ኢሳት ከአሜሪካ የስለላ ድርጅት
ጋር ንክኪ ካለው ከኦፕን ሶሳይቲ የ5 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ጉዳይ
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopiansemay ድረገጽ አዘጋጅ)
ጆርጅ ሶሮስ የተባለ ግለሰብ የሚመራው
‘ኦፕን ሶሳይቲ’ (Open Society) የሚባለው በጎ አድራጎት ስራ የተሰማራ
ድርጅት የሚመስል ተቋም ምንነቱ ከመነጋገራችን በፊት “የኢሳቱ መቶ አለቃ ሲሳይ አገና” ዕለታዊ በተባለው የዜና ትንተና ክፍለጊዜ
ላይ ስለ አማራ ክልል መኖር አለመኖር የተናገረው የተባለውን ትንሽ
ልበል። (እስካደምጠው ድረስ በፌስ ቡክ ያነበብኩትን ላቅርብ።
እንዲህ ሲል ሲሳይ ተናገረ ተብሏል፡-
"በአሁኑ ሰአት የአማራ ክልል የሚባል ነገር የለም። ክልሉ የቅማንት ፣ የአገው እና ኦሮሞም ጭምር ነው። ስለዚህ የአዴፓ መሪዎች የአማራ ክልል ህዝቦች እንጅ "አማራ" ብቻ እያሉ መጥራት ተገቢ አይደለም" (ሲሳይ አገና (ጁላይ 24/2019)
የአማራ ክልል የሚባል የለም ማለቱ
ምን ማለቱ ነው? መቶ አለቃ ሲሳይ “አብይ አሕመድ የተባለ “ዝርክርክ መሪ” አሞጋሽ ከሆነ ጀምሮ የሚናገራቸው ሁሉ ከጭንቅላቱ ውጭ
እየሆኑበት መምጣታቸው ብዙ ማሳያዎች አሉ። ይህ አባባሉ አንዱ ነው። በሁሉም “ክልሎች” አንድ ወጥ የሆነ ነገድ የለም። ትግራይ
የሚባለው እኔ የመጣሁበት ማሕበረሰብ ልክ እንደ አማራው “ክልል” አገው፤ሳሆ፤ትግርኛ፤አማራ፤ኩናማ” ይኖራሉ የክልሉ መጠሪያ ግን
ትግራይ/ትግሬ ይባላል። ክልሉ አዲስ ስም እስካልተሰጠው ድረስ ‘የትግራይ ክልል” ካልተባለ ምን ይባላል? አማራ ክልል የሚባል የለም
ከተባለ የትግራይ ክልል የኦሮሞ ክልል የሚባልም አይኖርም ማለት ነው።
(አፓርታይዱ እንዳለ ሆኖ) ኦሮሞ ውስጥም ለመቁጠር የሚያስችግሩ የተለያዩ ማሕበረሰቦች
አሉ።ግን ኦሮሞ ክልል ነው የሚባለው። ስለዚህ አማራ “ክልል” ሲመጣ አማራ ክልል የሚባል የለም ካለ “አማራ ብቻ” ልዩ የሚያደርገው
ሲሳይ ሊነግረን አይችልም። ሊነግረን የማይችልበት ምክንያት ደግሞ እንዳልኩት መቶ አላቃ ሲሳይ አገና አብይ አሕመድ የተባለ ሥርዓተ
አልባ ዝርክርክ መሪ አሞጋሽ ከሆነ ጀምሮ የሚናገራቸው ሁሉ ከጭንቅላቱ ውጭ ስለሆኑበት ጋዜጠኛነቱን ጥሎ የ “ፔሮት” ወፍ ባሕሪ
ይዟል።
ወደ ርዕሳችን እንግባ።
ኢሳት ቴ/ቪ ጣቢያ በሓላፊው አበበ ገላው በኩል “ከጆርጅ ሶሮስ” ዕርዳታ ስለመጠየቁ ጉዳይ አስመልክቶ
አንድ ነገር ልበል።
ለበርካታ አመታት የሻዕቢያ፤ የግንቦት 7 እና የኦነጎች ቱልቱላ (ፕሮፓጋንዳ)
ዋና አሰራጭ የነበረው የዘሐበሻ ድረገጽ (ለብዙ አማታት በማስረጃ የተቸሁባቸው በርካታ ሰነዶቼን በኢትዮ ሰማይ ድረገጽ መመልከት
ትችላላችሁ) ፤ ዛሬ ደግሞ አዘጋጁ ሔኖክ አለማዮህ “ሹክሹክታ” የሚባል ‘በዩቱብ’ የሚሰራጭ “በየስርቻው የሚደመጡ የሐሜት ሹክሹክታዎች”
(አንዳንዱ እውነት አንዳንዱ ውሸት) እያነፋነፈ ለሕዝብ በሚያስደምጠው የሹክሹክታው (የታብሎይድ) ክፍለ ጊዜ ‘ኢሳት’ የተባለ ጉደኛ የዜና ማዕከል
ከአበበ ገላው እና ከጠ/ሚ አብይ አሕመድ ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት በማድረግ የ5 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ እንዲደረግለት ከአሜሪካ የስለላ ድርጅት መዋቅር
ጋር ግንኙነት ያለው “ኦፕን ሶሳይቲ” ከተባለው
ድርጅት ዕቅድ ተይዞለት እንደነበር “ሹክ” ብሎናል።
እና በኋ ላ ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ምስጢር
መክሸፉን የሹክሹክታው ዜና አስደምጧል። አሁን ልነግራችሁ የምፈልገው ምስጢር ከሽፋል ወይስ አልከሸፈም የሚለው አይደለም። አበበ
ገላው የተናገረውን እንመልክት። እንዲህ ይላል።
“ኢሳት እንደማንኛውም ትርፋማ ያልሆነ
ድርጅት ከኦፕን ሶሳይቲ ዕርዳታ ለማግኘት ማመለክቻ ማስገባት የሚችል ሲሆን ለዚህም የየትኛውም አገር መሪ አማላጅነት ፈጽሞ አያስፈለገውም።” ብሎ አበበ ገላው በጉዳዩ አስመልክቶ ስለሰጠበት መልስ እንነጋገር። ትዝ ይላችሁ
አንደሆነ ስርዓተ አልባው (ዝርክርክ) አብይ አሕመድ ስለ ኢሳት አስመልክቶ የግል ሚዲያዎች ዕርዳታ አንደሚያስፈልጋቸው በተለይ ኢሳትን
እየጠቀሰ የተናገረውን ታስታውሳላች። ስለዚህ አበበ ገላው ከአብይ ጋር በምስጢር ፓሪስ/ፈረንሳይ አገር ስለ መገናኘቱ ምስጢሩን ሹሹክታ
ይፋ ቢያደርግም አበበ ግን “ውሸት ወይንም እውነት” ከማለት ይልቅ “ኢሳት እንደማንኛውም ትርፋማ ያልሆነ ድርጅት ከኦፕን ሶሳይቲ
ዕርዳታ ለማግኘት ማመለክቻ ማስገባት የሚችል ሲሆን ለዚህም የየትኛውም አገር መሪ አማላጅነት ፈጽሞ አያስፈለገውም።” ማለቱ ባንድ
በኩል ልክ ነው። ምክንያቱም ኢሳት በአበበ ገላው በኩል “ከኦፕን ሶሳይቲ” የገንዘብ ዕርዳታ ለማግኘት ኦፕን ሶሳይቲን ማመለከቻ
አስገብተህ ቀርቶ ሳታስገባም “ኦፕን ሶሳይቲ” እያሸተተ ወደ ኢሳት እንደሚመጣ የጆርጅ ሶሮስ ኦፕን ሶሳይቲ ድርጅት በሌሎች አገሮች
ያሳየው ልምድ በማየት ወደ ድርጅቱ ማማለከቻ የግድ ማስገባት የለብህም (ይህ የስላላ መዋቅር የሚረዱት ድርጅት ለወደፊት ዕቅዳቸው
ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት በራሳቸው ውስጣዊ ወኪሎቻቸው ያገኙሃል)። አበበ
ገላው ወደ እዚህ ድርጅት እጁን ለምን ዘረጋ? እንዴትስ አወቀው? የሚለው ጥያቄ ካለ እርሱ በስተቀር የሚያውቅ የለም። ጋዜጠኛ ስለሆነ
የሚል መልስ ሊኖር ይችላል፤ ግን ደግሞ ሁሉም ጋዜጠኛ እጁን ወደ ሶሰሮስ ሲዘረጋ አላየንም።ለዚህ ነው ግራ የገባን።
አበበ ገላው እንደማንኛውም በጎ
ሰሪ ድርጅት ማማልከቻ አስገብተህ ‘ኦፕን ሶሳይቲ” ዕርዳታ የሚሰጥ አይነት ሆኖ ‘ድርጅቱን እና አሰራሩን እንዲሁ አቅልሎ ለማሳየት’ እንደሞከረተው አይደለም።የድርጅቱ
አቋም ምንድ ነው ብሎ የጆርጅ ሶሮስ ገምጋሚዎች አጥንተውት የሚፈቀድ በጀት ነው። ለዚህም ይሆናል መለስ ዜናዊን የተካው በምስራቅ
አፍሪቃ እና በመላዋ አፍሪቃ የአሜሪካኖቹ “ቀኝ እጅ” በሆነው በአብይ አሕመድ አማላጅነት በኩል እንዲፈቀድላቸው ጥረት የተደረገው።
Open Society የስለላ ድርጅት
ነው። “ኦፕን ሶሳይቲ” George Soros “ጆርጅ ሶሮስ” የተባለው
የሃንጋሪ ተወላጅ አሜሪካዊ የናጠጠ ሓብታም ቢሊዮነር የዚህ ድርጅት ዋና መሪ ነው። Open Society “ኦፕን ሶሳይቲ” ምንድ
ነው? ይህ ድርጅት በአሜሪካ ውስጥም ሆነ በተቀሩት የዓለም አገሮች አብዮት እጆቹን በአገሮች ፖለቲካ ውስጥ በዘዴ ገብቶ፤ በየገራቱ
ተወላጆች የሚቀጥራቸው “ምስጢራዊ አባሎቶቹ” በኩል ድብቅ እጁን በማስገባት
ሊፈርሱ ወይንም ምጣኔ ሓበታቸው ሊበዘበዙ በዕቅድ የተያዙ የሃገራቶችን ስርዓት በመለወጥ ብጥብጥ የሚፈጥር
ወይንም የአሜሪካ ‘ቀኝ እጅ‘ የሆነ መሪ በሚገዛት አገር ለመንከባከብ የሚነጥፍ ከአሜሪካ የስለላ ድርጅት ጋር የተገናኘ ድርጅት
ነው።
ለምሳሌ በቅርቡ ወዳጄ ዶክተር አሰፋ
ነጋሽ የሰጠኝ “ማኒፌሰት ዴሰቲኒ ዲሞክራሲ ኣዝ ኮግነቲቭ ዲሶናንስ” ደራሲ ዊልያም ኢንግድሃል” MANIFEST DESTINY
DEMOCRACY AS COGNITIVE DISSONANCE (F. WILLIAM ENGDAHL) በሚል መጽሐፍ ውስጥ “ኦፕን ሶሳይቲ እና
ጆርጅ ሶሮ” ምንነት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል።
“George Soros and
his Open Society Foundations had been linked to the CIA by Chinese intelligence
and others. His Open Society institutions seemed to appear operational, of
course just by coincidence, in every situation where the CIA’s NED front and
the US State Department sought regime change to a pro-Washington government.”
ግልጽ አድርጌ በግርድፍ ስተረጉመው እንዲህ ይላል።
“ጆርጅ ሶሮ እና “ይፋዊ ማኅበረሰብ” (ክፍት ማሕበረሰብ) የተባለ ድርጅቱና ቅርንጫፎቹ ከሲአይኤ ጋር የተቆራኘ ተቋም
እንደሆነ የቻይና የስለላ ተቋማት እና በሌሎች ተቋማት ተረጋግጧል። በሥራ ላይ የሚገኙት እንኚህ
የጆርጅ ሶሮ
ተቋማት በእርግጥ በሁሉም ውስጥ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ተቋም ይመስላል። ነገር ግን
የዩናይትድ ስቴትስ የሲአይኤ NED ግንባር እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቶች በሚንቀሳቀሱባቸው ‘
አገሮች’ የመንግሥት (መሪ) ለውጥ እንዲደረግ በማድረግ ለዋናው ዋሺንገቶን
(ለአሜሪካ መንግሥት) ተገዢ የሆነው ሰው ያመጣሉ።” ይላል።
ከስያሜው ስንጀምር “ኦፕን” የሚለው
“ክፍት” ሲሆን “ሶሳይቲ” የሚለው “ማሕበረሰብ” ማለት ነው። ‘ክፍት ማሕበረስብ” የሚለው የሚነግረን “የሚከላከል/የሚያግድ/የሚያስቆም/በር/ደጃፍ/ተቆርቋሪ
መሪ” በሌለባቸው አገሮች/ማሕበረሰቦች ማለት ነው። ስለዚህም ዝግ የነበረ ማሕበረሰብ በቀላሉ በማፍረስ “ዘው ብሎ” የሚጋባበት ማሕበረሰብ
ማለት ነው። ከዚህ ውጪ ከድርጅቱ መሰሪ ተልዕኮ አሰያየም ሌላ ትርጉም አልሰጠውም።
እንግዲህ ኦፕን ሶሳይቲ እና ጆርጅ
ሶሮ የተባለው “ሃንጋሪ አሜሪካዊ” ቱጃር (ሃብታም) በሩስያ እና በመሳሰሉት አገራት የመንግሥት ለውጥ በማድረግ የምጣኔ ሓብት ብዝበዛ
እና ቀውስ ወይንም ብጥብጥ እንደሚያመጣ ይህ መጽሐፍ ይገልጻል። እንዲህ ያለ ተቋም ኢሳትን ለመርዳት 5 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለመለገስ
እንዴት በቃ ስንል መልሱ የድርጅቱና የሰውየው ማንነት ታሪካዊ ማሕደሩ
ስንመለከት የአሜሪካ የስለላ ድርጅት አሁን ያለው የኦሮሞዎች መንግሥት
ወደ ሥልጣን ያመጣ እንደሆነ መገመት እንደሚቻለው ሁሉ፤ ብርሃኑ ነጋ፤አንዳርጋቸው ጽጌ (ግንቦት 7 ) በባለቤትነት በሚቆጣጠርዋቸው
እንደ እነ “ኢሳት” በመሳሰሉ የፖለቲካ ድርጅት ቴ/ቪዥን ማዕከሎች ላይ እጁ ቢያስገባ ኢትዮጵያ ውስጥ እያየነው ያለው መሰሪ ዕቅድ
“ተጨማሪ ጉልበት” በማግኘት ዕቅዱን ለማሳካት ይቀለዋል።
ኢሳት ግልብጥ ብሎ በአንዴ የአብይ
አህመድ “ዝርክርክ ሥርዓት” ደጋፊ ሆኖ “ዋ! ብትነኩልኝ” ብሎ በ
“እፍ እፍ ፍቅር” ማበዱ ጥርጣሬ ውስጥ እንድንገባ አድርጎናል።
በዋናነት ለዚህም ይሆናል ብርሃኑ
ነጋ “አብይን እንደግፋለን” እያለ ያለው። ከዚያም አልፎ አንዳርጋቸው ጽጌ አትላንታ ከተማ አባላቶቹን ሰብስቦ “አብይ አሕመድ የሚመራው
“ፍኖተ ካርታ” (የመንግሥታዊ አስተዳደር መመሪያ) ግንቦት 7 “የሰጠው መመሪያ” እየተከተለ እንደሆነ” ይፋ አድርጓል። እንግዲህ
ጨዋታው ምን እንደሚመስል እዚህ ላይ ግልጽ ይሆንላችኋል።
ወደ እራሴ ትንታኔ ከመግባቴ በፊት
ሹክሹክታ እንዲህ ይላል፡
“አበበ ገላው ተከሰሰ” በሚል የ
ቱብ ርዕሱ ላይ ሂሩት ልሳነወርቅ የተባለች የኢሳት የሒሳብ ሥራ ሓላፊ “አበበ ገላው አስፈራራኝ” ብላ ፍርድቤት ከስሳዋለች” ሲል
ይገልጻል።ለዚያም ለጁላይ (ሓምሌ) 24/2019 ፍርድ ቤት ልታቆመው መሆኑን ገልጿል። ፍርድ ቤት አልተከሰስኩም ብሎ የካደ አበበ
ገላው በዛው ቀን ፍርድ ቤት ቀርቦ መልስ ሰጥቶ “ዳኛው በነፃ አሰናብታዋለች”። አልተከሰስኩም ብሎ ሲያበቃ በማግስቱ ፡ “የፍርድ
ቤት ውሎ” ብሎ በራሱ “ፌስ-ቡክ” መከሰሱን ከፍርድ ቤቱ የዋለለበት የክርክር ውሎ ዘርዝሮ ማማኑን ስንመለክት ፤ አበበ ገላው ከጆርጆ
ሶሮስ ድርጅት 5 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለማስፈቀድ ‘ፓሪስ’ ድረስ በመሄድ ከዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር በድብቅ ተነጋግሮ እንደነበር
ለሚነገረው ዜና፡ እውነቱን ንገረን ብለን ብንጠይቀው “እኔ አበበ
ገላው ከአብይ አሕመድ ጋር ፓሪስ /ፈረንሳይ/ አገር አልተገናኘሁም” ቢለን ማን ያምነዋል? እኔ በበኩሌ አላምነውም። ትንሽዋን የፍረድ
ቤት የመከሰስ ነገር ከካደ ትልቁን ነገር ያምናል ተብሎ የሚገመት አይደለም።
ሹኽሹክታ በመቀጠልም አበበ ገላውም
ሆነ ታማኝ በየነ ከኢሳት እንደራቁ ከገለጸ በሗላ፤ የጆርጅ ሶሮ 5 ሚሊዮን ለኢሳት ዕርዳታ ሊሰጥ የተባለው የገንዘብ ዕርዳታ “ውሃ
በላው” ብሎ እንዲህ ይላል።
“ኒዮ ሊበራል በመባል የሚከሰሰው
የጆርጅ ሶሮስ ፋውንዴሽን ለኢሳት የገባው የ5 ሚሊዮን ዶላር (200 ሚሊዮን ብር) ቃል በመጨረሻው ሰዓት ታጠፈ ሲል ውስጥ አዋቂው ሹክ ብሎናል። ይህንን ገንዘብ ለማስፈቀድ
አበበ ገላው ፓሪስ ድረስ በመሄድ ከዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር በድብቅ ተነጋግሮ እንደነበር ተሰምቷል።….” እያለ ያትታል።
ይህ ጉዳይ ከ8 ወራት በፊት የተጀመረ
ንግግር እንደሆነ ግልጽ ነው። ታስታውሱ እንደሆነ አንዳንድ ጸሐፊዎች ኢሳት ከአብይ አሕመድ የገንዘብ ዱጎማ እንዳገኘ ፍንጭ ጽፈው
እንደነበር ታስታውሳላችሁ። አሳሳቢ የሚያደርገው “ዜናው ልክ ከሆነ” አበበ እና ጆርጅ ሶሰሮስ ፤አብይ አሕመድ እና ጆርጅ ሶሮስ እንዴት ሊተዋወቁ
እና ሊገናኙ ቻሉ? ዓላማውስ ምንድ ነው? የሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ጥልቅ የስለላ እና የምሁራን ጥናት አጥኚዎች ሊገልጹት የሚችሉት
ጉዳይ እንጂ እንዲሁ በግለሰቦች መልስ የሚያገኝ አይሆንም። ሆኖም ጥርጣሬአችን ግን ማስቀመጥ እንችላለን።
ካሁን በፊት አንድ ጸሐፊ አበበ
ገላውን ለ ሲ አይ ኤ ይሰራል ብለው በሠራተኛነት ጠርጥረውት ትችት ጽፈውበት በራሴው በኢትዮ ሰማይ ድረገጽ እና በሌሎች ድረገፆች
ተለጥፎ እንደነበር ይታወሳል። እኔ እና አበበ ገላው ግንቦት 7 የሚባለው መሰሪ ድርጅት መጥቶ (አበበ ገላው እኔም ግንቦት 7 ነኝ”
ካለ በሗላ “ከመለያየታችን በፊት” በወቅቱ ወዳጆች ስለነበርን ያንን ጽሑፍ መለጠፍ እንዳልነበረብኝ ቅሬታውን በኢመይል ጽፎልኝ በራሱ
“አዲስ ቮይስ” ሲባል በነበረበረው የራሱ ድረግጽ ላይም እኔ ጌታቸው ረዳ ‘ድብቅ የወያኔ ማአከላዊ ሥራ አስፈጻሚ ከፍተኛ አመራር
አባል’ እንደሆንኩኝ አንድ ጸሐፊ የጻፈውን በራሱ ድረግጽ መለጠፉም ቅሬታየ የመልስ ምት ሰጥቼው እንደነበር ይታወሳል። ያንንም በራሴ
ድረገጽ ለጥፌዋለሁ። አበበ ገላው እርግጥ የ ሲ አይ ኤ አባል ነው
አይደለም የሚለው የሚያውቀው አንድ ፈጣሪ እና እራሱ ብቻ ነው። ነገር ግን አበበ ገላው ከጆርጅ ሶሮስ እና ከአብይ አሕመድ ጋር
ፓሪስ (ፈረንሳይ) በምስጢር መገናኘቱ የሚገርም ክስተት እና የሚገርም ሹኽሹክታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ምክንያቱም አሜሪካ በየአገሮቹ ያሉት
ስርዓቶች (ሪጂም ቼንጅ) ለመለወጥ ሲፈልጉ በሲኣይ ኤ ስር የተደራጁ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚመስሉትን የስለላ መዋቅሮችን እና
ጆርጅ ሶሮስን (ኦፕን ሶሳይቲ የመሳሰሉትን) በማሰማራት ነው የመንግሥት ግልበጣ /ለውጥ/የሚያካሂዱት። ስለዚህ ጆርጅ ሶሮስ አገራችን
ውስጥ እጁን ማስገባቱ በተለይ በኢሳት በኩል ንክኪ መደረጉ ባይገርምኝም አሳሳቢ ሆኖ አግኚቼዋለሁ።
ጆርጅ ሶሮስ በድርጅቱ “ኦፕን ሶሳይቲ”
አማካይነት በ1987 ጎረባቾቭ “ሶቭየት ሕብርት” እየመራ ሶቭየት ገና ሳትፈርስ ድርጅቶቹን እና ወኪሎቹን አሰማርቶ ለተማራማሪዎች
ለተቋማት እና ለዜና ማሰራጫ ጣቢያዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሲረጭ የነበረ መሰሪ ሰው ነው። ያውም “market economy
research” ማርኬት ኢኮኖሚ (ነፃ ገበያ) ጥናት ለሚያካሂዱ (ለአሜሪካ ነፃ ገበያ ፍቅር ለወደቁ) Yegor Gaidar እና
Anatoly Chubais የመሳሰሉ የሶቭየት ተወላጆች ዶላር ረጭቶ ሶቭየት ከፈራረሰች በኋ ላ የሰካራሙ የኔልሰን መንግሥት Yegor Gaidar እና Anatoly Chubais የመሳሰሉ የሐገሪቱ
ምጣኔ ሓበት “ዘራፊዎች” አገሪቷን እንዲበዘብዙ እነዚያ የመሳሰሉ ገፋፊ ማፋያዎች እንዲጠነክሩ ያደረገ አደገኛ ሰው መሆኑን ከላይ
ከመግቢያየ የተቀስኩት ያነበብኩት መጽሐፍ ይገልጻል።
እንግዲህ የኢሳት ባለቤት ነበረው
የግንቦት 7ቱ ብርሃኑ ነጋ ከሰይጣንም ቢሆን ትብብር ካገኘን
እንቀበላለን ሲለን የነበረው ንግግሩ የነ ጆርጅ ሶሮስ በነ አበበ ገላው በኩል ሲደረግ የነበረው የገንዘብ እርዳታ ቅንድባችንን
ይብልጥ አቁሞታል። አሜሪካኖች በተለያዩ ድርጅቶች እየገቡ ያራሳቸው ልጆች እየመለመሉ ብዙ አገሮች አፍርሰዋል። ለምሳሌ “ዩ ኤስ
አይ ዲ” የተባለው በኢትዮጵያ አምባሲ ቅርንጫፍ ሥር ያለው የበጎ አድራጎት ድርጅት “ቀዳሚ ስራው” ውስጥ ለውስጥ በአገሮች ላይ
ጣልቃ በመግባት የስለላው መርበብ መዘርጋት ነው።
ለምሳሌ ይህን ተቁዋም ኢትዮጵያ
ውስጥ የምትመራው ሴትዮ ባለ ጎፈሬዋ “ጊል ስሚዝ” የምተባለዋ የወያኔው የማነ ጃማይካ ውሽማ የነበረቺው ሴትዮ ነች። የመለስ ዜናዊ
‘ቀኝ እጅ’ አማካሪ ሆና በረሃ ውስጥ ወያኔን ስታማክር ነበር። ቆይታም መለስ ዜናዊ እስኪሞት ድረስ ምክር እና መመሪያ ሲያገኝ የነበረው ከእስዋ ነበር።
የወያኔ የሲ ኣይ ኤ መረጀ ክፍል በወያኔ ውስጥ ብዙ “ተቀጣሪዎች” አሉ። ለዚህም ነው አገራችን በዘር እየተባላች ያለቺው።
ስለ ጊል ስሚዝ ለማወቅ ከፈለጋቸሁ
በእኔው ድረገጽ (ኢትዮ ሰማይ) Meles Zenawi is a “wristband” gift donated to Ethiopians by
the CIA ( Friday, May 18, 2012 by Getachew Reda) የሚለውን ስታነብቡ “ጊል ስሚዝ” በኢትዮጵያ/ወያኔ/ፖለቲካ
የሰራቺው ሴራ በጥልቀት ትመለከታላችሁ። https://ethiopiansemay.blogspot.com/2012_05_18_archive.html
የ “ዩ ኤስ አይ
ዲ”
የሲ አይ ኤን ሚና በመጠበቅ በመንግሥታት ለውጥ እጁን የሚያስገባ “በጎ አድራጎት ድርጅት ተመስሎ የስለላ ስራ የሚሰራ
ድርጅት መሆኑ በብዙ ሰነዶች ተገልጿል። አንደኛው ማስረጃ ከላይ የጠቀስኩት “ማኒፌሰት ዴሰቲኒ ዲሞክራሲ ኣዝ ኮግነቲቭ ዲሶናንስ”
ደራሲ ዊልያም ኢንግድሃል” የሚለውን መጽሐፍ ስታነብቡ ስለ እነዚህ ድርጅቶች ስንክሳር አሰራር ታያለችሁ።ስለዚህ ነው ኢሳት ከኦፕን
ሶሳይቲ 5 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለማግኘት አበበ ገላው እና “ዝርክርኩ መሪ” አብይ አሕመድ በምስጢር ፓሪስ/ፈረንሳይ ውስጥ ተገናኝተው
ነበር የሚለው ዜና ቅንድባችንን አስቁሞታል።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopiansemay ድረገጽ አዘጋጅ)
No comments:
Post a Comment