Monday, November 15, 2021

የጽንፈኝነት ዘመን አገዎች እና ትግሬዎች ጌታቸው ረዳ 11/15/2021 ETHIO SEMAY

 

 

የጽንፈኝነት ዘመን አገዎች እና ትግሬዎች

ጌታቸው ረዳ

11/15/2021

ETHIO SEMAY

 በመግቢያየ ይሀንን ጥቅስ በመጀመር ልጥቀስ። የህ ጥቅስ የአንድነት ጸር የሆነው አገር አፍራሽ “አማራዊ ኢንተርሃሙዌው ጽንፈኛው” ቡድን አይመለከተውም።ይህ ንጹህ አመለካካት ያለው ከብሩህ ወላጆች ብቻ የተወለደ አማራውን ብቻ የሚመለከት ነው።

”የመጀመሪያ አማራ “ባለትልቅ ባህል” እና  “ባለ ትንሽ ባህል” ተብለው በሚታወቁ ሁለት መደቦች የተከፈለ ነው። አማራው ኃይሉን በከፍተኛ ፍጥነት እያጠናከረ ላ ቀር የሆኑትን አገዎች በቁጥጥር ማድረጉን ቀጠለ።  የባህል ልውውጥ በእንካ --በእንካ ቢሆንም፤ የአማራ ባሕል የበላይነቱን መያዝ ቻለ። አገዎች ከጥንታዊ አማራ የተማሩት የቴክኖሎጂና የአደረጃጀት ስልት አካባቢያውን መቆጣጠር ስላስቻላቸው፤ ባለ ማረሻ ሞፈርና ቀንበር ሌሎች የብረት መሣሪያዎችንና እርሻ ዘዴዎችን ማረስ ጀመሩ።” (“ቅማንት አረማዊ ኢትዮጵያዊ ገበሬ” -ደራሲ ፕሮፌሰር ሲ ጋምስት እንደጻፈው ) ትርጉም ወዳጄ ፕሮፌሰር ባዩ ቦጋለ ላቀው)

 

ይህ ጥቅስ ላቀርብ የቻልኩት ከታች እያነበባችሁ ስትደርሱ የምታገኙት ተያያዥ ምክንያት ነው።

ለ30 አማታት በተለይ በዚህ 4 አመት ጽንፈኞች ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየቋመጡ ነው። ከውስጥ ሥልጣን የያዘው ኦሮሙማው መሪ እና ወያኔ ከነጀሌዎቹ ሲደመሩ ብዙ ጽንፈኞች ተበራክተዋል።

 አገራችን ውስጥ ገንኖ ያለው ቋንቋን እና ድመበርን አስታክኮ ዓይነተኛ የማንነት መለያ ተደርጎ እየተወሰደ ከፍተኛ ስሕተት “ችግር” አምጥቷል።

ሕዝባችን ችግር ላይ ወድቋል።  ሕዝብ ማለት ምን ማለት ነው? ብለን ብንጠይቅ የግለሰቦች ስብስብ በማለት ቀጥተኛውን መልስ መስጠጥ እንችል ይሆናል። ግን በታሪክ ዓይን ትርጉሙ “ህዝብ የህይወት ታሪክ” ማለት ነው። የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ካለፈው የተወረሱ ቋንቋዎች በመጠቀማቸው የነገድ ጽንፈኞች ያንን ወደ ግል የፖለቲካ መጠቀሚያ አድርገው ብዙ ኪሳራ እያደረሱበት ነው።

እኛ ትግሬዎች ብቸኛዎቹ አክሱሞች ነን፤ እኛ አገዎች ብቻኞቹ አክሱሞች ነን የሚሉ ጽንፈኞች በእርግጠኛነት ሲናገሩ መስማት እጅግ ያስገርማል። ያ ደግሞ የሚናገሩት ቋንቋ እና የሚኖሩበት አካባቢ መሰረት በማድረግ ነው። ፖለቲከኞችም ሆኑ በጠቅላላ ህዝቡ የወረሰው ቋንቋ ፈጣሪዎቹ እነማን መሆናቸው በመላምት ካልሆነ “ታሪክ” እርግጠኛ ሆኖ ፈጠሪዎቹ እነማን መሆናቸው ሊነግራቸው አይችልም።

ምክንያቱም “ድምበርም” ሆነ “ቋንቋ” ግለሰቦች የፈጠሩት ሳይሆን የብዙ ማሕበረሰብ እና የአሕዛብ የዘመናት መስተጋብሮች ውጤት ስለሆነ።

የወላጆቻቸው ቋንቋ መናገር የዚያ ነገድ ሰው ናቸው ማለት የግድ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም “ቋንቋ” “ስልጠኔ፡ እና “የትውልድ ሐረግ” ካንድ ነገድ ወደ አንዱ በቅብብሎሽ ሲተላለፍ እማሀል ላይ ይቋረጣል፤ ወይንም ብዙ የቅርጽና የይዘት ለውጥ እያመጣ መጨረሻ ሌላ ሆኖ ይወለዳል። “ኦሪጂናሉ” ይከስማል ማለት ነው። የጠፉ ነገዶች እና ቋንቋዎች አሉ “አገራችን ውስጥ!!”። ለዚህ ነው ቋንቋውን ብቻ ስለተናገርክ “እኔ የዘመነ አክሱም ፈጠሪ ነኝ”  ማለት የማያስኬደው።

አሁን ኦሮሞዎች በታሪክ ማሕደር ከሄድን “አዲሶች ናቸው”፡ አሁን ተንሰራፍተው የሚኖሩባቸው ቦታዎች የኛ ነውና ውጣ እያሉ የሚያባርሩትን ነባር ኗሪ ስትመለከቱ አይገርማችሁም? (ያውም የሰው ልጅና ነብሰጡር አጋድመው እያረዱ!)። አንድ ማሕበረሰብ እዛው አካባቢ በመገኘቱ ጥንታዊ ባለቤት ነው ብሎ በሙሉ ልብ መሞገት አይቻልም።

ሰሞኑን መኳንንት የተባለ የአጎብ ማሕበረስብ አዝማሪ/ዘፋኝ/ በ ‘ድምጺ ወያነ’ ቀርቦ መቀሌ ውስጥ ሆኖ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ሳደምጥ በጣም ገረመኝ። ካሁን በፊት እዚህ ዋሺንግተን መጥቶ እያለ “ኩሩ ኢትዮጵያዊ” እያሉ ሲያሞካሹት ሰምቼ “የተቃወምኳቸው ሰዎች ነበሩ። ሲያንጸባርቃቸው ከነበሩ መንገዶች የወያኔ ፍቅር ስታዘበው ስለነበር ሁለት ትችቶች ጽፌ ነበር። ዛሬ ዓይን አፍጥጦ በግሃድ ወያኔ መሆኑን እና ጸረ-አማራ መሆኑን ነግሮናል።

አማራውን “የአገው ባህል ዘራፊ” በማለት ማሕበረሰቡን በጸያፍ ቃላት ሰድቧዋል። አልተመቸምና መተቸት አለብኝ አልኩ።

 “ትምህርት” እና “ሥርዓት” ያልገረፈው ይህ ዳንኪረኛ አማራን በዚያ አንደበት ሲኮንን ምንም ስቅጥጥ አላላውም። አማራ የኛ ሕዝብ ነው፤ ሁሉም ነገዶች የኛ ዘር ናቸው፡ ዜጎቻችን በፖለቲካ ሴራ ሲዘለፉ ዜጎች ነን እና እኛን ነክቶናል ማለት ነው።

እኔ ምሁር አይደለሁም “ገበሬ” ነኝ፤ ይልና እንደገና “አገውና ትግሬ” ብቻ አክሱማዊያን በማድረግ ሌላውን ገለል ያደርጋል። አገው መሆን እና ትግሬ መሆን ምንም ማለት አይደለም፡ ሁለቱም ከሁሉም ኢትዮጵያ በተለይ ከአማራው ጋር ተዋህደዋል።

ሆኖም የዛሬ የትግሬ እና የአገው ጽንፈኛ ፖለቲከኞች ያለፈውን  ታረክ እየመዘዙ የአክሱም ብቸኛ  ባለቤቶች ነን በማለት ባልነበሩበት የታሪክ ዘመን እጅግ ከሚገባቸው በላይ “ሲቀደዱ” እሰማለሁ። ግን ከሚገባቸው በላይ መቀደድ እውነታው አይቀይረውም።

አገዎችን ለማወቅ የቻልኩት ስለ ጥታዊ አክሱም ተመራማሪዎች የጻፉትም ሆነ የአዶሊስ ንጉሥ የሚባለውን የተወው ጽሁፍ እየደጋገምኩ ስመለከት “አክሱም ከተማ ውስጥ”  እንደነበሩ አያሳይም። እርግጥ ነው እንደማንኛቸውም የዚያው ጊዜ ሰዎች በአክሱም ነገሥታት የራሳቸው ቦታ እና የነገድ መጠሪያ ነበራቸው።

አገዎች “የአክሱማዊያን ከተማ ኗሪዎች እና ሃወልቱንም ወርቁንም ግንቡንም ሲያንጹ ነበር” የሚባለው ስሕትት እርማት ያስፈልገዋል። ያን መቀደድ እኔም ሳላውቅ እደግመው ነበር። የሚገርመው ደግሞ ከዚያም አልፈው ጤፍ ማምረትና ግብርናን ያስተማሩ ናቸው እየተባለ ሲቀደዱ ነበር። ያ ውሸት ነው። (ከላይ በጽሔፌ መግቢያ የጠቀስኩትን ይመልከቱ)

 “በአክሱም ንጉሥ በዘመነ ንጉሥ ካሌብ ሁለተኛ (በኤላ አጽብሃ) ጊዜ ከተጠቀሱት በምርኮ እና በነገዳቸው ተዋጽኦ አክሱም  የነገሥታቶቹ “ሚሊሺያዎች” (ሕዝባዊ ሠራዊት) ውስጥ አገዎች ተጠቅሰዋል።

ከነበሩ ወታደሮች ውስጥ “አታገው፤ገበላ፤አዘቦ፤ መአት፤አገው፤ሰበራት፤ስራኤ፤ዳማዋ ፤ ዳኩን (ዳኩዌን) ፤ላከን፣ ሐራ፤መቲነ፤ መሐዛ፤ ፋልሐ፤ ሐለን” እነዚህ ሁሉ በዘመነ ኢዛና ሁለተኛ (5ኛ ክ/ዘመን) እና በንጉሥ ካሌብ እና በሗላም በንጉሥ ዋዜባ የተገኙ ጽሁፎች ተጠቅሰዋል።

ሆኖም በጠቀስኩዋቸው ወታደራዊ አቀጣጠር የተመለመሉ ወታደሮች እንደሆኑ እንጂ እራሱ የአገው ነገድ መሰረቱ አክሱም አላደረገም፤ ወይንም አክሱሞች አገዎች አይደሉም። እንኳን አገዎቹ  የግዕዝ ነገዶች ነን  የሚሉ ትግሬዎች አክሱሞች መሆናቸው ምንም ማስረጃ አልተገኘም። አንዳንድ አገዎች እንደማንኛውም ዜጋ የአክሱም ኗሪ ሆነው ሊኖሩ ይችላሉ። ያግን ምንም ማለት አይደለም። ሆኖም ከከተማው ውጭ አሁን በሚኖሩባቸው ተራራዎች እና ቆላማ ስፍራዎች በአክሱም አስተዳዳር ሥር መኖራቸው እርግጥ ነው። ያ ግን የአክሱምን ሥልጣኔ ለሁለቱ ነገዶች ብቻ በብቸኛ ባለቤቶች አያደርጋቸውም።

እንደጠቀስኩት ከላይ የተጠቀሱት ወታደራዊ ስሞች ከየነገዳቸው የተወሰደ መጠሪያ ነው።

እንኳን ድሮ የትግራይም ሆነ የአክሱም ከተማ ኗሪም ሆነ በቀርቡ የሚጎራበተው “ቤገምድር” አስገራሚ ቅይጥነት የሚታየው ማሕበረሰብ ነው (የግሪክ ዘር፤ የአይሁድ ዘር የሶርያ፤ የመን ዘር፤ የቤጃ ዘር ሁሉ ለዘመናት የተዳቀሉበት ቅይጥ ማህበረሰብ ነው)። የመን ውስጥ “ከዳም” ተብለው የሚጠሩ እኛን የሚመስሉ ዛሬ ተገልልው በተራራው ስር በችግር የሚኖሩ ማሕበረሰቦች አክሱማዊያን የልጅ ልጆች… ሚሊሺያ ወታደሮች ናቸው።አክሱሞች ማንን ይመስላሉ ብትሉ እነሱን በዩ ቱብ እዩ እና ፍረዱ፡(አኔን አንተን አንቺን ነው የሚመስሉት)። አሻራው እዛ ማየት ትችላላችሁ።አሁን እነሱ ስትመለከቱ “ትግሬዎች አገዎች አማራዎች፣..” ብላችሁ በመልክ ልትለዩ ትችላችሁ? አንዳንዱ አይቻልም። በትጠይቁዋቸው እኔ ትግሬ ነኝ አገው ነኝ አማራ ነኝ አይሉም። በ6ኛው ክ/ዘመን አረቦች የጻፉት የመን ውስጥ ሁለት “አማራ” ነገሥታት እንደነበሩ ግን እርግጠኛነት ልነግራችሁ እችላለሁ።

አንዳንድ ጽሁፎች “ፈላሻዎች አገዎች” ናቸው የሚሉ አሉ። ንግግራቸውም ጥቂት ጥቂት ይለያል እንጂ አንድ ነው የሚሉም አሉ (እኔ አንድ መሆኑን አላውቅም)። እኔ ያነበብኩት ደግሞ “ቅማንት” የተባለው “የአገው ዝርያ ቅርንጫፍ(?)” ከፈላሻ ጋር ምግብ ከበላ ከማሕበረሰቡ ይገለል እንደነበር አንብቤአለሁ (Henry A. Stern በተባለ ደራሲ Falashas in Abyssinia የሚለውን አንብቡ)።

አክሱም የሚለው ቃል አገው ነው ብለን ስንጽፍ ነበር ፤ ሆኖም ከየመን የመጡ አበሾች የሰጡት አረባዊ ቃል ነው የሚሉ የትግራይ የድሮ ጸሐፍትም አንብቤአለሁ። ሌሎች ትርጉሞችም አሉ። ያንን በመሞርኮዝና አገዎች በአክሱም ወታደራዊ ቡድን መጠቀሳቸው “አክሱሞች” (የከተማው) ሆኖው ሳይሆን አክሱም ከሚያስተዳድራቸው ነገዶችና ከተማረኩ ነገዶች ውስጥ ወደ ወታደራዊ አገልግሎት ገብተው ለአክሱም ነገሥታት የወረራ ዘመቻ  ተልዕኮ “ሚሊሽያ” ሲመዘዝ “አገውም” እንደ ማንኛቸውም ነገዶች ተዋጊ ሚሊሽያ (ሕዝባዊ ሠራዊት) በማዋጣት ሲያገለግሉ  የነበሩ ናቸው።

አክሱም ውስጥ የነገሥታቱ የክብር ዘብ (ቦዲ ጋር) አገዎች ነበሩ የሚለው ውሸት ነው። አከሱም ነገሥታት የጻፉት ያንን አያሳይም። ሚሊሺያዎች ነበሩ፤  በቃ! ሌላ “ሳሪሃ ማሪሃ” የለውም።

አገዎች ተራራማ እና ድምበር አካባቢ ይኖሩ ስለነበር አገዎች ወታደር ከመሆን አልፈው’ የአክሱምን መንግሥት የሚረዱበት ሌላው መንገድ  ነበር። ይኼውም የአገዎች መንደር ከአክሱም ወደ ደቡቡ አቅጣጫ ስለበር ፤ ‘ንጉሡ “የዝሆን ጥርስ እና ዕጣን/ሽቶ…” አስይዞ የወርቅ ሳንቲሞች ለመስራት የሚያገለግል ወርቅ እንዲያመጡለት ነጋዴዎቹን ወደ ውጭ ወደ “ሳሱ /ካሱ/ (ሱዳን)” ሲልክ’ ነጋዴዎቹ “በአገው መንደር” አድርገው ስለሚሻገሩ በአገው “አገር ገዢ” መልካም ፈቃድና ትብብር  በሰላም እንዲልፉ ይተባበሩ ነበር።

በመጨረሻ ግን አገዎች እና ፈላሸዎቹ ከአክሱም ንጉሥ ጋር ተጣልተው አንገዛም ብለው ሲያድሙ በዚያው ተቃራኒ “በሰሜን” በኩል “ቤጃዎች” የንግድ መተላለፊያ መስመሮችን ሲዘጉ “በደቡብ” በኩል ደግሞ “አገዎች” የመተላለፊያ የንግድ መንገዱን በመዝጋታቸው፤ የንግድ አንቅስቃሴ ችግር ውስጥ አስገቡት።በዚህ ሰበብ “የወርቅ ሳንቲም” መስራት አቆመ።

እዚህ ላይ የአክሱም አወዳደቅ ልክ “ግራኝ አሕመድ” ኢትዮጵያን ባዶ ካደረጋት በኋላ “ኦሮሞዎች” ያንን ክፍት ቦታ ተከትለው ገብተው እስከ ትግራይ እና ጎጃም ጎንደር አገሪቱን በመውረር ድምጥማትዋን እንዳደረግዋት ሁሉ የአክሱም አወዳደቅም እንደዚያ ነበር። ዩዲት/እሳቶ/ አገው “ከሆነች” አገዎች አክሱም ድምጥማጥዋን አወጥዋት ማለት ነው። ምክንያቱም አገዎች አክሱምን ካቃጠሉ በላ፤ እነሱን ተከትለው “ትግረ ቤጃዎች” ከሰሜን መጡና ኣክሱምን አፈረሰዋት። ታሪኩ ይህ ነው።

ጉዲት አገው ከሆነች ጉዲት አክሱምን አጠፋቺው የሚለው ታሪክ አብራችሁ ስትመለከቱ አክሱም የነሱ ቢሆን ኖሮ ድምጥማጡን አያፈርሱትም ነበር።

ሃረንዳዋ እና ስናፊጅ (ትገረ ቤጃ) አክሱም ከተማን ወርሮ እዛው ሲኖር ከወደ 300 አመት በሗላ ትግሬዎች ያንን “የትግረ ቤጃዎችን ስም” ይዘው ግዕዝ አስወግደው “ከተለያዩ አካባቢያዊ መነጋገሪያ ቋንቋዎች’ ግዕዝ፤ቤጃ፤ኩናማ፤ዓረብኛ፤ ግሪክ፤…ወዘተ ወዘተ…ቀይጠው ሌላ ቋንቋ ይዘው ትግሬ/ትግራይ/ትግርኛ የሚል ቃል እና ማሕበረሰብ ተከሰቱ። ትግርኛ ውስጥ ያሉ አረባዊ ቃላቶች በርካታ ናቸው።

ማን ከማን ተበደረ የሚታወቅ ነገር የለም። ዓረቦች “ሐዘን፤ሞት፤ ኩሎም፤ ፍቅር፤ መዘከር፤ ቡና፤ ጀበና፤ ፍንጃል….” ወዘተ የሚል ሁሉ በትግርኛም አማርኛም ውስጥ ይገኛሉ። ስለሆነም ነው ቋንቋ ማን ፈጠረው? የሚለው መልስ ለማግኘት እጅግ ከባድ ፈተና የሚሆነው። ለዚህ ነው የታሪክ ደናቁርት “የኛ” “ኬኛ” እያሉ በአሰልቺ ፍትግያ ሲፋተጉ ስንመለከት ገራሚ ነው የምለው።

በ30 አመት ውስጥ አዲስ አበባ ያደጉ ወጣቶች “ህ” እንደ “ክ” ሲያደምጡና ሲጽፉ ማየት አግራሞትን ይፈጥራል። እንዴት ነህ (እንዴነህ)? ለማለት “እንዴነክ” እንዴት ነክ” ይላሉ። “አይዞህ” ለማለት “አይዞክ” ይላሉ፡ “አየህ? ለማለት “አየክ? ሲሉ ይገርሙኛል።

ይህ ለውጥ ጀማሪው ማን ነው? ቢባል ማንም መልስ ሊሰጥ አይችልም። አክሱም ስልጣኔም የውሱኖች ነገዶች ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ነገዶች ውጤት ነው። ከዚያም ባሻገር ”የሶሪያ፤ግሪክ፤ሮም፤የአይሁድ እስራሎች፤ የየመኖች፤ ‘የኮፕቲክ ግብፆች’ እና የዓረቦች… አስተዋጽኦ ውጤት ነው። ተስአቱ ቅዱሳን “የሶርያ| ሰዎች እንጂ ትግሬዎች ወይንም አገዎች አይደሉም።

የላስታ ላሊባ ነገሥታት አገዎች ናቸው የገነቡት ይላሉ። የግዕዝ እንጂ አገውኛ የሚያሳይ ምልክት የለም። አንድ ቦታ አንድ ሥልጣኔ ስለተመሰረተ “የኛ” ነው ማለት ይገርማል። አገዎች ብቻቸውን ያንን የላሊበላ ሥልጣኔ አልገነቡትም።  አንዳንዶቹ ስለ የ “ላሊበላ” ትርጉም ሲነግሩን እንዲህ ይላሉ፦

“ላሊ” ማለት በአገውኛው “ንብ” ማለት ሲሆን “በላ” የሚለው አማርኛ  ስለሆነ  ስለዚህ ይላሉ “|ንጉሡ አማርኛ ስለማይችል|” አጋጣሚ ንብ ስለነደፈው “ንብ በላኝ” ለማለት እንዳይል “ላሊ በላ” አለና በዛው ተሰየመ ይላሉ። ይህንን እኔ አልገዛውም።

ወደ መኳንንት ልመሰልሳችሁ፡

አገው በሉኝ ባዩ “አዝማሪው መኳንንት” አማራ የሚባል ሕዝብ “የአሸንዳ” ባህላችን ነጥቆ የአማራ ነው ብሎ እየጨፈረበት ነው ይላል። አሸንዳ አክሱም ስለተፈጠረ፤ ባለቤቶቹ እኛ አገዎች እና ትግሬዎች “ብቻ” ነን ባለቤቶቹ ይላል። መኳንንት በዚህ አላቆመም፤ “ወያኔ ካሸነፈ፤ አማራ ሲጨቁነን የነበረ ተፍቆ ብርሃን ይበራልናል!” ይላል።

መኳንንት እየዘፈነ የሚጨፍረው ምት የአማራዎች እንጂ የአገዎች አይደለም። እርሱ በምን ምስክር ወረቀት ነው የአገው ያደረገው? መኳንንት አገው ነኝ ካለ “አማሮች የሚጨፍሩበትን ብቸኛ እና አንድ ወጥ የሆነውን እስክስታቸውን ለአማራዎች በመተው” ያንን ትክክለኛ የአገዎች የሆነ “ጃንጥላ እያስከረከሩ በሽንጥና በቂጣቸው የሚያወዛውዙትን “የአገው/አዊ” ምት መጫወት አለበት።

የአማራዎች አስክስታቸው ተመሳሳይ እና ትከሻቸው እና አግራቸው ላይ የሚመቱት ምት ብቸኛ የነሱ ብቻ ነው። ሌላ እስክታ የላቸውም። ስለዚህ መኳኳንንት አማራ የኛን ባሕል ነጠቀ ከማለት የአማርኛን ዳንኪራ እስክስታ መምታቱን ተውና “ጃንጥላ ተይዞ በሽንጥ የምትዞሮውን እና በቂጥ የሚወዛወዘውን አገዋዊው ምት” መለማመድ ጀምር። መትፋት ያስነውራል ሲባል አልሰማህም?!

አክሱም የአገውና የትግሬ ብቻ ነው ብሎ የነገረህ ት/ቤት ማን ይባላል? “ደደቢት ት/ቤት ነው? ሆኖም ቀረ፤ ይህ ሁሉ ፈረንጅ፤ ሶሪያ (ተስኣቱ ቅዱሳን) አይሁድ፤ግሪክ፤የመን፤ ዓረብ… እዚያ ከተማ ሲርመሰመስ ለብቻው “አማራ” አልነበረም “አገውና ትግሬ ብቻ ነው፡ የሚባል ቅዠት እንዴት ተቀባይነት ሊኖሮው ይችላል!?

ደናቁርት ሆይ! ከነገድ  ቆጠራ ከድንቁርና ወጥታችሁ፤ ነገዳችሁ ሳታስወቅሱ በሰው ሰውነታችሁ ኑሩ!!! ኦሮሞዎች ተው እባካችሁ ስንላቸው መጨረሻ ሲበዛብን ከየት እንደመጡ መጻሕፈቶች መውጣት ጀመሩ። ስለዚህ መከባበር ጥሩ ነው። (አገው በዘመነ አክሱም People’s militia እንጂ ምንም አልነበረም)

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

 Mekuanint Tegadalay

ፃንሒት ምስ ስነ-ጥበባዊ ተጋዳላይ መኳንንት መለሰ 14 _11 _ 2021

https://youtu.be/F11aXd0SI48

    

No comments: