ከበበን
ዕጽዋን “የተከበበና በር የተዘጋበት ሕዝባችን” የሚለው እውነታው ሲፈተሽ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
11/5/24
ሕዝባችን ዙርያው ተከቦ፤ መውጫ በር አጥቶ በርሃብ ያለቀው ሕዝባችን የሚሉት የትግራይ ልሂቃን፤ መንጋውና ሚዲያቸው እራሳቸው ነፃ አድርገው ተጠያቂነት ሳይወስዱ ዛሬም በርሃብተኛው ሕዝብ መነገድ ቀጥለውበት ሌት ተቀን የሚያኝኳት “የተከበበ፤ በር የተዘጋበት ሕዝባችን” የሚለው እውነታው እማን ጋር ነው?
የትግራይ ሚዲያዎች ፤ ፋሺሰቶቹ የትሕነግ የ(ቲ ፒ ኤል ኤፍ ) መሪዎችም ሆኑ ልሂቃን ተብየዎቹ በማንኛውም ውይይታቸው ወቅት “ዕጽዋን ክባን” (ከበባና የመውጫ በር መፈናፈኛ ማጣት) የሚሉት ቃላቶች ከያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ አንደበት የምትደመጥ መሪ ቃል ነች።
ይህ ሁሉ ርሃብና ሞት መነሻው ምን ይሆን የሚለው ጥያቄ እያንዳንዳችን ብዙ መላምቶችና መከራከርያዎች አሉን። ትግሬዎች አብይን እና አምሐራን ሲከሱ መሪዎቻችን የሚልዋቸው “በትሕነግ መሪዎች በኩልስ?” ተብለው ሲጠየቁ “ኢትዮጵያ” የምትባል ሃገር ከታሪክዋ ከትግሬ ጫንቃ ወርዳ ስለማታውቅ ” ጦርነቱ አይቀሬ ነበር፤ የመሪዎቻችን ጥፋት ሳይዘጋጁ ወደ ጦርነት አስገቡን፤ ጥፋታቸው ያ ነው። በማለት “ወደ ጦርነት አስገቡን” ስትሉ ምን ማለት ነው? ለሚለው ጥያቄ ግን መልስ የላቸውም። ምክንያቱም ጦርነቱ እንዲፋፋም በኳስ ሜዳዎችና በየሚዲያው ሲናገርዋቸው የነበሩት ጦርነት ቀስቃሽ ቃላቶች “ሥልጣናችን ድንገት እንዴት ተነጠቅን?” “አምሐራ ወደ ሥልጣን መጣ” የሚለው ቅዠታቸውና ስልጣን ከእጃቸው ድንገት መውጣት ራሳቸውን ያስገረመ የሥልጣን መነጠቅ ለጦርነቱ መነሻ አንኳር እንደሆነና ያንን ተከትሎ የሰሜን ዕዝ አዘናግተው ጨፍጭፈው መሳሪያ ግምጃዎች ተቆጣጥረው የሃገሪቱ “ተምዘግዛጊ ሚሳይሎች” ሳይቀር እንደዘረፉ ሕሊናቸው ያውቃል (ያ ወንጅል ነው)።
በዛው ጦርነት ሕዝቡ መጎዳቱ አይቀሬ ነበርና ተጎድቷል። አስገራሚው ደግሞ አምሐራ ልሂቃን ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን የሚለው በነ ደብረጽዮንና በእነ ጌታቸው ረዳ መፈክር ተቀስቅሰው
የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን ስንቅ አስንቀውና አስታጥቀው መርቀው ወደ “አማራ እና ወደ ዓፋር “ክልል” ገብተው ያደረሱት ግፍ፤ ግድያ፤ ዝርፍያ፤ የሴቶች መደፈር፤
እንዲሁም የምግብ አቅርቦት እንዲዘጋ የመገናኛ አውታሮች እንዳይንቀሳቀሱ፤የከተማዎች መብራትና ስልክ በመበጣጠስ፤ ተደጋጋሚ ጦርነት በመክፈትና አውራ ጎደናዎቹን ድልድዮችን በማፍረስና በመቆጣጠር አምሐራና ዓፋር ሕዝብም አውከውታል።
ሌለውን ሕዝብ ያወኩትን ያህል ሕዝባችን የሚሉትን የትግራይ ሕዝብም አውከውታል። “የትሕነግ” መሪዎች ትግራይ ውስጥ በየመጋዝኑ ተከምሮ የነበረው ምግብ እና እንደዚሁም የተላከ እና አዲስ ምግብ ተጨምሮ በስርዓት ለትግራይ ሕዝብ እንዳይዳረስ ለዚህ ጉዳይ መዋል የሚችለው ነዳጅና ከተባባሩት መንግሥታት ምግብ ይዘው ወደ ትግራይ የተጓዙ የጭነት መኪኖች እየተመላለሱ ምግብ እንዳያመጡና በየአውራጃው እንዳያዳርሱ መኪኖቹ ባግባቡ ከመጡበት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ሲጠየቁ ወያኔዎች አሻፈረኝ ያሉበትን በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ “የዓለም አቀፍ ምግብ ተራድኦ መርሃ ግበር’’ በዋና ዳይረክተርነት ተመድቦ በቅርብ የትግራይን ሁኔታ በአካል እዛው ሆኖ የተመለከተና ያስተባባረ ኬኒያዊው እስቲቨን ኦማሞ At the
Center of the World in Ethiopia (S.W.Omamo) የተባለው አስገራሚ የአይን እማኝ የጻፈውን መጽሐፍ በዳሪክተሩና በትግራይ የምግብ አቅርቦት ዋና ሓለፊው በቲዊተር የተመላለሱብትን መልዕክት የዘገበውን እነሆ እንዲህ ይላል፡
In
the previous few months, I had tweeted and re-tweeted pieces like this:
<<
Concerning. None of the 149 trucks in the convoy that reached #Mekelle#Ethiopia
last week returned only 38 out of 466 trucks that entered #Tigray since 12 July
returned> We need trucks to deliver lifesaving assistance to people in
#Tigray.>> (P-35)
<<ባለፉት ጥቂት ወራት፣ ከትዊት ወደ ትዊት እንደገና ተደጋጋሚ ትዊት እያደረግኩላቸው ነበር።
<< የሁኔታው አሳሳቢበት!! - ባለፈው ሳምንት ምግብ ጭነው በኮንቨይ/በጥበቃ/ #ከአገሪቱ ወደ #መቀሌ ከገቡት 149 የጭነት መኪኖች ውስጥ አንዳቸውም አልተመለሱም። ከሓምሌ ወር ጀምሮ #ትግራይ ውስጥ ከገቡት 466 መኪኖች ውስጥ 38ቱ ብቻ ሲመለሱ ሌሎቹ ሳይመለሱ እዛው ትግራይ ውስጥ ቀርተዋል። (ገጽ 35)
<<
Continued encouraging progress with support of Federal, #Afar and #Tigray
authorities. We need hundreds more trucks to come out of Tigray so that large
volumes of food can be moved quickly to 5.2 million food insecure people in the
region………..>>
(ከፌዴራል፣ ከአፋር እና ከትግራይ ባለስልጣናት ጋር በመሆን አበረታች እድገት ቀጥሏል። ከፍተኛ መጠን ያለው ምግብ በፍጥነት ወደ 5.2 ሚሊዮን የምግብ ዋስትና ችግር ወደ ክልሉ እንዲሸጋገር በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ መኪናዎች ከትግራይ እንዲወጡ እንፈልጋለን።(ገጽ 35)_
እያለ ወያኔዎችን ለተዋጊዎቻቸው አመላላሽ አድርገው የያዝዋቸው የጭነት መኪኖች ተሎ እንዲመልሱዋቸው ከተማጸናቸውና ወደ የበላይ አካልም ስለ ሁኔታው ካመለከተ በኋላ
እንዲህ ይላል፡
<<
For me the issue was very simple: - On trucks, if WEP- contracted trucks did
not come out of Tigray, there was no way for us to deliver food into the region
at the required scale predictability. Millions of Tigrayans will go hungry….
The bureau Head had himself indicated to my team in Mekelle that the available
fuel in the region stood at mill of litters, but that the TPLF’s position was
that this fuel would not be provided to WFP and other humanitarian actors,
because there were other “more important strategic priorities’’ for the fuel
than humanitarian assistance “our fighters are fighting for Freedom. >>
(<< ለኔ ጉዳዩ በጣም ቀላል ነበር፡- በWEP በኮንትራት ያሉ ምግብ የምናመላለስብቻው የጭነት መኪናዎች ከትግራይ ካልወጡ፣ በሚፈለገው መጠን ወደ ክልሉ ምግብ የምናደርስበት መንገድ አይኖርም። በዚህ በምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ይራባሉ። የትግራይ የቢሮ ኃላፊው እራሱ መቀሌ ለሚገኘው ቡድኔ/ለወኪሎቼ/ እንደደገለጸው <<በክልሉ ያለው ነዳጅ በሚሊየን ሊትሮች መጠን ላይ እንደሚገኝ ፤ ነገር ግን የህወሓት አቋም ‘’ይህ ነዳጅ ለደብሊው.ኤፍ.ፒ. እና ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንደማይሰጥ ነበር የነገራቸው። ምክንያታቸውም ሲገልጹላቸውም “ከሰብአዊ ርዳታ ይልቅ ለነዳጁ አስፈላጊ ስትራቴጂካዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሌሎች ጉዳዮች ስላሉን እና “ተዋጊዎቻችንም ለነፃነት እየተዋጉ ” ስላሉ ነው የሚል ነበር።>>
ይላል።
Later,
I shared news of the TPLF’s position on fuel with WFP leadership, expecting
that this would lead to a denouncement of some kind…….
ይልና ኒውዮርክ ወይንም ጀኔቫ ላላው መ/ቤቱ ቢያመለክትም ምክንያቱ ባላወቀው ምክንያት አጥጋቢ መልስ ሳያገኝ ሲቀር ለትግራይ እርዳታ ሓላፊው ተመልሶ የጭነት መኮኖቹ ተሎ እንዲመለሱ እራሱ ቢጠይቀው አንተ “የአብይ ሮቦት” (አንተ የአብይ አሻንጉሊት ነህ) በሚል ስርዓት በጎደለው መልስ ሲመልስልኝ በጥንቃቄና ጭዋነት በተሞላ እንዲህ አልኩት ይላል።
<<
I respectfully but forcefully restating my basic points. We need trucks for our
operation. Trucks were not coming out of Tigray. We need fuel for our
operations. He himself admitted that the TPLF had fuel. He should let us have
it so that we could move food to vulnerable food insecure people. “We have
other priorities”, he responded. “Ask Abiy Government for fuel”. This was war.
Brutal.
(<< አሁንም በአክብሮትና በጥንቃቄ ግን በአጽንኦት መሰረታዊ ነጥቦቼን ደግሜ ነገርኩት። የጭነት መኪኖቹ ለሥራችን እንፈልጋቸዋለን። መኪናዎች አሁንም ከትግራይ እንዲወጡ አልፈቀዳችሁም። አብሮም ለሥራችን መቀናት ነዳጅ እንፈልጋለን ብየ ስለው፤ እሱ ራሱ በቂ ነዳጅ አለን ብሎ ሲያረጋግጥልኝ፡ ይህ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የምግብ ዋስትና ለሌላቸው ሰዎች ምግብ እንድንወስድ ሊፈቅድልን ይገባል ስለው። "ሌሎች ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች አሉን" ሲል መለሰልኝ። በመቀጠልም "ነዳጅ ከፈለግክ የአብይ መንግስትን ነዳጅ ጠይቅ" ብሎኝ እርፍ አለው።>> ይላል ገራሚው ዘገባው።
ደራሲው በመገረም “ጦርነት ነበር! እጅግ አረመኔ! ይልና “ለመሆኑ ሕዝብ በረሃብ እንዳይሞት ከሰብአዊ ዕርዳታ በላይ ቅድሚያ ሌላ
ጉዳይ አለን ሲሉን ከዚህ ወዲያ ቅድሚያ እና አንገብጋቢ ምን ኖርዋቸው ኖሮ ይሆን?” ሲል የተገረመበትን በሰፊው ይተነትነዋል።
አንግዲህ በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የምግብ ተራድኦ መርሃ ግብር ዋና ዲሬክተር ኬኒያዊው “ኦማሞ” የታዘበውን አለም አቀፍ የውሸት ዜና ዘጋቢዎች ባሕሪ እና የወያኔ መሪዎች ሓላፊነት የጎደለው ወንጀለኛ ባሕሪ በመደመም በዛች በመጽሐፉ
“This is a book about what I saw,
what I felt, what did as Representative and Country Director of United Nation
World Food Programme (WFP) in Ethiopia from 2018 t0 2021. How I did, what I
did, why and so what effect. What went well, what did not, and why. What I
learned. What surprised me, what exited me. What disappointed me. And why. እያለ የዘገበው የመግቢያ ገጽ መጽፉን ትግራይ ውስጥ፤ አማራ እና ዓፋር እና በትሕነግ መሪዎችና ተዋጊዎች የታዘበውን በሚገርም ሁኔታ ዘግቦታል።
እንግዲህ “የተከበበ፤ በር የተዘጋበት ሕዝባችን” እያሉ የሚናገሩለት ሕዝብ የችግሩና የከበባውና የመዘጋቱ ምንጭ ቅድሚያ ከሕዝቡ ይልቅ ለራሳቸው ተዋጊዎች ቅድሚያ በመስጠት ሕዝቡ ችግር ውስጥ እንዲገባ ሃላፊነቱ መውሰድ ያለባቸው እራሳቸው የትግራይ ብሔረተኛ መሪዎቻቸው እንደሆኑ ዓለም ምግብ ተራድኦ የኢትዮጵያ ወኪል ዲሬከተር የተመለከተውና የገጠመው አስቸጋሪ ሁኔታ በመጽሐፍ መልክ ሰፊ ዘገባ ማቅረቡን አንባቢዎቼ አማዞን ገበያ ላይ ገዝታችሁ አንብቡት። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል የሚባለው ይኸው በትሕነግና በትግራይ ምሁራን እና መንጋዎቻች ታይቷል።
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment