የአማራዉ ሕዝብ ዕልቂት በአንድ ዘር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት
Please visit http://www.ethiolion.com/ and http://www.ethiopatriots.com/ for PDF Format of the article.
ካለፈዉ እትም ክፍል ሦስት “የትግራዩን ኤሊት/ሊሂቅ” በወያነ ትግራይ ያለዉ አመለካከት ለማቅረብ ቃል ገብቼላችሁ ነበር፣፣ ያንን ለሚቀጥለዉ ሰሞን አስተላልፌዋለሁ፣፣ በሰሞኑን ከትግርኛ ሚዲያዎች አምዳችን የሚተላለፉትን ዜናዎችና የሚደረጉት ቃለ መጠይቆች በመተርጎም ለመተቸት እና ትግርኛ ለማትናገሩ ዜጎችም አብራችሁ ለመከታተል ያመች ዘንድ ያዘጋጀሁት አምድ ነበር እና አሱን ላስቀድም አልኩኝ፣፣ ለዚህም አንደኛዉ እንግዳ ስብሓት ነጋ ራድዮ መርሃዊት ከተባለዉ የትግርኛ ራዲዮ ጣቢያ ያደረገዉ አስገራሚዉ ቃለ መጠይቁ እና ሰሞኑን ከዶ/አሰፋ ነጋሽ በነፃነት ራዲዮ ላይ ሲከራከር ነበረዉ የዋሺንግተን ዲሲዉ የሕግ ጠበቃዉ የአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ቃለ መጠይቅ ከእዛዉ ከራዲዮ መርሃዊት ጋር ያደረገዉ ሌላኛዉ አስገራሚ ቃለ መጠይቅ (በሌላ አምድ ሙሉዉን ቃለ መጠይቅ አቀርብላችሗለሁ) ነበር እና ሁለቱንም በማዘጋጀት ላይ የትኛዉ ይቅደም ብየ ስወስን-የአቶ ሙሉጌታን መረጥኩ፣፣ ለምክንየቴም አቶ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ዘር ስለሆንን “የዘር ፍጅት” ሊከሰት አይችልም በማለት ግንቦት 7 ለትግራይ ሕብረተሰብ የአስተላለፈዉ መግለጫ መሰረት በማድረግ ሰፊ እርስ በርስ የሚጋጭ ቃለ መጠይቅ ከመስጠቱ ባሻገር እና የቃላት ጨዋታ ከመግባቱም ባሻገር “የዘር ፍጅት/እልቂት” ከ “ኤትኒክ ክሊንሲነግ- የጎሳ ፍጅት/ እልቂት” በትርጉም ቢለያይም በተግባር ያዉ የሰዉ ልጆች ሕይወት መቅሰፍት ነዉና “የሰዉ ልጆች ዘር የእርስ በርስ ፍጅት የሚያካሂዱት አረሜናዊ እርምጃ መሆኑን እንስማማ እና ” ኤትኒክ ክሊንሲንግ (የጎሳ ፍጅት)“በቲ ፒ ኤል ኤፍ” ሊካሄድ አይችልም በማለት ተከራክሯል፣፣አምዱን የመረጥኩበት ምክንያትም ለዚህ ነዉ እና የአቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ሙግት ቀንጨብ አድረጌ ላቅርብ እና እሳቸዉ ያልሰሙት ያላዩት የጎሳ እልቂት በዘመነ ህዝባዊ ሓርነት ትገራይ መንግሥት “ቲ-ፒ ኤል ኤፍ”/መንግሥት ባለስልጣኖችና ሹሞች እንደዚሁም ኦሮሞን እንወክላለን ነፃ አገር/ሕዝብ እናደርግሃለን በማለት የኦሮሞ ደግ ማሕበረሰብ ሰብአዊ ሕሊናዉን በማሳሳት የኦሮሞዉን ሕዝብ/ገበሬ በአማራዉ ሕብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲይዝ በማድረግ በአማራዉ ሕብረተሰብ የተፈጸመዉ እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ “የጎሳ ጽዳት” ከወያኔ የገበና ማሕደራችን ላስተላልፋችሁ ነኝ፣፣ ካሁን በፊት ይህንን ዘገባ ያላነበባችሁ ሰዎች ካላችሁ “አሳዛኝ ነዉና ‘ትንሽ ረጋ ብላችሁ ራሳችሁን በንዴት አትጉዱ” የተፈጸመዉን “አይፈጸምም” ወደ አሉት የዕልቂት ማህደር-ከመዉሰዳችሁ-በፊት-አቶ ሙሉጌታን ልጥቀስ፣-
አቶ ሙሉጌታ ግራ የገባቸዉ (ለእሳቸዉ ብቻ ሳይሆን ለእኔም ጭምር ግራ የገባኝ የግንቦት 7 ደንቆሮ መግለጫ ቃል በቃል ለትግራይ ህዝብ ያስተላለፈዉ “የትግራይ ሕዝብ (ሊሂቁን ከማስታወቅ እና ሃለፊነቱን እንዲፈትሽ ከማድረግ ይልቅ)የዘር ፍጅት ሲፈጸም (መፈንቅለ መንግስት ጋር/ሽብር? ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ጥቂት የአማራ (?) ህዳጣን/ሕብረተሰብ አባሎች ማለቱ ነዉ መግለጫዉ “ከዘር- ፍጅት” ጋር ያያያዘበት ምክንያት) ዝምታ ከመረጠ ዝምታም ወንጀል ነዉና በተባባሪነት ወንጀል ትጠየቃላችሁ፣ ብሎ አጠቃላይ ምንም የማያዉቀዉን ገበሬዉንም ጭምር (ለትግራይ ሕዝብ ብሎ) ላስተላለፈዉ “ደንቆሮ መግለጫ” በመዉቀስ ለትግራይ ሕዝብ የተላለፈዉ ግንቦት 7 መግለጫ መግለጫዉ ጥቅሱን ካነበቡ በሗላ፣ - አቶ ሙሉጌታ “……………………………………” “ኤትኒክ ክሊንሲንግ ግንቦት 7 እንዳለዉ TPLF –Ethnic Cleansing ያካሂዳል ማለት ነዉ (በመግለጫዉ መሰረት)፣፣ መጀመሪያ ይህ (ዉንጀላ) ከየት እንደመጣ አላቅም፣፣ ምክንያቱም “በዴፌኒሺኑ/Definition” ስትመለከተዉ ቲ ፒ ኤል ኤፍ “ማጆሪቲ/Majority” ሊሆን አይችልም፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቲ ፒ ኤል ኤፍ TPLF (ትግሬዉ) በቁጥር፣ ማይኖሪቲmainority ናቸዉ፣፣ “ሶ/So” ቲ ፒ ኤል ኤፍTPLF በማን ላይ ነዉ ኤትኒክ ክሊንሲንግ/Ethnic Cleansing የሚያካሂደዉ? ቲ ፒ ኤል ኤፍ /ፎች ትግሬዎች ናቸዉ፣፣ ትገሬዎች ማንን ነዉ “ዲፖርት/Deport” ሚያደርጉት? ማንን ነዉ ገፍተዉ የሚያወጡት( “ጠርገዉ የሚያወጡት”) ከኢትዮጵያ ጠርገዉ ለማስወጣት የሚመክሩትን አማራዉን ነዉ? ኦሮሞዉን ነዉ? ቢሞክሩስ እንደዚያ ማድረግ ይቻላል ወይ? ምክንያቱም “ማጆሪቲ/Majority” “ማይኖሪቲዉን/Minority ማስለቀቅ አይችልም፣፣ እራሱ አባባሉ “ቲኦሮቲካል ዊክነስ/Theorotical Weakness” አለዉ፣፣ ነገሮችን ለማጋነን ነዉ (እንደዚህ ዓይነት ቅስቀሳ ማካሄድ) ምክንያቱም በዓለም ዉስጥ እንዲሰራጭ እና ጋዜጠኞችም ዜናዉን አግኝተዉ እንደፈለጉት ስለሚጠቀሙበት (ሆን ተብሎ የተሰራጨ ነዉ)፣፣ኤትኒክ ክሊንሲንግ Ethnic Cleansing ወይንም በአማርኛዉ “የዘር ማጥፋት” የሚባል (ቃል) ለመጀመሪያ ጀሮየ ከግንቦት 7 ነዉ የሰማሁት፣፣”
በማለት ወንድሜ አቶ ሙሉጌታ አራጋዊ የጎሳ እልቂት “ማጆርቲ/majority” እንጂ “እንደ ቲ ፒ ኤል ኤፍ ማይኖሪቲTPLF/Minority ያለዉ የጎሳ እልቂት ማካሄድ አይችልም የሚለዉ ፈረንጆች የሚጭሩት ጽሁፍ/ትርጉም ብቻ በመመርኮዝ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በተደጋጋሚ ምን እንተደረገ ያወቁት አይመስለኝም፣ ካወቁትም በምን ዘዴ ይሄንን ከዚህ በታች ያለዉን በወያኔ ዘመነ መንግሥት የተፈጸመዉ የጎሳ ማጽዳት ስራ እንደሚመለከቱት ባላዉቅም፣ ለኔ ይህ ከዚህ በታች የተዘገበ ወንጀል የጎሳ እልቂት ሃላፊነቱ (የማንም ይሁን የማን ከሌሎች ተጠያቂዎች ጋር ጨምሮ) ወያኔም ለዚህ እልቂት በቀየሰዉ የጎሰ ፖለቲካ ግምባር ቀደም ተጠያቂ ነዉና ወያኔ ትግራይ በተዉኔት በዘፈን በፕሮግራም በቅስቀሳ አማራዉ በሌሎች ህዳጣን የኢትዮጵያ ሕብረተሰቦች እንዲጠላ እና እንዲጠቃ በአማራዉ ላይ ሲቀሰቅሰዉ የነበረዉ ጥላቻዉ በግብር እንዴት እንደዋለለት እንመልከት፣፣ በ እግረ መንገዳችሁም ‘ብሔር ብሔረሰብ ባንዴራዉን እያዉለበለበ በፍቅር እዮኖረ ነዉ ለሚሉዋችሁ “የወንጀለኞቹ አዳማቂዎች” ለምስኪኑ ገበሬ ያወረዱበትን ግፍ “ጉዳቸዉን እዩላቸዉና እና ፍረዱን ለናንተ ልተዉ”፣፣ እነሆ፣፤-
ልዪ ጥንቅር- ጦቢያ ቅጽ 8 ቁጥር 8 1993
ምስራቅ ወለጋ
የአማራዉ ሕዝብ ዕልቂት
ባንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት
ዘጋቢ ኦርዮን
የጎሳ ግጭት እና የሕዝብ ዕልቂት ዛሬ፣ዛሬ፣ጀሮአችን፣ እንዲያም ሲል ዓይናችን እየለመደዉ መጣና እንደሌላዉ ጊዜ ብዙም የሚሰቀጥጥና የሚዘገንን ወሬ አይደለም፣፣ ዛሬ ካለንብት ጊዜ ላይ የደረስነዉ ባለፉት ዓሥር ዓመታት የበደኖን፣ የአርባ ጉጉን፣የአርሲን፣ የአደባባይ ኢየሱስን፣ የገዴኦንና የጉጂን ወዘተ፣ ግጭት እና ዕልቂት ከስደትና ከፍርሃት ጋር መኖሩን በግዱ እየተለማመደዉ ነዉ ማለት ይቻላል፣፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሌለዉ ቀርቶ ለሰልፍ የወጣዉን ተማሪ፣ ለምርጫን የተነሳ ሕዝብ፣ በጥይት መደብደብና በቦምብ መጨፍጨፍ አዲስ ነግር እየሆነ አይደልም፣፣ ሞትን እና ዕልቂትን ሁሉም ከልጅ እስከ አዋቂ እየቀመሰዉ ነዉ፣፣ “ሞት ይለመዳል? ዕልቂት ይለመዳል?” ብሎ መጠየቅ ሌላ ነገር ነዉ፣፣ ሃቁ ግን ከሞትና ከዕልቂት ጋር እየኖርን ነዉ፣፣ ቡሬ ላይ በቆየሁባቸዉ ጥቂት ቀናት የተረዳሁት ይህንን ሃቅ ነዉ፣፣
ብዙዉ ሰዉ እንዲህ በተለምዶ ለአፉ ብቻ ካልሆነ በስተቀር ዛሬ “ግጭቱን ማን ፈጠረዉ? ግድያዉን ማን ፈጸመዉ?” ብሎ መጠየቁን ትቷል፣፣የትም ይሁን የት በጎሳዎች መካከል የሚቀጣጠለዉ ኹዉከት እና ግጭት በእነማን ፍላጎትና በእነማን ግፊት እንደሚካሄድ ልቡ ያዉቀዋል፣፣
በዚህ ምክንያት፣ የዛሬዉን የሃገራችንን ሁኔታ በዉል ለምታዉቁ አንባቢያን ሁሉ በዚህ ልዩ ጥንቅር ዉስጥ የምናቀርብላችሁ ታሪክ ምን ያህል አዲስ ሊሆንባችሁ እንደሚችል እናዉቅም፣ ፣ ብቻ በዚያም በሉት በዚህ አንድ ነገር ማረጋገጥ ይቻላል፣፣ በምስራቅ ወለጋ በአንድ ዘር ላይ ተነጣጥሮ የተካሄደዉን የጭፍጨፋና የዕልቂት ባለቤት፣ እጅ ከፍንጅ ሲያዝ ታዩታላችሁ፣፣ከዕልቂቱና ከሰቆቃዉ ተርፎ ጎጃም ዉስጥ፣ ቡሬ ከሚባል ከተማ ላይ የሰፈረዉ የጎጃምና የጎንደር የሸዋ የወሎ አማራ በእንባዉና በደሙ ይናገራል፣፣ ስሙት፣፣
ቡሬ ሰፈራ ጣቢያ
መጋቢት 15 ቀን ሐሙስ፣ ከማርቆስ ተነስቼ 10 ሰዓት ገደማ ቡሬ ደረስኩ፣፣ጓዜን ከአንድ ቦታ አስቀምጨ ወዲያዉ ወደ ከተማዉ ወጣሁ፣፣ ብቻየን ነኝ፣፣ ቡሬ ብዙ አላዉቃትም፣፣የከተማዋ ዋናዉ መንገድ ቡሬን ለሁለት ገምሷት ያልፋል፣፣አብዛኛዉ የከተማዉ ክፍል ከመንገድ በላይ ዳገታማዉን ሥፍራ ይዟል፣ቀሪዉ ከተማ ከመንገዱ በታች ቁልቁል ከሚታይ ረባዳ ቦታ ይገኛል፣፣
“ሠፋሪዎቹ የት ነዉ ያሉት?” ብየ መጠየቅ አላስፈለገኝም፣፣ ከአዉራዉ ጎዳና ዳር ላይ ቆሜ ሳማትር ከወደ ረባዳዉ የከተማዉ ክፍል፣ በብዙ ሁኔታ ተመሳሳይ የሆኑ ሰዎች እንዲት መንገድ ይዘዉ ሲመላለሱ አየሁ፣፣ ወደ መሐል ከተማዉ ይመጣሉ፣፣ በዚያዉ መንገድ ወደ መጡበት ይመላለሳሉ፣፣ ሕጻናት ልጆች ያዘሉ እናቶች ሕፃናት ልጆችን የተሸከሙ ወይም እጆቻቸዉን ይዘዉ የሚጎትቱ አባቶች ዕድሜአቸዉ የገፋ ባልቴቶችና ሽማግሌዎች በዚያ መንገድ ይመላለሳሉ፣፣ “እነዚህ ሠፋሪዎች ናቸዉ” አልሁ፣፣ ጊዜዉ እየመሸ ነበርና አንዱን ቀረብ ብየ ለማነጋገር ወሰንሁ፣፣ አንድ ሕፃን ደረቱ ላይ-አቅፎ-የያዘ-ጎልማሳ-አየሁና ሄድሁ፣፣
1 ጠጋ ብየ “ሰፋሪ መሰልኸኝ!” አልሁት፣፣
2 “አዎን ሰፋሪ ነኝ” አለኝ፣፣
1 “ምን ፍለጋ ቆመሃል?”
2 “ሥራ የሰራሁለት ሰዉ ነበረ፣፣ ገንዘብ እዚህ ድረስ አመጣልሃለሁ ብሎኝ እሱን እየጠበቅሁ ነዉ፣፣”
1 ”መሽቷል ከእንግዲህ ይመጣልሃል?
2 “ከእንግዲህስ መሽቷል፣፣ከእንግዲህ እንኳን አይመጣም፣፣ የሰዉ ነገር! አለና ለመሄድ ፊቱን አዞረ፣፣
“ቶሎ ብየ ወደዚህ እንሂድና እህል እንቅመስ” አልሁት፣፣
አንገቱን ሰበር አድርጎ “እሺ” አለ፣፣
አጠገባችን ከምትገኝ ጠላ ቤት ገባን፣፣ ምግብም አለ፣፣ እንጀራ በወጥ፣ ከጠላ ጋር ቀረበልንና በላን፣፣ጠጣን፣፣እየመሸ ስለሆነ ሰዉየዉ ወደ ሠፈር ጣቢያዉ ለመመለስ ልቡ ቆሟል፣፣በዚህ ሁኔታ ዉስጥ
1 “ይሄ ሕፃን ልጅ ያንተ ልጅ ነዉ?” አልሁት
2 “እህስያ፣፣ የኔ ነዉ እንጂ፣፣”
1 “እናቱስ?”
2 “እናቱማ በጥይት ገደሉብኝ፣፣”
1 “ሴቷን ልጅ?”
2 “አዎን፣፣” “ምን ምርጫ አለ”፣፣”ሴቱን ሕጣኑን፣ ሽማግሌዉንና ባልቴቱን አይደል የፈጁት፣፣መቸ መረጡ፣፣ እና የኼዉ ጨቅላ ልጅ ታቅፌ ቀረሁ፣፣” እያለ ሕፃኑን እንደታቀፈ ለመነሳት ሽመሉን ከጎኑ ሳበ፣፣
1 “ስንት ዓመቱ ነዉ?”
2 የልጁን ዓይን እያየ “ቀረብህ?” ሁለት ዓመቱ ነዉ፣፣ እናቱ ጥላዉ ስትሞት ጊዜ “ቀረብህ” አልሁት”፣፣ እያለኝ ከቤት ወጣን፣፣ ከመለያየታችን በፊት ስለ ሠፈራዉ ጠየቅሁት፣፣
1 “የሠፈራዉ ቦታ ከዚህ ይርቃል?”
2 አቅጣጫዉን በአገጩ እያመለከተ “አረ እዚህ ነዉ! ቅርብ አይደል?” አለኝ፣፣
1 “እናንተ እንደልብ እየወጣችሁና እየገባችሁ መሰለኝ፣፣ሌላስ ሰዉ መዉጣትና መግባት ይችላል?”
2 ምን ችግር አለዉ! ይሄዉ እንደሚያዩት እኛም ስንመላለስ እንዉላለን፣፣ ሌላዉም ሰዉ ከልካይ የለዉም፣፣ይመጣል፣ ይሄዳል!”አለኝ፣፣ ድህና እደር ተባብለን ተለያየን፣፣ በሁለት እጁ ቀረብህን ደርቱ ላይ ጥብቅ አድርጎ ይዞ በቁልቁለቱ ደፋ ደፋ እያለ ሄደ፣፣
ሠፈራዉ ቅርብ ነዉ፣፣”ሌላዉም ሰዉ ከልካይ የለዉም፣፣ ይመጣል፣፣ ይሄዳል፣፣ለነገ ዜናየ ጥሩ ዜና ነበር፣፣ የካቲት እና 17-ሁለት፣ ግን አጫጭር ቀናት ነበሩ፣፣ በእርግጥ አዲዩ “ሌላዉም ከልካይ የለዉም፣፣ይሄዳል.፣ይመጣል፣፣” ሲል የነገረኝ ከልቤ አልጠፋም፣፣ ቢሆንም ሠፈራ ጣቢያዉ በሩቁ መቃኘት ቀስ በቀስ መቅረብና ገብቶ መመለከት አስፈላጊ ነበር፣፣14,000 ሰፋሪዎች እንደያዙ የሚገመቱ አረንጓዴ ድንኳኖች በሩቁ ለሚመለከታቸዉ ረድፍ ጠብቆ የበቀለ ቁጥቋጥ ይመስላሉ፣፣ ከእነዚህ ድንኳኖች ዉስጥ ለመግባት ጭንቅላት ከጉልበት መታጠፍ፣ አለዚያም መንበርከክ ያስፈልጋል፣፣ ከዉጭ የቆመዉ ሕዝብ ሲታይ ድንኳኖች ዉስጥ ሰዉ የቀረ አይመስልም፣፣ ድንኳን ዉስጥ ሲገባ ደግሞ መረማመጃ ቀርቶ ጠጠር መጣያ ቦታ የለዉም፣፣ ዓይን ተወርዉሮ ማየት እስከሚችልበት ድረስ ሰዉ አንዱ ባንዱ ላይ ተነባብሮ ተኝቷል፣፣ ድንኳን ዉስጥ ያሉት ሁሉም ማለት ይቻላል ሕፃናትና ደካማ አረጋዊያን ናቸዉ፣፣ሁኔታዉ ይሄ ነዉ፣፣
አዩኝ አላዩኝ ብሎ ጥቂት ፎቶግራፍ ማንሳት ይቻል ይሆናል፣፣ ሰዎችን መራርጦ ተስማሚ ቦታ ይዞ ለመነጋገር ግን ሁኔታዉ አይፈቅድም.፣፣ በዚህ ቦታ የሚገኙ ሁሉም ሠፋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ”ሠራተኞችም” ይኖራሉ፣፣ ስለዚህ ከሰፋሪዎቹ ቀስ ብሎ ሰዉ ማፍራት፣ በሰዉ ዕረዳታ ምሥራቅ ወለጋ ላይ የደረሰባቸዉ ችግረ መግለጥ የሚችሉ ሰዎችን ማግኘትና አመቺ ቦታ ይዞ ማነጋገር አስፈላጊ ነበር፣፣ይኼ፣ ይኼ ጊዜዉን በላዉ፣፣ዛሬ ሁኔታዎችን ተባብሰዉ ወይም ተሻሽለዉ ሊሆኑ ይችላል፣፣አላዉቅም፣፣በወቅቱ ግን ከሠፈራዉ ጣቢያ በየዕለቱ ሁለት እና ሶሦት ሬሣ ይወጣ ነበር፣፣የሚሞቱት ሕፃናት ናቸዉ፣፣
ቡሬ እንኳንስ እንግዳ ልታስተናግድበት ለራሷም የምትጠጣዉ ዉሃ የላትም፣፣ለሠፋሪዎቹ ዉሃ በቦቴ ሲከፋፈል አይቻለሁ፣፣ የሠፈራዉ ጣቢያ የመጸዳጃዉ ሁኔታ ለወረርሽኝ እና ለበሽታ መቀስቀስ በሚያመች ሁኔታ የትም ነዉ፣፣ያሳፍራል፣፣በዚህ ላይ የአማራን ትምክሕት ለመዋጋት የቆሙት የክልል ሦስት ባለሥልጣናት ለእነዚህ ከወለጋ ተቀጥተዉ ጎጃም ለገቡት መከረኞች የሚራራ ልብ ያላቸዉ አይመስልም፣፣ ዘግይተዉ እየመጡ ላሉት ለወለጋ ተፈናቃዮች ዕርዳታ እንደደረሱ አይሰጥም፣፣ “እናንተማ ከብቶቻችሁና እህላችሁ ስትሸጡ ቆይታችሁ የመጣችሁ ስለሆነ ለእናንተ ዕርዳታ እንሰጥም”-እያሉ እንደሚጨክኑባቸዉ ስደተኞቹ ያስረዳሉ፣፣
የተዋለባቸዉን ግፍ ይናገራሉ
እነዚህ ምሥራቅ ወለጋ ላይ ከተፈፀመባቸዉ ዕልቂት ተርፈዉ ዛሬ ቡሬ ሠፈራ ጣቢያ የሚገኙት የአማራ ተወላጆች ወደ ወለጋ የሄዱ በተለያየ ጊዜ መሆኑን ይናገራሉ፣፣ ባጠቃላይ ግን “በደረግ ዘመን ከኢሐዴግ በሗላ” ብሎ በሁለት ጊዜያት መክፈል ይቻላል፣፣ በእነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ወለጋ የገቡት ገበሬዎች የእርሻ ቦታ ያገኙበት ሁኔታም ይለያያል፣፣ይሁን እንጂ በሁሉም የደረሰዉ ሰቆቃ አንድ እና ተመሳሳይ ነዉ፣፣ በመሆኑም በዛ በከራ ዉስጥ ያለፉት ሁሉ ስለደረሰባቸዉ ችግር የሚናገሩት ከመርሳትና ከማስታወስ ወይም ጥቃቅን የአጋጣሚ እና የአገላለጽ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር የሁሉም ታሪክ አንድ ዓይነት ነዉ፣፣ በዚህ ምክንያት አጠቃላይ ችግሩን በተመለከተ ከአነጋገርሗቸዉ ብዙ አርሶ አደሮች ዉስጥ ሁለቱ ብቻ. አንዱ በደርግ ዘመን ሌላዉ ከኢሕአዴግ በሗላ ወለጋ የገቡ አርሶ አደሮች የተናገሩት ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፣፣
በርይሁን አያሌዉ-
“አገሬ ወሎ ነዉ፣፣ ወደ ወለጋ የሄድሁት በ1976 ዓ.ም. ነዉ፣፣ በ176 መሬቱ ጫካ ነበር፣፣ መንግሥት ግቡ አለን፣፣ገባንበት፣፣ ስንገባ ምንም አልከፈልንም፣፣ ካርኒ ቆርጠን እንገብር ጀመር፣፣መሬቱ የመንግሥት ነዉ፣፣በ76 ችግር አልነበረም፣፣
ችግሩ የመጣ አሁን ነዉ፣፣ ኢሕአዴግ ከገባ በሗላ፣፣ በድንበር እንካሰሳለን፣፣ ስንካሰስ ቀበሌ የእኛን ማመልከቻ ከስር የነሱን በላይ ያደርገዋል፣፣ ቀበሌ ጨቆነን ብለን ወረዳ ስንሄድ ፖሊስ ጣቢያ እየወሰዱ ያስሩናል፣፣ቀበሌዉና ፖሊስ ጣቢያዉ አስከ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ “እናንተ ወሎዎች! እናንተ ቋሪቶች! እናንተ ጎጃሞች!በእኛ መሬት ማን ተከራካሪና ተሟጋች አደረጋችሁ?የዕለቱ ብቻ ብሉ፣፣ እኛ አገር ዉስጥ ባፈራችሁት ማዘዝ አትችሉም፣፣ የዕለቱን እየበላችሁ ተቀመጡ፣፣ ከእንግዲህ ወዲያ ማን አስቀምጣችሗል?”ይሉናል፣፣ እናም ልጅ ሆነን መጥተን እዚህ አደግን፣፣ እዚህ ተወልዶ ያገባ ሞልቷል፣፣ እየተዛመድን ነዉ፣፣ መንግሥት የሰጠንን መሬት ለቅቀን ወዴት እንሄዳለን? ደግሞስ በገዛ ሃብታችን እና አገራችነ እንዴት እንደዚህ ይሉናል?” እያልን ቆየን፣፣ ዕዉነት አልመሰለንም ቆየን፣፣
ወደ ሗላ ነገር አመጡ፣፣ ስንከራከር ያስሩናል፣፣ገንዘብ እየከፈልን እንወጣለን፣፣ አሁን ሌሊት ሌሊት ስርቆት ተጀመረ፣፣ የሌሊት ሌባ ድሮም የቆየ ነዉ ብለን ከብቶቻችን ስንጠብቅ ፖሊስና ምክር ቤት ከላይ መጥተዉ መሣሪያ ግዙ አሉን፣፣ መሣሪያ ገዝተን “አስመዝግቡ”-ሲሉን በሕጋዊ መንገድ አስመዘገብን፣፣ከዚያ “እናንተ በእኛ አገር መሣሪያ ልትይዙ አይገባችሁም” ብለዉ ሕግ አስመስለዉ ገፈፈዉ እዚያዉ ለእኛ ጓደኞች ለወረሞዎች አስታጠቋቸዉ፣፣
“ከብቶቻችን ሌሊት ሌሊት ይሰርቁ ጀመር፣፣ወደ ሗላ ቀን ቀን መዝረፍ ተጀመረ፣፣ “ከብቶቻችንን ለምን ትወስዳላችሁ?” ስንል እረኞቹን ገደሉብን፣፣ ምን እናድርግ እያለን ሳለን አንደገና “ተረጋጋ” -አሉን፣፣ መሣርያ ግዙ እና ሃብታችሁን ጠብቁ፣፣ከእንግዲህ ነገር የለም፣፣ የንብረታችሁ ጌታ ናችሁ” ሲሉን መለስን መሣርያ ገዛን፣፣ተነሱ አገር የነሱ መሣሪያ ነዉ የገዛነዉ፣፣ “አስመዝግቡ”-አሉን፣፣ አስመዘገብን፣፣ አሁንም ሁለተኛ ገፈፉን፣፣ “ከብቶቻችን ከተዉልን ደግ ነዉ”-ብለን ዝም ብለን ተቀምጠን “ሕጉንም ከላይ እንዳልሆነ አይተነዋል”፣፣ “”አቸንፈዉናል፣ተቸንፈናል” ብለን ተቀመጥን፣፣ እንዲያ ተቀምጠን እያለን ባለሥልጣኖች መጥተዉ “እናንተ እንግዲህ ያለባችሁ ወደ ክልል ሦስት መግባት ነዉ፣፣መግቢያችሁ ደረሰ፣፣ሃብትም ከዚህ ይዛችሁ አትሄዱም፣፣ አመላችሁን አሳምራችሁ ሹልክ በሉ፣፣ካልሸሎካችሁ ሕይወታችሁ ይጠፋል”አሉን፣፣መንግሥት እንዲህ ያደርግ አልመሰለንም፣፣አሁን ከብቶቻችንን ቀን ቀን ይዘርፉን ጀመር፣፣ ለመከላከልም አቅም አጣን፣፣መሣሪያችን ተገፍፈናል፣፣ ከዚያ በሗላ “ተነሱ” አሉን፣፣በቃ የሚገድሉትን “ገደሉ፣፣ ገደሉ፣፣ ገደሉ፣፣”’
ይህ የሆነዉ ሕዳር 21 ቀን ነዉ፣፣ ወረዳዉ በፊት መጥቶ ፈተሸ፣፣ ከዚያ ሠራዊት መጣ! ከየት እንደመጣ አናዉቅም፣፣ የታጠቁ ናቸዉ፣፣ “እቤትህ እንዳትቀር” እያሉ ገበሬዉን ጨምረዉ እነሱ ከፊት ከፊት ገበሬዉ ከሗላ ሆነዉ ሕዝብን ጨፈጨፉት፣፣ አጠፉት ከሞት የተረፈዉን ወደ እስር ቤት ወሰዱት፣፣ ከዛ እየሾለክን ሆሮ ከሚባል የመስመር ቦታ ላይ ተሰባሰብን፣፣ ያልተነሱት ቀበሌዎች እየደበደቡ ከኛ ዘንድ አመጧቸዉ፣፣ እዚያ ታክተን ቆየን፣፣ ሕጣናት በረሃብ እየተሰቃዩ ሞቱ፣፣ ደካሞች ሞቱ፣፣ ትንሽ አቅም ያለዉ እየሾለከ ከዚህ ደረስን፣፣
“ከ15 ያላነሱ የቀንድ ከብቶች፣ 12 ፍየሎች፣ አንድ አህያ ነበሩኝ፣፣እኩሌታዉ እዛ ቀረ፣፣ እኩሌታዉ ዓባይን እስክሻገር ድረስ ዝርፍያዉ አላቆመም ነበርና ወሰዷቸዉ፣፣ እህሉ ሁሉ እዛዉ ቀረ፣፣ መሣሪያ ነበረኝ፣፣ወሰዱት፣፣ስድስት ልጆች አሉኝ፣፣ሁሉንም ይዤ መጥቻለሁ፣፣”
ዓለሙ መኮንን
ከጎንደር በ1990-ነዉ ወደ ወለጋ የሄድሁ፣፣ መርጃ ጂረኛ ቀበሌ እኖር ነበር፣፣ መንግሥት “መሬት ባለቤት መሥርተህ ብላ” የሚል መስሎን ነበር፣፣ መጀመሪያ ስንደርስ ለመመዝገቢያ ሁለትም ሦስት መቶ የከፈልን አለን፣፣ያን ካስከፈሉን በሗላ ለባለ መሬት ያስተላልፍናል፣፣ባለመሬቱ መሬት ሰጥቼሃላሁ ይልና እንደመሬቱ መጠን ሁለትም ሰሦትም ሺሕ ብር ይቀበለናል፣፣ ከዚያ መሬት ይዘን እናርሳለን፣፣ ቀደም ብለዉ የሄዱት ተመርተናል ይላሉ፣፣
“መሬት ከሰጠን በሗላ ገንዘቡ ሲያልቅ ለመክሰስ ይነሳሉ፣፣ከገበሬ ማሕበር የክስ ደብዳቤ ይመጣል፣፣አክብረን መልስ ይዘን እንመጣለን፣፣ “አልተስተካከለም” ብለዉ ኪሳራ ይቆረጥብናል፤፤ የምናቀርበዉ መልስ አይታይም፣፣ እንታሰራለን “ዋስ ጥሩ” እንባላለን፣፣ አማራ መሬት ስለሌለዉ ዋስ አይሆንም ይሉናል፣፣ሌሎችን በ ሺ ብር እየገዛን ዋስ እንጠራለን፣፣ ከሳምንት በሗላ “ቅረቡ” ይሉናል፣፣እንቀርባለን፣፣ዋሳችን “ዋስትናየን አዉርጃለሁ” ይላል፣፣ ሺ ብር የከፈልነዉ ዋስ፣፣ታሰሩ እንባላለን፣፣ ሌላ ሺ ብር ከፍልን ዋስ እንጠራለን፣፣
በዚህ ስንማረር፣ በሗላ ስርቆት ተጀመረ፣፣ ስርቆት ይባላል እንጂ ዘረፋ ነዉ፣፣ ከግንቦት አስከ ሐምሌ 1992 ዘረፋዉ ቀጥሏል፣፣ሐምሌ 7 ቀን በሬ ተሰረቀ እረ!እሪ! ተባለ፣፣ተሰበሰብን፣፣ “ምን እናድርግ ምን ይሻላል?”ተባባልን፣፣ይህን ሁሉ የሚሰራን የገበሬ ማሕበሩ ሊቀመንበር ወይም ፀሃፊዉ ነዉ፣፣ታጣቂዎች ናቸዉ፣፣ በሬአችን እናስመልስ ብለን ከፀሐፊዉ ዘንድ ሄድን፣፣ ፀሃፊዉ “ደረጀ መለስ”ይባላል፣፣ እየሄድን እያለ የአየለ አዱኛ ቤት ተዘረፈ፣፣”ኡ!ኡ! ተባለ”፣፣የሄድነዉም ተመልሰን መጣን፣፣ከላይ እና ከታች ያለዉ ሰዉ ተሰባሰበ፣፣ እንዳጋጣሚ ቶክስ ተተኮሰና ሁለት ሰዉ ቆሰለ፣፣ ይህ የተፈፀመዉ ሓምሌ 8 ቀን ነበር፣፣ሓምሌ 10 ቀን “የበላይ አካል ነን” ብለዉ መጡ፣፣ ይህን ሁሉ የሚሠራን የበላይ አካል እየተሰኘ ነዉ፣፣ይህን የሰራን የመንግሥት አካል ነዉ፣፣ ገበሬዉ አይደለም፣፣ልንጮህለትም አቅቶናል፣፣ “እኛ እንግዲህ ይህን መንግሥት ብለን መቀመጥ እንችላለን? ዳኝነትስ እንዴት አለ ማለት ይቻላል?” ስንባባል፣ ሐምሌ 19 ቀን የበላይ አካል ተወካዮች መጡ ተባለ፣፣ ትክክለኛ ዳኞች ናቸዉ ሲባል ጊዜ ገበሬዉ ተሰበሰበ፣፣ ከክፍለሃገር፣ፖሊስ፣ከገበሬ ማሕበር የመጡ ናቸዉ፣፣
“የወረሞ ገበሬዎች ሣር አጨዱ፣ ደን ጨፈጨፉ ይሏችሗል” አሉን፣፣”መሬት ‘ሰጡን’ አረሱተ፣ እንጨቱን ቆረጡት ሣሩን አጨዱት አሉን፣፣አረስን ፣አጨድን፣ ቆረጥን፣፣ ይሄ ምን ጥፋት ሆኖ ይታያል፣፣?”አልን፣፣ “የእኛ ጥፋት ነዉ ብላችሁ እመኑ”ተባልን፣፣ “እረሱ ባልተባልን እንጂ ይሄ እንዴት አድርጎ ጥፋት ይሆንብናል?”ብለን ብዙ ተጨቃጨቅን፣፣ አሁን እናንተ ጥፋታችሁ በትክክል ካላመናችሁ፣ጥፋተኛ ንን ካላላችሁ “የወረሞ ክልል እናንተን ሊቀበላችሁ አይችልም” አሉን፣፣ እንዲህ ከሆነማ ምን እናደርጋለን? “በደለኛ በደለኛ ወታደር በደለኛ፣ ግን ቢሆንም ባላገር ይካስ”ከተባለ ይሄ በደል ከኛ ከሆነ ሣሩንም አጭደነዋል እንጨቱንም ቆርጠነዋል፣፣ ያዉ ለእንጀራ ብለን ነዉ፣፣ አልናቸዉ፣፣ ይሄ ጥፋት ነዉ ከተባለ ተቀብለነዋል አልን፣፣ወረሞዎችም ጥፋታችን ነዉ ብለዉ አመኑ፣፣
“ከእንግዲህ ተስማምታቸሁ ኑሩ ተብለን ሽማግሌዎች ከወረሞም ከአማራም ተመረጡ፣፣ የጠፋዉ ሁሉ በቅንጅት እንዲመለስ ተባለ፣፣ “አገሪቱ ኢትዮጵያ የሁሉም የጋራ ናት፣፣የወረሞም የአማራም ብቻ አይደለችም፣፣ አገሪቱ የጋራችን ናት፣፣ እኛ የሁላችሁ ዳኞች ነን” አሉን፣፣ ሽመግሌዎች ሲደክሙ ራቦር(ሪፖርት) ሲተላለፍ ቆየ፣፣ እኛ ቋንቋዉን አናቀዉም፣፣ ይሄ ሲሆን ብዙ ቆየ፣፣ እሱስ ሲመክሩ ቆይተዋል፣፣
‘ሕዳር 21 ቀን የማርያም፣ ዲቡክ ማርያም በዓል ነበር፣፣ወረዳዉ ‘ተሰብሰቡ” አለና ጠራ፣፣ለበዓሉ የመጣ ሰዉ ሁሉ አለ፣፣ ወረዳዉ እኔም በአካል አዉቀዋለሁ፣፣አሰፋ ፋይሳ ይባላል፣፣ ሌሊት ከምሽቱ 5-ሰዓት ገብቶ ነዉ ያደረ፣፣ የአካባቢዉ ሰዉ ይሰበሰብ ጀመረ፣፣ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ይሆናል፣፣ መትረየስ ጠምዷል፣፣ ሰዉ ሲሰበሰብለት፣ “በመትረየስ አጨደዉ”፣፣ ዓመት በዓልም ስለነበረ ተሰበሰበዉ ሰዉ ብዙ ነበር፣፣ አብረዉት የነበሩ ሁሉ ቶክስ ከፈቱ፣፣ ቶክስ ሲከፈት ሰዉ በየአቅጣጫዉ ሮጠ፣፣ ላዉንቸር አለ፣፣የማላዉቀዉ የመሣሪያ ድምፅም ነበር፣፣ ሲተኩሱ ሲገድሉ ዉለዉ ሄዱ፣፣ ሕዳር 21 ቀን ጥይት ሁሉ የሚተኮስ ከነሱ ነበር፣፣ ግን ከዚያም ወገን ሰዉ ሞቷል አሉ፣፣
“ሕዳር 25 ቀን እንደገና ጦር ተጭኖ መጣ፣፣ሠራዊት ነዉ፣፣መትረየስ፣ከላሽ ላዉንቸር ታጥቀዋል፣፣ቁጥሩ አይታወቅም፣ በቅጠሉ ቁጥር ነዉ፣፣ ብዛቱ ይነገር ቢባል 500 እና 600 ይሆናል፣፣ሰዉን ይገድል፣ቤትን ያቃጥል ጀመረ፣፣ በያካባቢዉ ሰዉ እየያዘ ገደለ፣፣ እኔ እንኳ በማዉቀዉ ብዙ ሰዉ ሞተ፣፣ከሕዳር ማርያም ጀምሮ ያለቀዉን ሰዉ እግዚሔር ይቁጠረዉ፣፣ እኔ እንኳ የማልረሳቸዉ ቁጥር የላቸዉም፣፣ “ገበያ ሙሉነህ፣ፈጠነ ገብሬ አያል አዱኛ፣ ጋሻዉ እዉነቱ፣ ጋሻየ ጌቴ፣ ይበልጤ መንግሥቴ፣ ይበልጤ ድረስ፣ አዘዘ ይበልጤ፣ይግዛዉ ታምራት፣አሻግሬ ገበየሁ፣ አስረግደዉ ዉቡ፣ ተስፋዬ አለማየሁ፣ ሰጤ ወርቅዬ፣ መልካሙ ዉባለም፣ ዉብ ሞንሟኔ፣ምሕረት እዉነቱ፣ ቢራሪ ታደሰ፣ ደስታዉ አብተዉ አባ በላይ ቃለ፣ ….አረ ስንቱ! ያለቀዉ ቁጥር ለዉም፣፣
እኔ ድሮ የማዉቀዉ በሃይለስላሴ ዘመን ደርሻለሁ፣ በደርግም አልፌአለሁ፣ ቤቱን ከፍቶ የሚቆይ አማና ሰዉ አይደበደብም፣፣ አይገደልም፣፣ ሰላም ነዉ ብለዉ ከቤታቸዉ የተቀመጡትን ሰዎች “ከክልል ሦስት ነን የመጣን፣፣ከባሕር ዳር ነን የመጣን፣፣” እያሉ ቤቱን ከፍቶ ሲያገኙት ያዉ መግደል ነዉ፣፣ገደሉት፣፣ ቤቱን በእሳት፣ክምሩን በእሳት አነደዱት፣፣ሰዉን በጥይት ፈጁት፣፣የሞተዉ ቁጥር የለዉም በሺ ነዉ፣፣ እስከ ሕዳር 27 እና 28 ድረስ ዕልቂት ነበር፣፣ ይተኩሳሉ፣፣ይገድላሉ፣፣
የተቀመጠዉን በዱላ፣የሮጦዉንም በጥይት ይሉታል፣፣ልጅም፣ ህጣንም፣ሴትም ዱላ የበዛበት “ፈቀቅ ሲል”በጥይት ነዉ፣፣ወንጀሉ ይሄ ነዉ አይባልም፣፣ጥያቄም የለበትም፣፣”ከመስመር ያለዉን አማራ በጠቅላላ አጥፉ ነዉ የተባልነዉ” አሉ፣፣ ወደ ድሬ ወደ ሃሮ የሚያወጣ መንገድ አለ፣፣ ከዚያ ወዲህ ሰባት ገበሬ ማሕበሮች ነን፣፣ እነዚያ በሙሉ “እንዲጠፋ ታዝዘናል”ይሉ ነበር፣፣“ትዛዝ ነዉ አባቴንም ባገኝ አልምርም፣፣ሁላችሁን እናጠፋችሗለን”አሉ፣፣ አጠፉን፣፣የተቀበረም-የለም፣፣ያለቀሰም-የለ፣፣ንብረትም-እዛዉ ከሰለ፣፣ሕይወትም እዛዉ አለቀ፣፣”
ከዕልቂቱ አስከፊ ገጽታ በከፊል፣-
(1) “ጌጣ ጌጡን አይተዉ አንቀልባዉን ለመዉሰድ በሃይል ጎትተዉ ሲፈቱት የሁለት ዓመት ሕፃን ከእናቱ ጀርባ ከሚነደዉ ቤት ደጃፍ ላይ ወድቆ በእሳት ተቃጥሎ ሞተ፣፣”
(2) “መልካሙ ዉባለም የተባለዉን ገድለዉ ምላሱን አዉጥተዉ ወሰዱት፣፣”
(3) አስረግደዉ ዉቡ የተባለዉን በጥይት አንካሴ አንገቱ ላይ፣ ወገቡ ላይ እግሩ ላይ ቸክለዉበት ሄዱ፣፣
(4) አንድ ሴት ሦስት ልጆቿን አስከትላ ስትሸሽ ወንዝ ላይ ስትደርስ በጥይት ገደሏት፣፣ ሦስቱ ልጆቹ በርረዉ ወንዝ ዉስጥ ገቡና እዛዉ ሞተዉ ቀሩ፣፣”
(5) አባ በላይ ዋለ የተባሉትን ዓይነ ሥዉር ገደሏቸዉ፣፣ አማራ! አማራ ነዉ! ብለዉ ብልታቸዉን ቆረጡት፣፣”
(6) መልካሙ ዉባለም አርደዉ ገደሉትና ምላሱን አዉጥተዉ ወሰዱት”
ማጠቃለያ፣- ፖሊሲዉ አማራን ማስወጣት ብቻ ሳይሆን አማራ እንዳይገባም ይከለክላል፣፣ ባለዉ የጎሳ ፖሊሲ መሠረት በአሁኑ ጊዜ የአማራዉን ተወላጅ እየጨፈጨፉና እያሳደዱ ከወለጋ ማስወጣት ብቻ ሳይሆን ወደ ወለጋም እንዳይገባም እገዳ እየተደረገ ነዉ፣፣ ከአንድ ወር በፊት ወለጋ ይኖሩ ከነበሩ አማራዎች ዉስጥ ዘመድ ጠይቀዉ ለመመለስ ጎጃም መጥተዉ ነበር፣፣ የካቲት 14 ቀን 1993ወደ ነበሩበት (ወለጋ)ለመመለስ በሦስት መለስተኛ አዉቶቡሶች ተሳፍረዉ ሄዱ፣፣ ኪራሞ ላይ ሲደርሱ 10የሚሆኑ የኦሮሞ ፖሊሶች አትሄዱም ብለዉ መለስዋቸዉ፣፣ ይሁን እንጂ ከሦስቱ አቡቶቡሶች አንዱ፣ የሰሌዳ ቁጥር 3-13316የሆነዉና የአቶ ተሻለ ዓለማየሁ በተባለዉ ሾፌር የሚነዳዉ በአጋጣሚ አልፎ ሄደ፣፣ ሁለቱ የሰሌዳ ቁጥር 3-39522-በአቶ ቴዎድሮስ ዘርዓይ የሚነዳዉና አቶ አምሳሉ ወርቅነህ የሚያሽከረክሩት የሰሌዳ ቁጥር 3-13282-አቶቡሶች ሰዎችን እንደጫኑ ተመልሰዋል፣፣ ቤተሰቦቻቸዉ ወለጋ፣ እነሱ ክልል ሦስት!!!/--/
በወያኔ ጎሰኛ ስርዓት የተካሄደዉ “የጎሳ -ጽዳት/ዕልቂት”የወያነ ትግራይ “ፖሊሲ/ሕገ መንግሥት” መንስኤዉ አይደለም የምትሉን ካላችሁ “ግፍ የተዋለባቸዉ አማራዎች በእንባቸዉ የመሰከሩት ማሕደር፣ዉሸት ከሆነ ይሄዉ ደግመን ለክርክሩ ጥሪ እናደርግላቸዋለን፣፣ሕሊናቸዉ በጎሰናነት የተበከለዉ የትግራይ ሊሂቆችምኤሊቶችም በዚህ አጋጣሚ ይህ ሰነድ ካነበቡ በሗላ “አንድ ዘር ነን እና አንጨፋጨፍም” “በወያኔ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሳ አልተጋደለም”የሚሉት ሰንካላ መከላከያቸዉ ከዚህ እንደሚማሩ እና መስመራቸዉም እንደሚያስተካክሉ ተስፋ አደርጋለሁ፣፣
“ጻድቃን፣ዓለምሰገድ፣አረጋሽ፣ተክለሃይማኖት፣ዓዉዐሎም፣ስየ፣ መለስ ፣ስብሓት፣ጸጋይ፣ ገብሩ ወ ዓረና”-ምንትስ ምንተስ የምትሏቸዉ ሁሉም በደም የታጠቡ የሲአይኤ ባለጌዎች ናቸዉና የወንጀሉ ነዳፊዎችና ተጠያቂዎች ስለሆኑ የትግራይ የሕግ ባለሞያዎች ከሌሎቹ ጋር ተባብራችሁ ይህ ወንጀል ሲፈጸም በሃለፊነት የሚጠየቁት ሁሉ ወደ ፍርድ የሚቀርቡበት መንገድ መሻት ሲገባችሁ “ያገራችን ሕዝብ ጨዋ ነዉ- አይጋደልም፣ አይበታተንም …” የሚለዉ ያረጀ ያፈጀ መሸፈኛ ትተን በነባራዊዉ ላይ እንረባረብ፣፣ የወያኔ ፖሊሲ ከመደግፍ ታቀቡ፣፣ ኢትዮጵያ ፍትሕ ትጠብቃለች ጌታቸዉ-ረዳ-ሳንሆዘ-ካሊፎረኒያ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
No comments:
Post a Comment