማስታጠቅና እና በሰበቡ “አብይና አደመቀ መኮንን ዓሊን” ጊዜ እየጠበቁ ማስጨነቅ፤ ሕዝብን የሚያስጨንቁ ገራፊዎችን መጥለፍና ራሱን የሚመስሉ ሕዝባዊየንን እያደራጀ ወደ ጫካ መግባትና ገብቶም “የኦሮሙማውን አማራ ብልጽግና ሰብስብ” መገርሰስ አሁናዊ አማራጭ የሌለው ነው እላለሁ።ዕርቅ ምንምን የሚባል አደንዛዥ የጠላት ስትራተጂ አለመሞከር ነው። ያው ውጤቱ በተለያየ ወቅት አይተነዋል።

ጦርነቱ ጎጂ ሆኖ የታየ ቢሆንም በሌላ መልኩ ተበታትኖ የነበረው አማራ ባንድ ልብ እንዲጓዝ ረድቶታል። የጎጃሙ የጎንደሩ የወሎውና የሸዋው ወጣትና ማሕበረሰብ ባንድ ምጣድ እየበላ ባንድ መቃብር ባንድ እሳት እየሞቀ “ጥቃቱ” ማየት አቅቶት የነበረው የ30 አመት የስነ ልቦና መታወር ጦርነቱ በድንገት ዓይኑ ገልጦለት እንዲያይ ስለረዳው ከነ ጉዳቱ ጠቀሜታውም ስላለው፤ ጦርነቱን እየተጠቀመ እራሱን በውግያ ልምድ እያዳበረ ጦርነቱ ሲቆም ‘አማራውን እየባረሩ የሚሽሞነሞኑ የኦሮሞ በጋሚዶ ሽፍቶችና ህጻንና ሽማግሌ  አራጅ መንግስታቸውን” መመከት እንዲችል ጦርነቱን ከነ ምናምነቴው መጠቀም አለበት የሚል ሃሳብ አለኝ።

አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ  (Ethiopian Semay)

 

 

 

No comments: