ሓሽፈራይ በተባለ ሞቃታ ኤርትራ እስርቤት ተደብድበው የሚሞቱ እስረኞች የሦስት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ
ሚስጥሩ ይፋ ሆነ
(ምንጭ Ethiopian Semay)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
“ዛራ ሚዲያ” የተባለ ኤርትራዊ
የተቃዋሚ ሚዲያ የኤርትራ ነፃነት ባርነት እንጂ ነፃነት ተብሎ መከበር የለበትም” በማለት ሰሞኑን ኤርትራ ነጻ የወጣችበት እየተባለ
የተነገረውን የሰሞኑን “ሆሆታ አከባባር ” በመቃወም ለ4 ቀን የቆየ “የኤርትራ ባርነት” በሚል ርዕስ 4 ቀን ሙሉ የተለያዩ ተናጋሪዎች
በማስተናገድ ‘ከባድመ ጦርነት ጀምሮ እስከ በኢሳያስ አፈወርቂ አገልጋዮችን በኩል በከፍተኛ ምስጢር ተይዞ የነበረ ኢሳያስ የፈለጋቸው
‘ባለትዳር ሴቶችን’ በምስጢር እያስጠራ በስካር መንፈስ ተጠምዶ ወጣት ሴቶች ጭምር እንዴት እንደሚደፍር እንዲሁም የኤርትራ ከፍተኛ
ባለሥልጣነት ከራሻይዳዎች ጋር በመመሳጠር “ሰዎችን በመሸጥ/ በሰዎች ዝውውር” ተግባር እንደተሰማሩና የኤርትራ መከላከያ ሓይል ተብሎ
የሚጠራው ወታደራዊ ክፍል የተመደበበትን ሓለፊነት ዘንግቶ በአስናዋሪ ተግባራት በመሰማራት የተሰማራበትን መጥፎ ድርጊት ለ4 ቀን
በዓሉን በማክበር አስመልክቶ የተደበቁ አሰቃቃ ምስጢሮችን ይፋ ባደረገበት
ያደመጥኩት ጉድ ነው ዛሬ የማካፍላችሁ።
መጀመሪያ ስለ ሓሽፈራይ እስርቤት
እንዴት እንደሚመስል ቅርጹን ልንገራችሁ፡
እሰርቤቱ የተገነባው ከመሬት “ውስተ
መሬት” (አንደር ግራውንድ) ነው። ከላይ ሲታይ አይታወቅም። ሆኖም ከላይ መሬት በሚስጢር የተገና ለማወቅ የሚያስቸግር ማስገቢያ
እና መውጪያ በር አለው። እስረቤቶቹ በርካታ ክፍሎች የተቆፈሩ የጉድጓድ ክፍሎች ናቸው። 11 መሰላሎች ተገንበተውበታል። እስረኛ
የሚያመልጥበት ዕድል ፍጹም አይችልም። እያንዳንዱ የጉድጓድ ክፍሎች 100 እስረኞች ይይዛሉ።ለ100 እስረኛ የተገነባው 200 እረስረኞች
በማስገባት በጎን ብቻ ወይንም ቆመው እየተሰቃዩ እየተጣበቡ እንዲተኙ ይደረጋል። ከዚህ ሌላ ከ9 በላይ የሆኑ ጉድጓድ ክፍሎች ለ
4 ሰው ብቻ የሚይዝ የከፋው የመቀጣጫ ጉድጓድ አለ።
የሚገርመው ደግሞ ይህ በዘልማድ
“ኣንደር” እየተባለ የሚጠራው የሓሽፈራይ እስርቤት ከሥር ያሉ ጉድጓዶች ከላይ ከታች እንደፎቅ እና የታች ምድርቤት ያለባቸው የጉድጓድ
ክፍሎች እያንዳንዱ የተጠላለፉ መሰላሎች አልዋቸው። የክፍሎቹ መጠሪያ ስም በኤርትራ ከተሞች ስም የተሰየሙ ናቸው። ወደ ታች ቤት
ምድር ያሉ “አቑርደት፤ተሰነይ፤አስመራ፤ታይታኒክ..ወዘተ የሚባሉ ክፍሎች አሉ። እነዚህ እያንዳንዳቸው 100 ሰው እንዲይዙ የተደረጉ
(200 እስረኞች እንደገቡበት የተደረጉ ናቸው)፤ ከነዚህ ወደ ጎን ወደ ኋላ የተሰራ አዲሱ እስረቤት ደግሞ
“ናቕፋ” ይባላል።
ሞቃታው ጥልቁ ጨለማ የተሰራው ናቕፋ
የሚባለው የምድርቤቱ ክፍሎች እያንዳንዱ ጉድጓድ 300 ሰው እንዲይዙ ተደርገው የተገነቡ ናቸው (አሁንም እጥፍ እንዲይዙ የተደረጉ
ናቸው ‘600’። ወደ እነዚህ ክፍሎች ለመግባት ውስብስብ በሆኑ 11 የጉድጓድ መሸጋገሪያ ጥልፍልፍ መሰላሎችን ማለፍ አለብህ።በነዚህ
የጉድጓድ ክፍሎች በጭቃ ስላልተለሰኑ አፈሩ እየፈሰሰ የጉድጓድ ቆላማ
ትሎች እስረኞቹን ደማቸው እየመጠጡ ሰውነታቸው እየበሉ ያቆስልዋቸዋል። ስለ እስርቤቱ ቅርጽ ምን እንደሚመስል የዘረዘርዋቸውን ካሳየሁዋችሁ
አሁን ደግሞ በእስር ቤቶቹ ጉድጓድ ውስጥ ሰለሚፈጸሙ እጅግ የሚዘገንኑትን ጥቂቶችን ልጥቀስ፡ -
ለሞት የተፈረደባቸው ሰዎች መቃብራቸው
እንዲቆፍሩ ከተደረገ በኋላ ጉድጓዱ ውስጥ እያሉ የሳዮናይድ ውሃ በላያቸው ላይ በመድፋት ተቃጥለው
እንዲሞቱ የመደረጉ ምስጢር እና በድብደደባ ብዛት የሚሚቱ ተመርማሪ እስረኞች እንዲሁም በእነ “ተኽላይ ማንጁስ” እውቅና እንክብካቤ
የሚደረግላቸው ሦስት ትላልቅ ዘንዶዎች ፤ ከበረሃ አጥምደው በማምጣት “ለማዳ እንዲሆኑ” በማድረግ የሞተ ሰው በሌለበት ጊዜ ቡቹላዎች/ትንንሽ
ውሾች/ እንዲራቡ በማድረግ ምግባቸው እንዲሆኑ ይደረጋል። ተቀጥቅጠው የሞቱ እስረኞች ሲኖሩ ደግሞ ሬሳቸው ለነዚህ ሦሰት ዘንዶዎች
ምግብ እንደሚሆኑ ከተነገሩ አሰቃቂ ምስጢሮች ይገኙበታል።
ይህ የተለያዩ የጭካኔ ድርጊቶች
የሚፈጸምበት አሰቃቃ እስር ቤት “ሓሽፈራይ” ይባላል።ከአንድ አመት በፊት ስትናገር ያደመጥኳት ‘ሓሽፈራይ’ ውስጥ የታሰረች “ነርስ”
ስትገልጽ ‘ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የራስ ፀጉርህ እራሱ እንደ ሳር እየተቃጠለ
‘ቡን ቡን’ እያለ በመርገፍ መላጣ እንደሚያደርግህ አሰቃቃው የጸጉር መርገፍ ስትናገር አድምጫለሁ። እዛ ሳሕል እና ሓሽከራይ የመሳሰሉ
ሞቃታ እስርቤቶች በመርማሪዎች ተደፍረው የሚያረግዙ ወጣት ሴቶች እንዲረሸኑ የተደረጉ ብዙ እንደሆኑ እና አንዳንዶቹም በሙቀቱ እና
በድብዳባ እርግዝናቸው እንዲያስወርዱ እንደሚደረግ መናገርዋን አስታውሳሉ።
ዛሬ ደግሞ ዛራ ሚዲያ የገለጸው
በዝግ “የብርት ኮንተይነር” ልብሶቹ አስወልቀው በጋለው “የብረት ኮነተይነር/ቀፎ/” እራቁቱ ለሦሰት ወር የታሰረ ወታደራዊ ባለማዕረግ
ውሃ ስለማይፈቅዱለት የሚጣልልትን በጣም የደረቀ ዳቦ በሽንቱ እየነከረ ይውጠው እንደነበር በሁለተኛው ‘ቪዲዮ’ ለ “ዛራ ሚዲያ”
ለአዘጋጁ ባንደበቱ በግል እንዳወያየው የተናገረውን ይዘረዝራል።
የጭካኔ ድርጊቶች በርዕሱ እንደሚመለከተው
ታሪኩ የተፈጸመው “ሓሽፈራይ” በተባለ ቆላማ መመርመርያ እስርቤት በከፍተኛ ኤርትራዊያን ወታደራዊ መኮንኖች በእነ ተኽላይ ማንጁስ
ዋና አዛዥነት እና ዮናስ በተባሉ የምርመራ ሓላፊዎች የሚካሄድ እስርቤት ውስጥ ነው። ይህ አሰቃቃ ድርጊት መፈጸሙ ምስጢሩ የወጣው
“ነጋሲ” በሚባል የኤርትራ ወታደር የነበረ ወጣት እራሱ በሚያዘጋጀው "Zara Media/ዛራ ሚዲያ” ላይ ነው;
የጭካኔ ድርጊት ፈጻሚዎች እነማን ናቸው በሚል ከኢሳያስ ጀምሮ እስከ ታች ጉምሩክ
እና ፖሊሶች እንዲሁም ድምበር ጠባቂዎች ያለው የሙስና እና የወንጀል መዋቅር የሰዎቹን ስም በመዘርዘር “የኤርትራ ባርነት” በሚል
ለ4 ቀን የሚቆይ ፤ ኢሳያስ አፈወርቅና ወታደራዊ መኮንኖቹ በሕዝብ ህይወት የሚያደርጉት አስነዋሪ ስነምግባር እና በሥልጣን መባለግ
የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የማጋለጥ ዘመቻ አሁንም ለ4ኛው ቀን በመቀጠል ላይ ነው።
በዚህ ወንጀልን የማጋለጥ ዘመቻ
ቀን ውስጥ ተደብቀው የነበሩ የባድመ ጦርነት ምስጢር በድርጊቱ የተካፈለ አንድ ኤርትራዊ እንዲህ ይላል፡ “በባድሜ ጦርነት ውስጥ
ኢሳያሰና ጭፍሮቹ የወያኔ ወታደሮች “መቓብር ስውዓት”(የ“አርበኞች መቃብር”) ሆን ብሎ በማፈራረስ በሙታን መቃብር እና ሓውልት
ወንጀል ፈጽሟል እያሉ ወያኔን ሲወነጅሉ አድምጣችኋል፤ ሓቁ ግን እኔ በማፍረሱ ሂደት
እንድካፈል ከታዘዙት አንዱ እኔ ነበርኩ ስለዚህ ድርጊቱ የተፈጸመው በራሳችን አለቆች የሴራ ተግባር እንጂ ማንም መቃብር ያፈረሰ
የለም” ሲል የተደበቀውን ምስጢር ይፋ አድርጎታል።
ትግርኛ ለማድመጥ የምትችሉ ምንጩ ይኼው ልስጣችሁ። ይህ አንደኛው ክፍል ሲሆን
ለ4 ቀን የሚደረገው በኔ አገላለጽ “ለ4 ቀን የሚቆይ ወንጀልን የማጋለጥ በዓል” የተለያዩ ስዕለ ድምፆች (ቪዲዮዎች) ተለጥፈዋል።አንዱ
ይኼው፤ የሚከተለው ነው።ዋና ዋናዎቹ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚ ጀኔራሎች እነማን ናቸው? የሚል የውይይት ርዕስ የማጋለጥ ዘመቻ ይኼው
ቀንዲ ገበርቲን ሓደግቲን ሓለፍቲን ጀነራላትን ኣብ ኤርትራ ሌ/ኮ ስምኦን ገብረድንግል & ሌ/ኮ ወልደዝጊ ባህታ ካልኦትን መን እዮም
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ Ethiopian Semay ይጎብኙ)
No comments:
Post a Comment