ሳይገዙ ራሳቸውን
ለቅኝ ገዢዎች ፖለቲካ የሸጡ ወዶ ገብ ባርያዎች ጋር ጥላቻን ስለማቆም መወያየት ቅዠት ወይንስ የዋህነት
ጌታቸው ረዳ
11/14/24
Ethiopian
Semay
ሦስት አምሐራዎች ሦስት ኦሮሞዎች ሦስት ትግሬዎች… ጥላችን
እንዴት እናቁም በሚል በኢትዮጵያዊው በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲው መምህር በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ሰብሳቢነትና አዘጋጂነት አሜሪካ
ውስጥ በፕሪንስተን ከተማ የተደረገ ውይይት ነበር።
ወደ ወቀሳዊ ትችቴ ከመግባቴ በፊት እሳቸውንም በሚያስመሰግናቸው
ነገሮች ልጀምር።
ይኼውም በኢትዮጵያ ምሁራን ታሪክ ውስጥ ከጣሊያን ወረራ
በኋላ ሀገር በቀል የሆነ ኢትዮጵያዊ ልብስ በመልሰበስ ታሪክ ውስጥ መመዝገብ ያለባቸው ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ምሁር ሆነው ከዚህ ሁሉ
ሚሊዮኖች ምሁራንና ከተሜ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ አለባባስ የተከተሉ ስለሆኑ በዚህ አዘጋጅ ብዕር በወርቅ የታሪክ መዝገብ ውስጥ ስማቸው
መመዝገብ አለበት እያልኩ እና የሳቸውን አርአያ ላለመከተል ችግራችን ምን ይሆን የሚል ጥናት ቢደረግ እጠቁማለሁ።
ሁለተኛው ስነ ትምሕረታቸው፤ የጥንት ታሪክ ምሁርና ከፍተኛ
ሊቅ ቢሆኑም የዘመኑ ፖለቲካ ቢገባቸውም፤ ውስብስቡ የዘመኑ ፖለቲካ ለመፍታት የሃይማኖት መጻሕፍት በሚንቁ ምሁራንና ባላንጣዎችን
የመጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክሮችን እየጠቀሱ ባላንጣዎችን ለማግባባት መጣራቸው የሚያስመሰግናቸወ ቢሆንም ከዚያ የላቀ መፍትሔ ቢሹ ይሻል
ይሆናል እያልኩ ኢትዮጵያዊ ፍቅራቸው ግን ከንግግራቸው የሚወደዱ ናቸው (የሚያስወቅሳቸው ያለፉት ሌሎች ሰነዶቻቸው በግሌ ሳልረሳ
ማለቴ ነው)።
አሁን ወደ ርዕሴና ወቀሳው ልግባ፡
ባለፈው ወር ጥላቻን እንዴት እናቁም በሚል የውይይት ግብዣ በማድረግ እሳቸው በርዕዮት ዓለሙ ምንጊዜም ሚዲያ ቀርበው በተናሩት መሠረት ከአማራ ፤ከኦሮሞና ከትግሬ ሦስት ሦስት ሰዎች ምንላባትም ስሙ ያልተጠቀሰ ከሌላ ነገድ 3 ሰዎች ጠርተው (12 ?) ማወያየታቸው ነግረውናል።በዚህም ልደቱ ግምባር ጠቀስ ተወቃሽ ሆኖ የውዝግብ ርዕስ ሆኖ እንደነበር ታስታውሳላችሁ።
ተደረገ ስለተባለ የ12 ሰዎች ውይይትም ለሕዝብ አውዲዮውም
ይሁን ቪዲዮው ባለቤቱ ለሆንነው ለኛ ለሕዝብ እንድናደምጠው አልተደረገም። ለምን?
የፕሮፌሰር ይስሐቅ ማሕደር የሚያሳየው በሚያዘጋጁዋቸው ብዙዎቹ
ግብዣዎች ድብቅና አነጋጋሪዎች ናቸው። ያም ሆነ ይህ የፕሮፌሰሩ ዓላማ ምንም ይሁን ምን ፤ ሙከራው ያላዋቂዎች የሚያደርጉት ፤ በስሜት
የተገፋፋ ግብዣ እንጂ ካንድ ዓለም አቀፍ ታዋቂ ምሁር የሚጠበቅ ዝግጅት አልነበረም። በዚሁ ባስተላለፉት የጽሑፍ ጥሪ አንድ አደገኛ ሐረግ ወደ መጨረሻ ደምዳሜ
ጽሑፌ አሳያችኋለሁ።
ላሁኑ ግን በዚህ ልጀምር። ከብዙ አመታት በፊት እንዲህ
ዓይነት ጥሪዎች እያጋላጥኩ መላቅጡ ያጣ በማስማማት ጥሪ ስም “ጅቡም
በጉም ፤ አህያውም አንበሳውም፤ ዘንዶውም ፤ እባቡም ፤ እንሽላሊቱም ፤ ዝሆኑም፤ዓሳውም፤… ወዘተ… ተበዳዩም በዳዩም ወንጀል አድራጊ
ድርጅትም ግለሰብም በገለልተኛ ተቋም በሕግ ከመታየቱ በፊት ባንድ ማዕድ
ሰብስቦ ለፖለቲካ ውይይት መጋበዝ እንደማይሰራ ስጽፍ ብዙ ስሰደብ ነበር ። እንዲያ የተሰደብኩበት ከአመታት በኋላ እውነተኛ ትችቴ
እውትነቱ ሲታይ ሰዎች አያፍሩበትም። ዛሬም ያንኑ እየደገሙት ነው። ምክንያቴንም ላስቀምጥ፡
ታስታውሱ እንደሆነ ውጭ አገርና ውስጥ አገር ያለው ድንዙዝ ሕብረተሰብ ግንቦት 7ም ሆነ ኦነግ እያጨበጨበ የሁለቱም አንድነት ሲያዳምቅ እኔ እና ጥቂት ሰዎች ይህ የጋራ ውይይትም ሆነ አንድነት ምናምን የሚባለው አይሰራም፤ ስንል ስንሰደብ ነበር። ለምሳሌ ግንቦት 7ን የሚነካ ሰው ጭራሽ መስጊድና ቤተክርስትያን እንደገባ ውሻ ነበር የሚቆጠረው። ሃቁ ግን ዘመነን ካሴ ሲያገለግልበት የነበረው ግንቦት 7 የተባለ ጸረ አማራ ድርጅት ነበር። ከአቶ ተክሌ የሻው ጽሑፍ ልዋስና ልጥቀስላችሁ፡
ለምሳሌ
ግንቦት 7
ማለት የግንቦት 7 አመራር አባል ለመሆን ከአማርኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ የሚናገር መሆን እንዳለበት ይደነግጋል።
በግንቦት 7 ልሣን በሆነው ጋዜጣቸው ቁጥር 25 ጥቅምት 2001 ዓም ርዕስ አንቀጽ፣ ለ250 ዓመታት በነጮች ሲገዙ የነበሩት ጥቁሮች ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ከበቁ፣ እኛም ለአሥር ሺ ዓመታት በዐማሮችና በትግሮች ስንገዛ የኖርነው ኦሮሞዎችና ደቡቦች ሥልጣኑን ከነሱ ነጥቀን በሚቀጥለው ጊዜ የኛ ጊዜ መሆን አለበት ብሉ ሲሰብክ የነበረ አደገኛ ድርጅት ነበር።
ምን ይህ ብቻ
«የደራሲው ማስታዎሻ» በሚል ርዕስ የሻዕቢያው ሰላይ ተስፋዬ ገብረአብ የጻፈውን ዐማራን፣ ምኒልክንና ቴዎድሮስን የሚዘልፍ፤ ኢትዮጵያን የሚበታትን የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን አራክሶና እንዳልነበሩ አድርጎ የጻፈውን፣ ያሳተመው ንብረትነቱ የግንቦት 7 የሆነው «ነፃነት አሳታሚ" ነበር። በዚህ አደገኛ ሰነድ ሽፋን ላይ ብርሃኑ ነጋ የሚያበረታታ ጽሑፍ አድንቆ አመስግኖ ጽፎለታል።
እንዲህ ያሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጥላቻን ለማስወገድ በሚል ይደረጉ የነበሩት ከሻዕቢያ ከኦብነግና ከነ ኦብነግ የጋራ ውይይቶች እርባና ቢስ የዥዋዥዌ አንደነትና ጥላቻን የማቆም ውይይት እንደነበሩ ኦነግና ግንቦት 7 <<በአፓርታይዳዊ “ኦርማ-ፕሮታንት” ርዕዮተ ዓለም ቀያሽና መሪ አብይ አሕመድ>> ጋባዥነት አአዲስ አባባ ገብተው ሳምንት ሳይሞላቸው ያሳዩት መወነጃጀል፤ ፍጥጫና መሰዳድብ እንዲሁም ኦነግ ያደረገው በጋሞዎችና አማራ የቡራዩ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ ሲታይ ተቃውሞአችን ልክ እንደነበር አሳይተናል። ያልነውም ልክ ነበር። አሁንም እየተደገመ ነው። “እባብን ያየ በሊጥ በረየ” የሚባለው ብንጠረጥር ያንን ያየን አሁን ሊደገም ነው ብለን ብንጠርጥር በኛ ላይስ እንዴት ጸረ አንደነት ናቸው ተብለን ይፈረድብናል?
ቢያነስ ከ1983 ዓ.ም እንደ ሰደድ ብሶበት የተቀጣጠለው
ጥላቻ በትግሬዎችና በኦሮሞ ናዚያውያን ፋሺሰቶች መሪነት ተጽፎ
በሕገመንግሥት እውቅና አግኝቶ ተቀርጾ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰጠ የመበጣበጫ ገጸ በረከት ሆኖ ከተሰጠ ጀምሮ የመበጣበጣችን
መነሻው “ጥላቻ” አንደሆነ ብዙ ሕዝብ ቢያምንበትም፤ በሚገርም ሁኔታ ለብጥብጡና ለጭፍጨፋው መነሻ ሕገመንግሥቱ ልክ እንደ ናዚ ጀርመኖችና
ፋሺሰት ጣሊያኖች ለሕገመንግሥታቸው እንደቆሙት ሁሉ ለጥላቻ መነሻው በሕገመንግሥታቸው መዝገብ ውስጥ ያጸደቁት የቋንቋና የዘር/ነገድ/
አስተዳዳር እንዳልሆነ ይከራከራሉ። የጥላቻው ሕገ መንግሥት ብለን ብዙዎቻችን ሃያሲያን የምንጠራው ይህ “አፓርታይዳዊ ሕገመነግሥት”
ካልተወደገደና ሕግምንግሥት አርቃቂቀዎችና በዘር (ነገድ) ጭፍጨፋ የተሳተፉት ሁሉ ተጠያቂዎች ካልሆኑ ጥላችን ለማስቆም ውይይት መፍተሔ አይሆንም።
ታዲያ “ጥላቻ የችግራችን ምንጭ ነው” ከተባለ ጥላቻን ለማስቆም ጥላቻን መመሪያቸው
ካደረጉት ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰብ ምሁራኖች ውይይት አስፈላጊ ነው የሚሉ ሰዎች የዘነጉት ነገር ጥላቻ አራማጆቹ በሚመሩበት የጥላቻ
ፖሊሲያቸው (ርዕዮተዓለማቸው/ideology/) እየተመሩ የተለያዩ ብሔራዊና ሰብኣዊ “ወንጀሎች” ፈጽመዋል። ወንጀል ፈጻሚው ደግሞ
ወንጀል ፈጽሜአለሁ አይልም። ተበዳይ ሆኖ ነው የሚናገረው (እየሆነ ያለውም ያ ነው)። ጥላቻን ለማስቆም፤ ወንጀለኛውን መለየትና
ማወቅ የመጀመሪያ ተግባር ነው። ወንጀለኛን በጉያ አቅፎ ጥላቻና ወንጀልን ማስቆም አይቻልም።
ውይይት ከመደረጉ በፊት ጥላቻን ለማስቆም መደረግ የሚገባቸው
ብዙ ነገሮች ቢኖሩም። ከነሱ ውስጥ ዋነኛው “ተጠያቂነትን” መቀበል ነው። ተጠያቂነት ሳይኖር የፈለገው “ውይይት” ቢደረግም ውጤቱ
“ጉንጭ አልፋ” ውይይት ነው የሚሆነው። በዚህ ረዢም የፖለቲካ ዕድሜየ የታዘብኩት ነውና እመኑኝ።
ባጭሩ ተጠያቂነት እንዲኖር ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ማድረግ የነበረባቸው
(ማድረግ ከነበረባቸው ላይቀር) የጥላቻ ፖሊሲ ፤የመገንጠል ፖሊሲ፤ የነገድ ፤የቋንቋ፤ የሃይማኖት አጭበርባሪዎች ፖለቲካው ውስጥ
እየረጩት ያለው የጥላቻ መርዝ፤ በተከታታይ ከ1966 ዓ.ም እስካሁን ድረስ ያሉት መሪዎች የተከተሉት አፍራሽና የጥላቻ አስፋፋ ፖሊሲ
በፖለቲካ የተሳተፉም ሆኑ የሚመሩ ሰዎች ተጋብዘው በፓነል መልክ ተዘጋጅቶ ሕዝቡ እንዲሰማውና እንዲወያይበት ማድረግ “ለቅድመ ተጠያቂነት”
ዝግጅት የሚረዳ ሃሳብ አንዲፍልቅ እና ለወንጀሉና ለጥላቻ ቅስቀሳ አራማጆች እንማን እንደሆኑ ስም እየተጠቀሰም ቢሆን ምን አንደተናገሩ፤ የጥላቻ ንግግራቸው ሕዝብ እንዲያውቀውና
ምንነታቸውና እነማን እንደሆኑ እንዲታወቅ ማድረግ እንጂ እሳት አስነሺዎች እንደ ጨዋ ፖለቲከኛ እየተጋበዙ እነሱን የሚያጋልጥ ውይይት ለሕዝብ ሳይነገር
ወንጀል አድራጊዎች የሚፈነጩበት ሜዳ እየተሰጣቸው ወንጀልንና
ወንጀለኞችን በዝምታ እንዲታለፍ ማድረግ ይብልጥ “ለጥላቻ ምክንያት መነሻው” መደበቅ ነው።
የፕሮፌሰሩን ጥሪ ባጭሩ ላስነብባችሁ፤ እንዲህ ይላል፡
Dear Brothers and
Sisters
This is an
invitation to bring together a few leaders of all Ethiopian religious, ethnic
and professional groups at home and abroad to discuss openly the root causes of
the hate that lead to anger and fighting. Can we explore together a way to embrace
each other weather as one people or different nations to promote peace and stop
our “writings and broadcast that generate hate and become obstacle to fight the
true enemies of our people; hunger, disease and illiteracy from our millions
suffer daily.
ወደ አማርኛ ልተርጉመው
ውድ ወንድሞች እና
እህቶች
ይህ ጥሪ በሀገር
ውስጥ እና በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሀይማኖት፣ የነገድ እና ሙያዊ ቡድኖችና መሪዎችን በመሰብሰብ ወደ ቁጣና ትግል የሚያመራውን
የጥላቻ መንስኤ በግልፅ ለመወያየት ነው። ሰላምን ለማስፈን እና "ጥላቻን የሚፈጥሩ እና የሕዝባችንን እውነተኛ ጠላቶች ለመዋጋት
እንቅፋት የሚሆኑ ጽሑፎችንን እና ስርጭቶችን ለማስቆም እንደ አንድ ሕዝብ ወይም የተለያዩ ሀገራት ሆነን መተሳሰብንና መተቃቀፍ የምንችልበትን
መንገድ አብረን በማሰስ የሕዝባችን ጠላት የሆኑትን በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝባችንን እያሰቃዩ ያሉትን ረሃብ ፣ በሽታና መሃይምነት
ላመቆም እንዲያመች…..።>>
እያሉ ለጥቂት ሚዲያዎች ያሰራጩት ባጭሩ ትርጉም ይህ ነበር። በጥሪው ላይ ያየሁት
አደገኛ ያልኩት ጥያቄ የጫረብኝ ስለ ተጻፈው ሐረግ ይህንን ልበልና ልደምድም።
(እንደምታውቁኝ እኔ ለበርካታ አመታት ብዙ ተከታይ ያለኝ ፖለቲከኞቹ የሚያነቡኝ
የቆየሁ ብቸኛ የትግሬዎች
ፖለቲካ ተቀዋሚ የሚዲያ ሰው ነኝ፡ ሆኖም እነ ልደቱ አያሌውም ይሁኑ ፕሮፌሰሩ ወይንም ሌሎች ሚዲያዎች ጽሑፎቻቸው
ሲልኩ እኔን እንደ መጽሐፍ ደራሲም ፤እንደ ሚዲያ ሰውም አይቆጥሩኝም…
ሚዲያ ከሚባሉት ግን በብዙ መንገድ የቆየውም ይሁን አሁን ያለው ፖለቲካ የምተንትን የቆየሁበት የምጨብጠውና የምለቀው የሚዲያ ሰው
ነኝና… ፡(እውነታ ነውና እንደ ጉራ አትቁጠሩት)፤ የምጽፈው ያነባሉ እንጂ የሚያሰራጩት ትላልቅ ሰነዶችም ሆኑ ጥሪዎች አይልኩልኝም) ፕሮፌሰሩ ያሰራጩት ጥሪ ያገኘሁት ከምንጊዜም ሚዲያ ያገኘሁት ቅንጫቢ ነው። )
ለማንኛውም በጥሪያቸው ላይ ያየሁት አደገኛ ሐረግ ልጥቀስ
፤
እንዲህ ይላሉ፡
<<Can we explore together a way to
embrace each other weather as one people or different nations to promote
peace…>> ሰላምን ለማስፈን እና "ጥላቻን የሚፈጥሩ እና የህዝባችንን እውነተኛ ጠላቶች
ለመዋጋት እንቅፋት የሚሆኑ ጽሑፎችንን እና ስርጭቶችን ለማስቆም እንደ አንድ ሕዝብ ወይም የተለያዩ ሀገራት ሆነን መተሳሰብንና መተቃቀፍ የምንችልበትን መንገድ አብረን በማሰስ….>>
ይላል የፕሮፌሰር ይስሐቅ ጥሪ።
አስበኸዋል!? ይላሉ የዘመኑ ወጣቶች አስባችሁታል /ይታያችሗል/ እንደ አንድ
ሀገር ወይንም እንደ የተለያዩ ሀገራት ሆነን የሚለው ጽሑፋቸው?
የተለያዩ ሀገራት ሆነህ እንዴት ነው መተሳሰብና መተቃቀፍ
የሚቻለው? የተለያዩ ሀገራት የሚባሉት ከ12 ቱ ታዳሚዎችስ እንማን ይሆኑ? ከሚያስተጋቡት ጥያቄና ፖሊሲ “ኦሮሞዎችና ትግሬ” ናቸው ስለ መጻኢ ሌላ አገርነት የሚያስተጋቡት። ታዲያ
“ኢትዮጵያዊያን አይደለንም” “ሌላ ሀገር” (አንደ ፕሮፌሰሩ አባባል የተለያዩ ሀገራት) ነን ከሚሉት ከነዚህ የምዕረባውያን
ፋሽቶች የመንፈስ ውራጅ ከሆኑ “ናዚያዊ ኦነጋውያን እና ፋሺታዊ ትሕነጋውያን” እንዴት ሆኖ ነው “ኢትዮጵያዊያን ነን ከሚሉ አምሐራዎች
ጋር ቁጭ ብለው ሳይገዙ ራሳቸውን ለቅኝ ገዢዎች ፖለቲካ የሸጡ ወዶ ገብ የናዚና የፋሺሰት ፖለቲካ ባርያዎች ጋር አፍላፍ ገጥሞ የተለያዩ ሀገራት ነን
ከሚሉት ጋር መተሳሰብና፤መተቃቀፍ የሚቻለው?
በክፍል ሁለት <<ሳይገዙ ራሳቸውን ለቅኝ ገዢዎች
ፖለቲካ የሸጡ ወዶ ገቦች>> በሚል ርዕስ እመለስበታለሁ፡
ጌታቸው ረዳ
No comments:
Post a Comment