Thursday, May 28, 2020

ሓሽፈራይ በተባለ ሞቃታ ኤርትራ እስርቤት ተደብድበው የሚሞቱ እስረኞች የሦስት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ ሚስጥሩ ይፋ ሆነ (ምንጭ Ethiopian Semay) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)


ሓሽፈራይ በተባለ ሞቃታ ኤርትራ እስርቤት ተደብድበው የሚሞቱ እስረኞች የሦስት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ ሚስጥሩ ይፋ ሆነ
(ምንጭ Ethiopian Semay)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
“ዛራ ሚዲያ” የተባለ ኤርትራዊ የተቃዋሚ ሚዲያ የኤርትራ ነፃነት ባርነት እንጂ ነፃነት ተብሎ መከበር የለበትም” በማለት ሰሞኑን ኤርትራ ነጻ የወጣችበት እየተባለ የተነገረውን የሰሞኑን “ሆሆታ አከባባር ” በመቃወም ለ4 ቀን የቆየ “የኤርትራ ባርነት” በሚል ርዕስ 4 ቀን ሙሉ የተለያዩ ተናጋሪዎች በማስተናገድ ‘ከባድመ ጦርነት ጀምሮ እስከ በኢሳያስ አፈወርቂ አገልጋዮችን በኩል በከፍተኛ ምስጢር ተይዞ የነበረ ኢሳያስ የፈለጋቸው ‘ባለትዳር ሴቶችን’ በምስጢር እያስጠራ በስካር መንፈስ ተጠምዶ ወጣት ሴቶች ጭምር እንዴት እንደሚደፍር እንዲሁም የኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣነት ከራሻይዳዎች ጋር በመመሳጠር “ሰዎችን በመሸጥ/ በሰዎች ዝውውር” ተግባር እንደተሰማሩና የኤርትራ መከላከያ ሓይል ተብሎ የሚጠራው ወታደራዊ ክፍል የተመደበበትን ሓለፊነት ዘንግቶ በአስናዋሪ ተግባራት በመሰማራት የተሰማራበትን መጥፎ ድርጊት ለ4 ቀን በዓሉን በማክበር አስመልክቶ የተደበቁ አሰቃቃ  ምስጢሮችን ይፋ ባደረገበት ያደመጥኩት ጉድ ነው ዛሬ የማካፍላችሁ።

መጀመሪያ ስለ ሓሽፈራይ እስርቤት እንዴት እንደሚመስል ቅርጹን ልንገራችሁ፡

እሰርቤቱ የተገነባው ከመሬት “ውስተ መሬት” (አንደር ግራውንድ) ነው። ከላይ ሲታይ አይታወቅም። ሆኖም ከላይ መሬት በሚስጢር የተገና ለማወቅ የሚያስቸግር ማስገቢያ እና መውጪያ በር አለው። እስረቤቶቹ በርካታ ክፍሎች የተቆፈሩ የጉድጓድ ክፍሎች ናቸው። 11 መሰላሎች ተገንበተውበታል። እስረኛ የሚያመልጥበት ዕድል ፍጹም አይችልም። እያንዳንዱ የጉድጓድ ክፍሎች 100 እስረኞች ይይዛሉ።ለ100 እስረኛ የተገነባው 200 እረስረኞች በማስገባት በጎን ብቻ ወይንም ቆመው እየተሰቃዩ እየተጣበቡ እንዲተኙ ይደረጋል። ከዚህ ሌላ ከ9 በላይ የሆኑ ጉድጓድ ክፍሎች ለ 4 ሰው ብቻ የሚይዝ የከፋው የመቀጣጫ ጉድጓድ አለ።

የሚገርመው ደግሞ ይህ በዘልማድ “ኣንደር” እየተባለ የሚጠራው የሓሽፈራይ እስርቤት ከሥር ያሉ ጉድጓዶች ከላይ ከታች እንደፎቅ እና የታች ምድርቤት ያለባቸው የጉድጓድ ክፍሎች እያንዳንዱ የተጠላለፉ መሰላሎች አልዋቸው። የክፍሎቹ መጠሪያ ስም በኤርትራ ከተሞች ስም የተሰየሙ ናቸው። ወደ ታች ቤት ምድር ያሉ “አቑርደት፤ተሰነይ፤አስመራ፤ታይታኒክ..ወዘተ የሚባሉ ክፍሎች አሉ። እነዚህ እያንዳንዳቸው 100 ሰው እንዲይዙ የተደረጉ (200 እስረኞች እንደገቡበት የተደረጉ ናቸው)፤ ከነዚህ ወደ ጎን ወደ ላ የተሰራ አዲሱ እስረቤት ደግሞ “ናቕፋ” ይባላል።

ሞቃታው ጥልቁ ጨለማ የተሰራው ናቕፋ የሚባለው የምድርቤቱ ክፍሎች እያንዳንዱ ጉድጓድ 300 ሰው እንዲይዙ ተደርገው የተገነቡ ናቸው (አሁንም እጥፍ እንዲይዙ የተደረጉ ናቸው ‘600’። ወደ እነዚህ ክፍሎች ለመግባት ውስብስብ በሆኑ 11 የጉድጓድ መሸጋገሪያ ጥልፍልፍ መሰላሎችን ማለፍ አለብህ።በነዚህ የጉድጓድ ክፍሎች  በጭቃ ስላልተለሰኑ አፈሩ እየፈሰሰ የጉድጓድ ቆላማ ትሎች እስረኞቹን ደማቸው እየመጠጡ ሰውነታቸው እየበሉ ያቆስልዋቸዋል። ስለ እስርቤቱ ቅርጽ ምን እንደሚመስል የዘረዘርዋቸውን ካሳየሁዋችሁ አሁን ደግሞ በእስር ቤቶቹ ጉድጓድ ውስጥ ሰለሚፈጸሙ እጅግ የሚዘገንኑትን ጥቂቶችን ልጥቀስ፡ -

ለሞት የተፈረደባቸው ሰዎች መቃብራቸው እንዲቆፍሩ ከተደረገ በላ ጉድጓዱ ውስጥ እያሉ የሳዮናይድ ውሃ በላያቸው ላይ በመድፋት ተቃጥለው እንዲሞቱ የመደረጉ ምስጢር እና በድብደደባ ብዛት የሚሚቱ ተመርማሪ እስረኞች እንዲሁም በእነ “ተኽላይ ማንጁስ” እውቅና እንክብካቤ የሚደረግላቸው ሦስት ትላልቅ ዘንዶዎች ፤ ከበረሃ አጥምደው በማምጣት “ለማዳ እንዲሆኑ” በማድረግ የሞተ ሰው በሌለበት ጊዜ ቡቹላዎች/ትንንሽ ውሾች/ እንዲራቡ በማድረግ ምግባቸው እንዲሆኑ ይደረጋል። ተቀጥቅጠው የሞቱ እስረኞች ሲኖሩ ደግሞ ሬሳቸው ለነዚህ ሦሰት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ ከተነገሩ አሰቃቂ ምስጢሮች ይገኙበታል።

ይህ የተለያዩ የጭካኔ ድርጊቶች የሚፈጸምበት አሰቃቃ እስር ቤት “ሓሽፈራይ” ይባላል።ከአንድ አመት በፊት ስትናገር ያደመጥኳት ‘ሓሽፈራይ’ ውስጥ የታሰረች “ነርስ” ስትገልጽ  ‘ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የራስ ፀጉርህ እራሱ እንደ ሳር እየተቃጠለ ‘ቡን ቡን’ እያለ በመርገፍ መላጣ እንደሚያደርግህ አሰቃቃው የጸጉር መርገፍ ስትናገር አድምጫለሁ። እዛ ሳሕል እና ሓሽከራይ የመሳሰሉ ሞቃታ እስርቤቶች በመርማሪዎች ተደፍረው የሚያረግዙ ወጣት ሴቶች እንዲረሸኑ የተደረጉ ብዙ እንደሆኑ እና አንዳንዶቹም በሙቀቱ እና በድብዳባ እርግዝናቸው እንዲያስወርዱ  እንደሚደረግ መናገርዋን አስታውሳሉ።

ዛሬ ደግሞ ዛራ ሚዲያ የገለጸው በዝግ “የብርት ኮንተይነር” ልብሶቹ አስወልቀው በጋለው “የብረት ኮነተይነር/ቀፎ/” እራቁቱ ለሦሰት ወር የታሰረ ወታደራዊ ባለማዕረግ ውሃ ስለማይፈቅዱለት የሚጣልልትን በጣም የደረቀ ዳቦ በሽንቱ እየነከረ ይውጠው እንደነበር በሁለተኛው ‘ቪዲዮ’ ለ “ዛራ ሚዲያ” ለአዘጋጁ ባንደበቱ በግል እንዳወያየው የተናገረውን ይዘረዝራል።

የጭካኔ ድርጊቶች በርዕሱ እንደሚመለከተው ታሪኩ የተፈጸመው “ሓሽፈራይ” በተባለ ቆላማ መመርመርያ እስርቤት በከፍተኛ ኤርትራዊያን ወታደራዊ መኮንኖች በእነ ተኽላይ ማንጁስ ዋና አዛዥነት እና ዮናስ በተባሉ የምርመራ ሓላፊዎች የሚካሄድ እስርቤት ውስጥ ነው። ይህ አሰቃቃ ድርጊት መፈጸሙ ምስጢሩ የወጣው  “ነጋሲ” በሚባል የኤርትራ ወታደር የነበረ ወጣት  እራሱ በሚያዘጋጀው "Zara Media/ዛራ ሚዲያ” ላይ ነው;

 የጭካኔ ድርጊት ፈጻሚዎች እነማን ናቸው በሚል ከኢሳያስ ጀምሮ እስከ ታች ጉምሩክ እና ፖሊሶች እንዲሁም ድምበር ጠባቂዎች ያለው የሙስና እና የወንጀል መዋቅር የሰዎቹን ስም በመዘርዘር “የኤርትራ ባርነት” በሚል ለ4 ቀን የሚቆይ ፤ ኢሳያስ አፈወርቅና ወታደራዊ መኮንኖቹ በሕዝብ ህይወት የሚያደርጉት አስነዋሪ ስነምግባር እና በሥልጣን መባለግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የማጋለጥ ዘመቻ አሁንም ለ4ኛው ቀን በመቀጠል ላይ ነው።

በዚህ ወንጀልን የማጋለጥ ዘመቻ ቀን ውስጥ ተደብቀው የነበሩ የባድመ ጦርነት ምስጢር በድርጊቱ የተካፈለ አንድ ኤርትራዊ እንዲህ ይላል፡ “በባድሜ ጦርነት ውስጥ ኢሳያሰና ጭፍሮቹ የወያኔ ወታደሮች “መቓብር ስውዓት”(የ“አርበኞች መቃብር”) ሆን ብሎ በማፈራረስ በሙታን መቃብር እና ሓውልት ወንጀል ፈጽሟል እያሉ ወያኔን ሲወነጅሉ አድምጣችል፤ ሓቁ ግን እኔ በማፍረሱ ሂደት እንድካፈል ከታዘዙት አንዱ እኔ ነበርኩ ስለዚህ ድርጊቱ የተፈጸመው በራሳችን አለቆች የሴራ ተግባር እንጂ ማንም መቃብር ያፈረሰ የለም” ሲል የተደበቀውን ምስጢር ይፋ አድርጎታል።
 ትግርኛ ለማድመጥ የምትችሉ ምንጩ ይኼው ልስጣችሁ። ይህ አንደኛው ክፍል ሲሆን ለ4 ቀን የሚደረገው በኔ አገላለጽ “ለ4 ቀን የሚቆይ ወንጀልን የማጋለጥ በዓል” የተለያዩ ስዕለ ድምፆች (ቪዲዮዎች) ተለጥፈዋል።አንዱ ይኼው፤ የሚከተለው ነው።ዋና ዋናዎቹ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚ ጀኔራሎች እነማን ናቸው? የሚል የውይይት ርዕስ የማጋለጥ ዘመቻ ይኼው
ቀንዲ ገበርቲን ሓደግቲን ሓለፍቲን ጀነራላትን ኣብ ኤርትራ / ስምኦን ገብረድንግል & / ወልደዝጊ ባህታ ካልኦትን መን እዮም
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ Ethiopian Semay ይጎብኙ)  


Tuesday, May 26, 2020

በሁለት ትግሬዎች የተጻፈ ስለ ወልቃይት መጽሐፍ አነበባችሁት? እንዲህ ይላል? ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ) Tuesday, May 26/2020


በሁለት ትግሬዎች የተጻፈ ስለ ወልቃይት መጽሐፍ አነበባችሁት? እንዲህ ይላል?
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)
Tuesday, May 26/2020

መጽሐፉ ከትግራይ ተልኮልኝ የደረሰኝ ምናልባት አንድ ወር ይሆነዋል። በሥራ መወጠር ምክንያት አላነበብኩትም። ጊዜ ሳገኝ አንብባቸዋለሁ ብየ ተራቸውን እየጠበቁ ካሉት መደርደሪያየ ውስጥ ካሉት ይህ በመዝገበ ጎይተኦም እና በጎይተኦም ተኸስተ የተባሉ የወያኔ ጋዜጠኞች ስለ ወልቃይት የተጻፈውን መስትያት መንነት- ታሪክን አማፃፅኣን ህዝቢ ወልቃይት ፀገዴ (2009 .)” የሚል መጽሐፋቸው ድንገት ስገልጠው ለማንበብ ዕቅድ ባይኖረኝም እስኪ ልየው ብየ በቁሜ ገርፍ ገረፍ ሳደርገው አስገራሚ የሆኑ የተዛቡ ፤በይሆናል የተተረጎሙ ትንታኔዎችን እስከ ገጽ 21 ድራስ ተመለከትኩት። ሙሉን ሳነበው እመለስበታለሁ። እስከዛው ድረሰ ግን እየሳቃችሁበትም ቢሆን አንብቡት።

ከላይ የተጠቀሰው መጽሐፍ የተጻፈው በትግርኛ ሲሆን የርዕሱ ትርጉም በአማርኛ ስተረጉመው እንዲህ ይነበባልየማንነት መስተዋት- የወልቃይት ሕዝብ ታሪክና አመጣጥይላል። ያንን ለወደፊቱ የምምለሰው ቢሆንም ካሳቀኝ ነገር ልተንትን።በነገራችን ላይ በመጽሐፉ መግቢያ ውስጥ ያሳተሙት ካርታ እንደ መቅድም የወያኔ ኢትዮጵያ ካርታ ነው። የትግሬ/ኢትዮጵያውያን አክሱማዊያን መሬትን አያከትትም። ክሐደት አንድ ከዚያ ይጀምራል።

ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት ግን አጋጣሚውን ልጠቀም እና አንድ ነገር ልበል። ሰሞኑን የታዘብኩት ነው። ይህንን ስተነትን አንድ የማላልፈው ቅረታ ለማንሳት ትዝ አለኝ። የወልቃይ ጉዳይ የኛ ጉዳይ ነው ብለው የወልቃይትንና አማራውን ሲያሰቃዩ ሲገድሉ ሲያስጨንቁ የነበሩትኤርትራኖችን እንኳን የነፃነታችሁን ልደት ቀን አደረሳችሁ (ትርጉሙምእኛ የድሮ የወያኔ ታጋዮች እነዚያ ጠላቶች ብለን አብረን ከናንተው ጋር የወጋናቸውን፤የገደልናቸውን ኢትዮጵያውያኖችን፤ ሲመኩበት የነበረውን ባሕራቸውን አስዘግተን ነፃነታችሁን የተቀናጃችሁ አርበኞች ኤርትራውያንለነፃነታችሁ በዓል እንኳን ደስ አላችሁ) የምትለዋ ድሮ የአማርን ወልቃይት ስታሸብር የነበረቺው ምንም ይቅርታ ሳትጠይቅ ዛሬ ኤርትራኖች ጋር ሆና የምታሽካካዋ ወልቃይቴ ነኝ ባይዋ ርስቴየተባለቺዋ የወያኔዎች (ነበር) ተጋይ ወታደር ሰሞኑን ያሳለፈቺው በፌስ ቡክ ያየሁት አንጀቴን ነበር ያቃጠለቺው። እስዋ ብቻ ሳትሆን ልክ እንደስዋ የወያኔ ታጋይ ሆኖ ለባንዳዎቹ ወግኖ ወልቃየቴዎችን ሲያስጨንቅ የነበረውአርበኛውን አሳምነው ጽጌንከሐዲብሎ የዘለፋቸውን ማፈሪያው ኮለኔል ተብየውኮለኔል ደመቀየተባለው ካሐዲ ለወልቃይቴዎቹ ስቃይ ከወያኔ ጋር ሆኖ የዘር ማጽዳት ስራ ሲራ የነበረውም ይቅርታ ሳይጠይቅ አሳምነውን መዝለፉ እጅግ ነው አንጀቴን ያቃጠለው።

ይህንን መተንፈሴ ጥሩ አጋጣመኒ ነው። ኤርትራኖችን እንኳን ለነፃነት በዓላችሁ በሰላም አደረሳችሁ የሚሉ ማፈሪያዎች እጅግ ያበሽቁኛል።በቁስላችን ላይ ጨው የሚነሰንሱ ከሓዲዎች ናቸው!

አሁን ወደ ርዕሳችን እንግባ፡

መስትያት መንነት የሚለው ስለወልቃይት የተጻፈው የሁለት ወያኔ ጸሐፍቶች መጽሐፍ የሚለው የአክሱም ሥልጣኔ የትግሬዎች ነው። ትግሬዎች 1494 ዓመተ ዓለም በፊት የነበሩ ናቸው ይለናል። ትግሬዎች በዛው ወቅት ማን ይባሉ ነበርአልነገሩንም ንጉሳችን ኢትዮጲስ ይባል ነበር ይሉና እርሱስ ማን ነበር ቢባልኩሽነው ይላሉ። ነገር ግን ኩሽ ትግሬዎች ናቸው የሚለው አባባላቸው፤-ዞር ብለው ራሳቸውን በራሳቸው ማንነታቸውን እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል።

የአክሱም መንግሥት የትግሬዎች መንግሥት ነው፡ የአክሱም መንግሥት ከድአማት ቀጥሎ የመጣ የሴም ዝርያ (ዘር) ያላቸው ሴማውያን የሚባሉ ከደቡብ አረቢያ በቀይ ባሕር ተሻግረው ወደ አክሱም የመጡ ሳባውያን ናቸው። ይላሉ፤ ንግሥነታቸውም 2 ክፍለዘመን ጀምሮ 1000 አመት የቀጠለ ነበር ይላል። እንግዲህ ትግሬዎችየኩሹ የኢትዮጵስ ዘር ነንብለው የነገሩንን እነኚህ ጸሓፊዎች ትግሬዎች (አክሱሞች/ትግሬዎች) ከሴም የአረብ ነገድ ነን ያሉትን ትንተና ያምታቱታል። እንግዲህ የኩሽ ቋንቋ ተናጋርዎች እነማን ናቸው የሚለው ከትንታኔአቸው ስንነሳ ለትግሬዎች የሚሰጥ የነገድ/ቋንቋ ዘርፍ ነው ወይ? የሚለው ለናንተ ልተወው። ስለዚህ ልክ ወያኔዎች በፖሊሲያቸው የጻፉትን አረቦች የነገርዋቸውን የአጋአዚያን እና የአበሻ አመጣጥ ታሪክ ትንተና እነዚህ ደራሲያንም በዚህ መጽሐፍ ደገሙት። (ይገርማል!)

ካሁን በፊት ወያኔ በፖሊሲው የቀረጸው ትግሬዎች ማንነት በተለይ አጋአዚያን ነን ለሚሉ ትግሬዎች ልክ እንደነዚህ ሁለት ደራሲያን አክሱም የሴማዊ አረቦች ሠልጣኔ ነው ብለው ጽፈዋል። ትግሬዎች ከደአማት በፊት ነበሩ ብለው የነገሩንን ውሸት ረስተው (የአክሱም ስልጣኔ የትግሬዎች ነው ያሉት ዘንግተው ሥልጣኔው የአረቦች (የሴማውያን ሥልጣኔ ነው ብለው ቁጭ አሉ!)

በደምብ እስክመለስ ድረስ ኢትዮጵያኖች የቦታ ስም ማውጣት የማያውቁ በትግሬዎች ስም ብቻ የተሰየመ እንደሆነ በመላዋ ኢትዮጵያ እየዞሩ የቦታዎችን ስም በይመስላል እያመሳሰሉ ቃላት እየቀየሩ የጻፉትን ጉደኛና አስቂኝ የቦታ ስም ዝርዝር ትርጉም ተመለክቱልኝ፡ እንዲህ ይላሉ፡-

የወልቃይት ስም አመጣጥ በትግርኛእንዴት ያለ ወርቃዊ መሬት ነውከሚለው፤የመሬቱ ልምላሜ እና አቀማመጥ ተገርመውወርቃዊብለው ሰየሙት፡ ከዚያምወርቃዊትሆነ፡ ከዚየም በጊዜ ሂደት ወርቃዊት የሚለው ወደ ወልቃይት ተለወጠ ይላሉ። እንዴት ወርቃዊት የሚለው ቃል አጥተውት ወደ ወልቃይትነት ተለወጠ የሚለው ግን ማስረጃውም ማብራሪያ አልሰጡም። ማስረጃቸውታላላቅ አባቶች እንደሉት ነው የሚለት

የሚገርመው ደግሞ በዘመነ አክሱም ጊዜም ቢሆን ነገሥታቱ በተውት ቅርስ ወልቃይት እንጂ ወርቃዊት ብለው የጻፉት ምንም ማስረጃ በሌለበት ነው ይህንን መከራከሪያ ያቀረቡት።
በዘመነ አክሱም ጀምሮ የነበረው ጠንካራ አካባቢ እንደነበርና የራሱ ንጉሥ የነበረው ወልቃይት (ከአክሱማዊው ንጉሥ ሐጻኒ ዳኒኤል ጋር የገጠመው ጦርነት ማስረጃ ነው) የተቆረቆረበት ጊዜ 1460-1470 በዘመነ አጼ ብእደማርያም ነው ይላሉ እነዚህ ጸሓፊዎች። አልገረማችሁም? ዕድሜዋም 500 እስከ 530 አመት ሆኗታል ይላሉ።

አክሱምወይንም በንጉሥ ኤዛና ብዕርአከሰመየሚለው የግዕዙ ቃል በትግሬዎች አጻጻፍ ወደ ትግርኛ ገልብጠው ያልሆነ አንካሳ ፊደል በመፍጠር ትክክለኛው አጻጻፍኣክሱምነው ብለው ሙሉውንወደአንካሳውን ፊደልብለው በመጻፍ ለውጠውአክሱምላለማለት ብትግርኛ አጻጻፍኣክሱምብለውታል (አማርኛ ወይንም ግዕዝን በመጥላት ማለት ነው_የትግሬ ነው ለማለት።) የተለያዩ አገው ቤጃዎች (በተለይ ቦጎስ ላይ ያሉት) ወደ ትግራይ እንደገቡትግራይ/ትግረከመሊው ስያኔ ጀምሮ የግዕዝ ፊደላት የልሳን አባባል እንዴት እንደተቦወዘ የምናውቀው ነው።

አርማጭሆ የሚለውን ተመልከቱልኝ፦

አርማጭሆ የሚለው ስም ከየት መጣ ይላሉ እነዚህ ደራሲያን በመጽሐፋቸው ውስጥ፡
ሓርማዝ ጮኸ” (ወደ አመርኛ ልተርጉምላችሁ - ሓርማዝ ማለትዝሆንማለት ነው፤ጮኸተጣራ ማለት ነው) የሚል ወደ አርማ ጭሆሆነ ይላሉ እነዚህ ደራሲያን። ጮኸ የምትለዋ የመጨረሻ ቃል ግን አማርኛ ስለሆነች ትግርኛ ስለማይገኝላት እንደወረደች አማርኛው እና ትግርኛው ደባለቁትና ያለምንም ሓፈርት ከልሰው አስቀመጥዋት። አይገርምም?

ፀሊም ማይ የሚለው ፀሉም ማይ ሆነ

ደምበ እያ የሚለው ደምቢያ ሆነ

ጣነየ የመኒል ወደ ጣና ሆነ (የጣና ባሕር ትግሬዎች እንዴት እንደሰየሙት ሲነግሩን ነው። እዛ ያለ ኗሪ ስም መሰየም አያውቅም?)

ጎርገረ ከሚል ጎርጎራ ሆነ

ፈገራ ከሚል ፎገራ ሆነ

ሃረር ከሚለው ሃረር ሆነ

አረ ማይ ከሚል ሃረማያ ሆነ (እነ ጃዋር ይህንን ሲሰሙ ምን እንደሚሉ አላውቅም)

ሽዋ የሚለው ደግሞ የሸዋ ልጆች ይህንን ሌላውን ጉድ አድምጡ፡
ስዋ የሚለው ሽዋ ሆነ (ስዋ ማለት በትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ ጠላ ማለት ነው)
እንኮ ሚለው አንኮበር ሆነ

ዝማይ የሚለው ዝዋይ ሆነ (ዝማይ ማለት በአማርኛ ይኸ ውሃ ማለት ነው)

ዝቆላ ከሚለው ዝቋላ ሆነ (ዝቆላ በትግርኛ ይኸ ቆላማ በረሃ ማለት ነው አማርኛው)

ዓደለ ከሚል ዓዴል (ሐርር አካባቢ ማለት ነው)

ካራ መሓራ ከሚል ካራማራ ሆነ (ካራ ማለት ቢላዋ ነው፤ መሓራ ማለትማራትማለት ነው- እንዴት እንዳገናኙት የሐርር ልጆች የካራማራ ትርጉሙን ንገሩን)

ቀብሪ ዳሓር ከሚለው ቀብሪ ደሃር ሆነ (የሗላ ቀብር ማለት ነው)

እያለ አስገራሚና አስቂኝ ትርጉም ይተነትናል። እናንተስ ምን ትላላችሁ? በነገራችን ላይ የሸዋ ሰዎች በጠላ ስም እንዴት እንደተሰየማችሁ አልገረማችሁም? ወይስ የሽዋ ጠላ እንደ ትግሬዎቹ ጠላ የሚወደድ ነበር?

የሚገርመው አማራ ማሕበረሰብ አክሱማዊ ሥልጣኔ ለኔም ይደርሰኛል ስላሉ ትግሬዎች (ወያኔዎች) አማራ ውን አይገባህም ብለው አክሱምን የአረቦች ስልጣኔ ነው ብለው ያለማፈር ዛሬም-ይተነትናሉ።

በዚህ አጋጣሚ ትግሬ መሆኔን ለማታውቁኝ ሰዎች ትግሬ መሆኔን እንድታውቁት እና ወያኔዎች እንዴት የትግራይ ታሪክ እያጣመሙ እኛን እንደሚያሰድቡ ለማሳይት እንጂ ትግሬነቴን-ከድቼ-ማለት-አይደለም።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay አዘጋጅ