Sunday, January 30, 2022

ሰበር ዜና ባሕርዳር ከተማ በናዚ ማጎርያ አዳራሾች የታሰሩ የንጹሃን ትግሬዎች ሁኔታ ጌተቸው ረዳ ETHIO SEMAY 1/30/2022

 

ሰበር ዜና

ባሕርዳር ከተማ በናዚ ማጎርያ አዳራሾች የታሰሩ የንጹሃን ትግሬዎች ሁኔታ

ጌተቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

1/30/2022


እንደምታውቁት በዕብዱ በሽተኛው አብይ አሕመድ የሚመራው “በናዚዎች ርዕዮተ   ዓለም ኢትዮጵያዉያን ትግሬዎችና የአማራዎችን  ዘር በማጥፋት አጀንዳ” ሌት ተቀን  የሚሰራው “የኦሮሙማው መንግሥት” በተባባሪ አሽከሮቹ እነ ተመስገን ጥሩነህ እና የኢሳቱ “ካቡጋ” (génocidaire መሳይ መኮንን) እንዲሁም መሰል አሽከሮቹ በንጹሃን ትግሬዎች የታወጀው የዘር ማጥፋት አወዋጅ ያደረሰው ስቃይ እየተከታተልኩ ካሁን በፊት ለአንባቢዎቼ ማቅረቤ ይታወሳል።

ንጹሃን ትግሬዎችን ከገበያ፤ ከሆስፒታል ከየመንገዱ እና ከየሞኖርያ ቤቶቻቸው እየታፈሱ ወደ “ኮንሴንትሬሽን ካምፕ” ታስረው መሰቃየት ከጀመሩ በርካታ ወራት ሆኗቸዋል። አንዳንዶቹ 10 ወራት አስቆጥሮዋል፤ አንዳንዶቹም አዋጁ ከታወጀ ወዲህ ያለ ምንም ማስረጃ ታስረው እተሰቃዩ ናቸው።

ጥፍር እየነቀለ እና የሴት ማሕጸንና እና  የወንድ ብልት ሲያኮላሽ የነነበረው የጌታቸው አሰፋ የወያኔ መንግሥት የጽጥታና የምርምራ ምክትል ሃላፊ የነበረው “ኦሮሞው ያሬድ” ሰሞኑን እንደፈታው ሰምተናል። ቀደም ብሎም እነ ጃዋር እነ በቀለ ገርባ እና ስብሓት ነጋ እና ስንት የሽብር፤የግድያናየ የጥላቻ ቅስቀሳ ሲያስፋፉ የነበሩ ቁንጮ “ሽብርተኞችን” ያለ ምንም የበደል እና የይቅርታ ማስፈርም ከወህኒ ቤት ሲፈታቸው ያልደነገጠ የልተገረም ሰው አልነበረም።

አስገራሚ ያደረገው ግን “ቁንጮ ሽብርተኞችን” ፈትቶ ምንም የሌሉበትን ንጹሃን ኢት ጵያዊያን የትግራይ ተወላጆችን በአዋጅ ለቅሞ ያሳራቸው እስካሁን ድረሰ ታጉረው እንዳሉ ታውቃላችሁ። የእንቆቁሉሹ አስገራሚውም ነገር አንዱ ይህ ነው።

በኦሮሙማው ናዚያዊ ጸረ ትግሬ የዘር ማጥፋት አዋጅ መሰረት ባሕርዳር ውስጥ የታሰሩ ንጹሃን ትግሬዎች ወደ ማጎርያው አዳራሽ በመሄድ ታሳሪዎችን አንድ ባንድ እያነጋገሩ  “ልትፈቱ ከፈለጋችሁ በድለናል አዎ ወያኔ ነኝ ብላችሁ ፈርሙ” እያሉ ስማቸው አድራሻቸው ቅጽ አስሞልተው እንዲፈርሙና እንዲለቀቁ በግድ እያስገደዱዋቸው ነው።

እምቢ ካሉ መውጣት አይችሉም። በሚገርም ሁኔታ “እንዴት በማናውቀው ፖለቲካ አባል ነን፤ ድጋፍ እንሰጥ ነበርን ብለን ያላደረግነውን አድርገናል ብለን እንፈርማለን? ይህ ነውር አይደለም ወይ? ብለው ሲጠይቁ፤ “ከፈለግክ/ከፈለግሽ/ ፈርም /እዚህ ፈርሚ/ካልሆነ ግን እዚሁ ትበሰብሳታለህ/ትቀምሳታለህ” እያሉ ንጹሃንን በማስፈራራትና በማስገደድ ላይ እንዳሉ አረጋግጫለሁ።

እንግዲህ ፍረዱ። ፍርድቤት ሳይሄዱ፤ሳይጣራ፤ ማስረጃ ሳይቀርብባቸው “በአዋጅ ታፍሰው” የታሰሩ ምስኪኖችን በግድ እያስፈራሩ ፈርም እያሉ እስረኛን ማስገደድን “በሕግ” ቶርች ወይንም “ኮሆርዥን” እንደሆነ  እየታወቀ በሽተኛው አብይ አሕመድና የግል አሽከሩ የሆነው ተመስገን ጥሩነህ ለትግሬዎች ያላቸው ጥላቻ ለማሳየት እየተበቀሏቸው ይገኛሉ።

ለዚህ ነው ማንም ድርጅትና ግለሰብ የሕግ ምሁር “አብይንና ተመስገን ጥሩነህ ከመላ አማራ ብልጽግና አማራር አባል” በዘር ማጥፋት ወንጀል አብይና አሽከሮቹ ለዓለም አቀፍ ፍርድቤት ካልተከሰሱ፤ ብዙ ጥፋት ያስከትላሉ የምለው ለዚህ ነው።

አሳዛኙ ብቀላ ድምበር እንደሌላው የሚያሳየን ደግሞ የሚከተለው አሳዛኝ ብቀላ ነው።

እነዚህ ንጹሃን ፈርመው ቢለቀቁም “ሥራቸው በሌላ ሰው ተተክቶ” ስለሚቆያቸው አብይና ተመስገን ጥሩነህ ከተቀሩ የአማራ ብልጽግና አማራሮች፤ “ትግሬዎች በረንዳ እንዲወድቁ ባቀዱት መሰረት” ‘በረንዳ አዳሪ’ ይሆናሉ።

በዚህ የሕይት ምስቅልቅል ትግሬዎች ሲሰቃዪ ማየታቸው የነዚህ እኩያን ሰዎች የዘር ማጥፋት ዕቅድ እርካታ እና ስኬት ለረዢም ጊዜ ዘላቂ ጠባሳ ትቶ የሚሄድ ብቃላ ነው ማለት ነው።

ቢሆንም የጊዜ ጉዳይ እንጂ እነሱም በሰፈሩት ቁና ይሰፈራሉ!

“እንድትፈቱ ከፈለጋችሁ እኔ ወያኔ ነኝ፤ ዕርዳታም እሰጥ ነበር፤ በወንጀል ተካፍያለሁ..…ብላችሁ ፈርሙ ካልሆነ አንፈታችሁም” እያሉ የሚያደርጉት ድርጊት ከመሪዎቹ መፈታት ስታነጻጽሩት እነ አብይና የአማራ ብልጽግና አመራር አባሎች ብቀላቸው ከተራው የትግራይ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ትግሬ እንጂ ከወያኔ መሪዎች ጋር እንዳልሆነ ከሚሰሩት አስነዋሪ “የመስገደድ ፌርማ” እናንተም በቤተሰቦቻችን ሕይት ላይ እየደረሰ ያለ የዘር ብቃላ ወንጀል እንድታውቁት ብየ ነው ይህንን ዜና ያካፈልኳችሁ።

ታሪክ ይዘግባል፤ሕይወትም ይቀጥላል።

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ  ETHIO SEMAY 1/30/2022


Friday, January 28, 2022

ካለፈው የቀጠለ ክፍል -2 -የአብይ አሕመድ የአእምሮ መቃወስ ከጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 1/29/2022

 

ካለፈው የቀጠለ ክፍል -2 -የአብይ አሕመድ የአእምሮ መቃወስ

ከጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

 1/29/2022

ዛሬ በ “ቲ ኤች ኤም” ዩ ቱብ ዜና መድረክ ሳደምጥ አመስግኜው የማላውቀውን የፕሮግራሙ አዘጋጅ “ስታሊን” ን አመሰገንኩት። ከዚህ ቀጥሎ የምጠቅሰው ረስቻቸው ከነበሩት የኣኢምሮ በሽተኛው የአብይ አሕመድ ንግግር “ስታሊን በሚገርም ቅንብር አዘጋጅቶ አስደምጦናል”። 

ንግግሩ በቪዲዮው የምታዩት ሲሆን ስለ የአእምሮ በሽተኛው “አብይ አሕመድ” መጽሐፍ ለምትጽፉ ደራሲያን እና የአእምሮና የሕሊና ተመራማሪዎች ለጥናት እንዲመቻችሁ በጽሑፍ ዘግቤ አቅርቤላችለሁ።

(-1-)-ኢትዮጵያዊያን ለመጓጓዣ “መኪና” መጠቀም እንደሌለባቸው እና ሓጢያት መሆኑን

(-2-)- ሌላው ደግሞ ስለ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ የዓባይን ውሃም ሆነ ሌሎች የወንዝ ፈለጎች ውሃውን ገድበን “ዕርሻ እና ለኤነርጂ” ማዋል የፈጣሪ ቁጣ ስለሚያስከትል መጠቀም እንደሌለብን ይመክራል።

የበሽተኛው ንግግር ቃል በቃል ይኸየው እንዲህ ይላል።

“እያንዳንዳችን እንድንሄድበት እንሮጥበት ዘንድ እግር ተሰጥቶን ስያበቃ እግራችንን መጠቀም ትተን መኪና መጠቀም ፈጣሪ ጋር እምያጣላ ነገር ነው። የተሰጠን እግር እያለ ለምን መኪና መጠቀም ተገድደን ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል።” (አብይ አሕመድ- የቪዲዮ ጽሑፍ ኢትዮ- ሰማይ)።

“ውሃም እራሱ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ መገደብ ስሕተት ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ውሃው “ኮርሱን ጠብቆ” እንዳይሄድ በየመሃሉ እያቆሙ ከዋናው ከተፈጥሮው መንገድ እያወጡ ለእርሻ ማዋል ለኤነርጂ ማዋል ከተፈጥሮ ጋር መጋጨት ነው።”

ይህ ንግግር አንባቢዎች እንድተነትን አይጠበቅብኝም። ምክንያቱም ግልጽ ነው። የሰው ልጅ በእግሩ መሄድ አለበት እያለ እራሱ ግን በመኪና ይሄዳል። የሰው ልጅ መኪና የሚባል መጓጓዣ መጠቀም የለበትን  ሌላ ቀርቶ በቅሎም ፈረስም አያስፈልግም ይላል። በእግር ብቻ መጓዝ አለባችሁ እያላችሁ ነው። ጤነኛ ሰው እንዲህ ይላል? እንዲህ የሚል ሰው በዚህ ዘመን እእምሮው የቀወሰ ሰው ብቻ ነው። መኪና መጠቀም ያበረታቱን አጼ ምኒሊክ ሲሆኑ፤ በዚህ ዘመን የተወለደው በአእምሮ ቀውስ እየተሰቃየ ያለው የጂማው በሻሻ ዕብድ ደግሞ በእግር ሂዱ እያለን ነው።  

የሚገርም በሽታው ደግሞ “የህዳሴ ግድብም ሆነ ማንኛውም የወንዝና የሃይቅ ፈለጎች” ጠልፈን ለእርሻም ሆነ ለመብራትና ለኢንዳስትርያል አግልግሎቶች ማዋል አይገባም። ሓጢያት ነው ፤ፈጠሪ ጋር ያጣላናል እያለ በፕሮተስታንት ፓስተርነቱ የቀወሰው ሕሊናው ድንገር አገር የመምራት ሎተሪ ሲደርሰው “ዕብድነቱን” መሸሸግ አልቻለም። ይኼው ኢትዮጵያ በአንድ የቀወሰ ሰው ጉድ ውስጥ ገብታለች። ሓኪሞች የለታላችሁ!?

እናንተን እንኳ አልወቅሥም፤ ምክንያቱም ተመርቃችሁ ሥራ እንዳታገኙ በረንዳ ላይ እንድትተኙ እያደረጋችሁ ስለሆነ (ትናንት የለጠፍኩት የአንድ ዶክተር አሳዛኝ ቃለ መጠይቅ ለጥፌዋለሁ ያንን ተመልከቱ)። ስለዚህ ሓኪሞችን አምርሮ የሚጠላበት እና የሚሰድባችሁ ምክንያት በዚህ በሽታው እንደሆነ ጥርጥር የለውም።

ለማንኛው የውጭ አገር ሐኪሞች እባካችሁ ይንን ቀውስ ወደ ጀኔቫ አስራችሁ አሳክሙልን። ወይ ኢትዮጵያ አገሬ ምን ጉድ ውስጥ ገባሽ?!

 


ጽሑፍን ተቀባበሉት

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Tuesday, January 25, 2022

የአብይ አሕመድ የማሰብ ችሎታና የዓዕምሮ በሽታው ከጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 1/25/2022

 

የአብይ አሕመድ የማሰብ ችሎታና የዓዕምሮ በሽታው

ከጌታቸው ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY

1/25/2022

ሁለት ዕብዶች እያስጨረሱት ያለውን ሕዝባችን በቅጡ ስላልተመረመረ እንጂ መንስኤው የሥልጣን ሽሚያ ቢሆንም ዋናው ሞተሩ ግን የሰዎቹ የጤንነት ሁኔታ ነው። የትግሬዎቹ ዕብደት ማየት የሚቻል እና ለ30 አመት ያየነው የዝሆን ያህል ትልቅ ዕብደት ስለሆነ የእነሱን ዕብደት ትተን “አብዮት” ወደ እሚባለው አዲሱ ዕብድ እንመልከት።

አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በቪዲዮ ተቀርጾ ያየነው አባቴ ነው የሚላቸው አባቱ እና ወንድሞቹ እንዲሁም የልጅነት ጓደኞቹ ነን የሚሉ የአብይ አሕመድ ጓደኞቹ ቃለ መጠይቅ አይተናል። በዛው ቪዲዮ የቅርብ ጓደኞቹ ነበርን የሚሉ የጅማ በሻሻ ጓደኞቹ ቢነግሩንም፤ አብይ አሕመድ ግንአንድ ነገር መናገር የምፈልገው በልጅነቴ ዘመን አንድም ጓደኛ አልነበረኝምሲል ያለ ጓደኛ ማደጉን ሳደምጥ የበሽታው መንስኤ ያለ  ጓደኛ ማደጉ ይሆን የሚል ጥርጣሬ አለኝ። ሰው እንዴት ያለ አንድ እንኳ ጓደኛ አይኖሮውም? ለመሆኑ እነዚያ እንዲያ ሲያደንቁት የነበሩት አብሮ አደጎቹ ጓደኞቹ ከምን ተነስቶ ነው ጓደኞቼ አልረነበሩም ብሎ የከዳቸው?  እውነትም ከሃዲ ነው።

አንዱ ያም ይሆን ወደ ሥልጣን ሲመጣ ዕልል ብሎ ያከበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በመክዳት የሕዝብ አደራ ከድቶ ሰው እያሰረ እያስደበደበ እና እያስገደለ ያለው? ንግግሮቹ ሁሉ እጅግ የተምታቱ የአታላይ ሰው ንግግሮች ናቸው። ንግግሮቹ እንኳ ስትመዝንዋቸው እርስበርሱ የሚታቱበት ጤናው የቀወሰ መሆኑንም ማሳያ ምልክቶች ናቸው። ኦሮሞ ያለመሆኑንም በሚሰድቡት ስድብ የተነሳ እኔ ኦሮሞ አይደለሁም ይልና እንደገና ኦሮሞ ነኝ እያለ መከራከሩ ስናደምጠው የሰውየው የሕሊና ተጽእኖው ከፍተኛ መሆኑን እናያለን።

ንግገሮቹ ሁሉ ስንፈትሻቸው የምር ብቃት የሌላቸው ብቻ ሳይሆኑ፤ ፍፁም ከደደብ ሕሊና የሚነጩ በውብ ቃላት የታጀቡ ፍሬ ከርስቺ እና አታላይ መሆናቸውን ያሳያል። አብይ አሕመድ ሥልጣን ላይ ከወጣበት በነዚህ 4 አማታት ጊዜ ጀምሮ ነገሮችን አስቀድሞ ሊተነብይና መውጫ ስልቶች (ኤክዚት \እስትራተጂ) መቀየስ የማይችልከውስጡ ለሚረብሹት የማንነት ቀውሶች መፈወሻ የሚሆኑት የአትክልት እና የአበባ መናፈሻዎች ሲኮተኩትና ሲያሳምር ተዘፍቆ ከርሞቸል ሲላቸውየቆዩ ነገሮች አድገው ድንገት አስፈሪ ሆነው ፊቱ ላይ ቆመው  ሲደቀኑበትየሚደናበር” በሽተኛ ሰው ሆኖ አይተነዋል።

ይህ የውሸት፤የመደናገርና የማታለል ባሕሪው፤ ከሞላ ጎደል የፖለቲካ ህይወቱን ስንዳስስ ገና 14 አመቱ ብረት ታጥቆ የኦነግ ታጋይ ከዚያም ኦፒዲኦ ካድሬ ሆኖ በወያኔ ሥርምእየዋሹ ሰውን በሚጎዱበትመስርያቤት ውስጥ ተቀጥሮሲዋሽ ሲያታልል፤ ሲሰልል፤ንፁሃን ሲያጠቃ  እና ሲያሳስር በመኖሩእንዲሁም ያለ ጓደ ደግናየማንነትቀውስ በፈጠረበት ጠማማ የጤና መዛባት ምክንያት አገሪቱ ምስቅልቅሏን አውጥቷታል።

የኢትዮጵያ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ከሆነበት ጀምሮ በዓለም ፊት የስልጣን ደረጃውንና የስልጣኑን ስፋትና የውስጥ እና የውጭ ጉዳዮችን ባለማወቁኢትዮጵያጠላት የላትም ሲል ቆይቶ ከሰዓት በሗላ ባንድ አዳራሽ ተገኝቶ ጥዋት ረፋዱ የተናገረውን ረስቶኢትዮጵያ ብዙ ጣለቶች ያላት አገር ናትብሎ ያፈርሰዋል።

አደገኛ የሆነው ባሕሪውየኢትዮጵያ መሪ ሆኖ” ሕዝብን አደራ እጠብቃለሁ ብሎንጉሥነቱን በይፋ በተቀባ ጊዜ” ሕዝብ ከጠላት እንዲጠብቅ የማለለትን ሃላፊነት ረስቶ  የሕዝብ ዋነኛ ጠላት ለመሆን በቅቷል” (በተለይ ለአማራ ማሕበረሰብ) በዚህ ምክንያት ያየነው የሰውየው የሕዝብ ጠላትነት  ዘፍጥረትሥር ሰድዶ እነሆ በዚህ ጦርነት ውስጥ አማራውን እያስቀየመ ትግሬ የሚባል በሙሉ ደግሞ ሰብስቦማጎርያ ቤት አስሮሽማግሌና ህጻናት እንዲሁም እርጉዞች ጭምር ሲያሰቃያቸው ይገኛል። በዚህም ምክንያት፣ ባለፉት ዓመታት፣ የሰውየው የማስተዳዳር ችሎታ ማነስ የሕሊና በሽታ ተጨምሮበት ሰውየው ወደ ለየለት ራስ ወዳድናርሲሰትነት” እናስኪዞፈሪንያነቱንበገሃድ ማየት ችለናል።

በዚህሲንድረምምክንያት የተነሳ የመንግሥት መሪነቱንየፖለቲካ መቀመጫውወደበሽተኛ ሶፋ መቀመጫቀይሮታል። ህመሙ ከባድ ስለሆነ በአእምሮ የሕክምና ሊቃውንት ሊታከም እንደሚገባው ምንም ጥርጥር የለውም። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ በሙያዊ ምልከታ ታካሚከመገለል” ይልቅ የአንድን ሀገር ኑሮ የመምራት ፍፁም ስልጣን ተሰጥቶት እነሆ አገሪቱ ከድጡ ወደ ማጡ ወስዷታል።በሁሉም በየሚኒሰትሮቹ ሥራ መስኮችና መስራቤቶች ድረስ  እየሄደ  ውስብስብ እነ ሁለገብ ችሎታ ያለው ለማስመሰል  ራሱ ለራሱ በቴ/ቪዥን ፊት ቆሞ ገለጻ ሲያደርግ አይተው የተማረኩለት የዋሃን ዜጎችውስብስብ እውቀትአለው እያሉ ሲያንጨበጭቡለት አይተናል። የእሱ ውስብስብነት ግን ፍጹም ቅጥ ያታ  የታመመ ሰው ተግባር ነው።  ጥልቅ የሆነ የበታችነት ስሜት ስላለውህመሙን ለማስታገስየሆነ ቦታ መሸሸግ ነበረበረትና ወደሶማሊያ፤ ሱዳን፤ ኤርትራ፤ ኬኒያ እና ወደ አፍሪካ እንዲሁም ዓረብ አገሮች ሄዶ ልዩ መሪ ለመምሰልሲዘባርቅከርሞየወርቅ ሃብል ተሸልሞመጨረሻየኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሆኜ እንዳገለግል ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በዛሬው ዕለት ሹመት እንደሰጡኝ ስገልጽ በኩራትና በደስታ ነውእያለየባዕድ አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሆንእንደሚያስከስስና ከሥልጣን እንደሚያስባርርበሽተኛ ሕሊናው ባለማወቁየታላቅ ታላቅነት ሹመትመስሎት እራሱን እና ኢትዮጵያን አዋርዷል።

የሱ ራዕይየኢትዮጵያ መሪ ሆኖ እንደገናየኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሬርመሆን  የበታችነት ስሜቱ እንዴት እንደሚፈውሰው የሚጮኽበት ስልት ነው። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የነበሩት ጃንሆይየኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ነኝ ቢሉ ወይንም / መንግሥቱ እንዲሁ ቢሉ ምንኛ ውርደት እንደሚሰማን ገምቱት። የዚህ ሰውየ ግን በመሪነት ደረጃም ስለማናየውቅሌቱምንም አልመሰለንም። 

በዚህም የበታችነት ስሜቱየኤርትራ አሻንጉሊትእስከመሆን ደርሳል። የበታችነት ስሜቱን ለማከም የአማራውን (ኢትዮጵያዊ) አርበኛጀኔራል (ፊልድማርሻል) አሳምነው ጽጌን” በማስገደል የመጨረሻውን የዕብደቱን ማሳያ ለመፈፀም የግድ ጀኔራሉን ገድሎ እንደገና የጀኔራሉን እርጉዝ ባለቤቱን አስሮ እርግዝናዋን እንድትወርድ ከሆነ በሗላአሳምነውን ከእስር የፈታሁት እኔ ነኝብሎ ገና ወደ ሥልጣን ሳይመጣ የተፈታውን ሰውየፈታሁትብሎ የሕሊና በሽተኛ መሆኑን አሳየን።

በሚገርም ሁኔታ አሳምነው ሲገደል አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለውአጭበርባሪ” “መሰሪበሳምነቱ ወደ ቶሮንቶ ካናዳ ሄዶ ሕዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽማን ማንን እንደሚገድል አስቀድሜ በዝርዝር ለጠ/ሚኒስተሩ አሳውቄ ነበርብሎ ተናግሮፓርላማ ተብየውይህንን አስገራሚ የወንጀል ምስጢራዊ “ሴራ” ይፋ ያደረገልን ንግግር በሽተኛው /ሚኒሰትሩም ሆነ አንዳርጋቻው ጽጌን ጠርቶ ጉዳዩ እንዲጣራ አላደረገም። ለምን ማለት አይቻልም፤ በሽተኛ የሚመራው አገር ፓርላማ ብሎ ነገር የለም-ማ!

ወያኔ በጫረው ጦርነት እስከ ደብረሲና ድረሰ መጥቶ  ዓፋር ሕዝባችን እና አማራውን ሕዝባችንን ሲያወድምበሽተኛውፓርክ ላይሕመሙን ሲያናፈስ” ነበር፤ በዚህ የተበሳጨ ሕዝብ ሲጮህበትና ወያኔ እየገሰገሰ መምጣቱ ሲመለከት በድንጋጤ ተውጦ ፤ እራሱ ወደ ቦታው ሄዶ ግማሽ ቀን እየቆየ በሄልኮፕተር በመመላለስ  ‘አስመሳይ’ እርምት በማድረግ ጫፍ የደረሰው ወያኔወደ ሗላ’ እንዲገፋ ተደረገ። ከጦርነቱ በኋላ፣ አሸነፍን ብሎ በውሸት ሲቧርቅ፤ ጮማ ሲቆርጥ፤ የዋሆችን ሲያስጨበጭብ ፤ ሽልማት ሲሸልም ጦር ሜዳ የተዋደቀው ብዙ ተዋጊ በመጸየፉ፣ ለማንኳሰስ ሞክሮየወደፊት አደጋ ናቸው የሚላቸውን አካባቢዎች ለይቶድሕረ ጦርነት የሚል ሴራ ጠንጥኖ ካለው የጭንቀት በሽታ ሌላ በከባድ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል።

በርካቶች ለጦርነት የሚደረገውን ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች እስከ መግለጽ ደርሰዋል። ሁላችንም እንደምናውቀው ግልጽ የሆነ ድል ወደ ተጨባጭ ሁኔታ አልደረሰም። ሰሞኑን አሽከሮቹን ሰብስቦ ከወታደራዊ እስከ ስቢል ሰዎችን ሰብስቦ እንዴ ሙያቸው ሲሸልምጦርነቱ እንዳለቀና ሞርየሚለው እንቅስቃሴ አቁሙ ብሎ ጦርነት የለም ብሎ የቦተለከው አብይ አሕመድ በተለይም የትግሉን ሃይል ከድቶ በፈሰሰው ደማቸው በተቀጠቀጠ አጥንታቸው እርከን ሜዳ ላይ የተገኘውን የመጨረሻ ሽልማት በመንፈግ ነው ሰሞኑን ሲቦርቅ ያየነው።

በሽተኛው እየተከተለው ያለው መንገድ የተቃወሙትን ሁሉ ጤንነቱን የተጠራጠሩት ሁሉ ወደ እስር በማስገባት የወያኔ መንገድ በከፋ መልኩ እየሰለጠነበት ነው። ኦሮሞ ወክሎናል ብለው ወደ ሥልጣን የተቆናጠጡት እነዚህ አዳዲስ አረመኔዎች እየለዩ የሚወነጅሉት ዜጋ  ከጀርባው ያለው ገበያ ይዞት የሚመጣ መዘዝ አላወቁትም።

 ጠንከር ያሉ እና ጠንካራ አስተሳሰብ ያላቸው መንፈሶች እየታሰሩ በስርዓቱ ተጨፍልቀው ሌሎች አድርባዮች ደግሞ ወደ አሳፋሪ ጥገኛ ደም ሰጪነት ተለውጠዋል። በሽተኛው ገዢ ሙሉ በሙሉ ባለማበዱ ሞኝ-ሞኙን እና የለየላቸው “የ-ዩቱብ ዕብዶችን” እየፈለገ በጥቅም እየደለለ እርስ በርስ እንዲጣላ ያደርጋል። ከዚያ በሗላ ዲያስፖራ የምትኖሩ ሁላችሁም ‘አማራ ትግሬ ኦሮሞ..’ አትባባሉ “ኢትዮጵያዊያን ናችሁ”፤ ሲል በመ፣በራሱ ግዛት ግን “ኦሮሞ ትግሬ አማራ….ነኝ” እንዲል አዳዲስ “ፓርታይ ክልሎች” እንዲከለሉ በማድረግ ላይ ነው። በሽታው ይህን ያህል ጥልቀት አለው (አክዩት አይደለም/ ክሮኒክ ነው)።

ሁሉም ነገር ከተነገረው እና ከተሰራ በኋላ የኢሳያስ አፈወርቂና የኦነግ ጀንዳ ለማስቀጠል ብቸኛው ብቃት ያለው ሃይልከጋሼ አበይ አሕመድ” ሌላ ሰው ማንም አይደለም። አብይ አሕመድ ለኢትዮጵያና ለአማራ ያልተገባ  ወደር የለሽ ጥላቻ እንዳለው አትርሱ። የቀረው የድጋፍ ቦታ ኦነግ (ኦነግ ሸኔ “የሽፋን ስም”) እና ኤርትራ ብቻ ነው። በግልጽ እንደሚታየው፣በኢትዮጵያ ሰማይ ጥላ ሥር ጀሮአችን እየሰማ በኦነግም በወያኔና አብይ መካከል እኛ በማናውቀው ከፍተኛ ደረጃ ንግግሮች እየተደረጉ ነው (ካሁን በፊት - ኤርትራ ጋርም ሆነ ኤርትራ ውስጥ ከነበሩት ኦነጎች ምን ስምምነት እንደተደረገ እንኳ ሕዝቡም ሆነ ፓርላማ ተብየ አያውቅም) ይህ ምስጢር ስለዚህ ሰውየ ባሕሪ ብዙ ይናገራል።

በከባድ ጫና ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ዜጎች ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ዘረፋ በማሸማቀቅ ድብደባ፤ ሞት እና እስራት ላይ ነው። በዚህ ታሪካዊ ወቅት በርካታ ማህበረሰባዊ-ታሪካዊ ዳይናሚክሶ-ች እርስ በርስ እየተጠላለፉ ይገኛሉ። ህዝቡ አልገዛም ባይነት በአዲስ ተቃውሞ “በጫና አስጨንቆ” ሌላአገራዊ የሆነ መሪ” እስካልተካ ድረስ የሀገሪቱ የዛሬ ችግር ብቻ ሳይሆን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከባድ ችግር ውስጥ ይወድቃል።

አርቆ አሳቢ መሪ ለማግኘት ከበፊቱ ወንጀሎች ነፃ የሆነ ንክኪ የሌለው ቅን ሰው መሆንና  ቅድመ ሁኔታው የፖሊቲካ ፍላጎት በአገር ፍቅርና ሉአላዊንተንናተጠያቂነትን” ማመን ያስፈልጋል። አብይ በተጠያቂነት አያምንም፡ የሀገሪቱን ደኅንነት ግድ የለውም፡ አማራ ሕዝብ ኦሮሞና ጉምዝ ሲታረዱና ሲባረሩ “አታካብዱት” ይላል። ሰውየው ከአገሪቱ ጋር ያለው ግንኙነት ለምክንያታዊ አእምሮ የማይታወቅ በሁሉም ዓይነት አለመግባባቶች የተሞላ ነው።

በጠቅላላው የስጋትና እና የጨለምተኝነት መፈልፈያ ሰው ነው። ሕመሙ የበረታ ስለሆነ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ስለሰውየው መተቸት ወደ እስር እንደሚዳርጋቸው ሰግተው ካልሆነ በቀር የሰውየው በሽተኛነት ሊጠፋቸው አይችልም። ባለፉት ዘመናት እንደዚህ ያለ በመሪነት ያለ መሪ በሕሊና በሽታ የታማ ቢኖር በጥቂት ሰዎች ነው። ይህ ግን በብዙዎቻችን በሽተኛነቱን አርግጠኞች ሆነን መናገር ችለናል። በመወያያ የዜና ማሰራጫና የውይይት መድረኮችም በሕሊና ጤንነቱ ብዙ ውይይት ተደርጓል።

 እኛ የሚያስፈልገን ያልተበረዘ ኢትዮጵያዊ መሪ እንጂ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲያስተዳድረን አይደለም

አብይ እና ተከታዮቹ በኦሮሙማ ስልቀጣ ስልት ኦሮሞ የተባለችዲፋክቶ አገርመላዋን ኢትዮጵያ መግዛት አለባት ብለው በጥልቅ ያምናሉ።  እኛ በስልጣን ላይ እስካለን ድረስ መላ አገሪቱ እና ህዝቦቿ በተግባራዊ መልኩ ለሁሉም ዓይነት ብዝበዛ የተዳረገ ዜጋበኛ ፈቃድ የሚንቀሳቀሱየእኛ አገልጋዮች ናቸው ብለው ያምናሉ። አብይባሌሄዶ ለሽማግሌወች የተናገራቸው ይህንኑ ነው

በሽተኛው መሪ በጦርነቱ ወቅት ለሀገራዊ ታማኝነትየከንፈር አገልግሎት” በመስጠት ጠላትን ለመዋጋት ከፍተኛ ድጋፍ ማሰባሰብ እንችላለን ብሎ ያምናል። በሰላም ጊዜ በመንገዳችን ላይ የሚቆምን ሁሉ ለመናድ የተነደፉ ህጎችን እንፈጥራለን ይላል። የጨዋታው ስም ሥልጣንን ማካበት ነው (የበሽተኛው አማካሪ ሌንጮ ባቲ የተናገረውም ይህንኑ ነው -3000 አመት እንገዛችሗለን ብሎናል አማካሪ ሆኖ እያለ አዲስ አበባ ከተማ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት- ዛሬ የሳውዲ አምባሳደር ነው)

 አብይ የጥቃትና የአጥቂ ሞኖፖሊነት አለን ብሎ ያምናል። የጥበቃ ወጪውን ለኦነግና ለኦፒዲኦ እስከሰጠን ድረስ ማንም አይደፍረንም የማዘዝ ብቸኛ ሥልጣን አለን ብሎ ያምናል። አምቢ ካላችሁ “ትግራይን” አስገንጥየ “ኦሮሞ” አገር እንዲመሰርት አደርጋለሁ እያለ እንደ በውሰጠ ሴራ እየነገረን ነው (አክራሪ እስላማዊ ኦሮሞ በከንቲባነትም ሆነ በፓርላማ ውስጥ እንዲሰገሰጉ የማድረጉ ምስጢሩ የኼው ነው)። “ኢትዮጵያ ውስጥ ጥበቃና እንክብካቤ የሚደረግለት ብቸኛ ሕዝብ አለ፡ እሱምኦሮሞይባላል።በዛውክልልየሚገደል ሕዝብ አለ፤ እርሱም “አማራ” ይባላል። በክልሉ የሚኖሩ አማራዎች እና ክርስትያኖች ቢገደሉ ተጠያቂ የለም። ጠያቂ ካለምአርፈህ ተኛ!!!” የሚል አጭር ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል።

አሁን አብይ አሕመድ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን ማዕበል በእርግጥ ማሰስ ይችላል? የአብይ አሕመድ የማሰብ ችሎታና የዓዕምሮ በሽታው አሳሽ (ኮምፓስ- ኤስ) አስይዘህ ችግሩ ብታሳያውም ሊገባው የማይችል ቀውስ ውስጥ ነው። ጽሑፉን ላላወቁ ለማሳወቅ ተቀባበሉት።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY