Wednesday, October 22, 2025

የአእምሮ በሽተኛ አለመሆኑን የሚጠራጠር ሰው ራሱ የአእምሮ በሽተኛ ነው! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ 10/22/25

 

የአእምሮ በሽተኛ አለመሆኑን የሚጠራጠር ሰው ራሱ የአእምሮ በሽተኛ ነው!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

10/22/25

እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ ተጠፋፋን፡፡ ሀገር በጠፋችበት ዘመን “እገሌ የት ጠፋ?” ብሎ የሚጠይቅ የሚዲያ ተከታታይ ሰው እንዲኖር መጠበቅ የዋህነት መሆኑን እረዳለሁና በየትኛውም የሶሻል ሚዲያ አውታር የእኔን ከሚዲያ መራቅ በሚመለከት አንድም ሰው አለመጠየቁ እምብዝም አላሳሰበኝም፡፡ እንደመግቢያ መሆኑ ነው፤ ደግሞም “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ይባል የለም? እንደዚያ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ላይ የተበተነው አፍዝ አደንግዝ ግን ቀላል አለመሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡

 አቢይ አህመድ አሊ ለቅጣት መምጣቱን በተደጋጋሚ ስንገልጽ የቆዬን ዜጎች አለን፡፡ ይህ ሰው “እንደሚነግሥ”ም ቀደም ብለን የምናውቅ ጥቂቶች አይደለንም፡፡ የተቸገርነው የጊዜው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ለራሱም ለኛም ሲባል በእናቱ ማሕጸን ሳለ ውኃ ሆኖ መቅረት የሚሻለው ሰው መንበረ ሥልጣኑን ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ለሰባት ዓመታት ይዞ ሀገርንና ሕዝብን መቀመቅ እንደሚከት በቀደምት አባቶች በትንቢት መልክ ይነገር ነበር፡፡ የንግርትና የእውነት ጊዜያት ስሌቶች ስለሚለያዩ ይመስላል ይህ መፃጉዕ ሰውዬ ሰባት ዓመቱን ጨርሶ ስምንተኛውንም ዓመት እያገባደደ የመሆኑ ምሥጢር አንዳንዶችን ግራ ቢያጋባ ትክክል አይደሉም አንልም፡፡ ትንቢተኞችንና ትንቢት አስተላላፊዎችንም ለትዝብት መዳረጉ አልቀረም፡፡ ይሁንና የተባለው አይቀርምና የእኛና የሀገር መደቆስ እውን እንደሆነ ሁሉ የአቢይ መንጋም መፈጠሩን እስከሚጠላ አራት ኪሎ መግባቱን የሚራገምበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ መንጋው ብቻ ሳይሆን መንጋው እወክለዋለሁ የሚለው የኦሮሞ ሕዝብም አሣሩን ሊያይ ዋዜማው ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን አጠቃላይ እውነት መጠራጠር የፈጣሪን ብቻ ሳይሆን የታሪክንም ፍርድ እንደመካድ ነው፡፡ሥልጣን በሸክላና በብርጭቆ ሊመሰል ይችላል፡፡ በእጅ የያዙት ሸክላና ብርጭቆ ደግሞ እጅ ሲዝል ወድቆ መሰበሩ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የሚጠበቅና የማይቀርም ነው፡፡ የቀ.ኃ.ሥ እጅ ዝሏል፤ የደርግ መንግሥት እጅ ዝሏል፤ የሕወሓት እጅ ዝሏል - በዚያም ምክንያት ሁላቸውም በሠፈሩት ቁና ተሰፍረዋል፡፡ አበድሮ ብድሩን ያልተከፈለ የለም፤ ከዚህ ሂደት ሊወጣ የሚችል ማንምና ምንም የለም፡፡

“እማዬ ጣቴን አሳከከኝ” አለቻት አሉ አንዲት ሕጻን ለአካል ጉዳተኛ እናቷ፡፡ እናትም “ልጄ፣ እኔም በአንድ ቀን አልተቆመጥኩም” በማለት መለሰችላት፡፡ አዎ፣ ሥልጣን ይዞ ሞቶ ያንን በሚሊዮኖች ደም የተጨማለቀ ሥልጣን ለማቆየት ሲልም ከደናቁርት ቢጤዎቹ ጋር ቀን ከሌት ውር ውር የሚለው አቢይ አህመድም ጣቱን ከማሳከክ ባለፈ አንጀቱና አንገቱ ተቆራርጦ የመጨረሻ እስትንፋሱ ሊዘጋ ግማሽ ግፋ ቢል አንድ ሐሙስ እንደቀረው እሱ ባያውቅ እኛ እናውቃለን፡፡ መጥፎነቱ አንዳንድ ጣሮች ረጂም ጊዜ፣ ብዙ ወጪ፣ ብዙ ትግስት፣ ብዙ ጸሎት … መፈለጋቸው ነው፡፡

  አቢይ አህመድ በሚዲያ ከተነገሩለት በመቶዎች የሚቆጠሩ የውሸት ንግግሮቹ ውስጥ እነዚህን የሚስተካከል የለም፡፡ እነዚህን የሰማ የሰው ዘር ደግሞ ይህን ሰው እንደዕብድ ከመቁጠር ባለፈ እንደአንድ ጤናማ ዜጋ እንኳን የሚቆጥር ከሆነ ራሱ ሰው ስለመሆኑ ያጠራጥራል፡፡ አንድ ሰው ጤነኛ መሆኑና አለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው መለኪያዎች አንደኛው የንግግሩ ይዘት ነው - እውነት ሀሰትነቱ ማለቴ ነው፡፡ አቢይ ሥልጣን በያዘ ሰሞን “አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ጠል ሕዝብ ይበዛል” ብሎ ሲናገር ያኔ ነበር ከሥልጣን መባረር የነበረበት - አማራንና ኦሮሞን ለማጣላት መፈለጉን ያሳበቀበት ንግግር ነበር፡፡ ለዚህ ሰው ከሥልጣን መወገድ ያቺ ብቻ በቂ ነበረች፡፡ ግን በሚገርም ሁኔታ የላከው የአጋንንት ጭፍራ ሽፋን እየሰጠው ይመስላል ከእርሱም አልፎ ስንቱን ምሁርና ትልቅ ሰው አበለሻሸውና የርሱ ባርያ አደረገው፡፡ ስም መጥቀስ አይገባም፤ አያስፈልግምም፡፡ እንጂ ፕሮፌሰር አልማርያም፣ ዶር. ብርሃኑ ነጋ፣ ዶር. ዳኛቸው አሰፋ፣ ረ/ፕሮ. ጌትነት አልማው … እያሉ መቀጠል በተቻለ፡፡

ከፍ ሲል “እነዚህን የሚስተካከል የለም” ወዳልኩት ሃሳብ ስመለስ አቢይ በዚያን ሰሞን “ ‹በ2030 ኢትዮጵያ ከሁለት የዓለማችን ኃያላን ሀገራት አንዷ ትሆናለች› የሚል ዕቅድ ነድፈናል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ በ2100 ኢትዮጵያ ከዓለማችን ሰባተኛዋ በኢኮኖሚና በሥልጣኔ የዳበረች ሀገር ትሆናለች፡፡” ማለቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ቅዠቱ ይቀጥልና ሰሞኑን በሶፎሞር ዋሻ ባደረገው ንግግር ደግሞ “በቀጣዮቹ ስድስት ዓመታት ውስጥ ሀገራችን ከአፍሪካ በዕድገትና ብልጽግና ስድስተኛዋ ሀገር ትሆናለች፤ በአሥር ዓመት ውስጥ ደግሞ ሰባተኛዋ ትሆናለች” በማለት ደረቱን ነፍቶ ቅንጣት ሳያፍር ደስኩሯል፡፡ እንዲህ የሚወሻክተውም እኛንም አጠገቡ የሚገኙ አሽከሮቹንና ደንገጡሮቹንም በሚገባ ስላወቀን ነው፡፡ አቢ በተፈጥሮው ከማያፍርባቸው ነገሮች ውስጥ ዋነኛው ውሸት በመናገር ማታለሉንና የሚጠላውን ሰው በግልጽም ሆነ በሥውር ማስገደሉንና ወደዘብጥያ አውርዶ ቁም ስቅል ማብላቱን ነው፡፡ ዓለም ታልፋለች እንጂ በነዚህ አይደራደርም፡፡ ጎሣን ከጎሣና ሕዝብን ከሕዝብ ማባላቱንም እንደሃይማኖት የያዘው የሚኮራበት ጌጡ ነው፡፡ የሚገርመው ይህን መሰሉን ሰው መሣይ የአጋንንት ውላጅ አድባር ተቀብላው ስምንተኛ ዓመት የሥልጣን ዘመኑን ሊያከብር መቃረቡ ነው፡፡ ዓለም እንዲህ ናት፡፡ ትገርማለች፡፡

እንደዚህ ያለ ቅዠትና ዕብለት የሚናር ሰው ዘመድ ቢኖረው ወዲያውኑ በሰንሰለት አሥሮ ወደሚቀርበው ጠበል ወይም ክርስቲያን ከሆነ ወደ ጠበል ነበር መወሰድ የነበረበት እንጂ በሞተርና በመኪና ታጅቦ ወደቤተ መንግሥት መሄድ አልነበረበትም፡፡ ይህ የሚያሳየን ሀገራችን ለይቶላት በዕብዶችና በወፈፌዎች የምትመራ መሆንዋን ነው፡፡ የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ የሚጠላና ይዞ የተገኘን ዜጋ የሚገድልና የሚያስር፣ እመራዋለሁ የሚለውን ሕዝብ በዘርና በቋንቋ ከፋፍሎ የሚያባላ፣ ከመናገሻ ከተማዋ ወጥቶ ዐርባና ሃምሣ ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ የማይቻልባትን አገር እየመራሁ ነው የሚል ብቸኛው የጉልቤ ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ ነው፡፡ ይህን ሰው ሳስብ ወደአእምሮየ የሚመጡብኝ የልቦለድ ገጸ ባሕርያት የ“ዲክቴተሩ” ጄኔራል አላዲንና የደራሲ ሰርቫንቴስ ዶን ኪሾት ናቸው፡፡   

በ2030 ኢትዮጵያ ከዓለማችን ሁለት ኃያላን ሀገራት አንደኛዋ የምትሆነው እንዴት እንደሆነ ለአብነት እንመልከት፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ 37.98 ትሪሊዮን ዕዳ እንዳለባት የሚነገርላት አሜሪካ እና 15 ትሪሊዮን ዕዳ እንዳለባት የሚነገርላት ቻይና በዓለም ሁለቱ በኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ የበላይነት ኃያላን መንግሥታት ናቸው ተብሎ ቢወሰድ (እነራሽያ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን ወዘተ. ቀርተው ማለት ነው) ከ12 ዓመታት በኋላ በ2030 ኢትዮጵያ አሜሪካንን ነው ወይንስ ቻይናን ገልብጣ የሁለተኝነትን ቦታ የምትረከበው? ይህን መጠየቅ የሚያስችል ጭንቅላት ያለው ሰው በአቢይ አካባቢ አለመገኘቱና እንዳይገኝም ሆን ተብሎ በአቢይ መሠራቱ በጄ እንጂ ነገሩ እጅግ አስጨናቂ ነው፡፡ ሀገራችን እየተነዳች ያለችው በምን ዓይነት ደናቁርት እንደሆነ ሲያስቡት ያሳብዳል፡፡ እንደዚህ ያለ ሰው እየመራት ይህች ሀገር አሁን ባለችበት ሁኔታ ራሱ ውላ ማደሯ ይገርማል፡፡ ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን ይህን ሰው የሰጠን ግን? ለቁርስ እንኳን የማይበቃ ደሞዝ ለበርካታዎቹ የመንግሥት ሠራተኞች እየከፈለ “ሀገሬ በልጽጋለች ከአፍሪካም በልጣለች” የሚል ወፈፌ ጠ/ሚኒስትር እኮ ነው ያለን፡፡ ጎበዝ እንጸልይ እንጂ!!

አቢይ የአእምሮ ጤናው የተቃወሰ ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ያበደ ነው፡፡ ይህ ጥርጥር የለውም፡፡ አዲስ አበባ ስለተብለጨለጨች የአቢይን ዕብደትና የኢትዮጵያን መፍረስ ልንክድ አንችልም፡፡ እግዚአብሔር ባይጠብቀንና እንደአቢይ የተጣመመ አካሄድ ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ለይቶልን ነበር - አሁን ለይቶልን ካልሆነ ማለቴ ነው፡፡ የሰው አንደርባዊ ፀጥታና መከራና ስቃይ ቻይነት ግን ይገርመኛል፡፡

በመጨረሻም አቢይን በጥቂት የእንግሊዝኛ ዐረፍተ ነገሮች እንድገልጸው ይፈቀድልኝ፡፡

Psychologically speaking, Abiy Ahmed Ali is a victim of both possession and obsession which mostly show the psychopathic illnesses of an individual. He is obsessed with his own nightmarish delusional thoughts because of which Ethiopia is almost at the verge of its death, God forbid.

Abiy Ahmed is surely possessed by demons, and as a matter of fact a person who’s possessed by such celestial beings has nothing to do out of his own will. Any person who is possessed by such beings may have little or no control over their own actions, as the being takes over their will”. Disappointingly, Abiy is under the servitude of the negative energy. As most of us understand, a person who has given in to the negative energy is loyal to Lucifer. Here on earth, there are hundreds of luciferian and satanic organizations which stand for the spiritual destruction and deterioration of human beings so much so that humans are denied their heavenly life after their death in the third dimension on earth. This Abiy Ahmed, their puppet in East Africa, who is the master of all kinds of treacheries, is hence the best instrument of the so called Beast, aka, 666, that is responsible for the suffering and massacre of Ethiopians, especially the Amharas, due to the fact that most of the Amharas were, to some extent still are, followers of Christianity.

ለማንኛውም አለሁ ለማለት ነው፤ ቸር ያሰንብተን፡፡ መጪውን የመከራ ጊዜ ቀለል አድርጎልን የማይቀረውን ብርሃነ ትንሣኤ ዘኢትዮጵያ ያሳየን፡፡ በማንኛውም ሚዛን ቢለኩ እርባና በሌላቸው የመከፋፈያ ሰበብ አስባቦች የሚለያዩና እስከመታኮስም የሚደርሱ የአማራ ፋኖዎችንና የትግራይ ጀግኖቻችንን ፈጣሪ አንድ አድርጎልን የቀድሞውን ደግ ዘመን ለማየት ያብቃን፡፡ ምኞት አይከለከልም መቼም፡፡ የጠብንና ግጭትን መንስኤ እያስታወሱ ዝንታለም መናፈር የዕውቀት መለኪያ አይደለምና በቀደመው ዘመን የተጣላችሁና የተበዳደላችሁ ሰሜናውያን ወደቀልባችሁ ብትመለሱ ሁላችሁንም ገድሎና አገዳድሎ በእናንተ ከርሰ መቃብር ላይ በምሥራቅ አፍሪካ ታዋቂ የሆነች የኦሮሞ ሪፓብሊክን ለመመሥረት የቋመጠ ኃይል አራት ኪሎን በመያዙ በጠባችሁ የምታተርፉት እናንተ ሳትሆኑ የጋራ ጠላታችሁ ነውና አስቡበት፡፡ ጊዜ ደግሞ የላችሁም፡፡ የገጠማችሁ ጠላት የሚናቅ አይደለም፡፡ ለመቃብራችሁ እንኳን በማይበቁ ቁርጥራጭ መሬቶች እርስ በራሳችሁ ስትጨራረሱ በማየት ዳር ቆሞ እየሳቀባችሁ ነው፡፡ መሳቅ መሳለቁ ሳያንስ በጀትም መድቦ እያጨራረሳችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ንቁ፡፡ ወደኅሊናችሁም ተመለሱ፡፡ ባለፈ ነገር ይማሩበታል እንጂ በንዴት እየተንጨረጨሩ ሌላ የመከራ ወቅት እንዲመጣ የሤራ ጥንስስና የነገር ቁርሾ አያበጁበትም፡፡ ያለፈ አለፈ፡፡ ዕርቅና ሰላም ይውረድ፡፡ በዳዮችና ተበዳዮች ተለይተው በይቅርታና በካሣ ስምምነት ይፈጠር፡፡ ዘላለም ለማይኖርባት ምድር ጠብን አውርሰን ትውልዶችን አናባላቸው፡፡ ጎጃም አቸፈር የነበረን ትግሬ፣ ትግራይ ተምቤን የነበረን አማራ፣ ጎንደር አዘዞ የነበረን ኦሮሞ በመሬትና በእርሻ ምክንያት ማን ነክቶት ያውቃል? በኔ ዘመን ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብትና ንብረት ነበር፡፡ ያን ዘመን እንመልሰው፡፡ ያኔ መኖር እንጀምራለን፤ ያለፉትን 35 ዓመታት ከነጦስ ጥምቡሳቸው መርሳት ለደገኛ ኑሮ መሠረት ነው፡፡ አጠፋሁ? ዋሸሁ?

Monday, October 20, 2025

ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶምን ገልጠን ብናያቸው ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/20/25

 

ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶምን

ጠን ብናያቸው

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

10/20/25

ዛሬ በሕይወት የሌሉ በኤርትራ ክ/ሃገር የተወለዱ ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶም የሶማሌ ወራሪዎችን ያርበደበዱ ዕውቅ ወታደራዊ ጀነራል ፤ በንጉሡ ዘመን የመከላከያ ሚኒስቴር የነበሩ ፤ የንጉሡ ሥርዓት ተሽሮ ደርግ በሚል መጠሪያ የተከሰተው ወታደሮች በተኩት የወታደሮች ሥርዓት ውስጥ የመጀመሪያው የጊዝያዊው ወታደራዊ መንግሥት ሊቀመንበር ሆነው በወታደሮቹ የተሾሙት ጀነራል አማን ዓንዶም ትውልዳቸው የባሕረ-ምድር የመረብ ምላሽ ቀጠና (ኤርትራ) የሐማሴን ተወላጅ ናቸው።

ትምሕርታቸው የተከታተሉት አዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤በሃገረ አሜሪም በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ እና ሱዳን ውስጥ ወታደራዊ ሥልጠና አድርገዋል።

በቅርቡ ባንድ የድረገጽ “ስዕለ ደምፅ” ሕትመት የቆየ ጀነራሉ ካንድ የውጭ ጋዜጠኛ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ  በወቅቱ ንጉሡን አስመለክተው የሰጡት አሉታዊ (ነጋቲቭ) ቃለምልልሳቸው አድምጨ ነበር።

ታዲያ ጀነራሉ ወደው አምነውበት ሲያገለግሉት የነበርውን ሥርዓት እርግፍ አድርገው በመክዳት ንጉሡ ለሃገራቸው ኢትዮጵያ ፤ ለመላው አፈሪካና ለዓለም ያበረከቱትን ታሪክ የማይሽረውን አስትዋጽኦ ለቤተሰቦቻቸው ብቻ የጠቀሙ ለሃገሪቱ ምንም እንዳልሰሩ ጥላሸት በመቀባት ሲናገሩ ሰምቻቸው፤ ይህ ገደብ የጣሰ ፍጹም አሉታዊ ልሳናቸው ሰዎች ለጀነራሉ የነበራቸው በጎ ገጽታ እንደገና እንዲፈትሽ ይህንን አቀርባለሁ።ጀነራሉን እስኪ እንደገና ገልጠን እንያቸውና ታሪክ በራሱ ሚዛን እንዲመዝናቸው ይህንን ላስተናግዳችሁ።

ታሪኩን ያቀናጀሁት ከተለያዩ የጀነራሉ ማንነት የቀረቡ ዘግባዎች ሲሆኑ ለዚህ ዋናው ድጋፍ የሆነኝ ደግሞ “ትዕድልቲ ቆራጽነት” (ደራሲ ሰናይ ከሰተ) (ቆራጥነትን መታደል) የሚል የትግርኛ መጽሐፍ ነው። ሰናይ ከሰተ ማለት እዚህ ውጭ ሃገር ሆኖ ከምስት አመት በፊት ወያነ ወሎ ውስጥ ገብቶ የቤት ለቤት ዘረፋ ፤ ንግድ ቤቶችን ፤ሆስፒታሎች፤ ከሊንኮች የግል ፋርማሲ ቤት መድሃኒቶችን ሲዘርፍ ፤ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ  ህጻናት ሴት ልጆችን ፤ መነኮሲቶችና ባለተዳሮችን ሲያምጽና እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጽም በነበረበት ወቅት “የውግያው ስልት/ንድፍ/” የሰጠኋቸውና የውግያ አማካሪ የነበረኩት እኔ ነኝ እያለ በፌስቡክ ሚዲያ በቃለ ምልልስ ሲናገር የነበረ፤ ከጦርነቱ በፊት ፍጹም ሃገረ ወዳድ ኢትዮጰያዊ የነበረ የትግራይ ተወላጅ ነው።

ሰናይ እንዲህ ይላል፤ (ለንባብ እንዲመች አጠር እያደረግኩ ነው የምጠቅስው፡

« ጀነራል አማን ሚካኤል ዓንዶም የመከለከያ ሚኒስትር ሆነው በተሾሙበት ወቅት በመላው ሃገሪቱ ሕዝባዊ ዓመጽ ተፋፍሞ  በሰራዊቱ ውስጥም አለመግባባት እና ሥራአተ አልቦነት ሰፍኖ የመስመር መኮንኖችም አለቆቻቸውን በቁጥጥር ሥር እያደረጉበት ባሉበት ሰዓት ስለነበር ፤ ዕዝ እና ቁጥጥር የላላበት ፈታኝ ወቅት በመኖሩ፡ ኤርትራ ክ/ሃገር ለነበሩ ወንበዴዎች ግን ወቅቱ የጫጉላቸው አየር የተነፈሱበት ነበር። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወታደራዊ ኃይላቸውና አሰላለፋቸው ሲያስተካክሉ ቆይተው የማጥቃት እርምጃቸውን በማስፋት “ጀብሃ” ትግራይና የኤርትራ ድምበር በሚያዋስነው “ኦምሓጀር” ወረዳ ውስጥ ሐምሌ 9/1974 ዓ.ም የማጥቃት እርምጃ በመውሰድ አንድ የብርጌድ አዛዥ የነበረ ኮሎኔል ገድሎ ከሥፍራው ተሰወረ።

በእርምጃው የተቆጡ ወታደሮች 200 የኦምሐጀር ሯሪዎችን በገፍ ጨፈጨፉ። በዚህ እርምጃ የተቆጡ በኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት የነበሩ 23 የኤርትራ ክ/ሃገር ተወላጆች የሥራ መልቀቂያ ማመልከቻ ለፓርላማው አቀረቡ።

በወቅቱ የሚኒስትሮች ዋና ሰብሳቢ የነበሩት “ራስ ሚካል ዕምሩ” ለመለቀቂያ ማመልከቻቸው ምክንያት ሲጠዩቁዋቸው ኤርትራኖቹ የሰጡት መልስ ኦምሐጀር የተፈጸመው ጭፍጨፋ እንደሆነ ሲገለጹላቸው፤በወቅቱ  የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ጀ/አማን ዓንዶምን ከነበራቸው የመከላከያ ሚኒስቴርነት ሥልጣናቸው በተጨማሪ የኤርትራ ክ/ሃገር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።

በዚህ መሰረት ወደ ኤርትራ ሄደው ከሕዝብ ጋር እንዲነጋገሩ ጉብኝት እንዲያደርጉ በተወሰነው መሰረት ወደ አሥመራ ሄዱ።

እዛው እንደደረሱም “ኤርትራ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት በንጉሡ ዘመን የነበሩ አድሐሪ ባለሥልጣናት እንደመፍትሔ የወሰዱት “ወታደራዊ ፍልሚያ” ነበር ፡ ዛሬ ግን ‹ኢትዮጵያ ትቅደም» በሚል መርሕ ተዘጋጅተን በዚህ ምድር ውስጥ የጥይት ጩኸት እንደማይሰማ  ላሳውቃችሁ እሻለሁ።» የሚል ንግግር ለሕዝብ አደረጉ።

ባጠቃላይ አሥመራ “ሳባ እስታዲዮም” ውስጥ ወደ 80 ሺሕ የሚገመት ሕዝብ በተሰበሰበበት እንዲህ የሚል ንግግር አደረጉ።

«እንደምታውቁት በኃይለሥላሴ ዘመን  ርትራን ጉዳይ አንስተህ መወያየት ከባድ ወንጀል ተደረጎ ይታይ የነበረ ጉዳይ ነው። ይህ እርምጃ ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ድምጻቸው እንዳይሰማ ያደረገ የመብት ረገጣ ነበር። ሆኖም በዓለም ታሪክ ኤርትራ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ግዛት የነበረች ነች። የኤርትራ ታሪክና ጀግንነት ኢትዮጵያው ሁሉ የሚያውቀው እውነታ ነው።» የሚል ንግግር ካደረጉ በኋላ፤

በተጨማሪ ኡምሐጀር ውሰጥ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የታመነባቸው ከላይ እሰከታች የነበሩት ወታደሮችና አዛዦች  ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በማድርግ ክሱም በወታደራዊ ፍ/ቤት እንዲታይ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

በወቅቱ በኡምሐጀር  ሕዝብ ተወዳጅነት የነበራቸው “ሻለቃ” ረጋሳ ጂማ (በኋላ ጀነራል) የነበሩት የኮለኔልነት ማዕርግ ተሰጥቷቸው  በብርጌድ አዛዥነት ተመድበው ወደ ኦምሐጀር ተመድበው እንዲያረጋጉ ተመደቡ።

ይህ እንዲህ እንዳለ፤ አሥመራ ውስጥ የሚኖሩ በሕዝቡ ተሰሚነት ይኖራቸዋል የተባሉ ከሽማግሌዎች፤ ከካሕናትና የመሳሰሉ የተውጣጡ ሰዎች ለማነጋገር ዓረቦች ያደራጁት “ጀብሃ” የተባለው ተገንጣይ ለመምታት አመቺ የሆነው ተቀናቃኙ  የክርስትያን ስብስብ ነው ተብሎ ሲነገርለት ወደ ነበረው ወደ “ሻዕቢያ” በመላክ በኛ በኩል ተኩስ የማቆም ፈላጎት ያለን መሆኑን “ፍላጎት” ብቻ ሳይሆን «የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከካምፑ እንዳይወጣ ጭምር እናደርጋለን» በላችሁ ንገሯቸው በማለት ሽማግሌዎቹን ወደ ሻዕቢያ ላኩ።

የጀነራሉ ከፈተኛው የመጀመሪያው ስሕተት ይህንን ውሳኔ ሲወሰኑ ከማንንም የመንግሥት አካልም ሆነ ባለሥልጣኖች ሳያማከሩ ለብቻቸው የወሰኑት ነበር።

ደራሲው እንዲህ ይላል፡

«የቶክስ ማቆም ስምምነት ግጭትን ከማቆም እና ደም ከመፍሰስ የሚገታ አንዱ አማራጭ መፈትሄ ቢሆንም፤ አንደኛው ወገን ብቻ ከካምፑ እንዳይወጣና እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ስምምነት መወሰን ግጭቱን የሚያስቆም ሳይሆን ግጭትን የሚያባብስ ነው። ያም ስለሆነ ሻዕቢያ ይህንን ዕድል በመጠቀም “ሰረጀቓ” በሚባል ንኡስ ወረዳ ከጀብሃ ጋር የተጧጧፈ ውግያ ሲያካሂድ የነበረበት ውቀት በመኖሩ ፤ ሽማግሌዎቹ ያንን መልዕክት የዘው መምጣታቸው ተፋላሚዎቹ ትንፋሽ የሚያገኙበት ዕድል አገኙ።

ሽማግሌዎቹ ሰረጀቓ እንደደረሱ በሻዕቢያ እና ጀብሃ መካከል የለየለት ውግያ መካሄዱን ሲያዩ “ጀነራል አማን አደራ ብለው አምነው የላኩዋቸው መልዕክት በልተው ፤ ሽማግልዎቹ የሚከተለው ንግግር ለሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መከሩዋቸው፦

«ምን እየሆናችሁ ነው? ከዛሬ ነገ ከአማራ መንግሥት ቅኝ “ነፃ ታወጡናላችሁ ብለን ስንጠብቃችሁ እርስበርሳችሁ ትጋደላላችሁ?!!” በማለት ሊያስታርቁዋቸው ገቡ።

ጀነራሉ የወሰኑት በክ/ሃገሩ ውስጥ በየጦር ሜዳ ካምፖች ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ሠራዊት ከካምፑ እንዳይወጣ ያደረጉት ስሑት ውሳነ ለተገነጣዮቹ የማጥቃትና የዝግጅት ዕድል የሰጠና የተግንጣዮቹ ሞራል ከፍ ያደረገ የልብ ልብ የሰጣቸው ያልታሰበ ዕድል ሰላገኙ ፤ ክጥቂት ወራት በኋላ ሁለቱ ተፋላሚ ኤርትራ ተገንጣይ ቡድኖች አንድነት ፈጥረው “መንግሥት ለመመሥረት” አስመራ ከተማን ለመያዝ ከተማይቱ ውስጥ ቶክስ በመክፈት ወደ ፍጹም ዕብደትነት አጎለበታቸው።

ደራሲው ይህንን በተመለከተ እንዲህ ይላል፤

  “ጀነራሉ ወደ ተገንጣዮቹ የላኩዋቸው ሰላም ለማምጣት የተላኩ ሽማግሌዎች አደራ በልተው ደም ወደ እሚፈስበት ወደ ተባባሰ ደረጃ  ሰለተጠመዱ ፤ ተገንጣዮቹ የልብ ልብ አግኝተው አሥመራ ከተማን ለመያዝ ያደረጉት ፍልሚያ  በጥር 1975 ዓ.ም በከተማዋ ያለቁ ሰላማዊ ሰዎች ተጠያቂዎች ናቸው።” ይላል።

ጀነራሉ ቀጥለው የፈጸሙት ከፈተኛ ጥፋት

የእንግሊዝ ኢምፐሪያሊዝም ፋሺስት ጣሊያንን ተክቶ  ኤርትራ ክ/ሐገር ውስጥ አዲሱ ቅኝ ገዢና ከፋፋይ አካል ለመሆን በወሰነበት ወቅት ከዚህ አዲሱ ቅኝ ገዢ ጋር ፊትለፊት ገጥመው ሕዝቡን በማንቃት «ፈደረሺን የሚባል የባዕድ ሃይሎች የጫኑብንን ዲቃላ አስተሳስብ አንፈለግም» በማለት  ኤርትራ ወደ እናት ሃገርዋ ወደ ኢትዮጵያ እንድትዋሃድ ያደረጉ “የሃገር ፈቅር ማሕበር” መስራች አባላት እንደ እነ ታዋቂዎቹ “መልአከ ሰላም ንብረኡድ ዲሜጥሮስ ገ/ማርያም እና  ቢትወደድ አስፍሃ ወልደሚካኤል ላይ “የወንበዴዎች ደጋፊ አባላት ክስ በማሰማት” የንጉሡ ደጋፊዎች ናቸው ተብለው ከታሰሩት እስር ቤት ውስጥ አብረው እንዲታሰሩ አደረጉ

ጀነራል አማን የፈጸሙት ሦስተኛው ጥፋት

ሻዕቢያና ጀብሃ ሰረጀቓ ላይ እርስበርሳቸው ሲተራረዱ ሃይላቸው በተዳከመበት ወቅት  በውቅቱ የዋልያ ክ/ጦር ዋና አዛዥ (በኋላ የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ሊቀመንበር) ወንበዴዎቹ መዳከማቸው ባደረጉት ጥናት ሰለተገነዘቡ ፤ አዳክሞ ለማጥፋት ምቹ ወቅት ነው ብለው ሰላመኑበት ተጨማሪ ሠራዊት በመጠየቅ ወሳኝ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ ሲያናግሩዋቸው ፤ ጀነራል አማን  ‘አይሆንም’ በማለት የተፈሪ በንቲን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ አሰናከሉት

በወቅቱ ለሃገሩ ሉዓላዊነት ሲዋደቅ የነበረው ሠራዊት ሁኔታው ሲሰማ ከፈተኛ ቅሬታና ሐዘን ተሰማው። ጀነራሉ ለእገዳው የሰጡት ምክንያት ይላል ደራሲው

«የተጀመረው የሰላም ሽምግልና እንዳይሰናከል የሚል ምክንያት ቢሰጡም፤ ሃቁ ግን «የስጋ ጉዳይ ሰልሆነባቸው ነው» ይላል ደራሲው። በሌላ አነጋገር «ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ» ማለቱ ነው።

ጀነራሉ ይህንን ተግባር ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ፤ የሰላም ምፍትሔ ሰነድ ብለው ባለ 19 ነጥቦችን ለሚንስትሮች ጉባይ አቅርበው ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠየቁ። የሰነዱ ዋናው ይዘት «ኤርትራ ውስጥ ዳግም ፍደረሽን እንዲጸድቅ የሚል ነው»

ደራሲው ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦

«ጀነራል አማን ያቀረቡት የፈደረሺን ዳግም መመለስ ሰነድ የሰላም አምጪ መፍትሔ መሰሎ ቢታይም ባንድ እጅ ማንጨበጨብ እንደማይቻል ሁሉ ሃገር ገንጣይ እሳት ጫሪዎቹ በሽማግሌዎቹ በኩል ስለ ተላከላቸው ጥያቄ መልስ ሳይገኝና አቁዋማቸው ሳያውቁ ጀነራሉ ተቻኩለው ሰነዱ እንዲጸድቅ መጠየቅ ባንድ እጅ እንደማጨብጨብ መሞከር ነው» ይላል።

ሰነዱ ወደ መኒስትሮች ጉባኤ እንደቀረበ በወቅቱ የደርግ ም/ሊቀመንበር ሻለቃ በኋላ የደርግ ሊቀመንበርና የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ፕረዚዳንት የነበሩት ኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም እንዲሁም፤ የደርጉ ባለሥለጣኖች ሻለቃ ብርሃኑ ባይህ፤ ሻለቃ አጥናፉ አባተ፤ ሻምበል መጎስ ወልደሚካኤል እና ሌሎች ደጋፊያቸውን በማስከተል ደርግ ዳግም ፈደረሺን የማጽደቅ አጀንዳ ሰላልነበረውና ሰላለተወያየበት ስብሰባው በዚህ ሁኔታ ሊነጋገር አይችልም በማለት ስብሰባው ተበተነ።

ፕረዚዳንት መንግሥቱ ጀነራሉ ይህንን ሰነድ ይዘው ለማጽደቅ የመጡበት ምክንያት «በፈደረሺን ሰበብ ኤርትራን የሚያስገነጥል ሰነድ ሳናሰላስለው እንድናጸድቅላቸው ድንገት ይዘውልን መጡ»

ሻለቃ ሑሴን አሕመድ (በኋላ ም/ጅነራል -የ2ኛ አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ) ጀነራሉ ከጦር መከላከያነት ወደ ደረጉ ሊቀመንበርነት ሆነው ከተሾሙ የአስተዳደረና የሕግ አማካሪያቸው ሆነው ከተመደቡት 7 በሕግና አስተዳደር ትምህርት የተመረቁ ባለሞያ ወታደሮች፤አንዱ የነበሩት ሑሴን አሕመድ ስለ ጀነራሉ አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡

« ጀነራል አማን ኤርትራ ደርሰው ወደ አዲሰ አበባ እደተመለሱ ባሕሪያቸውና የሥራ ፍላጎታቸው እየተቀየረ መጣ። የአመራር መንፈሳቸው እየተለወጠ መጣ። እኔ የአስተዳደር ጉዳይ አጋዥያቸው ሆኜ እሰራ ሰለነበር ከዕለት ዕለት ሥራዎችና ሁኔታዎች በተገቢው ከመከታተል ይልቅ ጊዜያቸው ከተለያዩ ታዋቂ ሰዎች ጋር መገናኘት ጀመሩ። የግል አማካሪያቸው ሆኖ የቀረበው የሕግ ባለሞያው ዶ/ር በረከተአብ ሃብተሰላሰ ነበር»።

ጀነራሉ ስለወሰዱት እርምጃ በወንበዴዎቹ ካምፕ ሽብራና ፍራቻ ፈጥሮባቸው ሰለነበር፤ የኤርትራ ሕዝብም ጀነራሉ ደግፎ በመታየቱ ተገንጣዮቹ ከሕዝብ ይነጥለናል የሚል ፍራቻ ሰላደረባቸው፤ ፈጣን ማጥቃት እንሚያደርጉ ዛቱ።

 በዛቱት መሠረት ጥቅምት 25, 1974 ዓ.ም አሥመራን በዙርያ በመክበብ ማጥቃት ጀመሩ። አብዮታዊ ሠራዊት በወሰደው የአጸፋ ማጥቃት እርምጃ ተገነንጣዮቹ ክፉኛ ተጨፍልቀው ሙትና ሙርከኛ ሆነው የተቀሩት ቁስለኞቻቸውም ይዘው ፈረጠጡ። ሆኖም ተገነጣዮቹ አስመራን መቆጣጠር ባይችሉም  ከከተማዋ የሚያሰወጡና የሚያስገቡ መውጫና መግቢያ 4 መንገዶች በ10 ኪ.ሚ. ራዲያስ ከብበው የክፍለሃገሩ ጸጥታ ከማንኛውም ወቅት በከፋ የስጋት ድባብ ውስጥ አስገቡት።

ጥታው ስጋት ምክንያት የሆነው ይህ ጥቃት ከመፈጸማቸው ካንድ ወር በፊት ሁለቱ ተገንጣይ ቡድኖች እርስበርሳቸው ሲተራረዱ በነበሩበት ወቅት እነ ተፈሪ ባንቲ ወቅቱ አመች ነውና እናጥቃቸው ሲሉ ጀነራል አማን አይሆንም ብለው ሠራዊቱ እንዳይንቀሳቀስ በማገዳቸው ተገንጣዮቹ እንደልብ ሲንቀሳቀሱባቸው ከነበሩት ተራሮችና ምሽጎቻቸው በሰፋት እንዲንቀሳቀሱ ዕድል የሰጣቸው የጀነራሉ ስሑት ወሳኔ ተገንጣዮቹ ሠራዊቱና አካባቢውን ሊያወኩ የበቁበት ምክንያት አንድ ወገን ብቻ (ሠራዊቱ) ከካምፑ እንዳይወጣ በማድረጋቸው ነው።

በዚህ ምክንያት ይሁን በሌላ ምክንያት ሻለቃ መንግሥቱ ሃይለማርያም የደህንነት ሚኒስትሩን  ተሰፋየ ወ/ልደሰልሴ መጀመሪያ ሕዳር 1975 ዓ.ም. ወደ አሥመራ ላኩት።    

ተሰፋየ ወ/ልደስላሴ አሥመራ ደርሶ እንደመጣ  ሻለቃ መንግሥቱ አጠቃላይ የደረግ አባላት ጉባኤ በመጥራት «ጓድ ተሰፋየ ኤርትራ ደርሶ ሰለመጣ በክፍለሃገሩ ያለው ሁኔታ እንዲነግረን ጉባኤው እንዲከፍትልን እጠይቃለሁ» በማለት ሰባሰባው ተጀመረ።

የደህንነት ሚኒስትሩ ተሰፋየ ወ/ልደስላሴ በክፍለሃገሩ  ሰላለው ሁኔታ አሲያስረዳ

« ወንበዴዎቹ ካሁን በፊት አይተነው በማናውቅ ጉልበት አግኝተው አሥመራ ዙረያ ከበብው በማንኛውም ወቅት ከተማዋ እንደሚቆጣጠሩና በማንኛውም ወቅት መንግሥት ሊያውጁ የሚችሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ጀነራል አማን ወደ ወንበዴዎቹ የላኩዋቸው የሽማግሌዎች « ልጆቻቸን ነፃ ሊያውጡን ተቃርበዋል» በማለት የሕዝቡን ልብ አሸነፍዋል። ከዚህ ወደ ክ/ሃገሩ የተሟላ ረዳት ጦር ካልላክን ወንበዴዎቹ ክ/ሃገሩን ይገነጥሉታል።» በማለት ንግግር አደረገ።

ይህ ንግግር በጥሞና ካደመጡ በኋላ ጀነራል አማን እንዲህ ሲሉ መልስ ሰጡ፦

«ለመሆኑ ከየት ያገኘኸው ዘገባና ጥናት ነው ይህንን ለማለት ያበቃህ? የኤርትራ ጉዳይ የሚፈታው በሠራዊት ሳይሆን  በሠላም ነው። ይህ ደግሞ እ ራሴ የያዝኩት ጉዳይ ሰለሆነ ለኔ ተወው» ሲሉ መልስ ሰጡ።

ይህንን አስመልክቶ ደራሲው እንዲህ ይላል፡

«ባጠቃላይ የጀነራሉ መልስ ምክያታዊ ቢሆንም፤ 3 ሚሊዮን ሕዝብ ለ10 ሺሕ የኢትዮጰያ ሠራዊት የሚደረግ ቁማር ነው። መዲናዋን ከብበው ወንበዴዎቹ ኤርትራ ነፃ ወጥታለች ብለው ለዓልም ሊያውጁ በተቃረቡበት ወቅት ባለፉት ሦስት ወራት ሙሉ ሠራዊቱ ከካምፑ እነንዳይወጣና ቶክስ እንዳይከፍት ሆኖ ወንበዴዎቹ እንዳሻቸው ቶክሰ ከፈተው መዲናዋን በከበቡበት አንድ ወገነ ብቻውን በአንድ እጅ እንዲያንጨበጭብ  በተደረገበት ሁኔታ “ሰላም፤ፈደረሺን ወዘተ..” በሚል መመጻደቅ “ጉዳትን በገዛ እጅ በራስ ማወጅ ነው”። ሰለዚህም የጀነራሉ ሐሳብ ቁማር መጫወት ሆኖ ሰለታየ በተሰብሳቢዎቹ ጀሮ አላገኘም»።

ተሰብሳቢው በድምፅ ብልጫ ድምፅ ተሰጥቶ ውሳኔ የሰጠበት ተብሎ አብዛኛው ሠራዊት ተጨማሪ ልዩ ተዋጊ ጦር ይላክ በሚል አጸደቀው። ጀነራሉ ደጋፊ ሲያጡ “የ3ኛ/አምበሳ ክ/ጦር ይላክ በማለታቸው፤ ውደቅ ሆኖ ኮንቨንሺናል አርሚ ሳይሆን በከባድ ተራራና ጸለቆች ወጥቶ ወርዶ መዋጋት የሚችል እግረኛ ብቻ ይላክ በሚል ውድቅ ሆኖ  በምትኩ ሌሎች ክፍሎች ሰለተላኩ (ከነሱ ውሰጥ ናቅፋ ውሰጥ ተአምር ሰርቶ የተዋጋ 15ኛ ሻለቃ) እና የመሳሉ ተዋግዎች ይላክ ሰለተባለ፡ ጀነራሉ  አኩርፈው «እኔ አሻንጉሊት አይደለሁም» በማለት ከመደበኛ ሥራቸው በመቅረት እቤታቸው ተቀመጡ። ሃገሪቱ ተጋፍጦባት ባለው ሁኔታ የሃገር መሪ እቤቱ መቀመጥ ማለት በሃገሪቱ ላይ የሚወርድ መከራ መገመት አያስቸግርም።

ሁኔታው አሳሳቢ ሰለነበር፤ ደርግ 4 ባለሥልጣኖች ጀነራሉን ለማነጋገር እና ችግሩን ለማወቅ ወደ ቤታቸው ላከ። ባለሥለጣኖቹ ጀነራሉ ይቅርታ ጠይቀው ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ቢጠይቁዋቸውም አሻፈረኝ በማለት ተስፋ አስቆርጠውና ቅድመ ሁኔታ አስይዘው ሸኙዋቸው።

ወደ ጀነራሉ መኖርያ ቤት ሊያነጋግሩዋቸው ከተላኩት የደርግ ሸምጋዮች አንዱ ከዛ በፊት በነበረው ያለመጣጣም ያስከተለው ሰብሰባ ላይ ጀነራሉ በመጥፎ ዓይን ያዩት ይደህነነቱ ሹም ኮለኔል ተሰፋየ ወ/ለደሰልሴ ሰለነበር ከሽምግልና መልስ ወዲያውኑ የመኖሪያ ቤታቸውና የመሥስርያ ቤታቸው ስልኮች እንዲጠለፍ አደረገ።

ከተጠለፈው ስልክ አንዱ የምድር ጦር እስታፍ ዋና አዛዥ የነበሩት ጀነራል ግዛው በላይነህ «ደርግ ሊያሰራኝ አልቻለም» የሚል የስልክ ልውውጥ ቀድቶ ተሰብሳቢው እንዲያደመጠው ኮለኔል ወልደሰላሴ አቀረበው።

ጀነራል አማንን ወክለው ወደ ደርግ የላኩዋቸው የ3ኛ ክ/ጦር (አንበሳ ክ/ጦር) አባሎች ከሐረር ወደ አዲሰ አበባ በመምጣት ስለ ደህንነታቸውና ሁኔታቸው እንዲያረጋግጡ ወደ ቤታቸው ሄደው ምን እንደገጠማቸው ሲጠይቁዋቸው፡  ሕዳር 22/1974 ዓ.ም አጠቃላይ የደረግ ሰብሰባ ሰላሚካሄድ እዛ ሂዳችሁ ስለተከሰተው ሁኔታ አስረዱን በሉዋቸው በማለት አስናበትዋቸው።

የጀነራሉ ደህንነት ያሳሰባቸው አባሎች ወደ ስብስባው በመሄድ ሁኔታው ለማዳመጥ ተገኙ።  ስብሰባውን የመሩት የደርጉ ም/ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማርያም ስለ ጀነራሉ እንዲህ ሲል ዘገባ አቀረቡ።

« ርትራ ከእናት ሃገርዋ ከኢትዮጵያ ጋር እንደትዋሃድ ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉት  መልአከሰላም ዲሞጥሮሰ ገ/ማርያም እና ቢትወደድ አስፋሃ ወ/ሚካኤል እንዲታሰሩ አድርገዋል።

አበዮታዊ ሠራዊት ከካምፑ እንዳይወጣ አግደው ቶክስ እንዳይከፍት በማድረግ ወምበዴዎቹ ግን እንዳሻቸው እንዲንቀሳቀሱና በሠራዊታችን ላይ ቶክስ እንዲከፍቱ ምቹ ሁኔታ ፈጥሩላቸው።

በመጨረሻም ርዕሰ መዲናዋ አሥመራ ከተማን ለመያዝ ከብበው ሲያሰጨንቁ ባለበት ወቅት  ከዚህ ረዳት ሠራዊት ይሂድ ሲባል አሻፈረኝ አይሆንም ብለው ሲያስቸግሩ በመጨረሻም ይላክ የምትሉ ከሆነም “መካናይዝድ ብርጌድ” ይሂድ በማለት ተቀባይ ሲያጡ በዚህ አኩርፈው እቤታቸው ተቀመጡ።»

በማለት ሻለቃ መንግሥቱ ለተሰበሳቢው ሲያስረዱ

ተሰብሳቢውም

«እውነት ጀነራሉ ይህንን ፈጽመው ከሆኑ  ተጠርተው እዚህ መጥተው እንሲያሰረዱን ይደረግ»

 ሲሉ፤ ሻለቃ መንግሥቱም፤ መምጣት አያሰፈለጋቸውም፤ ይህንን የስልክ ቅጅ አድመጡ ብለው ከጀነራል ግዛው በላይነህ ጋር አማን ያደረጉት የሥልክ ልውውጥ እንዲሰሙት ተደረገ።

ተሰብሳቢውም «መንግሥቱ ያንድ የመሳርያ ግምጃ-ቤት ሐላፊ የነበረ መኮንን ነው፤ አብረውት ያሉትም እንደዚሁ ናቸው፡ እያሉ ጀነራል አማን ለሻለቃ መንግሥቱ ያላቸው ንቀት የሚናገር ንግግራቸው ካደመጡ በኋላ ተሰበሳቢዎቹ በቁጣ ነደዱ።

ስብሰባው ዕልባት ለመሰጠት በማግሥቱ ቀጠሮ ተደርጎ ተበተነ።እዚህ ላይ ማወቅ የሚገባን፤ የጀነራሉ መኖርያ በመድፍና በታንክ ተከብቦ ስለነበር ጀነራሉ “የእቤት ቁም እስረኛ” እንደነበሩ ነው።

በይደር የተላለፈው ስብሰባ በማግስቱ ቀጠለ። ም/ሊቀመንበር መንግሥቱ ስብሰባውን በመክፈት “ይህች አገር አደጋ ላይ ነች። በተለይ በላቀ ሐላፊነትና እምነት የመሩናል ብለን የጣልንባቸው ሰዎች በተራቸው እኛው ጋ ብትራቸውን ለመሰነዘር እየቃጡብን ነው። ሰለዚህም አገሪቱን ለማዳን እርምጃ መውሰድ አለብን ካሉ በኋላ፡ ይህ እርምጃ የተባለው ከባድ እረምጃ በጀነራሉ ላይ ለመውሰድ በወቅቱ የደህንነት ኦፐረሺን ሐላፊ የነበርው ሻለቃ ዳንኤል አስፋው ወደ ጀነራሉ መኖርያ ዘንድ በመሄድ ተሎ በቁጥጥር ውስጥ እንዲያውላቸው ትዕዛዝ ተሰጠው።

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ሻለቃ ዳኒኤል አስፋው ወደ ጉባኤው አዳራሽ በመሄድ “ ጀነራሉ እጃቸው እንዲሰጡ ቢጠየቁ ፈቃደኛ አለሆኑም» በማለት አስረዳ።

ልክ በ05.00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቤተመንግሥት አርሞር ታንኮች ወደ ቦሌ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ጀመሩ።አቅጣጫቸው ያመሩት ወደ ጀነራሉ መኖርያ ነበር። ሻለቃ ዳኒኤል የሚመራው ይህ በመድፈኛ ታንክ የታጠቀ ልዩ ተልዕኮ የተሰጠው ሠራዊት የሚመራው “የአየር ሃየሉ ሻለቃ ዳኒኤል አስፋው” ነብር።

ሠራዊቱ ከጀነራሉ መኖርያ እንደደረሰ እጅ እንዲሰጡ ቢጠየቁ አሻፈረኝ በማለት መትረየስ በመጥመድ ካንድ ሰዓት በላይ የሚሆን የተኩስ ለውውጥ አደረጉ። ከዚያ በኋላ እጃቸው ለመያዝ ሰላለተቻለ፤ አንድ ታንክ የግቢውን መኖርያ በሩን በርግዶ ወደ ውስጥ ገባ። ሆኖም ባሳዛኝ ሁኔታ ጀነራሉ እራሳቸውን ገደለው ተገኙ።

ጀነራአማን ሚካኤል ዓንዶም ‘ሶባ’ በሚባል ሱዳን ካርቱም ከተማ  አቅራቢያ ወታደራዊ ካምፕ ውሰጥ የመኮንኖች  ሥልጠና በመውሰድ በከፈተኛ ማዕረግ የተመረቁ ቆፍጣና ወታደር ነበሩ። ጀነራሉ በ1924 ዓ.ም.በአሥመራ ከተማ ተውልደው መጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው አሥመራ ካምቦኒ ት/ቤት ተምረው ፤ ከዚያም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአሜሪካ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ትምህታቸውን ያጠናቀቁ ዕውቅ መኮንን ነበሩ። ሆኖም ያ ሁሉ ወታደራዊ ዕውቀትና ትምህርት አካብተው እሰከ ጀነራለነትና የሃገር ከላከያ ሚኒስትርነትና የሃገሪቱ ጊዝዊ ወታደራዊ መንግሥት ሊቀመንር ሆኖው ያገለገሉ የታወቁ ወታደር ቢሆኑም፤ የወቀቱ የፖለቲካ ስንክሳር በቅጡ የተረዱት ሰላለነበረ ለሞት ተዳረጉ

ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ጥፋቶች፤ ለማጠቃለል እንደገና ባጨሩ ላስታውሳችሁ፦

ከጣሊያን እና እንግሊዝ ቅኝ ገዢዎች ኤርትራን ነፃ አውጥቶ ኤርትራ ወደ እናት ሃገርዋ ለማዋሃድ “የሃገር ፍቅር ማሕበር” (ማሕበር ፍቕሪ ሃገር) መስረተው ከራቢጣ እሳላሞችና የመሳሰሉ አክራሪ ተገንጣይ ክርሰትያን አባሎች ማሕበሩን በግምባር መሪነት ታግለው አኩሪ ሥራ የሰሩ መልአከ ሰላም ንብረእድ ዲሞጥሮስ ገ.ማርያም እና ቢትወደድ አሰፍሃ ወ/ሚካአል እንዲታሰሩ ጀነራሉ በመወሰናቸው፤

 ከዚያም ለተገነጣዮቹ ምቹ ዕድል የከፈተ ያንድ ወገን የቶክስ አቁም ውሳኔ አሳለፈው ሰራዊቱ እንዲጠቃ በማድረጋቸው።

ተገንጣዮቹ ለማነጋገር ጀነራሉ የላኩዋቸው ሽማግሌዎች አደራ በመብላት ሳይመለሱ መሰወራቸው ሲረዱ፤ ቀደም ብለው ያስተላለፉት  ያንድ ወገን ቶክስ አቁም ውሳኔ ዳግም መፈተሽ ሲኖርባቸው ውሳኔውን ሳይሸሩ በዛው እንዲቀጥል በማድረጋቸው እና ተገንጣዮቹ አሥመራን እስከመክበብ ያድረሰ ውሳኔ መኖሩን ።

ከዚያም ረዳት ሠራዊት እንዲጨመር ሃሳብ ሲቀረብላቸው አለመቀበላቸው እና እንዲሁም ተገንጣዮቹ እርስበርሳቸው እየተታኮሱ እየደከሙ ስለነበር፤ ኮለኔል (በኋላ ጀነራል) ተፈሪ በንቲ ያቀረቡትን የመልሶ ማጥቃት ሃሳብ አልቀበልም ማለታቻው፡

ጦሩ ሳይንቀሳቀስ ካምፑ ውስጥ እንዲቀመጥ በመደረጉ በጥር 10/1975 ዓ.ም ተገነጣዮች አሥመራን ለመያዝ ቶክስ እስከመክፈት ጉልበት ማግኘታቸው፡

እንዲሁም ቅደም ጥናት ሳይደረግበት ኤርትራ በፈደረሽን እንድትተዳደር ካቀረቡዋቸው ነጥቦች መካከል እና ከላይ የቀረቡ ነጥቦች ተደማምረው  በጥረጣሬ ዓይን እንዲገቡ ሆነ።

በመረሻም ባሳዛኝ ሁኔታ ራሳቸው ገድለው ተገኙ።

ለዘገባው ደራሲ  ሰናይ ከሰተ እና የምሳሰሉ መረጃዎች እያመሳከርኩ ያጠናከረኩትን አንባቢ የራሱ ገንዛቤ እንዲወሰድ አድርጌአለሁ።

አምሰግናለሁ
 
ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

 

   

 

   

Thursday, October 2, 2025

የፋኖ ፖለቲካል ሃርለቶች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/3/25

 

የፋኖ ፖለቲካል ሃርለቶች

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

10/3/25

ባለፈው ሰሞን ፋኖ ተብየው ማፈርያ ታጣቂ የወያነ ዘረኛ መፈከር ተበድሮ «ወላጆቻችን ተማርከዋል እኛም ተደግመናል» በሉ እያለ ከሙርከኛ አያያዝ ሕግ ውጭ ፣ የቆሰለና ጣዕር ላይ ያለን ሙርከኛ ሲያስጨንቅ  ስምተን መገረማችን ሳናቆም እንደጋና ሰሞኑን “ወሎንና ጎጃምን አልፋችሁ ትግራይ እና ኤርትራ ያሉት “የፖለቲካ ውሹማዎቻችንን” ትነኩዋቸውና እነሱን ከመንካታችሁ በፊት እኛ “እንደ ነብር እንከመርባችኋለሁ” የሚሉ ፖለቲካል ሃርለቶች ለኛ “ለኢትዮጵያዊያኒስቶች” አደጋ ናቸው!

በግሌ ተስፋ ጥየበት የነበረው የፋኖ የትጥቅ ትግል ገና ጥይት ሳይቶኩሱ ወደ የሀገር መሪነት ኩፈሳ የሚቃጣቸው በአዳዲስ የጫካ ነገሥታቶች ግቡን ስቶ ቃናውን አጎምዝዘውታልና ዲያስፖራዎች የፋኖ “ነቀዝ” መሪዎችን ከነ ውሸታቸው ፤ወንጀላቸውና ባንዳዊ ንግግራቸው ጭምር ማድነቅና መደገፍ ከቀጠላችሁ ፋኖዎች ከተማዎችንና አስፋልቶችን መቆጣጥር ከቻሉም  አዲሰ አበባ ከገቡም፤ ውሸታሞች፤ ወንጀለኞችና ባንዳዎች ትግሉን እሰከመሩት ድረስ የተመኙትን የሥልጣን ስግብግብነት ያገኛሉ የምትሉ ተከታዮቻቸው ብዙም ተስፋ ባታደርጉ እመክራለሁ ኣያልኩ ይልቁኑ መሪዎቹ በሰራዊትና በገልለተኛ ደጋፊዎች የተውጣጡ አጣሪ ኮሚቴዎች የሰሩት ወንጀል እና ጥንካርያቸው እየተጣራ ነቀዞችን የሚተኩ ሌሎች እንዲመሩት ቢደረግ መለካም ነው እያልኩ ወደ ዋናው-ጉዳያችን-እንግባ።

በዙዎቻችሁ እንደምታውቁት፤ አሁን የታጠቁት የፋኖ መሪዎችም ሆኑ የነዚህ “ክሪሚናልስቶች” አጨበጫቢ አጃቢዎቻቸው አሁን አለን፤አለን እንድሚሉት ሳይሆን ወላጆቻቸው ሲጠቁ ጀሮ ዳባ ብለው ጣፋጭ ኑሮ ሲኖሩ የነበሩ አንዳንዱም ከጸረ አምሐራው ከግንቦት 7 ጋር ሆነው በከፍተኛ አመራርነት፤ ካድሬነት እና ታጣቂዎች ሆነው የኢሳያስና የአንዳርጋቸው ጽጌ ፖለቲካ ሲያገለግሉ የነበሩ አማራዎች ፤ እኛ በቁጥር በጣም ጥቂቶች የአምሐራን ሕዝብ ጥቃት ለማስቆም ስንጮህ እኛን ከማገዝ ይልቅ ሲሰድቡን የነበሩ ሁሉ ፋኖ የሚባል ታጣቂ ከመከሰቱ በፊት የነበሩበት መጫወጫ ሜዳቸው የት እንደነበር ማሕደራቸውን ማየት በቂ ነው።

ዛሬ የምንመለከተው ስለ የጎጃም ፋኖ አስረስ ማረ ፤ በሚስቱ በኩል የተመለመለው “የሻዕቢያው ፋኖ” ተፈራ ማሞ እና “ካፒተን ማስረሻ ሰጤ” የተባለው ባንዳዎችን ባንዳ በማለቱ ያልወደደለት የፖለቲካ Neophyte የሆነው የሸዋ ፋኖ ተዋጊ መሪ መከታው ማሞ እና የመሳሰሉ የፋኖ መሪዎች እየተጓዙበት ያለው “ስትራተጂ የሳተ” ጨዋታቸውን እንነጋገራለን።

መጀመሪያ እሰኪ Political Prostitution “የፖለቲካ ሽርሙጥና” ከመመልከታችን በፊት የፋኖ መሪዎች ነጸብራቅ የሆነው በጎጥ እየተዘላለፈ ሰላለው ሰለ የዲያስፖራው አማራ ማሕበረሰብ እንመልክት። እነዚህ ኮሚኒቲዎች የፖለቲካ ሽርሙጥናም ሆነ ስድነት፤ ውሸትና ባንዳነት በፋኖ ውስጥ የለም ባዮች ናቸው። ሰለ ነሱ ስትተችም ይንጨረጨራሉ፤ ያብዳሉ፤ስብዕናህንም ማሕደርሕንም ይጋፋሉ።

እውነታውን እያዩ በመሸሽ ላይ ያሉት እነዚህ “በኮግኒቲቭ ዲሶናንስ እሾሕ” የተሸነክሩት እነዚ እነ ማን እንደሆኑ ልንገራችሁ።

ባለፉት አመታት የብርሃኑና የአንዳርጋቸው ግንቦት 7 ባንዳነትና ዘረኛነት እያሽሞነሞኑ «ፓቶክ» ውስጥ ገብተው ጀሮአችንን ሲያደነቁሩን የነበሩት ግንቦት 7 ምን እንደነበር ስንጮህ አንሰማም ብለውን ወያነ ሲወድቅ ፤ የግንቦት 7 ማንነት ተገለጠላቸውና በቆምንበት ፊት ቆመው በአጫፋሪነታቸው ኮሸሽ ብለው ያፈሩ ፡

 ከዚያም ወደ አብይ አሕመድ አጫፋሪነት ገቡና እንደገና ዛሬ በፋኖ ደጋፊነት ግልብጥ ብለው አወራጃ ባወራጃ እየተሰዳደቡ በለመዱበት ባሕሪያቸው የሚያመልኩዋቸው የፋኖ መሪዎችን ላለማጋለጥ በፋኖ ውስጥ ዝርፍያ፤ ርሸና (ግድያ/ቶርቸር/ጠለፋ) ፤ እርሰ በርስ መገዳደል፤ ስድነትና “የፖለቲካ ሽርሙጥና” እየተፈጸመ እያዩ “የነፃነት መላዕክቶች የሚመሩት ድርጅት” ነው ብለው ፋኖ የፈለገው ጥፋትና ወንጀል ቢያደርግም መዳኚያችን ነው የሚሉ የዲያስፖራ አማኞቻቸው” (nationalist cult) አገር ውስጥ ላለው የትጥቅ ትግል ተጨማሪ አስናካዮች ናቸው

 ለመሆኑ “የፖለቲካ ዝሙትነት” ምንድ ነው?

የፖለቲካ ዝሙትነት ማለት፤ በኛ ሀገር እንመልከት፡ የባሕር በሮቻችንን ለዘጋብን ፤ እንድንዘጋም ፈርሞ ከሰጠ አካል፤ ሀገርን፤ ባሕልን ለማኮላሸት በሚደረግ አፍራሽ ትወና ውስጥ እዚህም እዛም አለሁ እያለ ዥዋዥዌ እየተጫወተ “ከተገነጠለ እና ለመገንጠል ለሚጥሩ ቡድኖች” ጋሻ (Shield) ለመሆን «የሀገር ጦር ሰራዊት እና መሪዎች መለየት ያቃተው ፋኖ» ወያነ እና ሻዕቢያን ትተናኮል “የእኔ ሬሳ ተሸጋግረህ እንጂ እነሱን መንካት አትችልም” የሚል ይፋ አዋጅ የሚያውጅ ልክ እንደ (የሻዕቢያው ፋኖ ‘ተፈራ ማሞ’) የጠላት ቀላጤ ሆኖ የሚያገልግል የፖለቲካ ድርጅት/ግለሰብ/ብድን/ማለት-ነው “የፖለቲካ ዝሙትነት” ማለት።

እዚህ ላይ እያወራን ያለነው ሰለ ወንድና ሴት ወሲብ አይደለም። እያወራን ያለነው፤ “የብሔር ብሔረሰቦች” አምላኪዎች ባጭሩ “ተገንጣዮች እና ግዛት አስመላሾች Secessionists and Irredentists የወጠኑትን የመገንጠልና ግዛት የማስመለስ ጥረታቸው በጦርነት ሞክረው አልሆን ሲላቸው አልፈርስ ብሎ የቆመን ግድግዳ (ሃገር) የሚያነቃንቁለትን ሰለ «የፖለቲካ ሸርምጦች (Political Harlots)» ተዋናይነትን ነው።

የፋኖ ጎጠኛ ትርኪምርኪዎች እያደረጉት ያሉት «የተለመደው የፖለቲካ ዝሙት ነው»። መልማዮቻቸው እስራተጂ አላቸው። የአቀራረቡ ስልት ደጎሞ “የብሔር ብሔረሰቦች ጥምረት” (Interethnic coalition) የጋራ ጠላት በጋራ የማጥቃት “ስም/ሽፋን” ተጠግቶ የፖለቲካ ሸርሙጦችን (Political Harlots)» ይቀጥራል። ይህ ስልት በ60ዎቹ በተማሪዎች እንቅስቃሴ የታየ ነው። ኤርትራኖች የተጫወቱት እንቅስቃሴ ስንመለከት ኤርትራኖች «የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትግራይ ተማሪዎች “የፖለቲካ ሃርለቶችን” እንዲሁም ከአማራ ተማሪዎች ዋለልኝ መኮነንን {ልክ እንደ የዛሬዎቹ የጎጃም ፋኖው አስረስ ማረ እና የወሎው “ጀነራል” (ተብየው) ተፋራ ማሞ ፤ ከዚያም ትግራይ ውስጥ የዳበረው “የፖለቲካ ሃርለቶች ስብስብ” 17 አመት ሙሉ ተጉዞ  ኤርትራን ለማስገንጠል ትግራይ ውስጥ ያየነው “የፖለቲካ ሃርለቶች ባሕሪ” ማለት ነው “የፖለቲካ ዝሙትነት” የምንለው ።

ወሎንና ጎጃምን አልፋችሁ ትግራይ እና ኤርትራ ያሉት “የፖለቲካ ውሹማዎቻችንን” ትነኩዋቸውና “እከመርባችኋለሁ” የሚሉ የፋኖ  “ፖለቲካል ሃርለቶች” ለሽፋን የሚጠቀሙበት ቃል  የፖለቲካ ውሽሞቻቸውን “ሻዕቢያ እና ወያነ” የሚለውን ስማቸውን ላለምጥቀስ ሲሉ የሚጠቀሱት የማምለጫ ቃል ሕዝብ የሚል ቃል ነው። «የትግራይ ሕዝብና የኤርትራ ሕዝብ» በሚል ሽፋን ነው

ሕዝብ ምን ማለት ነው?

 የትግራይ ሕዝብ መስሎኝ በየሚዲያው እያስተጋባ “አማራ የወሰደበንን የራያና የወልቃይት ርስታችንን ፈቅዶ ይመልስልን ካልሆነ አስገደደን በጉልበት እናስመልሰዋለን» እያለ ያለው “የትግራይ ሕዝብ” መስሎኝ?!!። (ኤርትራ ሕዝብ የሚባለውም እንደዛው ነው፡ ባሕራችን ትነኩና የሚከመሩባችሁ የኛ “ሃርለቶች” አዘጋጀተንላችኋል ወዮላችሁ የሚሉን እኮ ናቸው፡  አይደሉም እንዴ??)፤ ሰለዚህ ተፈራ ማሞ የአማራን ሕዝብ ወጣት ትውልድ እንዲሞትለት እያደረገ ያለው “ፖለቲካዊ ዘሙትነት”  ሃገርና “ኤርትራ” የተባለ ባዕድ ነኝ ብሎ የተገነጠለ ሕዝብን ነው የአማራ-ፋኖ ወጣት መስዋዕት እንዲሆን እያዘጋጀው ያለው።

 (ለሱዳንም፤ ለግብጽም ያንን ያደርጋል)። ትግሬዎች እኮ ኢትዮጵያ ሱዳን ብትወር ከሱዳን ጦር ጋር እንሰለፋለን ብለው ማስታወቂያ ለጥፈው ሰልፍ አድርገዋል። ወይ ዘንድሮ!!

ሕዝብም ይሁን ወያነና ሻዕቢያ አንድም ሁለትም ናቸውና “ፖልቲካዊ ዘሙትነታችሁን አቁም።

ሌላው ሽፋን “የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው» የሚባለውን እንመልከት።

“የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው» የሚል የፖለቲካ ዝሙተኞች የሚልክሰከሱብት ስልት ነው።ህ የከሰረ ለብዙ አመታት ሞግተነው በተግባር ከስሮ  ያየነው “የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው፡ በሚል የፖለቲካ ሽርሙጥና ፤ አክራሪ ውሃቢስቶቹን ፤ እሰላማዊ አባጃራዎችን ፤ እሰላማዊ ጃዋሮችን፤ ማሞካሸት የሻዕቢያ ፤ የነ ብርሃኑ ነጋ እና ተገንጣይ ኦሮሞዎችን (ኦንጎችን፤ ከማል ጎልቹዎቹን፤ ሌንጮ ባቲዎችን ፤ ሌንጮ ለታዎችን፤ ፤ የኦጋዲን ኦብነጎችን እንዲሁም “አማራ ተወካይ እንዳይኖረው የጣረ “ቪዥን ኢትዮጵያየተባለ አማራን ያገለለ ግንቦት 7 (ኢሳት) የሚመራው የኦነግና የሻዕቢያ አድናቂዎች ስብስብ እንዲሁም፤ ስየ አብርሃዎችን ወዘተ፣ ወዘተ-በማሞካሸት “የፖለቲካ ዝሙት” ሲፈጽሙ “የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው» በሚል ነበር።

ወዳጅነትና የየጋራ ጋጋታ ፈጥረው ሲያደንቁሩን ፤ እኔ ራሴ በግባር ቀደም  እና ጥቂት አገር ወዳዶች ታግለን የጣልነው ስልት ነው (ይህ ጉራ አይደለም-የዛው ጊዜ ጽሁፎች ቪድዮዎችን መፈተሽ ነው) ።  በእዛን ወቀት “የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው»  በሚለው ጋጋታ እኛን እየሰደበ የነበረ ደጋፊና አዳማቂ  ዛሬ ስሜቱን መለጎም አቅቶት ፤ የፋኖ ፖለቲካ ዝሙተኞችን በመደገፍ የሚከንፈው በዙውን የዲያስፖራው አምሐራ ማሕበርሰየዛኑ ጊዜ የፖቲካ ዝሙት ፈጻሚ ቡደኖች አጨባጫቢ ነበር።

 አሁንም እየተደገመ ያለው ያው ነው። የገረመኝ ነገር፤ በጎጃም እና በጎንደር ውስጥ ፋኖ ለፋኖ በተደጋጋሚ እይተታኮሱ እርሰ በርስ ሲጋደሉ እያዩ ከወያነ እና ከሻዕቢያ ጋር ተጠርንፈው  ለነዚህ ታሪካዊ ጸረ አማራ ጠላቶች ለመሞት ዝግጁ መሆናቸው አንዳንድ የፋኖ መሪዎቹ ሲገልጹ፤ እነዚህ ዲያስፖራዎች ደግሞ “የጠላቴ ጠላት አጋሬ ነው» ዘላቂ ሰላም ያመጣል ብሎ የፖቲካ ዝሙት ፈጻሚ ፋኖዎችን “ምንም ወንጀል ይፈጽሙ ፤ ለጀሮ የማይጥም ምንም ነውር ይናገሩ” ያለምንም ማመንታት ፤ ያደጉበትና የለመዱበት ጭፍን ድጋፍ ሲሰጡ ማየት የሚገርም ነው። ድመት መንኩሳ አመልዋን አትረሳ!!!!

አሁን ወደ ማስረሻ ሰጤ እና መከታው ማሞ ንግግሮች እናምራ፡


ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ጎጃም ውስጥ ካሉት ፋኖዎች ውስጥ ራሱን የቻለ የፋኖ ድርጅት መሪ እና  እስክድር ነጋ ከሚመራው “የሸዋ ፋኖ” የ አ. ፋ. ሕ. ድ.  አመራር አባል ነው። ትናንት ያደመጠኩት በካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በወሎ እና በጎጃም ፋኖ “የፖለቲካ ሃርልቶች” የፈጸሙት “ፖለቲካዊ ዝሙትን” አስመልክቶ የሰማውና (ማስረጃ አለኝ) ያለው ለኛ “ለኢዮጵያኒስቶች” ያስተላለፈለንን ካንድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጰያዊ የሚጠበቅ አርበኛዊ መልእክት  የሰማሁት በደስታና አከብሮት ነበር።፡ 

በተቃራኒ የሰጠው የ “አ. ፋ. ሕ. ድ.” ምከትል እና የ “አ. ፋ. ሕ. ድ.” ሰራዊት አዝማች የሚባለው “የፖለቲካ Neophyte” (የፖለቲካ ጀማሪ) የሆነው መከታው ማሞ የሚባለው ለማስረሻ የሰጠው መልስ አሳፋሪ ነበር።

ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ  ያንን ካስተላለፈ ወዲህ  ወደ አብይ ሊገባ ነው እያሉ ሲዝምቱበት ነበር። ቢገባም አባባሉ የሚሻር መልዕክት አይደለም።

ያም ሆኖ ማስረሻ ስለ “የፖለቲካ ሀርለቶቹ” የባንዳነታቸው እንቅስቃሴ በማስረጃና መረጃ አቀርባለሁ ሰላለ ያንን በጉጉት እንጠብቃለ

ካፒቴን ማስረሻ እንጀምር።


ሩ እንዲህ ይላል።


« ከተማ ውስጥ ከወያዎች ጋር በከተሞች ወጣ ገባ እያሉ በባንኮች በር ቆሞ ፎቶ መነሳትን እንደ ድ የሚቆጥሩ ፤ ከ2018 ጀምሮ የአማራን ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ እና ተዳፍኖ እንዲቀር  በታሪካዊ ጠላቶቻችን እጅ ተጠልፎ መውደቁንና በዚያው የሚንቀሳቀስ ሃይል መኖሩን በተወሰነ መልኩ በግልጽ አይተናል። ከወያኔዎች ጋር ተሰለፎ የአማራን ሕዝብ ጥያቄ እመልሳለሁ የሚል ፤ የአማራን ሕዝብ ጥያቄ እንዳይመለስ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር የቆመን አካል በጠላትነት ፈርጀን እኩል የምንታገለው መሆኑን በዚህ አጣሚ ለምግለጽ እፈለጋለሁ።......

ይልና

«እኛ ኢትዮጵያን እንወዳለን፤ እንደ ሀገር ኢትጵያ እንድትቀጥል እንፈልጋለን፤ ነገር ግን የወያነ ዓላማ አንግቦ ኢትዮጰያ እንድትበታተንና  ደካማ ሀገር እንድትሆን የሚፈልግ አውዳሚ ስብስብ በሕዝብ ትግል ወደ አንድ አካባቢ እንዲመሽግ እንደተደረገ የሚታወቀ ቢሆንም ....የዚህ  አጋርና የዚህ ፈረስ ሆኖ መምጣት ክሕደት በመሆኑ ማቆም እንዳለባቸው “በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ ባርበኛነት ስም የሚንቀሳቀስ  ማንኛውም አካል፤ ሊያቆም እንደሚገባ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።

ዝርዝር ሁኔታዎች በማስርጃና በመረጃ ለሕዝባችን የምናሳውቅ መሆኑን  እየገለጽኩ ስለዚህ በግራም በቀኝም ያሉ የፋኖ አመራሮችና የፋኖ አባላት የማንም ዕርዳታ ሳንፈልግ “በራሳችን መቆም  እንችላለን”። «በበሰበሰ ቁምባላ» የሚሸወድ  የአማራ ወጣት የሚታለል እንደሌለ መታቅ አለበት። ስለዚህ በራስችን እንቁም.......በራሳችን እንደንቆም እንጂ ከታሪካዊ ጠላቶቻቸን ጋር ያውም እንደ ሕዝብም እንደ ሃገርም በኢትዮጵያ ላይ የሚቆምር አካል ጋር መቆም አሰፋላጊ አለመሆኑ አውቆ ወደ ድርጅታችን እንዲመጡ ጥሪ ማድረግ እፈልጋልሁ። አመሰግናለሁ። (ማሰርሻ ሰጤ) (የጎጃም ፋኖ ጠ/ግዛት ዕዝ አዛዥና የአፍሕድ የውጭ ጉዳይ ሓላፊ)»። ይላል።

የመከታው ማሞ ያለመብሰል በልሹነትና ለባንዳዎቹ ድጋፍ ሰጪ ንግግሩ እንዲህ ይላል፦

«ምናልባት አርበኛ ካፕቴን ማስረሻ  በተለቀቀው (ንግግር) ሙሉ በሙሉ አላዳመጥኩትም ፤ሙሉ በሙሉ ባልሰማውም ዞሮ ዞሮ  በደረሰኝ መረጃ እንደ አመራር ፤ እንደ አፋሕድ ሥራ አስፈጻሚም የሚወክል እንደ ድረጅትም ምንም ዕውቅና የለውም። እንደ ድርጅትም እንደ ግልም ምንም የምናውቀው የለም። «(መልዕክቱም) አፍሕድን የሚወክል አደለም» ብየ ነው የምገልጸው። አንዳን ሰዎች ባስረዱኝ እንጂ በተሰጠው መልዕክት ላይ የአፍሕድ አቋም እንዳሆነ ለመግለጽ እወዳለ»። የላል መከታው ማሞ።

አንደኛ ፤ ...ሙሉ በሙሉ አላዳመጥኩት ፤ሙሉ በሙሉ ባልሰማውም” ይላል; በጆሮው ባላዳጠውም በክፊል አድምጫለሁ ይላል፤ ያቺ  4 ደቂቃ የማትሞላ ንግግር ግማን አድመጦ ግማሹ ላይ ሲደርስ ለማድመጥ የድረገጽ ሞገድ ችግር  እንዴት ሊገጥመው ቻለ? ለማድመጥ ሙሉውን እንዳደመጠው አልጠራጠርም፡ ቢሆንም ባላዳመጠውና በሁለተኛ ስማ በለው መረጃ (በሰከንድ-ፓርቲ) መረጃ ተንተርሶ መስ መስጠቱ ምን ይባላል? ምንስ አስቸኮለው? በካፒቴን ማስረሻ የተላለፈው መልዕክት ግለጽ እና አርበኛዊ  መልዕክት ነው። በሚገርም ነገር መልዕከቱ መከታ ማሞና ድረጀቱ በመገለጫ ሳይቀር በተደጋጋሚ ሲያስተላለፈው የነበረ መልዕክት ነው፡ (ማስረጃውም በዚህ ፌስ ቡኬ ባለፈው ሰሞን የተለጠፈው አበበ ያነበበው የድርጀቱ መግለጫ እንደገና አድምጡት) ምንም ልዩነት የለውም« ከወያኔዎች ጋር እየተላላሱ ያሉ የፋኖ አመራሮች አሉ፤ በራሳችን እንቁም.......በራሳችን እንድንቆም እንጂ ከታሪካዊ ጠላቶቻቸን ጋር ያውም እንደ ሕዝብም እንደ ሃገርም በኢትዮጵያ ላይ የሚቆምር አካ ጋር መቆም አይገባም።ከ2018 ጀምሮ የአማራ ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ እና ተዳፍኖ እንዲቀር  የሚጠሩ የፋኖ አካላቶች አሉ» የሚለው  «የተላለፈው መልዕክት አፍሕድን ሚወክል አይደለም» የሚለው የመከታ ሞሞ ምክንያት ምንድ ነው?  

የሚሸት ነገር አለ። የድሮው የብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 አሸከር *ታጣቂ?* የነበረው የዛሬ የጎጃም ፋኖ የጦር አዝማች ሆኖ ለብዙ ነገር ተጠያቂ የሆነው

ዝናቡ ከተባለው ጋር ለመነጋገር ጎንደር ድረስ ተጉዞ እየተመካከረ ቢሆንም ማስረሻን ለማስራቅ መልስ መስጠቱ ማስረሻ እንዳለው የሚሸት ነገር አለ ማለት ነው።

ዕድሜ መስተዋቱ

ጌታቸው ረዳ