በሁለት ትግሬዎች የተጻፈ ስለ ወልቃይት መጽሐፍ አነበባችሁት? እንዲህ ይላል?
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)
Tuesday, May 26/2020
መጽሐፉ ከትግራይ ተልኮልኝ የደረሰኝ ምናልባት አንድ ወር ይሆነዋል። በሥራ መወጠር ምክንያት አላነበብኩትም። ጊዜ ሳገኝ አንብባቸዋለሁ ብየ ተራቸውን እየጠበቁ ካሉት መደርደሪያየ ውስጥ ካሉት ይህ በመዝገበ ጎይተኦም እና በጎይተኦም ተኸስተ የተባሉ የወያኔ ጋዜጠኞች ስለ ወልቃይት የተጻፈውን መስትያት መንነት- ታሪክን አማፃፅኣን ህዝቢ ወልቃይት ፀገዴ (2009 ዓ.ም)” የሚል መጽሐፋቸው ድንገት ስገልጠው ለማንበብ ዕቅድ ባይኖረኝም እስኪ ልየው ብየ በቁሜ ገርፍ ገረፍ ሳደርገው አስገራሚ የሆኑ የተዛቡ ፤በይሆናል የተተረጎሙ ትንታኔዎችን እስከ ገጽ 21 ድራስ ተመለከትኩት። ሙሉን ሳነበው እመለስበታለሁ። እስከዛው ድረሰ ግን እየሳቃችሁበትም ቢሆን አንብቡት።
ከላይ የተጠቀሰው መጽሐፍ የተጻፈው በትግርኛ ሲሆን የርዕሱ ትርጉም በአማርኛ ስተረጉመው እንዲህ ይነበባል “ የማንነት መስተዋት- የወልቃይት ሕዝብ ታሪክና አመጣጥ” ይላል። ያንን ለወደፊቱ የምምለሰው ቢሆንም ካሳቀኝ ነገር ልተንትን።በነገራችን ላይ በመጽሐፉ መግቢያ ውስጥ ያሳተሙት ካርታ እንደ መቅድም የወያኔ ኢትዮጵያ ካርታ ነው። የትግሬ/ኢትዮጵያውያን አክሱማዊያን መሬትን አያከትትም። ክሐደት አንድ ከዚያ ይጀምራል።
ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት ግን አጋጣሚውን ልጠቀም እና አንድ ነገር ልበል። ሰሞኑን የታዘብኩት ነው። ይህንን ስተነትን አንድ የማላልፈው ቅረታ ለማንሳት ትዝ አለኝ። የወልቃይ ጉዳይ የኛ ጉዳይ ነው ብለው የወልቃይትንና አማራውን ሲያሰቃዩ ሲገድሉ ሲያስጨንቁ የነበሩት “ኤርትራኖችን እንኳን የነፃነታችሁን ልደት ቀን አደረሳችሁ (ትርጉሙም ‘እኛ የድሮ የወያኔ ታጋዮች እነዚያ ጠላቶች ብለን አብረን ከናንተው ጋር የወጋናቸውን፤የገደልናቸውን ኢትዮጵያውያኖችን፤ ሲመኩበት የነበረውን ባሕራቸውን አስዘግተን ነፃነታችሁን የተቀናጃችሁ አርበኞች ኤርትራውያን “ለነፃነታችሁ በዓል እንኳን ደስ አላችሁ) የምትለዋ ድሮ የአማርን ወልቃይት ስታሸብር የነበረቺው ምንም ይቅርታ ሳትጠይቅ ዛሬ ኤርትራኖች ጋር ሆና የምታሽካካዋ ወልቃይቴ ነኝ ባይዋ ርስቴ” የተባለቺዋ የወያኔዎች (ነበር) ተጋይ ወታደር ሰሞኑን ያሳለፈቺው በፌስ ቡክ ያየሁት አንጀቴን ነበር ያቃጠለቺው። እስዋ ብቻ ሳትሆን ልክ እንደስዋ የወያኔ ታጋይ ሆኖ ለባንዳዎቹ ወግኖ ወልቃየቴዎችን ሲያስጨንቅ የነበረው “አርበኛውን አሳምነው ጽጌን “ከሐዲ” ብሎ የዘለፋቸውን ማፈሪያው ኮለኔል ተብየው “ኮለኔል ደመቀ” የተባለው ካሐዲ ለወልቃይቴዎቹ ስቃይ ከወያኔ ጋር ሆኖ የዘር ማጽዳት ስራ ሲራ የነበረውም ይቅርታ ሳይጠይቅ አሳምነውን መዝለፉ እጅግ ነው አንጀቴን ያቃጠለው።
ይህንን መተንፈሴ ጥሩ አጋጣመኒ ነው። ኤርትራኖችን እንኳን ለነፃነት በዓላችሁ በሰላም አደረሳችሁ የሚሉ ማፈሪያዎች እጅግ ያበሽቁኛል።በቁስላችን ላይ ጨው የሚነሰንሱ ከሓዲዎች ናቸው!
አሁን ወደ ርዕሳችን እንግባ፡
መስትያት መንነት የሚለው ስለወልቃይት የተጻፈው የሁለት ወያኔ ጸሐፍቶች መጽሐፍ የሚለው የአክሱም ሥልጣኔ የትግሬዎች ነው። ትግሬዎች ከ1494 ዓመተ ዓለም በፊት የነበሩ ናቸው ይለናል። ትግሬዎች በዛው ወቅት ማን ይባሉ ነበር “አልነገሩንም”። ንጉሳችን ኢትዮጲስ ይባል ነበር ይሉና ፤ እርሱስ ማን ነበር ቢባል “ኩሽ” ነው ይላሉ። ነገር ግን ኩሽ ትግሬዎች ናቸው የሚለው አባባላቸው፤-ዞር ብለው ራሳቸውን በራሳቸው ማንነታቸውን እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል።
“የአክሱም መንግሥት የትግሬዎች መንግሥት ነው፡ የአክሱም መንግሥት ከድአማት ቀጥሎ የመጣ የሴም ዝርያ (ዘር) ያላቸው ሴማውያን የሚባሉ ከደቡብ አረቢያ በቀይ ባሕር ተሻግረው ወደ አክሱም የመጡ ሳባውያን ናቸው። ይላሉ፤ ንግሥነታቸውም ከ2ኛ ክፍለዘመን ጀምሮ 1000 አመት የቀጠለ ነበር ይላል። እንግዲህ ትግሬዎች “የኩሹ የኢትዮጵስ ዘር ነን” ብለው የነገሩንን እነኚህ ጸሓፊዎች ትግሬዎች (አክሱሞች/ትግሬዎች) ከሴም የአረብ ነገድ ነን ያሉትን ትንተና ያምታቱታል። እንግዲህ የኩሽ ቋንቋ ተናጋርዎች እነማን ናቸው የሚለው ከትንታኔአቸው ስንነሳ ለትግሬዎች የሚሰጥ የነገድ/ቋንቋ ዘርፍ ነው ወይ? የሚለው ለናንተ ልተወው። ስለዚህ ልክ ወያኔዎች በፖሊሲያቸው የጻፉትን አረቦች የነገርዋቸውን የአጋአዚያን እና የአበሻ አመጣጥ ታሪክ ትንተና እነዚህ ደራሲያንም በዚህ መጽሐፍ ደገሙት። (ይገርማል!)
ካሁን በፊት ወያኔ በፖሊሲው የቀረጸው ትግሬዎች ማንነት በተለይ አጋአዚያን ነን ለሚሉ ትግሬዎች ልክ እንደነዚህ ሁለት ደራሲያን አክሱም የሴማዊ አረቦች ሠልጣኔ ነው ብለው ጽፈዋል። ትግሬዎች ከደአማት በፊት ነበሩ ብለው የነገሩንን ውሸት ረስተው (የአክሱም ስልጣኔ የትግሬዎች ነው ያሉት ዘንግተው ሥልጣኔው የአረቦች (የሴማውያን ሥልጣኔ ነው ብለው ቁጭ አሉ!)
በደምብ እስክመለስ ድረስ ኢትዮጵያኖች የቦታ ስም ማውጣት የማያውቁ በትግሬዎች ስም ብቻ የተሰየመ እንደሆነ በመላዋ ኢትዮጵያ እየዞሩ የቦታዎችን ስም በይመስላል እያመሳሰሉ ቃላት እየቀየሩ የጻፉትን ጉደኛና አስቂኝ የቦታ ስም ዝርዝር ትርጉም ተመለክቱልኝ፡ እንዲህ ይላሉ፡-
የወልቃይት ስም አመጣጥ በትግርኛ “እንዴት ያለ ወርቃዊ መሬት ነው” ከሚለው፤የመሬቱ ልምላሜ እና አቀማመጥ ተገርመው “ ወርቃዊ” ብለው ሰየሙት፡ ከዚያም ‘ወርቃዊት’ ሆነ፡ ከዚየም በጊዜ ሂደት ወርቃዊት የሚለው ወደ ወልቃይት ተለወጠ ይላሉ። እንዴት ወርቃዊት የሚለው ቃል አጥተውት ወደ ወልቃይትነት ተለወጠ የሚለው ግን ማስረጃውም ማብራሪያ አልሰጡም። ማስረጃቸው ‘ታላላቅ አባቶች እንደሉት ነው የሚለት”።
የሚገርመው ደግሞ በዘመነ አክሱም ጊዜም ቢሆን ነገሥታቱ በተውት ቅርስ ወልቃይት እንጂ ወርቃዊት ብለው የጻፉት ምንም ማስረጃ በሌለበት ነው ይህንን መከራከሪያ ያቀረቡት።
በዘመነ አክሱም ጀምሮ የነበረው ጠንካራ አካባቢ እንደነበርና የራሱ ንጉሥ የነበረው ወልቃይት (ከአክሱማዊው ንጉሥ ሐጻኒ ዳኒኤል ጋር የገጠመው ጦርነት ማስረጃ ነው) የተቆረቆረበት ጊዜ በ1460-በ1470 በዘመነ አጼ ብእደማርያም ነው ይላሉ እነዚህ ጸሓፊዎች። አልገረማችሁም? ዕድሜዋም ከ500 እስከ 530 አመት ሆኗታል ይላሉ።
በዘመነ አክሱም ጀምሮ የነበረው ጠንካራ አካባቢ እንደነበርና የራሱ ንጉሥ የነበረው ወልቃይት (ከአክሱማዊው ንጉሥ ሐጻኒ ዳኒኤል ጋር የገጠመው ጦርነት ማስረጃ ነው) የተቆረቆረበት ጊዜ በ1460-በ1470 በዘመነ አጼ ብእደማርያም ነው ይላሉ እነዚህ ጸሓፊዎች። አልገረማችሁም? ዕድሜዋም ከ500 እስከ 530 አመት ሆኗታል ይላሉ።
“አክሱም” ወይንም በንጉሥ ኤዛና ብዕር “አከሰመ” የሚለው የግዕዙ ቃል በትግሬዎች አጻጻፍ ወደ ትግርኛ ገልብጠው ያልሆነ አንካሳ ፊደል በመፍጠር ትክክለኛው አጻጻፍ “ኣክሱም” ነው ብለው ሙሉውን “አ” ወደ “ኣ’ አንካሳውን ፊደል “አ” ብለው በመጻፍ ለውጠው “አክሱም” ላለማለት ብትግርኛ አጻጻፍ “ኣክሱም” ብለውታል (አማርኛ ወይንም ግዕዝን በመጥላት ማለት ነው_የትግሬ ነው ለማለት።) የተለያዩ አገው ቤጃዎች (በተለይ ቦጎስ ላይ ያሉት) ወደ ትግራይ እንደገቡ “ትግራይ/ትግረ” ከመሊው ስያኔ ጀምሮ የግዕዝ ፊደላት የልሳን አባባል እንዴት እንደተቦወዘ የምናውቀው ነው።
አርማጭሆ የሚለውን ተመልከቱልኝ፦
አርማጭሆ የሚለው ስም ከየት መጣ ይላሉ እነዚህ ደራሲያን በመጽሐፋቸው ውስጥ፡
“ሓርማዝ ጮኸ” (ወደ አመርኛ ልተርጉምላችሁ - ሓርማዝ ማለት ‘ዝሆን’ ማለት ነው፤ “ጮኸ” ተጣራ ማለት ነው) የሚል ወደ አርማ ጭሆ” ሆነ ይላሉ እነዚህ ደራሲያን። ጮኸ የምትለዋ የመጨረሻ ቃል ግን አማርኛ ስለሆነች ትግርኛ ስለማይገኝላት እንደወረደች አማርኛው እና ትግርኛው ደባለቁትና ያለምንም ሓፈርት ከልሰው አስቀመጥዋት። አይገርምም?
“ሓርማዝ ጮኸ” (ወደ አመርኛ ልተርጉምላችሁ - ሓርማዝ ማለት ‘ዝሆን’ ማለት ነው፤ “ጮኸ” ተጣራ ማለት ነው) የሚል ወደ አርማ ጭሆ” ሆነ ይላሉ እነዚህ ደራሲያን። ጮኸ የምትለዋ የመጨረሻ ቃል ግን አማርኛ ስለሆነች ትግርኛ ስለማይገኝላት እንደወረደች አማርኛው እና ትግርኛው ደባለቁትና ያለምንም ሓፈርት ከልሰው አስቀመጥዋት። አይገርምም?
ፀሊም ማይ የሚለው ፀሉም ማይ ሆነ
ደምበ እያ የሚለው ደምቢያ ሆነ
ጣነየ የመኒል ወደ ጣና ሆነ (የጣና ባሕር ትግሬዎች እንዴት እንደሰየሙት ሲነግሩን ነው። እዛ ያለ ኗሪ ስም መሰየም አያውቅም?)
ጎርገረ ከሚል ጎርጎራ ሆነ
ፈገራ ከሚል ፎገራ ሆነ
ሃረር ከሚለው ሃረር ሆነ
አረ ማይ ከሚል ሃረማያ ሆነ (እነ ጃዋር ይህንን ሲሰሙ ምን እንደሚሉ አላውቅም)
ሽዋ የሚለው ደግሞ የሸዋ ልጆች ይህንን ሌላውን ጉድ አድምጡ፡
ስዋ የሚለው ሽዋ ሆነ (ስዋ ማለት በትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ ጠላ ማለት ነው)
እንኮ ሚለው አንኮበር ሆነ
ስዋ የሚለው ሽዋ ሆነ (ስዋ ማለት በትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ ጠላ ማለት ነው)
እንኮ ሚለው አንኮበር ሆነ
ዝማይ የሚለው ዝዋይ ሆነ (ዝማይ ማለት በአማርኛ ይኸ ውሃ ማለት ነው)
ዝቆላ ከሚለው ዝቋላ ሆነ (ዝቆላ በትግርኛ ይኸ ቆላማ በረሃ ማለት ነው አማርኛው)
ዓደለ ከሚል ዓዴል (ሐርር አካባቢ ማለት ነው)
ካራ መሓራ ከሚል ካራማራ ሆነ (ካራ ማለት ቢላዋ ነው፤ መሓራ ማለት ‘ማራት’ ማለት ነው- እንዴት እንዳገናኙት የሐርር ልጆች የካራማራ ትርጉሙን ንገሩን)
ቀብሪ ዳሓር ከሚለው ቀብሪ ደሃር ሆነ (የሗላ ቀብር ማለት ነው)
እያለ አስገራሚና አስቂኝ ትርጉም ይተነትናል። እናንተስ ምን ትላላችሁ? በነገራችን ላይ የሸዋ ሰዎች በጠላ ስም እንዴት እንደተሰየማችሁ አልገረማችሁም? ወይስ የሽዋ ጠላ እንደ ትግሬዎቹ ጠላ የሚወደድ ነበር?
የሚገርመው አማራ ው ማሕበረሰብ አክሱማዊ ሥልጣኔ ለኔም ይደርሰኛል ስላሉ ትግሬዎች (ወያኔዎች) አማራ ውን አይገባህም ብለው አክሱምን የአረቦች ስልጣኔ ነው ብለው ያለማፈር ዛሬም-ይተነትናሉ።
በዚህ አጋጣሚ ትግሬ መሆኔን ለማታውቁኝ ሰዎች ትግሬ መሆኔን እንድታውቁት እና ወያኔዎች እንዴት የትግራይ ታሪክ እያጣመሙ እኛን እንደሚያሰድቡ ለማሳይት እንጂ ትግሬነቴን-ከድቼ-ማለት-አይደለም።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ
No comments:
Post a Comment