የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮመቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂ፣ ደሞዝ እና መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንዳይነጠቁ ተደርጓል
ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ምክንያት፣ባለፈዉ ሰሞን በአቶ አበበ በለዉ የአዲስ ድምፅ ራዲዮ ፕሮግራም ከሦስት የትግራይ ተወላጆች ጋር የተደረገዉ ቃለ መጠይቅ ቅጅዉን ሳዳምጥ፣ ከእንግዶቹ አንደኛዉ የመለስ ዜናዊ አመራር አረመኔነት ከዘረዘረ በሗላ የስርዓቱ ጨካኝነት ለማሳየት ምሳሌ የተጠቀመበት በእነ ገብሩ በእነ አረጋሽ እና ጓዶቻቸዉ የተደረገዉ ኢሰብአዊ እርምጃ በማዉሳት “እንኳን ሌላዉ አብረዋቸዉ ለታገሉት የቅርብ ጓዶቻቸዉ እንኳ ከድርጅቱ ሲያስወጧቸዉ ያለ ምንም መጠለያ እና ደሞዝ ነበር መሃል ሜዳ የጣሏቸዉ”የሚል ዓይነት እንደምታ ሲነገር በመስማቴ፣ እኔ ከያዝኩት ሰነድ ጋር ሳገናዝብ ታሪኩ ተቃራኒ እንደሆነ ስለተገነዘብኩ፣ በእጄ ላይ የሚገኝ በቴፕ/በደምፅ የተቀረጸ ስለ ጉዳዩ የሚያስረዳ ማለትም እነ ጸጋይ በርሄ እና ዓባይ ወልዱ የተባሉት የትግራይ የወያኔ ከፍተኛ ሹሞች “በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማሕበር”ብሎ ራሱን የሚጠራ የመለስ ዜናዊ ደጋፊ አካል ባዘጋጀዉ “የወያኔ ባዓል”ለማክበር በእንግዳነት ተጠርተዉ በ2005(በፈረንጅ) ወደ አሜሪካ መጥተዉ በነበሩበት ወቅት የተባረሩት የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ሲባረሩ የክብር ጠባቂዎቻቸዉ እና ደሞዝ እንዲሁም በነጻ ሲኖሩባቸዉ የነበሩባቸዉን መኖርያ ቤቶቻቸዉ እንደያዙ ሳይነጠቁ እንዲባረሩ እንደተደረገ ለተሰብሳቢዉ በቃላቸዉ አረጋግጠዋላቸዉ እንደነበር ማስረጃዉ ያረጋግጣል።
.የወያኔ ሹሞች ጉዳዩን አስመልክተዉ ሲያብራሩ፤ ይህም እንዲደረግ የሆነበት አንደኛዉ ምክንያት ይላሉ ‘ምናልባትም ከጊዜ በሗላ ወደ ልቦናቸዉ ይመለሳሉ የሚል እምነት ስለነበረ፣ ባይመለሱም “አብረዋቸዉ የታገሉ እና አብረዉ ብዙ ዉጣ ዉረድ ያዩ ጛዶቻቸዉ ስለሆኑ በሌላ ተቃዋሚ ሃይል እንዳይገደሉ ወይንም ላስቸጋሪ ኑሮ እንዳየይጋለጡ በሚል ድርጅታዊ ሰብአዊ እና ጓዳዊ ርህራሄ መሰረት በማድረግ እንደተወሰነ የሚገልጽ እንግዶቹ እዚሁ ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ እና ዋሺንግተን-ዲሲ ድረስም መጥተዉ ያረጋገጡትን ከሁለቱም የዕለቱ እንግዶች የተገለጸዉ ገለጻ በትግርኛ የተቀረጸዉ የቴፕ ድምፅ (ሰነድ) ወደ አማርኛ ተርጉሜ ከዚህ በታች ሳቀርብ፣- ‘የፀጋይ በርሄ አነጋገር ሁሌም ለጽሁፍ ቅንብር የማይመች ዝርክርክና የተተበተበ አነጋገር ስለሚጠቀም ለፅሁፍ አንባቢ እንደሚገባ በመጠኑ ተስተካክሎ እንዲቀርብ አድረጌአለሁ፣፣ የተስተካከለዉ ግን የአረፍተ ነገሮቹን ቅደም ተከተል አሰካክ እንጂ ቁም ነገሮቹ እንዳሉ የተናጋሪዎቹ መልሶች ናቸዉ፣፣
ከዚህ በተጨማሪ፣- “እነ ገብሩ….” እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከስራ ሲባረር ደሞዙ እንዳጣዉ ሁሉ እኛም ከህወሓት ድርጅታዊ ስራ ስንሰራ ቆይተን ስንባረር መንግስት ምንም የተለየ ጠቀሜታ አላደረገልንም፣ አልተንከባከበንም፣ የሚሉ ከሆነ ያዲስ ድምፅ አዘጋጅ ሁለቱንም ተቃራኒ ክፍሎች (እነ ፀጋይ በርሄ እና እነ ገብሩ) በእንገድነት ጠርቶ ትክክለኛ ታሪኩን ለሕዝቡ እንዲያስደምጡን አጋጣሚዉን በመጠቀም አደራ እላለሁ። ይህ ጎሰኛ አድልዎ የሚያሳየዉ ጎሰኞች ምንም ያህል ቢራራቁና ቢጣሉ በመከራ ሰዓት እርስበርሳቸዉ ጥለዉ እንደማይጣጣሉ ህያዉ ማስጃ ነዉ፣፣ ለዚህም ነዉ ጎሰኝነትን አጥብቀን የምንዋጋዉ፣፣ ሰነዱም እነሆ።-
የመድረኩ አዘጋጅ ከተሰብሳቢዎቹ የተሰጠዉ ጥያቄ እነ ጸጋይ በርሄን (ሃለቃ ፀጋይ) እና ዓባይ ወልዱን (ዓባይ ዴራ) እንዲመልሱት ባቀረበላቸዉ ጥያቄ ልጀምር።
ጥያቄ፣-
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር አባሎች የነበሩ በተፈጠረዉ ሁኔታ ከድርጅቱ ተባሯል፣፣ ሲባረሩ ለደህንነታቸዉ ጥበቃ፣ መኖርያ እና ደሞወዛቸዉን በሚመለከት የተወሰደ እርምጃ ካለ ብትገልጹልን?
ዓባይ ወልዱ፣-
…..ጥያቄዉ በተደጋጋሚ ለኛም ቢሆን ትግራይ ድረስ መቀሌ ድረስ ዉጭ የሚኖሩ አንዳንድ ወንድሞች ስልክ እየደወሉ ለምን ባዶ ሜዳ ላይ ያለምንም መተዳደርያ ጣላችሗቸዉ እያሉ ይጠይቁናል። ሁኔታቸዉን በሁለት መንገድ በመመለከት ዉሳኔ አድርገናል። አንደኛዉ ለደህንነታቸዉ ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ አስፈላጊነት ነዉ። ይኼዉም እንደምናየዉ “መጥፎ ትካል” (የተጠቀመበት ትግርኛ )/ (ከወያኔ ዉጭ ሌሎች “መጥፎ” ድርጅቶች/ቡድኖች) አደጋ እንዳያደርሱባቸዉ በማሰብ ጥበቃቸዉ ልክ እንደ ድሮዉ “ሴኪሪቲዉ” በቦታዉ እንዳለ ሆኖ “የትም ይኑሩ የትም ( የተግርኛዉ “አብዝሃለዉ ይሃሉዉ”)በሚኖሩበት አካባቢ ስጋት እንዳያድርባቸዉ ለማረጋገጥ አስፈላጊ ጥበቃ ይደረግላቸዋል።
ሁለተኛ “መኪኖቻቸዉ ተነጥቀዉ በእግራቸዉ እንዲጓዙ ተደርጓል” “መኖርያ ቤቶቻቸዉ ተነጥቀዉ አልባሌ ቦታ ወድቀዋል… ወዘተረፈ”የሚል እሮሮ እንሰማለን። ይሄ ለፕሮፖጋንዳ እንዲጠቀሙበት ራሳቸዉ የሚያወሩት ካልሆነ በስተቀር በእኛ በኩል የምናዉቀዉ እና የሚወራዉ ዉሸት ለየብቻ ነዉ። በጣም የሚገርመዉ በመንግሥት የተሰጣቸዉ መኪና እቤታቸዉ ግቢ ትተዉ በእግር ሲጓዙ የሚታዩበት ሁኔታ እኛም ታዝበናል። ይሄ ግን ሆን ብለዉ ራሳቸዉ ያደረጉት ነዉ።
መኖርያ ቤት በሚመለከትም ከተጠበቀላቸዉ ከሌሎቹ ጥቅማጥቅሞች የተለየ አይደለም። መኖርያ ቤቶቻቸዉም ቢሆን ሁሉም ሲኖሩባቸዉ የነበሩት መኖርያዎች ሁሉ እንዲኖሩበት ተደረጓል።መኪናቸዉ፣መኖርያ ቤቶቻቸዉ የነበራቸዉ ጥበቃ እና ደሞዝ ከቦታዉ ላይ እንዳለ ነዉ።ከሚኖሩባቸዉ ቤቶች አንድም ሰዉ ልቀቅ የተባለ የለም። እነሱም እንዲናፈስ የሚፈልጉት ወሬ ነዉ።
ለምሳሌ እንቅስቃሴአቸዉን በሚመለከት ብንመለከትም፣ እንደማንኛዉም ዜጋ በነፃ የትም መዘዋወር መንቀሳቀስ ይችላሉ፣ እየተንቀሳቀሱም ነዉ። ወደ ፈለጉበት ቦታ/ አገር ስልክ መደወል ይችላሉ፣በፈለጉበት መዉጣት መግባት ዉጭ አገር መሄድ መመላለስ ችለዋል። እኛ የምናዉቀዉ ሙሉ ነፃነታቸዉ እቦታዉ ላይ እንዳለ ነዉ የምናዉቀዉ። አገር ዉስጥ ያለ ሰዉ በዓይኑ የሚያየዉ ጉዳይ ነዉ። ለምሳሌ ከዚህ ከዉጭ ወደ እኛ እየደወሉ”መኪኖቻቸዉ ደሞዛቸዉ መኖርያ ቤቶቻቸዉ ነጠቃችሗቸዉ!ለምን እንደዚህ ታደርጋላችሁ?”እያሉ ይደዉሉሉናል። ይህ ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ዉሸት ዉጭ አገር ላሉ ዜጎች ሆን ተብሎ እንዲራባ እና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙበት እንዳሉ ነዉ እንየተገነዘብን ያለነዉ። ስለዚህ ወሬዉ ዉሸት ነዉ። ኑሮአቸዉ ድሮ ከነበሩበት የተለወጠ ወይንም የተቀነሰ ነገር የለም።
የመድረኩ አስተናጋጅ -ጥያቄ፣-
ጓድ ፀጋይ! ጓድ ዓባይ ባለዉ ላይ ተጨማሪ ካለህ?
ፀጋይ በርሄ.- ቡዱኑ (አንጃዉ) ከመገንጠሉ በፊት እያንዳንደቸዉ ሲኖሩበት ከነበረዉ ኑሮ የተቀነሰባቸዉ ነገር የለም፣፣ እንዳለ ነዉ፣፣ ጥበቃዉ፣መኖርያ ቤታቸዉ፣ደሞዛቸዉ እንዳለ ነዉ፣ አልተነካም፣፣ ለምሳሌ የገብሩ አስራትን ሁኔታ ብንመለከት “ወደ ሌላ ስራ ተዛዉሮ እንዲሰራ ሆኖ” ደሞዙም፣ጥበቃዉም፣ መኖርያዉም እንዳለ፣ እንደነበረ መሆኑ ይታወቃል፣፣ ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ በማሃሉ “መኖርያዉን ነጠቁት!የሚል ወሬ ተነዛ፣፣ ይህ ሲሆን ግን ለምሳሌ ገብሩ በቅርብ ጊዜ ከነበረበት መኖርያዉ ለቅቆ በራሱ ፍላጎት ወደ ሌላ መኖርያ ሄዷል የሚል ወሬ ሰምተናል፣፣ ገብሩ ከሚኖርበት መኖርያዉ “ዉጣ” ያለዉ ሰዉ ወይንም አካል የለም፣፣
በጥበቃዉም በኩል አሁን የምኖርበት መኖርያ ጠበብ ያለ ስለሆነ ከጠባቂዎቼ መርጬ የሚሰናበቱ አሰናብቼ የማስቀራቸዉንም አስቀራለሁ ብሎ ደህንነቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ጥበቃ ዘቦቹ መሃል መርጦ የሚፈልጋቸዉ አስቀርቶ ያልፈለጋቸዉ ጠባቂዎቹን ያሰናበታቸዉ ሁኔታዎች አሉ፣፣ ስለዚህ ቦታ ጠበበኝ ወዘተ…እያሉ ራሳቸዉ ከሚኖሩበት ሁኔታ የሚለቁበት ሁኔታ እንዳለ እናዉቃለን፣፣
ያም ሆነ ይህ በዚህ በኩል እኛ የወሰድነዉ ቀና እርምጃ እነኚህ ሰዎች ባለፈዉ ትግል ዘመን ጓዶቻችን የነበሩ ናቸዉ፣ እንደሰዉ (እንደሰባዊ ፍጡርነታቸዉም)መጠንም እንዲጎዱ የሚፈልግ ግለሰብም ሆነ መንግሥት የለም፣፣ ስለዚህ አሁን የያዙት አካሄድ ግን ሕዝባችንና ድርጅታቸን የሚበትን አካሄድ ነዉ እየተከተሉት ያሉት፣፣ ስለሆነም፣ ሁለት አማራጮች አስቀምጠናል-አንደኛዉ አማራጭ አሁንም የነበረዉ ትግል ፈር ተከትለዉ ወደ ህዝባቸዉ እንዲመለሱ ወደ ሕሊናቸዉ እንዲመለሱ ፣ ከስህተታቸዉ ተምረዉ እንዲቀላቀሉና ልዩነታችንን ይዘን አብረን እንድንጓዝ የማድረግ ጥረታችን ይቀጥላል፣፣
ሁለተኛዉ አማራጭ-እኔ እንደምረዳዉ እየተከተሉት ያለዉን መንገድ ድርጅታችንና ሕዝባችንን ወደ አደገኛ ጉዞ የሚያስገባ ሁኔታ እተከተሉ ስለሆነ እንታገለዋለን፣፣ እየታዘብነዉ/እያስተዋልነዉ ያለዉ ግን የተዛባ የጨለማ ጉዞ ግን ይበልጥኑ ወደ ዉስጥ እየገቡበት እንዳሉ ነዉ እየታዘብነዉ ያለነዉ፣፣ ስለዚህ ከዚህ ጉዟቸዉ ወደ ቀና መንገድ እንዲመለሱ እንጥራለን፣፣ ያ ክልሆነ ግን ሕዝቡም ካድሬዉም መታገሉ የማይቀር ነዉ፣፣ እየታገላቸዉም ነዉ፣፣”በማለት የነገብሩ፣ ተወልደ፣አረጋሽ አዳነ፣ ዓለምሰገድ ገብራምላክና የመሳሰሉት ወያኔ ለሁለት ተከፍሎ ሲባረሩ አንደማንኛቸዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለ ምንም መጦርያ እንደሚባረረዉ ሳይሆን የነበራቸዉ ጥበቃ እና ክብር ከነ ደሞዛቸዉና ነጻ መኖርያ ተለግሶላቸዉ ነበር የተሰናበቱት፣፣ በኔ በኩል ይኼዉ የያዝኩትን ማሕደር ይሄዉና በእናንተ በኩል በጉዳዩ ተቹበት፣፣ጎሰኛ እርስ በርስ ምን ያህል መጨካከን እንደማያስችለዉ ይህ በቂ መረጃ ነዉ እንላለን፣፣ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
Sunday, May 24, 2009
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
2 comments:
thanks again GR.Kep informing us.
Dear Getachew,
Thanks for telling the naked truth I always admire you for your stand
Abebe
Post a Comment