በታላቁ አንበሳ የተነሳው ጅብ
ጎንደሬው መሳፍንት ተስፉ
ትችት በጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/26/24
ይህ እስቲ እንደመግቢያ እንመልከት
1ኛ-<<እስላም የሆነ ኢትዮጵያን ማስተዳደር የለበትም! በባሕላችን ያልነበረ! >>
2ኛ-<<አምሐራ ምድር ውስጥ ( ያሉት ትግሬዎች ተለቃቅመው ወደ አገራችው ይውጡልን! ጎጃም ውስጥ በሁሉም ቦታ አሉ ሄደው ከነሱ ጋር ይግጠሙን
<<ትግራይ “ምናችን አይደለችም” እንጨብጣታለን! ትግራይን ደግሞ! አይ!>>
ሲል ጎንደሬው ተሰብሳቢ “ይደገም! ይደገም! ሲል ዘረኛነትን በጭብጨባና በጩኸት አፀደቀለት! የሚገርም ነው። ምኔም አይደለም የምትለው ሕዝብ መጨረሻው ዕጣ ፈንታው ምንድ ነው የሚሆነው? መባረር፤መገደል! ኦሮሚያ በተባለው አኬልዳማ ምድርም እንደዚሁ “አምሐራ ምናችን አይደለም” ስለተባለ ነው ደም እየፈሰሰ እየተፈናቀለ ያለው።አይደለምእንዴ? እንጨብጣታለን ሲል ምን ማለት ነው? መጨበጥ ማለት “በቅኝ ግዛት መያዝ፤ማብበርከክ፤ መቆጣጠር፤ማስጨነቅ…” ማለት ነው አደልም እንዴ? ከዚህ ወዲያ ዘረኝነት ከየት ይመጣል
ያ ሁሉ ዘረኛነቱን ተረስቶለት ሲያበቃ ትናንት ደግሞ ኢንተርሃሜው “መሳፍንት ተስፉ” በታላቁ አምበሳ እስክንድር ላይ የስም ማጥፋት ሲቀሰቅስ ሰማሁት።
ይህ <<እስላም ጠሊታውና ትግሬ ጠሊታው” ሰው
ታላቁ የሃይማኖት ዘርፍ የሆነው እስልምና እና አምሐራ ምድር የሚኖሩ ዘመዶቼ ተለቃቅመው እንዲገደሉ ወይንም ኑሮአቸው ተመሰቃቅሎ
እንዲጠረዙ’’ ለማወጅ ያልተሳቀቀ (ያልከበደው) ሰው የአንድ ታጋይ እስክንድር ነጋን ስም ማጠልሸት የሚግርም ባይሆንም፤ ሴራው ግን ለምን እስክንድር ላይ ይህ
ሁሉ መረባረብ አስፈለገ? የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ሰዎቹ ሌላ ስራ የላቸውም? ነው ወይንስ እነኚህ ማይሞች የወጡበት ዓላማ
አያውቁትም?
አሁን አሁን ገና ሳስበው የእስክንድርና ኔልሰን ማንዴላ የሕይወት ታሪክና የትግል ተሞክሮአቸው የደረሰባቸው የውስጥ ምቀኛ ስም ማጠልሸት አንድ ሆኖ አገኘሁት።
ማንዴላ ለሕዝቡ ነጻነት
ሲል የሚወዳት ባለቤቱና ልጆቹን ትቶ ነፃነትን መምረጥ ለዘመናት እስር በመግባት ተሰቃይቶ ነፃነትን አስገኘ። በኔልሰን ማንዴላ ላይ
ያኔም ሆነ ዛሬ ከሞተ በኋላም ስሙን በማጠልሸት የተጠመዱ ታዋቂ የሕዝብ መሪዎች አሉ። አንዱ “ማሌማ” የተባለው “Freedom of
Economic Freedom Fighters/EFF/” መሪ ነው። ይህ ወጣት ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ሲሆን የማንዴላ ስም አጥፊ እና
የባለቤቱ “ዊኒ ማንዴላ” ፖለቲካ ደጋፊ ሆኖ ማንዴላ “ከነጮች ጋር ተመሳጥሮ ለነጮች የሸጠን አሻጥረኛ ነው” እያለ ልክ እስክንድር
ነጋ ላይ በፋኖ ጎበዝ አለቃዎች እየደረሰበት ያለው የማያባራ ስም የማጥፋት ዘመቻ የተደረገበት የነፃነት ታጋይ ነበር።
እስክንድር ነጋም እየደረሰበት ያለው ተመሳሳይ ዘመቻ ነው። እስክንድር የትውልድ ሐረጉ ከሸዋ (የቆየ ቃለ መጠይቁን አድምጡ) የሆነ
ከፍተኛ ዘመናዊ ትምሕርት ካጠናቀቁ ሁለት ምሁራን እናት እና አባት የተገኘ የሃብታም ልጅ ነው። እስክንድር የተማረው ዋሺነግተን
ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ ውስጥ ነው። የፖለቲካል ሳይንስና ኢኮኖሚከስ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ወያኔ ሲገባ ወደ ሃገር በመሄድ ዘረኛው
የትሕነግ ሥርዓት ለመታገል በ1985 ዓ.ም የመጀመሪያ ጋዜጣው “ኢትዮጵስ” የተባለውን በማሳተም የተጨቆኑ ደምጾች ልሳን በመሆን ሥርዓቱን መታገልና ሕዝብን
ማንቃት ጀመረ። ከዚያም የትሕነግ የስለላ መርበቦች እንዲዘጋ አደረጉት፤ ቀጥሎም እኔ በስፋት ሳነባቸው የነበሩትን፤ “ሳተናው ምኒሊክ
እስኳል.. ወዘተ” የመሳሰሉ ጋዜጦችን በማሳተም ዘረኛውን ሥርዓት ሲታገል ቆይቶ በመጨረሻ ሁሉም ጋዜጦቹ ታገዱ።
ከዚያም የሰብአዊ
መብት ጥሰት ሲበረታ ያንን ለማስቆም 9 ጊዜ እስርቤት ገብቶ ተደብድቦ ስቃዩን አይቶ ረዢም አመታት ሲፈታ ሲታሰር ህይወቱን ለኢትዮጵያ
የሰጠ የነጻነት ታጋይ ነው። በዚህ ሥራው ዓለም መስክሮለት ሽልማት ተሰጥቶታል።
በተከታታይ
በ30 አመት ውስጥ ኢትዮጵያን በዘረኛ ፖሊሲ የገዙ ሁለቱ ዘረኛ ሥርዓቶች አምሐራን ግምባር ቀደም የጥቃት ሰለባ መሆኑን በመቀጠሉ
ባጠቃላይ የሀገሪቱ ሕዝብና አምሐራ ነፃ ለማውጣት ግምባር ቀደም ፖለቲከኛ ሆኖ የተለያዩ የትግል ስልቶችን በመቀየስ እስካሁን ድረስ
ማንም ኢትዮጵያዊ የነፃነት ታጋይ ያላደረገው አስገራሚ ሕዝብን አሰባስቦ ለትግል እንዲነሳሳ ሥርዓቶችን ያንቀጠቀጠና “ፊት ለፊት
ሳይሸሽ ሳይደነግጥ” የተጋፈጠ ልዩ የሆነ ትግል በማካሄድ የኢትዮጵያዊያን ቀልብና የሥርዓቱን መሪዎች ቀልብ ሳይቀር የሳበ ትግል ያቀጣጠለ ፤እነ ጃዋር መሐመድ ሳይቀሩ
የተገረሙበት ትግል ያካሄደ አስገራሚ የሆነ ሰው ሲሆን ፤ ለነፃነት የከፈለው የሕይወት ፤ የኑሮና የአካል መስዋዕት በብዕር ለመክተብ
በመጽሐፍ መልክ ይጠይቃል።
ለነፃነት
ሲሉ የሚወዳት ባለቤቱ እና እራሱ ለተደጋጋሚ ዕስር ተዳርገው በወቅቱ ነብሰ ጡር የነበረቺው የነፃነት ታጋይና ጋዜጠኛ ባለቤቱ “እስከዳር”
እስርቤት ውስጥ ሆና ብቸኛውን ወንድ ልጅ ተገቢውን ሕክምና ተነፍጋ ያልተሟላ ሕክምና ሰታገኝ በመከራ ልጃቸውን ወለደች። አፍሪካ
ውስጥ በቅርቡ እንዲህ ያለ የታጋይ ቤተሰብ የትግል ታሪክ እጅግ የሚገርም የማንዴላና የእስክንድር ተመሳሳይነት የታየው አዲስ
አበባና ጆሃንስ በርግ ውስጥ ነው።
30 አመት
ሙሉ ባሕሉን የጣለው አስቸጋሪው የአዲስ አበባው ወጣት ኢትዮጵያዊ ባሕል እንዲከተልና እራሱን እና ቤተሰቡን ከቅኝ አገዛዝና ዘረኛ
ሥርዓት ነጻ ለመውጣት በፖለቲካው እንዲሳተፍ አደገኛው ሥርዓት አስፈሪ ቢላዋ እየሳለበትና እየደበደበውም ቢሆን ታላቁ እስክንድር
ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል በኢትዮጵያ
የፖለቲከኞች ታሪክ የመጀመሪያ ነው።
እስክንድር አዲስ አበባም ሆኖ ጫካም ገብቶ ተቀናቃኝ አላጣም። ተቀናቃኞቹ ደግሞ የሥልጣን ሕልማቸው ሊነጥቃቸው
እንደመጣ በግልጽ ጦርነት የሚያውጁበት ለሕዝብ እንታገላለን የሚሉ አስመሳይ ነውረኞች ሲዝቱበት ተመሳሳይ ታሪክና የስም ማጠልሸት
ተዘግቦ ያለ ነው።
አንዲት ትንሽ ምሳሌ ልጥቀስ፡
አዲስ አባባ ውስጥ እያለ በአብይ አሕመድና በብርሃኑ ነጋ
የተቃጣበትን ማስፈራሪያና ስም ማጠልሸትን እንመለከታለን። ከዚያም ጫካ ውስጥ ፋኖ ከተቀላቃለም ተቀናቃኞቹን ተመሳሳይ ስም የማጠልሸትና የመግደል ዘመቻ እንመልከት
በአዲስ አባባ እንጀምር
የዘመነ ካሴ ሁለንተና መሪው የነበረው ብርሃኑ ነጋ ፤ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ጸረ አማራ ከሆነው “አ ኤም ኤን” ከተባለው የተገንጣይ ኦሮሞ የኦነጎች የፕሮፓጋንዳ ማሰራጪያ አውታር ላይ ቀርቦ ባደረገው ቃለ ምልልስ ስለ አብይ እና አዲስ አበባ (አስክንደር ነጋ ባለ አደራ) ጉዳይ ሲመልስ እንዲህ ይላል።
’አኔ አብይን ሙሉ ለሙሉ አምነዋለሁ!!!” ካለ በሗላ፤ “ታከለ ኡማም ቢሆን (እንደ አብይ አሕመድ) አሸጋጋሪ ነው” “በሕግም በምንም “የሌለ” ባላደራ “ምናምን” የሚባል ለኔ ብዙም እንትን አያደርገኝም……ታከለም ሆነ አብይ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አሻጋጋሪዎቻችን ናቸው”። ለዚህ ነው ወደ እዚያ ስለሚያሻግሩን እንርዳቸው አብረን እንሂድ የምለው።”>>
ሲል የዘመነ ካሴ የቀድሞ መሪ ብርሃኑ ነጋ እስክንድር ላይ የቅናት፤ የሴራ፤ ጠልፎ የመጣል፤ የማሳሰር
፤ስም ማጠልሸት ሲያደርግ ነበር። ብርሃኑ እና አብይ “ምናምን” የሚል ቃል እየተዋዋሱ እንዴት እንደሚጠቀሙ ታያለችሁ፡
ይቀጥልና አብይ አሕመድም
<<ባለ አደራ ነኝ ምናምን ከሚሉ ጋር ግልጽ ጦርነት እንገባለን>> አብይ አሕመድ እስክንድር ነጋ ላይ የመግደልና
ስም የማጥፋት እንዲሁም ማስፈራራት ዘመቻ የዛተበት።
እንደገና ጫካ ውስጥ ከፋኖ ተብየው ሥልጣን
የጠማው አደገኛው አዲሱ <<የጎጃሙ
”ፖል ፖት ክመር ሩዥ’’ ዘመነ ካሴ>> እስክንድር ላይ ያሰራጨው ታሪክ የዘገበውን የስም ማጥፋት ዘመቻ
ሰዎች ተሎ የመርሳት አባዜ ስላለን ይህንን ድጋሚ ላስታውሳችሁና መሳፍንት ወደ ተባለው ዘረኛ እመለሳለሁ፡
ይኼው እንመልከት፦ ታስታውሱ እንደሆን
የጎጃሙ ፖልፖት ዘመነ ካሴ እስክንድር ላይ የዛተው የቃላት ስም ማጥፋት ብቻ ሳይሆን እንደሚገድለው ወይንም እንደሚያስገድለው ነው።
የሁለቱ ልዩነት በፖልፖቱ አባባል መሠረት ልዩነታቸው <<የርዕዮተ ዓለም ግጭት
ነው>> ሲል ዘመነ ካሴ መግለጹን ታስታውሳላችሁ። የርዕዮተ ዓለም ግጭት
ያላቸው ድርጅቶች እና መሪዎች ደግሞ የሚፈታቸው “ጦርነትና መገዳደል ነው” ስለዚህ ዘመነ ካሴ እስክንድርን (ከቻለ) እራሱ ወይንም በተዘዋዋሪ ለማስገደል
ዝቷል። እስክንድር ከዚያ ሁሉ ስቃይና እስራት ወጥቶ ፤ ዛሬ ደግሞ በጎበዝ አለቃዎች በአምሐራ ደም ሥልጣን የሚጠማቸው እንደ
ዘመነ ካሴ የመሳሰሉ “የአምሐራ የነጻነት አኩሪ ምልክት የሆኑትን እንደ እነ ታላቁ እስክንድር ነጋን” ለግድያ ሲፈለግ
ከመገርምም አልፎ እኛ ትግሬዎች “መርመም” የምንለው አስገራሚ ደረጃ የሚያደርስ ነው።
ላስታውሳችሁ ቃል በቃል፤እንዲህ ያለውን;
<<(ግጭታችን) የዓለሙና የከበደ የሁለት ሰዎች
ግጭት አይደለም።ይህ የርዕዮተ ዓለም ግጭት ነው፡፡ የሌባና ፖሊስ ትንቅንቅ ነው። የትውልዱን ትግልና ድል ሊሰርቁ
ጭምብል ለብሰው ማጅራት መምቻ ቆመጥ ታጥቀው በጠራራ ፀሐይ በመጡ ሌቦችና የትውልዱን ደምና አብዮት ሰለሚጠብቁ ፖሊሶች መካከል ያለ ግብግብ
ነው።በሕልሜ የመጡብኝ
አሁን ነው”፡፡…. >> ማለቱን እናስታውሳለን።
“በሕልሜ የመጡብኝ አሁን ነው” ሲል፡፡ በሌላ ቀን ይህንን ሕልሙ ሳያፍር ሳይደብቅ በግልጽ የነገረንን እንደገና በተቀራራቢ ላስታውሳቸሁ፤
<<እኔ የነጋሽና አንጋሽ ዘር ስለሆንኩ ገና ከዘራችን/ ስንፈጠር ከመለዘራችን (ዲ ኤን ኤ) የመሪነት ቦታ የታደልን ፤ ከእናቴ ማህጸን ውስጥ እያለሁ የመሪነት ቦታ ሳልም የነበርኩኝ ባለሕልም ነኝ>>
ሲል ሲመኘው የነበረው የመሪነት ሕልም ማግኘት እስክንድር
ነጋ ስለተመረጠ ያንን ሕልም መራጮቹ ሳይሆኑ “እስክንድር እራሱ እንደነጠቀው” አስመስሎ እስክንድርን የዘመነ ካሴን ሥልጣን ሕልም
ነጣቂ አድርጎ በመፈረጅ ከርዕዮተ ዓለም ልዩነት
አልፎ የሥልጣን ሕልሜን ነጠቀኝ በሚል ነው ይህ ሁሉ ዛቻ እና ስም ማጥፋት ውስጥ የከተተው።
ይህ ሁሉ እስክንድር ላይ ጉትጎታ የሚነግረን ነገር ዘመነ
እና ቡድኑ የፖለቲካ ምጥቀታቸውና ልምዳቸው “ኤለመንታሪ” ስለሆኑ፤ እስክንድር ጫካ ላይ መገኘት የበታች ስሜት ስለተሰማቸው
አጉራዘለል ሕልማቸው በዚህ በተማረ ትዕግስተኛ ሰው እንደተሸማቀቁ ግልጽ ነው። እስክንድርን ጎስጉሰው፤ ጎስጉሰው ስም አጥፍተው ተስፋ
እንዲቆርጥ በማድረግ በመጨረሻ ምናልባትም ትቷቸው ይሄድ ይሆን የሚል
ተስፋ በመጣል ከትግሉ እንዲወጣ እያደረጉ ያሉት “ሴራ” እንደሆነ ግልጽ ነው።
ምናልባት ተስፋ ቆርጦ ትግሉን ቢተው ይሄው አላልናችሁም
ወይ ለማለት እንዲመቸው የጎጃሙ “ፖልፖት” እንዲህ ያለውን ላታውሳችሁ።
<<እሰከንድር ሲያምሰን ከርሞ ነገ ሽሉክ ይላል ያኔ እንተዛዘባለን።>> ያለውን አስታውሱ። አያችሁ የስም ማጥፋት ሴራው? <<እሰከንድር ሲያምሰን ከርሞ ነገ ሽሉክ ይላል ያኔ እንተዛዘባለን።>> የሚለው የምኞትና የተንኮል “ኮንሰፒራሲ” በግልጽ ማየት ትችላላችሁ።
እስክንድር ላይ ብቻ አይደለም “ፖለፖቱ ዘመነ” ዘመቻው
ያጧጣፈው። በቅርብ የራሱ ወዳጁም ጭምር ላይ ነው። እንዲህ ሲል፡
<<ወንድምን መታዘብ ትልቅ ሕመም አለው፡፡አንዳንድ ወንድሞቻችን በጨለማ ሄዱ አዝነናል፡፡>>
እያለ የሚለው የሄሊኮፕተር አብራሪው ሲታሰር ሲፈታ አብሮ
የታሰረና የተሰቃየ ፤ ሲደበቅ አበሮት የተደበቀ ፤ የቅርብ መስጢር አማካሪውና ጓዱ የነበረው የዘመነ ቃል አቀባይ የማርሸት ጸሃየ
የእናት እህት ልጅ ነው የሚባልለት <<ካፕቴን
ማስረሻ ሰጤን>> ነው፡፡ ጎጃም ውስጥ የራሱን ፋኖ ያደራጀ ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ ዘመነን አልመርጥም ብሎ
እስክንድርን ለመሪነት ድመጽ በመሰጠቱ ነው፡፡ (ወንድሞቻችን ከዱን
የሚለው ኡኡታው)፡፡
በዛው እወጃው ብዙ ነገር ታስታውሳላችሁ። “እኛና እነሱ”፤ “እኔ እና እሱ” የሚሉ
ቃላቶች ይጠቀማል። አገው ነው እያሉ የሚያሙት ዘመነ
ካሴ ተመልሶ እስክንድር ላይ <<እኔ ንጹህ አማራ እስክንድር ግን አማራ መስሎ ጭምብል በመልበስ የአማራዎችን
የኛን የንጹሃን አማራዎችን ትግል ለመጥለፍ የተቀላቀለን
አማራ ያልሆነ ሰው ነው።>> ሲል የፋሺስቶች ፍረጃ ውስጥ መግባቱንም ታስታውሳለችሁ፡፡
ይህ ደግሞ መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ ሲሆን እስክንድር ግን አማራ ሰላልሆነ ጭምብል በመልበስ መነሻው አማራ ቢሆንም መዳረሻየ ግን ኢትዮጵያ ናት ሲል “የርእዮተ አለም አመለካከት ልዩነት አለን” እያለ የገለጸው ተመሳሳይነቱ ፡ልክ እኛ ወያኔ የምንቃወም መዳረሻችንና መነሻችን ኢትዮጰያ ስንል የነበርን ትግሬዎች “ሸዋውያን ተጋሩ” የሸዋ ትግሬዎች እንደሚሉን ሁሉ ፤ የጽንፈኛ ፋሺስት ብሔረተኛነት አቀንቃኙ ዘመነ ደግሞ እስክንድር አማራ ሳይሆን አማራ መስሎ የአማራነት ጭምብል የለበሰ “የኢትዮጵያ አማራ” ማለቱ ነው (የኛ ያልሆነ ፤ ጭምብል የለበሰ “ጸጉረ ለወጥ”) ሲል፡፡የእብደቱና የብልግና ባሕሪው ማሳያ ብዙ ነው።
እራሱን የአማራ ሕዝብ ፖሊስ አድርጎ ሲሾም እስክንድር ነጋ ደግሞ “ማጅራት መቺ ሌባ” በማለት በጸያፍ ቃል ሲዘልፈው የነበረውንም ታስታውሳላችሁ፡፡
<<ፖልፖቱ ጎጃሜው>> እራሱን ጉልበተኛ ድመት (ዲገላ) እስክንድርን ደግሞ ደካማ ዓይጥ አድርጎ በመሳል “ትግሉ የአይጥና የድመት ነው (በፖሊሰና በማጅራት መቺ)” አሁንማ ተነቃቃን እኮ በማለት ደካማው እስክንድርን በ“ዲገላው ድመት” (በፖሊሱ ዘመነ ) ተይዞ እንደሚበላ/እንደሚዋጥ ተዝቶበታል፡፡
ይህ የመንደር አጉራ ዘለል ወጣት አንዲህ ያለ
ባሕሪ ያገኘው ኤርትራ ውስጥ እያለ ብርሃኑ ነጋ ጋር ሲላላክ ነው። ዓላማውም በተቃውሞ ለመምጣት የሚዳዱ አዳዲሶች ካሉ ለማስደንገጥ
ነው።
ይህ ሁሉ ሴራና የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያሳየው ፖለቲካ
በጠመንጃ ብቻ የሚገራ የመሰላቸው የፖለቲካ ጥበብ ያልተላበሱ በሕገ አራዊት የሚመሩ እንደ እነ ዘመነ ካሴ የመሰሉ አደገኛ
ታጣቂ ቡድኖች፡ እስክንደር ላይ ማሽካካታቸው አልበቃ ብሏቸው፤ አሁን ደግሞ ሰሞኑን
መሳፍንት የተባለ ጎንደር ውስጥ የሚንቀሳቀስ አንድ ታጣቂ ቡድን እመራለሁ የሚል ሽማግሌ እስክንድር ላይ ሲጮህና የስም
ማጥፋት ዘመቻ ከፍቷል።
ወደ ዘመነ ካሴ አሽከርነት የገባው <<የአረጋዊነት
ባሕሪ ያልተላበሰ>> ትንሽ ሰው። “እስክንድር ሊከፋፍልን መጣ፤ ከብልጽግና የባሰ ነው” ሲል አስገራሚ ድንቁርናው ሲተፋ በሚዲያ ሰማሁኝ።
እንደ ጅብ ተሰባስበው በአንበሳው እስክንድር ላይ እያስካኩት
ያሉት ጅቦችም ሆኑ <<እስላም የሆነ ኢትዮጵያን ማስተዳደር የለበትም>><<አምሐራ ምድር ውስጥ ያሉት ትግሬዎች ተለቃቅመው ወደ አገራችው ይውጡልን>>
በማለት የሚታወቀው የጎንደር ኢንተርሃሜው “ሁታዊው መሳፍንት” እንዲህ ያለ ቅሌት ውስጥ በመዘፈቅ የፈለገውን የጅብ ጩኸቱን ቢያስካካ በተግባር እንደሚታወቀው የጅቦች ማስካካትና ከበባ የአምበሳውን
ቅስም ከቶውንም ተሰብሮ አያወቅምና፡ እስክንድር ላይ መዝመት በእሳት መጫወትና የአምሐራውን ትግል
እንዲበላሽ ማድረግ ስለሆነ ጅቦች ማስካካታችሁን በሥርዓቱ ላይ አትኩሩ!@! አምበሳው ግን በጅቦች መስካካት ደምብሮም
አያውቅ!@!
ጌታቸው ረዳ Ethio Semay
No comments:
Post a Comment