Friday, July 26, 2019

ሯጭዋ ደራርቱ ቱሉ እና ኢትዮጵያን የገደለ ባንዳው መለስ ዜናዊ ጉዳይ ጌታቸው ረዳ facebook (Ethio Semay ድረገጽ)


ሯጭዋ ደራርቱ ቱሉ እና ኢትዮጵያን የገደለ ባንዳው መለስ ዜናዊ ጉዳይ
ጌታቸው ረዳ facebook  (Ethio Semay ድረገጽ)
ኢትዮጵያዊትዋ ሯጭ ደራርቱ ቱሉ የተለያዩ ድርጅቶች ላሳየቺው “ተጽእኖ ፈጠሪነት” በዚህ አሜሪካ አገር በሚገኙ ድርጅቶች ሽልማት ሰጥተዋት እና በክብርም ወደ ድርጅታቸው ማዕከል እየጋበዙ ምስጋና እና አክብሮታቸውን የገሉጹላትና ገናም ለመጋበዝ የተዘጋጁ አበሻዊ ድርጅቶች አሉ።  ሯጭዋ ደራርቱ ቱሉ ተፈጥሮ ያደላትን የመሮጥ ችሎታዋ ተጠቅማ እራስዋን እና የአገርዋን ሰንደቃላማ በማውለብለብ በዓለም መድረክ  የኢትዮጵያን ስም አስጠርታለች። ያንን ጥረትዋን እኔም እንደ ሌሎቻችሁ አከብራታለሁ። በተለይ ድግሞ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ‘ጥለት’ ያለው ዙርያ ለብሳ “አምሮባት” ሽብርቅ ብላ “የተገንጣይ ኦሮሞዎችን አንጀት አብግናዋለች”። ለዚያው ላሳየቺው ሽብርቅ ያለ ኢትዮጵያዊነትዋ እኔም አንጀቴን አርሳወለች። ስለዚህመ እኔም በዘንድሮዎቹ ወጣት አዲስ አበቤዎች የአማርኛ ዘይቤ  “ይመችሽ!” ብያታለሁ።


ሆኖም ያ ጀግንነትዋ እንዳለ ሆኖ ያ ቺው ጀግና ብለን የጠራናት እስፖርተኛ ተመልሳ አሳፋሪ የታሪክ ጭቃ የረገጠቺበትን የታሪክ ማሕደርም ገልጠን ማየት እኔ እንደ አንድ ተቺ ብዕርተኛ  የሚያስወቅሳትን ጎንዋን ይቅርታ እስካልጠየቀችን ድረስ ከጀግንነትዋ ማሕደር አብሮ የጎረበጠንን ማሕደርዋንም አብሮ ጎን ለጎን ለማንሳት እገደዳለሁ።


መለስ ዜናዊ አገራችን ቢያንስ ለ20 አመት ቀጥቅጦ ከቀድሞ አባቶቻችን እና እናቶቻችን የተረከብናትን ሰንደቃላማችንን በ44 ባንዴራዎች ተክቶ፤ የተረከብናቸው ሁለት ምን የመሰሉ ትላልቅ ዓለም  ቀፍ የባሕር ወደቦቻችንን ለጠላት በሽልማት ሰጥቶ፤ ኢትዮጵያን ያለ ወደብ አስቀርቶ ፤ ሕዝባችንን እርስ በርሱ በፋሺስቶች ርዕዮት በዘር አስተዳደር ከልሎ ፤አቃቅሮ፤አለያይቶ እስካሁን ድረስ ያላባራ የእርስ በርስ ጥላቻ መፈናቀል እና መገዳዳልን ትቶልን የሄደው “በፈጠሪ ቁጣ” የተቀጨው ትግራይ ያፈራቺው “ባንዳው መለስ ዜናዊ” በሞት ሲሰናበት ስቅስቅ እያሉ ለሕሊናችን እስኪሰቀጥጠን ድረሰ ካለቀሱ እስፖርተኞች መካከል አንድዋ  ደራርቱ ቱሉ ነበረች።


ደራርቱ ቱሉ ‘ቀንደኛ የአማራ ጠላት የነበረው ባንዳው የሞሶለኒው ሓዋርያ የነበረው በመለስ ዜናዊ’ ‘ሞት’ ምክንያት በሚገርም ሁኔታ በጣም ጥልቅ በሆነ አንጀትዋ እጥፍጥፍ ብሎ፤ አንደበትዋ በሚርገበገብ ድምጽ “ስቅስቅ ብላ” ስታለቅስ ያያት ጋዜጠኛ ድራርቱን በቃለ መጠይቅ የጠየቃትን እና የመለሰቺለትን መልስ በዚህ ቪዲዮ ውስጥ ለታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል። እስኪ አንዳንዶቹን መልስዋን በጽሑፍ ያጣቀስኩትን እንመመልከት፡

Derartu Tulu pays tribute to Meles Zenawi




ጋዜጠኛ፦   አትሌት ደራርቱ ምን ተሰማሽ?

ደራርቱ፡-       በጣም ደንግጫለሁ። ከሚገባው በላይ በጣም ደንግጫለሁ። በፍጹም የማይታመን ነበር …….እ. …ህህህህህ….!!!”  ብላ መናገር እስኪያቅታት ድረስ ሰቅስቅ ብላ ከልቅሶዋ ጋር እየተናነቀች የተመለከታት “ካድሬ ጋዜጠኛ” ጥያቄውን በመቀጠል፡ እንዲህ ሲል እንደገና ይጠይቃታል፡-


ጋዜጠኛ፦     (ሓዘንሽ) ይሰማኛል፡ ጠ/ሚኒሰትሩ ለዚች አገር ባለፉት 20 አመታት ያበረከቱት አስተዋጽኦ እንዴት ታይዩዋለሽ እንዴት ይሰማሻል?


ደራርቱ፡-   እንዴት ትገልጸዋለህ! ባጭሩ እግዚአብሔር ሲፈጥረው ፤ለሕዝብ አገልግል፤ ለሕዝብ ጥረህ ግረህ አብላ የተባሉ ነው የሚመስሉት።”


 ትላለች። የድራርቱ መልስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ከፈጣሪ የተሰጣት ኖህ ወይንም ሙሴ ነው ማለትዋ ነው።

ትቀጥልና 

 
ደራርቱ፡- ... “ለሃገራቸው ለወገናቸው አገልግሎት ሰርተው ያለፉ ሰው ናቸው!” ስትል ምስክርነትዋን ሰጥታለች።

ደራርቱ በመቀጠልም እንዲህ ትላለች፦

ደራርቱ፡-  ... “ባጭሩ አቶ መለስ ለኛ ለኢትዮጵያ ስጦታ ነበሩ!” ስትል ኢትዮጵያን ሊገድል፤ የባሕር ወደብ ሊዘጋ የተላከ እኩይ ፍጡር “ለኢትዮጵያ የተሰጠ ስጦታ” ስትል አንጀታችንን አሳርራዋለች። የደላው ሰው ከዚህ ወዲያ ምን ይጠበቅበታል?

እንዲህም ብላለች፦

 ደራርቱ፡-   ...   “(ጠ/ሚንስትሩ ) ያላደረጉት ያልሞከሩት/ ያልጀመሩት/) የስራ መስክ የለም። የቀራቸው ነገር ቢኖር በመጽሐፍ ሊሰጽፉት ያሰቡትን ቀርቷቸው ሊሆን ይችላል”” ትላለች። እንግዲህ ይህ የምትለን ንግግር የሰማቺው ጸረ አማራው መለስ ዜናዊ የቀረኝ ነገር ቢኖር ያደረግኩትን ገድል በመጽሐፍ መጻፍ ብቻ ነው የቀረኝ ፤ያንን ድግሞ ጥሮታ ስወጣ ወይንም ሥልጣን ስለቅ ለመጻፍ  ዓላማ አለኝ እያለ ሲመጻደቅ የነበረውን በቴ/ቪዥን  ያደመጠቺውን ነው የደገመቺው።ምናልባት ቢጽፍ ኖሮ “አማራውን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ባሕር ለመዝጋት የኢትዮጵያ 2 መቶ ሺህ ወታደር (ቤሰብ ሳይጨር! ቤተሰቦቻቸው ከጨመረ ወደ አንድ ሚሊዮን ቤተሰብ ያለ መጦርያ አስቀርቶ ለሕሊና ጭንቀት የዳረገ)... አባርሬ በረንዳ ለማኝ ማድረጉን ፤እስላማዊ ተቋማት እና ክርስትያናዊትዋ ኦርቶዶክሳዊት ተቋም እንዴት እዳፈራረሳቸው ሊጽፍ ዓላማ ኖሮት ሊሆን ይችል ይሆናል። በዚህ ጉዳይ መለስ ዜናዊ ሊጽፈው ያሰበውን መጽሐፍ ጉዳይ ዳራርቱ የምታውቀው ቢኖር ትግልጽልን ይሆናል።

ትቀጥል እና እንዲህ ትላለች።

 ደራርቱ፡-  .... “በተረፈ (መሪያቸን) ያላቀዱት ያላደረጉት ነገር የለም” ስትል እና በሚገርም አለቃቀስ ‘ስቅስቅ’ ብላ እያለቀሰች (መናገር እስክታቆም ድረስ) እንዲህ ስትል መልስዋን ደምድማለች።

 ደራርቱ፡- .... “በበኩሌ እኛ የእስፖርት ቤተሰቦች በገንዘባችን በጥረታችን ለእሳቸውም ዕድሜ ልኬን ሙሉ ለማገለግል ዝግጁ ነኝ ቃልም እገባለሁ።”

ስትል በሚገርም ሁኔታ መለስ ዜናዊ ከሞተ በላም  “እሳቸውንም…” እያለች   ዕደሜ ልክዋን የመለስ ዜናዊ “ሌጋሲ” ላመስቀጥል እና ለማገልግል ቃል ገብታለች።

አንባቢዎቼ እንደምታስታውሱት በዚህ ጉደኛ ክስተት  አዝማሪው፤ ተዋናዩ፤ ገጣሚውን ሁሉ ተችተናል። በዓለም ፊት ሕጋዊ እና ጥንታዊትዋ ሰንደቃላማችንን ወደ አፈር እየጣሉ የወያኔ ሰንደቃላማ ሲያውለበልቡ አይተናቸው ተችተናቸዋል (ተቺውም ቀዳሚው እኔ ነበርኩ)። ሓብት ያቀማጠላቸው በዚህ ክስተት የተበላሹ የእስፖርተኞች ታሪክ ነቅፈናል። እነ ሃይለ ገብረስላሴን ክፉኛ ተችተናል።  ደራርቱ ለምን ተተቸች የምትሉ አድናቂዎች እና ደራርቱ ወደ ጣይቱ የባሕል ማዕከል በክብር እንግዳነት በመጋበዝዋ ለጀግናችሁ ያላችሁን አድናቆት ለመግለጽ  የጻፋችሁትን የኢመይል ደብዳቤ ወደ ግል ኢመይሌ በግልባጭ የላካችሁልኝ ነፈዝ ምሁራን ይህንን ትችቴንም እንዳማይጠማችሁ ባውቅም፤ ታሪክ ነው እና ዕሬቱንም ተጋቱት!


ኢትዮጵያን ለዚህ ጉድ ላደረስዋት ባንዳዎች ዕምባ ያቀረሩት ሁሉ “ይቅርታ እስካልጠየቁን ድረስ” ብዕራችን አይዘነጋቸውም! መለስ ዜናዊ የደራርቱ፤የሃይሌ ገብረስላሴን፤ የቀነኒሳ በቀለ …ወዘተ ወዘተ “እናት፤አባት እህት ፤ ወንድም ፤ ልጅ፤ሚሰት፤ባል …….” ቢገድልላቸው፤ ጥፍራቸው ቢነቅልላቸው፤ማህጸናቸው ውስጥ የጋለ ብረት ቢለቅባቸው ኖሮ፤ ሃይላንድ ቢያንጠለጥልላቸው  ኖሮ…,አልቃሽ እስፖርተኞች ሁሉ እንዲያ ስቅስቅ ብለው አገር ለገደለ ጸረ አማራ ባንዳ የነበረውን መለስ ዜናዊን እየተንሰቀሰቁ አያልቅሱለትም ነበር። ቅር ያላችሁ አላችሁ? ቅር ይበላችሁ! እኔ እና ብዕሬ ሁሌም “አንድ ለናቱ ነኝ” እና ቅር ቢላችሁም ሆነ ቢመርራችሁም ዋጡት!
ጨርሻለሁ።
አመሰግናለሁ!
ጌታቸው ረዳ facebook  (Ethio Semay ድረገጽ) 



  

No comments: