Saturday, November 30, 2024

የ6 አመቱ የኦሮሙማ አንደበቶች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/30/2


         የ6 አመቱ  የኦሮሙማ አንደበቶች

       ጌታቸው ረዳ

      Ethiopian Semay 11/30/24

 ሰሞኑን አንድ ወጣት እንደ በግ አጋድመው አንገቱን ሲያርዱት የሚያሳይ ቪዲዮ እንደተሰራጨ ሰምተናል። አሰራጪዎቹም አራጁ ፋኖ እንደሆነ  የአብይ ኦሮሙማ ባለሥልጣኖች በኦነግ ሚዲያ ላይ ቀርበው መናገራቸው አድምጠናል። አራጅ ሆኖ የተገኘው ግን ኦሮሙማው ቡድን እራሱ እንደሆነ በማስረጃ ቀርቦ አይተናል።

በኦሮሙማ መርህ የሚመሩ የኦሮሞ ዩኒቨርሲቲ ት/ቤት ወጣቶች ግድያው በፋኖ ተፈጽሟል ተብሎ ስለተነገራቸው አድማ መምታታቸው አይተናል። ያ ዜና አየር ላይ እያለ፤ ከትናንት በስትያ በሚገርምና በሚያሳዝን መልኩ ግን አርሲ በሚባለው 99% እስላም በሆነው 1% አምሐራና ኦርቶዶክስ የሆነ ኗሪ ግን አንድ ቃል ከተናገረ በሜንጫ አንገቱ የሚቀላበት የጃዋር ትውልድ ቦታ በርካታ ሰዎች ተቀልተውና ታርደው መሞታቸው ቢዘገብም እነዚያ አድማ በመምታት ፋኖን እና አምሐራን በመዝለፍ መሬት ሲያውኩ የነበሩ “ተማሪዎች” ድምጻቸውም ከቶ አልተሰማም።  ይህ የኦሮሙማ ፕሮጀክት አንዱ ክፍል ነው። ኦነግ ማለት ብዙሓኑ የኦሮሞ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ድርጀት ነው። "ኦነግ" ማለት ኦሮሞ": "ወያነ" ማለት "ትግራይ ሕዝብ" ነው ስለው የከረምኩት ለዚህ ነው። ብዘሓን የሚባሉት ትግሬዎችም ሆኑ ኦሮሞዎች “ጣቱ” ክፍል ነው። ወጣቱ ደግሞ የነዚህ ድርጅቶች አማኝ ነው።

        የዛሬዋ ኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ ማንበብ የማይፈልግ ፎቶግራፍ ብቻ የሚያደንቅ ብዙ ደንቆሮ የተሸከመች ምድር ነችና እስኪሰለቸን ደጋግመን ስለዚህ “ኦሮሙማ” የሚባለው ፕሮጀክት/ግብ/ ፈልሳፊው ማን እንደሆነ ግቡና “ቅኔው/ፊቹን” ማሳወቅ ስላለብን ቢሰለቻችሁም እየመረራችሁ ዋጡትና ኦሮሙማ ምን ማለት እንደሆነ ከነግቦቹና ነግግሮች ለማየት ይህንን ማስረጃ አንቡቡ።

 ዘመናዊ ትምሕርት በቀሰሙ የኦሮሞ “ምሁራን” እምነት “ኦሮሙማ” የሚል ቃል <<ኦሮሚያን በቅኝ ግዛት የያዘው የአቢሲኒያ (ኢትዮጵያ) ተስፋፊነት ማለትም የቢሲያኒ ሃበሻዎች ሥልጣኔ ባሕል ፤ቋንቋ፤ እና ሃይማኖት የሚጻረር ነጻ አሮሚያ ለመመስረት የምንጠቀምበት አታጋይ መርህ ነው>> በማለት << (ኦሮሙማ) ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን የዐምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ ይታይ ነው።>> ሲሉ

 አንዳንዶቹ ደግሞ <<ኦሮሞነት>> ማለት እንጂ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጻረር ባሕሪ  ነገር የለውም ሲሉ ሰምተናቸዋል። ከላይ ያለው የመጨረሻው አባባል   የዋሃን ሊያታልል ይችል እንደሆን እንጂ ከሥር መሠረቱ የቃሉ አመጣጥና የቃሉ ለውጥ ከጥንት የተጻፉ መጻሕፍት ስንመረምር እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን ትርጉም ያለው የዜግነትና ሌላ ሃገርነትን የሚመኝ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የሚያልም አጠራር ነው።

        ስሙን የተፈለሰፈው በ18ኛው ክ/ዘመን ጀርመኖች የላኩት በጀርመናዊው የፕሮተስታንት ሚሺነሪ በምስራቅ አፍሪቃ የተመደበው የቅዥ ግዛት አስፋፊና ሰላይ የነበረው <<ዮሃን ክራፕፍ>> ነው።

ቃሉ “ዛሬ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊነትን ለመተካት የብሔረተኝነት መገለጫ አድርገው የሚያቀነቅኑት ኦሮሙማ ዕሳቤም መሠረቱ የተጣለው ኦርማኒያ  (ጀርመኒያ ከሚለው ተመሳሳይ የቅጂ ትርጉም) ከሚለው በክራፕፍ እሳቤ ውስጥ ነው የዛሬው “ኦሮሙማ” ስያሜ የመነጨው።

“ዐምሐራ ሕብራዊ ማንነቶችና ተግባሮች” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው ይህንን በማስረጃ ለማጠናከር ሲያቀርበው በገጽ 365 ክራፕፍ የዘገበውን እንግሊዝኛ እና አምሐርኛ ትርጉም እንዲህ ይላሉ፡

<< …their language they call “Afan Orma” the mouth of the Ormas; so as the Ga*ll*as have no general name to indicate their nationality or its seat, I propose to include both the designation of Ormania” (Travels, Researches, and missionary Labors, During an Eighteen Years’ Residence in Eastern Africa p.61)

ይህንን ወደ አማርኛ ሲተረጉመው

<<ጋ..ሎ…ች ቋንቋቸውን “አፋን ኦርማ” ይሉታል የኦርማዎች አፍ ብለው ይጠሩታል እናም ጋ..ሎ…ች ዜግነታቸውን ወይም መኖሪያቸውን የሚያመለክት አጠቃላይ የሆነ የጋራ  ቦታና ስም ስለሌላቸው መኖሪያ ቦታቸውን ይገልጥ ዘንድ “ኦርማኒያ የሚለውን መጠሪያ ሰጥቻቸዋለሁ።” ብሏል (ዮሀን ክራፕፍ)

 ቅስ እንደላይኛው። (ሰረዝና ድምቀት የተጨመረ)

“ዮሀን ክራፕፍ” ማለት የኢትዮጵያን አንድነትና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ለመበተን የተላከ ለዛሬዎቹ ኦሮሞዎች ላቲን ፊደል ቀርፆ የሰጣቸው ጀርመናዊ ፕሮተስታንት ሚሺኔሪ ነው። የሸዋ ኦርቶዶክስ አምሐራዎች ስለተከራከሩት የሸዋ አምሐራዎችን “ቆሻሾች” ይላቸዋል። ኦነጎች አምሐራን የመጥላት አባዜ ከየት እንዳገኙት ምልክቱን እዩት።

የክራፕፍ ውጤቶች የሆኑት የዛሬ ዘመን ኦሮሞ ምሁራንም ከላይ የተጠቀሰውን ሲያጠናክሩት በአንደበታቸው እንዲህ ሲሉ ያረጋግጣሉ፡

<< ኦሮሙማ “ኦሮሞነት” ነው ኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው የተለየ የሚያደርገው የኦሮሞን ማንነትና አጠቃላይ የሆነ ባህላዊ፤ ማህበራዊ፤ ሃይማኖታዊ፤ ልሳናዊ፤ ታሪካዊ ግዛታዊና ስነ ልቦናዊ ባህርያቶችን አንድ አድርጎ የያዘ መገለጫ ነው። ኦሮሙማ ኦሮሞዎች እንደ ሕዝብ የሚኖሩበትን ማረጋገጫ የሚሰጥ ማንነት ነው።>>

<<የኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን የዐምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ ይታይ ነበር>> (The Journal of Oromo Studies  VOLUME 9, NUMBERS 1 AND 2, JULY 2002 P.73) (The Journal of Oromo Studies  VOLUME 1 NUMBERS 1 AND 2, Winter 1994 p.97) (ምንጭ ዐምሐራ! ሕብራዊ ማንነቱና ተግዳሮቱ- ባንተአምላክ  አያሌው - ገጽ 365-366)

እንግዲህ ክራፕፍ የፈለሰፈላቸው “የኦሮሙማ ትርጉም” እና ለመጻፊያ የፈጠረላቸው የላቲን ፊደል እንዲሁም እንዲከተሉት ያስተማራቸው የጀርመን ፕሮተስታንት ባሕሪዎች የተቀኙት ኢትዮጵያን እንዲጠሉ የተቀረጸ አጀንዳ ስለነበር ኢትዮጵያዊነትን አብዝተው ይገፉታል፤ ኢትዮጵያዊ ፊደል የኦሮሞነት ጠላት አድርገው ይመለከቱታል። በሜንጫ የምትቋቋም “የኦሮሚያ እስላማዊ ሀገር” እንድትኖርም በግሃድ ይሰብካሉ። <<ከሩዋንዳ እስከ ኦሮሚያ>> የታየው የዘር ዕልቂት “የሰለፊ እስልምና” እና “በ18ኛው ክ/ዘመን ወደ አፍሪካ የመጡ የጀርመን የፕሮተስታንትና የካቶሊክ ሚሺኔሪዎች የተቀነቀነ” እንደሆነ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው ይገልጻል።

  አሁን ያለው ኦነጋዊው አብይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት የተቃኘው በዛው መስመር  በመሆኑ እራሱና  የሾማቸው የባለሥላጣናቶች ንግግር ኦሮሙማ ምን ማለት እንደሆነ ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው በመጽሐፋቸው   ለታሪክ ተዘግቦ እንዲቆይ  የዘገቡልንን እነሆ ለናንተም ይጠቅማልና እንመልከት፡

በመሪያቸው በአብይ አሕመድ ንግግር እንጀምር፡እነሆ፦

1ኛ- “ትናንት ያዋረደንን አዋርደነዋል፤ ትናንትና አትወጡም አትገቡም ብሎ አጥር ያጠረብን ዛሬ ወጥቶ መግባት ከእኛ ፍቃድ ውጭ አይችልም” (አብይ አሕመድ)

2ኛ- “ ሰው እየሞተ ችግኝ አይተከልም የሚለን ጠላት ነው፡ እንዳትሰሙት፡ ሰው እየሞተ የሞተበት ቦታ ችግኝ እንተክላለን ቢያንስ አስከሬኑ ጥላ እንዲኖሮው” (አብይ አሕመድ)

3ኛ- “ታስሮ ጀግና ለመሆን የሚሯሯጥ ጋዜጠኛ አለ….፡ ምርጫ ሳታሸንፍ ባለአደራ ምናምን የሚባል ጨዋታ ውስጥ የምትገባ ከሆነ ግልጽ ጦርነት ውስጥ እንገባለን። ይህ መታወቅ አለበት”(አብይ አሕመድ)

4ኛ- “አዲስ አበባ ውስጥ ያለው ማሕበረሰብ ኦሮሞ ጠል ነው” (አብይ አሕመድ)

5ኛ- “ሰዎቹ (ዐምሐራዎች) የሚችሉት ሦስት ነገር ብቻ ነው፦ “ጩኸት፤ልቅሶባ ስም-ማጥፋት” ለአልቃሾች ብትችሉ መሀረብ (ሶፍት) ማቀበል እንጂ ምን አስጨነቃችሁ? ያልቅሱ ተዋቸው። እኔ የሚያስጨንቀኝ ዝም ሲሉ፤ ሳይነፋረቁ ሲቀሩ ነው።ዝም አሉ ማለት  እኔ እነሱን እያስደሰትኩ እንደሆነይሰማኛል…!” (ሽመልስ አብዲሳ)

6ኛ- ኦሮሞ ሕዝብ እዚህ ነበር የተሰበረው፡ እዚህ ነበር መዋረድ የጀመረው፡ እዚህ ነበር ቅስሙ የተሰበረው፤ ‘ቱፋ ሙናን’፤ የዚያን ዘመን ታጋዮች የነፍጠኛ ሥርዓት እዚህ ነበር የሰባበራቸው። ዛሬ የሰበረንን ሰብረን፤ ከመሠረቱ ነቅለን፤ኦሮሞ በተዋረደበት ቦታ ተከብሮ ይገኛል።” (ሽመልስ አብዲሳ)

7ኛ- አዲስ አበባ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሠፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት በዋቆ ጉቱ እና በታደሠ ብሩ ስም ትምህርት ቤቶች ከፍተን የሚማርልን ተማሪ አጣን። ስለዚህ ተማሪ ከቡራዩ እየጫንን እናመጣ ነበር፡፤ አምና የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዐብይ በሰጡት ውሳኔ መሠረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች አስጀመርን። ከ 5700 በላይ መምህራን አዲስ አበባ ውስጥ አስገብተናል።” (ሽመልስ አብዲሳ)

8ኛ- ዓባይን ተሻግረን ባሕርዳር ድረስ ሄደን ግማሹን Convince ገሚሱን Confuse አደርገን ቁማር ቆምረን ቁማሩን በልተን ተሳክቶልን ተመልሰናል። እንዴት አደናብራችኋቸው ነው የምትሉት? ምን አገባችሁ?” (ሽመልስ አብዲሳ)

9ኛ- አዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን ህዳሴ ግድቡን ኦሮሞ መቆጣጠር እንዲችል ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ ኦረሞዎችን በማስፈር ዲሞግራፊውን እየቀየረ ነው! ክልሉ ውስጥ ኦሮሞ 37% ደርሷል። (ሽመልስ አብዲሳ)

10ኛ- ብልጽግናን የሠራነው ለእኛ እንዲመች  አድርገን ነው። ብልጽግና የኦሮሞ ነው። ብልጽግና ኦሮሞ ወይንም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው የሚመራው።… አምስት ቋንቋ የመረጥነው ለእነሱ አስበን አይደለም። ለኦሮሞዎች ብለን ነው። አማርኛ እየደከመ ነው፡ እየቀነሰ ነው። ኦሮምኛ ከአማርኛ በላይ እየተነገረ ነው።(ሽመልስ አብዲሳ)

11ኛ- “ለአዲስ አበባ ብዙ መፍትሔ አለ። አንደኛው በሕገወጥ ሆነ በሕጋዊ መንገድ ሰው ማስገባት ነው። ሌላኛው አዲስ አበባን የማትጠቅም ከተማ ማድረግ ነው። አራት አምስት የፌደራል ከተማ እንመሰርታለን። ድንበር የመካለያ አዋጅ ወጥቷል። ለስሙ ነው እንጂ ይጸድቃል። (ሽመልስ አብዲሳ)

12ኛ- የኦሮሞ ትግል ማዕከል አዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ብቻ ናት” (ሽመልስ አብዲሳ)

13ኛ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት። አደስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆንዋን ተከትሎ ኦሮሚያ መዝሙር በት/ቤቶች መሰጠቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።” (ሽመልስ አብዲሳ)

14ኛ- በቄሮ ትግል ፌስታሉን ይዞ ከእስር ወጥቶ ሲያበቃ ዛሬ “ባለአደራ መንግሥት ብሎ ራሱን መሾም አልያም ባለተራ መንግሥት ብሎ ለውጥን ማጣጣል በምንም ስሌት ተቀባይነት የለውም። መንግሥታችንን ለመፈታተን ባለተራ ባለአደራ እያለ የሚያላዝነው ወደ ትክክለኛ መስመር ለመመለስ እንሰራለን።” (አዲሱ አረጋ ቂጢሳ)

15ኛ- “እኔ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ ጠዋትንም ማታም ሻይ አብረን ስንጠጣ፤ የኦሮሞ ጥቅም አዲስ አበባ ውስጥ ለማስጠበቅ፤ በተለይም ካሁን ቀደም ተገፍቶ ከአዲስ አበባ ሲወጣ የነበረውን አርሶ አደርና ኦሮሞነት ከከተማ ውጭ እንዳይሆን ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ…ነው” (አዲሱ አረጋ ቂጢሳ)

16ኛ- ከሶማሌ የተፈናቀሉትን አምስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች  በአዲስ አበባ ዙርያ እና  በአዲስ አበባ ውስጥ አስፍረናል። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስድስት ሺሕ ሰዎችን አስገብተናል።”  (ለማ መገርሳ)

17ኛ- አዲስ አበባ  የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት። አዲስ አበባ ኦሮሚያ  ዋና ከተማ መሆንዋን ተከትሎ ኦሮሚያ መዝሙር መስጠቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።” (አበበች አደኔ)

እነዚህና የመሳሰሉ ሌሎች እዚህ ያልተጠቀሱ ንግግሮች <<የ Ormania መርህ>> የተከተሉ ያልተሸፋፈኑ ጉልህ የሆኑ ኦሮሙማዊ የአጀንዳ አፈጻ ጸም ምልክታዊ ንግግሮች ናቸው

ከዚህ አንጻር የ6 አመቱ የኦሮሙማ ፕሮጀክትና አንደበቶችን ስንመረምር በአምሐራ ሕዝብ ላይ የተካሄደው የዘር ማጽዳት ዘመቻ ስንመለከት እጅግ አክራሪ የተባሉት “ኦነጎች” እና “የሰለፊ ኦሮሙማ እስላሞች” በሕልማቸው ይሆናል ብለው ያልጠበቁት ያለ አብይ አሕመድ እገዛ የመንግሥትን መንበር ተጠቅሞ ለኦሮሙማ ፕሮጀክት (ግብ) መሳካትና መፋጠን ከአብይ አሕመድና ድርጅቱ በላይ የሚተባበራቸው ወንጀለኛ ቡድን አያገኙም።

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay


Wednesday, November 27, 2024

ዘመነን የነሸጠው ኢዲ አሚንነት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/27/24

ዘመነን የነሸጠው ኢዲ አሚንነት

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/27/2


ብዙ አመታት በፖለቲካው ውስጥ ቆይቻለሁ። የሚሆነውን እና የማይሆነውን የማየት ችሎታ ከተጋፈጥኩት ልምድ ማየት ችያለሁ። ብታምኑኝ ባታምኑኝም ዘመነ ካሴ የተባለ ካቅሙ በለይ የሚወጠር <<አምባገነን ልጅ>> በትአምር ባሕሪው ካልተወና ለሰራው ወንጀል ተጠያቂ ሆኖ ይቅርታ ጠይቆ ካልተመለሰ አምሐራን ነፃ ያወጣል ብላችሁ ከመደደም አሁኑኑ ሁለት ጊዜ አስቡበት።

ተከታዮቹ ከሚከተለው አምባገነንነት ባሕሪና ሴራው  እንዲታቀብ   ዘዴ ካላበጁለት የአማራን ማሕበረሰብ ትግል መጨረሻ ላይ  ያበላሸዋል።

አምባገነንነትን ያጠኑ ተንታኞች እንዲህ ይላሉ። የአምባገነኖች ፍልስፍና ምንድን ነው? አምባገነኑ ተገዢዎቹን ለማስገበር ወደ ም የግድ  በቂመንጃና የመሪነት ሥልጣን መቆጣጠር አለበት። ምክንያቱም ሥልጣን ካልያዘ የሚታዘዝለትና የሚያስጨንቀው ተከታይ አይኖሮውምና ነው።

አጉራ ዘለሉ ሥልጣን ላይ ቆይቶ ያደረጋቸው ወንጀሎችም አንድ ቀን እንደሚያስጠይቁት ስለሚያውቅ ሥልጣኑን እንደ መሠረታው የሕልውናው ገመድ “አጥብቆ ሳይለቅ” እስከ ቻለ ድረስ ማቆየት አለበት። ይህ የሁሉም አጉራ ዘለል ሰዎች ዓለም አቀፍ ባሕሪ ነው።

ነገር ግን በማንኛውም ሁኔታ የጫካ ንጉሦች  “ዘውድ ባይጭኑም” አድራጊና ፈጠሪ በመሆን የንጉሥን ባሕርይ ማሳየት የባሕሪው ተጽዕኖ ያስገድደዋልና እንደ ንጉሥነት ይንሽጠዋል። ዘመነ ካሴም እየነሸጠው ያለው ይህንኑ ንሸጣ ነው።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ውስጥ የምናየው አስገራሚና አሳፋሪ የአመራር ባሕሪም ይህ “ክሊክ” የሚመራው ቡድን ነው።

የአምሐራዎች ትግል እንደዚህ መበለሻሸቱ እጅግ አስገራሚና ፈረንጆች “ኦድ” የሚሉት አዲስ ክስተት ነው። እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የአምሐራ ትግል መቃናትና መበላሸት ስለሚመለከተኝ እኔ የምመከራችሁ <<ትግላችሁ ከመበላሸቱ በፊት አስቀድሞ አምባገነንነትን እና የሥልጣን ጥማትን ማራቅና ለትግሉ ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅባችሗል።

አሁን እያየነው ያለው ግን ይህ “ክሊክ” በልጅነት ድንፋታ የሚጓዝ በጣም አደገኛ ጎረምሳ  <<ኢዲ አሚን ዳዳ”” መሳይ  ጎጃም ውስጥ ድንገት መከሰቱ  የሚገርም ነው።

ከላይ የሚታዩት በዘመነ ካሴ የታፈኑ ሰለባዎች (ቪክቲምስ) ማለትም 

ዶ/ር አንድአላማው እና ጋዜጠኛ ወግደረስ በኢዲ አሚኑ ዘመነ ካሴ ንጉሣዊ አፈና ጠረዛ ላይ አስቀምጦ እንዲከተሉት ሲያሸብራቸው ይታያል። ይህ የአፈና ጉድ በአምሐራ ትግል ውስጥ ይከሰታል ብየ ገምቼ አላወቅም።

አስገራሚው ግን ይህንን አጉራ ዘለልነት የሚወዱለት ነፃ አገር ውስጥ እየኖሩ “ቀጥል” የሚሉ “ታምቡር” የሚመቱለት “ኩሊዎች” አሉት። አምሐራ ሆይ መች ይሆን በራስህ ልጆችም አጉራ ዘለልነት ጭምር ሳትደናገጥ ሰትታፈን ነፃ የምትወጣው? የሚለው አንገብጋቢ የአሁናዊ ጥያቄ ነው። አግራሚም አርማሚም ትዕይንት ነው! Take my word, this fellow is ethno-extremist and real Evil!!

ጌታቸው ረዳ

Tuesday, November 26, 2024

በታላቁ አንበሳ የተነሳው ጅብ ጎንደሬው መሳፍንት ትችት በጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/26/24

 

በታላቁ አንበሳ የተነሳው ጅብ

ጎንደሬው መሳፍንት ተስፉ

ትችት በጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/26/24

ይህ እስቲ እንደመግቢያ እንመልከት

1ኛ-<<እስላም የሆነ ኢትዮጵያን ማስተዳደር የለበትም! በባሕላችን ያልነበረ! >>

 2ኛ-<<አምሐራ ምድር ውስጥ ( ያሉት ትግሬዎች ተለቃቅመው ወደ አገራችው ይውጡልን! ጎጃም ውስጥ በሁሉም ቦታ አሉ ሄደው ከነሱ ጋር ይግጠሙን

 <<ትግራይ “ምናችን አይደለችም” እንጨብጣታለን! ትግራይን ደግሞ! አይ!>>

ሲል ጎንደሬው ተሰብሳቢ ይደገም! ይደገም! ሲል ዘረኛነትን በጭብጨባና በጩኸት አፀደቀለት! የሚገርም ነው። ምኔም አይደለም የምትለው ሕዝብ መጨረሻው ዕጣ ፈንታው ምንድ ነው የሚሆነው? መባረር፤መገደል! ኦሮሚያ በተባለው አኬልዳማ ምድርም እንደዚሁ “አምሐራ ምናችን አይደለም” ስለተባለ ነው ደም እየፈሰሰ እየተፈናቀለ ያለው።አይደለምእንዴ? እንጨብጣታለን ሲል ምን ማለት ነው? መጨበጥ ማለት “በቅኝ ግዛት መያዝ፤ማብበርከክ፤ መቆጣጠር፤ማስጨነቅ…” ማለት ነው አደልም እንዴ? ከዚህ ወዲያ ዘረኝነት ከየት ይመጣል

  ያ ሁሉ ዘረኛነቱን ተረስቶለት ሲያበቃ ትናንት ደግሞ ኢንተርሃሜው “መሳፍንት ተስፉ” በታላቁ አምበሳ እስክንድር ላይ የስም ማጥፋት ሲቀሰቅስ ሰማሁት።

ይህ <<እስላም ጠሊታውና ትግሬ ጠሊታው” ሰው ታላቁ የሃይማኖት ዘርፍ የሆነው እስልምና እና አምሐራ ምድር የሚኖሩ ዘመዶቼ ተለቃቅመው እንዲገደሉ ወይንም ኑሮአቸው ተመሰቃቅሎ እንዲጠረዙ’’ ለማወጅ ያልተሳቀቀ (ያልከበደው) ሰው የአንድ ታጋይ እስክንድር ነጋን  ስም ማጠልሸት የሚግርም ባይሆንም፤ ሴራው ግን ለምን እስክንድር ላይ ይህ ሁሉ መረባረብ አስፈለገ? የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ሰዎቹ ሌላ ስራ የላቸውም? ነው ወይንስ እነኚህ ማይሞች የወጡበት ዓላማ አያውቁትም?

አሁን አሁን ገና ሳስበው የእስክንድርና ኔልሰን ማንዴላ የሕይት ታሪክና የትግል ተሞክሮአቸው የደረሰባቸው የውስጥ ምቀኛ ስም ማጠልሸት አንድ ሆኖ አገኘሁት።

ማንዴላ ለሕዝቡ ነጻነት ሲል የሚወዳት ባለቤቱና ልጆቹን ትቶ ነፃነትን መምረጥ ለዘመናት እስር በመግባት ተሰቃይቶ ነፃነትን አስገኘ። በኔልሰን ማንዴላ ላይ ያኔም ሆነ ዛሬ ከሞተ በላም ስሙን በማጠልሸት የተጠመዱ ታዋቂ የሕዝብ መሪዎች አሉ። አንዱ “ማሌማ” የተባለው “Freedom of Economic Freedom Fighters/EFF/” መሪ ነው። ይህ ወጣት ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ሲሆን የማንዴላ ስም አጥፊ እና የባለቤቱ “ዊኒ ማንዴላ” ፖለቲካ ደጋፊ ሆኖ ማንዴላ “ከነጮች ጋር ተመሳጥሮ ለነጮች የሸጠን አሻጥረኛ ነው” እያለ ልክ እስክንድር ነጋ ላይ በፋኖ ጎበዝ አለቃዎች እየደረሰበት ያለው የማያባራ ስም የማጥፋት ዘመቻ የተደረገበት የነፃነት ታጋይ ነበር።

እስክንድር ነጋም እየደረሰበት ያለው ተመሳሳይ ዘመቻ ነው። እስክንድር የትውልድ ሐረጉ ከሸዋ (የቆየ ቃለ መጠይቁን አድምጡ) የሆነ ከፍተኛ ዘመናዊ ትምሕርት ካጠናቀቁ ሁለት ምሁራን እናት እና አባት የተገኘ የሃብታም ልጅ ነው። እስክንድር የተማረው ዋሺነግተን ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ ውስጥ ነው። የፖለቲካል ሳይንስና ኢኮኖሚከስ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በላ ወያኔ ሲገባ ወደ ሃገር በመሄድ ዘረኛው የትሕነግ ሥርዓት ለመታገል በ1985 ዓ.ም የመጀመሪያ ጋዜጣው “ኢትዮጵስ”  የተባለውን በማሳተም የተጨቆኑ ደምጾች ልሳን በመሆን ሥርዓቱን መታገልና ሕዝብን ማንቃት ጀመረ። ከዚያም የትሕነግ የስለላ መርበቦች እንዲዘጋ አደረጉት፤ ቀጥሎም እኔ በስፋት ሳነባቸው የነበሩትን፤ “ሳተናው ምኒሊክ እስኳል.. ወዘተ” የመሳሰሉ ጋዜጦችን በማሳተም ዘረኛውን ሥርዓት ሲታገል ቆይቶ በመጨረሻ ሁሉም ጋዜጦቹ ታገዱ።

ከዚያም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲበረታ ያንን ለማስቆም 9 ጊዜ እስርቤት ገብቶ ተደብድቦ ስቃዩን አይቶ ረዢም አመታት ሲፈታ ሲታሰር ህይወቱን ለኢትዮጵያ የሰጠ የነጻነት ታጋይ ነው። በዚህ ሥራው ዓለም መስክሮለት ሽልማት ተሰጥቶታል።

በተከታታይ በ30 አመት ውስጥ ኢትዮጵያን በዘረኛ ፖሊሲ የገዙ ሁለቱ ዘረኛ ሥርዓቶች አምሐራን ግምባር ቀደም የጥቃት ሰለባ መሆኑን በመቀጠሉ ባጠቃላይ የሀገሪቱ ሕዝብና አምሐራ ነፃ ለማውጣት ግምባር ቀደም ፖለቲከኛ ሆኖ የተለያዩ የትግል ስልቶችን በመቀየስ እስካሁን ድረስ ማንም ኢትዮጵያዊ የነፃነት ታጋይ ያላደረገው አስገራሚ ሕዝብን አሰባስቦ ለትግል እንዲነሳሳ ሥርዓቶችን ያንቀጠቀጠና “ፊት ለፊት ሳይሸሽ ሳይደነግጥ” የተጋፈጠ ልዩ የሆነ ትግል በማካሄድ የኢትዮጵያዊያን ቀልብና የሥርዓቱን መሪዎች ቀልብ  ሳይቀር የሳበ ትግል ያቀጣጠለ ፤እነ ጃዋር መሐመድ ሳይቀሩ የተገረሙበት ትግል ያካሄደ አስገራሚ የሆነ ሰው ሲሆን ፤ ለነፃነት የከፈለው የሕይወት ፤ የኑሮና የአካል መስዋዕት በብዕር ለመክተብ በመጽሐፍ መልክ ይጠይቃል።

ለነፃነት ሲሉ የሚወዳት ባለቤቱ እና እራሱ ለተደጋጋሚ ዕስር ተዳርገው በወቅቱ ነብሰ ጡር የነበረቺው የነፃነት ታጋይና ጋዜጠኛ ባለቤቱ “እስከዳር” እስርቤት ውስጥ ሆና ብቸኛውን ወንድ ልጅ ተገቢውን ሕክምና ተነፍጋ ያልተሟላ ሕክምና ሰታገኝ በመከራ ልጃቸውን ወለደች። አፍሪካ ውስጥ በቅርቡ እንዲህ ያለ የታጋይ ቤተሰብ የትግል ታሪክ እጅግ የሚገርም የማንዴላና የእስክንድር ተመሳሳይነት የታየው አዲስ አበባና ጆሃንስ በርግ ውስጥ ነው።

30 አመት ሙሉ ባሕሉን የጣለው አስቸጋሪው የአዲስ አበባው ወጣት ኢትዮጵያዊ ባሕል እንዲከተልና እራሱን እና ቤተሰቡን ከቅኝ አገዛዝና ዘረኛ ሥርዓት ነጻ ለመውጣት በፖለቲካው እንዲሳተፍ አደገኛው ሥርዓት አስፈሪ ቢላዋ እየሳለበትና እየደበደበውም ቢሆን ታላቁ እስክንድር ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል በኢትዮጵያ የፖለቲከኞች ታሪክ የመጀመሪያ ነው

እስክንድር አዲስ አበባም ሆኖ  ጫካም ገብቶ ተቀናቃኝ አላጣም። ተቀናቃኞቹ ደግሞ የሥልጣን ሕልማቸው ሊነጥቃቸው እንደመጣ በግልጽ ጦርነት የሚያውጁበት ለሕዝብ እንታገላለን የሚሉ አስመሳይ ነውረኞች ሲዝቱበት ተመሳሳይ ታሪክና የስም ማጠልሸት ተዘግቦ ያለ ነው።

አንዲት ትንሽ ምሳሌ ልጥቀስ

አዲስ አባባ ውስጥ እያለ በአብይ አሕመድና በብርሃኑ ነጋ የተቃጣበትን ማስፈራሪያና ስም ማጠልሸትን እንመለከታለን። ከዚያም ጫካ ውስጥ ፋኖ ከተቀላቃለም  ተቀናቃኞቹን ተመሳሳይ ስም የማጠልሸትና የመግደል ዘመቻ እንመልከት

በአዲስ አባባ እንጀምር

የዘመነ ካሴ  ሁለተና መሪው የነበረው ብርሃኑ ነጋ ፤ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ጸረ አማራ ከሆነው ኤም ኤንከተባለው የተገንጣይ ኦሮሞ የኦነጎች የፕሮፓጋንዳ ማሰራጪያ አውታር ላይ ቀርቦ ባደረገው ቃለ ምልልስ ስለ አብይ እና አዲስ አበባ (አስክንደር ነጋ ባለ አደራ) ጉዳይ ሲመልስ እንዲህ ይላል።

አኔ አብይን ሙሉ ለሙሉ አምነዋለሁ!!!” ካለ በሗላ፤ታከለ ኡማም ቢሆን (እንደ አብይ አሕመድ) አሸጋጋሪ ነው” “በሕግም በምንምየሌለባላደራ ምናምን የሚባል ለኔ ብዙም እንትን አያደርገኝም……ታከለም ሆነ አብይ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አሻጋጋሪዎቻችን ናቸው ለዚህ ነው ወደ እዚያ ስለሚያሻግሩን እንርዳቸው አብረን እንሂድ የምለው።”>>

ሲል የመነ ካሴ የቀድሞ መሪ ብርሃኑ ነጋ እስክንድር ላይ የቅናት፤ የራ፤ ጠልፎ የመጣል፤ የማሳሰር ፤ስም ማጠልሸት ሲያደርግ ነበር። ብርሃኑ እና አብይ “ምናምን” የሚል ቃል እየተዋዋሱ እንዴት እንደሚጠቀሙ ታያለችሁ፡

ይቀጥልና አብይ አሕመድም

<<ባለ አደራ ነኝ ምናምን ከሚሉ ጋር ግልጽ ጦርነት እንገባለን>> አብይ አሕመድ እስክንድር ነጋ ላይ የመግደልና ስም የማጥፋት እንዲሁም ማስፈራራት ዘመቻ የዛተበት።

እንደገና ጫካ ውስጥ ከፋኖ ተብየው ሥልጣን የጠማው አደገኛው አዲሱ <<የጎጃሙ ”ፖል ፖት ክመር ሩዥ’’ ዘመነ ካሴ>> እስክንድር ላይ ያሰራጨው ታሪክ የዘገበውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ሰዎች ተሎ የመርሳት አባዜ ስላለን ይህንን ድጋሚ ላስታውሳችሁና መሳፍንት ወደ ተባለው ዘረኛ እመለሳለሁ፡

ይኼው እንመልከት፦ ታስታውሱ እንደሆን የጎጃሙ ፖልፖት ዘመነ ካሴ እስክንድር ላይ የዛተው የቃላት ስም ማጥፋት ብቻ ሳይሆን እንደሚገድለው ወይንም እንደሚያስገድለው ነው። የሁለቱ ልዩነት በፖልፖቱ አባባል መሠረት ልዩነታቸው <<የርዕዮተ ዓለም  ግጭት ነው>> ሲል  ዘመነ ካሴ መግለጹን ታስታውሳላችሁ። የርዕዮተ ዓለም  ግጭት ያላቸው ድርጅቶች እና መሪዎች ደግሞ የሚፈታቸው “ጦርነትና መገዳደል ነው” ስለዚህ ዘመነ ካሴ እስክንድርን (ከቻለ) እራሱ ወይንም በተዘዋዋሪ ለማስገደል ዝቷል። እስክንድር ከዚያ ሁሉ ስቃይና እስራት ወጥቶ ፤ ዛሬ ደግሞ በጎበዝ አለቃዎች በአምሐራ ደም ሥልጣን የሚጠማቸው እንደ ዘመነ ካሴ የመሳሰሉ “የአምሐራ የነጻነት አኩሪ ምልክት የሆኑትን እንደ እነ ታላቁ እስክንድር ነጋን” ለግድያ ሲፈለግ ከመገርምም አልፎ እኛ ትግሬዎች “መርመም” የምንለው አስገራሚ ደረጃ የሚያደርስ ነው።

ላስታውሳችሁ ቃል በቃል፤እንዲህ ያለውን;

<<(ግጭታችን) የዓለሙና የከበደ የሁለት ሰዎች ግጭት አይደለም።ይህ የርዕዮተ ዓለም  ግጭት ነው፡፡ የሌባና ፖሊስ ትንቅንቅ ነው። የትውልዱን ትግልና ድል ሊሰርቁ ጭምብል ለብሰው ማጅራት መምቻ ቆመጥ ታጥቀው በጠራራ ፀሐይ በመጡ ሌቦች  የትውልዱን ደምና አብዮት ሰለሚጠብቁ ፖሊሶች መካከል ያለ ግብግብ ነው።በሕልሜ የመጡብኝ አሁን ነው”፡፡…. >> ማለቱን እናስታውሳለን።

“በሕልሜ የመጡብኝ አሁን ነው” ሲል፡፡ በሌላ ቀን ይህንን ሕልሙ ሳያፍር ሳይደብቅ በግልጽ የነገረንን እደገና በተቀራራቢ ላስታውሳቸሁ፤

 <<እኔ የነጋሽና አንጋሽ ዘር ስለሆንኩ ገና ከዘራችን/ ስንፈጠር ከመለዘራችን (ዲ ኤን ኤ) የመሪነት ቦታ የታደልን ፤ ከእናቴ ማህጸን ውስጥ እያለሁ የመሪነት ቦታ ሳልም የነበርኩኝ ባለሕልም ነኝ>>

ሲል ሲመኘው የነበረው የመሪነት ሕልም ማግኘት እስክንድር ነጋ ስለተመረጠ ያንን ሕልም መራጮቹ ሳይሆኑ “እስክንድር እራሱ እንደነጠቀው” አስመስሎ እስክንድርን የዘመነ ካሴን ሥልጣን ሕልም ነጣቂ አድርጎ በመፈረጅ ከርዕዮተ  ዓለም ልዩነት አልፎ የሥልጣን ሕልሜን ነጠቀኝ በሚል ነው ይህ ሁሉ ዛቻ እና ስም ማጥፋት ውስጥ የከተተው።

ይህ ሁሉ እስክንድር ላይ ጉትጎታ የሚነግረን ነገር ዘመነ እና ቡድኑ የፖለቲካ ምጥቀታቸውና ልምዳቸው “ኤለመንታሪ” ስለሆኑ፤ እስክንድር ጫካ ላይ መገኘት የበታች ስሜት ስለተሰማቸው አጉራዘለል ሕልማቸው በዚህ በረ ትዕግስተኛ ሰው እንደተሸማቀቁ ግልጽ ነው። እስክድርን ጎስጉሰው፤ ጎስጉሰው ስም አጥፍተው ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ በመጨረሻ ምናልባትም  ትቷቸው ይሄድ ይሆን የሚል ተስፋ በመጣል ከትግሉ እንዲወጣ እያደረጉ ያሉት “ሴራ” እንደሆነ ግልጽ ነው።

ምናልባት ተስፋ ቆርጦ ትግሉን ቢተው ይሄው አላልናችሁም ወይ ለማለት እንዲመቸው የጎጃሙ “ፖልፖት” እንዲህ ያለውን ላታውሳችሁ።

 <<እሰከንድር ሲያምሰን ከርሞ ነገ ሽሉክ ይላል ያኔ እንተዛዘባለን።>> ያለውን አስታውሱ። አያችሁ የስም ማጥፋት ሴራው? <<እሰከንድር ሲያምሰን ከርሞ ነገ ሽሉክ ይላል ያኔ እንተዛዘባለን።>> የሚለው የምኞትና የተንኮል “ኮንሰፒራሲ” በግልጽ ማየት ትችላላችሁ።

እስክንድር ላይ ብቻ አይደለም “ፖለፖቱ ዘመነ” ዘመቻው ያጧጣፈው። በቅርብ የራሱ ወዳጁም ጭምር ላይ ነው። እንዲህ ሲል፡

 <<ወንድምን መታዘብ ትልቅ ሕመም አለው፡፡አንዳንድ ወንድሞቻችን በጨለማ ሄዱ አዝነናል፡፡>>

እያለ የሚለው የሄሊኮፕተር አብራሪው ሲታሰር ሲፈታ አብሮ የታሰረና የተሰቃየ ፤ ሲደበቅ አበሮት የተደበቀ ፤ የቅርብ መስጢር አማካሪውና ጓዱ የነበረው የዘመነ ቃል አቀባይ የማርሸት ጸሃየ የእናት እህት ልጅ ነው የሚባልለት <<ካፕቴን ማስረሻ ሰጤን>> ነው፡፡ ጎጃም ውስጥ የራሱን ፋኖ ያደራጀ ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ ዘመነን አልመርጥም ብሎ እስክንድርን ለመሪነት ድመጽ በመሰጠቱ ነው፡፡ (ወንድሞቻችን ከዱን የሚለው ኡኡታው)፡፡

በዛው  እወጃው ብዙ ነገር ታስታውሳላችሁ። “እኛና እነሱ”፤ “እኔ እና እሱ” የሚሉ ቃላቶች ይጠቀማል። አገው ነው እያሉ የሚያሙት ዘመነ ካሴ ተመልሶ እስክንድር ላይ <<እኔ ንጹህ አማራ እስክንድር ግን አማራ መስሎ ጭምብል በመልበስ የአማራዎችን የኛን የንጹሃን አማራዎችን ትግል  ለመጥለፍ የተቀላቀለን አማራ ያልሆነ ሰው ነው።>> ሲል የፋሺስቶች ፍረጃ ውስጥ መግባቱንም ታስታውሳለችሁ፡፡

ይህ ደግሞ መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ ሲሆን እስክንድር ግን አማራ ሰላልሆነ ጭምብል በመልበስ መነሻው አማራ ቢሆንም መዳረሻየ ግን ኢትዮጵያ ናት ሲል “የርእዮተ አለም አመለካከት ልዩነት አለን” እያለ የገለጸው ተመሳሳይነቱ ፡ልክ እኛ ወያኔ የምንቃወም መዳረሻችንና መነሻችን ኢትዮጰያ ስንል የነበርን ትግሬዎች “ሸዋውያን ተጋሩ” የሸዋ ትግሬዎች እንደሚሉን ሁሉ ፤ የጽንፈኛ ፋሺስት ብሔረተኛነት አቀንቃኙ ዘመነ ደግሞ እስክንድር አማራ ሳይሆን አማራ መስሎ የአማራነት ጭምብል የለበሰ “የኢትዮጵያ አማራ” ማለቱ ነው (የኛ ያልሆነ ፤ ጭምብል የለበሰ “ጸጉረ ለወጥ”) ሲል፡፡የእብደቱና የብልግና ባሕሪው ማሳያ ብዙ ነው።

እራሱን የአማራ ሕዝብ ፖሊስ  አድርጎ ሲሾም እስክንድር ነጋ ደግሞ “ማጅራት መቺ  ሌባ” በማለት በጸያፍ ቃል ሲዘልፈው የነበረውንም ታስታውሳላችሁ፡፡

<<ፖልፖቱ ጎጃሜው>> እራሱን ጉልበተኛ ድመት (ዲገላ) እስክንድርን ደግሞ ደካማ ዓይጥ አድርጎ በመሳል “ትግሉ የአይጥና የድመት ነው (በፖሊሰና በማጅራት መቺ)” አሁንማ ተነቃቃን እኮ በማለት ደካማው እስክንድርን በ“ዲገላው ድመት” (በፖሊሱ ዘመነ ) ተይዞ እንደሚበላ/እንደሚዋጥ ተዝቶበታል፡፡

ይህ የመንደር አጉራ ዘለል ወጣት አንዲህ ያለ ባሕሪ ያገኘው ኤርትራ ውስጥ እያለ ብርሃኑ ነጋ ጋር ሲላላክ ነው። ዓላማውም በተቃውሞ ለመምጣት የሚዳዱ አዳዲሶች ካሉ ለማስደንገጥ ነው።

ይህ ሁሉ ሴራና የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያሳየው ፖለቲካ በጠመንጃ ብቻ የሚገራ የመሰላቸው የፖለቲካ ጥበብ ያልተላበሱ በሕገ አራዊት የሚመሩ እንደ እነ ዘመነ ካሴ የመሰሉ አደገኛ ታጣቂ ቡድኖች፡ እስክንደር ላይ ማሽካካታቸው አልበቃ ብሏቸው፤ አሁን ደግሞ ሰሞኑን መሳፍንት የተባለ ጎንደር ውስጥ የሚንቀሳቀስ አንድ ታጣቂ ቡድን እመራለሁ የሚል ሽማግሌ እስክንድር ላይ ሲጮህና የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቷል።

ወደ ዘመነ ካሴ አሽከርነት የገባው <<የአረጋዊነት ባሕሪ ያልተላበሰ>> ትንሽ ሰው። “እስክንድር ሊከፋፍልን መጣ፤ ከብልጽግና የባሰ ነው” ሲል አስገራሚ ድንቁርናው ሲተፋ በሚዲያ ሰማሁኝ።

እንደ ጅብ ተሰባስበው በአንበሳው እስክንድር ላይ እያስካኩት ያሉት ጅቦችም ሆኑ <<እስላም የሆነ ኢትዮጵያን ማስተዳደር የለበትም>><<አምሐራ ምድር ውስጥ ያሉት ትግሬዎች ተለቃቅመው ወደ አገራችው ይውጡልን>> በማለት የሚታወቀው የጎንደር ኢንተርሃሜው “ሁታዊው መሳፍንት” ንዲህ ያለ ቅሌት ውስጥ በመዘፈቅ የፈለገውን የጅብ ጩኸቱን ቢያስካካ በተግባር እንደሚታወቀው የጅቦች ማስካካትና ከበባ የአምበሳውን ቅስም ከቶውንም ተሰብሮ አያወቅምናእስክንድር ላይ መዝመት በእሳት መጫወትና የአምሐራውን ትግል እንዲበላሽ ማድረግ ስለሆነ ጅቦች ማስካካታችሁን በሥርዓቱ ላይ አትኩሩ!@! አምበሳው ግን በጅቦች ስካካት ደምብሮም አያውቅ!@!

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay

Friday, November 22, 2024

የወያኔዎች እና የኦነግ አብይ አሕመድ የ33 አመት ኢትዮጵያ ይህንን ትመስላለች! እንኳን እንኳን ቀረችብኝ! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/22/24

 

የወያኔዎች እና የኦነግ አብይ አሕመድ የ33 አመት ኢትዮጵያ ይህንን ትመስላለች! እንኳን እንኳን ቀረችብኝ!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/22/24

ባሕሉን በጣጥሰው አንዲህ ያለ አስደግጭና አሳፋሪ ማሕበረሰብ አፍርተው ኢትዮጵያን አሳደግን ሲሉን፤ ይህ ሕዝብ ታግለን ነፃ ብናወጣውስ የባሕል ወረራ የተፈጸመበት ማንቱን የረሳ እንዲህ ያለ ሕዝብ ያጋግማል ተብሎ ይታሰባል?! ጉዱ በመሻ ጽሑፌ ይቀርባል።

ይህ የባሕል ወረራ እንዲደረግብን የታቀደው በጣሊያን ወረራ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በ14ኛው በ16ኛው ፤ በ18ኘው በ19ኛው እና በመለስ ዜናዊ እና አብይ አሕመድ በገዝዋት ኢትዮጵያ የቀጠለ ነው።

ለምሳሌ  በትንሹ ራስ አሊ ዘመነ መንግሥት  በኛ አቆጣጠር በ1822 ወይንም 1821 ዓ.ም አካባቢ ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ነበር የተባለው የእንግሊዝ የታሪክ ምሁርና የፓርላማ አባል የነበረው “ሎርድ ቶማስ ባቢነግቶነ ማካውላይ” (Thomas Babington Macaulay)  ስለ ጉብኝቱ አስመልክቶ በፈረንጆች 1827 ዓ.ም (በኛው ዘመ አቆጣጠር ለፓርለማው ጉባኤ የተናገረው የማይረሳ አደገኛ ንግግሩ እያመረቀዘ መጥቶ በትግሬዎችና ኦሮሞ ፖለቲከኞች ማዳበሪያ አግኝቶ እነሆ ዛሬ በ33 አመት ውስጥ በቪዲዮው የምታዩት ማንንቱን ጥሎ የባሕል ወረራ የተፈጸመበት ማሕበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ ዐይኑን አፍጦ ለማየት በቅተናል።

 ቪዲዮውን ለማየት ከመሽቀዳደማችሁ በፊት እንዴት ንዲህ ሊከሰት እንደቻለ “ሎርድ ቶማስ ባቢነግቶነ ማካውላይ” (Thomas Babington Macaulay) ንግግር እነሆ፦

<< አፍሪካን ከጫፍ እስከጫፍ በስፋት የተዘረጋው ይህ ክ/ዓለም  ሁሉንም ተዘዋውሬ አይቻለሁ።  አንድም ሌባም ሆነ ለማኝ ሰው አላየሁም፤ በዚህች ሀገር (አትዮጵያ ማለቱ ነው) ያየሁት ሃብት እና እንደዚህ ያለ ከፍተኛ የሞራል እሴቶች ከቶውንም የትም አላየሁም ። እንደዚያ ያለ ማሕበረሰብ አከርካሪን ሰብሮ ለማስገበር መንፈሳዊ እና ባህላዊ ቅርሶቿ  በዘዴ እንዲሰበሩ ካለደርግን በስተቀር ይህችን ሀገር እንቆጣጠራታለን  ማለት ዘበት ነው። ይህንን ለማድረግ አሮጌውን እና ጥንታዊውን የትምህርት ስርዓቷንና  ባህሏን ሁሉ  በእንግሊዝ ባሕልና በአንግሊዛዊ የትምሕርት ስርዓት እንዲተካ ሀሳብ አቀርባለሁ ፣ ምክንያቱም አፍሪካውያን የውጭ ባሕል ሁሉ ስልጡን ነው ብለው እንዲያምኑ ከተደረገ የራሳቸው የሆነውን ባሕልና ትምሕርት ንቀው ከጣሉት ሌላው  ከራሳቸው የሚበልጥ ነው ብለው ስለሚቀበሉት፣ ለራሳቸው ያላቸውን ግምት በመቀነስ፣ የአፍ መፍቻ ባህላቸውንና ራሳቸው የሚገልጹበት ሃገራዊ ማንተቻውን  ሁሉ ያጣሉ። በዚያ ጊዜ  እኛ የምንፈልገውን ይሆናሉ፣ በእውነት የበታችና ተጨቋኝ የሆነ ህዝብ ይሆናሉ>>

እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 1835 የሎርድ ማካውላይ የእንግሊዝ ፓርላማ  ከተናገረው ጠቅለል ብሎ ላንባቢ በቀላሊ እንደገባው  አድርጌ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት። እንግዲህ በዚህ መልክ ኢትዮጵያ በ33 አመት ውስጥ ከጥንት ተያይዘው የመጡ ክቡር ባሕሎቻችን በጥበብ እንዲፈርሱ ከተደረጉ በኋላ ራሳችንን የምንገልጽባቸው ሃገራዊ ማንነተቻን በቸልተኛነት አስነጥቀን ወራሪዎች የሚፈልጉትን ሆነንላቸው። እነሆ ባስነዋሪ ባሕል ተዘፍቀናል። ይህንን ስዕለ ድምፅ እንድታዩና የ33 አመት ዕድገትን ሥልጣኔ ምን ውስጥ እንደዘፈቀን ይህንን እንድታዩ እጋብዛለሁ።  አሁን አሁን ሳየው እንኳን እንዲህ ያለቺው ኢትዮጵያ ሄዶ ማየት ቀረቺብኝ ብያለሁ !

ሴቶችን ጠልፈው ልጅ እያስወለዱ የተወለዱትን ልጆች ይሸጣሉ

https://youtu.be/iO4HZCT8Fno?si=KZhDJcS9NkElQgFp