ከመከላከያ ጎን እንቆማለን ብለው
ጦርነቱ ሲካሄድ ድጋፍ ከሰጡ የትግራይ አባ ሰላማ ቦርድ አባላት ጥቂቶቹ በማስረጃ ተጋለጡ
(Ethiopian Semay)
7/12/23
ለዛሬ አጥብያ ሌሊቱኑ ለትግርኛ አንባቢዎቼ በትግርኛ ይህንን በሚመለከት ጽፌ ነበር። በዚያው የትግርኛ መልእክቴ ያጠነጠነውም አቤቤች አደኔ የተባለች “የኦሮሙማ አዲስ አባባ ከንቲባ” ፤ ፋሲል የኔአለም” (አሳት EMS) በተባለው ወራዳ ግለሰብ በትግራይ ጦርነት ወቅት የዘመናችን “ጣይቱ” ሲል የሰየማትን ሴትዮ አዲስ አባባ ሆና በጦርነቱ ወቅት << ትግሬዎችን ፈቅደን እንዲኖሩ ብናስቀምጣቸው ጁንታው አሸነፈ እያሉ ይጨፍራሉ>> እያለች “የቀይ ሽብር” ዘመቻ ዘርግታ ትግሬ ሁሉ እያደነች ፤ ትግሬ የተባለ (ሁሉም ትግሬ) የከተማው ኗሪ በፕሮፋይል አጀንዳ “እያስደበደበች፤ ንብረቱ እያስቀማች ስታስር እና ስታስገድላቸው የነበረቺውን አቤቤች አዳኔን እነዚህ “የትግራይ ሃገረሰብከት ተዋህዶ አባ ሰላማ ክሳቴ ብርሃን” የሚል ሕገ ወጥ ተቛም የመሰረቱ ጳጳሶች እኔ <<የትግራይ ጳጳሶች ማሌሊታዊ መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን”>> ብየ የምጠራቸው ጉደኞች የትግሬ ጳጳሶች፤ መቀሌ ድረስ ጋብዘው “አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ” በቀይ ምንጣፍ እ፤ል፤ል እያሉ እጅ እየነሱ ተቀብለዋታል። አብረዋትንም የሄደው ሽመልስ አዱኛም እንደዚሁ መስቀላቸው እያወዛወዙ በፍቀር ሲቀበሉ <<ለትግሬዎች እንባቸው ያፈሰሱትን አባ መትያስን>> ግን አናነጋግርም ብለው ቤተክርስትያን እንዳይገቡ ዘጉባቸው። ጉዳቸው ግን ከዚህ በታች ያስቀመጥኩት የቪዲዮ ርዕስ እና ቀን አደምጡ።
ቪዲዮውን እስከ መጨረሻ ተከታተሉት። በቪዲዮው ላይ በፎቶ የምታይዋቸው
የትግራይ አባሰላማ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቦርድ አባላት ሁለቱ ለምሳሌ በNovember 17/2020 <<አቡነ ኤልያስ እና
አቡነ እንጦስ>> ጦርነቱን ደግፈው ለመከላከያ እደግፋለሁ ብለው ደረታቸው ላይ መስቀል አስደግፈው “መሃላ ገብተው፤ባርከው”
ድጋፍ ሲሰጡ ጦረነቱን እንደ ተቀረነው “ይለይለት” እያሉ አዲስ አበባ ሆነው በወቅቱ November 17/2020 በወጣው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ኮርፐረሽን የሕዝብ ግንኙነት
መምርያ ፌስ ቡክ” ላይ ዜናው ለጥፎት ነበር ሲል Ethio 360
ሃብታሙ አያሌው መረጃውን ይፋ ድርጎታል።
እነዚህ የወያኔ ጳጳሳት በምን ሞራላቸው ይሆን ሌሎቹን ጳጳሳት ጦርነቱን አላወገዙም ብለው የኮነንዋቸው?
አራት ከሎ እና የመቀሌ ፖለቲካ፤ የብርሃኑ ጁላ ወለፈንዲ ዛሬ ምን አለ ? ሓምሌ 4 2015 Ethio 360 ቪደዮውን አድምጡ
ጽሑፉን አሰራጩት እባካችሁ!
ጌታቸው
ረዳ
ሃብታሙ አያሌው
የትግራይ “መንበረ አባ ሰላማ” ጳጳሳትን አጋለጣቸው
No comments:
Post a Comment