የኢሳት እንግዳው ዮሐንስ ዘለቀ ማነው?
Editor’s
Note
The fellow who is the subject of the following topic written in Amharic
is one of the Israelite communities better known as Falasha/Bete Israel/ living
in USA. He is been the guest of the so called Ethiopian Satellite (ESAT) the
mouthpiece of Berhanu Negga, a TV station financially aided by foreign powers
through Ginbot 7 postured as Amhara (based on the following commentary).
As I have been saying all along, there are many elements who acted as
Ethiopians still fooling you big-time, but they do not believe they are
Ethiopian natives, they are wolfs in sheep’s’clothing. For the life of me, I
don’t understand the honest motive there is inviting to Ethiopians’ media as
guests those who denounce their “Ethiopiawinet race” and called themselves
native citizens of Israelite race; surprisingly still allowed to talk about
Ethiopia current politics.
I say, if you are not Ethiopians?! Stay out of it! Leave that for us and
leave us alone. Stay with your beautiful race called Israelite. Leave Ethiopia
alone as you already denounce your race.
We knew, After the change
of power took place in Ethiopia, the subverters took advantage of the 1991
“crisis” and the Imperialists power (Israei Mosad/US/CIA)moved in with a large
cargo plane and took the Felasha to Isralel with permission and collaboration
of the new mercenaries /native banda namely TPLF.
From 1977 on words new modern slave
trade flourished in Africa. Many Africans including Ethiopians started to be
recruited as a maid to Arabs and also Felashas traded for money and transferred
to Israel as Israelite native citizens.
If you want to read more of it… read my old commentary
Slave Trade in Tens of Thousands of Ethiopians Branded as “
Falasha” “Black Jews” Smuggled out of Ethiopia was the Direct Rape of Our Dignity Recorded in History Getachew Reda (Editor
Ethiopian Semay)
Now, let
us go to read
የኢሳት እንግዳው ዮሐንስ ዘለቀ ማነው?
የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ | ለመሆኑ የኢሳት እንግዳው ዮሐንስ
ዘለቀ ማነው? (ዴቭ ዳዊት)
እያንዳንዱ አማራ ይህን እንዲያነብ እና እነማን ናቸው ጠላቶችሁ እነማን ናቸው ታሪኩን ጥላሸት እሚቀቡት እሚለውን ሊገነዘብ ይገባል ።
Yohannes Zeleke is a man of many
hats” ይላል ዴቪድ ካግሰዌል የተባለው ሰው ኦክቶበር 24-2014 ትራቭልፐልስ ዳት ካም በተባለ ድረ ገጽ ላይ በጻፈው ጽሁፉ። አብሮ አደጎቹ እና በቅርበት በዋሽንግተን የሚያውቁት ደግሞ “ዮሐንስ ስጡ” ይሉታል። በተለምዶ ያለገደብ የሚዋሽ ሰው “ስጥ” ተብሎ ይጠራ የለ?!እኛ ደግሞ ዮሐንስ ብዙ የበግ ለምዶችን ደራርቦ የለበሰ ተኩላ ነው እንላለን፤ ብለንም አንቀርም በእውነት ካራ እያንዳንዱን ለምድ እየገፈፍን ተኩላነቱን እናሳያለን። ማርች 29-2017 ዓ.ም. ኢሳት የተባለው የቁጭ በሉዎች የወሬ ቋት ይህንን ግለሰብ ቃለ መጠይቅ አደረግሁ ብሎ በአማራነታችን ላይ አፉን እንዲያላቅቅ ካደረገው በኋላ “ለመሆኑ ዮሐንስ ዘለቀ ማነው?” የሚለውን መልስ ለማግኘት እንዲህ እና እንዲያ ስንል ቆይተን አማራዊ የሆነው ወገናችን እውነቱን ያውቅ ዘንድ ከነማስረጃው እነሆ ብለናል!መልካም ንባብ።
የ15 አመቱ አርኪዮሎጂስት
ዮሐንስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጁላይ 4 ቀን 1963 ዓ.ም. በጎንደር ተወለደ። ታድያ ትራቭል ፐልስ ከተባለ ድረ-ገፅ ጋር በ ኦክቶበር 24-2010 ዓ.ም. ባደረገው ቃለ ምልልስ በህይወቱ ጉልህ ከነበረው ክስተት አንዱ ሀገሪቱን የናጣት አብዮት ሲሆን በዚህም ወንድሙን፣አባቱን እና አያቱን በአብዮቱ እንደተነጠቀ ይገልፅ እና በሱ የደረሰው ግን የተለየ እንዳልሆነ ይልቁን አብዛኛው ሰው ከቤተሰቡ አንድ እና ሁለት ሰው እንዳጣ ይገልፃል። ድረ-ገፁ በ1981 ዓ.ም. አካባቢ ፕሬዝደንት ሬገን የአሜሪካንን በር ለኢትዮጵያኖች ክፍት እንዳደረጉ እና በተለይ ከጎንደር አካባቢ በጅምላ ወደ አሜሪካ እንደተሰደዱ አውስቶ ዮሐንስን ለምን ወደአሜሪካ አልመጣህም ሲለው እንዲህ በማለት ነበር የመለሰው ፡-
“I didn’t want to
leave my mother,” said Zeleke. “I had several chances to leave, but if you lose
someone from family due to the revolution, you were called counter
revolutionary, so you couldn’t leave. I had a chance to come to America for a
scholarship. I was working as an archaeologist with the ministry of culture
since 1978.”
ሲተረጎም
ይህን ይመስላል “እናቴን ትቼ መሄድ አልፈለኩም። ለመሄድ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩኝ፤ግን ከቤተሰብህ አንዱን በአብዮቱ ካጣህ ፀረ አብዮተኛ ተብለህ ትፈረጃለህ ስለዚህ መሄድ አትችልም። በስኮላርሺፕ ወደ አሜሪካ የመምጣት ዕድል ነበረኝ። ከ1978 ጀምሮ በባህል ሚንስቴር ውስጥ በአርኪዮሎጂስትነት
እሰራ ነበር።”
ከዚህች መልስ ብሎ ከተናገራት ውስጥ ሁለት ትልልቅ ውሸቶችን እናውጣ።
በ15 ዓመቱ በምን ተዓምር ነው አርኪዮሎጂስት ሆኖ ተመርቆ ፕሮፌሽናል ስራ በባህል ሚኒስቴር ውስጥ ሊሰራ የሚችለው?
“ከቤተሰብህ መካከል በአብዮቱ ሰው ከተገደለብህ መሰደድ አትችልም” ያለው ለመሆኑ ያ ሁሉ አሜሪካ የገባው የጎንደር አማራዊ ቤተሰቡ ያልተገደለበት ነበር ማለት ነው? ይሄ ትልቅ ውሸት ነው። እንዲያውም አብዛኛው የተሰደደው ቤተሰቡ የተገደለበት እና እሱም ሊገደል እየተፈለገ የነበረው ነው።
( ማስረጃ ይሆን ዘንድ ቃለ ምልልስ ያደረገበትን የድረ-ገፅ ማስፈንጠሪያ/Link/ ይመልከቱ፡-
http://www.travelpulse.com/…/meet-the-tour-operator-yohanne…)
የትምህርት ደረጃ
ከላይ የጠቀስነው ትራቭል ዳት ካም የተባለው ድረ-ገጽ ዘገባውን በመቀጠል እንዲህ ይላል “ምንም እንኳን ወደ አሜሪካ መሄድ ባይችልም ወደ ሶቭየት ህብረት ግን ለትምህርት ሄደ።” መቼ ተመረቀ?ምንስ አጠና? የሚለውን ደግሞ Strategy XXI የተባለው የአምባገነን ሀገራትን ገፅታ በአለም ፊት በመገንባት የህዝብ ግንኙነት እና የሎቢ ስራ በመስራት የሚተዳደረው ድርጅት ዮሐንስን በአማካሪነት ያቀፈ ሲሆን በድረ-ገፁ የዮሐንስን የትምህርት ደረጃ፣ መቼ እና የት እንዲሁም ምን ተማረ የሚለውን እንዲህ ይገልፀዋል፡- “Dr. Zeleke has a
B.A. in History (1992) and an M.A. in Archeology (1993) from the St. Petersburg State
University in Russia and a Ph.D. in Archeology (1997) from the Russian Academy
of Sciences”
ሲተረጎም
“ዶ/ር ዮሐንስ የባችለር ኦፍ አርት ዲግሪውን በታሪክ ትምህርት በ1992 ዓ.ም. በአርኪዮሎጀ የማስተር ዲግሪውን በ1993 ዓ.ም. ከራሻው ሴንት ፒተርስበርግ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪውን በአርኪዮሎጂ በ1997 ዓ.ም. ከራሽያ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ተመረቀ” ይለናል። እንግዲህ ዮሐንስ እንደ ኤዲ አሚን ዳዳ ለራሱ ረጃጅም ማዕረጎችን እየሰጠ በየድረ-ገፁ ቢለጥፍም እውነታው ደርግ በመውደቂያው ዋዜማ በኮታ ተዋፅኦ እና በኢሠፓ አባልነቱ ወደ ሶቭየት ህብረት ከላከው በኋላ በ29 ዓመቱ የመጀመሪያ ዲግሪውን በታሪክ ትምህርት በ1992 ዓ.ም. ያገኘ ሲሆን ሶቭየት ፈራርሳ በለውጡ ክፉኛ ከደቀቀችው ራሽያ ነው እንግዲህ እነዚያን ብራና በአምስት አመታት ሰብስቦ በአንድ ጊዜ ዶክተር የሚለውን ስያሜ ያገኘው።ከዚህ ባሻገር የአሜሪካኖቹ ጆርጅ ታውን እና በርክሌ ዩኒቨርሲቲዎች ከ1998-2003 ዓ.ም. የመስክ ጥናት እና ምርምር ሲያደርጉ ዮሐንስ ከ13 ዓመቱ ጀምሮ በግሉ የቱሪስት አስጎብኚ [Tour Guide] ሆኖ ይሰራ ስለነበር /ከ13 አመቱ ጀምሮ ከቤተሰቡ ወጥቶ በቱሪስት አስጎብኚነት ትናንሽ ልጆች ለፈረንጆች ስለ አካባቢው እያስተረጎሙ እና መንገድ እያሳዩ ገንዘብ እንደሚያገኙት ሁሉ እሱም ያንን እየሰራ ይተዳደር እንደነበር
https://blog.privatefly.com/…/interview-with-a-global-tour-…
መመልከት ልብ ይሏል/እና አካባቢውን ስለሚያውቅ በቡድኑ ውስጥ እንዲካተት ተደረገ። ይህንንም እንደአንድ ትልቅ ስኬት በመቁጠር በነዚህ ተቋማት ውስጥ የጥናት ቡድን አባል እና መምህር እንደነበር አድርጎም የራሱን ገፅታ ሲገነባ ይስተዋላል።
ፀረ-አማራው ዮሐንስ
ከላይ በጠቀስነው ትራቭል ዳት ካም በተባለው ድረ-ገጽ ላይ ዮሐንስ ጎንደር እንደተወለደ ቢናገርም ኤፕሪል 6-2017 በተላለፈው የኢሳት ቃለ ምልልስ ክፍል ሁለት ላይ /
\ ይመልከቱ/
ከ6ኛው ደቂቃ 4ኛው ሰከንድ ጀምሮ በክፍል አንድ ላይ ራሱ ፈጥሮ “ጎጃም ውስጥ ከኦሮሞ ያልተዋለደ ቡዳ ነው ይባላል” የምትለውን አባባሉን እንዲያብራራ የቁጭ በሉዎች አውራ የሆነው ጋዜጠኛ ሲጠይቀው በ6ኛው ደቂቃ 37ኛው ሰከንድ ላይ ዮሐንስ ራሱ አባቱ የጎጃም ቡሬ አካባቢ ሰው እንደሆነ እና እሱም የጎጃም አማራ እንደሆነ ይናገራል። እኛ ግን ይህቺን የለበሳትን የአማራዊነት ለምድ በማስረጃ ገፈን ይህ ግለሰብ አማራዊ እንዳይደለ ይልቁን በርካታ የወንጀል እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎችን በአማራ ህዝብ ላይ ያሰራጨ መሆኑን እንዲህ እናሳያለን።
“ኩላኑ” /Kulanu/ በመባል የሚጠራው የአይሁድ ድርጅት ተቀማጭነቱን በኑዮርክ ከተማ ያደረገ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በዋናነት በመላው ዓለም የተበታተኑ አይሁዳውያንን መርዳት፣ ስለ ጁዳይዝም እምነት ማስተማር እና በሂደትም ከሰፊው የአይሁድ ማህበረሰብ ማለትም እስራኤል ካሉት ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው። ይህ ድርጅት በተለያዩ ቀጣናዎች ተከፋፍሎ የሚሰራ ሲሆን ዮሐንስ ዘለቀም የኢትዮጵያ እና አካባቢው አስተባባሪ ከሆኑት ሁለት ግለሰቦች አንዱ ነው። ይህ ድርጅት ምንም ማስረጃ ባልቀረበበት እና ዮሐንስ የሚያቀርበውን አፈ ታሪክ እንዳለ በመቀበል ሄርየት ቦጋርድ በ2009 በፃፈው ፅሁፉ፡-
ሀ.
ቀደምት አማራዊ አባቶቻችን የመሰረቷትን የአዳዲ ማርያም ቤተክርስቲያንን ፈላሻዎች ለሲናጎግ /የአይሁድ
የእምነት ቤት/ እንደሰሯት በኋላም ክርስቲያኖች እንደወረሷቸው በማስመሰል በአማራዊው ላይ የታሪክ ዝርፊያ እንዲፈፀም ጉልህ ሚና ተጫውቷል።
ለ.
በመካከለኛው ዘመን የተገነቡ የጎንደር አቢያተ መንግስታትን “በአይሁዶች/ፈላሻዎች/ ነፃ ጉልበት የተገነቡ” በሚል ለ2700 ዓመታት ቤተ እስራኤላውያኑ እምነት፣ባህል
እና ትውፊታቸውን
ጠብቀው እንዲኖሩ
ያደረገውን እና በእንግዳ ተቀባይነት ጨዋ ስነ-ምግባሩ የሚታወቀውን አማራዊውን ታሪኩን በዚህ መልኩ እንዲቆሽሽ ዮሐንስ ብቸኛውና ዋነኛው ሰው ነው። ለግንዛቤ እንዲረዳ አይሁዳውያን ሀገር አልባ በሆኑበት ሁለት ሺህ አመታት ውስጥ በተለያዩ ሀገራት ተበታትነው የነበረ ሲሆን በየዘመኑ በእንግድነት ያስጠጓቸው ሀገራት ከሀገራቸው እንዲለቁ አባረዋቸዋል። ከግሪክ፣ከራሽያ፣ከኢንግላንድ፣በሰባተኛው ክፍለ-ዘመን-ከሳኡድ-አረቢያ፣ ከግብጽ፣ ከስፔን፣ ከፖርቱጋል፣ ከቱርክ፣ከጀርመን፣ከሞሮኮ፣ከአልጄሪያ ብቻ በየዘመኑ አይደለም ወግ ልማዳቸውን መጠበቅ ኑሯቸው እንኳ ነገ ምን ይመጣ ይሆን በሚል የዛፍ ላይ እንቅልፍ እንዲሆን ተደርጎ ነበር።ታድያ አማራዊው ብቻ ነው “እንግዲህ በቃን እንሄዳለን” እስካሉበት ዘመን ድረስ ባዕድነት ሳይሰማቸው እንዲኖሩ ያደረገው።
ሐ. ዮሐንስ ዘለቀ እና ቢጤዎቹ ተረቶቻቸውን ሲቀጥሉም የአማራውያንን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በነዮሐንስ ዘለቀ /ስጥ/ አያቶች በሆኑት በአይሁዶች እንደተሰራ እና ሀገሪቱንም ለ200 ዓመታት እንዳስተዳደሯት ይናገራል። ለመሆኑ ከመቼ ወዲህ ነው አይሁድ በሰራው ነገር ላይ የመስቀል ቅርፅ የሚያደርገው? ሲጀመር ላሊበላ ራሱ የመስቀል ቅርፅ ነው ያለው።ሲቀጥል በየግርግዳ
እና መስኮቱ ላይ ለቁጥር የሚያታክት መስቀል ነው ያለበት።ታድያ አይሁድ ከሰራው እንዴት የሚጠላውን እና የማያምንበትን መስቀል በየቦታው መቅረፅ ፈለገ?
ዮሐንስ በሚፈጥራቸው ተረቶች እና አንድም ማስረጃ ማቅረብ በማይችልበት እንዲሁ የጥላቻ ዘሩን አሰራጭቷል የአማራዊውን ታሪክ በመዝረፍም ያለበትን የትንሽነት በሽታ /Inferiority complex/ ለማስታገስ እየሞከረ ይገኛል። ዮሐንስ የካሉኑ የኢትዮጵያና አካባቢው አስተባባሪ እንደሆነ እና ሄርየት ቦጋርድ የፃፈውን ከዚህ መመልከት ይቻላል
ዮሐንስ በሚፈጥራቸው ተረቶች እና አንድም ማስረጃ ማቅረብ በማይችልበት እንዲሁ የጥላቻ ዘሩን አሰራጭቷል የአማራዊውን ታሪክ በመዝረፍም ያለበትን የትንሽነት በሽታ /Inferiority complex/ ለማስታገስ እየሞከረ ይገኛል። ዮሐንስ የካሉኑ የኢትዮጵያና አካባቢው አስተባባሪ እንደሆነ እና ሄርየት ቦጋርድ የፃፈውን ከዚህ መመልከት ይቻላል
እና
ዮሐንስ ፀረ-አማራ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ኦርቶዶክስም ነው!!!
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2003 የተቋቋመው እና በአህፅሮተ ቃል ቢና /BINA/ ወይም የሰሜን አሜሪካ የቤተ እስራኤል የባህል ማዕከል /The Beta Israel of
North America (BINA) Cultural Foundation, Inc./ ዋና ተልዕኮው የቤተ እስራኤል ወይም ፈላሻዎችን ታሪክ እና ባህል ማስተዋወቅ፣ በኢትዮጵያ በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚገኙ ፈላሻዎችን ማጠናከር፣ ወደ አሜሪካ የሚመጡ ፈላሻዎችን መርዳት እና የመሳሰሉት ሲሆን ይህ ተቋም በ2013 አስረኛ አመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር ዮሐንስ ዘለቀ “The Story of
Ethiopian Jews,” የተሰኘ ባለ አምስት ገፅ ግን ብዙ መርዞችን የያዘ ፅሁፍ አቅርቦ ነበር። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ፡-
ሀ. በገጽ 2 አንቀጽ1 ላይ አማራዊውን ቅማንት መጤ አይሁድ ነው ይለናል።የዚህ ሰው ነውረኝነት እና ድንቁርና የሚጀምረው ደግሞ “ምናልባት” ብሎ በመጀመር ታሪክን ሊፅፍ በመሞከሩና መከራከሪያ ብሎ ያቀረበው ፌዝ ነው። ለማንኛውም እንዲህ ነበር ያለው
“Perhaps the earliest Hebraic people came to
the land of Ethiopia during the time of the prolonged drought and famine in Canaan at the time
of Abraham. These are ancestors of the Qemant, who worship the Lord in the same
manner as Abraham did.”
ሲተረጎምም
“ምናልባት ቀደምት
የዕብራውያን/አይሁድ/ ህዝቦች
ወደ ኢትዮጵያ የመጡት
በአብረሃም ዘመን
በከነዓን ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የድርቅ እና የረሃብ ወቅት
ነው።እነዚህ ሰዎች
የቀደሙ የቅማንት አባቶች
ሲሆኑ አምልኳቸውም አብረሃም
አምላኩን እንደሚያመልክበት ያለ ሥርዓት ነው።”
እስኪ በዚህ ሎጂክ እኛም እናስብ እና እንዲህ እንበል ከዚያ ያስኬዳል ወይስ አያስኬድም የሚለውን እንይ።
ምሳሌ ነው
“ምናልባት ቀደምት የቁሬሽ /መካ ይኖሩ የነበሩ እና እስልምናን በመጀመሪያው የተቀበሉ የነብዩ መሃመድ ጎሳዎች ናቸው/ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በነብዩ መሀመድ ጊዜ በተከሰተው የሙስሊሞች መሳደድ ወቅት ነው።እነዚህ ሰዎች የቀደሙ የወሎ ሙስሊሞች አባቶች ሲሆኑ አምልኳቸው ነብዩ መሃመድ አምላካቸውን እንደሚያመልኩ ያለ ሥርዓት ነው” ብንል ይሄ እውነት ነው?አይደለም!!!
ምክንያቱም የአምልኮ መመሳሰል የዘር አንድነትን አያሳይም።ጣና ሀይቅ ላይ ካሉት ገዳማት መካከል ናርጋ ስላሴ በሚባለው ገዳም በኦሪት እንደተጠቀሰው የቀደሙ አማራውያን የኦሪቱን መስዋዕት የሚያቀርቡበት አለት እና ንዋየ ቅድሳት ዛሬም ድረስ አለ። ታዲያ አማራ አይሁዳዊ ነው?
አምልኮ እኮ የምትቀበለው እንጂ በደም የሚተላለፍ አይደለም። ደግሞስ “ምናልባት” ብሎ ጀምሮ እርግጠኛ ሆኖ ድምዳሜ ላይ ይደረሳል እንዴ? ደግሞም ያልተገነዘበው ነገር ቅማንት አይሁድ ከሆነ መጤ እንግዳ ነው ማለት ነው።እንግዳን ደግሞ አንተ ካልፈለግከው በማንኛውም ሰዓት ልታባርረው ትችላለህ ማለት ነው።
ለ.
ሌላው በዚሁ በገፅ ሁለት የመጨረሻው አንቀፅ ላይ እንዲህ በማለት ይፅፋል “The history of
Ethiopian Jews has never been told in a way that is based on archaeological and
historical facts. Most writers have recognized the fact that Ethiopian Jews
were the founders of the early Ethiopian state and the Church of Ethiopia. But they have been denied credit for
their contributions to the history and civilization of Ethiopia and world
Jewry.”
ሲተረጎምም
“የኢትዮጵያ
አይሁዶች ታሪክ በአርኪዮሎጂያዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች ላይ ተመስርቶ ተነግሮ አያውቅም። በርካታ ፀሐፍት የኢትዮጵያ አይሁዶች የኢትዮጵያ የመንግስት ስርዓትንና ቤተክርስቲያንን መስራቾች ናቸው የሚለውን እውቅና ይሰጡታል። ነገር ግን ለኢትዮጵያ ታሪክ እና ስልጣኔ እንዲሁም ለአጠቃላዩ የአይሁድ ማህበረሰብ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ተክዷል።” ለዚህ ታሪካዊ ዝርፊያ ጉንጭ አልፋ ክርክር ማድረግ ባያስፈልግም አንድ ነገር ብቻ ብለን ማለፍ እንፈልጋለን። ሲጀመር የኢትዮጵያ አይሁዶች እንደማንኛውም አይሁድ ክርስቲያን አይደሉም።ታድያ በምን ስሌት ነው የቤተ ክርስቲያኗ መስራች የሚሆኑት? ሲቀጥል መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው በ34 ዓ.ም. ማለትም ክርስቶስ ወደ ሰማይ ባረገ በመጀመሪያው ዓመት በፊልጶስ እጅ የተጠመቀው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እንጂ ሌላ አልነበረም።ያ ሰው ደግሞ አማራዊ እንደነበር እኛም ጠላቶቻችንም እኩል የምናውቀው ነው። በእርግጥ ዮዲት ጉዲት ብዙ ቤተክርስቲያናትን አቃጥላለች። ይህም እንደ አስተዋፅኦ ይቆጠር ካለ ማለት ነው።
ሐ. በመቀጠል በገፅ 2 የመጨረሻው አንቀጽ እና በገፅ 3 የመጨረሻው አንቀጽ ላይ እንዲህ ይላል፡-
“In the
past, the history of Ethiopian Jews was told by different groups of people
including: (a)……(b) the Ethiopian Orthodox Church, which sought to annihilate
and demonize the Ethiopian Jewish population as the Antichrist”
ሲተረጎምም
“ባለፉት ጊዜያት የኢትዮጵያ አይሁዶች ታሪክ በተለያዩ አካላት ይነገር ነበር ከነዚህም መካከል :-(a)……(b)የኢትዮጵያ አይሁዶችን ፀረ-ክርስቶስ ናቸው በማለት የምታሰየጥናቸው እና እንዲደመሰሱ የምትፈልገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንዷ ናት።”
አማራዊ ወገናችን ሆይ! እንግዲህ በቅዳሴ ፀሎቷ በየዕለቱ “በስደት እና በምርኮ ያሉትን አንተ /ፈጣሪ/ አስባቸው” እያለች የምትፀልየውን፣ ምዕመኖቿ ማንም ቢሰደድ በእንግድነት እንዲሁ እንዲቀበል ፈሪሃ እግዚአብሔርን ያስተማረችውን፣ዮዲት ፈላሻዋ ለ40 ዓመታት ስታሳድዳት እና ስታቃጥላት ድርሳናትና ንዋየ ቅድሳቶቿን ስታወድም ቀን ጠብቃ ልበቀል ያላለችውን ለሁሉም በእኩል የምትፀልየውን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ነው እንግዲህ ዮሐንስ በተረቱ የሚያብጠለጥላት።
መ. በገፅ 4 የመጨረሻው አንቀጽ ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል
“Due to
the nature of church doctrine and its policy of forced conversion, the silent Islamic
population was forced to rebel against Emperor Lebne Dengel.”
ሲተረጎምም “በቤተክርስቲያኗ የዶግማ ባህርይ እና አስገድዶ ሃይማኖትን የማስለወጥ ፖሊሲ ምክንያት በዝምታ ይገዛ የነበረው የሙስሊም ማህበረሰብ በአፄ ልብነ ድንግል ላይ እንዲያምጽ ተገደደ።”
ሲጀመር የቤተክርስቲያን ዶግማ በጊዜ መርዘም እና ማጠር አልያም በሁኔታዎች መቀያየር የሚለወጥ አይደለም።ታድያ የቤተክርስቲያን የትኛው ዶግማ እና ምን ላይ የተፃፈው ነው ሃይማኖትን በግድ እንዲቀየር የሚያዘው እና ነው እንደዚህ ብሎ የሚፅፈው?ለምሳሌ የትግሬው ንጉስ ዮሐንስ ሃይማኖትን እንደሽፋን በመጠቀም የወሎ አማራውያንን በግፍ ጨፍጭፏል ግን ያ የቤተክርስቲያን አስተምህሮም
ዶግማም አልነበረም።ታድያ
ጭፍን ጥላቻ ካልሆነ እንዴት ዮሐንስ ዘለቀ ደፍሮ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ በሌለ ነገር ይኮንናል?
የዮሐንስ ዘለቀ ስር የሰደደ የኦርቶዶክስ ጥላቻ እና በቴዎድሮስ ታሪክ መቆመር እንደሚታወቀው በኢሳት አይዞህ ባይነት ዮሐንስ ዘለቀ ለከት
የለሽ ንግግሩን
የጀመረው በክፍል
አንድ በ
ማርች 29-2017 ነው። እናም በዚህ ፕሮግራም 52ኛው ደቂቃ ከ 40ኛው ሰከንድ ጀምሮ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ሲያወራ
“በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ ልጅ ካሳ ተነስቶ ቴዎድሮስ ነኝ ብሎ ነገሰ እናም ሀገሪቱን በደም አዋዥቃት፤ አሁን የኔን አያት ብትጣይቀው ሥ… ያ እብድ ነው የሚልህ ……….ድራስቲክ የሆነ የመንግስት ለውጥ እንደዚህ አይነት ክራይስስ ያስከትላል።”
በዚህ ንግግር መሰረት ቴዎድሮስ ፈጣን የመንግስት ለውጥ አመጣለሁ በሚል “እብደት” ሀገሪቱን
በደም አዋዥቋት
ሲል በ2013 ለ ቢና አስረኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ባቀረበው
“The Story of Ethiopian
Jews,” በተሰኘው ጽሁፉ ገፅ 5 አንቀጽ 1 ላይ እንዲህ ይላል
“Once again, in 1847, a Jewish
emperor, Tewodros II, appeared and begun to reunite and modernize Ethiopia. The
Ethiopian Orthodox Church, especially the Egyptian Patriarch, would not
recognize Tewodros as the legitimate Emperor of Ethiopia. First of all,
Tewodros was born to a Jewish family in Quara. Secondly, he sought to separate
church and state. Third, Tewodros wanted to introduce technological change in
Ethiopia. The church was very backward in its thinking and could not reconcile
technological changes with religious faith. It saw Tewodros’s attempt at
introducing technology as an act of blasphemy. Fourth, Tewodros wanted to
educate the masses. The church resisted this because it saw education of the
masses as a threat against church doctrines and its control of the populace.
There were many church-instigated uprisings and bloodshed in several parts of
the kingdom”
ሲተረጎም
“በ1847 ቴዎድሮስ የሚባል አይሁዳዊ ንጉስ ኢትዮጵያን ሊያዘምን እና አንድ ሊያደርግ ተነሳ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተለይ የግብጹ ጳጳስ የቴዎድሮስን ንግስና እውቅና መስጠት አልፈለጉም። ምክንያቱም በመጀመሪያ ቴዎድሮስ የተገኘው ቋራ ከሚኖሩ የአይሁድ ቤተሰብ ነው፤ሁለተኛ ቤተክርስቲያንን ከመንግስት
መለየት ይፈልግ ነበር፤ ሶስተኛ ቴዎድሮስ ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ይፈልግ ነበር ግን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአስተሳሰቧ በጣም ኋላ ቀር እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከእምነቱ ጋር ማጣጣም የማትችል በመሆኑ ቴዎድሮስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማስተዋወቅ ያደረገውን ጥረት ቤተክርስቲያኗ እንደ ክሂዶተ-እግዚአብሔር መመልከቷ፤ አራተኛ ቴዎድሮስ ብዙሃኑን ለማስተማር ፍላጎት ማሳየቱ እና ቤተክርስቲያኗ ይህንን ለዶግማዋ እንደ አንድ አደጋ በመውሰዷ እና በህዝቡ ላይ የነበራትን ስልጣን አደጋ ውስጥ ይከታል ከሚል ስጋት ነበር። በዚህም ቤተክርስቲያኗ የቀሰቀሰችው አመጽ እና ደም መፋሰስ በተለያዩ ግዛቶች ተፈጽሟል።”
ከላይ ኢሳት ለሚባለው በእርጥባን ለሚተዳደረው የቁጭ በሉዎች የወሬ ቋት ቴዎድሮስ
ለውጥን በፍጥነት
አመጣለሁ ብለው ሀገሪቱን በደም አጠቧት ይል እና ለአይሁዶቹ ደግሞ አማራዊውን ንጉስ የአይሁድነት ካባ ደርቦለት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቴዎድሮስ አይሁዳዊ ስለሆነ ገና ከመጀመሪያው ልትቀበለው አልወደደችም ይላል።
በሌላ በኩል ቋንቋን ከነ ሰዋሰው፣ዜማን ከነአገባቡ፣ቅኔን
ከነአቋቋሙ፣ስነ ፈለክን ከቀን አቆጣጠር፣መጽሐፈ ሄኖክን ከመጽሐፈ ጥበብ፣ ኦሪትን ከብሉይ አስማምታ አይሁዱንም ሙስሊሙንም ቤቴ ቤታችሁ ብላ የኖረችውን ያቺን ስንዱ እመቤት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነው እንግዲህ ማንም አያየኝም በሚል ወገኖቼ ለሚላቸው አይሁዶች በዚህ መልኩ የሚያማት። ለማንኛውም ዮሐንስ በቢና (BINA) ድረ ገጽ ላይ የጻፈውን ሙሉ ጽሁፍ ለማስረጃነት ታዩት ዘንድ በሚከተለው አድራሻ ታገኙታላችሁ;
http://www.binacf.org…/The%20Story%20of%20the%20Ethiopian%…
ለማንኛውም ለአማራዊ ወገናችን እንዲህ ልንልህ እንወዳለን። ማንም ተነስቶ “እኔም አማራ ነኝ ግን…..” ብሎ አማራን እና አማራዊ የሆነውን ባህልህን እና እሴትህን የሚሰድብ እና የሚያንቋሽሽ ከሆነ እሱ አማራ አይደለም።ተጠራጠር!!!ተጠራጥረህም
ዝም አትበል እውነቱን ፈልግ ያን ጊዜ ያጠለቃት ለምድ ስትወልቅ ተኩላነቱን ትደርስበታለህ።
የመጨረሻው ለምድ
ሲገፈፍ- ዮሐንስ የወያኔ አማካሪ ነው!!!
አይጋ ፎረም የተባለው የወያኔ ድረ ገፅ በዲሴምበር 2014 ባወጣው ዘገባ መሰረት የኔሽናል ቱር አሶሴሽን አባል የሆኑ ጋዜጠኞች፣አስጎብኚዎች
እና በዚህ ሙያ የተሰማሩ ሰዎች ከአሜሪካ ተነስተው ለአስር ቀናት የሚቆይ ጉብኝት እንዳደረጉ እና የኢየሩሳሌም የጉዞ እና የትራንስፖርት ድርጅት ባለቤት የሆነው ዮሐንስ ዘለቀ አብሮ እንደነበር ያትታል።
http://aigaforum.com/…/Ethiopia-Tourism-NTA-Magazine-Dec201…
ነገር ግን አይጋ ሊነግረን ያልወደደውን አንድ ሀቅ ራሱ ዮሐንስ በቅርብ ባቋቋመው እና አፍሪካን ሌጀንድ ቱርስ /african legend tours/በሚል የድርጅቱ ድረ ገፅ ላይ
https://www.africanlegendtours.com/other-services
እንዳስቀመጠው በጄንዋሪ
24-2012 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ የወያኔ ትግሬ አምባሳደር የነበረው ግርማ ብሩ በኤምባሲው የኢትዮጵያ የቱሪዝም የአማካሪዎችን ቦርድ የሰበሰበ ሲሆን ከነዚህ የአማካሪ ቦርድ አባላት መካከል ዮሐንስ ዘለቀ አንዱ ሲሆን ፌብሯሪ 14
2012 ዓ.ም ይፋ የተደረገውን የስራ ዕቅድንም
/Action Plan / በዋናነት ያዘጋጀውም እሱው
ነበር።
በስራ ዕቅዱ ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው በአሜሪካን
ሀገር የሀገሪቱን
ገፅታ መገንባት፣
አሜሪካን ከሚገኙ ልክ የሱ ድርጅት አይነት አስጎብኚ ድርጅቶች እና ዛሬ ላይ በትግሬዎች በበላይነት በተያዙ ኢትዮጵያ ባሉ አስጎብኚ ድርጅቶች መካከል የቢዝነስ ትስስሮችን መፍጠር እና መሰል ተግባራት ላይ ያጠነጥናል።
በዚህም መሰረት በኤፕሪል 9-2013
ዓ.ም ኤምባሲው ባዘጋጀው የቢዝነስ ትውውቅ ላይ ከኢትዮጵያ የተጋበዙ 14 የትግሬ ድርጅቶች ተሳታፊ ሲሆኑ ትግራይ ኦንላይ የተባለው የትግሬ ድረ-ገፅ
ሁኔታውን በዚህ መልኩ ነበር የገለፀው
“A “Business to Business Meeting” designed at
bolstering Ethiopian Tourism Market in the US and engage American Tour Operators with their Ethiopian
counter-parts was held at the premises of the Ethiopian Embassy here today, a
press release obtained from the Embassy stated. The event is seen as an ideal
venue for creating the necessary enabling conducive environment for networking
of enterprises deployed in the hospitality industries of the two countries,
according to the press release.
በሌላ በኩል አፍሪካን ቱር አሶሴሽን ስለዚሁ ስብሰባ በድረ-ገጹ [http://www.africa-ata.org/texas2.htm] ግርማ ብሩ፣ የባህል ሚንስቴር ምንስትሯ ታደለች ዳነቾ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ /ከ2012 ጀምሮ ደግሞ የቱሪዝም አማካሪዎች ቦርድ አባል የሆነው/ ዮሐንስ ዘለቀ ንግግር አቅራቢዎች እንደነበሩ ያትታል።
በሌላም በኩል በሴፕቴምበር 2016 በአሜሪካ የወያኔ ኤምባሲ በድረ ገጹ
http://www.ethiopianembassy.org…/NewsletterSeptember2016.p…
ባወጣው ዘገባ መሰረት በኦገስት 30-2016 የወያኔ ትግሬ ኤምባሲ ገጽታውን ለመገንባት በማሰብ የሀርቫርድ እና የማሳቹሴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ክለብ አባላትን በመሰብሰብ ስለሀገሪቱ ሲደሰኩሩ ከነበሩት እና ሀገሪቱ “ተለውጣለች፤መጥታችሁ ጎብኙን” እያለ ሲያላዝን የነበረው ዮሐንስ ዘለቀ አንዱ ነው። አዎ ዮሐንስ ስጥ የወያኔ ትግሬው አማካሪ፣ ሁለት ልጆች የወለደችለት ሴት በዚህ ውሸታም ባህርይው ምክንያት በአይኔ ላይህ አልፈልግም ብላ ወደ ሚንሶታ ጥላው የሄደችው፣ ትናንት በዌል ፌር ይኖርበት በነበረበት ቤት ዛሬም በዚያ የሚኖረው ዮሐንስ ዘለቀ። እነሆ ታዩት ዘንድ የኢሳት ታላቅ ወንድም የሆነው የወያኔው ኢቢሲ ወይም የድሮው ኢቲቪ የኦገስት 30-2016ቱን የነዮሐንስን ንግግር
ከታች በምታዩት
ቪድዮ ላይ በምታዩት መልኩ ነበር ያቀረበው።
በመጨረሻም ለአማራዊው አንድ ነገር ልንል ወደድን። ደግመን ደጋግመን በዘመናት እንዳየነው ከእኛ ውጪ ለእኛ ማንም ሊሆነን አልያም ሊታደገን እንደማይችል የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ብቻ በቂ ምስክር ነው። ስለሆነም ለአማራ ህዝብ ትግል እና የመጨረሻ ግባችን ለሆነው ግዮናዊውን አባት ሀገር ለመመስረት የሚዲያ ሚና የማይተካ እና ለነገ የማይባል ነው።
ይህንን በልቦናህ ካኖርክ ዘንድ የራሳችንን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ በንቃት እንድትሳተፍ፣ በማንነትህ እና በዘርህ ላይ ጥላቻን በሚዘሩ ላይ ጀርባህን በመስጠት ባንተው ኪስ በሁለት እግራቸው እንዳቆምካቸው ሁሉ ኪስህን በማጥበቅ እና የሸፍጥ ሴራቸውን በማጋለጥ እንድታንበረክካቸው
ልናሳስብህ እንወዳለን።
No comments:
Post a Comment