የወያኔ አሽከሮች የትግሬ ሚሊሽያዎችን የማደራጀትና የማስታጠቅ
ጥሪው ሲፈተሽ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
Aigaforum and Tigraionline slogan- critiqued by Ethiopian Semay |
በዚህ ርዕስ ሦስት ነጥቦችን እንመለከታለን (1) በርዕሱ የተመለከተ
ጉዳይ እንፈትሻለን (2) ዶ/ር አብይ ትግሬዎችና ወያኔ አንድ ኣይደሉም የሚለው (ቲ ፒ ኤል ኤፍ እና ትግሬዎች አንድ አይደሉም)
(3) ትግሬዎች በዚህ ስርዓተ ዘመን (ስርአቱ የሚለው ወያኔን ማለት ነው) አልተጠቀሙም፡ (4)- የትግራይ ሕዝብ ልማትና ዲሞክራሲ
ለማምጣት ነው የታገለው ብሎ አብይ ስለተናገራቸው ነጥቦች አጠር አደርገን እንፈትሻለን።
ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት አብይ ፓርላማ ውስጥ ስለ አደረገው
ጥያቄና መልስ ክብር ሰጥቼዋለሁ። አንጀት የሚያርስ! በማለት የሚሰጠው ክብር እየሰጠሁ መተቸቴም መብቴን እንድታከብሩልኝ እጠይቃለሁ።ይህ
ካልኩኝ በኋላ እንቀጥል።
በትልቁ ርዕስ ልጀምር።
ሰሞኑን ወያኔ ከምንም ተነስቶ የብዙ ሺሕ ኢትዮጵያውያን ህይወት
የበላውን የባድሜን እና የ17 ገጠሮች ድምበር ያለምንም ማንገራገር ለሻዕቢያ እሰጣለሁ ስላለ ብዙ ዜጎችን ትግሬዎች ጭምር አስቆጥቶ
በወያኔ ባንዳዎች ላይ ያልበረደ ቁጣ ማስከተሉን ታስታውሳላችሁ። ባንዳዎቹ
ያልጠበቁት የሕዝብ ቁጣ ስያዩ ያንን ለማብረድ ሲሉ በተካኑበት ውሸትና ማታለያው መንገድ በመጠቀም የራሱን ውሳኔ “ኢሕአዴግ” ነው
የወሰነው “ፓርላማ ስላላየው ጉደለት አለው” ወዘተ..ወዘተ.. እያለ በመቀላመድ ከወንጀሉ ሊያመልጥ ሞክሯል። ሰሞኑን ፓርላማ ላይ
አብይ ያደረገው ንግግርም የሚያሳየው ውሳኔው ተግባራዊ ይደረግ ያልነው እኛ ሳንሆን ፓርላማው በመለስ ዜናዊ መሪነት ተቀብለነዋል
ብላችሁ የወሰናችሁ እንናተ ስለሆናችሁ ያንን እስካልሻራችሁት ድረስ ውሳኔውን እንዲፈጸም መወትወት የናንተ ሓለፊነት መሆን ነበረበት፡
ሆኖም የናንተን ውሳኔ ተቀብሎ ሥራ አስፈጻሚው ሓላፊነት ለመወጣት መዘጋጀቱ አያስወቅሰውም ሲል “በቁም ሙታኖች የተሞሉበት የወያኔው
ፓርላማ አባሎችን መልሶላቸዋል። ይህ ቦምብ መልስ ዱብ እዳ ስለሆነባቸው
ደንግጠው ውጠዋት ዝም አሉ።
መገንዘብ ያለብን አብይ በቀጥታ ወያኔዎችን ማሳጣት አልፈለገም
እንደሆን እንጂ ‘ኢሕአዴግ’ የሚባለው ያለ ወያኔዎች ያለ እነ ደብረጽዮን ተሳትፎና ውትወታ ዝም ተበሎ በነ አብይ አነሳሽነት ውሳኔው
አልፈጸመም። ባጭር አማርኛ ‘ኮርኳሪዎቹ ወያኔዎች እንጂ አብይ እንዳልሆነ’ መገመት አያዳግትም። ባንዳዎቹ ፓርላማ ወስዶ ማስወሰን
ነበረበት ብሎ የሚዘላብደው እራሱን ለመደበቅ ካልሆነ አብይ እንዳለው “ፓርላማ ተብየው” በባንዳው መለስ ዜናዊ መሪነትና ጎትጓችነት
የተካሄደ ሴራ ነው። ያውም የአልጄሪስ ስምምነት ከመደረጉ በፊት ቀደም ብሎ ከ4 ቀን በፊት ፓርላማው ውሳኔውን ሳይደርሰው ነበር
ፈርሞ ያጸደቀው (ስዩም ተሾመ ያቀረበው የሰነድ ማስጃ በድረገጾች ተለጥፈዋል እሱን ተመለክቱልኝ)። ስለዚህ በኢትዮጵያውያን ደም
እና መስዋእትነት ብቻ ሳይሆን በትግሬዎች ድምበሮችና ኗሪዎች ህይወት የተቋመረው
“ህወሓት” እንጂ አብይ እንዳልነበረ ከተደረገው የአልጀሪሱ የአገር ክሕደት ወንጀል ሰነዶች መፈተሽ ያስፈልጋል።
እንዲያም ሆኖ ሓፈረተ-ቢሱ “የባንዳዎቹ (ህወሓት) ማዕከላዊ
ኮሚቴ” ተሰብስቦ ካወጣው የጋራ መግለጫ ውስጥ “ሦስት” ነጥቦችን በማንሳት ባለፈው ሰሞን “አገሪቷ ወደ ብረት ፍትግያ መግባትዋ አይቀሬ ነው ስላችሁ አላመናችሁኝም”(ጌታቸው ረዳ) በሚል ርዕስ በጻፍኩት ሐተታ ላይ ባንዳዎቹ የአልጄሪስ ስምምነት ምክንያት ተጠቅሞ ቀስ በቀስ የወያኔን
ስልጣን በመሸርሸር ላይ ያለው ሕዝባዊ ንቅናቄ ለማፈን እንዲመቸው በዶ/ር አብይ እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች እቃወማለሁ ያለበት
ምክንያት በዝርዝር ገልጫለሁ።
አሁን እየታየ ያለው ጥገናዊ ሆኖ ነገር ግን ይደፈራሉ ተብለው
የማይታሰቡ ክስተቶች እየደፈረ በመምጣቱ ከወራቶች በፊት ባንዳዎቹ በመደናገጣቸው መቀሌ ውስጥ የተለያዩ የህወሃት ድርጅቶችን በመጥራት
(ከአዲስ አባባ ጭምር ወጣቶችን በመጥራት) ስብሰባዎች በማካሄድ “በተስፋና
በስጋት” ላይ ነን በሚል ፈራ ተባ እያለ አንዴ በግልጽ አንዴ ዳር ዳር እያለ ባካሄዳቸው ስብሰባዎች ላይ በሕዝብ ግፍት
እየመጣ ያለው ዘግምተኛ ለውጥ እያሰጋው እንዳለ በትግርኛ ያደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ተከታትለነዋል።
ሰሞኑን ደግሞ በውጭም በውስጥ አገርም የሚኖሩ የወያኔ ተከታዮች
‘የባንዳ አለቆቻቸውን ልሳን እና ስጋት’ በማስተጋባት በዶ/ር አብይ መሪነት እየተጋሄደ ያለው ብዙ ኢትዮጵያውያን የወደደው ዝግምተኛ ግን የተዘጋው በር ከፋች የሆነው ለውጥ በመስጋት
በትግራይ ሕዝብ ህልውና እንደመጣ በማስመሰል የትግራይን
ሕዝብ ‘የፍርሃት ፕሮፓጋንዳ” መንዛት ጀምረዋል።ከላይ ከመግቢያው ላይ የሚታዩት
ሁለት ስዕሎችና መፈክሮች በስተግራ የፕሮፌሰር አስራት ምስል የሚታየው ትግራይ ኦን ላይን በሚበላው (ትግሬዎች ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ የጀግንነት ዲ ኤን ኤ በደሙ ውስጥ
አለው ብሎ የሚያስተምር) በጸረ አማራ ቅስቀሳው የታወቀ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ አሰራጭ ድረገጽ ላይ የተለጠፈ ሲሆን “ያልተደበቀው የአማራ አክራሪዎች አጀንዳ” በማለት በዶ/ር ደብረጽዮን
ገብረሚካል (አሁን የወያኔ ሊቀመንበር ያለው) የተቀነባበረው የውሸት ሰነድ ታስረው ለሞት የተዳረጉትን የፕሮፌሰር አስራትን ምስል
“ከአሸባሪነት እና ከጸረ ትግሬነት” በማገናኘት በድረገጹ ላይ በመለጠፍ የአስተማሪዎቻቸው የነደብረጽዮን የነ ስብሓት ነጋ ኮቴ መከተሉን
አይተናል።
ቀጥሎ ወደ ቀኝ በኩል ያለው የትግርኛ መፈክር ያው ሌላው
‘የታወቀው የወያኔ “ወግ አጥባቂ” አይጋፎረም ላይ እና በትግራይ ኦን ላይን ላይ የተለጠፈ መፈክር ነው። ወደ አማርኛ ሲተረጎም
(ሚሊሽያና ይፍለጦ፤መንእሰያት ይወደቡ፤ ሕድሪ ይቀበሉ፤ ሸጥ ማዓንጣ ከምቀደምና!” “ሚሊሺያዎቻችን ይወቁት፤ወጣቶች ይደራጁ፤ አደራ ይረከቡ፤ ዛሬም እንደጥቱ ወገባችንን ጠበቅ ማድረግ ይጠበቅብናል!”
ይላል። ይህ ጥሪ ለትግሬ ሚሊሽያ እና ወጣቶች ብቻ የተደረገ ጥሪ ነው። ጥሪው የሩዋንዳው ኢንተርሃሙዌ ቡድን አዘማሚያ የተቀዳ የሚሊሺያና
የወጣቶች ጥሪ ይመስላል። ሩዋንዳ ውስጥ በስልጣን ላይ የነበረው የፕረዚዳንት ሃቢያሪማና አንድ ወጥ የሆነ የሁቱ ጎሳ መንግሥት ተልእኮው
ለማስፈጸም CDR (ወይንም “MRND” (ብሔራዊ አብዮታዊ ልማታዊ እንቅስቃሴ- mouvement révolutionnaire national pour le
développement)የሚባል ድርጅት በመመስረት (ወያኔዎች ሪቮሊሺናሪ ዲሞክራሲ እንደሚለው) በውስጡ ደግሞ “ኢንተርሃሙዌ” (ትርጉም
- “አብረው የሚሰሩ”) የሚል እንቅስቃሴ በመፍጠር ዋናው ተልእኮው “በጠላት ላይ ማትኮር” የሚል ተልእኮ የነበረው ነው።
አሁን በነዚህ የወያኔ አሽከሮች ጥሪ የምናየው፤ የወያኔ መሪዎች
መቀሌ ውስጥ ባደረጉዋቸው በርካታ የተከማቹ ስበስባዎች የትግራይ ሕዝብ
እና አባሎቻቸው ‘በጠላት እና ተባባሪዎች” ላይ ማድረግ እንዳለባቸው ደጋግመው ተናግረዋል። ሩዋንዳም በተጠቀሱት ድርጅቶች ሁለት ጠላቶች ተብለው የተመደቡ የጠላት ምደባዎች ነበሩ። ዋናው ጠላት እና
የጠላት ተባባሪዎች (Hutu Malcontents)። ዛሬ በወያኔ አምላኪዎች እየተደረገ ያለው የጎሳ ጥሪ በትግሬዎች ላይ የተጠራ
ጦርነት የታወጀ ይመስል “ሚሊሺያዎቻችን ይወቁት፤ወጣቶች ይደራጁ፤
አደራ ይረከቡ፤ ዛሬም እንደጥቱ ወገባችንን ጠበቅ ማድረግ ይጠበቅብናል!” በማለት “የፍርሃት ቅስቀሳ” በማካሄድ “ትግሬዎችልጆቻቸውን
ገብረው ደማቸውን አፍስሰው ዲሞክራሲ ያመጣ የወያኔ አብዮት” ያልተዋጠላቸው
እና ሊዋጥላቸውም የማይፈልጉ ቀንደኛ የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች” ስልጣናችን ሊቀሙን፤ማንንታችን
ሊፈታተኑን መልካቸው እየለዋወጡ እየተደራጁ ሊፈታተኑን እየመጡ ነው እና እንደ ጥንቱ ‘ተደራጅ’ በማለት ሚሊሺያ እና ወጣት ትግሬዎች
ወገባቸውን በማጥበቅ ለትግል እንዲዘጋጅ ጥሪ አድርገዋል።
ታስታውሱ እንደሆነ ሩዋንዳ ላይም ሁቱዎች በቱትሲ ጎሳዎች ላይ
ተመሳሳይ ጥሪ አድርገው ነበር። “The Tutsi inside or outside the country extremist and
nostalgic for power, who have NEVER, recognize and will NEVER recognize the
realities in the 1959 social revolution
and who wish to reconquer by all means necessary including arms” (The Fate of
Africa - Martin Meredith). እንግዲህ ወያኔዎች እና ተከታዮቻቻው የሚሉትም ከላይ በፎቶግራፍ እንዳሳየሁዋችሁ “Fedralism is Dead” (የፌደራሊዘም የመጨረሻ ግባተ መሬት
ተፈጽሟል) ይላል። የፌደራሊዝም ስርዓት ሊዋጥላቸው ያልፈለጉ እና ከቶም የማይዋጥላቸው የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች “ፌደረላዚዝማችንን ገድለውታል” ስለዚህም የትግራይ ሕዝብ
ልጆች የገበርንበትን “ፌደራሊዝም” የማይዋጥላቸው ጠላቶቻችንን ለማስቆም “ሚሊሺያዎቻችን ይወቁት፤ወጣቶች ይደራጁ፤ አደራ ይረከቡ፤ ዛሬም እንደጥቱ ወገባችንን ጠበቅ ማድረግ ይጠበቅብናል!”
በማለት ጥሪ አድርጓል።
“The National Movement of Amhara is a militant aggressive group which is openly threatening the Ethiopian federal system and the Ethiopian constitutional order. In addition to threatening the government, this movement is showing extreme hostility towards the Tigrai people.”… “The government of Tigrai should start recruiting volunteer fighters to beef up the local militias for additional defense force. What is left of the TPLF should learn from its mistakes and start focusing in defending Tigrai and its people. TPLF should start denying the reality facing Ethiopia and start telling the people of Tigrai what dangers are developing and what options they have instead of telling them they have only one option. All Tigrai civic organizations, business communities, and other political groups should start reorganizing just like the time of armed struggle.”
በማለት የፍርሓት ጥሪ በማስተጋባት ለ27 አመት ሕዝብን ያሰቃዩበት የነበረውን ፋሺስታዊው የህወሓት ስርኣታቸው ችግር ውስጥ መግባቱን ሲያውቁ ዛሬ የሩዋንዳን አይነት የፍርሓት ፕሮፓጋንዳ ጥሪ በማድረግ የወያኔ አሽከሮች የትግሬ ሚሊሽያዎችን፤ወጣቶችን፤ነጋዴዎች፤የሲቪክ ማሕበሮች እና የትግራይ ፖለቲካ ድርጅቶች የማደራጀትና የማስታጠቅ ጥሪ በማስተላለፍ እንደ 1967 የትጥቅ ትግል እንዲጀመር ጥሪ አድርገዋል። ምስጢሩ ደግሞ አስቀድሜ እንደገለጽኩት በዶ/ር አብይ እየተመራ ያለው ዘገምተኛ የጥገና ለውጥ ቀስ እያለ ባንዳዎቹን እየተፈታተነ ቅዠት ውስጥ ስለከተታቸው አለቆቻቸው እና ተከታዮቻቸው በለውጡ ላይ የትጥቅ ጥሪ እንዲደረግ ያላቸው የመጨረሻው አማራጭ ዕድል እየፈተሹ ነው። ባለፈው ቃለ መጠይቄም ሆነ በጽሑፌ እንደገለጽኩት ለውጡ ያለ ምንም ደም ይሆናል የሚባለው ቅዠት መሆኑን እንድታውቁ ያለኝን ስጋት እገለጻለሁ (ሌላ ታምር ካልተከሰተ በቀር)።
በሚቀጥለው ክፍል ሁለት አብይ በፓርላማ ውስጥ ስለተናገራቸው ነጥቦች (*2) ዶ/ር አብይ ትግሬዎችና ወያኔ አንድ ኣይደሉም የሚለው (ቲ ፒ ኤል ኤፍ እና ትግሬዎች አንድ አይደሉም) (*3) ትግሬዎች በስርዓቱ ዘመን (ስርአቱ የሚለው ወያኔን ማለት ነው) አልተጠቀሙም፡ (*4)- የትግራይ ሕዝብ ልማትና ዲሞክራሲ ለማምጣት ነው የታገለው ብሎ አብይ ስለተናገራቸው ነጥቦች የተሳሰቱ ታሪካዊ እና ሰነዳዊ ድጋፍ የማይገኝለት ሃሳቡን በተቃውሞ ሃሳቤን እተነትናለሁ። ይህ ደግሞ ለበርካታ አመታት ወያኔን ከሚቃወሙት ፖለቲከኞች እና የነ አንዳርጋቸው ጽጌ “ትግሬዎች ከደርግ በባሰ የምጣኔ ሃብት ኑሮ እየኖሩ ናቸው” ብሎ ያለውን ዓይነቱ እና የአብይ “ትግሬዎች በውሃ ጥም እየተሰቃዩ ነው” ሙግት የማያዋጣ ከመሆኑ አልፎ ለ27 አመት ትግሬዎች ከማንኛቸውንም ጎሳ በታሪካችን ባልታየ ሁኔታ በመላው አገሪቱ ተንሰራፍተው ተጠቃሚዎች እንደነበሩ ሰነዶች አሉን። ይህ ክርክር ሰንቀጥል “በጸረ ትግሬነት” የሚመድቡን ገራገሮች አሁንም አሉ። ካልተሳሳትኩ አብይ በዚህ የወነጀለን ይመስለኛል።
ለኛ ትግሬዎች ፍቅር ማሳየት የሚመሰገን ቢሆንም ፖለቲካው ላይ ስንመጣ ግን እኔ እንደ ትግሬነቴ ሁኔታውን መካድ ከሞራልም ከፖለቲካም የሚያስጠይቅ ስለሆነ ክርክራችን ይቀጥላል። ጥቂቶች “ተጠቅመው ሊሆኑ ይችላሉ” የሚል ቋንቋ አብይ ብቻ ሳይሆን ከአብይ በፊት የነበሩ የትግራይ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችም ሲያመነዥኩበት የነበረው የማያዛልቅ “ቃል” ነው። አብይ የመደብ እንጂ የብሄር ቅራኔ አሁንም ኢትዮጵያ የለም” ሲልም ሽምጥጥ አድርጎ “አማራው ከማህበራዊ፤ከፖለቲካ ከምጣኔ ሓብቱ” በተቀረጸው ፕሮግራም የወያኔ ስርዓት ለ27 አመት አማረውን ምሁርና ገጠሬ ሆን ብሎ ሲያገልልና ሲያጎሳቁል፤ ሲአስር እና ዘር ሲያመክን የቆየ መሆኑን በመካድ “ወደ መደብ ጭቆና” አዙሮታል። እየተማመንን መሄዱ ፖለቲካው ስርዓት ይይዛል፤ሕግም’ሓቅም የክብር ቦታቸውን ይይዛሉ ማለት ነው።። ክፍል ሀለት ይቀጥላል፡-
ስለሆነም ትግራይ ኦን ላይን አንዲህ ይላል፦

(Establishment of National Movement of Amhara and its
danger for Ethiopia Tigrai Online, June 11, 2018)

ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment