እምብዛ
ታደሰ እና ታሪኩ ዲሽታ ጊና
ጌታቸው
ረዳ
ኢትዮ
ሰማይ ድረግጽ አዘጋጅ
11/14/2021
ETHIOPIAN
SEMAY
ታስታውሱ እንደሆነ በሙያው
የድረገጽ “ኢንጂኔር” እና የሙዚቃ ባለሞያ የነበረ ‘ማዕዶት’ የተባለ የትግርኛ ሙዚቃ በመዝፈን ታዋቂነት አግኝቶ የነበረው በሰኔ
2021 ወር ወያኔ የገደለቺው እምብዛ ታደሰ የተባለ ዓዲጉዶም ገጠር የተወለደው የትግራይ ተወላጅ ባሰቃቂ አገዳደል መቀሌ ውስጥ
መገደሉን ይተወሳል።
ታሪኩን ሳታነብቡ የቀራችሁ
አንባቢዎች ልትኖሩ ስለምትችሉ ስለ አገዳደሉ ትንሽ ልበል።
እምብዛ ከፖለቲካ ንክኪ ነጻ የሆነ በፍላጎቱ በመነሳሳት በጦርነቱ ለተጎዱ
የትግራይ ማሕበረሰብ ሰብኣዊ ዕርዳታን በሚመለከት ለማስተባበር ከሚኖርበት ከአዲስ አባባ ወደ መቀሌ ሄዶ በነበረበት ወቅት በሹፌርነት
እንዲያገለግል በመንግሥት የተቀጠረለት ሹፌር ከነብሰገዳይ የወያኔ ቡድን ጋር ባደረገው ምስራዊ ግንኙነት እምብዛ ታፍኖ እንደተገደለ
ይታዋሳል።
ወጣቱ
በመቀሌ ከተማ በግምት ከቀኑ ሰባት ሰዓት በኃላ ባለቤቱ እና ልጆቹ ወደ እሚኖሩበት
ከተማ ወደ አዲስ አባባ ለመብረር ከቢሮ
ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ የአየር ማረፊያ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንዳለ ታፍኖ ደብዛው በመጥፋቱ በፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሐይሎች በተከናወነ አሰሳ ሙዚቀኛው በጨካኝ የከተማ ሽብር ተልእኮ አስፈፃሚ ወንጀለኞች በዓይደር ልዩ ስሙ ” ማረሚያ ቤት” በተባለ ስፍራ ተገድሎ ተጥሎ “ለጅቦች” ከተጣለበት
ስፍራ ቁርጥራጭ የሰውነት አካላቱን በመለየት በተጨማሪ ምርመራም፤ በአረመኒያዊ አፈፃፀም በጭካኔ የተገደለው እምብዛ መሆኑን ታወቀ።
በእነ ጌታቸው ረዳ በነ ደብረጽዮን
እና በነ ጻድቃን በነ ወዲ ወረደ ነብሰ በላ የወያኔ አመራሮች ትዕዛዝ ቁርጭራጭ አካላቱ ተለቅሞ ከተቀበረበት ቆፍረው ሬሳውን በማውጣት
እንደገና ለጅብ እንደሰጡት ድጋሚ ዜናው ሰምተናል።
ያ የጭካኔ አገዳደል እንዳይበቃ
ዛሬ ደግሞ አዲስ አባባ ውስጥ በታዋቂው ድምጻዊ ታሪኩ ጋንጊሲ (የዲሽታ ጊና ዘፋኝ) “የግድያ
ዛቻ” ደርሶት በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱት እያለቀሰ አዝኖ አሳዛኝ ትዕይንት ለማየት በቅተናል። ካሁን በፊት በተዋጣለት ሙዚቃ በመደሰትዋ
ባለቤቱ ‘ታሪ እወደሃለሁ’ እያለች ስታለቅስ እዝኖ እንዲህ ስታየው ምን እንደሚሰማት ገምቱ።
ታሪኩ በቅርቡ ባወጣው “ዲሽታ
ጊና” ሙዚቃው ዓለም በሙሉ ያስጨፈረ አስገራሚ በሆነ የሙዚቃ “ሪትም” (ምት) ታዋቂነት ማግኘቱ ሁላችን እናውቃለን።
ሆኖም፤ ወያኔን “ዱቄት” አድርገን
ሁለተኛ በጋንታ እንኳ መደራጀት በማይችልበት ዕድል “አመድ” አድርገነዋል ብለው አብይ አሕመድና “የጦር ጀኔራሎቹ” በተናገሩት ምላሳቸው እንደገና ሳያፍሩ ተመልሰው “የወያኔ ተዋጊ ሃይሎች በመደበኛው የመከላከያ
ሃይላችን መግጠም ስላልቻልናቸው የሕዝብ ድጋፍ ያስፈልገናል እና ሕዝባዊ የጦርነት ድጋፍ ለሰልፍ ውጡ ተባለ።
በጥሪው መሰረት ታሪኩም አዲስ
አባባ በተደረገው የጦርነት የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ “የተሰማው
የሰላም ድምጽ” በማስተጋባቱ ምክንያት የስድብ ውርጅብኝ እንዳይበቃው ኢንተርሃሙዌው ቡድን እንደሚገደለው የግድያ ውሳኔ አስተላለፈበት።
ይህ የዜጎች የመናገር መብት
ከመጣስ አልፎ በመስመራቸው ያልሄደን ሰው በግድያ እንደሚወገድ በወያኔ አይተነዋል። ዛሬ ደግሞ በአብይ አሕመድ ኢንተርሃሙዌው ቡድን ደጋፊዎችና መሰል አጨብጫቦዎች
ታሪኩን ለመግደል ዝተዋል።
እነዚህ ነብሰ ገዳዮች ወደ
ጦር ሜዳ ወርደው ከመታኮስ ይልቅ “እራሳቸው በማይካፈሉበት የተለመደው
“የበለው፤ቁረጠው ቀረርቶ” ባለማስሰማቱ ምክንያት ከፖለተካ ደባ ነጻ የሆነ በቅንነት የተሰማውን የሰላም ስሜት ለሕዝብ በማስተላለፉ
የግድያ ዛቻ ሲደርስበት የኦሮሙማ ባለሥልጣኖች ሁሉ “ዕርቅ እና ሽምግልና” ሲሰብኩ ግን በነሱ ላይ “የግድያ ማስፈራራት አልደረሰም።
ለምን ቢሉ “ኢንተርሃሙዌው
የሚያንቀሳቅሱት እነሱ ስለሆኑ፤ ጌቶቻቸው ሚናገሩት ሁሉ “የሃዋርያት ቃል ነው” ብለው ስለሚያምኑ ‘ቅር’ አይላቸውም።
የወያኔ ኢንተርሃሙዌውም ቡድን
ባሕሪው ልክ እንደነዚህ ነው። እምብዛ ታደሰ ሲገደል የወያኔ ቡችሎች “ዕልልታቸው” አቅልጠውት ነበር። ይህ የፋሺስት ተከታዮች ባሕሪ
በመላ አገሪቱ ተስፋፍቷል።
ፋሺሰቶች ምክንያታዊነትን ማለትም
“ራሺናል” አስተሳብን ያወግዛሉ። ፀረ-ምክንያታዊነት የሆነ መንግሥትና ተከታይ ለ30
አመት ሥር ሰዷል። በወያኔም በኦነግ /አብይ/ ተከታዮች የምናየው ይህ ነው። ይህ ትውልድ “አብሪ” ሀሳቦችን እንደማይቀበል ተደርጎ ተቀርጿል።
አስቦ ከመሄድ ይልቅ በደመነብስ ይደነፍል። እኔ ፌስቡክ አባልነት ከገባሁ
አንድ አመት ከምናምን ውስጥ እየታዘብኩት ያለው አብዛኛው የ45 አመት ትውልድ “በግንፍልነት እየተነሳሳ “የጭንቀት” እርምጃዎችን ሲከተል ታዝቤአለሁ።
የአገራችን የሃገር ግንባታ ሂደት በሰንት ጭንቅ እንደተገና አያውቅም። ሀገርን አንድ ላይ በሚያደርጉ ስሜቶች አይጓዝም። ድጋፉም ውሳኔውም በደመ ነፍስና በነገድ የሐረግ ሰንሰለት
ተያይዞ ከከነፈው ጋር አብሮ ይከንፋል። ይህ ደግሞ የፋሺሰቶች መንጋ ዓይነተኛ
መለያ ባሕሪ ነው።
ለ27 አመት እና አሁን ለ3
አመት ሥልጣን ላይ ያለ መንግሥት የሚከተለው ባሕሪ “ፋሺስታዊ ርዕዮት” መሆኑን ለክርክር አይቀርብም (ወያኔ ማለት ያው ኦሕዴድ/ብልጽግና
ማለት ነው)። ወጣቱን ያስተማሩት በጣም ጨካኝ፤ ሰውን በበማስፈራራት የሚደነፋ፤ አረጋዊያንን የማያከብር ሃገራዊ ክብር የሚያነቋሽሽ
“ባለጌ ትውልድ” እንዲሆን ቀርጸው በአምሳያቸው ወልደውታል።
ለፋሺስት መሪዎችም ሆኑ ተከታዮቻቸው
ማንኛውም ነገር ምክንያታዊ የሆኑ ትንታኔዎች ሁሉ ስህተት ናቸው። ሰዎች መነሳሳት የሚችሉበት ዘዴ በስሜት እንጂ በምክንያት አይነሱም።ለዚህ
ነው በስሜት መሪዎችን የመደገፍ ወይንም ሰዎችን የመግደል ፍላጎት እያደረባቸው አገሪቱ ችግር ላይ የወደቀቺው።
መሪያቸው አብይ የሚናገረው
ስታደምጡ በስሜት ስለሚከንፍ ዛሬ የተናገረው ነገ ተቃራኒው ሲነጋር እንሰማዋለን። ለዚያም እርማትም ሐፍርትም አይሰማውም። ምክንያት
ትውልዱ እና ዕድገቱ በዛው ርዕዮት ተቀርጾ ያደገ ስለሆነ ሕዝብ ይታዘበኛል
የሚል ሰቀቀን አይሰማውም።በስሕተታቸው አመላክቶ የሚሞግታቸው ሰው አይመቻቸውም።
ምክንያቱም ከነሱ ሌላ ውጭ
ያለው አመለካካት “በማስፈራራት በፍራቻ” እንዲዋጥና እንዲገዛላቸው ይፈልጋሉ።
ትናንት ሄንሪክ ሂምለር
(Heinrich Himmler 1900-1945) የተባለው የናዚ ሂትለር መንግሥት ያደራጀው “ኤስ ኤስ” የተባለው ወታደራዊ የታጠቀ
መንጋ ሠራዊት መሪ ሆኖ የተመደበው የዚህ ሰው የግል ታሪክ ስመለከት
ነበር ያመሸሁት። ታዲያ ሄንሪክ “አይሁድ” መጥፋት አለበት የሚለው መፈክሩን በተመለከትኩት የግል ህይወት ታሪኩ በዩቱብ ሳደምጥ
አይሁዶች ብቻ ሳይሆኑ ናዚን የሚቃወሙ ነጭ ጀርመኖችም ጭምር የሚያንጸባርቀው ትዕቢትና ጭካኔ በጣም ያስፈራል። በዚያ ረዢም የፊለም ማሕደር “ናዚስ ኢን ፓወር” በሚል ርዕስ
ውስጥ የሰማሁትን ላካፍላቸሁ።
እንዲህ ይላል፡
“The best
political weapon is the weapon of terror. Cruelity commands respect. Men may
hate us, but we don’t ask for their love, only for their fear” (ሄንሪክ ሂመለር- Heinrich
Himmler) ስተረጉም እንዳላበላሸው እንዲህ ነው፤
“ምርጡ የፖለቲካ መሳሪያ “ሽብር”
ነው። ጭካኔ “አክብሮትን” ያዛል። ሰዎች ሊጠሉን ይችላሉ፣ እኛ ግን “ፍቅራቸውን አንጠይቅም”፣ የምንጠይቀው ‘’ፍራቻቸውን” እንዲያሳዩን
ብቻ ነው” (ሄንሪክ ሂመለር) ይል ነበር።
አሁን ደግሞ ይባስኑ የታሪኩ
ዲሽታ ጊና ህይወት ለመቅጠፍ አሰፍስፎ የተዘጋጀ ጅብ መኖሩን ስንሰማ ኢንተርሃሙዌው ዓለም ያወቀው ዘፋኝ “የግድያ ዛቻ ደረሰበት” ተብሎ ሲሰማ ኢትዮጵያዊያን የነበረንን
ዝና እንዴት እንደሚበላሽ ልብ አላሉትም።ልብ ቢሉም ፍላጎታቸው በማስፈራራት ማስፈጸም ነውና።
እነዚህ በደመ ነብስ የሚጓዙ
ወረበላዎች ማንም ይሁን ማን በመስመራቸው ካልተጓዘ ምርጫቸው እርሱን/እርስዋን/ ማጥፋት ነው።
ጣሊያናዊው ማኪያቬሊ ሰዎችን
ማታለል/ማጭበርብር/ ሰላምን እና ስርዓትን የሚጠብቅ ቢሆን ኖሮ የሞራል አስፈላጊነት ባላስፈለገ ነበር ይላል።መሪዎቹም ተከታዮቹም
በበሰበሰ ሞራል የሚዋዥቁ ናቸው። ይህ የተለመደ ግድያ በደርግ ወቅት ነበር፤ በወያኔ ዘመን ነበር፤ አሁንም አለ። ይህ ዕብደት እንደ
ሥልጣኔ እየተያዘ ሕግ እየጣሰ ነው።
በዲሞክራሲ ስም የ30 አመት
የኢትዮጵያ መሪዎችና ተከታዮቻቸው ስንት ጊዜ በማጭበርብር እና ዜጋን በማሰር፤ በማስፈራራት ጨዋታ ውስጥ እንዲህ እንዲቀጥሉ እንፈቅዳለን?
ይህ እንዳይቀጥል፤30 አመት
ሙሉ እየተነደፍንም ሆነ ከሥር እየተወጋን ፍትሕን ከመከላከል ያልቦዘንን በታሪክ እርሻ የምንገኝ የፍትሕ ሰብል አምራች ገበሬዎች ልፋታችን መና እየቀረ ነው። ለምን?
ጽሑፉን ሼር አድርጎ የመጋራት
ጠቀሜታ የማይፈልጉ የአብይ አሕመድ ጀሌዎች “ሼር” እንዲደረግ አትጠይቅ ማለት ጀምረዋል። ሃሳብን ለላደረሳቸው እንዲደርስ ማድረግና
ያላየ ያልሰማውን ማሕበረስብ እንዲያወቅ ይረዳል። ስለዚህ ተጋሩት። የአብይ ኣህመድ እና የተለያዩ የኢንትርሃሙዌው መንጋዎች “ምርጡ
የፖለቲካ መሳሪያ “ሽብር” ነው፤ ሲሉ እኛ ደግሞ “ምርጡ የፖለቲካ
መሳሪያ “መረጃ” ነው እንላለን።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment