ኦሮሙማ ፓወር እና አማራዊው ኢንተርሃሙዌው መንጋ
ጌታቸው
ረዳ
ኢትዮ
ሰማይ (Ethiopian Semay)
11/16/2021
ዕለተ
ቅድሜ
የኢሳት ቴ/ቪዥን ጋዜጠኛ በሆነው “ጀነሳይደሩ” መሳይ መኮንን እና የ“አብን”
አመራር አባል በሆነው “የሱፍ ኢብራሂም” የኢንተርሃሙዌው መሪዎች ምክንያት በንጹሃን ትግሬዎች ላይ ብዙ ጥቃት እየተፈጸመ ነው።
መንግሥታዊ መዋቅሩን የተቆጣጠረው የብልጽግና “የኦሮሙማ ፓወር” እና “አማራዊው
ኢንተርሃሙዌው ሚሊሽያ” ትግሬዎችን የመግደል እና የማጽዳት ዘመቻ ዛሬም በከፋ መልኩ እንደቀጠለ ነው። እየተካሄደ ያለው “የግድያ፤የዘረፋ፤
ሰብስቦ የማሰርና አፍኖ የመጥፋት ዘመቻው” ውጭ አገር የሚኖሩ የፌስቡክ ኢንተርሃሙዌ ሚሊሺያ አባላት “ግፋ በለው” የዘር ማጥፋት
ዘመቻ ድጋፍ እያገኘ ነው። “ፌስ ቡክ” ለዘር ማጥፋት ቅስቀሳ እየዋለ ነው። “ትዊትር” እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ሰምተናል። ፌስቡክ
ግን “ለኢንተርሃሙዌው” ክፍትና ምቹ ሆኖ እያየነው ነው።
ከአዲስ አባባ ወደ ባሕርዳር ለመንግሥት ሥራ ለመስራት የሚሄዱ የትግራይ
ተወላጆች እየታፈኑ ነው። የት እንዳሉም ስለማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ጭንቀት ላይ ናቸው። አፈናው በዚህ መልኩ ቀጥሏል። ንጹሃን ለሆኑ
ትግሬዎች ኢትዮጵያ “ሳውዲ ዓረቢያ ሆናባቻቸዋለች”።
ታሪክ የዘገበው፤ የሩዋንዳ ዜጎች በሆኑት በቱትሲ ነገድ ላይ የዘር ጭፍጨፋ
ሲጀምር “የሁቱ ፓውር መፈክር” “us against them-all of us against all of them” ( እኛ በነሱ ላይ-
ሁላችንም በነሱ ላይ) የሚል ነበር። በዚህ መፈክር ተመሳሳይ በውስጥ አገር እና በውጭ አገር የሚኖሩ ‘አማራዊ ኢነተርሃሙዌው መንጋ”
በየፌስቡኩ ተመሳሳይ መፈክርና መልዕክት እየተንጸባረቀ እንደሆነ “በዚህ ፌስቡክ እየመጡ የሚጽፉት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ፍላጎታቸው”
የምትመለከቱት ነው።
ዛሬም የመንግሥቱን መዋቅር የተቆጣጠረው “የሁቱ ፓወር የብልጽግና አፋኝ
የፖሊስ አባሎች” በ “us against them-all of us against all of them” መፈክር መሰረት “በአማራዊው ኢንተርሃሙዌ
ሚሊሽያ” ጠቋሚነት ቤት ለቤት እየሄዱ “በዘር ማጽዳት” አዋጁ መሰረት
ትግሬ የተባለ በሙሉ እየተጎተተ ወዴት እንደሚወሰዱ እንደሆነ ወይንም መጨፍጨፋቸው ወይንም በህይወት መኖራቸው የሚታወቅ ነገር የለም።
ልክ እንደ ዘመነ ደርግ “ከቤት ለቤት አሰሳ” በኢንተርሃሙዌው ሚሊሺያ
ጠቋሚነት ከማሰር ሌላ “በጥናት ከተነደፉ የማጥመጃ ሥፍራዎች” አንዱ ከቤተክርስትያን መልስ በሗላ ወደ እየቤታቸው ሲሄዱ ከከቤተክርሰትያን
“ደጀ ሰላም” (በር) አድፍጦ በመጠባበቅ በፖሊሶች ታፍነው እየተወሰዱ ነው።
በጎንደር በባሕርዳር የተገደሉ የትግራይ ሰዎች አሉ። ከታሰሩ በሗላ ቤቶቻቸው
እየተዘረፉ ነው። ያልታሰሩ ትግሬዎችም መታወቂያ ከሌለህ ወይ ገንዘብ ስጠኝ ወይ አስርሃለሁ እየሉ ቤት ለቤት በማንኳኳት ኢንተርሀሙዌው
ሚሊሺያ ንጹሃን ትግሬዎችን የማስጨነቅ ዘመቻ ጀምሯል።
“እዚህ ቤት ትግሬ ይኖራል” እያለ የሚጠቁም ደግሞ “አማራዊው የኢንተርሃሙዌው
ሚሊሽያ ነው”። ለዘመናት ከሚኖሩበት ቤት እየተጎተቱ ወደ ደጅ የተጣሉ ሰዎችም አንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህ በመንግሥት አዋጅ
የታወጀ የትብብር ዘመቻ ስለሆነ በዜጎች ላይ የሚደርስ “ግድያም ይሁን ዘረፋ እንዲሁም ገንዘብ ስጠኝ ወንጀል እና በሴቶች ላይ አመጽ”
ለሚደረጉ ጥቃቶች ማንም አይጠይቃቸውም። በዚህ ደረጃ ቀጥሏል።
በዚህ ሁኔታ በመላው የትግራይ ሕዝብ የታወጀ የዘር ማጥቃት ዘመቻ የትግራይ
ተወላጆችን እያስቆጣ ስለሆነ “የትግራይ መገንጠል” ፍላጎት ከማንኛወንም ጊዜ የበረታ ስለመጣ ትግራይ አንደምትገነጠል ምንም ጥርጥር
የለውም። ትግራይ ስትገነጠል፤ ኦሮሞ ይከተላል፤ ሌላውም ሌላውም። እንግዲህ ይህ ነው የተፈለገው? የሚለው ጥያቄ ለአንባቢዎች እተዋለሁ።
አገር ሲፈርስ በመላው አገሪቱ “የሚያስከትለው ሰበብ” ፌስቡክ ላይ ተድጦ
“ኮምፕዩተር ኪቦርድ” እንደመጫንና እንደመፎለል” ቀላል እንዳልሆነ ከፈረሱ አገሮች ማየት በቂ ነው።
አገር ሲፈርስ
የእያንዳንዱ ኢንተርሃሙዌው ሚሊሺያ አባል “ቤተሰብ ሰቆቃ፤ስደት” ሲከሰት ያኔ ዘግይቶ የሚመጣ “ከንፍርን በሓዘን ቁጭት መመጠጥ”
ጠቀሜታ የለውም።
ትግሬ በሙሉ “አባልም አባል ያልሆነም” ይፋ የሆነ የዘር ማጥፋት አዋጅ
“በመንግሥት እና በአማራዊው ኢንትርሃሙዌው መንጋ” ስለታወጀባቸው በንፁሃን ቤተሰቦቻችን መጠቃት ተጨንቀናል፤ተበሳጭተናል። “ ጊዚው
ለራሱ ሲል ያልፋል። ይዘገያል እንጂ ሁሉም እንደየ ስራውና እንደየ ምኞቱ የእጁን ያገኛል።
ኢትዮጵያ ገደል አፋፍ ላይ ነች ነበር ስንል የነበረው፤ ዛሬ ግን ቆማ ሳይሆን ኢትርሃሙዌው መንጋ “ገፍትሮ
ገደል ውስጥ አስገብተዋታል”። ይህ የጅምላ ጥቃት ሰበቡ ብዙ ስለሚሆን፤ የዘር ማጽዳት ጥቃት እንዲቆም ልብ ላላቸው ዜጎች የተቻላቸው
እንዲጥሩ አደራ እላለሁ። እንዲህ ከቀጠለ፤ አገር ትቀጥላለች ተብሎ የሚታሰብ አይሆንም። ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚሉ “ትምሕርት”
የጎደላቸው ሰዎች አገሮች እንዴት እንደፈረሱ ለማወቅ መጻሕፍቶችን
መመለክት ለግንዛቤ ይረዳል።
ሰሞኑን ከአንድ ሰው በቀር መልእክቶቼን ሼር ማድረግ አቁማችሗል፡፡ምክንያቱ
ይገባኛል። ኢንትርሃሙዌው ቡድን ይህንን መልዕክት ሕዝብ እንዲመለከተውና ግንዛቤ እንዲያገኝ አይፈልግም። ማዕቀቡ ተባበሪነትን ያሳያል።
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay)
11/6/2021
No comments:
Post a Comment