Monday, November 14, 2011

ሕሊና ቢስ ተቃዋሚዎች ሚዲያዎቻቸውና የሻዕቢያ ገበን

To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ sign.ከታች የሚታየው የወያኔ ገበና ማህደር አዲሱ መጽሐፍ ለመግዛት $30.00 ዶላር ሲሆን የአምናውይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፍ ደግሞ $25.00 ወይንም ሓይካማ የሚል የትግርኛ መጽሐፌ ደግሞ $15.00 ዶላር ብትልኩ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።

Getachew Reda P. O.Box 2219 San Jsoe, CA 95109  Phone (408) 561 4836 getachre@aol.com Phone (408) 561 4836

ሕሊና ቢስ ተቃዋሚዎች ሚዲያዎቻቸውና የሻዕቢያ ገበን

(ክፍል 1)

ጌታቸው ረዳ


ባለፈው ሰሞን  ጣሊያን አገር ውስጥ በስደት የሚኖር ዳግማዊ ይመር በተባለ ወጣት ኢትዮጵያዊ በጣሊያንኛ የተዘጋጀ የኢትዮጵያውያን ሕይወት በሚመለከት  ካገራቸው ሲሰደዱ ወደ ሱዳን በማምራት ከዚያም በደላሎች በኩል ገንዘብ በመክፈል ወደ አውሮጳ አገሮች ለመሻገር ወደ ሰሐራ ምድረበዳ ሲያቀኑ “በደዊን” በተባሉ የኤርትራ (ራሻይዳ/ሀረንዱዋ) እና የሊቢያ የግብጽ ምድረ በዳ ቅይጥ ዝርያዎች በባርነት ተሽጠው ለመግለጽ የሚያዳግት የሕይወት ፈተና ሴቶች እየተደፈሩ ወንዶች እየተገረፉና እየሞቱ ያለፉበት ሕይወት በባርነት ተይዘው ከነበሩ ዜጎቻችን ጋር ያዘጋጀው  ቃለ መጠይቅ አቅርቤላችሁ  የነበረውን ጉዳይ የታወሳል።
በሊቢያ ፖሊሶችም ሆነ በራሻይዳ/በደዊን ዘላኖች እና ባርያ ፈንጋይ ድርጅታዊ ቡድን በዜጐቻችን ሕሊና እና ሕይወት የደረሰው ለማመን የሚያስቸግር ግፍ ስንመለከት በሊቢያ ፖሊሶች ወይንም በበደዊን ዘላኖች ላይ የሰው ባሕሪነታቸውን  ስንገመግም እኛ በሰብአዊ እና በማሕበራዊ መተሳሰብ ባሕሪያችን ከእነሱ የተሻልን እየመስለን በኢሰብአዊ ድርጊታቸው እየተቆጣን ለዜጎቻችን ያዘንን ሰዎች አለን። ስለ እኛነታችን የጭካኔ ባሕሪ አለፍ ብሎ  በዜና በጋዜጠኞች የሚጻፉ ቁርጥራጭ ዘገባዎች እንጂ ሙሉ ታሪኩን የሚዘግብ ክፍል ስለሌለን በደዊኖች እና አረቦች እንዲሁም ሊቢያዎች በዜጎቻችን ያደረሱት ግፍ እየተመለከትን በነሱ  ላይ ስንቆጣ የእኛነታችን ጨካኝነት ግን አላወቅነውም። ስለሆነም የኛ ባርያ ፈንጋዮች እና ብልት ቆራጮች የሰው ልጅ ከነሕይወቱ ወደ ገደል ገፍትሮ መግደል፤ 12 ሺሕ፣ 30 ሺሕ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎቻችን ከነ ልጆቻቸው ከነበሩበት ከተወለዱበት አካባቢ በጉልበት እተገፈተሩ እንዲባረሩ ሲደረግ የዜና ዘጋቢዎቻችን የሚያስተጋቡት እምብዛም ነው። ቢዘግቡትም ዘገባዊ ክትትል (ፎሎው አፕ) ስለማያደርጉ  ተደጋግሞ ሲፈጸም ልማዳዊ በማድረግ ቸል ብለው ወደ ቡድናዊ  የፖለቲካ ዜና ወይንም  በአዳዲስ የማይረባ ዜና ትኩረት ይጠመዳሉ።
ለምሳሌ ባለፈው ወር “ኢሳት” የተባለው ዋሺንገቶን ዲሲ መሰረቱ ያደረገ  እነ ክንፉ አሰፋ (ኢ ኤም ኤፍ ድረ ገጽ አዘጋጅ) እነ የግንቦት 7 እና የመሳሰሉት ዘረኞችና እነ ንአምን ዘለቀ የመሳሰሉ ለሻዕቢያ ተቆርቁረው ባደባባይ ከሻዕቢያ “ማሕበረ ኮም’ ጋር ትከሻ ለትከሻ ተያይዘው ያገራችንን ሰንደቃላማ እያውለበለቡ ለሻዕቢያ መጠቀሚያ ፕሮፓጋንዳ  የሚጮሁ ግለሰዎች የሚመሩት የስዕለ ድምፅ የዜና ማሰራጫን ስትመለከቱ ወገንተኛ  መሆኑን የምትታዘቡበት ሁለት ነገሮች በቅርቡ የተከሰቱትን ልጠቁም። በቅርቡ “ሶሴፕ”  የተባለ ለብዙ አመታት ለማንኛውም ሰው ሶማሊ ኢትዮጵያ  ኤርትራ ሱዳን… ጥቃት ሲፈጸምበት ቀድሞ በመጮህ ዜናውን ለተለያዩ  የዓለም ተቋማት እያሳወቀ ተወዳዳሪ የሌለው በጐ ስራ የሰራ የእስረኞች ተከራካሪ ተቋም ሲጮህለት የነበረው ፤ላለፉት 19 ዓመታት በወያኔ ወህኒ ቤት ያለ ፍትሕ በቂም በቀልነት ሲማቅቅ ቆይቶ ሰሞኑን የተፈታው አቶ አበራ የማነ አብ ከእስር ሲፈታ ኢትዮ ላዮን  አሲምባ እና ደብተራው የተባሉ ድረገጾች ዜናውን ሲዘግቡት


የሻዕቢያ አሽቃባጮች  ለሆኑት ለእነ ኦነግ፤ለግንቦት 7፤ ለኦጋዴን ነፃ አውጪ… የመሳሰሉት የፖለቲካ ማሰራጫ የሚያገለግሉ እንደ  እነ ኢትዮ ሚዲያ፤ ኢትዮፎረም (ክንፉ አሰፋ) አቡጊዳ እና የትግራይ ጠላቶች የሚያካሂዱት ኢካድ ፎረም (ካረንት አፈይርስ) የተባለ ድረገጽ ግን የአቶ አበራ መታሰር እና መፈታት ከጉዳይ ሳይቆጥሩ ትናንት የታሰረው ደበበ እሸቱ ከወራት በሗላ ከትናንት በፊት ለተፈታው የቅንጅት/ የአንድነት አመራር የሆነው ተዋናይ ደበበ እሸቱ ሲፈታ ግን ኢሳትም ሆነ ከላይ የተጠቀሱት የግንቦት 7 እና የተገንጣይ ቡድን መናኸርያ አውታሮች የሆኑት ድረ ገፆች አሸብርቀው ደስታቸውን በመግለጽ በማስተጋባት ላይ ናቸው። ሶሴፕ በዚህ በኩል “ መብት ለኛ በደል ለነሱ አያዋጣም በማለት ሕዳር 1/2004 ዓ.ም ያወጣው የቅሬታ መግለጫ ውስጥ ለነኛ ወገንተኞች ማለት በኢትዮኢያዊነት የሚነግዱ የሻዕቢያ እና የተገንጣይ መልከቶች የሆኑ ድረ ገፀችና ራዲዮኖች” ያስተላለፈውን የቅሬታ መግለጫ  በኢትዮ ላየን፤ በአሲምባ እና ደብተራው በመሳሰሉ ያንድነት የዜና አውታሮች የተለጠፈውን ያወጣውን የቅሬታ መግለጫ ይመልከቱ።
በሚቀጥለው ምዕራፍ 2 በሚቀጥለው ሰሞን ግንቦት 7 የተባለው ጽንፈኛ እና ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵ ጠላት ደመኛ ጠላት ከሆነው ሻዕብያ ጋር እየተሞዳመደ ያለው ስራ በጣም አሳፋሪ የባንዳነት ስራ እየፈጸመ ስለሆነ ሻዕቢያ በትግራይ ሕዝብ በጽኑ ተፈላጊ ወንጀለኛ እና ደመኛ መሆኑን የፈጸመቸው ግፎች ላንባቢዎቼ ሳቀርብ የግንቦት 7 ባንዳዎች የወገኖቻችንን ሬሳ እየተሻገሩ ከሻዕቢያ ጋር እየተሳሳቁ 






የሚፈጽመሙት ተልእኮ መወገዝ  አለባቸው።

የትግራይ ህዝብና የኢትዮዮጵያ ሕዝብ ሻዕቢያን በወንጀል ይጠይቀዋል። በጽኑ! ግንቦት 7 ተባለ ድርረጅት እና አብረውት የሚብጡ የትግራይ ተወላጅ ተቃዋሚዎች ካሉ ካሁኑኑ ሕዝባችን እንዲኮንናቸው በሚቀጥለው ሳምንት የሩዋንዳ ዘር ማጽዳት ስራ የሚመሳሰል ሕዝባችን ይ  የፈጸመው ሻእቢያ ገበና ዝርዝር ይቀርባል ተከታተሉት።
ለዛሬ የማተኩረው ግን አደገኛ የሆነው የነዚህ ያዲስ አበባዊነት እና በአብሮሽ ፤አብሮሽ ዱለታ ትውውቅ  ውጭ አገር በስደት መናኸርያ እንደ ዳመና እየተሰባሰበ  ያለው እየተጠራቀመ የመጣው አደገኛ የሆነ የሊሂቃን ቡድን ጥምረቱ ስታስተውሉት  ላንድነት የቆምን ነን ይበል እንጂ በግብር እያሳየን ያለው ትእይንት ያው የምናውቀው ካገር በመሸሽ በስደት እየኖረ ካሁን በፊት ለቅንጅትን መፍረስ እንደ ማፊያ አይነቱ ተንኰል በመጎንጎን የወያኔ ዕድሜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጥምረት ጥርቅም የሆነው ክፍል ካለፈው ባሕሪው እና አፍራሽ ቡድናዊ ሚና ሳይመረምር ስሕተቱ  ዛሬም በአደገኛ “የአርቦሽነት” የፖለቲካ ሽረባ በመሸረብ አንድነታችን የማፍረስ ስራ ላይ መቃጣቱን ቀጥሎበታል።በትዕቢት እየቀጠለ በማይክሮፎን የሚለፍፈው ውሸት በማግስቱ እየተጋለጠበት ሳይጣጣም እምቢ ብሎት አንዴ ከጠባቦች አንዴ ከፈረንጆች አንዴ ከሻዕቢያ እዚህም እዚያም በመርገጥ የሚዘላብደው እርቃኑ የወጣ ፖለቲካ ለምንታዘበው ክፍሎች በእጅጉ ይገርማል።
ይህ ከቅንጅት መፍረስ ካዲስ አበባ እየተጠራቀመ ወደ ውጭ አገር እየተጠራራ ወደ ስደት  የመጣው አደገኛ ቡድን ታዋቂ ሰዎችን በቡድንተኝነት ስሜት ከብቦ በተለያዩ የሕሊና መሳቢያ እየተጠቀመ ጅሆ (ሆስተጅ) ሙርከኛ አድርጎ ገራ ገር ታዋቂ  ሰዎችን በስነ ኣኢምሮ ካቴና አስሮ ለጉራው መጠቀሚያ ሲገለገልባቸው ይታያል።በጣም የሚገርመው ደግሞ ታዋቂ የሚባሉት የድሮ ቅንጅት መሪዎች ቃላችንን አናጥፍም ብለው ሲፎክሩ ቆይተው ወላጆቻችን እና ዘመዶቻቸን የቀመሱት የፋሽስቶቹ የእሳት ጠበሳውና ሉጓሙ ሲጠብቅባቸው ሕዝቡን እየጣሉ ትምህርት እንማራለን ብለው ውጭ አገር  በመምጣት ወደ ተማሪ ዓለም ተለውጠው እንማራለን የሚሉትን “ትምህርት” ከመቀጠል ፈንታ ዛሬም የአደገኛውና  የከፋፋዩ ወገንተኛው ቡድን መገልገያ መሆናቸውን እየቀጠሉበት ነው።የሚያስቅ ሳይሆን አሳዛኝ ድክመት ነው። እነኚህ ታዋቂ የሚባሉት ግለሰዎች ለጊዜው በየስብሰባው እየጋበዙ የድግሳቸው ማጣፈጫ  ጨው እና ምጥሚጣ እያደረጉዋቸው እንደሆነ እየታዘብን ነው። ለወደፊቱ  ደግሞ እነ ስየ አብርሃ ሆኑ እነ ብርቱካን መዲቅሳ እና አንዲሁም አሜሪካኖች ተራራ ላይ ወጥተህ ተፈላሰፍ አንቀልብሃለን ስለ ገንዘብ አታስብ ብለውኛል ብሎ እያለን ያለው  በሻዕቢያ ኤርትራ ተራራ ላይ ወጥቶም ይሆን እዚህ አሜሪካ ዳገት ተራራ ላይ ወጥቶ የተሰጠው ትምህርታዊ ጥናት ያገባድድ አያገባድድ የምረቃውን ቀን ሳይነግረን ድምፅ ማጉያው ከንፈሩ ላይ ሰክቶ፤ በየቦታው የሆነ ያልሆነ የመንደር ወሬ እየለቃቀመ “የአነጐችን አንድ መሆን አሁን አሁን ገና አሁን ስብሰባ ከመግባቴ በፊት ‘ኢመይል’ ክፍቼ ሳነበው የተሰማኝ ደስታ ስመለከት ኦነጐች የመገንጠል ጥያቄ አቆሙ ደስ ይበላችሁ። ኦነጐችን እና ኦጋዴኖች ተገንጣዮች ናቸው የሚሉዋቹህ ዋሾች በመጪዋ ዲሞክራሲያዊት ገነታዊት ኢትዮጵያ ቦታ ስለማይኖራቸው የተበላ ኦቁብ  መሆናቸውን እወቁ …” በማለት የሚዘላብደው የግንቦት 7ቱ መሪው ብርሃኑ ነጋ እና መሰሎቹ በትምህርት ጥናታቸው ይዘንላችሁ መጣን እያሉን ያለውን ድምፅ  አንድ ወዳጄ የላከልኝ “ለልጅ ምክር፤ ለአባት መታሰቢያ የተበላ በሩይ ወልደስላሴ (ብላቴን ይመስሉኛል ማርጋቸው) መጽሐፍ ውስጥ ሳነብ በጸረ አንድነት ቡድኖች ላይ የከፈቱት የማጥላላት ዘመቻ እና የተገንጣይ ጓዶቻቸው እፍ እፍ ጊዜያዊ አርቦሽነት ስናደምጥ የሚደመጠው ድምጻቸው “ሲጮሁ እለቁ እለቁ ያሉ የሚመስሉ ጠጉራቸውም ለማየት የሚያስጠይፍ ወፎችን” ይመስላሉ። ብላቴን እንደሚሉት ““ከወፎችም ወገን ድምጣቸው ያማረ ጠጉራቸው የለሰለሰ ይገኛሉ። ሲጮሁ እለቁ እለቁ ያሉ የሚመስሉ ጠጉራቸውም ለማየት የሚያስጠይፍ ወፎችም አሉ” ይላሉ። እነኚህ በውጭ አገር የሚንቀሳቀሱት በተቃዋሚነት ባርቦሽነት ባዲስ አበባነት እየተሰባሰቡ የሚገኙት መርዛማ እና ጐሰኛ/ወገንተኛ የሊህቅ ስብስቦች” በምዕራባውያን አሰተማሪዎቻቸው የተሰጣቸውን የቤት ስራ ትምህርት ሳያገባድዱ እየተቻኮሉ “ዘው” እያሉ የሚለፈልፉት ውሸት ትዕግሰት እንዲኖረን የሚገፋፋ አይደለም።

ይህ ውጭ አገር በተቃዋሚነት እየቀጠለ ያለው ቡዱን የተጠናከረው በንግድ ጨዋታ የተካኑ ተንኰለኞች የተበተቡት ድር በመሆኑ ትግል ዓለም ልምድ ለሌላቸው ወጣት ዜጎች በቀላሉ ያርበኝነት የምስክር ወረቀት በገንዘብ እየገዙ እንዲጭበረበሩ አድርጓል። ሌላም ሌላም።

አንድ አስገራሚ ነገር ላንሳላችሁና ላጠቃልል። “ገለልተኛ” ብሎ ራሱን የሚጠራ ኢሳት የተባለው የዜና ማሰራጫ ስትመለከቱት ባለፈው ሳምንታት ደ/ር ግሬጐሪ ከተባሉት አሜሪካዊ የሰው ልጆች መብት ተከራካሪ አበበ ገላው በተባለው ወጣት ጋዜጠኛ የተካሄደው ቃለ መጠይቅ የታዘብኩት ነገር ቢኖር አዘጋጁ የጋምቤላዎች እና የኦጋዴኖችን እና 200 የሚያክሉ በ1997 ምርጫ በወያኔ ፖሊሶች የተገደሉ ሰላመዊ ተቃዋሚዎች ብቻ ወያኔ የፈጸማቸው የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን በእንግዳው በኩል እንዲረጋገጥ ደጋግሞ ሲጠይቅ ፤ ለ30 ዓመት (20 ዓመት ብቻ አይደለም) ሙሉ በወያኔዎች እና በሻዕቢያዎች እንዲሁም  በኦነጐች እና በኦጋዴን ነፃ አውጪዎች የተለያዩ የሃይማኖት ሽብርተኞች ያደረሱት በአማራው ሕብረተሰብ የደረሰውን የዘር ማጥፋት ጥቃት አንድም ቃል አንድም አረፍተ ነገር ከጥያቄው ውስጥ አላስገባም።
ጋዜጠኛው አበበ በለው ከ200ው የሰላመዊ ሰልፈኞች ግድያ እና ከጋምቤላው ጥቃት በላይ በአማራው ሕብረተሰብ ያውም እስከ ሁለት ዓመት በፊት ሳይቀር (በዚህ ኢትዮጵያን ሰማይ የተለጠፈው ጀርምን ራዲዮ ያስተላለፈው ዘገባ አሁንም እዚህ ተለጥፏል ያድምጡትActive Ethnic Cleansing in Ethiop http://youtu.be/aJDyueu2Kek  ) ትኩስ ተከታታይ ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ ወጣቱ ዘንገቶት ሳይሆን ኢሳት የተባለው የስዕለ ድምጽ ዜና ማስተላለፊያ ጣቢያ ጋር የግንቦት 7 መሪዎች የሚባሉት መሪዎች ከጣቢያው አካላዊ ብልቶች/ማሓውር ውስጥ አንዱ ስለሆነ፤ ይህ ግንቦት 7 የተባለው ጣቢያውን ከመሰረቱት የጣቢያው አንደኛው አባል (“ማሓውር” ብራንች ማለት ነው በትግርኛው) የመሰረተው ግንኙነት ከሻዕቢያ ጀምሮ እስከ ድርጊቱን ፈጽመዋል ከሚባሉ ወንጀለኞች (ኦነጐች እና ኦጋዴን ተገንጣዮች…) የሚዳራ ወዳጃቸው ስለሆነ አልፎም የነሱ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል እስከሚመስሉ ድረስ የሚቆሙላቸው ድርጅት በመሆኑ እነሱን ላለመስከፋት በአማራው ላይ በየአቅጣጫው በተከታታይ የተቀነባበረው እና ቀጣይ በአማራ ሕብረተሰብ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ጋዜጠኛው አበበ ገላው ለዶ/ር ግሬጐሪ አንዲት አረፍተ ነገር ሳያነሳለት ማለፉ እኔኑን ባያስገርመኝም አንባቢዎቼ ግን ቃለ መጠይቁን እንደገና ልብ ብላችሁ እንድታደምጡ እና የናንተ ትዝብት እንድትጨምሩበት እጠይቃለሁ።ከተሳሳትኩ እታረማለሁ።
ኢሳት ገለልተኛ ነኝ ይላል። እንዴት ሆኖ? በተወሰነ የፖለቲካ መሪ እና ድርጅቶች ላይ ዘመቻ ማካሄድ እንዴት ገለልተኛ ያሰኘዋል? ባለፈው ሰሞን በኢሳት ላይ እንግዳ ሆኖ የተላለፈ መደብ “ደ/ር ፈቃደ ሸዋ ቀና” የተባለ የግንቦት 7 አባል በኢንጂኔር ሃይሉ ሻውል ያፈሰሰው ዘለፋ ይታወሳል። የድሮው ኢትኦጵ መጽሄት/ጋዜጣ አርታኢ የዛሬው የአሳት ስዕለ ድምጽ አዘጋጅ ሲሳይ አገና የኦነጉ ዲማ ነገዎ እንግዳው ሆኖ ሲያነጋግረው “ኦነግ የኢትዮጵያ/የደረግ ሠራዊት እንዳይፈርስ ተከራክረናል” ብሎ እስካፍንጫው የገማ ውሸት ሲዋሸን እያዳመጠ መቶ አለቃ ሲሳይ አገና  እራሱ ወታደር መሆኑን እያወቀ “ኦነግ” የተባለ ተገንጣይ፤ጸረ ማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን “በፊት አውራሪነት”/ግምባር ቀደም ሆኖ ወታደሩ እንዲፈርስ ያደረገው ኦነግ  መሆኑን በሚገባ አንጀቱ እያወቀው  ዲማ በታሪክ ፊት ሲዋሽ ቸል ብሎ ሲያልፈው (የዘር ማጥፋቱን ጉድ ለወያኔ ብቻ ሲጣል የተደመጠው አስገራሚ የኦነግ የየለንበትም ክሕደት በዋዛ በቀላሉ  ነካ ነካ ተደርጎ እንዲያልፍ ያደረገውን ሳናነሳ ማለት ነው) እኔ በጣም ተገርሜአለሁ።

ሰሞኑንም የገረመኝ ደግሞ ኢያሱ በርሐ የተባለው ዘረኛ እና ትዕቢተኛ/ትምክሕተኛ በወያኔ ህንፍሽፍሽ ጊዜ የሚገደሉት ሰዎች “በደላላነት” የ“አ ሽ ዓ”መሪዎች ፎርማቶሪ ሆኖ በእንደርታ ተወላጅ ተዋጊ ሃይሎች የፈጸመው አሰቃቂ ገበና ተረስቶ ዛሬ “ኢሳት” የተዋጣለት አርቲስት እያለ ድሮ ሜዳ ጫካ ሆኖ ሲዘላብዳቸው የነበሩትን ጸረ ኢትዮጵያ ዘፈኖችን “በኢሳት”  ጣቢያ በመልቀቅ “ኢያሱ ተገደለ ወይስ ሞተ? ” እያሉ ሲያዘፍኑልን ያደመጠ ሕሊና ያለው ሰው ሳይገርመው አልቀረም። በጣም የገረመኝ ግን ሕንድ አገር ውስጥ የዜጋ ያለህ እያለ ኢየሩሳሌም አርአያ ከእናት አልባ በሽተኛ ህጻን ልጁን ታቅፎ የድረሱልኝ ጩኸት ሲጮህ ደንታ ያልሰጣቸው  የኢሳት ዋና ዋና ሰዎች  ለቅንብር እንዲመችላቸው ማቀናበሪያ ፕሮግራማቸው በማድረግ አርአያ ተስፋማርያም አገር ውስጥ እያለ የዘገባትን ጽሑፍ አስደምጠውናል። መቸም የነዚህ ግለሰዎች ወገንተኛነት፤ትዕቢት የማያውቅ አድማጭ እውነት ይመስለው ይሆናል። አሳት ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን (ሁሉም አንኳ ባይሆኑ) እንደሚዘላብዱት ሳይሆን ለቡድናቸው ብቻ የሚጮሁ የሚደርሱ “ወገንተኞች” መሆናቸው ባለኝ ሰነድ በተጨባጭ መከራከር እችላለሁ ። አጫዋች  እና  ዘፋኝ ታማኝ በየነ ጌታቸው ረዳ ስለ አርአያ (እየሩሳሌም) አርዳታ ጉዳይ ምን ብሎ ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቦልህ ነበር ብላችሁ ጠይቁት። ምን እንደሚመልስላችሁ ከነገራችሁኝ በሗላ መረጃው እነግራችለሁ።  በትግርኛ አንዲህ ያለ ነገር ሲገጥም እንዲህ ይባላል “አድጊ አብ ምእራጋ መስከብ ትወልድ ዒሉ ሓዲጋ”  “ አህያ ልታረጅ ስትል ውርንጭላን መውለድ ትታ የእንግዴ ልጅ ትወልዳለች” ። እንግዲህ እንዲህ አይነት ኩራት የሚያሳዩት ለምን ይመስላችል? ሊሂቅና አርቦሽ አርቦሽነት ስብስብ ሲጎለብት ጉልበት ያለው/ኦምኒፖተንስ ስለሚመስለው ኩራታቸው መከራ ነው። አንድ ትግርኛ ምሳሌ ልጨምር “ አድጊስ ሳልሳይ ርእሳ እንተ ኾነት ዝብኢ ዝኽእላ ኣይመስላን” (አህያ ሦስት እራሷ ጋር ስትሆን ጅብ የሚችላት አይመስላትም”)
ኢሳት ግንቦት 7ን እያገለገለ ነው። ኢሳት እንደሚዘላብደው ገለልተኛ ሳይሆን ወገንተኛ መሆኑን አያጠያይቅም። አጫዋቹ እና ዘፋኙ (ኮመዲያን ይሉታል መሰል እንግሊዞች) ከላይ የጠቀስኩት ታማኝ በየነ የተባለው እንኳ ባለፈው “የኢሳት ዕርዳታ ማሰባሰቢያ ዕለት”  ባዘጋጀው መድረክ ላይ “ሰዎች ኢሳት  የግንቦት7 ነው ይላሉ፡ አይደለም! ቢሆንስ!” ሲል በጣም ኩራትና ልበ ደንዳናነት በተሞላበት ፈረንጆች “ጐ ቱ ሄል- ዘ ሄክ ዊዝ -ዩ! " ሦ-ዋት!” እንደሚሉት አይነት ድርቅና የተሞላበት ንግግር መናገሩ አድምጬዋለሁ። ሰውየው  ጥሩ ኢትዮጵያዊ መሆኑን  አልክደውም - ቢሆንም ትንሽ የሚጐድለው ነገር አለ። እሱ እና ብርቱካን መዲቅሳ በተንኰል በተካኑ ጋዜጠኞች እና ኤሊት ጋንጐች “ጁሆ” መሆናቸው ልብ አላለውም።  ሰውየው ለዚህ አባባሌ  አሳቂ  ችሎታው እራሱን ሊያስቀው ይችል ይሆናል፤እውነታው ግን አሱም እራሱ “ሂፕመታይዝድ” ያደረጉት ክፍሎች እንዳሉ አልተረዳውም እና ጊዜ ሲፈጅ ሲባንን ይረዳው ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።
ኢሳት የግንቦት 7 ቢሆንስ ምን ልትሆኑ ነው! ማለቱ እጅግ አስገራሚ መልስ ነው። ግንቦት 7 ኢሳት የሚቆጣጠረው ከሆነ “  አይ ሃቭ ኤ ፕሮብሌም” ይላሉ ፈረንጆች “ባባሉ ችግር አለኝ”ማለት ነው። ግንቦት 7 አደገኛ አድር ባይ እና ውሸታም የሆነ ከሻዕቢያ ጋር የተቧደነ ፤ሻዕቢያ በሕዝባችን ላይ ያደረገው ግፍና የዘር ማጥፋት ወንጀል ግድ የሌላው፤ አሁን በየሳሕል እና በየጉራንጉሩ ዛፍ ተከላ እና ወረቅ ለቀማ ባሰማራቸው በባርነት የተያዙ አይናቸው የታወሩ ሻዕቢያ የትም የጣላቸው  ዜጎቻችን ቸል ብሎ ስቃያቸው ያልተሰማው ኢሳያስ ጋር ነጋ ጠባ እጅ የሚነሳው አንዳርጋቸው እና የብርሃኑ ድርጅት ደንታ ቢስ ካሃዲ መሆኑ ታማኝ በየነ ካላወቀው በሚቀጥለው ጽሑፌ የሊቢያ፤የሰሓራ በደዊን ባርያ ፈንጋይ አረመኔዎች ከሰሩት ወንጀል ያልተናነሰ ያውም የከፋ ዘገባ በተጨባጭ ከሰለባዎቹ የተገኙ በትግርኛ የተደረጉ የቃል ምልለሶች ባማርኛ ተርጉሜ  ዘግቤ  አቀርብላችለሁ። ታማኝም እንዲያነበው እና “ቢሆንስ! ምን ልትሆኑ ነው” ከሚለው ድርቅና ያድነው ዘንድ እንዲያነበው እዚህ ጋር እጋብዘዋለሁ። ለቅምሻ እነሆ  በክፍል ሁለት በሚቀጥለው ሰሞን ይለጠፋል።

ታሪኩ የተገኘው በቅርቡ “ጥልመት’ ከተባለ በወያኔው  በዶክተር ሰለሞን ዕንቋይ የተጻፈ የተገኘ ጥናት እና ታሪክ ነው።
“ቄስ ተኽለ አረጋይ የተባሉ የትግራይ ሠው የኤርትራ ወጣት ተማሪዎች በኢትዮጵያውያን በተለይ በትገሬ ሰዎች ላይ በሻዕቢያ ቅስቀሳ ተነሳስተው  የፈጸሙት ዘር የማጽዳት ዘመቻ እንዲህ ይገልጹታል… ይላል መጽሐፉ


““ቄስ ተኽለ አረጋይ የተባሉ የትግራይ ሠው ከረን ውስጥ ሲኖሩ ባረንቱ በኢትዮጵያ (በባድሜ ጦርነት ወቅት) ሠራዊት እጅ ከወደቀች በላ ወጣቶቹ በማግስቱ የወሰዱት እርምጃ እንዲህ ያስታውሱታል “ባረንቱ ውስጥ ባላስረጋ በተባለ ቦታ ተሰብስበው የነበሩ ወጣት ተማሪዎች ‘ዛሬስ የሚገደል ሰው አጣን፡ ሁሉም አጥርተናቸዋል መሰል። እነኚህ አጋሜዎች ሁሉንም ፈጅተናቸዋል መሰለኝ  የሚገደል አጋሜ በከተማው ውስጥ ብንፈልግ ልናገኝ አልቻልንም! ሲሉ ሰማቸው። ያኔ እኔኑን ያስፈራኝ ጉዳይ እነሱን መስየ/ኤርትራዊ መስየ ነበር የምዘዋወረው እና ደንገት እንዳይነቁብኝ ተጠራጠርኩና በውስጤ በጣም ሰጋሁ።
በወቅቱ አንድ የትግራይ ሰው የሆኑ ቄስ ወዳጄ አጥቻቸው እሳቸውን ፍለጋ ስዘዋወር ነበር የህ አስፈሪ የግድያ ዘመቻ ሲነጋገሩ ያደመጥኩት። ቄሱን ስፈልግ በድንገት ከአንድ የቆሻሻ መጣያ ቦታ አንድ ሬሳ ተጥሎ አየሁ። ህ ሬሳ ምንድ ነው? ብየ ስጠይቃቸው ‘የአንድ አማራ ሬሳ ነው” አሉኝ።

ሌላ ሦስት ሬሳ ደግሞ ጉል (ጉልዒ) ዛፍ ስር ወድቆ ተመለከትኩኝ። ከነዚህ ሬሳዎች አንደኛው ይኼ የምታዩት ከወደ እዚህ በኩል ያለው ሬሳ ‘አደንዝዝ” እየተባለ በፈረስ ስም  ስንጠራው የነበረው አጋሜው እኮ ነው እየተባባሉ ሰማቸው።…” 

በጣም ዘግናኝ የሆኑ የሻዕቢያ እና ጀሌዎቹ ዘግናኝ ገበና በክፍል ሁለት በሚቀጥለው ሰሞን ይቀጥላል። እነ ታማኝ በየነ ኢሳት የግንቦት 7 “ቢሆንስ!” እያሉ በድርቅና የሚደነፉት ዕብጠት ባንዳው የግንቦት 7 ድርጅት ከጌቶቹ ከሻዕቢያዎቹ ጋር ሲሞዳመድ ወገኖቻችንን የወደቀበት እሬሳ እየረገጠ አዛዣቸው ኢሳያስ አፈወርቂን ለመማጸን በደም መሬት ላይ እየተረማመደ መሆኑን መታወቅ አለበት። ይቀጥላል…።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ Ethiopiansemay.blogspot.com ( just Goole it Ethiopian Semay) getachre@aol.com












3 comments:

Alemu said...

Alemu, Thank you Ethiopian Semay for the information, keep up the good work, ethiopia needs just only a couple of great people not those trush like G7 head of members and easator olf, their blood is ethiopian but their mind is not, they need have their corner, please keep up the next part 2 once again thanx all

Ha said...

Re Melat,
Thank you Eth- Semay
Please explain how come you call others moron when I see no valid reason and content from you and blame others for your own stupidity and luck of understanding what the current political entering shows in black and white, or you are one of those blind supports of those politically wicked individuals any ways time will tall. HAi

Anonymous said...

Melat,

I can't understand why you are verbally abusing Getachew instead of challenging his idea. He is telling you the truth. EMF, Ethiomedia, ECAD etc are very biased. They are repeatedly caught red handed trying to cover up the crimes of OLF, ONLF..Getachew is telling the truth. Try to prove him wrong then it will be constructive.