እዉን የወያነ ተከታዮች ከዓፋር ግመሎች ባነሰ የኢትዬጵያን ባንዴራ አያዉቋትም?
(ጌታቸዉ ረዳ)
Getachew Reda P. O. Box 2219 San Jose, CA. 95109 Telpone 408 561 4836 getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
እዉን የወያነ ተከታዮች ከዓፋር ግመሎች ባነሰ የኢትዬጵያን ባንዴራ አያዉቋትም?
(እያዝናና ልብ የሚሰብረዉ የወያነ ትግራይ ትራጀዲያዊ ተዉኔት!)
ካለፈዉ ግንቦት ወር ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በወያነ ትግራይ ተከታዮች የታዘብኩት ነገር ኢትዮጵያዊነት እና ወያነነት ስሜት እጅግ አደገኛ በሆነ መልኩ እየተፋጨ እንደሆነ ነው። ወያነ ትግራይ ብዙዎቹን የትግራይ ማሕበረሰብ በዉድም በግድም ከዚያም አልፎ ስሜት በሚኮረኩሩ ቅስቀሳዋች ተንተርሶ ወደ ዓላማዉ አሰማርቶ ብዙ አገራዊ ነክ ጉዳዮችን በጎጂ መልኩ አንዳንዴም በአደገኛ መልኩ በግልጽ እና በምስጢር የሚያከናዉናቸዉ ፖሊሲዎቹ ደጋፊዎች እና አድማቂዎቹ ሆነዉ ለብዙ ዓመታት አብረውት ተጉዘዋል።
ቁጥራቸዉ ለመገመት ባልችልም በርከት ያሉ የትግራይ ተወላጆች ወያነ ትግራይ ለሁለት ከተሰነጠቀ በሗላ በመለስ ዜናዊ እና በስብሐት ነጋ የሚንቀሳቀሰዉ የህዛባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ቡድንን በመቃወም ተቃዋሚው ወደ ሆነው ወደ ስየ እና ገብሩ (ዓረና ትግራይ)በማንዘበል-“ዞር አሉ አልሸሹም”ብየ ወደ ምጠራዉ የመገንጠል መብት የሚያከብረው እና ለመገንጠል መብትም ቆሚያለሁ ወደ ሚለዉ ወደ ዓረና ትግራይ በመዞር የመልስን ወያነ እየተቃወሙ መሆናቸው ይታወቃል።
ዘንድሮ እየተጠናከረ የመጣዉ በጥበት የተበከለው ሌላዉ የወያነ ትግራይ አጨብጫቢዉ ክፍል ደግሞ በጣም ዑወር የሆነ ግን በዓድዋ አሉሙናይ፤ በሽረ አሉሙናይ፤በአክሱም አሉሙናይ፤በንግስተ ሳባ በአጼ ዮሐንስ፤ በምንትስ …በምንትስ….አሉሙናይ እየተሰባሰቡ ለየአካባቢያቸው እና በተማሩበት አዉራጃ/ወረዳ/ትምህርት ቤት ማሳደሻ እና ትምህርት ቤት፤ቤተመጽሕፍት ማሰርያ፤ሽንት ቤት ማሰርያ ወዘተ በሚል መነሻ የዋያነ ትግራይ ተገዢነቱን በግልጽ ማጉላት ጀምረዋል። ይህ የወያነ ትግራይ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ከበረሃ ጀምሮ ምን ዓይነት ኢትዮጵያዊነት ያስተምር እንደነበረ እና ከበረሃ ወደ በትረስልጣን ከወጣ በሗላም በየመጽሔቱ ተደጋግሞ ከሚጠራላቸዉ የበደኖ፤የአርባጉጉ፤የወተር፤የአረካ፤የጎንደር፤የአንዋር መስጊድ ወዘተ…ጭፍጨፋዎች በረሃ እያለ እሱ እና መሰል ተገንጣዮች/ጠባብ ብሄረተኞች እሰራዋለሁ ብሎ በደብተሩ ለኢትዮጵያ ይዞላት የመጣዉ ስብክበትና ሲያስተምርበት የነበረዉን የፖሊሲዉ ውጤት አድናቂዎች በመሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋወሪ የወያነ ትግራይ መሰሪ ወያነነት በመከተል የአገራቸዉን ሰንደቃላማ ከማክበር እና ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ በአገሪቱ ታሪክ ተሰምቶ ታይቶ የማይታወቅ የትግራይ ሕዝብ ሰንደቃላማ በመጣል እና በማናናቅ ወያነ ትግራይ ብሎ ራሱን የሚጠራ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት ባንዴራ በማዉለብለብና ቀዳሚ ክብር በመስጠት በየጭፈራ ቤታቸዉና በየስብሰባቸዉ ይህንኑ የድርጅት ባንዴራ አገራዊ ሰንደቃላማ አድርገዉ በመዉሰድ አሳፋሪ የታሪክ ወንጀል በመፈፀም ላይ ናቸው። “እንኳን እኛ ግመሎቻችን የኢትዮጵያ ባንዴራ ያዉቃሉ”የተባለላቸዉ ዓፋሮች ለኢትዮጵያ ያላቸዉ ተሟጋችነት እና ቀናኢነት እንዲህ ሲናገሩ በ“አሉሙናይ ሰበብ” ፤ በ“ልምዓት ዓዲ ብወዲ ዓዲ” ሰብብ “የፖለቲካ ድርጅት” ባንዴራ “የኢትዮጵያ ባንዴራ” መስሏቸዉ ከፊት ለፊታቸዉ በየጠረጴዛቸዉ በክብር የሚያዉለበልቡት የመለስ/ስብሓት ወያነ ትግራይ ፕሮፖጋንዳ ሰለባዎች እዉን ከዓፋር ግምል ባነሰ የኢትዮጵያን ባንዴራ አያውቋትም?ከዚህ ወዲያ የትግራይን ሕዘብ ወዴት ይወስዱትይሆን?እያዝናና ቀስ እያለ ልባቸዉን የሚሰብረዉ የወያነ ትግራይ ትራጀዲያዊ ተዉኔት ውስጥ ገብተዉ ተወናያን መሆናቸዉን ማቆሚያቆሙት መች ይሆን? እንደገና ሌላ ቁጭት አንሰማ ይሆን? ለማንኛዉም መሰንበት ደጉ ይባላል እንሰንብትና ጉዟቸዉን አብረን እንታዘብ። ባህሩ አስነጥቆ ያስነጠቀዉን ቡድን ባንዴራ በክብር ሲያዉለበልብ ማየት አስገራሚ ዘመን እንደዚህ አላየሁም። በታሪክም አላነበብኩም። ልብ የሚሰብር ጥቁር ነጥብ የጣለ የታሪክ ክንዉን። ጌታቸዉ ረዳ (408)-561-4836 getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
No comments:
Post a Comment