Monday, June 30, 2008

TPLF demanded Tigrayans to pay money if wanted to be deported from Egypt, while offered Eritreans free deportation from Egypt to Ethiopia

ኢትዮጵያ ለትግሬዎቹ “ባዳ“
ለኤርትራዎቹ ግን "ቤት ለእንግዳ”
( ጌታቸዉ ረዳ)
(ሳን ሆዘ -ካሊፎርኒያ)

ዛሬስ ዕረፍት ልዉሰድና እስቲ አዕምሮየን እረፍት ልስጠዉ እልና፤ በጎን፤ ሌላ ዕረፍት የ ማይሰጠን ጉድ በየደቂቃዉ ከዚህም ከዚያም እየጎረፈ አላሳርፍ ሲለኝና ወደ መከረኛዎቹ ወደ እናንተዉ ለመጮህ ሚድያ ዉስጥ እገባለሁ።

ለነገሩ ዛሬ ይህ ዜና ስጽፍ እሁድ ነዉና በፈጣሪ ትዛዝ ማረፍ ነበረብኝ። በደምቡ መሰረት ማለት ነዉ። ወያኔዎቹ ሚድያና ተቃዋሚ ነን ከሚሉት ሜዲያዎቹ አንዳነዶቹን ልጎብኝና እስኪ እንደሰዉ አንድ ቀንም ቢሆን ከማንምበብ ልረፍ ብየ ነበር። አልሆነም።

(1ኛ) ያፍራሾችና ጸረ አማራ ፐሮፖጋንዲሰቶች የነ ብርሃኑ ነጋና የነ አንዳረጋቸዉ (በትናቸዉ) ጽጌ መናሃርያ የሆነዉ የአብራሃ በላይ “ኢትዮ-ሚድያዉ” ስጎበኝ፤ እንዳመሉ “እነ በትናቸዉ ጽጌን አሽቀርቅሮ” ማስታወቂያቸዉ ለጠፎላቸዋል። ድምጻቸዉ ጠፍቶ የነበረዉ ድሮ (የዛሬዉን አላዉቅም) ትገሬዎች ዓለም አቀፍ ማህበር በሚል ባዶ ድርጅት ሲመሩ የነበሩት ጀርመን አገር የሚኖሩት ድምጻቸዉ ለብዙ ጊዜ ተሰዉሮ የነበረዉ ዶ/ር ግደይ አሰፋ የተባሉት የትግራይ የእንደርታዉ ሰዉ ፤ በበታኙ፤ በጸረ አማራዉ በ አንዳርጋቸዉ ጽጌ እና በብርሃኑ ነጋ “ግንቦት 7” በተባለዉ “አስቂኝ” ድርጅት ሐምሌ ወር መጀመርያ አካባቢ ሊያዘጋጀዉ ባቀደዉ ስብሰባ ላይ ፡ በእንግዳነት የተጠሩበት ማስታወቂያ አይቻቸዉ “ሥጋ ኣድጊ ሰብሔ ኢልካ ኣይብላዕን” (የአህያ ሥጋ የሰባ ነዉ ተብሎ አይበላም) የሚለዉን የትግርኛ ምሳሌ ትዝ ብሎኝ ፤አድፍጠዉ የቆዩት ሰዉ “ዛሬ” ዘለዉ “ምንነቱ ባልተወቀዉ ሰባሁ በሚለን “ግንቦት 7” ከሚባል አህያ ዘንድ መቆማቸዉ “አግራሞቴ ሳልጨርስ” ወደ ወያኔዉ ዓይጋ ፎረም ስዞር ደግሞ አግራሞቴ በሚከተለዉ ዜና አባባሰብኝ። ‘Ethiopia Offers To Receive Eritrean Refugees In Egypt” ምንጭ ዓዋተ .ካም ይላል።

ትግርኛ ለማታነቡ ወገኖቼ ሆይ!
ባለፈወ 10 ቀን የትግርኛዉ ቪ ኦ ኤ ጋዜጠኛ “በትረ-ሥልጣን” በቀጥታ በሳዉዲ -ዓረብና እና በግብፅ በ አስዋን አስር ቤት ዉስጥ ቁጥራቸዉ በጣም በርካታ የትግራይ ተወላጆች በስልክ አነጋግሮ ነበር። ክርስትያኖች በመሆናቸዉ ብቻ የሳዉዲ ፖሊሶች በሌላ ወንጀል አሳብበዉ ያልሰሩትን ነገር እንደሰሩ አሰመስለዉ ፤በሳዉዲ እስር ቤቶች ለ10 ኣመትና 5000 ጅራፍ ጥዋት ጥዋት 50 ጅራፍ እነዲገረፉ ተፈርዶኦባቸዉ፤ እየተሰቃዩ ሁለት ዓመት ሙሉ ለወ ያኔዉ አምባሳደር “አድነን! ኡ! ኡ!” ብለዉ ተማጽነዉት “ታገሱ! “አላቅም! ብሎናልና፤ ዉጭ የምትኖሩ ወገኖች ድረሱልን”። ብለዉ ያስተላለፉትን ኡኡታ፤ በራሴዉ “ ዌብ ሎግ” አቅርቤዉ ሕዝቡ እነዲተባበር አንድ ነገር እንድናደርግ ፤ ባቀረብኩት የ እንድረስላቸዉ የጽሁፍ ልመና እስካሁን ድረስ ተለጥፏል። አንድም ከትግራይ ማሕበሮች አስካሁን ድረስ አልደረሰላቸዉም ።የጨሆላቸዉም ሆነ ይህነን በሚመለከት፤ ለኔ የጻፉት መልስ የለም። አስካሁን ድረስ ጉዳዩ በቅርብ ብከታተለዉም “ጀሮ ዳባ” ብለዉ ለነ ገብሩ አስራትና ለነ አንዳረጋቸዉ ጽጌ ፤ በነ ብርሃኑ ነጋ ቀልባቸዉ ተሰልቦ “ጊዜ አቸዉና ፤ዌብ ሳይታቸዉ፤ ጊዜአቸዉ” ለተጠቀሱት በታኝ ግለሰቦች መስዋእት እያደረጉ መሆናቸዉን ለናንተዉ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖች በስደተኞቹና በታሳሪዎቹ ስም እገልጻለሁ፡

በአገር ስም፤ የይስሙላና የቡድን ፤የዘመድ ፤የጎሳ፤ የ አዉራጃነትና የጛደኛነት ስብስብ” ሽር ጉድ” ከመቸዉም በባሰበት መልኩ እንደወረርሺኙ እንደ 1991 ዓ/ምሕረቱ፤ የቡድን አሰላለፍ መልክ እየያዘ እየተስፋፋ ሁኔታዉ መምጣቱን ቅሬታየን ለማስተላለፍ እወዳለሁ። አዲስ መልክ እየያዘ የመጣዉ ሸረኛ፤ ጎሰኛ፤መንደርተኛ የቡድንና የልሁቃን ነን ባዮች “ትግል አስወራጅ” (ኮለ ክሽን ኦፍ አቦርቲቭ ጋንገሰተርስ) ስበስብ አደገኛ እየሆነ መምጣቱ እና ትኩረት እንዲሰጠዉ በዚህ አጋጣሚ ደግሜ ሳስገነዝባችሁ ወደ 10 ዓመቱ (ወያኔ ለሁለት ከመከፈሉ በፊት እነ አንዳረጋቸዉ፤ የመሳሰሉት…. ስብስቦች) አስነዋሪ ስበስብ እተመለሱ መሆናቸዉን ለመግለጽ እወዳለሁ።

( 2- )ግብፅ አገር ኢትዮጵያዊያን ከየመንደሩ እየተለቀሙ በአስዋን አስር ቤት ዉስጥ በመታጎር፤ በርካታ ከትግራይ ከ/ሐገር የመጡ ስደተኞች” ጥዋት- ጠዋት ፊታቸዉ ወደ “ፀሐይ” ሐሩር ለረዢም ሰዓታት አዙረዉ ተገደዉ በቅጣት መልክ እንዲቀመጡ በስቃይ ላይ እንዳሉ እና ፤ ከዚህም አልፎ በርከት ያሉ ፤ኢትዮጵያዊያን ወደ ኤረትራ ፤ወደ ኢሳያስ አፈወርቄ አንዲተላለፉ በመደረጉ ፡ ስደተኞቹ ለትግርኛዉ ለ ቪኦ ኤ ጋዜጠኛዉ በሰጡት ቃለ መጠይቅ መሰረት “ እኛ ኢትዮጵያዊያን አንጂ ኤርትራዊያን ስላልሆንን፤ የምንባረር ከሆነ ወደ ኢትዮጵያ ወዳገራችን ላኩን” ብለዉ ቢጮሁም፡ ግብጾች አሻፈረን በማለት ወደ ኤርትራ እየላኩዋቸዉ አንደሆኑ እና ለመባረር በመጠባበቅ ላይ ያሉትም ፤ተመሳሳይ ዕጣ እንዳይደርሳቸዉ ግብጽ ላለዉ የወያኔዉ አምባሲ ወደ አገራቸዉ አንዲመልሳቸዉ ከግብፅ መንግሥት ጋር እነዲነጋገርላቸዉና ይህ ኢ-ሰብአዊ ድረጊት እንዲያቆምላቸዉ ቢማጸኑት “ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከፈለጋችሁ ፤እያንዳንዳቸሁ 200 የአሜሪካን ዶላር መክፈል ይኖርባችሗል። ካልሆነ ግን ወደ ኤርትራ ቢያባርሯቸሁም፤ ጉዳያችን አይሆንም” ሲላቸዉ “ገንዘባችን የግብጽ ፖሊሶች ዘርፈዉናል። እኛ ያለነዉ አስር ቤት ባዶ እጃችን ነን። ብንለዉ: ሊሰማን አልቻለም፡፡ ወገኖች ድረሱልን!!!!” በማለት ኡኡታቸዉ በቪኦኤ ያሰሙትን ኡኡታ፤- ወያኔ ለትግራይ ስደተኖቹ (ለኢትዮጵያዊያኖቹ) ገንዘብ “ካልከፈላችሁኝ” ወደ አገራችሁ “አትመለሷትም !! ” በማለት ጀሮ ዳባ ሲላቸዉ “በጎን ግን “ኤርትራዊያኖች ወደ ኢሳያስ ቢሄዱ ስለሚገላቸዉ ኤርትራዊኖቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በነጻ እንደሚቀበላቸዉ ለግብጽ ጥያቄ ማቅረቡ ስንታዘብ፤ ይሀ በመንግስትነት የተቀመጠ “ሽፍታ” የ ኤርትራዊአኖች መንግስትና አጋር አንጂ፤ ለኢትዬጵያ ዘጎች የቆመ እንዳልሆነ ለ17 ዓመታት የተከራከርነዉ አቋማችን ይፋ እየሆነ መጥቷል።

ኢትዮጵያ ለትግሬዎቹ “ባዳ“ ለኤርትራዎቹ ግን ቤት “ለእንግዳ” የወያኔ አዲሱ ክስተት ለማት እየበቃን ነዉ።
ታለቁ ጌታ ሆይ! ከባለ ብዙ ዘርፍ ጠላቶቿ አትዮጵያን ጠብቅ!

No comments: