ለትግራይ ታጋዮች የቀረበ ጥሪ
ጥሪ አቅራቢ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
Latest Note from the editor
The second image is
from Geza Tegaru Pal Talk. I posted this image for my readers so you will have
a minimum understanding how TPLF followers think about their leaders. I visited
TPLF cults' Pal Talk called Geza Tegaru Pal Talk this morning to study the mind
of these cults how they still think about their leaders even after they heard
the proclamation to give Badime to Eritreans. I simply wrote the following on
their board saying;-
" Tigray fighters and elites have now serious
challenges. They need to form a secret body and arrest TPLF leaders for
conspiring against the people of Tigray/Ethiopia -for giving away Badime and
other localities without the consent for the people of Tigray or
Ethiopia."
this made this fool by the name Solda-17 irritated and
bounced me from his PalTalk room. How naive and foolish this cults can be is
beyond me. That is why TPLF is doing what it is doing now,
because there are many fools like this illiterate fellow and his
likes who can go extra mile to die for them regardless they raped their mother,
sisters, their land, , their dignity, their property Mind slavery is unbreakable chain.
Tigrayns are at this moment shackled with this brutal unbreakable chain.
ወያኔዎች አብይን አሳምነው ባድመ፤ዛላምበሳ እና ቡሬ ለኤርትራ
እንዲሰጥ ወትውተው ውሳኔ ላይ ደርሰው ከ60 ሺሕ ኢትዮጵያውያን በላይ ህይወታቸውንና አካላቸው የሰውባቸው ቦታዎች ከንቱ መስዋእት
እንዲሆን አድርገዋል።
የወያነ ትግራይ መሪዎች ብዙዎቹ “ኤርትራኖች” እንደሆኑ ብዙ
ጊዜ የተነጋገርንበት ስለሆነ ወደ እዛው አልገባም። ዋናው ተጠያቃዎቹ ትውልደ ኤርትራ እና ትግሬዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ቀንደኛ ተጠያቂዎች
በትውልዳቸው ትግሬዎች የሆኑትን እና ለነዚህ መሪዎች አምኖ 27 አመት በኢትዮጵያ ህልውና የተቋመሩ የውጭ ቅጥረኞችን አጅበው ፤ደግፈው
ወደ መንግሥት ሥልጣን ያመጡልን አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ተጠያቂ ነው።
የወያኔ መሪዎች ‘ጸረ አገር’ ናቸው፤ ‘ቅጥረኞች” ናቸው “ብሔራዊ
ስሜት የሚባል DNA ከህዋሳታቸው ውስጥ የለም” ጸረ ብሔራዊ ሰንደቃላማ፤ጸረ ታሪክ፤ በደም እና በክሕደት የሚጓዙ ክፉ አራዊቶች
ናቸው፡ ‘አትደግፉዋቸው’ እያልን ለ27 አመት ሙሉ የትግራይን ሕዝብ ብንመክርም፤ መልሳቸው እኛን መስደብ ነበር። በተለይ በእኔ
እና በጥቂት ወዳጆቼ ላይ የወያኔ ትግራይ “ጀሌዎች” ጭራሽኑ ትግሬነታችን ሁሉ ለመንጠቅ ሞክረዋል። ያ ሁሉ ችለን 27 አመት ተጉዘን፤
ይህ ካሃዲ ቡድን በየቀኑ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ‘ባዕድ’ የማያደርገው የባዕድ ስራ እየወሰኑ ውሳኔዎቻቸው ኢሕጋዊ መሆናቸወን በማስረጃ
ብናሳያቸውም፤ በምንም መልኩ ሊሰሙን አልቻሉም።
አሁን ባዳ ለኢሳያስ ተሰጠች ሲባል የወያኔ ‘ጀሌዎች” መንጫጫት
ጀምረዋል። ጉዳዩ የሚያሳዝን ቢሆንም፤ እኔ ደግሞ እንኳን ደስ አላቸሁ! እሰየው እላለሁ። ስቃዩ አሁን ሊሰማችሁና ስታለቅሱ ማየቴ
እጅግ “ደስ ባይለኝም” እጅግ ደስ ብሎኛል። ተው የሚታመኑ አይደሉም ብንል እኛን ማመን አቅቶአችሁ የመሪዎቻችሁን ‘ውሸት” ትመገቡ
ነበር። መጨረሻ ሌለውን ሕዝብ እንዳስለቀሱት እናንተም እንደሚያስለቅሱ እርግጠኛ ነበርኩ። ይኼው ዛሬ እንናተንም ደረሱላችሁ።
ደጋግመን ያለመሰልቸት ቢረዳችሁ ብለን “የአማራ መሬት” ለሱዳን
አስረክበው፤ ሌላውንም አገራዊ እሴቶችን ሁሉም ሸጠው፤ሸጠው ሲያልቅባቸው መጨረሻ ወደ ትግራይ መሬት እንደሚዞሩ ይህ መዘዝ እንደሚያመጡባችሁ
ነግረናል። ኤርትራን ባሕርን አስገንጥሎ ያለ ባሕር ሲያስቀሩንና ውሳኔውን ስንቃወም የናንተ መልስ “ዓሰብ ዓሰብ” የሚሉ “ደርጎች
ናቸው”፤ “ጦርነት ናፋቂዎች” “የከሰሩ ናቸው” እንዲህ ናቸው፤እንዲህ
ናቸው…. እያላችሁ መሪዎቻችሁ የመገቡዋችሁን ውሸት እናንተ ተቀብላችሁ ‘ጀሌነታችሁ” ለማስመስከር ሰደባችሁን። ያንን ሁሉ ችለን
“የአልጀሪስ ስምምንት” ጸረ ኢትዮጵያ እና በሁለቱም ተሟጋች ወገኖች ትውልዳቸው ኤርትራኖች እና በኤርትራኖች ውክልና የተካሄደ ነው
ብለን ብንልም፤ ያኔም አንሰማችሁም ብላችሁ የሰላም ማምጫያ በር ነው አፋችሁ ክደኑ እያላችሁ ሰደባችሁን። አሁን መጨረሻ ያ ሁሉ
የአማራ መሬት ለሱዳኖች ሽጠው ሲያልቅባቸው ወደ ትግራይ መሬት በመዞር “ባድመን እና ዛላምበሳን…” ወደ ኤርትራ በነፃ ሰጡ። ነገ
ሻዕቢያ ጦሩን አሰማርቶ ወደ ወልቃይ ቢገባ እና አጋመ አውራጃም የኔ ነው ብሎ ጦሩን ቢያሰማራ፤ ዋስትናችሁ ምንድ ነው? ምክንያቱም
ለኢሳያስ ወደ ባድመ መምጣት ምክንያቱ ባድመ ሳይሆን ምክንያቱ ሌላ ነው። ዛሬም ባድመ ቢሰጥ ነገ ወልቃይት ይገባል። እንደ አለቆቻችሁ’አሲያስ
አያደርገውም! “አብዷል እንዴ?” “የጠላ ቤት የደርጎች ወሬ ነው” ብላችሁ ካላጣጣላችሁት ፤’ “ኢሳያስ ካበደ ዘመን ሆኖታል ነገም
ወልቃይት ይጠይቃል።” ወያኔዎች ዕድሜ ከሰጣቸው አማራ ከሚወስደው ወንድማችን ይውደው ብለው ወልቃይትነም ሽሬ-እንዳስላሰ”
አንደሚሰጣቸው ዋስትና አለን ማለት አትችሉም? ለባድመ ለዛላምበሳ..ዋስትና ከሌላችሁ ለወልቃይት ለዓሊቴና ለዓዲግራት ሽሬ ምን ዋስትና
አላችሁ? “ንዓደየ- አነ -ንዓደየ” አጫፋሪ ተከታይ ጀሌዎች እስካላጡ ደረስ “ኢትዮጵያ አየር መንገድን፤ ኤሌክትሪኦክን እና ዋና
ዋና ዕምብርት ያገሪቷ ሞቶሮች ለአልጠግብ ባይ የውጭ እና የውስጥ ከበርቴ እስከሸጡዋቸው ድረስ ገና መቀሌንም ለውጭ ኢንቬስተር ለባለ ሃብቶች ይሸጡዋታል። ዋስትና አላችሁ? ምንምን?
ለባድሜ ከሌላችሁ ለሌላው እንደማትሸጥ ምን ዋስትና አላችሁ?
ባድሜ ዛላምበሳ እና ቡሬ ዓዲምሩግ (ባዳ) የትግራይ መስተዳድር
የነበሩ ናቸው (ሦስቱን አውቃቸዋለሁ)። ሻዕቢያ ጦሩን ክተት ብሎ ወደ ባድመ አስገብቶ ሲያበቃ በኢትዮጵያውያኖች ድረሱልን ኡኡታ
ዕርዳታ ተደርጎ ሻዕቢያ ‘ተዋርዶ ሸሽቶ’ ወጣ። ብዙ ሺሕ ሕዝብ መስዋእት ተደርጎ ሻዕቢያ ከተባረረ በሗላ ማንም ሳያስገድዳቸው
(ኤርትረም እርዋ ወደ አልጄሪስ ሳትሄድ) እነ መለስ ዜናዊ ‘በሻጥር’
እራሳቸው “ወደ አልጄሪስ ሄደው” ጾሮና የትግራይ መሬት ነው ቢባሉ አንወስድም የኤርትራ ነው ብለው ዳኞችን ግራ አጋብተውና ዳኞቹ
እስኪገርማቸው ድረስ ‘ለኤርትራኖች ስጡዋቸው ብለው አስገደድዋቸው። ዳኞቹም ገርሟቸው ካላችሁስ እሺ ብለው “ሰጥዋቸው””። የተቀረው
ባድሜንም መጨረሻ ወያኔ “እሺ” ብሎ ዛሬም ይኼው ለናት አገራቸው ለኤርትራ ሸለሟት። ከዚሕ ዜና በሗላ ትግሬዎች በየ “ገዛ ተጋሩ
ፓልቶክ” እየየ!! ብለው ምርር ብለው ማልቀስ ጀምረዋል። እኔ ደግሞ ‘በደምብ አልቅሱ! እሰየው! ይውጣላችሁ! ብታለቅሱም እራሳችሁ
ያመጣችሁት ጣጣ ነውና እራሳችሁ ተዋጡት” እላለሁ። ወያኔዎች የሚታመኑ አይደሉም፤ “አትመንዋቸው” ብለን ብንወተውት መልሳችሁ “ስድብ
ነበር።
ይግረም ብሎ አሁንም አንዳንድ ደናቁርት ጀዎችሌ ወየኔዎች ብምንም
መልኩ አንክዳቸውም ምንምን እንኳ ውሳኔው ስህተት ቢሆንም፤መስዋእት የከፉሉ ስለሆኑ…. \ሲል አንድ እንደርታዊ ሽማግሌ (ላስ ቬጋስ)
በገዛ ተጋሩ ፓልቶክ ሲናገር ሰምቼው ‘እነዚህ ሰዎች ነገ እናታቸውን ሚስታቸውን ቢደፍሩላቸውም ምንም እንኳ ስሕተት ቢሆንም መስዋእት
የከፈሉ አርበኞቻችን ስለሆኑ…” እያሉ ይቀር እንደሚሏቸው ከዚህ መረዳት ይቻላል። ብየ አግራሞቴን ይዤ ከፓልቶኩ ወጣሁ። አንዱ ሰላማያዊ
የተባለ ጎበዘ ትግሬ እነዚህ ሰካራሞች ናቸው ፖለቲከኞች አይደሉም ብሎ ሲከራከር “ለጂራ” የተባለች ምስኪን ጀሌ ‘አትስደባቸው’
ፐርሰናል ነው” እያለች ትከላከልላቸው ነበር። ሰላማዊም “ሰካራማች አይደሉም ብለሽ የመከራከር መብትሽ ነው እኔ ግን እነዚህ ሰዎች
ፖለቲከኞች ሳይሆኑ ናላቸው በመጠጥ የዞረ ብሔራዊ ጉዳዮችን በቅጡ ያልተረዱ፤በቀላሉ በሌሎች ሊሸነፍ የሚችል በመጠጥ ሱሰኞነት የደከሙ
ናቸው፤ አገር ያስደፈሩ ቅጥረኞች ናቸው” ቢላትም ያው “የለየላት ካልት ስለሆነች መከላከሉን ቀጥላበታለች።
ጀሌዎች ሆይ! አሁን ማልቀሱን ተውት እና፤ እርግፍ አድርጋችሁ
“ወያኔ’ የሚባሉ መሪዎቻቸውሁ ከትግራይ መሬት አስወግዱ። የመጀመሪያ አርምጃ መውሰድ ያለባችሁ ነባር የትግራይ ተዋጊዎች በሰራዊትም
ይሁን በሌላ ስራ የተሰማራ ታጋይ ጥሪ አስተላልፋችሁ (በድብቅም በይፋም) ስብሰባ እንዲጠራ በማድረግ ውይይት ካደረጋችሁ በሗላ ፤
ሳትውሉ ሳታድሩ “መላው የወያኔ አመራር” በታጋዮች ቁጥጥር ስር
አውላችሁ /እሰርዋቸው”። ከዚያ ማን እና ለምንስ እንዲህ ያለ ትዕዛዝ ሊያጸድቅ አንደተገፋፋ እንዲጣራ የትግራይ ወታደራዊ
(የታጋዮች) መፈንቅለ ህወሓት በማካሄድ፤ ሓላፊነት የሚወስዱትን በሚቋቋም አጣሪ ኮሚቲ እንዲጣራ።
አጣሪ ኮሚቴዎች በታጠቁ ሰዎች መሆን አለበት። ሕዝብ ውሳኔ
አሳልፎ ነው የተላለፈው ካሉም በየትኛው ስብሰባ እንዲህ ያለ ውሳኔ እንደተላለፈ “መፈንቅለ ወያኔ” ኮሚቴው ማጣራት አለበት። የትግራይ
ምሁራን አሁን ትልቅ ፈተና አላችሁ ይህንን እንድትወጡ ታጋዮችን መጥራት እና ማስተባበር ይኖርባችሗል።ካልሆነ ማልቀስ የሚፈይደው
ነገር የለም። ነገ ወልቃይት፤ሽሬ፤ከዚያም አዲግራት መምጣቱና ከዚያም “ለሳም ስንል ተስማምተናል ውሰዱ” ማለታቸውን አይቀርም። እናታቸውን
ኢትዮጵያ ማሻሻጥ የለመዱ “የባዕድ ደላሎች” ስለሆኑ “ትግራይን” ማሻሻጥ አዲስ አይሆንባቸውም። ጉዳዩ አንጀቴን ቢያሳርርረኝም፤
ስታለቅሱ ሰምቼ ግን እሰየው! ነው ያልኩት። በጣም ነው የረካሁት! ያመረታችሁት ነው ያፈሳችሁት! የማይታመን ማመን ውጤቱ ይኼው
ነው።የአማራ መሬት ለሱዳን አሳልፈው ሰጥተዋል ብለን ስንል አንዳልሰደባችሁን ሁሉ- ዛሬ በባድሜ ስታለቅሱ ጥሩ መማሪያ አምላክ ልኮላችሗል።
ከዚህ ወዲያ ልብ ከገዛችሁ ማለት ነው። ግን እጠራጠላሁ ልብ የምትገዙ አትመስሉም። የሚያሳዝነው ግን ከመላ አገራችን ከጫፍ ጫፍ
መጥቶ ደሙን አፍስሶ ያስከበረውን መሬት በአለቆቻችሁ ላይ ባትበቀሉ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቶውንም ይቅር የሚላችሁ አይመስለኝም።፡ኢሳያስ
ነገ ወደ ወልቃይት ወደ ሽሬ እና አዲግራት ቢመጣ የሚረዳችሁ እንደሌለ ማወቅ አለባችሁ። ስለዚህ የወያኔ መሪዎች ላይ ዕርምጃ ውሰዱ!
አገር ሱቅ አይደለም ለችርቻሮ የሚሸጥ። መልዕክቴን ተግባራዊ አንደምታደርጉት ተስፋ አለኝ!!
ETHIOPIA: ERITREAN FORCES BOMB
BORDER TOWN OF ADIGRAT
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment