Thursday, July 31, 2025

ሃገረ-ትግራይ የሚሉ የቤጃ-ትግሬ ዝርያዎች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/31/25

 

ሃገረ-ትግራይ የሚሉ የቤጃ-ትግሬ ዝርያዎች

ጌታቸው ረዳ  

Ethiopian Semay 7/31/25

ሰላም ለክሙ! ሰላም ለናንት ይሁን ፡ ደህና ናችሁ?

"ሃገረ-ትግራይ" የሚሉ ሃገር አወዳሚ የትግራይ ተወላጆች በብዛትና በግሃድ ወደ መደረክ ከመጡ ወደ 7 አመታቸው ነው። ያለ ምንም ሥጋት እንዲንቀሳቀሱ የፓርቲ ምዝገባ ቦርድ ሕጋዊ ዕውቅና የሰጣቸው ደግሞ ሃገር አውዳሚው በታሪክ የሚመሳሰላቸው መንትያቸው “ኦነጋዊው” አብይ አሕመድና ጀሌዎቹ ናቸው። 

ወደ ዝርዝር ከመግባቴ በፊት ትግራይ የሚለው ስም ትርጉሙ ምን ማለት ነው? ይህን ስም ይዞት የነበረው ማሕበረሰብ አብዛኛው በድብልቅ እርሻ እና በከብት አርቢነት (ዘላን ሆኖ) ሲኖር የነበረ ማሕበረሰብ በመኖሩ ትግረ/ትግሬ/ትግራይ የሚለው ሥም እስካሁን ድረስ መተርጎም የሚቻለው ስሙን ተሸከሞት ወደ አሁኑ ትግራይ (ከወርዒ ምላሽ እስከ ብዙዎቹ የወያነ ቁንጮ መሪዎች ከመጡብት ዓድዋ እና አካባቢ) መጠሪያውን ተሸከሞት የመጣው ”አርብቶ አደር” ማለት ነው ቢባል ለእውነታው አይርቅም እላለሁ (The very name Tigre/Tigray means nomadic pastoralists)።

ትግራይ የሚለው ስም ራሱ አርብቶ አደር ማለት ነው፡ የምልበት ምክንያትየአሁኑ ትግራዮች መጠርያ መነሻቸው ሴማዊ ተናጋሪ የነበሩ ጥንታዊ በጃ/በጋ “ትግረ” ማሕበረሰብ የነበሩ ፤ በኋለኛው ዘመን በደቡብ እና ምስራቅ ሠብረው  ወደ መላዋ ኢትዮጵያ እንደተዘረጉት እንደ 16 /ዘመን ጋ&ላዎቹ  “ትግረ-በጃዎቹም” ከመረብ ምላሽ ወዲያ በሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ምድረበዳማ ምድሮች ሲኖሩ የነበሩት ብጃዎች መረብ ላሽ ወደ ታች ወደ አክሱምና ዓደዋ ደጋማ ቦታዎች ላይ ወረራ ለማድረግ ሞክረው የነበሩ ነገርግን በግእዝ አክሱማዊ ንጉሠ ነገሥት በተደጋጋሚ የተሻሩ ነገዶች ናቸው።

ትግሬ (ትግረ) በጃዎቹ ወደ አክሱም እየተጠጉ የመጡበት አጋጣሚ ሰበቦቹን እንመልከት

ዓረብ ሃገራት ውስጥ መናልባትምበዋናነት የመንውስጥ አይሁዶች በክርስቲያኖች ላይ ግፍ ይፈጽሙ ስለነበርፉን ለማስቆም ፤ በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የአክሱማዊው አፄ ካሌብ ወደ  ዓረብ (የመን) አገሮች ታዋቂ ዘመቻ ማድረጉ ይታወቃል። የካሌብ ጄኔራሎች ክልሉን ድል አድርገው ሰላምን ለረጅም ጊዜ መስርተዋል ሆኖም አረቦች እና “ምናልባትም” አይሁዶች “የሳሳኒድ የፋርስ ሀይል” (የኢራን ሃይል) ገብቶ እንዲያድናቸው ጥሪ በማድረጉ፤ የሳሳኒድ የፋርስ ሀይል” ጣልቃ በመግባት የኢትዮጵያን/አክሱማዊያኖችን/ ጦር ወግተው ከዓረብ ሃገር አስወጥቶ እየተከተለ አሳደዳቸው።

  ፋርሳውያን እና ዓረብ ደጋፊዎቻቸው ኢትዮጵያውያንን ተከትለው ባህር አቋርጠው እስከ ኢትዮጵያ የባህር ዳርቻ ድረስ እንደመጡ ይታመናል። ወይ በዚህ ወቅት ወይም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በ7ኛው ክፍለ ዘመን “የሙስሊም ዓረብ ኢምፔሪያሊዝም” መነሳት ተከትሎ ታላቁ የአክሱማውያን የአዱሊስ ወደብ በቀይ ባህር ላይ ወደብነቱ እንዲኮላሽ ተደረገ። አስተውሉ፡ ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን እና የኤደን ባህረ ሰላጤውን “በሙሉ” ለብዙ ሺህ አመታት ተቆጣጥራለች (ጥንት ቅድመ ክርስትና ዘመን ጀመሮ)።

አዱሊስን ጥፋት ተከትሎ ወይም በተመሳሳይ ጊዜ የአክሱምን መጥፋት እና የግእዝ አክሱማዊ ስልጣኔ ማክተም ተከሰተ ማለት ነው። በአጠቃላይ የፋርስ ወይም የሙስሊም አረብ ኢምፔሪያሊስቶች ጥምረቱን እንደ ተለመደው “የትግሬ አርብቶ አደሮች” አክሱምን ለመውረር በዚያች የጭንቀት እና የድክመት ሰት ላይ እንደተለመደው መረበን ለመሻገር ጥሩ አጋጣሚውን አግኝተውታማኝ” ሆነው በመገኘት ያው ትግሬዎቹ መጀመሪያ መረብ መላሽ ወዲያ ያሉት “ቦጎስ ፣ ሐማሴን ፣ ሰራየ እና አከለጉዛይን” አጥቅተው ከተቆጣጠሩ በኋላ ከዚያም “መረብን ተሻግረው” አክሱም ተቆጣጠሩና የአክሱም ያልነትና ግእዝ ስልጣኔ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና ሃይማኖቱን አኮላሹት። በእውነቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስልጣኔ እንደወደቀ ለዘላለሙ አሸለበ። ከዚያ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የትግራይ እና የትግርኛ ቋንቋን መስማት ጀመርን።

የአክሱማውያን እና የቅድመ-አክሱማውያን ዘመን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቦታ እና የነገዶች/የዝብ ስሞች ያሏቸው ጽሁፎች በድንጋይም ተቀርጸው ተጽፈው ይገኛሉ። ነገር ግን ትግረዎቹ አክሱም ካወደሙዋትና ከተቆጣጠርዋት በኋላ ካልሆነ “ትግረኛ/ትግራይ” የሚባል ቃል ወይንም ዝብ ሲነገር ሰምተን አናውቅም።

በታሪካዊ ጂኦግራፊ በትግሬ ወይም በትግራይ የተያዘው የግዛት የመጀመሪያ ወሰን በደቡብ ወርዒ መላሽ እና በምስራቅ ዓድዋ እንደሆነ ይታመናል። ስለዚህም የጥንቷ ትግራይ የአክሱምን ጥፋት ተከትሎ አክሱም እስከ ወርኢ መላሽ ድረስ እና ወያነ መስራቾች ከመጡበት አካባቢ በምስራቅ በኩል እስከ ዓድዋ ድረስ ትግራይ የሚል መጠሪያ ሰጥተውት እንደነበር ይታመናል። በእርግጥም እስከ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ድረስ ትግራይ  ተብሎ የሚጠራው የመጀመሪያ የግዛት መጠሪያ ወሰናቸው ይህ ብቻ ነበር።

ዓድዋ ለመረብ እና ለመረብ መላሽ ቅርበት ስላለው በሁለቱ መካከል ያለው የጠበቀ ግንኙነት ከጥንታዊው ክስተት ጀምሮ ሊሆን ይችላል።  ሆኖም የአክሱምን ወረራና ውድመት ተከትሎ ትግሬዎቹ ቀስ እያሉ ወደ ተለያዩ ቦታዎች መንቀሳቀሳቸውን (መጉሮፋቸውና መዋሃዳቸውን) አላቆሙም። በዋነኛነት አገው እና አገው ያልሆኑ ነገዶችን (ዛሬ ትግራይ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ) ሌሎች ነገዶችን እየዋጡና እየተዋጡ ወደ ደቡብ እየተንቀሳቀሱ ከነባሩ ግዕዝ ማሕበረሰብ ተደባልቀው እንደቀጠሉ ይታመናል። እና (continued perhaps to migrate as far south as Harar giving rise to the Adere Semitic speakers, and perhaps also to the Tigri Worji, etc.. They may also have moved to the center of Ethiopia giving perhaps rise to the Gurage –another Semitic speaking group both closely related to Tigre.. The fascinating exploration of the Tigrai past has only started with this small research work of mine and a lot remains to be uncovered.- ምንጭ Aleme Eshete -PhD በግል የደብዳቤ ውይይት ስናደርግ ለዚህ ጸሐፊና ላንድ ስተኛ ሰው የተላላከንበት የኢመይል ልውውጥ)

ይህ ነገድ ዘላን በመሆኑ ታሪካዊ አመጣጡ እና የአክሱም ሥልጣኔ አጥፊ በመሆኑ ወያነ የአክሱም ስልጣኔን እወክላለሁ እያለ የግእዝ ባሕል፣ ቋንቋ እና ፊደል የሚጸየፍ እና ዓረብና ላቲን ቋንቋ አፍቃሪ ሆኖ ኢትዮጵያን ለ27 አመት ሲገዛ የራሱን ማንነት የገለጠበት አጋጣሚ ሲሆን በእነዚህ በመሳሰሉ ሁሉ ምክንያቶች "ወያነ" ወይንም “ትግራይ” የሚለው ስያሜ በጥንት የኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ ኩራትና ክብርን አያበረታታም ዛሬ ትግራይ የሚለው አጠራር የተምቤን የዓጋመ የእንደርታና የራያ ሕዝብ ያለመቀበል አዝማሚያ ሲያሳዩ እያየሁ ነው

ጣሊያናዊው ጥንተ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ኮንቲ ሮሲኒ እንዳለው የትግሬዎች ታሪክ ይብዛም ይነስም ፣ በ15ኛው እና በ16ኛው ክፍለ ዘመን በደቡብ ምስራቅ የጋ#ላ ዘላን አርብቶ አደር የተደገመው ወረራ ታሪክ ድግምግሞሽ ነው። ይለዋል።

ጽሑፌን ላማሳርግ ያህል፦

አክሱምን እንዳፈረሰዋት ፤ ኢትዮጰያን ለማፍረስ ዛሬ ደጎሞ ሃገረ-ትግራይ” የሚሉ “የቤጃ-ትግሬ” ዝርያዎች “ኢትዮጵያ ሂደትዋን ያላጠናቀቀች “የብዙ ሃገሮች-መንግሥት”  ከሚሉት ጋር የሚለየን “የኢትዮጰያ ሕዝብ/ሃገር ሃገራዊነን ተጋመዶ ያጠናቀቀ - “አንድ ሀገ-መንግሥት” (ዋን ነሺን ስቴት)  ሕዝብ ነው፡ልበት ምክንያት ሕብረተሰቡ ከተለያዩ አቀጣጫዎ የዘመናት ፍሰትና መጋመድ (መዋሃድ) ኢትዮጵያ ል ሃገርነት እንዴት እንደተገነባች አዲስ የመጡትን በየአቅጣጫው አስገብታ በተፈጥሮአዊ ሕግጋት ቀስ በቀስ  እያዋሃደች መሰረታዊ ማንነትዋና ባህሎችዋ ሳይናወጡ ቢቆዩም ፤ ብሚያሳዝን ክስተት በነዚህ 50 አመታት ውስጥ ጥንታዊ ባሕሪያቸው በደመነብስ  የሚታገላቸው አንዳንድ የነዚህ “ዝርያዎችና አምሳያዎቻቸውበየነገዱ ብቅ እያሉ ኢትዮጵያን ልክ እንደ አክሱም ሥልጣኔ ለማውደም እየጣሩ ይገኛሉ። ስለሆነም እነዚህን ያለ ምሕረት መጋፈጥ ይኖርብናል። 

በሚቀጥለው ሳምንት አምሐራዎችስ እነማን ናቸው? የሚለው እንመለከታለን።

አመሰግናለሁ

ታቸው ረዳ Ethiopian Semay

Monday, July 28, 2025

ከፋሺስቶች ላቅ ከናዚዎች ከፍ ያለው የወያኔ ትግሬ ጭካኔ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/28/25

 

ከፋሺስቶች ላቅ ከናዚዎች ከፍ ያለው የወያኔ ትግሬ ጭካኔ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

7/28/25

ደደቢት ከወያኔ መሰረታዊ ሜዳ ላይ፣ ዜሮ ስድስት (ባዶ ሹድሽተ) ተብሎ የሚጠራ እስር ቤት፤ ለትግራይ ሕዝብ የናዚ ስርዓት የሚፈጽሙበት ነበር::  ይህ ከአደጉ በሗላ (ምስገበሉ) የተመለሱበት ሜዳ ስለነበር፤ ለሞት ተፈርዶ ወደዚሁ ሜዳ የሚላክ እስረኛ፤ ስጋውን በፍጹም አሞራ አልበላውም::የእስር ቤቱ ጭካኔና ስርዓት አጽረጋ ከተባለው ስፍራ እንደጀመሩት ዓይነት ነበር:: የኢዲህ ደጋፊ ነህ፣ ልጅህ ወይም ወንድምሀ የኢዲህ ታጋይ ነው፣ ተብሎ ይያዝና፤ ወደዚሁ ዜሮ ስድስት "ባዶ ሹዱሽተ" እስር ቤት ይወሰዳል፤ እንደደረሰም ስለ ንብረቱ ብዛትና መጠን የትስ እንዳለ ይጠየቃል::

መጠይቁ እንደበቃ ለጥቂት ቀን ደህና ቀለብ እየተሰጠው በሁለት በሶስት ቀን ውስጥ ከሌላ ተመሳሳይ እስረኛ ጋር እየተረዳዳ፣ ቢያንስ ሁለት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ  እንዲቆፍር ይታዘዛል፤ የጉድጓዱ ስፋት ወይም ዓይነት የሰው መቃብር አይመስልም፤ እንደ ውሃ ጉድጓድ ጠበብ ብሎ እየተቆፈረ አፈሩ ዙሪያውን ይከመራል፤ እስረኛው የቁም መቃብሩn ጭሮ እንዳበቃ ይወጣና በገመድ እጅና እግሩ ታስሮ፣ ዓለም በቃኝ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ ይመልሱታል::

ወያኔዎች እስረኛቸው ከመሞቱ በፊት ሲሰቃይ ማየት በጣም ያረካቸዋል::ቶሎ እንዳይሞት ትንሽ ቂጣና ጥቂት ውሃ በሜንጦ መሳይ በገመድ (በመገለል) ያቀብሉታል:: ሽንትም ሆነ ዓይነ ምድር መፀዳጃው ከዚያችው ጉድጓድ ውስጥ ነው::አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በሗላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት የለም:: እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋት በጎኑ መተኛት አይችልም::ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም ብቻ ነው::

ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር ፣ ሌሊት በብርድና በጤዛ እየተሰቃየ፤ የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ በሚፈጠሩት ትሎች (ዱቃ) ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም:: ቆዳውን ሰርስረው፣ ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱቃዎች ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው ቅብር ያድርጉታል::

አንዴ ወደ ቆፈራት ጉድጓድ ከተጣለ በሗላ፤ በምንም ተአምር መልሶ መውጣት የለም::እስረኛው በዚያች ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እግሩን መዘርጋትና፤ በጎኑ መተኛት አይችልም::ተጨብጦ መቀመጡ ከደከመው፣ አቅሙ ከቻለ ማድረግ የሚችለው መቆም ብቻ ነው::ኩርኩም ብሎ ቀን በፀሐይ ሃሩር ሌሊት በብርድ በጤዛ እየተሰቃየ፤ የተፈጠረባትን ቀንና አገር ዘር ሲረግም፤ ከመሞቱ በፊት ከመሬቱና ከሰውነቱ በሚፈጠሩት ትሎች (ዱቃ) ሰውነቱ እየተበላ፣ በሰው ላቦትና በመሬት ሙቀት የሚፈጠሩት ትሎችም፤ መርዘኞች ስላልሆኑ ቶሎ አይገድሉትም::ቆዳውን ሰርስረው፣ ስጋውን በልተው፣ አጥንቱን መፈርከስ ሲጀምሩ፣ እስረኛው በመጨረሻው በአፍና በአፍንጫው በዓይኖቹም ትሎችና ድዱ ይፍለቀለቁና፣ አሰቃቂ በሆነ መርገም ህይወቱ ከላፈች በሗላ፣ በዚህ የመርገም ትእይንት የማይሰቀቁ ወያኔዎች በጉድጓዱ ዙሪያ ያለውን አፈር መለስ አድርገው፣ እጅ እግሩን ታስሮ እንደ ተኮረኮመ እዚያው ቅብር ያድርጉታል::

ታዲያ  ከዚሀ አሰቃቂ ሞትና አውላላ ሜዳ ላይ ሳይታሰር እህልና ውሃ አጥቶ ከወደቀው ህይወቱ ሳታልፍ ጆፌ አሞራ (ንስር) ዓይኑን ሲነጥቀው መከላከል ካቃተውና ከነህይወቱ አሞራ ሥጋውን ከሞረቸፈው ሻዕቢያ ግፍ ከፈጸመበት ምርኮኛ የደርግ ሠራዊት የትኛው የሻል ይሆን? ብለን ብንጠይቅ ለሚዘገንን የተለያየ አሰቃቂ ሞት፤ ከናዚ ላቅ ብለው የተገኙ፤ ሰው ለሰው ህመም መፈወሻ ከቅጠልና ክፍራፈሬ መድኃኒት ለማግኘት ምርምር በምካኄድበት ዘመን የሻዕቢያ እና የወያኔ ፈላሰፋዎች (የአጎትና የአክስት ልጆች) በታሪክ ለትውልድ የሚያሳፍርና የሚያስኮንን፤ በወገን ላይ መግለጽ የሚያስቸግርና የሚዘገንን ጭካኔ አገዳደላቸው አይበላለጡም ብሎ ማለፍ ይቻላል።

በጉድጓድ ውስጥ ከነህይወቱ በትል ተበለቶ እንዲሞት የሚፈርዱበት ዓላማቸውን ላላመነና የሚጠረጠሩት የትግራይ ተወላጅ ብቻ ነው። በዚህ የጭካኔ አገዳደል ተሰቃይተው እንዲሞቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች እነ “ሃበተ ገብረተንሳይ፤ ተኽላይ ገብረመስቀል ፤ ወይዘሮ ወርቂ ምንጭራ እና ልጃቸው አቶ አታክልቲ ሥዩም ( በከተማ ሸራሮ ራፖል ጸሓፊ የነበረ ልዑል ራሥ ሥዩም መንገሻ ልጅ)” አሉበት።

በነገራችን ላይ ምናልባት ታሪኩን ለማታውቁ ፤ራስ መንገሻ ሥዩም ከለውጡ በፊት ቀደም ብሎ፤ አቶ አታክልት ሥዩምን ፤ ወንድሜ አይደለህም፤ አባቴም ልጃቸው መሆንክን አልነገሩኝም ብለው ያለተቀበሉት በሽሬ አውራጃ ሰየምት አድያቦ ውስጥ የሚኖር ሰው ነበር።

እናቱ መደባይ ታብርና ሠመማ ያደጉ ከጠቁር ቤተሰቦች (ድሮ ባርያ) ተብለው ተንቀው ከሚጠሩ ወይዘሮ የተወለደና፤ እናቱም እስከለውጡ ድረስ በከበረቴ ሥርዓት ጥላ ያዥ አስከትለው በስናር በቅሎ በመንሸራሸር እሰከ እርጅናቸው ድረስ ተከብረው የኖሩ ወይዘሮ ነበሩ።

ምንም እንኳ ራስ መንገሻ አታክልትን በወንድምነት ባይቀበሉትም ቅሉ፤ የተወለደበት አውራጃና የአካባቢው ሕዝብ የመሳፍንት ዘር መሆኑን ስለሚያውቁ ፤ ወያነ ትግራይም ዘሩንና ሐረጉን ስለሚያውቅ አረጋገጦ ነበር ለሞት ያበቃቸው።.......

ግደይ ባሕሪሹም - አሞራ -ገጽ 207-209

 እያለ የወያኔዎች የጭካኔ ጥግ ይዘረዝራል።

አመሰግናለሁ።

  ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay