Thursday, July 12, 2012

“አለባብሰው ቢያርሱ ……….”


I have two topics for you all. One is for the Diaspora Ethiopian Lawyers

This is Home Work for Ethiopian Lawyers living in the Diaspora. I want all the so called Ethiopian Lawyers to do something about these Animals in Saudi Arabia who are still in their barbaric stage. Ask us financial contribution to sue the Saudi beasts in the world court. Send an investigation now!!!!!!!!! At least try

(1) !!!!!!!!! Meles is killing our people inside and outside Ethiopia intentionally to destroy Ethiopia for ever its pride.

I like all my readers to see the following video how the Saudi Arab Human Animals in Jedha collaborated with the mercenary Meles Zenawi of Ethiopia caught on Camera abusing Ethiopian Woman. How long are these beasts who look like human, but worst beasts than the God created Animals of the jungle on this civilized world continue to abuse Ethiopian Women? How long is Meles Zenawi selling Ethiopian Women to his Arab masters for such sad situation? Let the Arabs remind their memory when that time comes of accounting. It is time a change to come to Saudi Arabia as the rest of the Arab world. It should have come first before any of them. These are 16 police officers of Saudi calling themselves Men struggling to chock one poor woman's neck as if she is a Tiger or a lion that intimidates these so called themselves MEN. There is time for all said King Solomon!!!!!!! Editor Ethiopian Semay.

ከአዘጋጁ ማስታወሻ፦

ከዚህ በታች የሚቀርበው ጽሑፍ “አብረሃ በላይ” በሚያዘጋጀው  “ኢትዮሚዲያ” ተብሎ በሚታወቀው የነ ብርሃኑ ነጋ እና መሰል ግለሰዎች እና ቡድኖች የሚለቀልቁበት እና የሚለቃለቁበት ድረገጽ ላይ በሕዝብ እንዳይነበብ “የታገደ” ለኢሳቱ ጋዜጠኛ ለፋሲል የኔዓለም ከእውቁ ገጣሚና ጋዜጠኛ “ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን” የተሰጠ መልስ ነው። መልካም ንባብ። (ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
Fasil YeneAlem of ESAT

 “አለባብሰው ቢያርሱ ……….”
ከወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

                 አሀዱ

ዕለተ ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2004 ዓም አመሻሹ ላይ ሞባይሌ ተንጫረረች፡፡አንስቼ ወደ ጆሮዬ አስጠጋኋት፡፡ ጓደኛዬ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰለሞን ነው፡፡

"ሳይቸግርህ ሰዎቹን ካክተህ...." ያለ መሰለኝ፡፡ "ምን አልከኝ?" አልኩት የተናገረ ማረጋገጥ "የቀድሞው አለቃህ ፋሲል የኔዓለም በቃሊቲ ምስጢሮች የተነሳ የፃፈውን ኢንተርኔት ላይ ተመልከት" አለኝ፡፡

በማግስቱ ማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓም ከጠዋቱ 4 ሰአት አካባቢ ሌላው ጓደኛዬ አለማየሁ ባዘዘው "ፋሲል ወንዱ ልክ ልኬን" እንደነገረኝ ደግሞ አበሰረኝ፡፡ ወዲያው ወደኢንተርኔት ቤት ጎራ አልኩ፡፡ እናም የፌስ ቡክ ገፄን ከፈትኩት፡፡ ሁለት መልዕክቶች አሉኝ፡፡ በየተራ ከፈትኳቸው፡፡ አንደኛው ቅዱስ ያሬድ ኤፍሬም የተባለ ሰው የላከልኝ ነው፡፡ ሰባት ጊዜ ወድቆ የተነሳውን "ቅዱስ ያሬድ" እያሰብኩ መጠቆሚያ ቀስቱን ወደፖስታው መራሁት፡፡

የፋሲል የኔዓለም ፅሁፍ ከፊቴ ተዘረጋ፡፡ አነበብኩት፡፡ ሁለት ዓይነት ሥሜት ተሰማኝ አንድም ደስ አለኝ፡፡ መፅሐፌ በዓለም ዙሪያ እየተነበበ ነውና፡፡ አንድም አዘንኩ፡፡ ፋሲል የኔዓለም በእያንዳንዱ የፅሁፉ መስመር ውስጥ ሲንጨረጨር ታየኝከልብ አዘንኩለት!!

                     ክልዔቱ

እያዘንኩ ሁለተኛውን መልዕክቴን ለማየት መጠቆሚያ ቀስቱን ወደ ፌስ-ቡኬ ፖስታ ሰደድኩት፡፡ የፖስታው መሸፈኛ ተነሳልኝ፡፡ የጋዜጠኛ ተስፋዬ /አብ ፅሁፍ በኮምፒውተሩ ስክሪን ላይ ፈሰሰ፡፡

ተስፋዬ "የቃሊቲ ምስጢሮች" መፅሐፍ ውስጥ ካነበባቸው ታሪኮች መሀል በዝዋይ ማረሚያ ቤት 14 ዓመት ሙሉ የታሰረውና የመፈቻውን ቀን ናፍቀውን ሁሴን (የኦነግ ወታደር የነበረ) ታሪክ ነቅሶ አውጥቷል፡፡ እናም እጥር ምጥን ባለው ፅሁፉ እንዲህ ብሎ አሳርጓል፡-

"...እነሆ እኔም ተክዤአለሁ፡፡ ሁሴን በኦነግነት ተይዞ የታሰረው ሌንጮ ለታ እና ዲማ ነገዎ መራ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ ልክ እንደሁሴን በአስር ሺህዎች በወያኔ ማጎሪያ ተወርውረዋል፡፡ የት እንደደረሱ ማይታወቅ የተረሱ እስረኞች ቁጥር ዳርቻ የለውም ይህንን እያሰብኩ የወሰንሰገድን መፅሐፍ አጥፌ ተከዝኩ፡፡...."

እኔም ልክ እንደተስፋዬ ተክዤ የፌስቡክ ገፄን ከረቸምኩት፡፡ ሆኖም የተከዝኩትና ያዘንኩት ለእኔ አልነበረም፡፡ ለቀድሞው "አለቃዬ" የእስር ቤት ጓደኛዬ የአሁኑ የኢሳት ፊታውራሪ ለሆነው ፋሲል የኔዓለም ነው

                     ሠለስቱ

አንጋፋው ምፃ ተሾመ ምትኩ "አስራት" ሚል ርዕስ ባሳተመው ካሴት ሁሌም ሳደምጠው ሚመስጠኝ አንድ ዘፈን አለ፡፡ "እሹሩሩ ማሞ" የሚል፡፡

".....እሹሩሩ ማሞ እሹሩ ማሙዬ

ዘመን አሳለፍኩኝ አንተን ተሸክሜ አንተን አንጠልጥዬ..."

ይላል ምፃዊው፡፡ ልጁን እያባበለ ወይም እያጫወተ አይመስለኝም፡፡ ሚያድግና ከትከሻ ማይወርድ ልጅ በመሆኑ እየተማረረ እንጂ፡፡ እኔም እንዲሁ እሹሩሩ ማለ የምችል አይመስለኝም እነፋሲል የኔዓለም ግን አሁንም እሹሩሩን ይሻሉ መሰለኝ ማለቃቀስ ጀምረዋል

እንደመሰለኝ ለፋሲል ማለቃቀስ ምክንያት ሆነ የኔው መፅሐፍ ነው አንድ አንባቢ መፅሐፌን አንብበው ግምማዊ ፅሁፋቸውን ኢትዮ-ሚዲ እና ኢኤም ኤፍ በተባሉ ድረገፆች አውጥተዋል፡፡ ሆኖም ገምጋሚው ስማቸውን አልገለፁም፡፡ ፋሲል የኔዓለም "ጎንትለውኛል" ባይ ነው በእሱ አባባል "ስብዕናውን ማጨቅየት" ነው በግምገ ሰበብ ብዕራቸውን ያነሱት፡፡ ፋሲል ለእኚህ "ሥም የለሽና ሥም አጥፊ" ገምጋሚ ምላሽ ባይሰጥ ደስ እንደሚለው፣ ግን ደግሞ እንዳልስቻለው በመጀመሪያው አንቀፅ ያትታል

"...በህይወቴ ሙሉ ደስ ሳይለኝ ከፃፍኳቸው ፅሁፎች መሃል አንዱ ይህ ነው፡፡.." ብሎ ይቀጥላል፡፡ እናም ሶስት ገፅ ሙሉ የመልስ ምት ያለውን ፅሁፍ ያስነብበናል፡፡

የእስር ቤት ጓደኛዬና የቀድሞ "አለቃዬ" ችግርም ከዚሁ ከመንደርደሪያው አንቀፅ ይጀምራል፡፡ ደስ ሳይለው ሚፅ ሰው፣ ደሰታውን ሚነጠቀው በራሱ ዕጅ ነውና፡፡ ስለዚህም አዘንኩለት፡፡ ደስ ያለውን ትቶ ደስ ያለውን ማድረጉ፡፡ ነው? ቢሉ መነውን ያላወቀ መድረሻውን እንደማያውቅ ሳይታለም የተፈታ ሐቅ ነውና፡፡ የፋሲልም መል ፅሁፍ እንደዚያው ነው። ዒላማውን የሳተ "ለስም የለሹ" መፅሐፍ ገምጋሚ መልስ ብሎ ከቸከቸው 3 ገፅ ፅሁፍ ሚሱ ነጣጠረው በእኔ "የቃሊቲ ምስጢሮች" ደራሲ ላይ ነውና። ስለዚህ የፋሲል መል ምት ገና መነሻው ነው የከሸፈው ዓላማ ሲከሽፍ ደግሞ ያሳዝናል ቢሆንም......

አርባዕቱ

የሆኖ ሆና ፋሰል የኔዓለም ለስም አልባው ገምጋሚ በሰጠው ምላሽ ማለ የፈለገው “በማተ ልዳኝ!"ነው በማተቤ ዳኙኝ እንጂ ካለሥም ስም አትስጡኝ ነው። እንዲያ ከሆነ ዘንዳ ጥያቄው አንድና አንድ ነው ሚሆነው። ማነው ባለማተብ!? ማነው ማተቡን የበጠሰ!? ማነ የተበጠሰ ናተቡኑን ለመቀጠል ባህር ማዶ የተሻገረ!? ማነ ከነማተቡ ያለ!? መል ከባድ አይደለም ቀላልም አይደለም ሁሉም የማተቡን ልክ ሚመጥነው በአንገቱ ልክ ነውና። ቢሆንም ያገሬ ሰው “አንገት የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነው” ሚለው እንዲሁ ለይምሰል አይደለም አንገት ለማተብም አዙሮ ማየትም ይጠቅማል ነው እናም እስ የ”አፄ ፋሲል”ን መልስ ተብዬ ፅሁፍ ዞር ዞር ብለን እንፈትሸው በየተራ፡-

"....የቃሊቲ ባልደረባዬ የነበረው ወሰንሰገድ /ኪዳን መፅሐፍ ማሳተሙ እጅጉን ተደሰቻለሁ ወሰን ብዙ ተሰቃይቷልአብዛኛውን ጊዜ እሱ ባልፃፋቸው ፅሁፎች /በዋና አዘጋጅነት ስሙ ስለተቀመጠ/ ፍርድ ቤት መላልሷል፡፡… ይላል ፋሲል ስለእኔ

ይገርማል! ፋሲል ማለ የፈለገው ጋዜጠኛ አይደለም፤ አይፅፍም፤ ሌሎች በፃፉት ነው ሲከሰስ የኖረው ነው እንደእውነቱ ከሆነ አንድ ጋዜጣ ከዳር እስከዳር ብቻ (በዋናአዘጋጁ) እንደማይለቀለቅ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። በጋዜጣው ለወጡ ፅሁሮች ደግሞ ሙሉ ኃላፊነቱን ሚወስደው ዋና አዘጋጁ ነው። እኔ ለበርካታ ዓመታት ይህንን ኃላፊነት በፅናትና በቁርጠኝነት ተወጥቻለሁ ኃላፊነት ከበደኝ ብዬ አላፈገፈግኩም አልሸሸሁም የፈረንጅን እርጥባን ለመቃረም ባህር ማዶ አልተሻገርኩም ግንባሬን አላጠፍኩም። ለፋሲል የኔዓለም ምስጢር የሆነበት ታዲያ ምኑ ነው!? ቀድሞ ነገር ፋሲል ይህንን ማለ ምን የሞራ ብቃት አለው!?  መቼ ወደነፃው ፕሬስ መጥቶ፣ መቼ ጋዜጠኛ ሆኖ ነው!?  "”መቼ መጣሽ ሙሽራ መቼ ቀነጠስሽ ሽምብራ” ሚባለው እንዲህ ያለ ነገር ሲገጥም መሰለኝ፡፡ ደርሶ ጀግና መምሰል፣ እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ ማለት ትርፉ ዘበት ነው። ጎበዝ ሰው ይታዘባል!!

                   አምስቱ

…"...ወሰንን በሥራ ዓለም ብዙ አላውቀውም። አዲስ ዜና ከሁለት ወር በላይ የሰራ አይመስለኝም ከአራት ቀናት የበለጠ ቢሮ ውስጥ ተገናኝተን የምናውቅ አይመስለኝም…ብዙ ጋዜጠኞቻችንን የሚያዘናጋብን የ‹ጀበና› ቤት ደንበኛ መሆኑም ብዙ እንዳላውቀው አድርጎኛል፡፡…” ይላይ ፋሲል፡፡

አባባሉ ሞላ ጎደል ውነ አለው ጭቦ ይጎላበታል እንጂ፡፡ እርግጥ ነው አዲስ ዜናን ስንሰራ ብዙ አንተዋዋቅም፡፡ ልንተዋወቅም የምንችልበት ሁኔታ አልነበረም እሱ ከዶ/ ብርሃኑ አፍ የሚንጠባጠብ የሥልጣን ፍርፋሪ ለመለቃቀም ውሎ አመሻሹን ሲባዝን እኔ ቢሮ ነኝእሱ ከፖለቲከኞቹ በላይ ፖለቲከኛ መስሎ ለመታየት ሲንደፋደፍ እኔ ከሕዝብ ጋር ነኝ ሕዝብ ውስጥ የሕዝቡን የልብ ትርታ እያዳመጥኩ

አንድ አብነት ብቻ ልጥቀስ፡- ፋሲል የኔዓለም የዶ/ ብርሃኑ ነጋ ነጠላ አቀባይ ነኝ እያለ ሲያሸረግድ (በወርሃ ነሐሴ 97 ዓም ሁለቱን ሳምንታት)  እኔ ባህርዳር እና ጎንደር ከተማ ውስጥ ዘገባ ላይ ነበርኩ፡፡ ጋዜጠኝነት ሕዝብ ውስጥ እንጂ ፖለቲከኞች ቢሮ ውስጥ ብቻ ሚገ አይደለም ያለመተዋወቃችን ምክንያት ይኸው ነው እኔ የሕዝብ እሱ የሹመኞች ወገን መሆናችን፡፡

ይልቅስ የገረመኝ "ወሰን የጀበናቤት ደንበኛ መሆኑ አልተዋወቅንም" ያለው ነው ጫት ቤት ማለቱ ነው ጫት ይቅማል ለማለት ነው እንዲህ ፍርጥ ፍርጥርጥ አድርጎ መናገር እያለ እንደ"ሥራቤት" የምን ነገር ማዟዟር ነው!? ቢሆንስ ችግሩ ምንድነው? አንድ ሰው ቢጠጣ፣ ቢያጨስጮማ ቢቆርጥ ጋዜጠኝነቱን ምን ይከለክልዋል? "ጋዜጠኞቻችንን ያዘናጋብን" የሚለውስ  የተዘናጉት ጋዜጠኞች™‹የትኞቹ ናቸው!? የነቃሁና የበቃሁ ጋዜጠኛ እኔ ብቻ ነበርኩ ማለ ነው!? ማን መስዋዕትነት ማነው ጉራ ሚነፋው? ኧረ ጎበዝ! ሌላው ቢቀር ህሊና ሚባ ነገር አለ፡፡ ወይስ ባህር ማዶ ሄደው መሽጉ ህሊና ባል ነገር ይጠፋል ማለ ነው!? አድነነ ከማአቱ ማለት ኼኔ ነው፡፡

              ስድስቱ

"....እስር ቤት ወሰንን ማወቅ ችያለሁ፤ ጥቃትን ማይወድ ደፋር  በመሆኑ እወደዋለሁ፡፡ አዛኝና ለማንም የማይጨነቅ ነው /የሥነፅሁፍ ችሎታውን ሳንጠቀምበት ቀርተናል/ ...." ይላል ፋሲል፡፡

እንደእውነ ከሆነ እነዚህ ውዳሴዎች አስፈላጊ አልነበሩም ስለችሎታዬ የፋሲል መወድስ ሚያሻኝም አይደለሁም "ችሎታው ሳንጠቀምበት" ያለው ግን በመጠኑ አስፈግጎኛል፡፡ የእኔ ችሎታ ለእነፋሲል አይነቱ መጠቀሚያ ውል አይችልም፡፡ ችሎታዬን ሚውለው ለሕዝብ ጥቅም ብቻ ነው፡፡ "መጣፍ" ሳይሆን መፃ እንደምችል ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እንደፋሲል አልጥፍም፤ ነገር አልደርትም፡፡ የፋሲል ውዳሴ ማያስፈልገኝ ለዚህ ነው። የፋሲል ከንቱ ውዳሴ አሰስ ገሰሱን አስከትሎ እንደሚመጣም አውቃለሁ፡፡ እንደሚከተለው ያለ ዝባዝንኬ፡-

"....የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከቅንጅት መሪዎች የተሻለ ሥነ ምግባር እንደተላበሱ አድርጎ ያቀረበበት ክፍልወሰን የትግል ታሪኩን ለጀበና ውጦት ይሆን የሚል ጥያቄ አሳድሮብኛል፡፡ ሰዎች ለመኖር ሲሉ እምነታቸውን ይሸጣሉ፤ ወሰን ግን እንዲህ በቀላሉ ህሊናውን እንደማይሸጥ እመሰክራለሁ፡፡....ወሰን ባላወቀው ወይም ሆን ብሎ የአሳዳጆቹ መጠቀሚያ ሊሆን እንደማይች እገምታለሁ፡፡... " ይላል ፋሲል፡፡

የምን መዘላበድ ነው እሱ!? አንድ ሰው ማለት የፈለገውን በግልፅና ፊትለፊት ተናግሮ ቢወጣለት ነው ሚሻለው። እዚህና እዚያ እየረገጡ መውሸልሸል ህሊና አለኝ ብሎ ከሚያምን ሰው ሚጠበቅ ተግባር አይደለምእንዲያ ከሆነ ደግሞ ፋሲል ስለህሊና ነፃነት የመናገር ብቃት የለውም ማለት ነው ህሊና ጫካ አይደለም በራስ ላይ መሸፈት አያስችልም፡፡ አይሸፍጥምም፡፡ ህሊና ለእውነት ከእውነ ጋር ነው ሚኖው። እኔም "በቃሊቲ ምስጢሮች" መፅሐፍ ውስጥ የከተብኩት ያየሁትን፣ ያስተዋልኩትን፣ ማውቀውን ሐቅ ብቻ ው። አንዲትም ቃል ሃሰት የለበትም

ፋሲል ከየት እንዳመጣው ላውቅም እንጂ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከቅንጅት መሪዎች የተሻለ ሥነ ምግባር እንደተላበሱ አድርጌ አልፃፍኩም ምክንያቱም የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከእኔ ጋር አልታሰሩም ከእኔ ጋር ስለታሰሩት የቅንጅት መሪዎችና ጋዜጠኞችን ውሎና አዳር እንዲሁም አመለካከት ብቻ ነው የፃፍኩት ሕዝብ ያላየውን ነገር ግን ማየት የሚገባውን እውነት ነው የገላለፅኩት፡፡ የፋሲል መንጨርጨር ገበናዬ ለምን ተገለጠ የመነጨ ካልሆነ በቀር፡፡

በነገራችን ላይ ማንበብና ማነብነብ ሁለት የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ለፋሲል መናገር ያለብኝ አይመስለኝም ገበናው የተጋለጠ ሰው ከማንበብ ይልቅ ሚቀናው ማነነብ ከሆነ ችግሩ ሌላ ነው፡፡ ፋሲል ያላነበበውን ማነነቡ ችግሩ የከፋ መስሎ ታይቶኛል፡፡

እዚች ላይ አዛኝ ቅቤ አንጓቹ ፋሲል የኔዓለም "ወሰን ሳያውቀው ወይም ሆን ብሎ የአሳዳጆቹ መጠቀሚያ ሆኗል" ያለወግ ላርመው እሻለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እኔ አሳዳጅ የለኝም፡፡ ጠላት የለኝም የሚያሳድደኝ ካለ እሱ እውነ ብቻ ነው። እውነትን ከመናገር ደግሞ ወደኋላ አልልም፡፡ "የቃሊቲ ሚስጥሮች" የፃፍኩት ለመኖር ስል አይደለም ምክንያቱም 97 ዓም በፊት እኖር የነበረውን ኑሮ ሚከለክለኝ ማንም የለም መፅሐፉን በመፃፌ ዩማገኘውም ማጣው የተለየ ነገር የለም። እስር ቤት ስጥ የሆነውን የተፈጠረው "ቁጭ" ነው ያደረግኩት፡፡ ያውም በአክብሮት ጭምር። የማንንም ስብዕና ሳልነካ፡፡ በአጭሩ "የቃሊቲ ምስጢሮ" የፃፍኩት የታሪካችንን ሌላ ገፅታ ለማሳየት ነው፡፡ የሀገር ታሪክ ስለሆነ ነው። ታሪክ ደግሞ ታሪክ ሊባል ሚችለ በጎውን መጥፎንም ማሳየት ሲችል ነው ለትውልድ አስተምህሮት ሚኖረው። ከዚህ የዘለለ ዓላማም ዒላማም የለኝም "አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ" ነውና

              
      ሰባ


ፋሲል የኔዓለም "የቃሊቲ ምሰጢሮች" አሁን በመፅሐፍ መልክ ታትሞ ለአንባቢያን መቅረቡ ለምን እንዳንገበገበው አልገባኝም ምክንያቱም 2002 . በእኔ አሳታሚነት ለንባብ ይቀርብ በነበረው "ሐራምቤ" ጋዜጣ 24 ሳምንታት በተከታታይ ተተርኳል፡፡ በተለይ እሱን የሚመለከተው ክፍል ከየካቲት እስከ ነሐሴ ወር 2002 . ነው በምድረ-ኢትዮጵያ ለንባብ የበቃው አሁን "ሐራምቤ" ጋዜጣ ለህትመት ያልበቃው ክፍል ታክሎበት ነው መፅሐፍ ሆኖ የመጣው፡፡

የሆነ ሆኖ እኔን ከሁሉ በላይ የገረመኝ ፋሲል የኔዓለም ".... ወሰን በእኔ ላይ ያቀረበው ወቀሳ ለምንበገንዘብ አልደገፈኝም› የሚል በመሆኑ ለሞራሉ መጎዳት አስተዋፅኦ አድርጌ ይሆናል.." ብሎ መዘላበዱ ነው፡፡

ቀድሞ ነገር ፋሲል የኔዓለም ምን ሆኖ፣ ምን አለውና ነው እኔን በገንዘብ የሚረዳኝ? የምን አጉል መኮፈስ ነው እርግጥ ነው እስር ቤት ውስጥ ስድስት ወር ሳይሞላን ከእስር ተፈትቶ፣ የስደተኝነት ሊቼንሳ አግኝቶ፣ "ሳይገድሉ ጎፈሬ" እንዲሉ ያልኖረበትን የጀግንነት ካባ ደርቦ፣ ከምስኪኑ ዲያስፖራ በትግል ስም ዶላር አሰባስቦ ለመኖር ሲቋምጥ የነበረው ፋሲል የኔዓለም ነው እንጂ እኔ አይደለሁም እናም ታጋይ ፋሲል ገና ምኑም ከምኑ ሳይያዝ ያለመው ተሳክቶለታል "ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ላይ ቂጥጥ" ብሏል፡፡ ይመቸው!!

ፋሲል ከእስር ቤት ሳይወጣ ባህር ማዶ ዘልቆ ጀግና ለመሆን ሲያልም፣ የእኔ ምኞት አንድ ብቻ ነበረ ከእስር የመፈታት ዕድል ካገኘሁ ለአንድ ጊዜም ቢሆን በሙያዬ ላይ መገኘት፣ ለአንድ ጊዜም ቢሆን ጋዜጣ ማሳተም ነበር ማልመው፡፡ ህልሜንም አሳክቻለሁ "ሐራምቤ" ጋዜጣን 6ወር አሳትሙአለሁ"ሐራምቤ" እንደገና ተከስሼ፣ እንደገና ቃሊቲን ጎብኝቼአለሁ ይህንንም ፍሷን ማር "አውራምባ" ጋዜጣ ላይ ፅፌዋለሁ፡፡ የዋስትና ገንዘብ ከፍለው ከዳግም እስራት ያስወጡኝ "አዲስነገር" እና "አውራምባ" ጋዜጠኞች መሆናቸውን የምናገረው በኩራት ጭምር ነው፡፡ ይህ ማለት የምፅፈው እነፋሲል የኔዓለም ከምስኪኑ ዲያስፖራ ሚሰበስቡት ገንዘብ እንጥብጣቢ ይወድቅልኛል ብዬ አይደለም ማለ ነው

ያኔ ብቻ አይደለም፤ አሁንም እየፃፍኩ ነው ወደፊትም እፅፋለሁ፡፡ የምፅፈው ማስመሰል፣ አጉል ታጋይ መባል፣ መመፃደቅ፣ ለከንቱ ውዳሴ አይደለም፡፡ የምፅፈው ለሕዝብና ለሃገር የተሻለ ምኞት ስላለኝ ነው  የምፅፈው ማንንም ተመክቼ፣ ማንንም ተገን አድርጌ አይደለም፡፡ የእኔ ተገን እና መመኪያ ውነትና ውነ ብቻ ነው የምፅፈው ሳላፈገፈግ ው። የሥነምግባር ትጥቅ መታጠቅ ማለ ደግሞ ይኼ ነው። እንጂ ያልተረዱትን ነገር ማንዴላ ምናምን እያሉ መደስኮር አይደለም በዚሁ ባበቃ ነው ሚሻው። በመጨረሻ ግን....

                   በመጨረሻ

"....ገምጋሚው ፋሲል በእስረኞች የተጠላ መሆኑን ከየት አመጡት? ምናልባት ወደፊት ሚወ የወሰን መፅሐፍ አግኝተውት ይሆን?" ሲል በፅሁፉ ውስጥ ላቀረበው ስጋታዊ መጠይቁ ምላሽ ሰጥቼ ይህንን ፅሁፍ ልደምድም፡፡

የኢሳት ፊታውራሪ ፋሲል የኔዓለም ሆይ!! ሥጋትህ ከንቱ ነው ወደፊት የሚታተም መፅሐፍ ቢኖረኝም እናንተን ስለማይለከት አትስጋ፡፡ ለዚህ ቃል እገባልሃለሁ፡፡ የሥጋትህ ምንጭ ግን ይገባኛል፡፡ አሁን "የቃሊቲ ምሰጢሮች" ብዬ ባሳተምኩት መፅሐፍ ውስጥ ያላካተትኳቸው እጅግ አሳፋሪ ታሪኮች እጄ ላይ እንዳሉ ጠንቅቀህ ስለምታውቅ ነው። ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮ የመኖር ባህል፣ ታሪክ፣ ምነ ጋር በእጅጉ የሚጣረሱ እና የወረዱ ተግባሮችን "ሕዝብ ላይ መትፋት ነው" በሚል አጭር አገላለፅ ትቼዋለሁ፡፡ ከዚህ በላይ መውረድ ከዚህ በላይ መዝቀጥ ሞት፣ የሞት ሞት ነውና፡፡

ቢሆንም ምናልባት ገንዘብ ካገኘሁ አንተ "እጅግ ውብ" ብለህ የመሰከርክላቸው ግጥሞቼን ናሳተሜ አይቀርም፡፡ ላኢጮኛህ ጭምር ማስታወሻነት ያበረከትኩላትን ግጥም ጭምር፡፡ በነገራችን ላይ ዘንግተህ ካልሆነ እስር ቤት የፃፍኳቸው ግጥሞች ሁለት ብቻ አይደሉም ብዙ ናቸው ትዝ ይልህ እንደሆነ ሁላችንም እስረኞች በምንታደምባቸው ምሽቶች "አጭር ፀሎት" የሚል ግጥም አንብቤ ነበረ፡፡ "ያቺ ፀሎቴ" በእርግጥም ሰምራልኛለችና ግጥሟን ጋብዤ ልሰናበትህ፡፡ ግጥሟ ውስጥ በእርግጥም እኔን፣ በእርግጥም ምኞቴን፣ በእርግጥም ፅናቴን፣ በእርግጥም እምነቴን ታገኘዋለህ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ በእርግጠኝነትም ታውቀኛለህ፡፡ እነሆኝ ግጥሟን ለስንብት፡-
አጭር ፀሎት
ፈጣሪ ሆይ
ረዥም ፀሎት የለኝም፣ ልፀልይ ብልም አልችልም
ለትንሣኤ ሞት አብቃኝ ብዬ አጓጉል አላስቸግርም
ይህቺኑ ዕድሜዬን በወጉ ፅናቱን ብርታቱን ስጣት
ከተገፉ ጋር አቁማት የደሀ ፍቅር ሸልማት
ይህቺኑ ዕድሜዬን አጣፍጣት - ከታሪክ መዝገብ አኑራት፡፡
ቁምነገር ማይገኝበት ረዥምና ዘልዛላ ዕድሜ አልለምንህም ቆሜ።
በትንሳዔ ለው ህይወት በጭራሽ ቁብ አይሰጠኝም
ከሞት በኋላ ለመኖር ናፍቆት ጉጉቱ የለኝም
እንኳንስ ሁለቴ ህይወት አንዱንም መኖር ታክቶኛል
የሰው ልጅ ሥቃይ ሰቆቃ ጩኸቱ አደንዝዞኛል፡፡
ሰው በሞላበት ምድር ላይ ሰው የሚሆን ሰው ጠፍቶ
ግፍና በደል በርክቶ ሕግ ስብዕናው ሞቶ
ሎሄ ዋይታ እየናኘ
ሀዘን እየተቃኘ
በትንሳዔ ህይወት ፈጥረህ ዳግመኛ ከምታኖረኝ
ለድሆች አጋር መከታ እዚሁ አንደዜ ሰው አርገኝ 
አሁን ባለው ህይወቴ ሰው መሀል ለሰው አቁመኝ፡፡
ይኸው ነው አጭር ፀሎቴ- ረዥም ፀሎት የለኝም
ልፀልይ ብልም አልችልም - ጌታ ሆይ አላስቸግርም
ጌታ ሆይ ሰው አርገኝ አንዴ - ይህቺኑ ህይወቴን ሸልመኝ
ንኛው ህይወት ይቅርብኝ - ለሰው ስለሰው አኑረኝ፡፡
ወሰብ ሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

Posted at www.ethiopisnsemay.blogspot.com
Email getachre@aol.com



 



No comments: