Tuesday, April 29, 2025

እፊታቸን ላይ ውሃ እንደ ያዘ እንስራ ፍርክሽክሹ የወጣው የፋኖዎቹ ትግል አምሐራ አምሐራን መግደል ጀምሯል! ነገ የገደሉትን ሬሳ ወደ መጎተት ተዛውሮ እንዳናይ ያሰጋል ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/28/2025

 

እፊታቸ ላይ ውሃ እንደ ያዘ እንስራ ፍርክሽክሹ የወጣው የፋኖዎቹ ትግል አምሐራ አምሐራን መግደል ጀምሯል! ነገ የገደሉትን ሬሳ ወደ መጎተት ተዛውሮ እንዳናይ ያሰጋል

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

4/28/2025


“አድማጭ የታዘበኛል” የማይሉ ሲዋሹ እጅግ እስከ-ጥግ ድረስ የሚቀደዱ፤ የተቃዋሚያቸውን ስም ለማጠፋት ሲፈልጉ  ራሳቸውን ለትዝብት የሚጥሉ፤ ዓለም ይዘግቡዋቸውን የሃገራችን ታሪኮችን የሚያጠለሹ “የወያነ ፤ የኦነግ/አብይ-ኦሮሙማ እና ፤ የሻኧቢያ መሪዎች” የውሸት ባሕሪ ለብዙ አመት ታዝበናቸዋል። ዛሬ ደግሞ በጎበዝ አለቆች የሚመሩ ፋኖ ብሎ ራሱን በውሸት የሚኮፈስ የነዚህ ደረጀቶች ባሕሪ” የተላበሰው የጎጃሙ የፍሺስት ዱርየ ታጣቂዎች መሪ የሆነው የዘምነ ካሴ “አፈቀላጤ” ነኝ የሚል “ጮርቃ” የመገዳደል ጦርነት እንዳወጀ ሲናገር አሁን ጥዋት ሰማሁት (አዲስ አዋጅ ባይሆንም)።

ይህ «ትንሽ ሰው» የመግደል አዋጅ ብቻ ሳይሆን ሲዋሽም ዳርቻ የለውም።፡እስክንድርና ጋዶቹ የሚመሩት “የአምሐራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት” “ድርጅቱ ስላዳከምነው የትጥቅ እርዳታ የሚያገኘው ከአብይ አሕመድ ነው” ሲል “አድማጭና ታሪክ” ይታዘበኛል ሳይል ሳይሰቀጥጠው የድርጅቱን መሪዎችና የድርጅቱን አወቃቀር ዓላማና ስም በውሸት ከማጠልሸቱ ባሻገር፤ ይህ ለአምሐራና ለኢትዮጵያ የቆመ ብቸኛ የሽምቅ ታጣቂ እኛ ብቻ ስለሆንን “መደምሰስ አለበት፤ ጀምረናቸዋል፤ ጦርነት ገጥመናል፤ አዳከመነዋል፤ እናጠፋቸዋለን!” ሲል በፋሺት የብሔረተኛ ድንፍታ ሲጎረን ዛሬ ጠዋት ሰማሁትና ገረመኝ።

 ከበዙ አመታት በፊት የአንድነት ሃይሎች ነን ሲሉ የነበሩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድረጀቶችና ምሁራን “ቤተ ክርስትያናት ሲቃጥሉ የሚያቃጠለው ወያኔ ነው ፤ ሃየማኖት የሚጻረር  ሃገራችን ውሰጥ ካለ ወያኔ ሌላ የለም እያሉ “ከኦነግ” እና ‘’ከእስላማዊ ኦሮሞ ነጻ አውጪ” ግምባር ጋር በየ ሃገራቱና ከተማዎች” እያዞሩ ባንዴራቸውን በየ አዳራሹ እያስጌጡና ገራገሩን አድማጭ እያስጨበጨቡ ጥብቅና ቆመው ሳያቸው በነበረው ወቅት ሰልገረመኝ «በዚህ ቀውስ ውስጥ እንዴት ልንገኝ ቻልን?» በሚል አንድ ጽሑፈ ጽፍይ ነበር።

አሁንም በደጋሚ የአምሐራን ሕልውና እጠብቃለሁ ብሎ “በሚያስቅ ጉጉት” ራሱን ለማንገሥ ሲል «እኔ አጠናፉ አባተ አይደለሁም ፤ “እኔ የፋኖ ንጉሥ ነኝ ፤ ሳልወለድ ትንቢት የተነገረልኝ ፤ከዘር የተላለፍልኝ አንጋሽና ነጋሽ ነኝ” እያለ የጎጃም ጀልዎቹን የሚያስፈነድቅ በልጣብልጥ የ የጎጃሙ ታጣቂ መሪ ዘመነ ካሴ እስክንድርን ካላጠፋሁ (የድሮ ነገሥታትን እያነሳ) “ጎጃም መንገሥ አይችልም” በሚል ማሃይም አስተሳሰብ ጦርነት እንደገጠመ አስነግሯል።

 እንደምናውቀው ይህ ሰው መምሕራንና ተማሪዎች ሲያዋከብ፤ ሲጠልፍ፤ ሲያግት ፤ ሲያስር ፤ ሲረሽንና የፋኖ ታጣቂዎቸን እኔ ካልመራሁ ብሎ (እያፈነ ሲያሰገድልና አስገድዶ ሲያታግል - ኮ/ል ጌታሁንና በሥሩ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን (ወደ ዘመነ ታጣቂ ታፈነው ምን እንደደረሰባቸው እና የተቀሩትም እንዴት ወደ ዘመነ እንደተቀላቀሉ ታሰታውሳላችሁ) ፤ የጋዜጠኞችንና የዶክተሮችን አፈና እና እገታ ልብ ይለዋል)። አሁን ደግሞ “እስክንድርንና ታጋዮቹን” ካለገድልኩና ካላጠፋሁ ብሎ ከአምሐራ ታጋዮች ጋር ጦርነት ጅመርያለሁ ደምስሻለሁ ሲል እውነተኛ አምሐራዎች መጠየቅ ያለባችሁ «በዚህ ቀውስ ውስጥ እንዴት ልንገኝ ቻልን?» ማለት አለባችሁ።

ብዙ አመሐራ ወጣቶች ፋሺዝምና የብሔርተኛነት እንቀሰቃስዎች ባሕሪ ምን እንደሚመስል  የሚያውቁ አየምሰሉም። በፋሺስታዊ እንቅስቃሴዎች መካከል የተለመዱ ጭብጦች የሚያጠቃልሉትን እንመልከት፡-

“ፈላጭ ቆራጭነት፣ ብሔርተኝነት (የዘር ብሔርተኝነት እና ሃይማኖታዊ ብሔርተኝነትን ጨምሮ) ፤ ወታደራዊ ድንፋታነተን ፤ የአካባቢ አጉራዘለል አለቃነት ስሜትና አልገዛ/አለገብርም የሚልውንም ማንበረከከ የፋሺዝም ባሕሪያቶች ያጠቃለሉ ናቸወ። ጎጃም ውስጥ አቆጠቁጦ እያየነው ያለውንም ይህንኑ ባሕሪ ነው።ሰለዚህም አምሐራ ምሑራንና ወጣቶች በዚህ ቀውስ ውስጥ እንዴት ልንገኝ ቻልን? በለው ቢጠይቁና ቢመራመሩ ችግሩ ሊታያቸው ይችል ይሆናል እላልሁ።

በዚህ ጥያቄ ውስጥ እንዴት ልንገኝ ቻልን? የሁላችን ጠያ መሆን ያለበት የመወያያ ርዕስ መሆን ያለበት ነው። ለጥያቄው መልስ ስጡ ብትባሉ ብዙዎቻችሁ የምትሰጡት መልስ የለመዳቸሁት መልስ ሰልሆነ “ዲሞክራሲ” በመታጣቱ ነው እንደምትሉ በእርግጠኛነት መናገር እችላለሁ።

 እንዲህ ያለ ድምዳሜ ልትይዙ የቻላችሁበት ምክንያት “የፖለቲካ መሪዎችና ተቃዋሚ ሚዲያዎች” በዚህ እምነት ብዙ ጊዜ ደጋግመው ሲያስተምሩና ሲሞግቱ በመስማታችሁ፤ ያንን እንደ እውነታ ተይዞ ዲሞክራሲ ያለማመን  ለዚህ ዳርጎናል፤ ወደ እሚለው ድምዳሜ ልትድርሱ አስችሏችሗል (እውነታ ቢኖሮውም ቅሉ)  ለመሰደዳችን እና ለመበጣበጣችን ዓይነተኛ ምክንያት ዲሞክራሲ በመታጣቱ ሳይሆን፤የምንከተላቸው መሪዎችና ድርጅቶች/ወይንም መንግስት እና ሚዲያ፤ “ስለሚዋሹንም ጭምር ነው። አንዳንድ የፋኖ መሪዎች እየተከተሉት ያለው ባሕሪ ይህንኑ ነው።

ማስተዋል ያለባቸሁ ጥያቄ ያለ ዲሞክራሲ ለዘመናት የኖሮው የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ የራስ ግጭት ሲከሰት ተሰብስቦ እየፈታ ፤ የሚያጔጉ 3 የባሕር በሮች ዋና ሆኖ ፤ ሕዝቡም የነጮችና የዓረቦች ገረድና ዘበኛ ለመሆን ወደ ስደት ሳይሄድ፤ እንዴት ኖረ ብለን ብንጠይቅ ፤  መሪዎቹ “በውሸት አትማሉ” የሚለው ሃየማኖታዊና ሕጋዊ መመሪያ በመተግበር ነው።  ቅማል ሱሪ ያስፈታል ፤ ውሸት ሃገር ይፈታል” የሚለው ዕውቀት ስለነበራቸው ነው።

መሪዎች (ጫካም ይኑሩ ከተማ)  እንደ ዛው በዚህ 50 አመት ውስጥ ያሳዩት የውሸት ባሕሪ በታሪካችን አላየንም። ሕዝቡን እየዋሹ አስከፊ ዘመን አምጥተውለት እነሆሲሰደድ፤ሲዋረድ፤ ሲንገላታእንደዛሬ ስቃይ ደርሶበት አያውቅም 

ለዚህ ሁሉ መከራና መበጣበጥ “መሪዎች” ገድለው ሳይቀጡ፤ እንደገና ሥልጣን ሲሰጣቸው ፤ ሲዋሹ ድጋፍና ጭብጨባ ሲቸራቸው ፡ አምባገነኖችን እየካብን በአገራችን ውስጥ ቁቡል ሆኖ በመታየቱ ነው

ለብጥብጥ ባሕሪ ምክንያት ዲሞከራሲ ማጣት ሳይሆን፤ ከዚህ ዘልቀን መሰረታዊ መነሾውን መመርምር ያስፈልጋል። የሚጎመዝዙ ዋሾ መሪዎችና ነብሰ ገዳዮችና ወረበላ ታጣቂና መሪዎች በፋኖ ድርጅቶች ውስጥ በገፍ ተፈልፍለዋልአሰገራሚ ያደረገው ደግሞ “የፋኖ መሪዎ በዋሹ ቁጥር፤ ሕብረተሱም አብሮ ይዋሻል፤ወይንም ሲዋሹ ይታገሳቸዋል፤ወይንም ያምናቸዋል። ውሸት ሕብረተሰብን የሚገድል እና የሚያጋድል፤የሚያሳስት መሰረታዊ የሆነ ማሕበራዊ ነቀርሳ እንደመሆኑ መጠን ፤ ‘ዋሾ’ መሪዎች በዋሹ ቁጥር ሕብረተሰቡም አብሮ እየዋሸ ወይንም ‘እየታገሳቸው’ በሄደ ቁጥር የሚፈለገው ሰላማዊ የሆነ ፍትሕ የነገሰበትና ‘ተጠያቂነትን’ የሚያከብር ስርዓት እንዳይመጣ እንቅፋት ይሆናሉ ማለት ነው። አሁን እየሰማነው ያለውና እያየን ያለው የፋኖ ይህንኑ ነው። (በተለይ ትችቴ በዘመነ ታጣቂ ላይ ነው፡ በወያኔ የታዘብኩት ባሕሪ በዚሀ ልጅ እያየሁበት ነው)።

 ውሸት የሚል ቃል ስደጋግም በቀላል አትዩት። ውሸትና ዋሾ መሪዎች” የመቀበል ባሕል እያጎለበትን በመምጣታችን ለቀውሳችን ተጠያቂዎች መሪዎቹ ሳይሆኑ እኛ የመሆናችን ጉዳይ አስገራሚ ያደርገዋል። ተጠያቂነት ያለው ስርዓት እንዳይሰፍን ዋሾ ‘መሪዎች’ ልቅ እየለቀቅን፤ እነሱ ሲያብዱ ባልታሰበ ድንገተኛ እምርታ እኛም እነሱ ጋር እየዋሸን እና እያበድን ቀስ በቀስ “ዕብድ ሕብረተሰብ” ወደ መሆን እየተሸጋገርን ነው፡ ይህንን እንመን።

 በፋኖ ላይ የታየው ባሕሪ ፡ፋኖ ከመመስረቱ በፊት የነበረ ነው (ወያኔ ባሕሪ ከዘመነ አመራር የማመሳስለውም በምክንያት ነው)። ለ37 አመት ፤ የሃይማኖትም የፖለቲካ መሪዎችም ከእውነት ርቀው “እየዋሹና ወንጀል እየሰሩ” ሕዝብን ሲመሩ ባመጡት ሰበብ የቀወሰ ሕብረተሰብ በብዛት እየተበራከተ መምጣቱ አሁን ያለው ፋኖ ላይ ገሃድ ወጥቶ እያየነው ያለው የሥልጣን ጉጉትና የመዋሸት ባሕሪ የዚ እውነታ ስበት (ገራቪቲ) ነው።

ይህ “እገሌን ካላጠፋሁ አላርፍምና ፤ ጥላሸት የመቀባት (የመዋሸት) ባሕሪና ወንጀል ሠርቶ ሳይጠየቁበት ተንደላቅቆ በነፃነት መኖር አፍሪካ ውስጥ ቢታይም በተለይም “ኤርትራም ሶማሌም እኛም  ማንታችንን ያጣን ማሕበረሰብ ወደ መሆን የተከሰተበት ሰበብ ይኼው ተጠያቂነት ያለመኖር ምክንያት ነው።

በኮሎኒያሊስቱ ኦሮሙማው መንግሥትም ይሁን በፋኖ መሪዎች እያየነው ያለው ፋሺስታዊ ብሔረተኛነትና ክፍለሃገራዊነት ልክ እንደ ፍትሓዊና የሕልውና መከላከያ መንገድ አድርገው ሕብረተሰቡ ሲዋሹት ሕብረሰተቡም አብሮ በመዝለሉ የቀው ተዋናይ እና ሰለባ ሆኗል።

ውለን አድረን ለጠንን ባልንበት ዘመን ወደ አራዊት ባሕሪ ተለውጠን አምሐራን አምሐራን በመግደል የተጀመረው ወንጀል ሬሳ እንዳይቀበርም እየተደረገ መሆኑንም እየሰማን ነውአሁን ደግሞ አምሐራን አምሐራን መግደል መጀመራቸውና “እንዳይኖሩ ሁሉንም እንጨርሳቸዋለን” እያሉ ያለ ምንም ሰቀቀን በሚዲያ “የጭፍጨፋ ወንጀል” እንደሚፈጽሙ በኩራት በመደንፋት ስብእናቸውን አሽቀንጥረ የጣሉ ወያኔ የሚያስንቁ “የጫካ ነብሰገዳይ ወረበላዎች” አፍጠው መተዋል። አምሐራዎች ኢትዮጰያዊ የአምሐራ ባሕሪያቸውን ጥለው ወደ አረመኔያዊ ባሕሪ ገብተል።

ፋሺስታዊና አክራሪ የብሒረተኛነት በሸታ ፋኖ ውስጥ ገብቶ ይፋ ሆኖ እየኮሩበት ነው። የብሔርተኛ ፖለቲካ መጨረሻው ስብእናን ነጥቆ የራሱ ያልሆነውን ነገድ በቻ ሳይሆን አሁን እያየነው እንዳለው የጎጃም የዘመነ ፋኖ አምሓራን ለመጨፍጨፍ ዛቻ እንዳወጀው ሁሉ በመጨረሻም የራሱንም ወገን እንደሚበላ እያያችሁት ነው።

አስቸኳይ የእርማት መንገድ እንዴት እንደሚወሰድ ባላውቅም ፤ እርማት ካለተደረገበት መግደል ብቻ ሳይሆን ዘመነ ካሴ እንደደነፋው «ጥይት አርከፍክፌበት ጥይት ካለቀብኝ መላ ስውነቱን በእሳት አቃጥለዋለሁ” ሲል እንደተናዘዘው ሁሉ» ብሔርተኛ ክዚያም አልፎ ሬሳውን መሬት ለመሬት እየጎተተ፤ እየረገጠ፤ ሬሳ እንደሚያቃጥል (ሰንደቃላማ ያለበትን የእስክንድር (መስል) ከናቲራ ሲያቃጥሉ የዘመነ የጎጃም ፋኖ ወረበላ ታጣቂዎች የሚናገሩትና የሚሰሩት ሥራ ጥሩ ማሳያ ነውበሞተ ሬሳ ላይ ጥላቻውን እንዲገልጽ የሚያስገድድ አደገኛ በሽታ እንደሆነ ነው ደጋግመን ስናስጠነቅቅ የነበረው

አሁን በጎጃሙ ዘመነ ካሴና በቃል አቀባዩ (ደም የጠማው ማሃየሙ ማርሸት) ዛሬ የዘር ጭፍጨፋ (የጅምላ ገደያ አዋጀ) ሲያወጅ ያደመጥኩት እስክንድርና መከታው ማሞ፤ ኮ/ፋንታሁን ሙሃቤ ፤ ደረጀ በላይ ፤ ሰለሞን አጣናውና አበበ...፤ ጌታ አስራደ ወዘተ..የመሳሰሉ ሐቀኛ አምሐራ ኢትዮጵያዊያን የሚመሩት “የአፋሕድ ፋኖ” ታጣቂ ላይ “የመጨፍጨፍ አደገኛ “የሽብር አዋጅ” በወቅቱ ማስቆሚያ ካልተበጀለት ያስጠነቀቅነውን ማስጠነቂያ ሳንሞት በዓይናችን ለማየት በዝገታ እያየን ነው

 ታሰታውሱ እንደሆን “ወያኔን” ሰቃወምና ስተች አምርረው የጠሉኝ ሺዎች ነበሩ፤ ስለው የነበረው አልተቀብሉኝም፡ ዛሬ ያ እውነታ ተረደተውት ይፋ ወጥቶ ስለው የነበረውን እውነታ ተቀብለው እያየሁ ነው። የጎጃም ፋኖ የዘመነ ተከታዮችም እኔን ይጠሉኛል የስደቡኛልም። በዛው የመሰደብ ውሽንፍር ሰላለፈኩ አለገረመኝም።

ተከታዮቹ በወንዝ ልጅነትና አካባቢነት እየተሰባሰቡ መሪዎቻቸው ሲዋሹና ወንጀል ሲፍጽሙ ሽፋንና መድረክ እየተሰጣቸው፤ በግልብነት  እየተጓዙ ፖለቲካው እና ሃይማኖቱ ወደ እንሰሳ ባሕሪ አስገብተውታል።የማታ እራት ለማግኘት “ጠላ፤ የስሙኒ አረቄና ሲጋራ” እየሸጡ ለጆቻቸው የሚያሳደጉ ድሃ እናቶች አሰርው ፤ ገርፈው በማሰቃየት “እንዳይሸጡ” አግደው ወደ ልመና እንዲሰማሩ እያስገደዱዋቸው ይገኛሉ። አፈሙዛቸው ወደ ድሆችም አዙረውታል። ለዚሀ ነው “ወረበላዎች” ናቸው የምለው።

ይህንን የወርበላ ታጣቂ ቡድን በመከተል “ውሸትና ወገንተኛነት ፖለቲካውንም ሃይማኖቱንም የዜና አውታሮችን ሳይቀር ተቆጣጥሮአቸዋል። በውሸት የሰከሩ ዜጎች የሚሰሩት ስራ በገሃድ እያየንና እያደመጥን ነው። ውሸት አየር ነገር አይደለችም። በማሕበረሰቡ ሕሊና ውስጥ የምትኖር፤ ጠበቃዎችና ተከላካዮች ያሏት የሰዎች ባሕሪ ነች።

ሕብረተሰቡ ከሚዋሹ ታጣቂ መሪዎች አብሮ የማበዱ ምክንያት እራሱ ሕብረሰተሰቡ ብቻ ሳይሆን፤ ውሸትን በመድረክ አደባባይ እንዳይጋለጥ “ውሸትን የሚያደንቁ” በየ ቲከ ቶከና ዩቱበር እንደ አሸን የፈሉ “የተካኑ ስም አጢፊዎችን” በማሰማራት ፍተኛው የአጥፊነት ድርሻውን የያዙ ከፈሎችም አሉ

ሚዲያዎች፤ የድርጅቶችን ጸያፍ ድርጊታዊ ምስጢሮችን ፤ አውራጃዊና ከባቢያዊ የትውልድ ሐረግነትን በመከተል አንዳንዱም ለፖለቲካ እና ጊዜያዊ ተወዳጅነት ለማግኘት ሲሉ ፤ የሽብር ስራዎች ወደ እሚቃወሙት መንግስት ብቻ እያዞሩ የፋኖ ሽብርተኞች የሚፈጽሙዋቸው ሽብሮች ውሸቶች ፤ አፈናዎች፤ እገታዎችና ግድያዎችን በመደበቅ የተባባሪነት ሙያ እያካሄዱ ናቸው።

እነኚህ የቲከቶክና ዩ-ቱበሮች (የሚዲያ ክፍሎች) ለምሳል “ዘመድኩነ በቀለ” የተባለው “ሲፍረዘኒክ” እዚህ ልጥቀስና እነዚህ መሳይ “ጥላሸት ቀቢዎች” ሕብረተሰቡ ካልነቃባቸው አደገኛ የሕብረተሰብ ጠንቆች ሊሆኑ እንደሚችሉ ደጋግሜ ገልጫለሁ። የዘመነ ካ ፕሮፓጋንዲስት የሆነው ይህ ሰው አድማጮቹን የማሳምን ችሎታው ከፈተኛ ነው፡ ሆኖም ቀረብ ብሎ በጥንቃቄ ሲያጠኑት “ገለባ ፕሮፓጋንዳ ነው”። ሆኖም ሂትለር እንዳለው፦

«በብልሃት እና የማያቋርጥ ፕሮፓጋንዳ ሰዎች ገነትን እንደ ገሃነም እንዲመለከቱ እና በጣም መጥፎውን ሕይወት እንደ ገነት እንዲቆጥሩ ማድረግ ይቻላል። የላል፤ ሂትለር።

እየሆነ ያለውም ይህ ነው። እነኚህ ክፍሎች፤ በሕዝብ ምርጫና ፍላጎት የተከሰቱ ስላልሆኑ፤ በድምፅ ብልጫ የሚመረጡ ወይንም የሚወርዱ አይደሉም። እነኚህ ሚዲያዎች በተለያየ ስም እየተጠሩ፤ ለትርጉም የማይመቹ፤ “እራሳቸው በራሳቸው የመረጡ” ከማሕበረሰቡ ጫንቃ መውረድ የማይችሉ  “ነገሥታት” ናቸው። ሰልሆነም ፤ በይፋ ካልተጋፈጥናቸው፤ አደገኛ ድርጅቶችና ግለሰቦችን ወደ ሕዝቡ እያስተዋወቁ፤ የሕዝብ ሕሊና በመጥለፍ፤ ወደ ስልጣን ጎትተው ሊያመጡብን የሚያስችላቸው ዕድል እያመቻቹ ነው። በሌላ አነጋጋር አስፈሪ “ሞንስተሮችን” (ዘንዶአዊ-ድራጎኖችን) በነዚህ የሚዲያ ሰዎች ብዕርና ምላሰ ውስጥ ተወልደው ያድጋሉ ማለት ነው

ሚዲያዎች ጎጂም ጠቃሚም ሊሆኑ ይችላሉ። አደገኛ ባህሪ ሲከተሉ ግን ማሕበረሰቡ ከሚቆጣጠረው ዓለም ውጭ የሚኖሩ Dual character ድርብ ጸባይ የያዙ ክፍሎች የመሆን ባሕሪ አላቸው። እነኚህ ክፍሎች አገርን ማበጣበጥ፤ ጨቋኝ መሪና ግለሰብን ማንገስ የሚያስችል ሰላቢ የብዕር ችሎታ ስላላቸው፤ ማሕበረሰብን ማፋለስ ወይንም የማረጋጋት ችሎታ አላቸው። ውሸት በነዚህ ክፍሎች ትጎለብታለች ወይንም ትታገዳለች። ስለሆነም፤ ለቀውሳችን ምክንያት መዋሸትና ወንጀል ፈጽሞ ተጠያቂ ያለመሆን ባሰመርንበትም አሻግረን ለመድረስ የምንጓጓለት ወደ “ዲሞክራሲ” የሚወስደን መንገድ አጉራ ዘለሎችን በማወደስ ዘጊ ሃይል ሊሆኑ ይችላሉ። ስልዚህም እያስቸገሩን ያሉት ‘ሚዲያዎች እና መሪዎች” በውሸት ነቀርሳ ሲበከሉ፤ የሚፈለገው ሰላማዊና የዲሞከራሲያዊ (የእኩልነት) ስርዓት ልናይ አንችልም።

ያለ ምንም ማመንታት ወደ ቀውስ ገብተናል። ውሸትን እና ውሸታም የመንግሥትም፤ የፖለቲካ ድርጅት ሆኑ የሽምቅ ታጣቂ ተዋጊ መሪዎች (እውነትና ማሰርጃ ባለው ውንጀላ) ካልተተቹና ካልተጠየቁ፤ ቀጣዩም “ወሃ ቅዳ ውሃ መልስ” (garbage in garbage out!) ነው ። ባሳዛኝ ሁኔታ የፋኖ ትግል እየሆነ ያለው «ገዳይ ውጣ - ገዳይ ግባ» ነው።

እፊታችን ላይ ውሃ እንደ ያዘ እንስራ ፍርክሽክሹ የወጣው የፋኖዎቹ ትግል አምሐራ አምሐራን ለመግደል የዘመነ ፋኖ ታጣቂ በይፋ አውጀዋል። ማወጅ በቻ ሳይሆን ታጋዮች መግደል ጀምሯል! ነገ የገደሉትን ሬሳ ወደ መጎተት ተዛውሮ እንዳናይ ግን ያሰጋል።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

Friday, April 25, 2025

ይህን መልእክት የማያነብ [የአማራ ፋኖ] ኋላ ይቆጨዋል! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay 4/25/25

 

ይህን መልእክት የማያነብ [የአማራ ፋኖ] ኋላ ይቆጨዋል!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Ethiopian Semay

4/25/25

ስለአንድ የፋኖ መሪየአክስቴ ልጅ ነው” ከምትል ወጣት በቲክቶክ የሰማሁት እውነት ከሆነ የፋኖ ትግል አመራር - ሁሉም ባይሆን የተወሰነው ክፍል - ጥሩ አንደበት ግን መጥፎ ምግባር ባላቸው ሰዎች እጅ ላይ ወድቋል ማለት ይቻላ

 ይህ ደግሞ መገለጥና መታወቅ መፍትሔውም መፈለግ ይኖርበታል። ያቺ የአክስት ልጅ ነኝ ባይ ወጣት ልጅ የተናገረችው ውሸቷን ከሆነ (ቢሆንልኝ ደስ ይለኛል) ኩነኔው ወደሷ ይሂድልኝ፡፡ ከአንድ ዕብድ ሰው ጋር ስታወራ በቲኪቶክ ሰምቻት ብዕሬን ከማንሣት ልቆጠብ አልቻልኩም። ልጂት የተናገረችው ውሸት እንዲሆን እየተመኘሁና እየጸለይኩ “እውነት ቢሆንስ? በሚል መነሻ ሃሣብ መማማሪያ ይሆናልና ቀጣዩን ሃተታ ጻፍኩ።

 ደግሞም ከአፍ የሚወጣ እንጂ ወደ አፍ የሚገባ ሰውን አያረክሰውምና የተነገረውና የሚነገረው ሁሉ እውነትም ሆነ ሀሰት በዚያ መስመር የሚነጉዱ ሰዎች ይመለሱ ዘንድ የማስጠንቀቂያ ደወል ስለሚሆናቸው በዚህ መልክ መነጋገሩ መጥፎ አይደለም፡፡ በሚያልፍ ብልጭልጭ ዓለም የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ ማስቀመጥ ቀጣይ የራስን ትውልድ ሳይቀር መቅጣት ነውና ታጋዮቻችን ከትዕቢትና ከዕብሪት ሊቆጠቡ ይገባል። ምክርን መስማት ደግሞ የትልቅነት ምልክት ነው በተለይ አለኝ የምትለውን ነገር በሴከንዶች ውስጥ ልታጣ በምትችልበት የአሁኑ ብልጭልጭ ዓለም፡፡ ዛሬ የኔ ነው ያልከው ነገ የለም፡፡

አንድ መሪ ቀርቶ ተራ ታጋይ ሴት አውል ወይም ሴሰኛና ዘማዊ ከሆነ እሱም ትግሉም አበቃለት፡፡ ዘማዊነት የኃጢኣቶች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ ምክንያቱም ወሲብ ማለት ክርስቶስ የተሰቀለበትን የጌቴሰማኒ ትዕምርተ - ዕርፈ መስቀል አንገቱ ላይ ተሸክሞ የሚዞር አንድ ክርስቲያን በአንድ ካልተወሰነ ከብዙ ነገሮች ጋር የሚያነካካውን ኃጢኣት ይሠራል ዝሙተኛ ሰው ፍቅር አያውቅም፡፡ አመንዝራ ሰው ጥዶ ዘለል ነውና ቤተሰባዊ ትስስሩ ልል ነው፡፡

 ሰኛ ሰው የራሱንና ከሰውም ጭምር የሚቀማትን ሴት ቁሣዊ ፍላጎት ለማርካት ሲል ብዙ ገንዘብ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ ያን ገንዘብ ለማግኘት ሲል ደግሞ የማይሠራው የሙሥናናምዝበራ ወይምማጭበርበርናማታለል ዕኩይ ድርጊት የለም፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ‘’ሌባ ነጋዴና’’ ‘’አጋች ሸኔ’’ እስከመሆን ይደርሳል፡፡ ሞራላዊ፣ ወግ-ልማዳዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ሥነ ምግባራዊ ክሮቹን በወሲብና እሱን ተከትለው በሚጠናወቱት የሀብትና የሥልጣን ፍቅር ምክንያት በጣጥሶ ይጥላቸዋል፡፡ በዚያም ምክንያት ከብዙ እንስሳት የወረደ “animalism”ን ይዋረሳል።

 በአማራ ፋኖ አካባቢ እነዚህ ጠያፍ የኦሮሙማ መታወቂያዎች እየታዩ እንደሆነ መስማት ከጀመርን ቆዬን፡፡ የኦሮሞና የትግሬ ወሮበላ ሲዘርፍና ሲያግት ወንጀል፣ የአማራ ፋኖ ወይም በአማራ ፋኖ ስም የሚነሣ ወምበዴ ሲዘርፍና ንጹሕ ዜጋ ሲያግት ጽድቅ የሚሆንበት ሁኔታ ደግሞ ሊኖር አይችልም። ይህ ዓይነቱ double standard “ለራስ ሲቆርሱ…” ዓይነት ብልጥነትን የተመረኮዘ ሞኝነት ነው። አማራ ራሱን ማጥራት ያለበት ብዙ ነገር አለ፡፡ ቤትን ክፍት እየተው ሰውን ሌባ ማለትም በተለይ በዚህ ቀጣፊው በበዛበት ዘመን አያዋጣም፡፡

 ከፍ ሲል ያዬነው ዓይነት ራሱን ወደሸቀጥነት የለወጠ መሪ በፊት የነበረው ጠንካራ ጎን በይሁዳዊ ገንዘብ ወዳድነት ይለወጥና መላ ትኩረቱ ኢጎውን ወደማስደሰት ተዛውሮ ሚሊዮን ዜጋ ቢጠበስ ቢቀቀል ደንታው አይሆንም፡፡ ሚሊዮን ከመኖሪያው ቢፈናቀል፣ በቆንጨራ ተጨፍጭፎ በዶዘር ቢቀበር ሃሳቡ አይበላውም።በአጭሩ ወደ አቢይነት ይቀየርና ልጆቹንም ሆነ እናቱንና አባቱን ሳይቀር በጅምላም ሆነ በችርቻሮ ባወጡ እስከመሸጥ ይደርሳል፡፡

ይህ ዓይነቱ ሰው የቀንና የሌሊት ልሙ ቆነጃጅቱ ሣዱላዎች ናቸው ወይም ይህን ፈተና እንኳን ቢያልፍ የአራት ኪሎ ምርኮኛ ሆኖ በሥልጣን ፍቅር እየናወዘ ዓላማውን ይስታል፡፡ ባለዝናና ባለገንዘብ የምታሳድድ አንዲት ሴት ትታው የምትመጣው ሌላ ወንድ - ባልም ሊሆን ይችላል - መኖሩ ደግሞ ሊዘነጋ አይገባም። ሴሰኛ መሪ በምናብም በእውነትም ከስንቱ ጋር እንደሚቀያየምና ለነፃነት ትግል ሊያውለው የሚገባውን ጥይት በሴቶች ሳቢያ ለሚገጥምበት ሻምላ ውጊያ ሊጠቀምበት እንደሚችል ይታያችሁ።

የደራሲ ሰርቫንቴስ ምናባዊ የልቦለድ ገጸ ባሕርይ ዶን ኪሾት በለው፡፡ አንድ መልካም ዝና የነበረው የተቃውሞው ፖለቲካ መሪ ደግሞ በጊዜ ሂደት በማይረባ ፍላጎት ተጠልፎ በዱሮ ስሙ እየነገደ ብዙ የዋሆችን በማታለል ከጎኑ ሊያሰልፍ፣ እንደበግም ሊነዳቸውና የበረከተ መርገሙ ተባባሪ ሊያደርጋቸው ይችላል ይህ አዝማሚያም እየታዬ ነው ምን አለፋችሁ - እንደነዚህ ያሉ መጥፎ ደባል ጠባያት ያሉት ሰው የፋኖን ትግል የሚመራው ከሆነ እመኑኝ ወደሊማሊሞ ገደል እንጂ ወደአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ሊሆን አይችልም፡፡ ይህን መሰሉን የሰው ውራጅ አለመታገል ደግሞ ከሰውነት ተራ መውረድ ነው፡፡ ነፃነት በይሉኝታ አትመጣምና፡፡

አታጋይ መሪ አርአያ መሆን ይገባዋል ቢቻል እንደክርስቶስ ባይቻል ደግሞ እንደሆቺሚንና እንደቸኩቬራ ይህም ባይቻል እንደማኅተመ ጋንዲና እንደኔልሰን ማንዴላ፡፡ታጋዮች እየተራቡና እየተጠሙ እየታረዙም ገና በጫካ ያለ መሪ ጌታዋን የገደለች በቅሎ የሚመስል ካገኛትም ጋራ የሚጋደም ከሆነ ትግሉን በአፍጢሙ ደፋው አውቃለሁ - መፍረድ ቀላል ነው ይገባኛል - መናገርና መጻፍም እንደዚሁ ቀላል ነው፡፡ ነገር ግን የነገሮች አካሄድ የተጣመመና አክሳሪ መስሎ እየታየኝ ዝም ብል የ35 ዓመታት ልፋቴን ገደል እንደመክተት ያህል ነው፡፡

 ያበጠው ይፈንዳ የሚሰማኝን እናገራለሁ፡፡ አንድ ሰው ባለፈው ብሶቴ ምክንያት ሰለጠነች ቢሏት የባሏን መጽሐፍ እንዳጠበችው ሴት መስሎ አቅርቦኛል፡፡ እውነትን በመጻፌ ልሰደብም እንደምችል ስለተረዳሁበት በእውነቱ አልተከፋሁም - እንኳንም የክብርት ባልተቤቴን መጽሐፍ አጠብኩ፡፡ ማጠቤን የምቀጥልበት መሆኔን የምገልጠው ለትምክህት ሣይሆን ከእውነት መንገድ ላለመውጣት ያለኝን ፅኑ አቋም ለማሣወቅ ስል ብቻ ነው፡፡

ሌሎችን በስድብ ስታጥረገርግ መደሰትና የራሴ የምትለውን ግን ያጠፉ ቢያጠፉ ሳትተች ማሽሞንሞን የሚያዛልቅ አይደለም፡፡ ደግሞስ ገና ምን ታዬና! የአማራን ትግል የሚጠልፉና የመቶ ሺዎችን መስዋዕትነት ለግል መጠቀሚያ የሚያደርጉ ጥቁር ውሻ ይውለዱ ብዬም እራገማለሁ፡፡ በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም የምንለው ወደን አይደለም። ይሉኝታና ሀፍረት ሲቀብር እንጂ ሲያነሳ አልታየም፡፡ “ትግሉን ይጎዳል፣ ትግሉን ያጓትታል፣ ቲሪሪም ቲሪሪም…” ከእንግዲህ አይሠራም፡፡ በመሠረቱ የአማራ ጠላቶች በፋኖ አመራርም ይሁኑ፣ በፋኖ ሠራዊትም ውስጥ ይሁኑ፣ ከፋኖ ውጪም ይሁኑ… ዕድሜያቸው ሊያጥር ቀኑ ቀርቧል

 የሚጠበቀው ዓለም አቀፉ የአማራና የኦርቶዶክስ ጠላት በራሱ የቤት ሥራ ከአሁኑ በበለጠ በደምብ እስኪወጠር ድረስ ነው ያንንም በከፍተኛ ጉጉት እየተከታተልነው እንገኛለን፤ ውስጠ ምሥጢሩ የሚገባን ጥቂቶች፡፡ ያም ሂደት ጊዜውን ጠብቆ እየተፋፋመ ነው፡፡ ዕድሜ ለወንድም ፑቲንና “ዘመድ አዝማዶቹ”፡፡ ምዕራቡ ዓለም ከአውሮፓ ጭምር የተሟላ የቤት ሥራውን ሲጀምር እንግሊዝኛ እኔስ ለምን ይቅርብኝ in the mean time ኢትዮጵያም እፎይታ ታገኝና ልጆቿ የዘመናት የችግር ቋጠሯቸውን ፈትተው የጋራ መፍትሔ በመፈለግ በማይማን የእነ እንቶኔ ተላላኪዎች ተይዞ የነበረ መንበራቸውን በምርጫና በምርጫ ብቻ ይቆጣጠራሉ፡፡ ያኔ ሲ አይ ኤ የለ፤ ኤፍ ቢ አይ የለ፤ ኤም አይ ፋይቭና ሲክስ የሉ፤ ሞሳድ የለ - ሰላም ብቻ። ያኔ ጃዝ ብለው የላኩብን ዕብድ ኦሮሙማ ወደ … ይሄዳል።

 ቂላቂል ጸሐፊ እንዳልመስልህ “ወደ ማዳጋስካር” የምልልህ ጅሌ፡፡ ለነገሩ እሱም ያኔ ብርቅ ነው - አይገኝም፡፡ ኦሮሙማ/ኦነግሸኔ የሕወሓት ዕድል ይናፍቀዋል አልኩህ እኮ በቀደምለታ በሰደድኩልህ ጦማር፡፡ ፈጣሪ የውሻን ደም እንኳን በከንቱ አያስቀርም፡፡ ትንሽ ታገስ ብቻ፡፡ ግፍና በደል ባከማቹት ደመና ምክንያት የሚጥልን የበቀል ዶፍ ዝናብ ሊከላከል የሚችል ጃንጥላ የሠራ አካል እስካሁን በዓለም አልታዬም፡፡

  አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንላለን፤ እናም በግልጽ ነው የሚሰማኝን የምናገረው፡፡ የገዛ ዘመዱ በዚያ መልክ በገሃድ ራሷንም ሳትሸፋፍን ስትመሰክር ሳይ ወሽመጤ ነው የተቆረጠው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ራሱ የሰይጣናዊ ምግባር መገለጫ ሆኖ እኔን ከሌላው ሰይጣን ከአቢይ ነፃ አወጣሃለሁ ቢለኝ ምፀት ነው፡፡ ለዚህ ነው ፋኖ እንደግመል ሽንት የኋሊት እየተጎተተ የመከራችን መራዘም፣ የትንሣኤያችንም መዘግየት ዋና ምክንያት ሆኖ እንደምናስተውለው የወቀሳና ስሞታ ሰለባ ሊሆን የቻለው፡፡ እንጂ እንደትግሉ አጀማመር ቢሆንማ ኖሮ ነፃ ከወጣን ሁለተኛ ዓመታችንን ልናከብር ወደ ፈንዲሻ መሸጫ ሱቅ ሄደን ወረፋ በያዝን ነበር፡፡

 ደግሞ እኮ ዕድሉ ሆኖ ከአዳነች አበቤና ከአቢይ አህመድ ከነበለጠ ሞላና ከምርኮኛ አሥር አለቃ ጁላ በስተቀር ፋኖን የማይናፍቅ አዲስ አበቤ አልነበረም፤ አሁን ግን ሰው ተስፋ እየቆረጠና የ“እየመጡ ነው” መፈክርም እየደበዘዘ መጥቶ ኢትዮጵያውያን ከፋኖ ይልቅ የማይቀረውንና እንደሰውም የማይሆነውን የእግዚአብሔርን ፍርድ መጠባበቅን መርጠዋል - ለምን ይዋሻል፡፡ የፋኖኣዊ placebo effect ራሱ እየተሸረሸረ መጥቶ ፋኖ በመጥፎ መሪዎቹ በሠራው ስህተት ምክንያት ብዙዎቻችን የተስፋችንን የዲሽ አቅጣጫ እየቀየርን እንገኛለን፡፡

 ስለሆነም ለአንድ ወይም ለጥቂት ራስ ወዳዶች ሥጋዊ ፍላጎት ዕርካታ ሲባል በተለይ 60 ሚሊዮኑ አማራና በአጠቃላይ ደግሞ 130 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቁሙ መቀመቅ መውረድ የለበትምና ኅቡኣን ባለምጡቅ አእምሮ ፋኖዎች ብዙም ሳይረፍድ የምታደርጉትን አድርጋችሁ ይህን ዕልቂት የታወጀበት ሕዝብ በአፋጣኝ ድረሱለት - የምታደርጉትን ስታደርጉ ግን ቆቅ ሆናችሁ እንጂ ዕርግብ ሆናችሁ እንዳይሆን አደራ፡፡ አቢይና የአቢይ ተፈጥሮ ያለበት ሰው ሁሉ ትንሽ ከጠረጠረ ማጣራት ሳያስፈልገው የምግብና የመጠጥ መርዝን ጨምሮ ባገኘው መሣሪያ ያገኘውን መረፍረፍ ነውና ጠባዩ ተጠንቀቁ፡፡ እናም ለሕዝብ ስትሉ ጥቂት ጥፋት ብትሠሩ ምንም አይደለምና ተመካከሩ፡፡

በከንቱ አትውቀሰኝ ወንድሜ፡፡ ምን ማለትህ ነው - 60 ሰው የጫነ የሕዝብ አውቶቡስ መንገድ ላይ ደንቃራ ሆኖ የገባበትን አንድ ሰው ለማዳን ሲል ገደል ገብቶ አንድ ሰው ያድናል ወይንስ አንድ ሰው ገጭቶ 60 ሰው ከሞት ይታደጋል? ንገረኛ! የምን መተፋፈር ነው፡፡ በማይገራ የግል ፍላጎቶቻቸው ኅሊናቸው ታውሮ - በሴት በለው፣ በንዋይ በለው፣ በሥልጣን በለው በሌላ ነገር - ትግሉን የሚያውኩ አመራሮች ካሉ እንዲመለሱ መምከርና ማስመከር ተገቢ ነው፡፡ ካልሆነ ግን ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ እነሱን አስወግዶ ሀገርንና ሕዝብን ማትረፍ ቀጠሮ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡

የነሱ ኢጎ ክፍተት ተደፍኖ አያልቅምና ስንት ሰው እስኪያልቅ እሹሩሩ ይባሉ? ስንት ሀብት ንብረት፣ ስንት ላዕላይና ታኅይ መዋቅር፣ ስንት ትምህርት ቤትና ሀኪም ቤት እስኪወድም ይጠበቅ? የምን እሹሩሩ ነው፤ የምን እሽኮኮ ብሎ መዞርና መሰቃየት ነው፡፡ “ለዚህ ለዚህማ ብልጽግና ምን አለን?” ልል ከጅሎኝ ነበር የሚጠብቀኝን አሽሙርና የብልጽግናነት ፍረጃ ፈርቼ ተውኩት፡፡

  የባለጌ አመራሮችን ወግ ገታ አድርገን ወደተዛማጅ ጉዳይ ጎራ ብለን ስለአንድ ጠቃሚ ነጥብ ብናወሳ ደስ ይለኛል፡፡ እሱም የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን የሚሰጠውን ጠቀሜታ በተመለከተ ነው፡፡ የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን ጥቅሙ ጎልቶ እሚታየው እዚህ አካባቢ ነው - የተለያዬ ባሕርይና ሥነ ሕይወታዊ ሥሪት ያላቸው ሰዎች በተለያዬ ሥፍራ የሚገኙ ፋኖዎችን በነፃነት መምራታቸው ለትግሉ በቀላሉ አለመጠለፍ የራሱ አወንታዊ ሚና አለው፡፡ እንዲህም ስንል ለአብነት ፋኖን የሚያውኩት አመራሮች በጊዜ ሂደት በየግዛታቸው እየታወቁ ይመጣሉ - አሁን አካባቢ በሁሉም ግዛቶች እየታወቁ እንዳሉት ማለት ነው፡፡

 በአራቱም የአማራ ግዛቶች የሚገኙ ሃቀኛ የአማራ ልጆች በሂደት የአመራሮቻቸውን የንግግርና የተግባር ሥሙርነት እየተረዱና እየለዩ ይመጣሉ፡፡ ሴተኛ አዳሪዋ "አጭበርባሪ አይተኛኝም" ያለችውን አስተማሪ ብሂል የሚያስታውሰውና ለተግባራዊነቱም የሚተጋው ጨዋና አስተዋይ ታጋይ ፋኖ በብኩን አታጋዮቹ ላይ ይነሣል በሰርጂካል ምጥን ውስጣዊ ኦፐሬሽንም እነዚያን በፍቅረ ንዋይና በፍቅረ ወሲብ የተመረዙ ወገኖች በዘዴና ትግሉን በማይጎዳ ሁኔታ ያስወግዳል፡፡ ይህ ክስተት እውን እንዲሆን ታዲያ የፋኖ decentralized ውቅር ጠቀሜታ አለው - ውድ ልሂቆቻችን “A blessing in disguise” ወይም “mixed blessing.” ይሉታልኝ ይህን መሰሉን አጋጣሚአንድ ቢሆን ግን በቀላሉ ይጠፋል ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላም፡፡ “ሁሉ ነገር ለበጎ ነው” የመባሉ ምሥጢር ትዝ አላለህም እዚህ ላይ? አዎ፣ ወንድም እህቶቼ፡- መታመናችን ለአንድ አምላክ ይሁን እንጂ አምላከ ሰማይ ወምድር በቅርብ ይጎበኘናል፡፡

አሁንና በዚህች አጋጣሚም በቅርቡ ያልኩትን ልድገመው - አማራ ይሄን የከረፋና የጠነባ የኦነግ-ሸኔ ሥርዓተ ካኒባሊዝም ዝንጥ አድርጎ ያሸንፋል፤ ወደመጣበት እንጦርጦስም ይመልሰዋል፡፡ እንዲህ ስናገር ውስጤን ምን ዓይነት ሃሤት እየተሰማኝ እንደሆነ ልገልጸው አልችልም፡፡ ግን ግን… ቢሆንም - “ሃታኡ መሌ - haa ta'u malee  ይላሉ ወንድሞቼ - ልድገመው ቢሆንም ነፃነት በእጅ የድንጋይ ውርወራ ሬዲየስ ውስጥ የምትገኝ መሆኗ ጥርጣሬ ውስጥ ባይገባም የምታስከፍለው ዋጋ ግን ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ሥነ ልቦናዊ ድንዛዜንና ምንግዴነትን ሁሉ ያካትታል፡፡

ለምሣሌ በአሁኑ ወቅት እጅግ ብዙው ዜጋ ብልጽግናንም፣ ፋኖንም፣ ኦነግንም፣ ወያኔንም፣ ኡጉጉሙ ኢትዮጵያንም … ከመጤፍ ሳይቆጥርና ጭርሱን ረስቶ የዕለት እንጀራው ላይ ብቻ ተደፍቶ ነው የሚታዬው፡፡ ይህ ጤናማ አይደለም፡፡ እኔን መሰሎች አንጋፋ ዜጎችን የሚያቃጥለን አንዱና ትልቁ ነገርም ይሄው ነው፡፡ በሌላ ምሣሌ 130 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህችን መጣጥፍ የሚያነበው ከመቶ ከበለጠ ተዓምር ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ያላቸው ሀገራት የኛን የመሠለ ችግር ቢገጥማቸውና አንድ ሰው የኔን የመሠለ መጣጥፍ ቢፖስት 1.5 ሚሊዮን ሕዝብ ያነበዋል ተብሎ ይገመታል - ግማሽ ሚሊዮኑ  በድጋሚ ገርቦት ማለቴ ነው፡፡ [ይህን ጽሑፍ ጀምሬ እዚህ ገደማ ደርሼ ዕረፍት ማድረግ ላይ እያለሁ ከደቂቃዎች በፊት ዛሬ የደረሰኝ መረጃ ቅንፍ ከመክፈቴ በፊት የተናገርኩትን የሚያፈርስ ነው፡፡

የክፉ ቀን ደራሼና እጅግ ሲበዛ አስታዋሼ የኢትዮሰማይ ድረገጹ ጌታቸው ረዳ  በትናንትናው ዕለት ብቻ 1636 ሰዎች ጽሑፌን ከእርሱ ድረገጽ እንዳነበቡ ነገረኝ - የዘሀበሻው ደግሞ ቢጣራ ከዚህ እንደሚበልጥ አልጠራጠርም፡፡ በተለጠፈ በአንድ ሰዓት ውስጥ ደግሞ 1002 አንባቢ እንደተመዘገበ አብሥሮኛል - ተመስገን ነው ኧረ]

ጥሩ ነው፡፡ ዋናው ደግሞ ተግባር ነውና ፋኖ እንዲጸዳ፣ ቤቱን እንዲጠርግና እንዲያሰማምር፣ ታጋዮችን በሁሉም ረገድ ለድል እንዲያበቃ፣ የጠላት ሠርጎ ገቦችን እንዲመነጥር ወዘተ. አቅሙ ያላችሁ ችላ አትበሉ፡፡ የነፃነት ትግሉ እየጠራና ይበልጥ እየሠመረ ሲሄድ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ የሁሉንም ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ተሣትፎ ይጠይቃል፡፡ ዘረኝነት ሊጠፋ ጥቂት ጊዜ ቢቀረውም በምኞት የሚጠፋ ነገር የለምና በተለይ ዕውቀት፣ ገንዘብና ሃቀኛ ፋኖዎችን የማግኘት access ያላችሁ ምሁራን፣ ሀብታሞች፣ ታዋቂዎች … በርትታችሁ ተሣተፉ፡፡ ነጻነት መምጣቷ እርግጥ ነው፡፡ ያኔ እንዳንተዛዘብ አሁን ማድረግ ያለብንን እናድርግ - ግን ራሣችንን ጠብቀን፤ (አቢይ ጋ ቀልድ የለም)፡፡ እኔ እንደሆንኩ ዘርፍጤ ነኝ፡፡ ከውሽንፍሩ ከተረፍኩ ማንም እየተነሣ “እንዲህ ነበርኩ፤ እንዲህ አድርጌያለሁ” ቢል መዝገብ ማገላበጣችንና ማጋለጣችን አይቀርም፡፡

 ቆነጃጅቱ እየመጡ ነው … እነሱ ሲመጡ ሥራ ላይ የሚውለው ሰውነት ነው - ዝቅ ሲል ደግሞ ኢትዮጵያዊነት፡፡ አሁን አማራ አማራ የምንለው በወቅቱ ቅኝት ለመሄድ ሲባልና የተሻለ አማራጭም በማጣት ነው፡፡ አማራ ጠላቶቹ እንደሚሉት ሳይሆን በቁጥር የሰማይ ከዋክብትና የምድር አሸዋን የሚያስንቅ ሆኖ ሳለ በመቶዎችና በጥቂት ሽዎች የሚገመቱ ከሁሉም ነገዶች በተለይም በፊት ከትግሬና አሁን ከኦሮሞ የወጡ አሰለጥ ደም መጣጮች ሊጫወቱበት የበቃው በአማራነት መደራጀትን ከዘር ሐረግም ከባህልም ከሃይማኖትም ስላላገኘውና ስለሚጠየፈውም እንጂ እንደነሱ ቢደራጅ አንታርክቲካ ድረስ ሊያሳድዳቸው በቻለ ነበር፤ በዚያ ላይ አማራ በሆዳም ልጆቹ ብዛትና ራሳቸውንም ጭምር በመጨረሻው ለማይምራቸው ጠላት በሚያሸረግዱ፣ የገዛ ወገናቸውንም በሚያስጨርሱ የጥቁር ለጥቁር ባንዳዎቹ ኆልቁ መሣፍርትነት አይታማም - በሌላ በዚያ ላይ ደግሞ አማራ is highly porous for gatecrashers and has also been willingly intermingling with other tribes for millennia. በዚያም ሳቢያ አማርኛን የሚናገር ሁሉ አማራ ነኝ እያለ ተመሳስሎ ገብቶ  ያጃጅለዋል፤ ይሰልለዋል፤ ለጠላቶቹ ሠይፍም አሣልፎ ይሰጠዋል፡፡

 አሁን አሁን ግን የሚያስፈራ አማራ እየተፈጠረ ነው፡፡ ወዮልሽ አማራን ስትጨፈጭፊና ስታስጨፈጭፊ የነበርሽ ሁላ!! (አቤት ስንቱን ቀባጠርኩት! ማበድ ከዚህ በላይ ይኖር ይሆን? አፉ በሉኝ፡፡

 አፄ ቴዎድሮስ በሎሬት ፀጋየ ገ/መድኅን ዋቀዮ በኩል “…ሳይነጋ እንዳስመሸሽብኝ ጊዜና ትውልድ ይፍረደን፤ ሳልነቃ እንዳስፈረድሽብኝ … ያም ሆኖ ለራስሽ እንጂ ለኔ ከቶም አታልቅሺ ...” ያለው ለካንስ ወዶ አልነበረም፡፡)

Ethiopian Semay