Saturday, October 5, 2024

ልርሳቸው ብትልም መርሳት የማይቻል የፍቅርም የሰቆቃም ድምፆችና ትውስታዎች ይታገሉናል! ጌታቸው ረዳ 10/5/2024 Ethiopian Semay


ልርሳቸው ብትልም መርሳት የማይቻል የፍቅርም የሰቆቃም ድምፆችና ትውስታዎች  ይታገሉናል!

ጌታቸው ረዳ

10/5/2024

Ethiopian Semay

በፍቅር ትውስታ ልጀምር፦ስለ ሰቆቃና የምሬት ትውስታዎች ቪዲዮው ይነግራችኌልና ሰለዛው ብዙ አልልም። ሁላችንም አንዴ ወይንም ተደጋግሞ ብዙ ጊዜ ወጣት ሆነንም አርጅትንም  ልርሳው ብትልም መርሳት የማይቻልህ ሁሌም የሚታገልህ የፍቅር ትዝታ (ትውስታ) አለ። እንኳን ሰው እንሰሳም በዚያው ባሕሪ እንደሚራመዱ መጽሐፍ አንብቤ አለሁ። እንሰሳ ካጠገቡ የነበረ ወዳጁ ሲያጣ “ድብርት ውስጥ ይገባል። እኛ ትዝታ/ትውስታ የምንለው ማለት ነው።

 መርሳት የማይቻል ፍቅር አለ። ታዋቂው ጥቁር አሜረካዊው Nat King Cole – (አን ፎርጌተብል)  (የማይረሳ) የሚል ዘፈን ዓለም ያስደነቀ የፍቅር ዘፈን ፈጥሮ ከዚህ  ዓለም ተሰናብቷል። አንድን ነገር የማይረሳ ነው ብለህ ስትል፡ እጅግ በጣም ውብ ፤ ቆንጆ፡ አስደሳች፡ ወይም ያልተለመደ ፡ ለረጅም ጊዜ እንድታስታውሰው የሚጫንህ ልዩ  መስሕብ አለ።

ወደ ሰቆቃና ወደ የተጨቆኑ  ድምጾች ስንመለክትም፤ ሰዎችም አራዊቶችም በተፈጥሮአቸውመታፈንን” ይቃወማሉ/አይወዱም። የሰቆቃ ድምጽ የሚናገሩና ሰንሰለቱን በጥሳችሁ አዚ ወይም አምሐራ ሁኑ (ነፃ ሕዝቦች ሁኑ) የሚል የነ ማርቲን ሉተር፤ የነ ማንዴላ፤ የነ ጋንዲ ድምፆች ከሰው ልጆች ሕሊና አይረሱም።

በነገራችን ላይ አግዓዚያን እና አምሐራ ትርጉም ያልገባችሁ ሰዎች ስለምትኖሩ የግዕዙና አማርኛ ትርጉም አግዓዚያን ማለት ነፃ ሕዝብ/ሕዝቦች ማለት ሲሆን አምሐራ ማለት ደግሞ ነፃ ሕዝብ ማለት ነው። ለዚህ ነው ሊቃውንት አምሐራዎች የአክሱም አግዓዚያን ነበሩ ብሎ በታሪክ የሚዘግቡት። *በነገራችን ላይ ትግራይ ውስጥ የከርሰ መሬት ቅሪት ተራማሪው “ተኽለ ሓጎስ” ሓውዜን ወረዳ ውስጥ ጥንታዊ የሆነ “ዓዲ አምሐራ” (የአማራ ሃገር/ሃገረ አግዓዚ/ምድረ አምሐራ/) የሚባል ጥንታዊ ወና እርሱና አብረውት ለጥናት የሄዱ ተመራማሪዎች በጥናቱ የተገኙ አዳዲስ ግኝቶች እና ሃውልቶች እንዲሁም ወና/ህንጻዎች/ጥንታዊ ዕቃዎችና ጌጦች ሲቆፍሩና ሲመዘግቡ ይህ አንደኛው አዲስ ግኝት እንዳገኙ ጠቅሶታል። በዚህ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ።

ኢትዮጵያ ውስጥም የብዙ አርበኞች ድምፅ የብዙ ነገሥታት ድምጽ የብዙ ደራሲያን እና ገጠሚያን ዘመሪያን እንዲሁም ተዋንያኖች የማንረሳቸው አሉ። ከሃይማኖት መሪዎች ጣሊያንን የተጋፈጡት “የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስንና፡ በቅርቡ አምናም የዘመናችን ዳግማዊው ግራኝ አሕመዱአብይ አሕመድ” ያመጣብን የአገር በቀል ቅኝ ግዛትን የተቃወሙት የብፁዕ የአቡነ ሉቃስ የፍላጻ የነፃነት ድምጽ የምንረሳቸው ድምፆች አይሆኑም። በህይወት ኖሮ ከብዙ ግርፋትና ስቃይ የተረፈው በህይወት ቆይ ያለው ፈጣሪ በህይወት አቆይቶት ፋኖን እየመሩ ካሉት በርካታ መፈክሮቹ ፤ የትግል ድመጾቹና በአርአያነቱን መርሳት የማይቻል የምናስታውሰው ታላቁ እስክንድር ነጋን እና  በአሳዛኝ ሁኔታ ባጭር የተቀጨው  አርበኛ ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ ከተጠቀሱት ድምፆች ተደምሮ  የማይረሱ የነፃነት ደወሎች ናቸው።

 እነዚያን ተከትሎ ጭቆና እና ዘረኝነት ያንገፈገፋቸው በርካታ ወጣቶች ፤ እናቶችና እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ያሉ ምሁራን የማንረሳቸው የነፃነት ደወል የማይረሱ ናቸው። እነሱን አንድ ባንድ ለመቀስ ቦታ አይበቃም።በዚህ ስዕለ ድምፅ (ቪዲዮ) የምትሰሙት የአንድ አምሐራ ወጣት ሰቆቃና የብርቱነት ድምፅ የደወለው “ የነፃነት ደወል”  እንደ መሪ ብርሃን ሆኖ በታሪክ ማሕደር መግባት ካለባቸው የማይረሱ የትውስታና የብርቱነት ደምፆች አንዱ ነው።

ታሪክ ያሳየን የጨቋኞችና የዘረኞች ዙፋን ይዋል ይደር እንጂ በተጨቋኞችና በግፉአን የነፃነት ድምፆች ተፍርክርከው ፤ የማይገሰሱ የሚመስሉት ባለ ጊዜዎች መጨረሻ ግብአተ መሬታቸው አይቀሬ ነው።

ለዳግም ነፃነት ዛሬም ሳንሰለች እንበርታ!

ጌታቸው ረዳ

 

No comments: