Wednesday, October 30, 2024

ክፍል 3 የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬትና እውነታዎች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/30/24

 

ክፍል 3 የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬትና እውነታዎች

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 10/30/24

ወደ ዋናው ርዕስ ከመግብቴ በፊት ሚዲያ ተብየዎቹ ሚዛናዊ ያልሆኑ ባሕሪያቸው በፕሮፌሰሩ ብቻ ላይ ለይተው እንዴት አንደተንጫጩ ያሳዩት አድላዊ የትችት ሽፋን አንድ ነገር ልበል።

በበኩሌ ፕሮፌሱን በሚተችበት ጎን ተችቻለሁ። በሚመሰገንበትም እንዲሁ። አሁን በሚዲያው ላይ ሰሞኑን ያየሁት ግን እጅግ የሚገርም ዘረኛ አድላዊ እና ወገንተኛ የሚዲያ ሽፋን ነው። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ ሲናገረው የምንጮህ (እንዲያውም ታች ካሉት የትሬ ናዚዎች እኩል ንግግር አይደለም) አሉላ ሰለሞንና ቄስ ሰረቀብርሃን፤ ወዘተ የመሳሰሉ የትግሬ “ሐሰን ንጌዜዎች” ከአምሐራ ጋር የተዋለደ ትግሬ እንዲፋታ፤ ማንኛውም ትግሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፤ ከኢትዮጵያ ካቶሎክ፤ ከኢትዮጵያ ፕሮተስታንት ቤተጸሎቶች እንዳይጽልዩ ፡የአማራዎች ዋሻ ነው። ያ ዋሻ መፍረስ አለበት!! ብሎ  ሲያውጁ፡-

 ኢትዮጵያዊያን ምግብ ቤት አንዳትመገቡ መርዝ አድርገው እንዳይፈጅዋችሁ ፤ በመርዝ ተመርዛችሁ ከመሞት ለመዳን ከፈለጋችሁ መፍትሄው ትግሬዎች፤ ኤርትራኖች እና በአካባቢያችሁ ባሉት የኦሮሞ ንግድ ቤቶች/ቢዝነስ/ ካሉ ከነሱ ጋር ተገበያዩ። የሚለው የአሉላ ሰለሞን አዋጅ ፤ በተለይ ደግሞ ያቺ ልሙጥ ባንዴራ የሰቀሉ ወይንም በንግድ ቤቶቻቸው ውስጥ ካያችሁ እንዳትገበያዩ ሌላ ቀርቶ ቅመምም ጭምር እንዳትገዙ። ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችን አይወዱህም እና ባጭሩ ከነሱ እራስክን ነጥል። ወዘተ…ወዘተ……..>>  የሚል

 አደገኛ ንግግር ሲያሰራጭ እና የፋሺሰቱ የወያኔው ሚሊሺያው ቄስ “ሰረቀብርሃን” (ቄስ ካቡጋ) አብረው በአምሐራ ሕዝብ ላይ የጥላቻ ንግግር ሲያውጁ እንደ ርዕዮት ሚዲያ የመሳሰሉት ግን በፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘን ላይ ለመኮነን ልዩ ዝግጅት አዘጋጅተው ያሞጠሞጡበት ምላሳቸው የትግሬ “ካቡጋዎችና  ሐሰን ንጌዜዎችን”   ከማውገዝ ይልቅ እንደውም የፖለቲካና የሃይማኖት ተንታኞቻቸው አድርገው በተደጋጋሚ እየጋበዙ እስከዛሬ ድረስ እየቀረቡ ሲየወያይዋቸው አይተናል። ለምን በፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ላይ መረባረብ ተፈለገ?

የሚለው ላንባቢዎች ትዝብት እተውና በነገራችን ላይ “ካቡጋና ሐሰን ነገዜ” ማን እንደሆኑ ለማታውቁ ካቡጋ የሚባለው ሰውየ በሩዋንዳ ዋና ከተማ “ኪጋሊ ከተማ”  አር ቲ ኤል ኤም ተብሎ የሚታወቀው በቱትሲ ጭፍጨፋ ከፍተኛ ሚና የተጫወተ የራዲዮው ዋና ሃላፊ ሲሆን “ሐሰን ነገዜ” ደግሞ በቀረጸው ዘረኛ ሰነድ 35 አመት የተፈረደበት “ካንጉራ” የተባለ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የነበረ በመጽሔቱ ላይ “የሁቱ አስርቱ ትዕዛዛት” ተብሎ የሚታወቀው የቀረጸ ፤ ከቱትሲ ጋር የተጋቡ ሁቱዎች እንዲፋቱ ፤ግብይት እንዳያደርጉ ….የጥላቻ  ሰነድ  ያሳተመ ሁቱ ነው።

ፍርዱን ለናንተ ልተውና ወደ ርዕሴ ልግባ።

ባለፈው ሁለት ተከታታይ ትችቶች ስለ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ  “ዓለም አቀፍ የፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ” ተብሎ በሚጠራ የሚዲያ ውይይት ቀርቦ ስለ ልደቱ አያሌውና ስለ መሳሰሉ ፖለቲከኞች ከገንጣይ እና አስገንጣይ ቡድኖች ጋር ሁሌም እያደረገ ያለው የጋራ ውይይት ማድረጉን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን የሰጠው አስተያየት ተገቢ ሲሆን። በዛው ውይይቱም ተጓዳኝ የማይገቡ ብየ የፕሮፌሰሩ የማይጥም ንግግሮቹም አብሬ በክፍል 1 ስተች በሁለተኛው ክፍል ትችቴ  ደግሞ ሊናቁ የማንችላቸው እጅግ ጠቃሚ ክርክቹ ሕዝብ እንዲያውቃቸው አቅርቤአለሁ። ከፕሮፌሰሩ ንግግር የተደመጡ የቁጣ ንግግሮቹ  ምክንያት ተሳብቦ እውነታ ያለቸው ያቀረባቸው የታሪክ ፤ የፖለቲካዊና አሁናዊ አምሐራ ላይ እየደረሰ ያለው አድላዊ እና የዘር ጭፍጨፋ መታፈን እንደሌለባቸው ነው የዚህ ተከታታይ ትችቶቼ።

ስለዚህም በዚህ እንቀጥል፡

አንዳንዶቻችሁ አንደምታውቁት ይህ አብይ አሕመድ የሚመራው “መንግሥት” የኦነግ ኦረሙማ ሥርዓት ነው። ባጭር አገላለጽ <<ኦነጎች የሚመሩት ኦሮሞአዊ ሰርዓት ነው>> በሌላ መንገድ ኦሮማዊ ነው ስንል ብዙ ኦሮሞዎች (3/4ኛው- 95%) የሚደግፉት ርዕዮት የሚያራምድ ነው ማለት ነው። አብይ አሕመድ ኦነግ ነው። በሥሩ ያሉ የሾማቸው ቀጀላ መርዳሳ፤ እነ ደ/ር ዲማ ነገዎ፤ እና በጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አምሐራ ታወቀው ሌንጮ ባቲ (እኛ ኦሮሞዎች  ኢትዮጵያን ኦሮሞ አምሳያ እንደገና ቀርጸን ለ3000 አመት አንገዛችሗለን ብሎ የተናገረ፡ አሁን ዋሺግተን ከተማ የሚገኘው በአሜሪካ የአብይ አሕመድ ኤምባሲ የኦነግ አምባሳደር ተወካይ) እና ከንቲባ (የነበረች) ጫልቱ የምትባለዋ አደገኛ ኦነግ አባል (ከብዙ አመታት “ኦርቶዶክስ ታቦትን ሽንት ቤት ተጥሎ እንዲሰነብት” ያዘዘች) ፤ “የኦሮሞው ካቡጋ” የኦሮሚያ ክልል ፕረዚዳንት ሽመልስ አብዲሳአበበች አደኔታከለ ኡማብርሃኑ ጁላ ፤ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ይልማ መርዳሳ፤ ዲና ሙፍቲ - (የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ቃል አቀባይ የነበረና "ገዱ አንዳርጋቸው" ፓርላማ ውስጥ አማራን ትጥቅ ማስፈታትም ሆነ "በደል ስለ መፈጸሙ በመቃወም ለታሪክ የሚቀረጽ አስገራሚ ንግግር ሲያደረግ “ዲና ሙፍቲ” ለመሰል ኦነግ ፓርላማዎች በዓይኑ ጥቅሻ እያመላከተ "ገዱ አንዳርጋቸው" በክፉ እንዲታይ በካሜራ ተቀርጾ ለሕዝብ ተላልፎ ያነው ሌላው ኦነግ ነው) እንዲሁም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ከፍተኛ እና ዝቅተኛ በፍትሕ መ/ቤቶችና በፖሊስ ሰራዊት የተሰገሰጉ … ወዘተ… ወዘተ…. የመሳሰሉ  የኦነግ አባሎችና የሰልቃጩ የኦሮሙማ ፕሮጀክት አስፈጻሚ ለኦነግ ፖለቲካ ያደሩ ናቸው ስርዓቱን የሚመሩት።

 ከተጠቀሱት አንዱ ዛሬ በሚኒሰትር/በፓርላማ አባልነት ደረጃ ተሹሞ የሚገኝ “የኦነግ መሪ አንዱ” እና የመሳሰሉትን  ሰዎች በሚመለከት ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ አንዲህ ብሎ ነበር፡

“<< የዶ/ር ዲማ ነገዎ ንግግርና የእሱ ትንቢትና ምኞት ዛሬ ላይ እየተፈጸመ ስለ መሆኑ>> እንዲህ ሲል ያስታውሰናል፦

አቢይ አህመድ ሥልጣን ላይ እንደወጣ በሕገወጥ መንገድ አቶ ታከለ ኡማ የተባለ አንድ በዘረኝነት አስተሳሰብ የሰከረ የኦሮሙማን ፓለቲካ በቅጡ ሊያስፈጽም የሚችል የኦሮሞ ካድሬ በከንቲባነት ሾመ። ታከለ ኡማ ከተነሳ በኋላ ደግሞ የኦሮሙማው መንግሥት ወ/ሮ አዳነች አበቤ የተባለችውን የኦህዴድ ካድሬ ከንቲባ በማድረግ የአዲስ አበባን ከተማ የህዝብ ስብጥር ሥር ነቀል በሆነ መንገድ የመቀየር እቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ። እነዚህ ሁለት ከንቲባዎችና በስራቸው ያሰለፏቸው የኦሮሙማ ፋሽስታዊ ፓለቲካ አራማጆች ባለፉት አምስት ዓመታት የፈጸሟቸው ድርጊቶች፤ የተገበሯቸው ዘረኛ ፓሊሲዎች በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባሉ ከተሞችና ክፍለ ከተማዎች ዛሬም የቀጠለው የዘር የማጽዳት ድርጊት (በሱሉልታ፤ ሰበታ፤ አቃቂ፤ ቦሌ ቡልቡላ፤ ለገጣፎ፤ አሁን ደግሞ ሸገር ብለው በሰየሙት የአዲስ አበባ ክፍል ወዘተ) ከዚሁ የፋሽስታዊ አገዛዝ መሰረት ከሆነው የሶሻል ዳርዊኒስት አስተሳሰብ የሚነሳ ነው።

እነ ሀጂ ጀዋር መሃመድ ዓቢይ አህመድ ሥልጣን ላይ በወጣ ማግስት ሃሮምሳ ኦሮሚያ  (Resurgence of a Dominant Oromo Nationalism and Consciousness) በሚል ሥም በአዲስ አበባ ያሉትን የኦሮሞ ተወላጆች በዜግነት ሳይሆን በአዲስ የኦሮሞን የበላይነት፤ የኦሮሞን ልዕለ-ሰብዕና የሚሰብክ ፋሽስታዊ አስተሳሰብና አመለካከት በመቅረጽ (super-man status of Oromos) ያከናወኑት ሰፊ የሆነ የፓለቲካ ሥራ፤ ተስፋፊነትን፤ ድንበር-ገፊነትን፤ እብሪተኛናትን ጦረኛነትን የሚያበረታታ፤ የኦሮሞን ልዩ ጥቅምና የኦሮሞን የበላይነት የሚሰብክ ፋሽስታዊ የሆነ በሶሻል ዳርዊንዝም አስተሳሰብ የተቃኘ አደገኛና ጽንፈኛ እንቅስቃሴ ነበር። የአዲስ አበባ አካል የነበረን ሰፊ አካባቢ “ሸገር” በሚል ሥም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በማካተት አሁን ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጽዳት ድርጊት (እስካሁን 112000 ቤቶች ፈርሰዋል፤ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች (አማራዎች፤ ደቡቦች፤ ጉራጌዎች ወዘተ) መንገድ ላይ እንዲበተኑና ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። ናዝሬትና ደብረዘይትን በመሳሰሉ ከተሞችም ተመሳሳይ ማንነትን መሰረት ያደረገ የማፈናቀል ድርጊት በስፋት እየተፈጸመ ነው። የአዲስ አበባን ኦሮሞነት ለማረጋገጥ በፍጥነት እየተገነቡ ያሉት የኦሮሚያ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች ግንባታ፤ በከተማዋ ውስጥ ያሉትን የአስተዳደር፤ ቢሮክራሲና የፓሊስ ተቋሞች በኦሮሞ ተወላጆች የሙሙላት ግልጽና ሰፊ እንቅስቃሴ ወዘተ ከዚህ ፋሽስታዊ የኦሮሙማ የአፓርታይድ ሥርዓት መስፋፋት ጋር የተገናኙ ናቸው።

የኦሮሞ ቋንቋን ትምህርት በግዴታ ኦሮምኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ባልሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች ላይ የመጫኑ ድርጊት፤ ነባር የሆኑና ህብረ-ብሄራዊ ቀለም ያላቸው ሀገራዊ ምልክቶችን፤ ህንጻዎችን፤ ተቋሞችን፤ ታሪካዊ ስፍራዎችን በታላቅ ፍጥነት የማፍረስና የማጥፋቱ ዘመቻ  የፋሽስታዊው የኦሮሙማ እቅድ አካል ነው። ይህ የኦሮሙማ የፓለቲካ ንድፍ ወይም ፕሮጄክት ታሪካዊ ስፍራዎችና ምልክቶችን የማፍረስና የማውደም ዘመቻን የሚያካትት ሲሆን በተጨማሪም ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣን የአንድ ሀገር ህዝብ የወል ትውስታ ሥር-ነቀል በሆነ መንገድ (destroying the collective memory of a people in a radical manner) በማጥፋትና በመደምሰስ ኦሮሙማ የተባለውን የኦሮሞን ነገድ የበላይነት የሚሰብክ ፋሽስታዊና ጽንፈኛ የሆነ የአፓርታይድና የአድሎ ሥርዓት ለመተካት የሚደረግ አደገኛና ሀገር-አፍራሽ የሆነ ድርጊት ነው። እዚህ ላይ አንባቢ እንዲረዳ የምፈልገው ፋሽስቶች እነሱ የራሳቸውን ጥቅም በተመለከተ እናስከብራለን የሚሉትን ዓላማ ሁሉ በጭፍንነት ለማሳካት ከፍተኛ ቁርጠኛነትና የዓላማ ጽናት ያላቸው መሆኑን ነው፡፡

ይህንን በምሳሌ ለማስረዳት ዲማ ነገዎ የተባለው (ዛሬ የዓቢይ አህመድ አንዱ ዋነኛ አማካሪና የፓርላማም ተወካይ የሆነ የኦነግ ዋና ሊቀመንበር በነበረበት ወቅት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር መስከረም 1990 ዓመተ ምህረት (ማለትም ከዛሬ 33 ዓመት በፊት) ሙላሃየም (Mulheim) በምትባል ትንሽ የጀርመን ከተማ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ የተናገረውን ነገር ላስታውሳችሁ። ከ33 ዓመት በፊት በዚች የጀርመን ከተማ የኢትዮያ ተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶች (ኢህአዴግ፤ ኢህአፓ፤ መኢሶንና ኦነግ) በጀርመን የኢትዮጵያ መንግስት አምባሳደር (አቶ ጥበቡ በቀለ) ጭምር በተገኙበት ስብሰባ ላይ የኦነግ መሪ የነበረው ዲማ የሚመራውን ኦነግ የተባለውን ድርጅት የፓለቲካ መዳረሻና ግብ በተመለከተ “የኦነግ የፓለቲካ ዓላማ ምንድነው” ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው ምላሽ የሚከተለው ነበር። “የኦነግ ዓላማ ኦሮሚያን ነጻ አውጥቶ ፊንፊኔ ላይ የኦሮሚያን ነጻነት ማወጅ ነው”። በዚህ ስብሰባ ላይ እንደኔው ተገኝቶ አዳማጭ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ

<< “አቶ ዲማ አንተ ፊንፊኔ የምትላት የዛሬው አዲስ አበባ ናት። በዛሬዋ አዲስ አበባ ውስጥ ደግሞ አብዛኛው ነዋሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ አይደለም። ታዲያ እናንተ ኦነጎች ፊንፊኔ የምትሏት አዲስ አበባ ላይ ነጻነታችሁን ስታውጁ፤ የኦሮሞ ነገድ ተወላጆች ያልሆኑት የዚች ከተማ ነዋሪዎች ምን ይሆናሉ? እጣ ፈንታቸውስ ምንድነው” >> ብሎ ጠየቀው።

 ዲማ ነገዎም

<< “ኦሮሞ ያልሆኑትን ኮሪዶር ከፍተን እናስወጣቸዋለን” >> ብሎ መልስ ሰጠ>>

  ይላል ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ።

በመቀጠል

በወቅቱ እዚያ ስብሰባ ላይ የነበርነው ብዙዎቻችን ይህንን የዲማን ምላሽ እንደ አስቂኝ ነገር ወይም የእብድ ንግግር አንድርገን ቆጥረን ያለፍነው ይመስለኛል። በወቅቱ በዚህ የዲማ ንግግር ሲስቁ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩ አስታውሳለሁኝ። ግን ዲማ የሚናገረው ነገር አስቂኝ አልነበረም፤ አስቂኝ እንዳልነበረም ባለፉት አምስት ዓመታት ዲማ ይናፍቀው የነበረው የኦሮሞ መንግሥት ሥልጣን ላይ ወጥቶ ያደረጋቸውን ነገሮች ማየቱ በቂ ነው። ፋሽስቶች የራሳቸውን ጥቅም በተመለከተ እናደርገዋለን፤ እንፈጽመዋለን ለሚሉት ቃል ታማኝ ስለሆኑ ዲማ ከ33 ዓመት በፊት የተናገረውን ነገር ዛሬ እሱ የሚሳተፍበት የኦሮሙማው መንግሥት በተግባር እየፈጸመው ነው

 

ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን የኦሮሙማው መንግስት ዛሬ በሸገር፤ በሱሉልታ፤ በለገጣፎ፤ በሰበታ፤ በናዝሬት፤ በደብረዘይት፤ በአዲስ አበባ ወዘተ ሥልታዊ በሆነ መንገድ እያካሄደ ያለው የዘር ጽዳት ነው። ይህንን ከእዚህ በላይ ዲማ ነገዎ የተናገረውን ሁሉ እሱ መናገሩን የሚመሰክሩ በርካታ ሰዎች ዛሬም በጀርመን ሀገር ይኖራሉ ብዬ አስባለሁኝ። እኔ በምኖርበት በሆላንድ ሀገር የሚኖርና እንደ እኔው እዚያ ስብሰባ ላይ የነበረ ሀገሬ ሃዲስ የተባለ ግለሰብ በህይወት ስላለ ምስክርነቱን ሊሰጥ ይችላል።

እንደምታሳውሱት የወያኔ ትግሬዎች መንግሥት ከትግራይ ክልል በታች በሚኖረውና በዚህ የፋሽስታዊ ሥርዓት በተመረረው ህዝብ ትግል በሚንገዳገድበት ወቅት እነ ዲማ ነገዎ ግንቦት ሰባትን ሽፋን በማድረግ ጥቂት ለዝናና ለታይታ በየቦታው ጥልቅ ብለው የሚገቡ የአማራ ተወላጆችን በአጃቢነትና በአጫፋሪነት ይዘው ግንባር Formation of Alliance of Arbegnotch Ginbot 7 & Oromo Democratic Front

ፈጠርን ብለው ኢሳት በሚባለው የግንቦት ሰባት ልሣን በነበረው የፕሮፓጋንዳ ቴሌቪዥን ሰፊ ሽፋንና ህዝብን የማደናገር ሥራ ይሰሩ ነበር። በተለይም ብርሃኑ ነጋን በመሳሰሉ እጅግ ጸረ-አማራ የሆኑ ግለሰቦች ሲዘወር የነበረው ግንቦት ሰባት ኦነግ ከተባለው በአማራ ጥላቻ ጥርሳቸውን ነቅለው ባደጉ የኦሮሞ ፋሽስቶች ጋር በማበር አማራ የተባለውን ሰፊ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ አካል ከማናችውም የኢትዮጵያ ፓለቲካ ለማግለል በብርቱ ሰርተው ጥረታቸውም ሰመረላቸው። ወያኔን አሽቀንጥሮ የአማራዎች አስተዋጽዖም ተረስቶ አማራን ጭራሹኑ የማያቋርጥ የጥቃት ዒላማ ያደረገ የኦሮሙማ መንግሥት ወደ ሥልጣን ላይ መጣ። የዚህን የኦነግና የግንቦት ሰባት ጥምረት በማምጣት ዋና አስተባባሪ በመሆን ኦነግ ውስጥ ለውጥ መጥቷል እያለ ድንቁርናና የእውቀት-እጥረት በሚፈጥረው ግትርነት በየመድረኩ ሲሰብክ የነበረውና በተለይም በእነ ኢሳት ላይ ሰፊ ሽፋን ይሰጠው የነበረው ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ነበር።

እነሆ ጌታቸው በጋሻው በ2011 እ.አ.አ. በመድረክ ላይ ወጥቶ ካደረገው ንግግር ኦነግን የመሳሰሉ የነገድ ድርጅቶችን አስመልክቶ የተናገረው የሚከተለው ነው።

<< “ሁለተኛ፡ የዘር ድርጅቶች የትግሉ አካል እንዲሆኑ መጣር ያስፈልጋል:: ይህ አዲስ ሀሳብ አይደለም፣ ያልተጀመረ ሙከራም አይደለም። በዚህ ረገድ ድርጀት ለድርጅት ውይይት ለጀመሩትና አንዳንድ ትብብሮችን እያሳዩ ላሉት የፖለቲካ ኃይሎች፣ ማለትም ለግንቦት 7፣ ለኦነግ፣ ለኦብነግ፣ ለአፋር ድርጅትና ተባባሪ ለሆኑት ሌሎችም ያለኝን ምስጋናና አድናቆት ለመግለጥ ይፈቀድልኝ።...................ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የዘር ድርጅቶችን፣ በተለይም ኦነግን፣ እንደ ፀረ-አንድነትና እንደ ጠላት በመፈረጅ፣ ምናልባት ወንዝ ለማታሻግር ትንሽ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ለመሸመት ባዶ የመግለጫ ጋጋታና ፍሬ-ቢስ ጫጫታ የሚረጩ እንዳሉ መገንዘብ ይበጃል። በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሕዝብ መሀል ጥላቻን የሚዘሩና በድርጅቶች መሀል ሊኖር የሚችለውን መግባባትና መተባበር ለማደፍረስ የሚያከሄዱት ኃላፊነት የጎደለው ተግባራቸውም ሊጋለጥ ይገባል።..........

......ለመሆኑ፣ በመጀመሪያ ደረጃ፣ እነኝህ “በኢትዮጵያ አንድነት” ስም ይህንን ያህል የዘር ጥላቻ የሚነዙ ከፋፋይ ኃይሎች ዛሬ ማን ሆነው ነው፣ ዬት ቆመው ነው፣ ማንን ይዘው ነው የዘር ድርጅቶችን እንዋጋቸዋለን የሚሉት? ለአገር አስባለሁ የሚለው ወገን እውነት ለአገር አሳቢ ከሆነ በመጀመሪያ የራሱን ድርጅታዊ ድርሻና አቅም ከነዚህ ሁሉ የዘር ድርጅቶች ጋር አነጻጽሮና አወዳድሮ ይመለከታል፤በዚያም የሚናገረውን ይመጥናል፤ የሚጽፋቸውና የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች በሕዝበ የወደፊትና የዛሬ ህይወት ላይ ምን የፖለቲካ ውጤት እንደሚኖራቸው ይመረመራል፣ በዚህም ኃላፊነትን ይወስዳል። እስቲ ስለ እውነት እንጠይቅና ከእነኝህ ድርጅት ኮናኞች ውስጥ ዬትኛው “የአንድነት ኃይል” ነው፣ ዛሬና ወደፊት፣ ይህን የሚቀፈቅፈውን የጠላትነት አቋሙን ይዞ ኦሮሚያና ኦጋዴን ተብለው በተከለሉ ግዛቶች ውስጥ ሄዶ ለማደራጀት፣ ለመመልመል ለማስታጠቅና የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ የሚችለው? ምነው ሁኔታዎችን ቢለዩና የሚናገሩትን ቢያውቁ፤ ምነው አቅማቸውን ቢመዝኑና አደብ ቢገዙ!>>  (ጌታቸው በጋሻው ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ የምንለውን ለኦበ2011 እ.አ.አ. በመድረክ ላይ ወጥቶ ካደረገው ኦነግን የመሳሰሉ የነገድ ድርጅቶችን አስመልክቶ የተናገረው)  ምንጭ -(ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ (Ethiopian Semay) 4/6/23 ከኦሮሙማው የፋሽስት መንግሥት ጋር ድርድር አይሞከር ለፋሽስቶች ድርድር ጠላቶቻቸውን አዘናግቶ የማጥፊያ መሳሪያ ነውና!!!!!! ክፍል ሁለት፡) ከሚል የተገኘ።

ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው በአሜሪካ ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች ተቀጥሮ  የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ነው። የጸረ ኢትዮጵያውና ጸረ አማራው የ60ዎች የተማሪዎች እንቅስቃሴ  አመራር አባል እና ቆይቶም የኢሕአፓ አመራር አባል የነበረ ነው። አርባ ምንጭ ያደገ የአምሐራ ነገድ ተወላጅ ነው። እኛንኑን “ኢትዮጵያ፤ኢትዮጵያ” እያልን ኦነጎችን በመቃወማችን << እነዚህ የጥላቻ ቀፍቃፊዎች ምነው ሁኔታዎችን ቢለዩና የሚናገሩትን ቢያውቁ፤ ምነው አቅማቸውን ቢመዝኑና አደብ ቢገዙ!>> እያለ ለኦነጎች ወግኖ ሲዘልፍን ሲንቀን ከላይ አይታችኋል። ጭራሽኑ እንደውም “ኦነጎች የመገንጠል ጥያቄ ጠይቀው አያውቁም” የሚለው ንግግሩ ቪዲዮው ከብዙ አመታት በፊት አቅርቤላችሁ እንደነበር አስታውሳለሁ።ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውም ለኦነጎች እንደ ልደቱ አያሌው ለወያኔዎች ስስ ልብ የነበረው ፖለቲከኛ ነው።

ይህንን በሰነድ ሳስጨብጣችሁ የፕሮፌሰር ብታሙ ተገኘ ንግግር ይህንን አንዳንዶቻችን የምንቀበለው <<ኦሮሙማ የውስጥ ቅኝ ግዛት ስርዓት>> የሚከተሉት ባሕሪ ለአምሐራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ህልውና አደገኛ እየሆነ መምጣቱና <<የኦሮሞና የትግሬ ናዚዎች በአምሐራ ሕዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየፈጸሙ የሕዝቡን ኑሮ ከሚያመሰቃቅሉ የኦሮሞ ናዚዎችም ሆኑ የትግሬ ናዚ ፖለቲከኞች ጋር አምሐራ ነኝ የሚል ፖለቲከኛ አብሮ የሚወያይበት መንገድ ለናዚዎቹ መንገድ መጥረግ ካልሆነ ለተጨፍጫፊው ሕዝብ ምንም የሚያመጣው ጠቀሜታ የለውም ፤ ባይ ነው ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ።

ፕሮፌሰር ሃብታሙ ልክ ነው። እኔም ሆንኩ አንዳንድ ወዳጆቼ  አምሐራዎች ራሳቸውን ችለው በመሳሪያ የመከላከል አቅማቸው  እኩል እስኪገነቡና “ሪኮግኒሽን/ርስፔክት” እስክያገኙ ድረስ ከጠላት ጋር መሞዳሞድ እርባና ቢስ ነው ብየ በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ጽሑፍ ለብዙ አመታት አቅርቤ ሰሚ አላገኘሁም ነበር። ውጤቱ ደግሞ ከላይ በማስረጃ እንዳሳየሁዋችሁ ነው። ስለዚህ የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ጠቃሚ ክርክሩ መታፈን የለበትም ፤ በአመክንዮና በእውነተኛ ታሪክና ፖለቲካ የተደገፈ ምሬቱንም መቀበል አለብን የሚለው የመጨረሻ ጽሑፌ እዚህ ላይ እያቆምኩ ፤ ከናዚ ኦነጎችም ሆኑ ፋሺሰት ትግሬዎች ጋር የሚደረግ የጋራ ውይይት ሳይሆን ካስፈለገም የሚዲያ “ዲቤት” እንጂ እንደ ዕርግብ እየተላላሱና “ጋሼ…” እየታባሉ እየተጋገሱ አፍ ላፍ ገጥሞ መፍትሄ አምጠለሁ ማለት መቆም አለበት።

ናዚዎችና ፋሺሰቶች ውይይት ሳይሆን ሃይል ያስፈታቸዋል ፤ ለውይይት በተጠጋሃቸው ቁጥር ሕዝብን ወደ መጨፍጨፍና ማባረር ነው የገቡት ፤ በፍቅር፤ በወንድምትና በዕልልታ ተሞክረው ተፈትነው ወድቀው አይተናል። እነ ጃዋርን ጃኖ እና ካባ ያለበሰ ፡ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ስለፍቅር ስለ ሰላም ብላ ለአክራሪ “ኦርሞፕሮዎቹ” ፕሮተስታንቶቹ ለአብይ አሕመድ ከነ ባለቤቱ የጣት ቀለበት አበርክታ ፤ በአምሐራ ሕዝብና በኦርቶዶክስ አማኞች የተነጠፈላቸው ዘምባባና አበባ ረግጠው የአምሐራ ሙስሊምና አምሐራ ኦርቶዶክስኖችን ደም ካፈሰሱ አካላት ጋር መሞዳሞድ ይብቃ። የዳንኪራው ምት ሲቀየር እስክስታውም እንዲሁ መቀየር አለበት።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) ድረገጽ አዘጋጅ

 

 

 

Saturday, October 26, 2024

የዘመነ ካሴ የራስ መካብ ባሕሪ እየጎላ መምጣቱ አደገኛነት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 10/26/24

 

የዘመነ ካሴ የራስ መካብ ባሕሪ እየጎላ መምጣቱ አደገኛነት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል!

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

10/26/24

ስለ አምባገነኑ ወጣት ዘመነ ካሴ የሚተነተኑ አደገኛና ራስን የመካብ ትምክሕታዊ ባሕሪዎቹ ስንገልጽ ተከታዮቹ አይቀበሉን ይሆናል። ያ ግን ለብዙ አመታት የመንጋዎች ባሕሪ ምንነት ስለምናውቅ ልክ እንደ ብርሃኑ ነጋ አምላኪዎች <<ስንምክራቸው>> አልሰማ ብለውን እንደነበረና ቀኑ ሲደርስ የብርሃኑ ነጋ ምንነት እውነታው ሲገለጥ እንዳፈሩት ሁሉ የዘመነ ካሴ ተከታዮች <<አውራጃዊነትና ስሜታዊነት>> በብዙዎቹ ተከታይ መንጋዎቹ ያየነው ስለሆነ የጊዜ ጉዳይ ሳይባል ይኼው አሁን አሁን የልጁ የመንደር ጎረምሳዊ ባሕሪው እየጎላ ምንነቱን ይሉኛል የማይል “ኢጎው” እየፈካ መጥቷል።  

ፈረንጆች ራስን በራስ መካብ “ኢጎኢዝም” ብለው ይጠሩታል። <<“ኢጎ” የመልካም አመራር ጠላት ነው>> ይላሉ የዚህ ባሕሪ ምንነት ያጠኑ ባለሙያዎች ሲተነትኑት። ኢጎ ከፋሺስት ባሕሪ ጋር የተጣመረ መሆኑን ብዙ መጻሕፍቶች ጠቅሰውት ተመልክቻለሁ። የተጋነነ ኢጎ ባህሪያችንንም ያበላሻል። ልክ እንደ ዘመነ ካሴ ንግግሮች የስኬታችን መሐንዲሶች መሆናችንን ስናምን፣ <<ጨካኝ>> ፣ <<የበለጠ ራስ ወዳድ>> <<ጉራን ከመጠን ማብዛት>> እና ሌሎችን ንግግሮችና ነጥቦችን <<የማቋረጥና ያለማድመጥ>> እድላችንን ይጨምራል።

በሁሉም ንግግሮቹ ላይ ዘመነ ራሱን የሚጠራው “አርበኛ” እያለ ራሱን  የሚጠራ እና የሚያሞካሽ “ዘመነ ካሴ” እራሱ ጨካኝ መሆኑን እና ተያይዞ በትውልዱ የነገሥታት ልጅና ትልቁ ዝሆን እንደሆነ አመራር እና ጀግንነት ሲወለድ ከእትብቱ ጋር እንደወረሰው ግምባሩ ላይ የተጻፈበት “ዕድል” መቀበልና ማክበር እንዳለብን ሰሞኑን ሞቷል ሲባል አልሞትኩም ለማለት ለማስተባበል በመጣበት ንግግሩ ላይ ተናግሯል።

በተፈጥሮ አመራርና ጀግንነት የተሰጠው ዝሆን የሆነ ይህ በፉከራና በራስ መካብ የሚንጎባለል ወጣት አሳሳቢ ባሕሪ እንዳለው እያን መጥተናል (እኔ እንኳ እንደምታውቁት ካወቅኩት ቆይቷል)።

 የሚናገራቸው ትዕቢታዊ የዘወትር ባሕሪው ለዚህም ምሕረት የለሽ መሆኑን ያሳየን ሰው መሆኑን በተግባር ጎጃም ውስጥ ካለ እሱ በቀር ሌላ የፋኖ አመራርና የፋኖ ሃይል እንደማይኖር ፤ ከኖረም በማንቁርታቸው እየታነቁ ለሱ እንደሚገዙ በመሃላ እንደሚያስምላቸው፤ ከመሃላው የወጣ እንደሚረሸን እና እምቢ ያሉትንም ሰዎች አፍኖ ከማሰር እስከ መግደልና ማስጨነቅ፤ሽማግሌዎችና እናቶች እምብርክክ ማስኬድን የመሳሰሉ፡ጭካኔዎች አሳይቶናል።

ይህ “ኢጎ” የተጠናወተው የመንደር ጎረምሳዊ ባሕሪው በጥለቅ ለማየት የፖለቲካ ተንታኙ የርዕዮት ሚዲያ አባል <<ቴዎድሮስ አስፋው>> በሚደነቅ ግሩም ትንተና ስለ ዘመነ ካሴ አስፈሪ ባሕሪው ምን እንደሆነ ለማድመጥ እነሆ ይህንን  ቪዲዮ ሊንክ ተጫኑ።

ከብልፅግና ግድያ ያመለጠው በራሱ አንደበት ግን እየሞተ ያለው ... ‪@EthioSelam_ኢትዮሰላም #tewodros

 

https://youtu.be/uGVWkXpkLOA?si=KMWB-BI-QiwxRDvA

 

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)   

 

Wednesday, October 23, 2024

የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬቶችና እውነታዎች ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 10/23/24

 

የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬቶችና እውነታዎች

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay) 10/23/24

ወደ ትችቴ ከመግባቴ በፊት ይህንን ልበል፡

ባለፈው ሰሞን ፕሮፌሰር ሃብታሙ <<አለም አቀፍ የፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ>> በተባለው የነዘመነ ካሴ ደጋፊ ሚዲያ ቀርቦ በልደቱ ቤተሰብና ንብረት ላይ የተናገረበት ነጥብ በማውገዝ መተቸቴን ይተወሳል። አንዳንድ ሰዎች በግል የውስጥ መልዕክት ሲልኩልኝ የባለፈው ሳምንት በፕሮፌሰሩ ላይ መተቸቴ ፕሮፌሰሩ እኔ አብዝቼ የምነቅፈውን የጎጃም አማራ ፋኖ መሪ የዘመነ ካሴ ደጋፊና በውጭ አገር አስተባባሪ አባል ስለሆነ ያንን ለመቀጥቀጥ እንደተጠቀምኩበት ጽፈውልኛል።ይህ ግን እውነትነት የለውም። ከፕሮፌሰሩ ይልቅ ልደቱ አያሌውን በተደጋጋሚ ለብዙ አመታት ተቺቼዋለሁና በመግቢያው ላይ ታስታውሱ እንደሆነ፤ ያልኩት ነጥብ “ፕሮፌሰሩን የተቃወምኩት በፕሪንስፕል” አንደሆነ ገልጫለሁ። ስለዚህ በዚህ እንዲያዝልኝ።

ዛሬ ደግሞ የማቀርበው ለፕሮፌሰሩ ድጋፍና ያሰማን ብሶት መደመ እንዳለበትና እውነተኛ ምሬት መሆኑን በድጋፍ ስመጣ  የዘመነ ካሴ ደጋፊ መሆኑን እያወቅኩም ቢሆን ፕሮፌሰሩ ስለ አምሐራ ሕዝብ ስቃይ፤ግፍ ብሶት፤ ታሪክና ስለ ኦሮሞዎች ወረራ አስመልክቶ የጠቀሰው እውነትነት ስላለው በዚህ ዛሬ እተቻለሁ።

ፕሮፌሰሩ ብዙ አውነታዎች አሉት። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ከሺዎቹ አምሐራ ምሁራን አንዱ ሲሆን፤ እንደ አምሐራነቱ በወላጆቹና ቤተሰቦቹ ላይ እንዲሁም ምንም ፖለቲካ በማያውቅ አምሐራ ገበሬና ሰራተኛ ሕዝብ በአክራሪና ተገንጣይ ኦሮሞ ፖለቲከኞችና በአክራሪ ውሃቢ ኦሮሞና በአክራሪ ፕሮተስታንት ቡድንና ድርጅቶች ለብዙ አመታት አንዳንዱም ወደ 400 አመታት የሚወስድ ጥቃት በኢትዮጵያና በአምሐራ እንዲሁም በኦርቶዶክስ አማኝ ሕዝብ የደረሰና እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ግፍ በምሬት ለማስረዳት ሞክሯል።

ይህንን ለማስረዳት በሚሞክርበት ጊዜ ሰዎች ሰሚ ሲያጡ ምሬታቸው ከልክ ሲያልፍ ፤ በቃኝ የሚሉበት ወቅትና ስሜታቸው ሲገነፍል አላስፈላጊ ንግግር ላለመናገር ቁጣቸውን መቆጣጠር ከምሁራን የሚጠበቅ ነው። ለዚህ ነው ስለ ልደቱ ያነሳው ነጥብ የተቃወምኩት።

ስለሆነም ፕሮፌሰሩ ልክ እንደ ኦነጎቹ እሱም ሳይሸሽግ ለሚያደርጉት የዘር ማጥፋት ወንጀል መልሱ ነግሯቸዋል።  ለኦሮሞዎች ኢትዮጵያ ባዕድ ናት፤ ኢትዮጵያ በኦሮሞዎች መልክ እንሰራታለን፤ 3000 አመት እንገዛችኋለን፤ ኢትዮጵያ አቢሲኒያዎች (በተለይ ነፍጠኞች፤ ምኒልኮች) የሰርዋት አገር ናትና አገራችን አይደለችም ብላችሁ ሕዝባችንን ከመጨፍጨፍ አቁማችሁ ባዕድ ነን የሚለው ስሜታችሁን ይዛችሁ ወደ መረጣችሁበት ጥንታዊ አገራችሁ አቅኑ፡ ሲል እቅጩን ተናግሯል።

ለምን እንደዚያ አለ የሚል ጠያቂ ተቃዋሚም ደጋፊም ሊኖር ነው። ግን እርሱ ያለው እነሱ በሚሄዱበት መንገድ በመመልከት የሰጠው መልስ ነው። ብዙ ታገስናቸው፤ ካሁን አሁን ይሻላቸው ይሆን፤ እየተባለ በብዙ አምሐራ ሕዝብና ኢትዮጵያዊያን ብዙ ተዘመረላቸውተቀደሰላቸውዕልልታ ተቸራቸው ድጋፍ ተሰጣቸውመልሳቸው ግን አምሐራን ቤተ ክርስትያነትን፤ ቅርሶችን ማውደም ሆነ የሚያወድሙት ሁሉ የኛ ነው ስለማይሉት ፤ ባዕዳዊ ስሜት ስለሚሰማቸው ሥልጣን ይዘውም ይሁን ሥልጣን አይያዙ መፈክራቸው “አገራችን አይደለም” ወይንም “በመስፋፋትና በጭፍለቃ ስሜት ‘’ሁሉም ኬኛ” የሚል ስሜት ስላላቸው ልክ 400 አመት በፊት ያደረጉት ነባሩን ሕዝብ በመዋጥ ዛሬም ያንን እየደገሙት እያየን ነው፡ ይህ እኛ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም ስሜታቸው እነሱን ለማቀፍና ለማብረድም የሕዝቡን ዕልልታ፤ድጋፍ (ደማችሁ ደማችን ነው ተዋህደናል) የሚል ግጥምና ዝማሬ ቢደረግላቸውም ከምንም አይቆርጡትምና እውነቱን መነገር አለበት። ነው የፕሮፌሰሩ ክርክር።

በአጽንኦት የሚናገረው ፤ አሁን ምሬታችን የናንተ ያህል ግልጽና ጣራ ስለደረሰ ፤ ኢትዮጵያ አገራችን አይደለችም ካለችሁ፤ አምሐራ ጠላታችን ነው እያለችሁ ከተከለለው አፓርታይዳዊ ኦሮሚያ ከሚባለው የ27 አመት አዲስ ስምና ክልል አምሐራ ውጣልኝ እያላችሁ ሕዝባችንን ከመጨፍጨፍ ስላልቦዘናችሁ፤ ካሁን በኋላ ይለይለት ግልጽ ግልጹን መናገር ከተባለ እናንተም ወደ ጥዊ ቦታችሁ ተመልሳችሁ በመሄድ አገራችን ወደ እምትሉት አቅኑ። ሲል ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ምሬቱን እንደ እነሱ በግልጽ ሳይደብቅ ተናግሯል።

ነፃነታችንን አክብሩልን፤ ሁሉም በየስሜቱ ለመድረክና ለውይይት ይቅረብ ካላችሁ የኔ መስመር ይህ ነው፤ ነው የፕሮፌሰሩ ሙግት። ውደዱት አትውደዱት ግልጽ ነው። ዝምታ ብዙ አመታት ውጦን ነበር አሁን ግን መልስ መስጠት ጊዜው ነው።  እንለያይ ካላችሁም በዚህ ነው የምንለያው የሚል ነው የዶክተር ሃብታሙ መስመር።

አሁን ያሉት ኦሮሞዎች የባዕድ ሰሜት አሳድረዋል፡ ስለሆነም አገራችን ነች ብለው ስለማይቀበልዋት አምሐራውና ኦርቶዶክስ እንደሁም ያለፉት የነገሥታት ዘውድና አስተዋጽኦ በክፉ አይን የሚያዩ ስለሆኑ ሕዝባችንም በየሰዓቱ ሌትም ቀንም ያለ ዕረፍት እየጨፈጨፉት ስለሆነ አብሮነት ችግር ላይ ወድቋል ፤ በግልጽ እንነጋገር ነው የፕሮፌሰሩ ሙግት። ትክክል ነው። በግልጽ እንወያይ። መደባበቅ ዛሬውኑ መብቃት አለበት። የደረሰው እና እየደረሰ ያለው ውድመትና ጭፍጨፋ ዓይን ገላጭ ነው።

አሁን ያሉት ኦሮሞዎች ሃገራዊ ባሕልና ሃገራዊ እሴት የሚጻረሩ ናቸው። በአክራሪ ውሃቢ እስላም ፤ በአክራሪ ፕሮቴስታንት በግምባር ቀደም ጸረ ኢትዮጵያዊ ነባር ባሕል፤ ጸረ አምሐራና ጸረ ኦርቶዶክስ በሆነው ኦነግ የተሰበኩ አዲስ ትወልድ ኦሮሞዎች ብዛት ያለቸው ስለሆኑ፤ በተሰበኩበት ተልዕኮ መሰረት አምሐራና ኦርቶዶክስ አንዲሁም አምሐራ የሆነ እስላም ላይ ሳይቀር በተጠቀሱት ክፍሎች ለዘር ማጥፋት  ጭፍጨፋ ጥቃት እንዲጋለጡ ተደርጓል፡

እውነታውን እንነጋገር። አብዛኛው ኦሮሞ እየተከተለውና እየተቀበለው ያለው አክራሪ ውሃቢያና አክራሪ ፕሮተስታን ኦነጋዊው ፖለቲካ እሴት፤ የሐሰት ትርክቱ ተቀብሎታል። ኦነጋዊያን ከአክሱም አልፈው መላው የሱዳንና የግብፅ ሥልጣኔ የኛ ነው ብለዋል። ኦነግም ሆኑ ወያኔዎች መገንጠል የኢትዮጵያ ማፍረሻ ከአምሐራ ጭቆና ነፃ ማስገኛ መንገድ ነው ብለው ሃገር ለማፍረስ  የመገንጠል ሕገመንግሥት ቀርጾው አሁንም አፓርታይዱ ሕገ መንግሥት ህያው ሆኖ አለ። ፕሮፌሰሩ የሚለው፤ እንግዲህ መገንጠል ከፈለጋችሁና አትኑሩ ካላችሁን አሁን ያለው ከሕግ ውጭ በአመጽና በሴራ የያዛችሁት ሰፊ ክልል የናንተ ስላለሆነ ከ16ኛው ክ/ዘመን በፊት ወደ ነበረው ወደ ጥንት ቦታችሁ ወደ ኋላ አፈግፍጉ፤ ነው እያላቸው ያለው። እውነት ነው።

አሁን ያለው ቦታ ከሕግ ውጭ ከወያኔ ጋር ተመሳጥረው ያካለሉት አፓርታይዳዊ የስልቀጣ እርምጃ ነው። ሌለው ዜጋ መብት የለውም። ባለቤቶቹ እነሱ ናቸው። ለዚህ ነው “ውጣልኝ” እያሉ ዘፈን ቀርጸው ወጣቱን እያስጨፈሩት ያሉት። ከዚህ አልፎ ሰሞኑን ደግሞ ከ8 ሚሊዮን በላይ ኦሮሞዎች እየተደመጠ ያለ Warra Boole (ዋራ ቦሌ አራት ኪሎ) የሚል “ሶና ታከለ” የተባለ አክራራ ኦሮ ዘፋኝ “አምሓራ የተባለቺው” ፍቺ በሌለው ሕልም 4 ኪሎ ተመኝታ ኦሮሞ ባለቤቱ ባለባት አዲስ አባባ ባለቤት ለመሆን ትፈልጋለች” እንደሚል ኦሮምኛ አዋቂዎች ተርጉመውታል።

  ከዚህ አልፎ “ኦሮሚያ ክልል” የተባለው አፓርታይዳዊው ክልል ያለምንም ማስረጃ የሃሰት ትርክቱን ለወጣት ኦሮሞዎች ሲቀሰቅስ የጻፈውን ልጥቀስ ፤ እንዲህ ይላል፡-

<< ጥቂት የነበሩ አዲስ መጤዎች (ያሁኖቹ አምሐራዎችና ትግሬዎች) ከአገሬው ተወላጅ ጋር ተቀላቀሉ.... የኦሮሞ ክልል በ4ኛ ክ/ዘመን በአክሱማዊው ኢዛና ተገፍተው መሬታቸው በሴም ቋንቋ ተናጋሪዎች ተነጠቀ....>>

 ይላል፡ የአብይ አሕመድ ኦሮሚያ ክልል (የኦሮሞ ታሪክ ከ16ኘው መ/ክ/ዘ ከሚል የሃሰት ትርክታቸው ገፅ 24-25) :- ምንጭ ባንተአምላክ አያሌው።

ይህንን እንጠይቅ፦ የአክሱም ሥልጣኔ የኦሮሞዎች ከነበረና ኦሮሞዎች አክሱም ውስጥ ከነበሩ፤ እንዴት ነው ንጉሠ ነገሥት ኢዛና “ኦሮሚያ ክልል” የሚባል ክልል ሳይኖር ወደ ክልላቸው መጥቶ አባረረን የሚሉት?

ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ የሚለው አውነትነት አለው። ኦሮሞዎች ከብት አርቢዎች እንደነበሩና ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ እንጂ ከተማ ቆርቁረው ቤተጸሎት ገንብተው ህንጻዎች አንጸው፤ ፊደል ቀርጸው አያውቁም። የኛ ግንብ ፤ የኛ ከተማ፤ የኛ ፊደል የሚሉት አንዲትም ነገር የላቸውም። ይላል። ልክ ነው

ዐምሐራ ፡ ማህበራዊ ምንነቱና ተግዳሮቱ
 የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌውም ፤እንዲህ ይላል፡

<< ኦሮሞ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ቋሚ ከተማ እንኳ አልነበረውም፡ ኦነጋውያን እንዳዉም ከተሞችን የቆረቆሩ አጼ ምኒልክን ከተማን በሃገራችን ሠሩብን እያሉ ሲከሱ መስማት ያሳዝናል። የኦሮሞ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ አክሱም ፤ በሱዳንና በግብፅ ለተገነቡ ታላላቅ ከተሞችና ሥልጣኔዎች ባለቤት ከሆነ ቢያንስ ሃይልንና  የበላይነትን ባገኙባቸው በ16ኘው መቶ ክፍለ ዘመን ለምን ራሱን የሚገልጥ አንድ የሥልጣኔ አሻራ አላሳረፈም?>> ይላል ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው። (ሰረዝ የተጨመረ)

በዚህ መልክ ተገቢው ጥያቄ ፕሮፌሰር ሃብታሙም ሆነ ባንተአምላክ የተጠቀሰ ሃቅ ነው:: ታዲያ ከግራኝ አሕመድ ወረራ በላ ወደ መሃል ሃገር የተስፋፋው ኦሮሞ ተገንብቶ ያገኛቸውን ሥልጣኔዎችና ቅርሶች እንዲሁም ከተሞችን ከማድነቅና ከማክበር ይልቅ ማውደም እና የባዕድነት ስሜት ለምን ተሰማቸው ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው።

ውሃቢ እስላም ኦሮሞዎችም ሆኑ ኦነጎችን እንደ ሶማሌዎች እንደ ናይጄሪያዎችና ኬኒያዎች ለመላው ኦሮሞ ያስታጠቁት ዐረብኛ ልሳንና የላቲን ፊደል የማንነት መለያቸው የማድረግ ጉድ ስትመለከቱ ሃገራዊ ፊደል የሆነውን ግዕዝም ሆነ አምሐርኛን ከመጥላትና የባዕድነት ስሜት ያመነጨው ነው።

 ግዕዝ ልንሰማው የማይገባ ልሳን ነው ብለው በላቲን ፊደል በተጻፈ በኦሮምኛ ይቀድሳሉ ፤ ይዘምራሉ። የሚያሳዝነው ይላል ደራሲ ባንተአምላክ:- 

<<አማርኛ የቅኝ ግዛት ቋንቋ ነው፤ግዕዝ ልንሰማው የማይገባ ልሳን ነው የሚለው ከሳሽ እርሱ  ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጭ ብሎ በቅኝ ገዢዎች የላቲን ቋንቋ እየጻፈ፤ በዓረብኛ ቁርአን እየቀራ ፤ መድረሳ እየተማረ ፤ መስጊድ ውስጥ በአረብኛ እያመለከ ነው>> ይላል

 እውነት ነው። በአረብኛ ማምለክና መማር ወይንም በላቲን መጻፍ አንድ ሰው ካመነበት ነውር አይደለም። ከባሕር ማዶ በመጣ በአረብኛ እየተገለገለ፤ከላቲን በተደቀሉ የቅኝ ገዢዎች “ሆሄ” እየጻፈ ሃገር በቀል የታሪክ የማንነት የሥራ ቋንቋዎች የሆኑትን አምሐርኛና ግዕዝ ይውደሙ በምኖርበት አካባቢ አይሰሙ ማለት ግን ነውር ነው። ይላል ደራሲ ባንተአምላክ። ለዚህ ነው ፕሮፌሰር ሃብታሙም እንዲህ ያለውን እሳቤ ያለውን ሰው እንዴት ብለን ኢትዮጵያዊ አድርገን እቀበለው? የሚለው በዚህ ወረርሺኝ ተቀብሎ የኔ ብሎ እየተጠቀመ ላለው ለመላው ኦሮሞ ሕዝብ ነው ምሬ። የፕሮፌሰሩ ክስ እና ምሬት እውነትነት አለው።

ባንተአምላክ አያሌው ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡

<<የሚቀርበውን ክስስ በየትኛው የፍርድ ሚዛን እውነት ብለን አንመዝነው? በአረብኛ ሲማሩ በራሳችን ቋንቋ አልተማርንም ፤ በላቲን ወይንም በአረብኛ ሲጽፉ በራሳችን ቋንቋ አልጻፍንም ሳይሉ በአማርኛ ሲማሩ፤ በግዕዝ ሲዘምሩ ግን የባይተዋርነት ስሜት የሚይሰማቸው ከሆነ ችግሩ የማን ነው?>> እውነት ነው፤ እውነትም ችግሩ የማን ነው? (ድምቀትና ሰረዝ የተጨመረ)

ርዕሱ እና ጉዳዩ አወያይ ስለሆነ በክፍል ሁለት ስለምመለስበት እስከዛው ግን የሚገርመኝና እናንተንም ይገርማችሁ ይሆናል ብየ የምገምተው ሃሰተኛ ስብከታቸው እነዚህ አክራሪ ኦሮሞ ምሁራን የሚሉት ስያጡ ፤ እንዲህ ይላሉ፡

<<ኦሮሞዎች ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡበት ምክንያት አምሐራዎች ቅኝ ስለገዙን ቁጣችንን ለማብረድ ሚሰቶቻችንን በብዛት አዘውትረን እንደበድባለን>> እስከማለት ደርሰዋል።

ከባንተአምላክ ያገኘውን የጥቅሱ ምንጭ ከራሳቸው ኦሮሞ ጆርናል እና ፈረንጆቹ ኦሮሞዎቹ ነገሩን ብለው የጻፉት ልጥቀስ፤- 

<< ሚሰት መደብደብ በኦሮሞዎች ዘንድ እጅግ የተስፋፋ ነው። ሰሊህ የወንዶች ፈጣን ቁጣና ጭካኔ ዋናው ምክንያት ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ተደጋጋሚ አደጋዎች ጭንቀት ከምዕተ ዐመት ቅኝ ተገዥነት የተነሣ የሚፈጠር አቅመአልባነት ነው።>> Journal of Oromo Studies VOLUM E 4, NUMBERS 1 & 2, July 1997 p. 135 Kelly (1992:327-340), ትርጉም ባንተአምላክ አያሌው ገጽ 218-219)

<<Also Observers that wife-beating is wide-spread among the Oroma Oromo. He hints that this escalating male aggression may be attributed, among, other factors, to the constant crisis , stress and disempowerment associated with a century of colonialism >> (Journal of Oromo Studies VOLUM E 4, NUMBERS 1 & 2, July 1997 p. 135 Kelly (1992:327-340),

እንግዲህ << ኦሮሞዎች ሚስቶቻቸውን የሚደበድቡበት ምክንያት አምሐራዎች ቅኝ ስለገዙን ቁጣችንን ለማብረድ ሚሰቶቻችንን በብዛት አዘውትረን እንደበድባለን>> እስከማለት የሚደርስ በሽተኛ ኦሮሞ ምሁር ዋነኛው ተልዕኮው (የራሱን ሚሰት መደብደብ አረመኔነቱን ማሳያ መሸሸጊያ ለማድረግ የተጠቀመበት ቢሆንም፤ ዋናው መልዕክቱ ግን ጎሰኛነት ዕውር ነውና ተጨቁነሃል እናቶቻችሁን ልንደበድብ ምክንያተችን አምሐራ ስለጮቆነን መወጣጫ አደረግናቸው እያሉ የሚያስተምሩት በላቲን ፊደል ያደነቆሩት አምሐርኛ ማንበብና መስማት የማይችል ኦሮሞ ወጣት ቂምና በቀል እንዲያረግዝና ለዚህ ጭፍጨፋ ተወናይ እንዲሆን አድርገውታል።

ስለዚህም ነው ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝም ሆኑ ሌሎች አምሐራ ነገድ ምሁራን  አብዛኛው ኦሮሞ ልሂቅና ፖለቲከኛ በበታችነት ስሜት እየተሰቃዩ ሚስቶቻቸው ሲደበድቡ ሳይቀር አምሐራ ነው እንዲህ ያደረገን እያሉ በሚያስቅና በሚገርም ሁኔታ በየጆርናሉ ሲጽፍ የሚውለውም በዚህ የጨቋኝና ተጨቋኝ ሐሰተኛ ትርክት ምክንያት ነው።

ይቀጥላል.........

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


Tuesday, October 22, 2024

በልደቱ አያሌው ቤተሰቦች ላይ የተሰነዘረው ውግዘት የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ በጽኑ ይኮንናል! ምክንያቴን ላስረዳ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 10/22/24

 

በልደቱ አያሌው ቤተሰቦች ላይ የተሰነዘረው ውግዘት

የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ በጽኑ ይኮንናል! ምክንያቴን ላስረዳ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

10/22/24

ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ በልደቱ አያሌው ቤተሰብ ትውልዶች የውግዘት አመለካካቱን ብቃወመውም በዛው ውይይት ላይ ስለ አምሐራው ጥቃትና ስለ ጸረ አምሐራ ቡድኖችና ግለሰቦች ያቀረበው ነጥብ ግን የማይጣል መሆኑን ላስምርበት እፈልጋለሁ በዚህም ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ ሳከብረው የነበረ ምሁር ነበር። በፕሮፌሰሩ ላይ ትችት ሳቀርብ ቅር እያለኝ ሳልወድ በግድ ፕሪስፕል መከተል ስላለብኝ በፕሮፌሰሩ ላይ ትችቴ እነሆ!

በረራ  ቀዳሚት አዲስ አበባ  በሚል አስደናቂ የታሪክ መጽሐፍ ጽፎ ያስነበበን ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ በብዙዎቻችን አድናቆት ተችሮት የነበረ  ምሁር ነው። አለመታደል ሆኖ ፕሮፌሰሩ ሲያቀብጠው ይሁን ሆን ብሎ አለም አቀፍ የፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ ተብሎ በሚጠራሃሰተኞች ሚዲያላይ ሁሌም በመገኘት መድረክ ላይ በሚተላለፈው ከታች በምለጥፈው ዩቱብ ቪዲዮ የልደቱ አያሌው ንብረት ላይና የቅርብ  ቤተሰብና የልደቱ አያሌው 7 ትውልድ እርግማን እንዲደርስባቸው በመማጸን ለአማራ ማሕበረሰብ ማስተላለፉን ጥሪ ከዚህ ጽሑፍ ጋር አብሮ የተለጠፈው ቪዲዮ ያስረዳል። ፕሪፌሰሩ ምን እንደነካው ባላውቅም በቀላሉ የሚታለፍ ውግዘት አይደለም።

ይህ ሰው ጤናማ ሕሊና ወጥቶ ወደ እዚህ ዓኢነት ንዴት  እንዴት እንደተሸጋገረ ባላወቅም ውግዘቱ የሰብአዊና የዜግነት እንዲሁም የነገድ ማንንትን የሚነጥቅ ጥሪ ነው። ልደቱ አያሌው በሚከተላቸው አንዳንድ የፖለቲካ ስሑትነቱን ካንዴም ሦስቴም መተቸቴን ተከታታዮቼ የምታውቁት ነው። ሆኖም በፖለቲካ ስላልተጣጣምን የልደቱ ሃብትና ንብረት ፤የልደቱ ቤተሰብና 7 ትውልድ እርግማን እንዲደርስበት ቅስቀሳ ማድረግ በጣሊያን ፋሺሰቶች በሶቭየት ሶሺያሊስቶች ደርግ በኢትዮጵያ ናዚዎች በጀርመን   ሁቱዎች በሩዋንዳ ወያኔዎች በትግራይ በቅርቡ ደግሞ በዘመነ ካሴ የሚመራው ጫካኝ እና ዝሆን ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራ የአማራ ፋኖ በጎጃም ተቃዋሚዎቻቸውን በመሰወር በማፈን በማሰር፤ በመግደል፤ ሽማግሌዎችን የእምብርክ ማስኬድ ንብረታቸውን በመንጠቅና በመውረስ፤ ቤተሰቦቻቸውን ከማሕበራዊ ትስስርና ግብይት እንዲገለሉ ጥሪ በማድረግ የታወቁና ብዙዎቹም በዓይናችን ያየናቸው ድርጊቶች ናቸው።

ዛሬ ደግሞፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው ላይም ምንም እንኳ የተለየ አቋም ቢኖሮውም ለኢትዮጵያ ፍቅር የለውም አይቆረቆርም ብሎ ማለት ትክክል አይደለም። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ የልደቱ አያሌውን 7 ትውልድ ድረስ የሚደርስ ብቀላ (ቬንጀንስ) ማሳወጅ የሩዋንዳ  ሁቱዎች ሞደሬት ተብለው በሚጠሩ ሁቱዎች ላይ ካስተላለፉት እንዲሁም በአምሐራ ጥላቻ የሰከረው አረመኔው የወያኔው አሉላ ሰለሞን በአማራ ሕዝብ እና ከአማራ ጋር በተጋቡ ትግሬዎች ላይ ያስተላለፈው እና  የተላያዩ የጎሳ የፋሺሰቶች ያስተላለፏቸው የብቀላናጥይላቻ ጥሪዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል። ፕሮፌሰር ሃብታሙ ያስተላለፈው ጥሪ መወገዝ አለበት  

ጌታቸው በየነ የተባለው ሰው የሚመራው የአለም አቀፍ ፋኖ አስተባባሪ ኮሚቴ International Fano coordinating Committee የተመሰረተው በሚከተሉት ነሓሴ 15/2016 ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፋኖ ተዋጊ መሪዎች ፈቃድና መግለጫ በደብዳቤና አስልክ ድምጽ ቅጅ እውቅና እንደሆነ በተላለፈው የቪዲዮ መግለጫ እንደሆነ እናውቃለን።

ፈቃጆቹም  የሚከተሉት ናቸው፦ እነዚህም በስልክ ስማቸው እየጠሩ ከየትኛው ፋኖ እንደተወከሉ ይናገራሉ፡

በጎጃሙ አስራስ ማሬ ይጀምራል፤ እንዲህ እያሉ

አስረስ ማሬ ዳምጤ ( የአማራ ህዝባዊ ልሳን አመራር ነኝ)

ሻለቃ ሰፈር መለሰ )አማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ተወካይ

ደሳለኝ …..አማራ አንደነት ምክር ቤት አሰባሰቢና የኮማንዶ አባልና ብርጌድ አዛዥ

ዋርካ ምሬ ወዳጆ (የምሥራቅ ፋኖ ዋና አዛዥና የመላው አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ)

አበበ ሙላቱ (ከሸዋ ፋኖ አንድነት ምክርቤትሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ )

ይህ ሚዲያ (በዚህ ድርጅት ሚዲያ የምናደምጣቸው ሰዎች ካሁን በፊት የተቸሁበትን ጽሑፍ ታስታውሳላችሁ) ለመመስረት የተፈለገበት ምክንያት መግለጫቸው አንደሚለው በአለም ዙርያ አድቮከሲና ዲፕሎማሲ፤የሎጅሰቲክ፤ የገንዘብ ዕርዳታስራዎች ለማከናወን እንደሆነ ይገልጻል። በደብዳቤው መጨረሻ መግለጫና በስልክ የሚደመጠው መፈክር ክናዳችን መዳኚያችን ይላል።  ይህ ከሆነ አድቮካሲውና ዲፕሎማሲው በተቃዋሚዎቻቸው ላይ 7 ትውልድ ዘሮቻቸው ብቀላን ለማወጅ ከሆነና በአካባቢያቸው ለነሱ የመይገብር ሁሉ አንዲታፈንና ንብረቱ እንዲወረስ ካደረ  እውነትም ካሁን በፊት  <<አማራ ውስጥ ገንግኖ እያቆጠቆጠ ያለው ፋሺዝም ካሁኑ ካልተወገዘ ለአገርም ለአማራ ሕዝብም አደጋ አለው! ጌታቸው ረዳ 8/14/24

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024_08_14_archive.html

ኢትዮጵያዊ አማራ እና ንጹህ አማራ እኛና እነሱ የዘመነ ካሴ የፋሺስት ፍረጃ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/20/2024

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024/07/ethiopian-semay-7202024.html

 

በሂደት ላይ ያለው የዘመነ ካሴ ረዢሙ የቢላዋ ምሽት Zemene Kassie’s night of the Long Knives in the making ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ 8/1/24

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024/08/zemene-kassies-night-of-long-knives-in.html

በጎጃም አማራ ፋኖ ውስጥ ገንግኖ እያቆጠቆጠ ያለው ፋሺዝም ካሁኑ ካልተወገዘ ለአገርም ለአማራ ሕዝብም አደጋ አለው! ጌታቸው ረዳ 8/14/24

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2024_08_14_archive.html

የሚሉ ትችቶቼን ጊዜ ወስዳችሁ አንብቡዋቸው።

ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ብቻ አይደለም በሚቃወሙዋቸው ላይ ይህ የንብረት መወረስም ሆነ የሃይል እርምጃም መወሰድ  አለበት ብሎ የሚሰብክ፤ በዚህ አጋጣሚ አንድ ያልጠበቁኩዋቸው ትልቅና ምሁር ሰው ብየ ስገምታቸው የነበሩት አቶ ተክሌ የሻው (የጨካኙ የዘመነ ካሴ ድጋፊ ናቸው<<ከቴድሮሰ እስከ መንግሥቱ ኃይለማርያም>> ድረስ የተድርጉ ጭፍጨፋዎችና ጭካኔዎቸ ሁሉ ፋኖም ለሥልጣን ሲባል ማድረግ አለባቸው ሲሉ በሚያስተላልፉት ዩቱባቸው አደምጬአቸው በጣም ነበር የደነገጥኩት፡ (ሰውየው አማራን በማደራጀት እዚህ አሜሪካ ቀዳሚ ሚና የነበራቸው በበጎ ሳያቸው የነበሩ ሰው ናቸው) ብሔረተኛ መሆን አደገኛና ድንገት ደራሽ ጎርፍ ነው የምለውም ለዚህ ነው።

አሁን ደግሞ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ በልደቱ ላይ የንብረት መውረስና 7ትውልዱ እና በመላ ቤተሰቡ ላይ የውግዘት ጥሪ ለአማራ ወጣትና ተዋጊ ማስተላለፍ አዝጋሚው ፋሺዝም እየተንፏቀቀ አማራው ማሕበረሰብ ላይም እያቆጠቆጠ ነው።

ይህ የሚያሳየን / አሰፋ ነጋሽ ስለ ፋሺስት ሕሊና ደጋግሞ እንዳስገነዘበን፡

<<በዚህ አይነት በጎሳ ብሄርተኝነት አይምሮአቸው የተመረዙ ሰዎች የግል ማንነታቸው መገለጫ የሆነውን እንደ ሰው የማሰብ ችሎታቸውን ለጎሳ መሪዎቻቸው አሳልፈው ስለሚሰጡ የአንድ በጎሳ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በሙሉ የጎሳ መሪዎቻቸው የሚነግሯቸውን እየሰሙና እየተከተሉ እንደ አንድ ሰው ወይም እንደ ጎሳ መሪያቸው ማሰብ ይጀምራሉ። ይህ ፈረንጆች “group thinking” የሚሉትና የአንድ አክራሪ የጎሳ ድርጅት ተከታዮች አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብ (homogenization of thought) ተሸካሚዎች የሚሆኑበት ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት በአክራሪ የጎሳ አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በጎሳ መሪዎቻቸው ትዕዛዝ(ውሳኔ) ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል። የጎሳ መሪዎቹ የወደዱትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ። የጎሳ መሪዎቹ የመረጡለትን ነገር ሁሉ ለመቀበል ይገደዳል። ምን እንደሚያስብ፤ ከማን ጋር ቡና መጣጣት እንዳለበት፤ ከማን ጋር መወያየት፤ ማንን ማፍቀር ማንን መጥላት፤ በየትኛው የፖለቲካ ስብሰባ ላይ መሳተፍ ወይም አለመሳተፍ እንደሚገባው ወዘተ የጎሳ መሪዎቹ ይነግሩታል። በዚህ አይነት የግል ማንነቱን ያጣ ሰው ይሆናል።>> (ሰረዝ የተጨመረ)

ከላይ እንዳነበባችሁት አማራው ውስጥ ብቅ እያለ ያለው የፋሺዝም ቡቃያ << እኛና እነሱ፤ እኔ ንጹህ አማራ እገሌ ግን አማራ መስሎ ጭምብል በመልበስ የአማራዎችን የኛን የንጹሃን አማራዎችን ትግል  ለመጥለፍ የተቀላቀለን አማራ ያልሆነ ወዘተ…… (ዘመነ ካሴና አሰግድ እስክንድር ነጋ ላይ የገለጹበት አገላለጽ ነው) በሚል  የፋሺስቶች ፍረጃ ውስጥ ገብቷል፡፡ ዛሬም በፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ልደቱ አያሌወ ላይ የዘሰነዘረውልደቱ አማራ እይደለም ፤ንብረቱ የተገነባው በአማራ ሕዝብ መሬትና ርስት ነው! የሚለው የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ፋሺስታዊ የጽንፈኛነት  ልክ አንደ የፋሺስዝም ብሔረተኛነት አቀንቃኙ ዘመነ ካሴ እስክንድር ላይ <<እስክንድር አማራ ሳይሆን አማራ መስሎ የአማራነት ጭምብል የለበሰ.. “የኢትዮጵያ አማራ (ትግሬዎች እኛን ሽዋውያን ተጋሩ  እንደሚሉን) ማለቱ ነው ( የኛ ያልሆነ ጭምብል የለበሰጸጉረ ለወጥ”) የሚለው የነ ዘመነ ካሴ ዕብደት ከፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ ፋሺሰታዊ ዕብደት ጋር ተመሳሳይ ነው ፋሺዝም እያቆጠቆጠ ነው የምለውም ለዚህ ነው።

ለማጠቃለል፡

ስለዚህም ፋሺስቶች አስተሳሰብን ሳይሆንወንድነትን” ( በጡንቻ/masculinity)  በማሳመን ጠላታቸውን ከማስደንገጥ  አልፈው አንደ እነ ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ ያሉ ሰዎች እየሰሩበት ያለው በጠባብ ጎሰኛነት  በጠባብ አማራነት የተመረዙ ወጣቶችን በሚጠልዋቸው ሰዎችና ተቃዋሚዎቻቸው ላይ 7 ትውልድ የሚሻገር ጥላቻ (በቀል) እንዲይዙ የማይበርድ እርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር የማድረግ ሙከራ ስለሆነ ምንም እንኳ በልደቱ አያሌው ላይ ያለኝ የፖለቲካ ልዩነት ሰፊ ቢሆንም ፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኘ በፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው  ንብረትም ሆነ በራሱና በቤተሰቡ እንዲሁም በሚቀጥለው 7 ትውልዱ ላይ ብቀላ እንዲረገዝ ያስተላለፈው ጥሪ በጥበቅእቃወማለሁ!!” እያልኩ ይህ ፋሺስታዊ አዋጅ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው የአማራ ወጣትና ምሁር  የፕሮፌሰር ሃብታሙ ተገኝ አደገኛ የብቀላና የጥላቻ አዋጅ  አንድትኮንኑት ጥሪ አቀርባለሁ። ሥልጣን ላይ ያሉ በሽተኞች ሕመም ማከም አቅቶን ስንሰቃይ ጤነኞች ናቸው የምንላቸው የብዙዎቹ ምሁራኖቻችን በሽታ ሲታከልበት ጭንቀታችን ከምንችለው በላይ ሆኖብናል

ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian Semay አዘጋጅ)